ሐዋርያዊ መልሶች
66.8K subscribers
193 photos
187 videos
11 files
655 links
“እኔም፦ ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ እወርድም ዘንድ አይቻለኝም፤ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ስለ ምን ሥራው ይታጐላል?“
ነህምያ 6: 3
YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
Download Telegram
እስቲ ጥያቄ ለሉተራኖች..

ሉተራኖች ከካልቪኒስቶች የተሻሉ በመምሰል እግዚአብሔር ፈቃዱ ሁሉንም ሰው ለማዳን ነው ይላሉ.. ዌል እስቲ እዚህ ላይ እንጠይቃቸው..

ጥያቄ:- የእግዚአብሔር ምርጫ በክርስቶስ ሥራ ቢሆንም በራሱ በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ነው ወይስ አይደለም..??

1. በራሱ ፈቃድ ላይ አልተመሠረተም ካላችሁ ማስረጃ አቅርቡ.. ሲቀጥል አስቀድሞ ሳይፈቅድ መምረጥስ ምንድን ነው..??😁😁 ከመረጠ በኋላ ሊፈቅድ ነው..??

2. መልሳችሁ አዎ በራሱ ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ነው የሚል ከሆነ የእምነት መግለጫችሁም እንደዛ ስለሚል[FC SD XI, 87] ቢያንስ ከቤተ እምነታችሁ አንጻር ልክ ናችሁ.. አሁን ጥያቄው እንዲህ ይቀርባል:

⁉️ ምርጫ በፈቃድ ላይ ከተመሠረተና እግዚአብሔር ደግሞ ሁሉም እንዲድኑ ፈቃዱ ከሆነ.. ለምን እንደ ፈቃዱ ሁሉንም ሰው አልመረጠም..??

የኔን እይታ ግን ላስቀምጥ የሉተራኖቹን

- እግዚአብሔር በራሱ ፈቃድ ብቻ ሰዎችን ለማዳን መርጧል
- ለመዳን የተመረጡት ደግሞ ውስን ሰዎች ናቸው
- ስለዚህም ፈቃዱ ለእነዚህ ሰዎች ብቻ ነው

አንድ ጊዜ ምርጫን በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ ብቻ ከመሠረትክ በኋላ ወደ ኋላ ተመልሰህ እግዚአብሔር ሁሉንም ለማዳን ይፈቅዳል ማለት ሞኝነት ነው።

@Apostolic_Answers
261👍25😱5
ከላይ ላለው ጽሑፍ ማብራሪያ
180👍18
እኔ ታውቃላችሁ ቲም ፖል ነኝ.. አላገባም ምናምን.. ግን ደግሞ ልታገባ ላሰብከው ወዳጄ አንድ የመጨረሻ ነገር ልንገርህ..??

“ከጠበኛና ከቍጡ ሴት ጋር ከመቀመጥ፡
በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።”
[ምሳሌ 21: 19]

✌️😁
🤣455😁6844👍23🤔10😱5🤩3
ቆይ ቆይ ግን.. አሁን ለምሳሌ በትዳር ውስጥ ሆናችሁ ግን ደግሞ ሃሪፍ ትዳር ባይሆንስ.. ባል በሚስቱ ላይ መራራ የሚሆንባት ሲልም ከዛ የሚከፋባት ዓይነት ቢሆንስ..?? አልያም ሚስት ነዝናዛና ምንም ባሏን የማታግዝ ብትሆንስ..??

ዌል ምንም ችግር የለውም እንደ አዲስ መመካከር ከዚያም የንስሐ አባት ይዞ ማማከር.. በቁርባን ካልተጋቡ ምስጢሩን መፈጸም.. ማታ ማታ ለትንሽ ደቂቃ አብሮ መጸለይ መጀመር.. ከዛ ጸዴ እየሆነ ይሄዳል..
462🥰41👍37👏21🤣12🙏6😢3
ኧረ አንዳንድ ሰው ቪዲዮ ሲሰራ ለነገ አያስቀርም😁😁

https://vt.tiktok.com/ZSHrf8KQK/

———
🤣18420😁8🔥6👍5👏1😱1
ሉተር በሕይወቱ ከገጠሙት ትልቅ ፍርሃትና ጭንቀት ውስጥ ግንባር ቀደሙ ከቅድመ ውሳኔ ጋር የተያያዘው ነበር.. ሉተር በአንድ ወቅት ላይ "እግዚአብሔር እኔን ለማዳን ያልመረጠኝ ቢሆንስ?" በሚል አደገኛ ጭንቀት ውስጥ ነበር.. ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ማንን ይምረጥ ማንን አይምረጥ ማንም ሊያውቀው አይችልምና ነው[ይህንን በኋላ ላይ የእግዚአብሔር ድብቅ ፈቃድ ብለውታል]። ለሉተር እግዚአብሔር አንዳንዶችን መርጦ ሌላውን ለምን ተወው? የሚለው ጥያቄ ለጭንቅላት አስጨናቂ ነው እንጂ በዚህ ምክንያት በማለት ምክንያትን አያቀርብም..

ለዚህ ድንጋጤው ደግሞ ያመጣው መፍትሔ፡
1. እግዚአብሔር ሁለት ፈቃዶች አሉት፡ ድብቅ ፈቃድ[hidden will] እና የተገለጠ ፈቃድ[revealed will].... እናም ምንም እንኳን ምርጫው በዋናነት የሚመሠረተው በድብቁ ፈቃድ ላይ ቢሆንና እኛም ባናውቀውም እንኳን ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ግን የተገለጠውን ፈቃዱን መመልከት ብቻ በቂ ነው ስለ ድብቁ ፈቃዱ ምንም ማሰብ አያስፈልግም የሚል ነው።

2. ይህ የተገለጠው ፈቃዱ ብለው የጠሩት ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለምሳሌ "ያመነ የተጠመቀ ይድናል" የሚል ስላለ ይህንን በመያዘ በቃ ካመንክ እና ከተጠመክ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ አሳብ ይዘህ ተመርጫለሁ ብለህ ብቻ አስብ.. ከዛ ውጪ ድብቁን ፈቃዱን አታስበው የሚል ነው። ስለዚህም ሉተርም እንዲህ ያለ ጭንቀት ሲመጣበት "ተጠምቂያለሁ" እያለ በመናገር ከጭንቀት ለማምለጥ ይለማመድ ነበር።

ሉተራኖች በሌለ ነገር መጨነቁን ትታችሁ እንደው በጌታ ብታርፉስ..??😁😁

@Apostolic_Answers
377😁66👍24🔥15🙏11😢10🥰7😱4
ምርጫ በክርስቶስ፡

እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ እንደመረጠን ሲናገር "በክርስቶስ መረጠን" በማለት ነው። ይህ ምን ማለት እንደሆነ በቀላሉ ልንገራችሁ..

ኢየሱስ እውነተኛው የእግዚአብሔር ልጅ ነው.. አሁን በሐዲስ ኪዳን ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ለመሆን የግድ ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን አለባቸው.. ያኔ በክርስቶስ በኩል እነርሱም የእግዚአብሔር ልጆች ይሆናሉ። ጌታ እውነተኛ የወይን ግንድ ነው ይህ ጌታ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ ደግሞ በእርሱ ላይ የምንጣበቅ ቅርንጫፎቹም ከግንዱ የተነሣ ልጆች እንሆናለን.. ይህ አንድንነት ደግሞ የምናገኘ አምነን ስንጠመቅ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱሳችን ይናገራል [ሮሜ ፡3፣ ገላ 3፡27]

ምርጫም ላይ እንዲሁ ነው.. እውነተኛው የእግዚአብሔር ምርጥ ጌታ ኢየሱስ ነው.. በኢሳ 42፡1 ላይም እንደተነገረው "ምርጤ" ተብሏል.. ሰው በሐዲስ ኪዳን በዚህ በእግዚአብሔር ምርጫ ውስጥ ለመግባት የግድ በዚህ በእግዚአብሔር "ምርጥ" በክርስቶስ አካል ላይ መጣበቅ አለበት.. አካሉም በተ ክርስቲያን ናት.. አምኖ የሚጠመቅ ሁሉ የእግዚአብሔር ምርጥ ነው ማለት ነው.. ምክንያቱም ከክርስቶስ ጋር አንድ ስለሚሆን..

ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ በክርስቶስ መረጠን ሲባል በጌታ የሚያምኑትንና የሚጠመቁትን በማየት ማለት ነው.. "በክርስቶስ" ከተባለ በኋላ ያለ እምነትና ጥምቀት ማለት አይቻልም.. ምክንያትም ከጌታ ጋር አንድ የምንሆነው በጥምቀት ነውና.. ሲቀጥል ደግሞ ያለ ፈቃዳችንም አይደለም እሱንም ልናስተውል ይገባል.. ፈቅደን ነው አምነን ምንጠመቀው

@Apostolic_Answers
409👍38🤣8🤩4🥰2👏2🙏1
ማዘር በጣም ነው ምትወደኝ.. ማለት በጣም አይገልጸውም..

ትንሽ ግራ የገባኝ ግን ማዘር የዚህን ያህል ከወደደችኝ ጌታ ምን ያህል ይሆን የሚወደኝ..?? ወይ ተአምር.. ኧረ ጌታ ስለማይነገረው ፍቅርህ እናመሰግንሃለን.. እኛም ደግሞ መልሰን እንወድህ ዘንድ እርዳን.. አንተን መውደድን በልባችን አፍስስ ከማለት ውጪ ምን እንላለን..
2.29K🥰189🙏106😢39👍35🔥18🤣15👏5🙈4
ስለ ቀና ትብብራችሁ.. ጌታ ያክብራችሁ.. እናመሰግናለን..
🔥386277🙏73🤩14😢6
ደስ የሚል ቀን.. ሰግደን ጨረስን..

ዮሐዴ ነው የሚቀረው.. ጥብጣቦ ላይ 470 ታዞ ይግባኝ እየጠየቀ ቢሮ ነው አሉ..
🤣1.76K😁18098🤔14👍12👏9🙏8
ክሪስቶስ አኔስቲ (ክርስቶስ ተነስቷል)
1.69K🙏95🔥80🥰36👏9👍8
ለዝሙት ፈተና ትልቁ መፍትሄ ምንድን ነው..??

ዌል እንግዲህ “ዝሙትን መሸሽ” ልትሉ ትችላላችሁ.. መልካም እሱ ትልቁ መንገድ ቢሆንም በዓለም ለሚኖር ሰው ግን በዚህ በጣም የሚፈተን ከሆነ በመሸሽ ብቻ ላይወጣው ይችላል.. ዝሙት ትንሽ ፈጠን ይላል አንዳንዴ እና ሊደርስብህ ይችላል.. እና ምን ተሻለ..?? ጳውሎስ እንዲህ ይላል:-

“ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።”
[1ቆሮ 7: 2]

@Apostolic_Answers
1.01K😁263🙏76🤣45🔥42👍30😢16🤔10🥰4
አንድ ወዳጄ ከቅዱስ ቁርባን ጋር በተያያዘ ከታች ያለውን ላከልኝና ስለማምንበት አጋራኋችሁ:-

በእውቀት እና በእምነት እንዲሁም በትህትና ሆነን ክርስቶስን በመፈለግ ውስጥ.. ከቅዱስ ቁርባን ቶሎ ቶሎ ቢያንስ በሳምንት አንዴ ስንሳተፍ በውስጣችን ሊከሰቱ ከሚችሉ ነገሮች ውስጥ:-

ከታች የተዘረዘሩት ሃሳቦች ቀስ በቀስ በሕይወታችን ውስጥ እያደጉ የሚሄዱመሆናቸው ሳይዘነጋ እንዲሁም በሕይወታችን ውስጥ መውደቅ መነሳቱና አንዳዴ ጥሩ ያልሆነ ሙድ ውስጥ በመግባት መፈተኑ እንዳለ ሆኖ ነው..

1. እግዚአብሔር አባታችን እንደሆነ ማወቅ ብቻ ሳይሆን የምርም ውስጣችን ላይ የአባትነት እና ልጅነት ስሜቱ በጣም ያድጋል..

2. በጸሎትም ይሁን በዝማሬ ውስጥ እንዲሁም ቅዱሳት መጽሐፍትን በማንበብና በመማማር ጊዜ ጌታ ቅርባችን እንደሆነ ይታወቀናል..

3. የሆነ ነጻነት ይሰማናል.. ምንም እንኳን ለእግዚአብሔር ባሪያዎቹ ብንሆንም.. በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ የምርም የእግዚአብሔር ትንሽ ልጆቹ እንደሆንን በማሰብ ውስጥ የሚመጣ የሆነ ነጻነት.. በፍርሃት እና በትህትና ወደ እግዚአብሔር መቅረባችንን የማያስቀር ዓይነት ነጻነት..

4. ቅዱስ ቁርባን በጣም ይርበናል.. ቶሎ ቶሎ ለመቀበል የመናፈቅ ነገር.. በሳምንት ከአንዴ በላይ ምናምን..

5. የጌታን መምጣት መናፈቅና እርሱን በጣም ተስፋ ማድረግ (ቸርነቱንና አባትነቱን በማሰብ)

@Apostolic_Answers
917🥰114🙏37👍27🔥12