Arba Minch University
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎቹን እየተቀበለ ነው
ዩኒቨርሲቲው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹን በማጠናቀቅ ነባር ተማሪዎችን ከትናንት መስከረም 21/2012 ዓ/ም ጀምሮ እየተቀበለ ነው፡፡
በቀጣይ መስከረም 24 እና 25 በየካምፓሳቸው ከተማሪዎች ጋር የጋራ ውይይቶች ከተደረጉ በኋላ የመማር ማስተማር ሥራ የሚጀመር ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት ባሳወቀው መሠረት መስከረም 28 እና 29 አዲስ ተማሪዎችን ቅበላ ያካሂዳል፡፡
ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

Charity @Arba Minch
ይሄ Group የተከፈተው በአርባምንጭ የሚገኙ አቅመ ደካማ ተማሪዎችን በቁሳቁስ እንድናግዛቸው ነው።
📝ደብተር
📝 እስኪሪብቶ
👗👖👕👡👟የተጠቀምንባቸውን አልባሳት
ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች እርዳታዎችን እናደርጋለን።
እባካችሁ Pin የሚደረጉ መልዕክቶችን አንብቧቸው።
https://telegram.me/charity_AM

ቀን፡-26/01/2012 ዓ/ም
ማስታወቂያ
ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ
ዩኒቨርሲቲው ቀደም ሲል ባሳወቀው መሠረት የአዲስ ገቢ ተማሪዎች የቅበላ ጊዜ መስከረም 28 እና 29 መሆኑን በድጋሚ እያሳወቀ የአዲስ ገቢ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ከትምህርት ሚኒስቴር ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በሶፍት ኮፒ የተላከ በመሆኑ ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በመያዝ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው ያሳስባል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መካከለኛ አመራሮች የአመራርነት ሥልጠና እየተሰጠ ነው
ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በመጡ ባለሙያዎች ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው የአመራርነት አቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ከዛሬ መስከረም 26/2012 ዓ/ም ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ የአመራርነት ሥራ በአንድ ተቋም ውጤታማነት ላይ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ ገልፀው መሪነት የራሱ ሳይንስ ያለው ተግባር በመሆኑ በአመራርነት ሥራ ላይ ሆኖ በአጫጭር ሥልጠናዎች ላይ በመሳተፍ የአመራርነት ዕውቀትና ክህሎትን በተሻለ ደረጃ ታጥቆ መስራት የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በሥልጠናው ዳይሬክተሮች፣ የኮሌጅና ት/ቤት ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና አስተባባሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

AMU community rejoices in Dr Abiy Ahmed’s Noble Prize victory
Friday, 11 October 2019 19:37
Leading officials and entire university community, AMU President, Dr Damtew Darza, congratulated Prime Minister, Dr Abiy Ahmed, for winning The 2019 Noble Peace Prize for phenomenal efforts in ending hostility with bitter foe Eritrea in a short span of assuming his office. He said, we are proud of him and certainly strive hard to play constructive role in ensuring overall development of Ethiopia.
Read more: AMU community rejoices in Dr Abiy Ahmed’s Noble Prize victory.
https://www.amu.edu.et/index.php?option=com_content&view=article&id=1693:amu-community-rejoices-in-dr-abiy-ahmeds-noble-prize-victory&catid=1:amu&Itemid=244

www.amu.edu.et
Arba Minch University
The official website of Arba Minch University. Arba Minch University is a national university in Arba Minch, SNNPR, Ethiopia. It is approximately 435 kilometres south of Addis Ababa, Ethiopia.
የሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የፍሬሽ ማን ኮርሶችን በየካምፓሱ ለሚያስተባብሩ አስተባበሪዎችና በሪከርድ ሠራተኝነት አዲስ ለተመደቡ ባለሙያዎች በ SMIS አጠቃቀም ዙሪያ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
በሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ተባባሪ ሬጂስተራር አቶ ሶፍያን አብዱልመናን እንደገለፁት አስተባባሪዎቹና ባለሙያዎቹ አዲስ እንደመሆናቸው ሲስተሙን በተሻለ ሁኔታ ማስተዳደር እንዲችሉ ለማድረግ ሥልጠናው ተዘጋጅቷል፡፡ በሥልጠናው ከቅበላ እስከ ምረቃ ድረስ ያለው የሲስተሙ አሠራር በዝርዘር ለሠልጣኞች ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ዶ/ር በለጠ ይልማ በበኩላቸው አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ወደ ተግባር እየተቀየረ በመሆኑ በተለይ ለ1ኛ ዓመት አዲስ ተማሪዎች የሚሰጡ የጋራ ኮርሶች ጋር ተያይዞ ለውጦች በመኖራቸው ከዚህ ቀደም የነበረውን የ SMIS ዘዴን ከአማካሪው ድርጅት ጋር በመሆን እንደገና ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከዚህ ቀደም የነበረው ዘዴ እንደገና እንዲሻሻል ተደርጓል ብለዋል፡፡
የዘንድሮውን የምዝገባ ሂደት አስመልክቶ አስተያየት የሰጡት ዶ/ር በለጠ በአጠቃላይ እንደ ሀገር በተሰሩ የግንዛቤ ሥራዎች ምክንያት የዩኒቨርሲቲያችን ነባር ተማሪዎች በተባለው ጊዜ ወደ ግቢ እንደገቡና የምዝገባ ሂደቱም በተባለው ጊዜ ተደርጎ የመማር ማስተማሩ ሥራ በወቅቱ ተጀምሯል ብለዋል፡፡
ከአዲስ ተማሪዎች ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም ተማሪዎች በካምፓስና በት/ክፍል ደረጃ ተመድበው ከላይ ይላኩ እንደነበር አስታውሰው ዘንድሮ ግን ተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ብቻ ተብለው ለዩኒቨርሲቲው ተመድበዋል፡፡ የተመደቡትን ተማሪዎች የግድ ወደ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች መመደቡ ግድ በመሆኑ ቀላል ሶፍትዌር በማዘጋጀት ከሰው ንኪኪ ነፃ በሆነ መንገድ በሎተሪ ዘዴ ተማሪዎች ወደ 6ቱም ካምፓሶች እንዲደለደሉ ተደርጓል፡፡ ምደባው ከቅሬታ ነጻ እንዲሆን አድርጎታልም ብለዋል፡፡
አሁን ላይ የክፍል ምደባ ሥራ በየካምፓሱ የተጠናቀቀ በመሆኑ የማስተማር ሥራው ጥቅምት 05/2012 ዓ/ም በይፋ እንደሚጀመር ዶ/ር በለጠ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የበቆሎ መፈልፈያ መሳሪያ አዘጋጅቶ ለ3 ወረዳዎች ለሙከራ አቀረበ
ዩኒቨርሲቲው በጋሞ ዞን ውስጥ ከሚገኙ 3 ከፍተኛ የበቆሎ አምራች ወረዳዎች የመጡ ሞዴል አርሶ አደሮች በተገኙበት ጥቅምት 4 እና 5 የበቆሎ መፈልፈያ መሣሪያ ለሙከራ አቅርቧል፡፡
ከምዕራብ አባያ 3 ቀበሌያት 20፣ ከቁጫ 10 ቀበሌያት 20 እና ከዳራማሎ 7 ቀበሌያት 40 ሞዴል አርሶ አደሮች ተገኝተው የመፈልፈያውን አጠቃቀም እንዲለምዱና ለሌሎች እንዲያሸጋግሩ በአያያዙና አጠቃቀሙ ዙሪያ በዘርፉ ባለሙያ ገለጻ ተደርጓል፡፡

ለተማሪዎች አገልግሎት ሠራተኞች የተግባቦት ስልጠና ተሰጠ
የስነ-ትምህርትና ስነ-ባህርይ ሣይንስ ት/ቤት ለዋናው ግቢና ጫሞ ካምፓሰ የተማሪዎች አገልግሎት ሠራተኞች ከመስከረም 19-20/2012 ዓ/ም ከተማሪዎች ጋር የተሻለ ተግባቦት ለመፍጠር የሚያስችል ስልጠና ሰጥቷል፡፡
https://m.facebook.com/Amu.edu.et.1

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
"የአስተዳደጌ ፣ የትውልዴና የማህበረሰቤ ነጸብራቅ ነው"
ድምጻዊ ሮፍናን ኑሪ ነገ በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የኔ ትውልድ ለሚላቸው ወጣቶች የህይወት ተሞክሮውን ያካፍላል፡፡ መልካም ቆይታ ይሁንላችሁ የአርባምንጭ ተማሪዎች!
ቦታ:- አባያ ካምፓስ መመረቂያ አዳራሽ
ሰአት:- 8:00
ማሳሰቢያ: -ለሁሉም ካምፓስ ተማሪዎች ከ 7:00 ሰአት ጀምሮ የሰርቪስ አገልግሎት ይኖራል
#ቲክቫህ_ኢቨንት
@tikvahethmagazine @emush21

#AMU_promotes_four_senior_staff_to_Associate_Professors_rank
Arba Minch University Senate in its communiqué released on October 30, 2019, has stated that four of its senior academic staff, who had applied for the position of Associate Professor, have been promoted with immediate effect; as supporting documents submitted by them have been duly evaluated and verified.
Four Assistant Professors, Dr Alemayehu Hailemichael, Dr Fekadu Massebo and Dr Ramish Duraisamy from College of Natural Sciences and Dr Yechale Kebede, College of Social Sciences and Humanities of Geographical and Environmental Studies department had applied for the academic position of Associate Professor.
Having evaluated and verified the supporting documents by all four applicants against the stated Senate Legislation under Article 8 (8.1 to 8.5), AMU Senate found that compared to required elements such as Effective Teaching (40%), Publications (35%), Participation in University affairs (15%) and Professional and related public services (10%), Dr Fekadu Massebo could successfully make it up to 95.03%, Dr Alemayehu Hailemichael has 99.31%, Dr Ramish Duraisamy, 88.35% and Dr Yechale Kebede had 95.32% to his credit, hence all were promoted to the positon of Associate Professor.
One must know that following required criteria for the position of Associate Professor is stated under The AMU Senate Legislation under Article 8 (8.1 to 8.5), it says, apart from a PhD degree or its equivalent, one must have 4 years of effective teaching experience as an Assistant Professor.
Further one must have at least two articles published in a reputable journal since last promotion or must have a textbook/book based on original research to his/her credit or 4 realized artistic or professional projects or one published article and two realized artistic or professional projects or one publication and release of one technological package through a nationally accredited mechanism since becoming an Assistant Professor
And most importantly, applicant must show active participation in the affairs of the university along with potential contribution in Community Service, which is recently been made absolutely mandatory by the Ministry of Science and Higher Education as part of academics.
(Corporate Communication Directorate

የግንባታ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅና የዩኒቨርሲቲውን የገቢ አማራጮች ለማስፋትና ለማሳደግ እየተሠራ ነው
በ2012 በጀት ዓመት በዩኒቨርሲቲው በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቁ በትኩረት እየሠራ መሆኑን የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ገለፀ፡፡ የኢንተርፕራይዞችን መዋቅርና አሠራር በመቀየርና ሌሎች አዳዲስ የገቢ ማስገኛ ዘዴዎችን በመቀየስ 47 ሚሊየን ብር ገቢ ለዩኒቨርሲቲው ለማስገኘት እንዳቀደም ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡
የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲው በሚገኙ 3 ኢንተርፕራይዞች ከዚህ ቀደም ሲስተዋሉ የነበሩ የመልካም አስተዳደር፣ የፋይናንስና የንብረት አያያዝ ችግሮች እንዲቀረፉ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ቀደም ኢንተርፕራይዞቹ ኦዲት ተደርገው አለማወቃቸው የቅሬታ ምንጭ እንደነበር የተናገሩት ወ/ሮ ታሪኳ አሁን ላይ የኢንተርፕራይዞቹ ከ2009-2010 ዓ/ም አፈፃፀም ኦዲት ተደርጓል፡፡
ኢንተርፕራይዞቹ የተለያዩ ስያሜዎችን ይዘው 3 መሆናቸው እንዲሁም ከዚህ ቀደም የነበረው መመሪያ እምብዛም ጠቃሚ እንዳልሆነ በዳሰሳ ጥናት በመታወቁ አዲስ የኢንተርፕራይዝ ማሻሻያ መዋቅር መመሪያ ተዘጋጅቶ የተለያዩ ደረጃዎችን አልፏል፡፡ መዋቅሩ በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ በተቀመጠ አቅጣጫ መሠረት በሕግ ባለሙያዎች ታይቶ አስተያየት የተሰጠበት በመሆኑ በቅርቡ ጸድቆ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በመመሪያው መሠረት ሦስቱ ኢንተርፕራይዞች ወደ አንድ በመምጣት በውስጡ የተለያዩ ቅርንጫፎች ያሉት ሆኖ ‹‹የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኢንተርፕራይዝ›› በመባል እንደሚዋቀር ወ/ሮ ታሪኳ ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በነጭ ሳር ካምፓስ ቅጥር ግቢ እያስገነባ የሚገኘውን የነዳጅ ማደያ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ሥራ ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑን የጠቆሙት ም/ፕሬዝደንቷ ማደያው ተጨማሪ አገልግሎት መስጫ ሕንፃዎች ያሉት በመሆኑ ሕንፃዎቹን በማከራየት ዩኒቨርሲቲው ገቢ እንደሚያገኝ ገልፀዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ከሚገኙ ንግድ ቤቶች የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ፣ ግንባታው የተጠናቀቀውን የእንግዳ ማረፊያ ሥራ ለማስጀመርና በዩኒቨርሲቲው የሚገኘውን የመዋኛ ገንዳና የስፖርት ጂምናዚየሞች ለአገልግሎት ምቹ ለማድረግ የተለያዩ ቁሳቁሶች ግዥ በመፈጸም ከዘርፎቹ የሚገኘውን ገቢ ከፍ ለማድረግ ጽ/ቤታቸው በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን ወ/ሮ ታሪኳ ተናግረዋል፡፡
ከግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር ተያይዞ በዩኒቨርሲቲው በግንባታ ላይ የሚገኙ ነባር ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቁ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የጠቀሱት ም/ፕሬዝደንቷ የካፒታል በጀት እጥረት፣ የውጭ ምንዛሪ ችግርና የዋጋ ንረት የዘርፉ ተግዳሮቶች ቢሆኑም ችግሮቹን በመቋቋም ውጤታማ ለመሆን እየሠራ ነው ብለዋል፡፡ 2011 ዓ/ም እንደ አገር ከነበሩ ችግሮች ጋር በተያያዘ ዘርፉ ትልቅ ችግር ውስጥ የነበረ መሆኑን አስታውሰው በችግሮች ውስጥም ቢሆን የጨረስናቸው ፕሮጀክቶች ለስኬታማነታችን ማሳያዎች ናቸው ብለዋል፡፡ በቅርቡም የጫሞ ካምፓስ ቤተ-መጽሐፍትና የጂኦግራፊ ቤተ-ሙከራ እንዲሁም የአባያ ካምፓስ የመምህራን ቢሮ ሕንፃዎች እየተጠናቀቁ በመሆኑ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ርክክብ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ከሚገኙ ትልልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ አንዱ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ታሪኳ በ2012 በጀት ዓመት ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከዩኒቨርሲቲውና ከግንባታ አማካሪ ድርጅት ጋር የግንባታ ሂደቱን 90 በመቶ ለማድረስና በ2013 በከፊል ሥራ እንዲጀምር ጽ/ቤታቸው የሆስፒታሉን ዋና ግንባታና የሆስፒታሉን የፍሳሽ ማስወገጃ ጨምሮ በትኩረት እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው 22 የሚሆኑ ነባርና አዲስ ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ የሚገኙ ሲሆን በ2012 በጀት ዓመት ለፕሮጀክቶቹ ማስፈጸሚያ 450 ሚሊየን ብር ተመድቧል፡፡

Master Scholarships 2020 for Peace Studies at University of Innsbruck in Austria.
Application for the Innsbruck Master Awards for Peace Studies in Austria – 2020/2021. Entry is now open at the University of Innsbruck in Austria.
The Peace Studies Fund aims to support students of the MA Program in Peace Studies by contributing to the program’s existing scholarship.
➡️ http://bit.ly/2KBy0Rx