ሐዋርያዊ መልሶች
67.6K subscribers
195 photos
207 videos
11 files
680 links
“እኔም፦ ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ እወርድም ዘንድ አይቻለኝም፤ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ስለ ምን ሥራው ይታጐላል?“
ነህምያ 6: 3
YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
Download Telegram
ሐዋርያዊ መልሶች Chat
እኛ እንዴት ነው መረዳት ያለብን ትንሽ ብትልበት
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በተያያዘ ከላይ ላለው እኛስ እንዴት ነው መረዳት ያለብን ለሚለው..

1. መጽሐፍ ቅዱስን እንደ መጽሐፍ ቅዱስነቱ ስንቀበለው በጥቅሶችና በመጽሐፉ መካከል ልዩነትን እየፈጠርን አይደለም.. ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ ስንል የእግዚአብሔር ቃል እያልን ከሆነ ጥቅሶችንም ሊመለከት የሚችል ነው

2. መጽሐፍ ቅዱስ አይሳሳቴ(infallible) ነው..?? ለሚለው ጥያቄ ያው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንጩ ራሱ እግዚአብሔር ነው ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ እስትንፋስ ወይም ቃል እየተባለም ይጠራል.. ስለዚህም እግዚአብሔር አይሳሳቴ ነውና መጽሐፉም ሊሳሳት አይችልም.. እዚህ ላይ inerrancyን እና infallibilityን አብዝቶ በመለያየት ጥቅሶቹ inerrant ናቸው እንጂ infallible አይደሉም ለሚለው ሙግት የቃሉን ትርጉም ማየት በቂ ነው.. infallible ማለት ስህተት የማይሰራ(incapable of making mistake) ብቻ ሳይሆን ስህተት ሊሆን የማይችል(incapable of being wrong) ማለትም ነው.. መጽሐፍ ቅዱስ ስህተት ሊሆን አይችልምና አይሳሳቴ(infallible) ልንለው እንችላለን ነው።

ይህ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ ባስልዮስ ቅዱሳት መጽሐፍት የትምህርት መመዘኛና ዳኛም ሊሆኑ እንደሚችሉ ያስቀምጣልና(letter 189:3) መዳኘት የሚችሉት እነርሱ አይሳሳቴ ናቸውና ነው።

ስለዚህም ይህንን infallible የሚለውን ቃል ለመጽሐፍ ቅዱስ በሃገር ውስጥም በውጭ ሃገርም ያሉ ኦርቶዶክስ መምህራን የሚጠቀሙበት ለዛ ነው.. ሁለቱን ቃላት በመለያየት አንዱን እንጠቀማለን አንዱን አንጠቀምም የሚል ግን ከሚታወቅ የኦርቶዶክስ መምህር ሰምቼ አላውቅም..

3. መጽሐፍ ቅዱስ አይሳሳቴ ነው ስንል መጽሐፍ ቅዱስ ሙስሊሞቹ ለቁርአን እንደሚሉት ቃል በቃል እንደው ብቅ ያለ ሳይሆን በሰዎች አገላለጽ ዘመናትንና ባህልን ባማከለ መልኩ የተጻፈ ነውና በውስጡ ለድኅነታችን ከተሰጠን አስተምህሮ አንጻር ምንም ዓይነት እንከን የማይገኝበት እንከን አልባ ነው እንላለን.. ስለዚህም የቁጥር ልዩነትም ሆነ ሌላ ሌላ እንደ ኦርቶዶክስ ለእኛ አሳሳቢ አይደለም ማለት ነው።

ሌላ ጥያቄ ካላችሁ ከታች ኮመንት ላይ እያየሁ እመልሳለሁ
271🥰24🙏21👍9👏7🔥3
"የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል"
[ዕብራውያን 4፡ 12]

ለመጨመር ያህል እዚህ ላይ ጳውሎስ እንደሚናገረውም መጽሐፍ ቅዱስ እንደ አንድ የታሪክ መጽሐፍ እንዲሁ የሚነበብ ብቻ ሳይሆን በቅን ልብ ለሚያነበው በውስጡ እግዚአብሔር actively የሚሠራበት መጽሐፍ ነው(በጽሑፍ ያለው ብቻ ሳይሆን በተሰበከውም መሆን እንደሚችል ግን ይያዝ) ለዛም የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራም ነው የሚለው.. ከዚህ አንጻር የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ነውና ሁሌም ይሠራልና አይሳሳቴ ነው ሊባል ይችላል..

@Apostolic_Answers
👍260233🙏31👏21🥰4🤣4🔥2
ይሄ ጊዜ ኧረ ተመልሶ መምጣት አለበት.. ቶሎ እንመለሳለን በጌታ እርዳታ.. ቆንጂትን ደግሞ ፎሎው አድርጉልኝ በኔ ስም😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMAcKVyE4/
248🤣13🙏8😁5
ዛሬ በጌታ ቀን ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል:

ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና።
[ዮሐንስ 5: 19]

ይህንን ጥቅስ በመያዝ አንዳንድ ሰዎች “ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም” ይላልና ወልድ አምላክ አይደለም ይላሉ.. ታድያ ግን በተቃራኒው ይህ ክፍል ራሱ የወልድን አምላክነት እንዴት እንደሚያሳይ አብረን በ2 ነጥብ እንይ:

1. “አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ..” የሚል ቃል አለ.. ስለዚህም ወልድ የሚያደርገውን ሁሉ የሚያደርገው አብ ሲያደርግ ያየውን እንጂ ሌላ አይደለም.. ይህንን ደግሞ የተናገረው ስለ መለኮታዊ ሥራ ነው.. ከላይ ያንን የአልጋ ቁራኛ ፈውሶት ስለነበር “አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም እሠራለሁ” በማለት ነው ከላይ የጀመረው.. ስለዚህም መለኮታዊ የሆነ ነገርን ከአብ የተለየ በራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም.. ስለዚህም በዚህ ነጥብ ላይ ምናስተውለው ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ ሥራ ሊኖረው እንደማይችል ነው..

2. “አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርገዋል” ይላልና ወልድ ከአብ የተለየ ምንም መለኮታዊ ሥራ የለውም.. ግን ደግሞ አብ የሚያደርገውንስ ምን ያህሉን ወልድ ያደርገዋል..?? ካልን መልሱ “አብ የሚያደርገውን ሁሉ” የሚል ይሆናል.. ለምሳሌ ከታችም እንደተቀመጠው አብ ሕይወትን እንደሚሰጠው ወልድም እንዲሁ ይሰጣል.. ስለዚህም አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ካደረገና ወልድ ደግሞ ከአብ የተለየ ሌላ ምንም ነገር ከሌለው በመለኮት ከአብ ጋር ፍጹም አንድ ናቸው ማለት ነው.. አብ እውነተኛ አምላክ እንደመሆኑ ወልድም ከአብ የተገኘ እውነተኛ አምላክ ነው.. ምንም እንኳን ሁለት አካላት ቢሆኑም መለኮት ግን አንድ ነውና ሁለት አካል አንድ አምላክ እንጂ ሁለት አማልክት አንልም ነው።

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
1.17K🙏111🔥48👍23👏15😢4🤣4🥰2😱1
ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከ‍እምነት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።
[1ጢሞ 6: 10]

ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነው.. ለምትወደው ነገር ትገዛለህና ገንዘብን ወደድክ ማለት ሳታስበው ለገንዘብ መገዛት ትጀምራለህ.. በሌላ አማርኛ የገንዘብ ባርያ ትሆናለህ..

ከዚያም በአፍህ “ጌታ ጌታ” እያልክ በልብህ ግን ለጌታ ሳይሆን ለገንዘብ ትገዛለህ.. ምክንያቱም ጌታችንም እንዳለን ለሁለት ጌቶች መገዛት አንችልምና.. ስለዚህም ገንዘብን በአግባቡ መጠቀም እንጂ ከገንዘብ ጋር ፍቅር ውስጥ ልንገባ አይገባም..

መልካም ጾም ጸሎት

@Apostolic_Answers
874🙏142👍45🔥13👏9
አውግስጢኖስ ብዙ መልካም ጽሑፎች አሉት.. በተለይ ኑዛዜውን ብዙ ሰው ይወድለታል.. እኔም የምወደው አባት ነው..

የጸጋ እና የምርጫ(ቅድመ ውሳኔ) ትምህርቱ ግን.. በተለይም ቀደም ሲል የነበረ እምነቱን “ተሳስቼ ነበር” እያለ መቀየር ሲጀምር ምናምን.. ምናለ ከሱ ቀደም እንደነበሩ አባቶቹ የታመነውን ይዞ ቢቀጥል ያስብላል..

ለማንኛውም ግን እኛ አባቶችን ስንቀበል ነጥለን አንድ አባት ብቻ አንይዝም.. እንደዛ ቢሆን እኛ ራሳችን የግለሰብ በሆንን ነበር.. ይልቁንም በጌታ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን የአባቶች ስምምነት(consensus patrum) ነው ምንመለከተው.. ስለዚህም አውግስጢኖስም እርሱ በነበረበት ሰዓት በነበሩና ከሱ በፊት በነበሩ አባቶች ይመዘናል ማለት ነው.. እንደዛም ሆኖ ግን አውግስጢኖስ ሃሪፍ አባት ነው..

@Apostolic_Answers
415👍40🔥22👏10🙏3😱2
ከፊትህ አትጣለኝ፥
ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።

በጣም ትልቅ ጸሎት
1.55K🙏209🥰34👍32😢19🔥16
ኧረ በቅዱስ ሚካኤል ዛሬ ቅዳሴ ላይ ሕዝቡን እየዞርኩ ወንጌል አሳልሜ ዲያቆን የሆንኩ የሆንኩም መስሎ እየተሰማኝ ነው..

እስቲ አንድ ጊዜ “ተረጋጋ” እንላለን😁😁
🤣994359🥰60😁47🔥29👍15
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ ጊዜ ትዝ ይላችኋል አይደል.. መሠረት ደፋር ስታሸንፍ ምስለ ፍቁር ወልዳን ካሜራ ፊት አውጥታ ለዓለም ሁሉ እመቤታችንን ስታሳይ..

ያኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ ክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ ደስ አላቸው.. ያው ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ካቶሊክን ጨምሮ ማለት ነው..

አሁን ደግሞ እኛ ሃገር የቲክቶክ አዋርድ ላይ አንዳንድ ልጆች ሲያሸንፉ የወላዲተ አምላክን ስም መጥራታቸው ለአንዳንዶች የሚጨንቅ ሆኗል እና ያሳዝናል..

ሰው አባቱን ወይም ወንድም እህቱን አለያም እናቱን ቢጠራ ምንም ችግር አይኖረውም.. እናቱን ማርያምን ግን ከጠራ ያበሳጫል.. እዛ መድረክ ላይ እኮ እየሰበኩ አይደለም እነዚህ ልጆች.. ያው ፍቅራቸውን እየገለጹ ነው እና ይግለጹ በጣም ደስ ይላል..

@Apostolic_Answers
1.83K👍103🔥36🙏35🤣17🤩12👏11😢6🤔3😱1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዚች እንጀምር እስቲ ከመጨረሻው😁😁

ከታች በትንሹ የተጻፈው የአማርኛ ትርጉሙ ነው..
799🙏54🔥30👍17🥰8🤔6🤣5👏4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መዓዛ ያለው ሽቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
736🥰68🙏26🔥15🤩2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጣም ይቅርታ ጋይስ ግን ይህ ስም..
1.14K🥰160🔥47😢37👍10👏9🤩1
በማይነገር ስጦታው..

ጋይስ ነጻነቴን ስጡኝ ልዘምርበት😁😁
1.3K🥰109👍79😁44👏40🙏32🔥31🤣16😢6🙈4
ኢየሱስ አሁንም ድረስ በሰማይ አብን ይለምነዋል(ይጸልያል) እንዴ..??

በውስጥ የደረሰኝ ጥያቄ ነው..

ጌታችን በምድር ሳለ ጸልዩዋል ወደ አብ ማልዷል.. ግን ደግሞ ልክ እንዲሁ አሁንም በሰማይ የጸሎት እና ልመና ድርጊት እየተካሄደ ነው እና ምልጃ ምንለውም እሱን ነው የሚል ትምህርት በቤተ ክርስቲያን ደረጃ በየትም ቦታ አላውቅም.. ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ የሰራው ሥራ ለዘላለም ሕያው ነው.. ለዘላለም ሕያው የሆነው ደግሞ የማይለወጥ ክህነት ስላለውና በአብ ቀኝ አሁንም ድረስ ተቀምጦ ስለሚኖር ነው.. ስለዚህም ስለሁላችን ሞቶ የተነሳው ጌታ በአብ ቀኝ አለና በእርሱ የተሰራው ሥራ ሁሌም የሚያገለግል ነው..

ስለዚህም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ “ይጸልያል” የሚለውን ቃል የተጠቀሙ ሊቃውንት ቢገኝ እንኳን በምድር ላይ የሰራው ሥራ ሕያው መሆኑን ከማመልከት አንጻር ይሆናል እንጂ አሁንም የቀረ ጸሎት ያለ ይመስል እየደጋገመ እየጸለየ ይኖራል የሚለው ከክርስትና ራቅ ያለ መሰለኝ😁😁

ምንም ሆነ ምን ግን ከምን አንጻር እንደተጠቀሙት እናያለን እንጂ እንዲሁ ቃላት እየመዘዝን የራሳችንን አስተምህሮ ማለትም አሁንም ጌታ በአብ ፊት እየተማጸነ ነው የሚል ትምህርት መመስረት ከባድ ይመስለኛል..

- በፕሮቴስታንቶቹ እንኳን ለምሳሌ እነ ካልቪን የኢየሱስን ምልጃ ሲያስረዱ በመስቀል ላይ ሞቶ ከዚያም መነሳቱን እንጂ አሁን ላይ ይለምናል ማለት አይደለም እያሉ ነው..(commentary on romans 8:34)

- በካቶሊካውያን ዘንድም የምልጃን አሳብ ሲያብራሩ የጌታ መካከለኛነት እንደሆነና በመስቀሉ ሥራ የተከናወነ እንደሆነ ሲያስሰቀምጡ የቅዱሳንን ግን ጸሎት ልመና ብለው ይለዩታል(catholic encyclopedia, intercession(mediation)

ኢየሱስ በሰማይ ይለምናል የሚለው ቃል የቤተ ክርስቲያን ልምድም እንዳልሆነ ይናገራሉ(George haydock, comm. On romans)

- በግብጽም እነ አቡነ ሺኖዳ የጌታችንን አስታራቂነት ሲያብራሩ ከመስቀሉ ሥራ አንጻር ያደርጉትና ጸሎት ልመናን ግን ለይተው ለቅዱሳን ይሰጣሉ..(comparative theology, on intercession)

- የኛ ሃገር ሊቃውንትም ይማልዳል የሚለውን ሲያብራሩ በእለተ አርብ በመስቀል ላይ በሠራው ሥራ ለዘላለም ስለሚያስታርቅበት እንደሆነ ነው የሚያስቀምጡት(የሮሜም የዕብራውያንም አንድምታ ትርጓሜ)

@Apostolic_Answers
745👏53👍32🙏29
መልስ:- በውስጥ ሥላሴ ላይ ለተጠየኩት:

1. አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ 3 አካላት ካልኩ በኋላ መለኮት ደግሞ ሲባል 4ኛ ይመስለኛል እንዴት ልረዳው..??

2. ወልድ መላኩ ከአብ የሚያንስ ያስመስልብኛል
390🙏56👍24🔥10😁6🥰5👏5🤣3
ቅዳሴ ላይ የሚሰጥ ትምህርት..

በጥንቷም ቤተ ክርስቲያን ትምህርት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባት በቅዳሴ ሰዓት አሉ.. ግን ትምህርቱ የሚሰጠው “ጻኡ” ከመባሉ በፊት ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባባት ቀጥሎ ነው.. ከዛ በኋላ ቅዳሴው የሚጠናቀቀው በቅዱስ ቁርባን እንጂ በትምህርት አይሆንም ማለት ነው.. ስለዚህ ከቅዱስ ቁርባን ቀጥሎ ምንም ዓይነት ወንጌልም ሆነ ምንም ነገር አይሰጥም በቃ መዝጊያ ነው የሚደረገው..

እኛ ሃገርም እንደዛ ቢሆን ጥሩ ነበር ያው የእሁዱ ቅዳሴ ላይ ብዬ አሰብኩ.. ያው ምንም ከአባቶቼ እኔ ባላውቅም እንኳን ማለት ነው..

መልካም የጌታ ቀን
492👍50🤔17🤣17🔥10
አሁን ከቤት መውጣት ግድ ሆኖብኝ ልወጣ ስል እቺን ኮፍያ ለማድረግ አሰብኩ.. እና ልበሳ ምን አገባን አትሰግጥ እንግዲ

እሺ አርማዋን እንድታዩልኝ ነው ሎል.. አርማው ላይ X እና P ይታያችኋል.. በግሪክ “ክርስቶስ” ሲጻፍ χριστός ነው እና የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን ፊደላት ተጠቅመው የሰሩት ነው.. ጥንት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታወቅ አርማ ነበር.. christogram በመባል ይታወቃል..

ከጎን እና ከጎን የተጨመረው ደግሞ Aα (አልፋ) እና Ω(ኦሜጋ) ነው.. ጌታ ኢየሱስ አልፋ እና ኦሜጋ ነው.. ዙሪያውን ደግሞ ያለው ጽሑፍ የጌታ ጸሎት ነው

በድጋሜ መልካም የጌታ ቀን😁😁
1.45K🔥114👍55😁41👏22😱5🙈4😢2🙏1
በአምላክ ማመን
ሐዋርያዊ መልሶች
ላይቭ ላይ በነ ዘሚካኤል የተሰጠው ትምህርት.. አጭር ደቂቃ ናት ግን ተረጋግታችሁ ቀስ ብላችሁ አድምጡት
👍219122🙏24🔥6😱5
ሕጻን ልጅ አይታችሁ ከሆነ ሌላ ሰው ሊመታው ሲል ሮጦ አባቱ ወይም እናቱ ሥር ድብቅ ይላል..

ጋይስ በወጣትነት እድሜያችን በቀላሉ ኃጢአት እንዳይመታንና እንዳይጥለን የሆነ ሮጠን የምንሸሸግበት ነገር አያስፈልገንም..?? አባትም እናትም ወደሆነን ጌታ ኢየሱስ ሮጦ መሸሸግ ብቻ ነው ለኛ የሚበጀው.. እርሱ ብቻ ነው ታዳጊያችን.. አልያ ግን በጣም ሰንካላ አቅመ ቢስ ነን.. ሁሌም በጌታችን ፊት በራሱ አቅም እንደሌለው ሕጻን ልጅ ብቻ እንይ ራሳችንን..
848👍69🔥35🙏28🥰15
መሸሸጊያዬ - የእግዚአብሔር ልጅ

ለ3 ደቂቃ የሚቆይ..??🙄🙄
942🥰111🙏37🔥32👏29😢13🙈3😱2