ለሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እየወጣ ያለው የተጋነነ የገንዘብ መጠን..
ኢዮባ ሰሞኑን የለቀቀው አንድ በጣም ጸዴ አሳብን የያዘ ቪዲዮ አለ.. እና ይህ አሳብ በጣም ስለሚገዛኝ በአጭሩ ላስቀምጥላችሁ..
1️⃣ በዙሪያችን ስንት የተራበ እና በችግር የሚኖር ክርስቲያን እያለ በሕንጻ ላይ ሕንጻ መደረቡን ብቻ ማየት ክርስቲያናዊ አይደለም.. ለሕንጻዎቹ በሚወጣው የተጋነነ የገንዘብ መጠን ትልልቅ ፋብራኪዎችን ወይም ሌላ የገንዘብ ምንጭ መሆን የሚችል ነገር በማቆም በዚያ አካባቢ ያሉ ሥራ ያጡ ክርስቲያኖችን ወደ ሥራ ማስያዝ.. ከዛ በሚገኘው ገንዘብ ደግሞ ሕንጻውም ይሠራል.. ክርስቲያኑ እየተራበ በሕንጻ ላይ ሕንጻ መደረብ ግን ክርስቶሳዊ ፍቅርን ማጣት አልያም አለማስተዋልም ሊሆን ይችላል..
2️⃣ ሕንጻ ለማሠራት በዚህ ደረጃ እንደምንደክመው.. እረኛ እንደሌላቸው በጎች በየኃጢአት እና ዓለማዊ መንደሮች ላይ ተበትነው ያሉ ክርስቲያኖች ለመሰብሰብስ መቼ ነው የምንደክመው..?? ክርስቲያኖችን በየቦታው ተጥለው ማየት እኮ ልብን ይሠብራል.. ወይስ “የራሱ ጉዳይ ነው.. ከፈለገ አቅራቢያው ካለ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ይችላል” ብለን እየተቀመጥን ነው..?? ጌታ የጠፉትን ሊፈልግ ወደ ጠፉቱ መጥቷል.. የክርስቶስ ልብ ካለን ይህን እናደርጋለን..
3️⃣ ቤተ ክርስቲያን እንደ ወላጅ ለልጆቿ በዚህ ልክ ስትሰራ ሕዝቡን ሁሉንም ደግሞ መያዝ ትችላለች.. መልሰው ደግሞ ራሳቸው አብልጠው ያግዟታል በገንዘብም ቢሆን እና ከራሳችንም አልፈን በሌላ ቤተ እምነት ውስጥ ያሉ የተቸገሩ ወንድም እህቶቻችንን ደግሞ መደገፍ እንጀምርም ይሆናል ማለት ነው..

❤965👍136🔥34👏34🙏18🥰5🤔3
የአውግስጢኖስ አንዱ ስህተቱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ "Decretive" ብቻ አድርጎ ማስቀመጡ ነበር.. ነገሩ እንዲህ ነው፡
ለአውግስጢኖስ እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ ለማዳን ቢፈቅድ እርሱ ሁሉን ቻይ ነውና በቃ የሱን ፈቃድ ማንም ሊያስቆመው አይችልም.. ስለዚህም ሁሉም ሰው መዳኑ አይቀርም ነበር፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው አልዳነምና ይህ የሆነው እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው ለማዳን ስላልፈቀደ ነው.. [Enchiridion, chap. 103]
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ግን ዮሐንስ ዘደማስቆም እንደሚያስቀምጠው በሁለት ከፍለን [antecedent እና consequent will] ልናየው እንችላለን[exposition bk 2, chap. 29]..
1. የእግዚአብሔር ቀዳሚ ፈቃዱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ ነው.. ይህ በእኛ ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ከራሱ ፍቅር የተነሣ ብቻ ነው.. ይህን antecedent will [ቀዳሚ ፈቃድ] እንለዋለን.. እግዚአብሔር ሁሌም መልካምን ብቻ ነው የሚፈቅደው
2. የእግዚአብሔር ቀጣይ(ደሃራዊ) ፈቃዱ ግን በሰዎች ምላሽ ላይ የሚመሠረት ነው። ለምሳሌ ከድኅነት አንጻር የእግዚአብሔር ደሃራዊ ፈቃዱ የሚያምኑ ሁሉ ይድኑ ዘንድ ነው.. ይህንን Consequent will እንለዋለን
ስለዚህ አውግስጢኖስ ይህንን ባላገናዘበ መልኩ እግዚአብሔር ገና ከጅምሩ ሰዎችን ሁሉ ለማዳን ባይወድ ነው ብሎ ማስቀመጡ ስህተት ነው ማለት ነው.. እርሱ ብቻ ሳይሆን ካልቪኒስቶችም አሁን ያሉት
@Apostolic_Answers

❤240👍37🙏12🤣7🔥5
የሉተራኖች እጅግ የተወዛገበው የቅድመ ውሳኔ እና የእግዚአብሔር ፈቃድ ትምህርት፡
ጥያቄ 1፦ እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ ለማዳን ፈቅዷል..??
- ሉተራኖች፦ አዎን ፈቅዷል
ጥያቄ 2፦ እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ ለማዳን መርጧል..??
- ሉተራኖች፦ አልመረጠም፣ የተወሰነ ቁጥር ያላቸውን ብቻ ነው የመረጠው.. ከነሱም ውጪ የሚድን የለም.. [Brief Statement of the Doctrinal Position of the Missouri Synod - of the election of grace, 35-36]
ጥያቄ 3፦ እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ ከወደደ ታድያ አንዳንዱን ለማዳን መርጦ ሌላውን ለምን ተወው..??
- ሉተራኖች፦ እንጃ.. ሊፈታ የማይችል ምስጢር ነው.. [እነ ፍራንዝ ፒፐር "Crux theologorum" ብለውታል.. ምስጢር ነው ነው ሎል]
ጉዳዩ ግን ወዲህ ነው.. አዎ እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ ይወዳል.. ታድያ ግን አንዳንዶች ድነው ሌሎች ያልዳኑት በሰዎቹ ፈቃድ ደግሞ ነው..

❤284👍38🤣12🤔9🥰7😢1🙏1
ላስቸግራችሁ ጋይስ..
የተወደደው ወንድማችን ኢያሱ(መራኁት) ቻሌንጅ ተሰጠውና ከታች የማስቀምጥላችሁን የቲክቶክ አካውንት 60k ቢያስገባ ያው ሳንቲም ሊሰጡት ነው.. ፕሊስ ጋይስ ሁላችሁም ፎሎው አድርጉለት..
👇👇👇
https://www.tiktok.com/@ahaty.tours?_r=1&_t=ZS-959j6zSm7oz

❤324👍68🤔5😱1😢1
እስቲ ጥያቄ ለሉተራኖች..
ሉተራኖች ከካልቪኒስቶች የተሻሉ በመምሰል እግዚአብሔር ፈቃዱ ሁሉንም ሰው ለማዳን ነው ይላሉ.. ዌል እስቲ እዚህ ላይ እንጠይቃቸው..
ጥያቄ:- የእግዚአብሔር ምርጫ በክርስቶስ ሥራ ቢሆንም በራሱ በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ነው ወይስ አይደለም..??
1. በራሱ ፈቃድ ላይ አልተመሠረተም ካላችሁ ማስረጃ አቅርቡ.. ሲቀጥል አስቀድሞ ሳይፈቅድ መምረጥስ ምንድን ነው..??😁😁 ከመረጠ በኋላ ሊፈቅድ ነው..??
2. መልሳችሁ አዎ በራሱ ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ነው የሚል ከሆነ የእምነት መግለጫችሁም እንደዛ ስለሚል[FC SD XI, 87] ቢያንስ ከቤተ እምነታችሁ አንጻር ልክ ናችሁ.. አሁን ጥያቄው እንዲህ ይቀርባል:
⁉️ ምርጫ በፈቃድ ላይ ከተመሠረተና እግዚአብሔር ደግሞ ሁሉም እንዲድኑ ፈቃዱ ከሆነ.. ለምን እንደ ፈቃዱ ሁሉንም ሰው አልመረጠም..??
የኔን እይታ ግን ላስቀምጥ የሉተራኖቹን
- እግዚአብሔር በራሱ ፈቃድ ብቻ ሰዎችን ለማዳን መርጧል
- ለመዳን የተመረጡት ደግሞ ውስን ሰዎች ናቸው
- ስለዚህም ፈቃዱ ለእነዚህ ሰዎች ብቻ ነው
አንድ ጊዜ ምርጫን በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ ብቻ ከመሠረትክ በኋላ ወደ ኋላ ተመልሰህ እግዚአብሔር ሁሉንም ለማዳን ይፈቅዳል ማለት ሞኝነት ነው።

❤257👍25😱5
እኔ ታውቃላችሁ ቲም ፖል ነኝ.. አላገባም ምናምን.. ግን ደግሞ ልታገባ ላሰብከው ወዳጄ አንድ የመጨረሻ ነገር ልንገርህ..??
“ከጠበኛና ከቍጡ ሴት ጋር ከመቀመጥ፡
በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።”
[ምሳሌ 21: 19]
✌️😁
“ከጠበኛና ከቍጡ ሴት ጋር ከመቀመጥ፡
በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።”
[ምሳሌ 21: 19]
✌️😁
🤣452😁68❤44👍22🤔10😱5🤩3
ቆይ ቆይ ግን.. አሁን ለምሳሌ በትዳር ውስጥ ሆናችሁ ግን ደግሞ ሃሪፍ ትዳር ባይሆንስ.. ባል በሚስቱ ላይ መራራ የሚሆንባት ሲልም ከዛ የሚከፋባት ዓይነት ቢሆንስ..?? አልያም ሚስት ነዝናዛና ምንም ባሏን የማታግዝ ብትሆንስ..??
ዌል ምንም ችግር የለውም እንደ አዲስ መመካከር ከዚያም የንስሐ አባት ይዞ ማማከር.. በቁርባን ካልተጋቡ ምስጢሩን መፈጸም.. ማታ ማታ ለትንሽ ደቂቃ አብሮ መጸለይ መጀመር.. ከዛ ጸዴ እየሆነ ይሄዳል..

❤458🥰41👍36👏21🤣12🙏6😢3
🤣184❤20😁8🔥6👍5👏1😱1
ሉተር በሕይወቱ ከገጠሙት ትልቅ ፍርሃትና ጭንቀት ውስጥ ግንባር ቀደሙ ከቅድመ ውሳኔ ጋር የተያያዘው ነበር.. ሉተር በአንድ ወቅት ላይ "እግዚአብሔር እኔን ለማዳን ያልመረጠኝ ቢሆንስ?" በሚል አደገኛ ጭንቀት ውስጥ ነበር.. ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ማንን ይምረጥ ማንን አይምረጥ ማንም ሊያውቀው አይችልምና ነው[ይህንን በኋላ ላይ የእግዚአብሔር ድብቅ ፈቃድ ብለውታል]። ለሉተር እግዚአብሔር አንዳንዶችን መርጦ ሌላውን ለምን ተወው? የሚለው ጥያቄ ለጭንቅላት አስጨናቂ ነው እንጂ በዚህ ምክንያት በማለት ምክንያትን አያቀርብም..
ለዚህ ድንጋጤው ደግሞ ያመጣው መፍትሔ፡
1. እግዚአብሔር ሁለት ፈቃዶች አሉት፡ ድብቅ ፈቃድ[hidden will] እና የተገለጠ ፈቃድ[revealed will].... እናም ምንም እንኳን ምርጫው በዋናነት የሚመሠረተው በድብቁ ፈቃድ ላይ ቢሆንና እኛም ባናውቀውም እንኳን ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ግን የተገለጠውን ፈቃዱን መመልከት ብቻ በቂ ነው ስለ ድብቁ ፈቃዱ ምንም ማሰብ አያስፈልግም የሚል ነው።
2. ይህ የተገለጠው ፈቃዱ ብለው የጠሩት ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለምሳሌ "ያመነ የተጠመቀ ይድናል" የሚል ስላለ ይህንን በመያዘ በቃ ካመንክ እና ከተጠመክ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ አሳብ ይዘህ ተመርጫለሁ ብለህ ብቻ አስብ.. ከዛ ውጪ ድብቁን ፈቃዱን አታስበው የሚል ነው። ስለዚህም ሉተርም እንዲህ ያለ ጭንቀት ሲመጣበት "ተጠምቂያለሁ" እያለ በመናገር ከጭንቀት ለማምለጥ ይለማመድ ነበር።
ሉተራኖች በሌለ ነገር መጨነቁን ትታችሁ እንደው በጌታ ብታርፉስ..??😁😁

❤375😁66👍24🔥15🙏11😢10🥰7😱4
ምርጫ በክርስቶስ፡
እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ እንደመረጠን ሲናገር "በክርስቶስ መረጠን" በማለት ነው። ይህ ምን ማለት እንደሆነ በቀላሉ ልንገራችሁ..
ኢየሱስ እውነተኛው የእግዚአብሔር ልጅ ነው.. አሁን በሐዲስ ኪዳን ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ለመሆን የግድ ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን አለባቸው.. ያኔ በክርስቶስ በኩል እነርሱም የእግዚአብሔር ልጆች ይሆናሉ። ጌታ እውነተኛ የወይን ግንድ ነው ይህ ጌታ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ ደግሞ በእርሱ ላይ የምንጣበቅ ቅርንጫፎቹም ከግንዱ የተነሣ ልጆች እንሆናለን.. ይህ አንድንነት ደግሞ የምናገኘ አምነን ስንጠመቅ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱሳችን ይናገራል [ሮሜ ፡3፣ ገላ 3፡27]
ምርጫም ላይ እንዲሁ ነው.. እውነተኛው የእግዚአብሔር ምርጥ ጌታ ኢየሱስ ነው.. በኢሳ 42፡1 ላይም እንደተነገረው "ምርጤ" ተብሏል.. ሰው በሐዲስ ኪዳን በዚህ በእግዚአብሔር ምርጫ ውስጥ ለመግባት የግድ በዚህ በእግዚአብሔር "ምርጥ" በክርስቶስ አካል ላይ መጣበቅ አለበት.. አካሉም በተ ክርስቲያን ናት.. አምኖ የሚጠመቅ ሁሉ የእግዚአብሔር ምርጥ ነው ማለት ነው.. ምክንያቱም ከክርስቶስ ጋር አንድ ስለሚሆን..
ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ በክርስቶስ መረጠን ሲባል በጌታ የሚያምኑትንና የሚጠመቁትን በማየት ማለት ነው.. "በክርስቶስ" ከተባለ በኋላ ያለ እምነትና ጥምቀት ማለት አይቻልም.. ምክንያትም ከጌታ ጋር አንድ የምንሆነው በጥምቀት ነውና.. ሲቀጥል ደግሞ ያለ ፈቃዳችንም አይደለም እሱንም ልናስተውል ይገባል.. ፈቅደን ነው አምነን ምንጠመቀው

❤408👍37🤣8🤩4🥰2👏2🙏1
ማዘር በጣም ነው ምትወደኝ.. ማለት በጣም አይገልጸውም..
ትንሽ ግራ የገባኝ ግን ማዘር የዚህን ያህል ከወደደችኝ ጌታ ምን ያህል ይሆን የሚወደኝ..?? ወይ ተአምር.. ኧረ ጌታ ስለማይነገረው ፍቅርህ እናመሰግንሃለን.. እኛም ደግሞ መልሰን እንወድህ ዘንድ እርዳን.. አንተን መውደድን በልባችን አፍስስ ከማለት ውጪ ምን እንላለን..

❤2.26K🥰189🙏105😢38👍34🔥18🤣15👏5🙈4
ደስ የሚል ቀን.. ሰግደን ጨረስን..
ዮሐዴ ነው የሚቀረው.. ጥብጣቦ ላይ 470 ታዞ ይግባኝ እየጠየቀ ቢሮ ነው አሉ..

🤣1.73K😁177❤96👍12🤔12👏9🙏8
ለዝሙት ፈተና ትልቁ መፍትሄ ምንድን ነው..??
ዌል እንግዲህ “ዝሙትን መሸሽ” ልትሉ ትችላላችሁ.. መልካም እሱ ትልቁ መንገድ ቢሆንም በዓለም ለሚኖር ሰው ግን በዚህ በጣም የሚፈተን ከሆነ በመሸሽ ብቻ ላይወጣው ይችላል.. ዝሙት ትንሽ ፈጠን ይላል አንዳንዴ እና ሊደርስብህ ይችላል.. እና ምን ተሻለ..?? ጳውሎስ እንዲህ ይላል:-
“ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።”
[1ቆሮ 7: 2]

❤925😁243🙏71🤣41🔥40👍26😢15🤔9🥰4