ArcCon Construction & Trading
58 subscribers
24 photos
2 videos
2 files
7 links
This Channel Is intersts Who For wants To Any Construction Work, Sale Or Buy Any Material's and Others.
Download Telegram
Channel photo updated
This Channel Is Created For Who Are Intersted in Civil Engineering & Related Sector And Also For Cajolers.
Forwarded from Cornerstone Consulting Architects & Engineers
የኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ።።
ከአለም በ63ኛ ደረጃ ሲገኝ በአፍሪካ ደግሞ በቁመቱ በ7ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ከፍታ አለው።
ከምስራቅ አፍሪካ ደግሞ በአንደኝነት ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ይህ ምስሉ የተያያዘው ህንጻ በአገራችን ከሁሉ በላይ ቁመታምና በቴክኖሎጂ የበለጸገ ህንጻ ነው። ስራው በንድፍ ግንባታ (design build) መልክ ለ China State Construction Engineering Corporation የተሰጠ ስራ ቢሆንም ከደንበኛው ከኢትዮዽያ ንግድ ባንክ በኩል ደግሞ በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ስር ያለው ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴከኖሎጂ አያሌ ባለሙያዎች አሰማርቶ ስራውን ይቆጣጠራል።

ህንጻው በ2007 መጨረሻ የተጀመረ ሲሆን አሁን ከ6 አመት በኋላ በመጨረሻው የመገባደጃ ምእራፍ የደረሰ ይመስላል።

አራት የምድር ቤትና 46 ወለሎች ያሉት 209.3 ሜትር የሚረዝም ህንጻ ሲሆን 1500 መኪኖችን ማቆም ይችላል

ከቅርብ ዘመናት ወዲህ የከተማው ፋይናንሽያል ማእከል የንዋይ መሰረታቸውን ባደረጁ የግል ባንኮች ሰማይጠቀስ ህንጻ እየተሞላ መጥቶአል። መንግስትም ሆነ ማህበረሰቡ እነዚህ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች በሚፈጥሩት ህብረምስል (silhouette) ኩራት እየተሰማቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ ከሚሰነዘሩት የጽሁፍና የምስል አስተያየቶች መገመት ይቻላል።

እስካሁን ያልተነጋገርንባቸው ነገር ግን አሉን። እነዚህ ህንጻዎች በዚህ ቁመት ያስፈልጉናል ወይ? የስራ ማስኬጃ ወጭያቸው ምን ያህል ነው? የስነምህዳር ተጽእኖአዋቸው እንዴት ነው? እነሱን የሚሸከም የአቅርቦትና የፍሳሽ (waste) መሰረተ ልማት አካባቢያቸው አለ ወይ? በነሱ ዙርያስ በቂ የህዝብ መጓጓዣና የመኪና ማቆምያ አቅርቦት አለ ወይ?

ያው አንድ ነገር እንረዳለን። የወደላይ ግንባታ ሩጫ ከጥግግትና ከመሬት ምጣኔሀብት አስገዳጅነት ባለፈ ከአለማቀፉ የጥንካሬና የዘመናዊነት ተምሳሌትነት አስገዳጅነትም ይመነጫል። ለነገሩስ ባብላጫው ግዜ ኪነህንጻ ከማስፈለጉ በፊት ተምሳሌትነቱ ይቀድም የለ? የሰው ልጅ ለተምሳሌት (symbol) የማይከፍለው ነገር የለም። የፓሪሱን የአይፍል ማማ፣ የፈርኦኖችን ፒራሚድ፣ የአክሱምን ሀውልት፣ የሮምን ቅዱስ ዮሀንስ ካቴድራል፣ የአሜሪካውን ኢምፓየር ስቴት ህንጻ፣ የሲድኒ አፔራ ቤት እንዲሁም የዱባዩን ቡርጅ ከሊፋ ህንጻዎች ለአብነት መውሰድ ይቻላል።

እኛም በባለመለሎው በንግድ ባንክ ህንጻ አማካኝነት የራሳችንን ማንነት ለመቅረጽና ለሌላው ለማሳየት የቻልነውን ሞክረናል። እሱም ህንጻ የከተማችን ህብረምስል ላይ ለሚመጡት አያሌ ዘመናት ተጽእኖውን እንዳሳረፈ ይኖራል። አዲስአበባን የሚጎበኙ ሰዎች አእምሮ ጓዳ ላይ የማይለቅ አሻራውን አስቀምጦ ይቀራል። ጎብኝዎች እግሩ ስር እየገቡ እንዲሁም አዲስ ከተበጁት እንደ የወዳጅነት ፓርክ ከመሳሰሉት ገላጣ ቦታዎች ላይ ሆነው ምስሉን ለማስቀረት ይጥራሉ።

በነገራችን ላይ የድሮዋ የንግድ ባንክ ዋና መስርያ ቤት በግራ በኩል ኩስምን ብላ ትታያለች፡፡

ኪነህንጻ ከምጣኔ ሀብትና ከተግባራዊ እሳቤዎች ጋር ብቻ ይያያዛል ያለውስ ማነው? ግን ቢሆንም እነዚህን ሰማይ ፋቂ ህንጻዎች መገንቢያና አመታዊ ማስተዳደርያ ዋጋ ብናውቀው ይጠቅመናል።

ነገርን ነገር ያነሳዉ የል? ከሁሉ በላይ የሚገርመው በተራም በሹመኛም አፍ የሚነገረው "ይህ ዱባይ እንዳይመስላችሁ ...... መዲናችን ነች" አይነት ንግግር ነው፡፡ ያው ይሄንን ያመጡብን እነዚህ ቀውላላ ህንጻዎች መሆናቸውን ሳንዘነጋ ዱባይን ለመምሰል መሰቃየት እንደሌለብን ደግሞ ደጋግሞ ልብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አዲስ አበባ ከፍ ባለ መልክአ ምድር ላይ ያለች ነገር ግን ለምድር ወገብ የቀረበች በመሆኑ ያገኘችው አስደማሚ የ Afro Alpine ዘወትር የማይሰለች የአየር ንብረት ባለጠጋ መሆንዋን አልሚዎችና ባለሀብቶች ማወቅ አለባቸው፡፡

አስከፊ አየር እንዳላቸው እንደ መካከለኛዉ ምስራቅና የአውሮፓ ከተሞች እንዳሉ መስኮታቸው ከማይከፈት አምሳና መቶ ፎቅ ውስጥ ከምንከረቸም እንደው ከመካከለኛ ከፍታ ባልበለጡ ህንጻዎች ከተማይቱ ብታምር ምን ይመስለናል? ባይሆን በቸርችል ጎዳና እንደተበጀው የእግረኛ መንገድ የከተማይቱን መንገዶች አበጅቶ ለኦሎምፒክ የሚወዳደሩትን ርዋጭ ቱሪስቶች መሳብ አይሻልም?

ብቻ ጽንፍ ሳይያዝ አዲስ አበባንም ሌላ ከተማ ማስመሰል ስቃይ ውስጥ ሳንገባ በ60ዎቹ ወርቃማ ዘመናት የተፈጠሩትንም ውብ ማንነቶችዋን ሳንንድ ከተማችንን እንዴት ምቾትዋን ከፍ እናርግ የሚለው ላይ ብዙ በሳል ንግግሮች ያስፈልጉናል፡፡ ንግድ ባንካችንንም ክፉ አይንካብን፡፡

Do we build tall out of need or out of the need for symbolism? Are we showing that we are not lagging behind or do we need the spaces in the sky scrappers in the midst of the bustling metropolis?

But isn't architecture also about symbolism and the projection of self image to the whole wide world ? Anyways the commercial bank of Ethiopia will remain to be that icon of the city burning its impression in the minds of both the dwellers and the tourists in the city.

Image Credit: Dawit Benti
👍1
👆👆👆Selam Consulting Architect & Engineers. @ Hawasa; Ethiopia
Sister Campany Of ArcCon.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለ ማሪያም ደሳለኝ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ሀገራዊ የአቅርቦት ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት የምንችለው የማምረት አቅማችን በብዛት፣ በጥራት እና በፍጥነት ማደግ ሲችል ነው ብለዋል። የምርት አቅርቦት እንዲያድግም በመንግስት አቅም ከሚሰሩት በተጨማሪ የግሉን ዘርፍን በሰፊው ማሳተፍ እንደሚጠይቅ አውስተዋል።
ፋብሪካው በአመት 5 ሚሊየን ቶን ሲሚንቶ ማምረት የሚችል ሲሆን÷ ግንባታው በ18 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ አመላክተዋል። ተጨማሪ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን በሃገር በቀልና በውጭ ኩባንያዎች እንዲገነቡ በማድረግ የሲሚንቶ አቅርቦት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እንሰራለንም ነው ያሉት።
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 ምንጭ FBC