A+ Tutorial Class Official
19.3K subscribers
414 photos
15 videos
168 files
59 links
📚 A+ Tutorial Class ለ መጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠቃሚ የሆነ አጋዥ ቲቶርያል በመስጠት እንዲሁም የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለግቢ ፈተናዎቻቼው የሚያግዟቸውን pdfs, ያለፉ አመታት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች Mid and Final Exams የሚያቀርብ ቻናል ነው።

እኛን ለማግኘት : በ @Aplus_support_Admin በኩል ማንኛውንም ጥያቄዎትን ሊያደርሱን ይችላሉ።
Download Telegram
🚨 Important Updates Available.

🔥 የ A+ Tutorial የፍሬሽማን Application መማሪያ አፕ ላይ ተመዝግባችሁ እየተማራችሁ ያላችሁ ተማሪዎች Playstore ላይ በመግባት update አድርጉት⤵️

📱https://play.google.com/store/apps/details?id=com.aplus.depthabdre.tutorial

👏 ከ 2013-2018 ዓ.ም ድረስ የተለያዩ ግቢዎች ላይ የወጡ የ mid exam ጥያቄዎችን በቻፕተር በመከፋፈል ፥ በአንድ ቻፕተር ከ 100 በላይ ጥያቄዎች ለመረዳት ግልፅ በሆነ መንገድ ተብራርተው አፑ ላይ ተጭነዋል። በጥያቄዎቹ ማብራሪያዎች ላይ እያንዳንዱ የሞጅሉ ቻፕተር ገፅ በገፅ ተዳሰዋል።

🎉 ከ Worked Solutions በተጨማሪ በ አንድ lesson ብቻ ከ 30 በላይ ጥያቄዎች በ quiz መልክ ታኛላችሁ ፥ በአጠቃላይ በ አንድ ቻፕተር ከ 100 በላይ የ quiz ጥያቄዎች የተካተቱ ሲሆን ፤ በአንድ ቻፕተር
worked Solution + Quiz ከ 200 በላይ ጥያቄዎችን ታገኛላችሁ።

🥺 በየትኛውም ግቢ የምትመደቡ ተማሪዎች እነዚህን ጥያቄዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ስለምትፈተኗቸው ትኩረት ሰጥታችሁ ስሯቸው።

🔜 በቅርቡ በ A+ Tutorial የተዘጋጁ ከግቢ ፈተናዎቻችሁ ጋ በቀጥታ የሚገናኙ ፈተናዎችን ስለምንፈተናችሁ ያቀረብንላችሁን ቲቷርያል እና ፈተናዎች በደንብ ስሯቸው።

💡 ቅርፃወቸውን እየቀያዬሩ በዬአመቱ የሚወጡ ጥያቄዎች ከተለያዩ ግቢዎች በጥንቃቄ ተመርጠው ከነ ማብራያቸው የተዘጋጁ ሲሆን ፤ ለጥያቄዎቹ የቀረቡት ማብራሪያዎች ግቢ ላይ ፈተናን በምን መልክ መስራት እንዳለባችሁ የፈተና አሰራርን technique ን የሚያሳዩ ፥ የፈተና አሰራር system ን እግረ መንገዳችሁን እንዲታውቁ የሚያደርጉ ናቸው።

▶️በተጨማሪም የፍሬሽማን ሞጁሎችን በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችሉ ፥ ከ real world ጋ የሚገናኙ ፤ በቀጥታ ከ ህይወት ጋ የሚገናኙ ገላጭ ቲቶርያሎችን ስለሆነ ያዘጋጀንላችሁ የፍሬሽማን ኮርሶችን ለመረዳት ጊዜ ቆጣቢ እና ብዙ ነገር አቅላይ ናቸው ፤ ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች A+ Tutorial ላይ ለመማር ከ playstore ላይ አፑን በመመዝገብ ቲቶርያሎቹን ማግኘት ትችላላችሁ።

💬 ስለ ቲቶርያሉ መረጃ ለመጠዬቅ : @Aplus_support_Admin ን ይጠቀሙ።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤12🔥2
🎯 የጥሪ ማስታወቂያ

ጅማ ዪኒቨርሲቲ በ2019 አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎቹ ጥቅምት 4 እና 5 ጥሪ አድርጓል።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10😱1
📣 Exam Week.

🎉 በጣም አስፈላጊ በሆኑ topics ላይ ልትፈተኑ ነው።

🏆 ከ ሰኞ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በ A+ Tutorial የዘተጋጁ ፤ ከግቢያችሁ ፈተናዎች ጋ በቀጥታ የሚገናኙ ጥያቄዎችን እንፈትናችሗለን።

🐌 ሰኞ - General Psychology.

🔤 የፈተናው ይዘት - Chapter One Essence of Psychology.

🏃 Number of Questions - 20.

🔥 የ ጥያቄዎቹ ይዘት Case Study ና Conceptual ሲሆኑ ፤ ጥያቄዎች በቀጥታ የሚወጡ ሳይሆኑ ጥልቅ መረዳትን የሚጠይቁ ሲሆኑ ከሞጁሉ ከፍ ባለ መንገድ በጥልቀት ያቀረብንላችሁን ቲቶርያሎች መረዳታችሁን የሚገመግሙ ናቸው።

🚨 ከ 20 ው ጥያቄ 15 እና ከዛ በላይ የሚያመጣ ተማሪ በዬትኛውም ግቢ የሚወጡ የሳይኮሎጂ ቻፕተር 1 ጥያቄዎችን መስራት ይችላል።

😱 ማን ሰቃይ እንደሆነ የምንመለከትበት competitions ነው ፤ ጀግና የሆነ ተማሪያችን ልዩ ተሸላሚ ይሆናል።

⏰ ፈተናው የሚጀምረው ሰኞ ከምሽቱ 1:30 ሲሆን እስከ 4 ሰአት ድረስ መፈተን ትችላላችሁ።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10👏2
....ከታሪኬ ላካፍላችሁ❗️
#LifeSharing

ለሴቶች ብቻ (ወንዶች ተቀየሱ ...!)

📚 እህታችን ስለ ፍቅር መምክር አለብህ ብላ የሷን የፍሬሽነት ገጠመኟን አጫውታናለች ተከታተሏት።

★"ልጁን ለመጀመርያ ጊዜ እንዳየሁት ነበር ፍዝዝ ብዬ የቀረሁት ፡ ወድያው ከሱ ሌላ ወንድ ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ ነበር ድንዝዝ ያደረገኝ
ከዛም ምን ዲፕ እንደሚማር  ለማጣራት ሞከርኩ፥ ጓደኞቹንም አስቀድሜ ተዋወኩ  ስለ ልጁ አብዝቼ ስጠይቃቸው አፍቅረሽው ነው ❓አሉኝ ።

📚 ብዙም ሳያንገራግሩ ስልክን ሰጡኝ  የሆነ ቀን library አብሮኝ ተቀምጦ የምሆነውን አሳጣኝ የምገባበት ሁላ ጠፋኝ ልጁ የኔን ነገር ሰምቶ መሰለኝ
ተገናኝተን እንድናወራ እድል ተፈጠረልን ከዛም ተገናኘን ፤ ስለ ራሱ አወራኝ እኔ በሱ ፍቅር እብድ ልል ጫፍ ደርሼ ነበር እሱ ግን ቺክ እንዳለውና ይባስ ብሎ ሊያስተዋውቀኝም እንደሚችል ነግሮ ቅስሜን አንኮተኮተው ።  የዛን ሰሞን እንዴት እንደሆንኩ ማስታወስ ሁሉ አልፈልግም መማር እስኪያቅተኝ ድረስ ክላስ ምናምን መቅጣት ስራዬ ሆነ እና ሁሌም እሱን መፈለግና መኳተን ፤ ብቻ ብዙ ለፋሁ ።

📚 የሆነ ቀን መንገድ ላይ ተጋጨን  ከዛም *M ሰላም  ነሽ  ❓ አለኝ አስከትሎም ለምን እራት አልጋብዝሽም ❓ አለኝ  በዛ ፍጥነት እንደዛ ማለቱ ምንም አልመሰለኝም እንደውም ደስ ነበር ያለኝ coz ፍቅሩ ልቤን ደፍኖት ነበር ። ከዛም በጣም እንደሚያፈቅረኝ ነገረኝ ሁሌም እንገናኝ ምናምን ይለኝ ጀመር፤ ብዙ ጊዜም አብረን ተገናኘንም ።


❌ግን ለመጨረሻ ጊዜ ስለ እሱ ማሰብ ያቆምኩት  እራት ጋብዞ መጠጥ ምናምን አጠጥቶ ሞቅ ሲለኝ ብሎም መስከሬን አውቆ ያን ምሽት እንደልቡ ተጫወተብኝ ። እና ሁሌም ለፍሬሽ ሴት ተማሪዎች መምከር የምፈልገው ማንኛውንም ወንድ እንዳያምኑ ነው፤ አብዛኛው ወንድ ምናልባትም ሁሉም ማለት በሚቻልበት ሁኔታ ሴትን ልጅ የሚፈልጉት ለስሜት እንደሆነ ብቻ እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ
ለየትኛውም የግቢ ወንድ ልባቸውን መስጠት እንደሌለባቸው ፤ ግቢ ውስጥ ፍቅር ምናምን ጭራሽ እንደማያስፈልግ አደራ ማለት እወዳለሁ ።

💬 ከኔ ደባሪ አጋጣሚ ብዙዎቻቹህ እንደምትማሩበት ተስፋ አደርጋለሁ ፤ አመሰግናለሁ"★

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤48👍3
📌መጀመሪያ ግቢ ስንደርስ ማን ጋር ነው ምንገናኘው  ❓


📚 ግቢ በር ላይ ከመኪና ኦር ከታክሲ እንደወረዳቹህ በመጀመሪያ የምታገኙት እንኳን ደህና መጣቹህ የሚል ፈገግ ያለ ፊት ነው ። ( like አስጌ ዴንዴሾ ) እዚህ ጋር መርሳት የሌለባቹህን ፤ ላገጠጠላቹህ በሙሉ ሻንጣ እንዳትሰጡ በተለይ መናሀሪያ የምትወርዱ ከሆነ በጣም ተጠንቀቁ አንገታቸው ላይ or ደረታቸው ላይ ባጅ ያጠለቁ እሱንም የዩንቨርሲቲው ማህተም ያለበት መሆኑን ቼክ አርጉ አንዳንድ ከተሞች ላይ በጣም የተደራጁና ረቀቅ ያሉ ሌቦች ስለሚኖሩ be take care. የትኛውም ግቢ አዲስ ተማሪዎች በሚገቡበት ቀን በር ላይ የተለየ ዝግጅት በማድረግ ጥብቅ ፍተሻ ይደረጋል ።

📚 ማንኛውም ተማሪ የያዘውን ሻንጣ ከፍቶ ሳያስፈትሽ እግሩ ወደ ግቢ አይገባም ። ከፍተሻው በተጨማሪ  ግን ሁሉም ተማሪ የዶርምና ብሎክ ቁጥር ማወቅ አለበት እሱም ከግቢ ውጭ ወይም ግቢ ውስጥ ይለጠፋል አንዳንዶች ግቢዎች ደግሞ ዌብሳይት ላይ አስቀድመው ይለቃሉ። የብሎክና ዶርም ቁጥራችሁን ካወቃቹህ ጓዛችሁንም ካስፈተሻቹህ በኋላ ቀጥታ የምትሄዱት ወደ ዶርም ነው ።(ነባር ተማሪዎች ብሎክ ድረስ ይሸኟቹሃል)
ብሎካቹህ ጋር ስትደርሱ ground ላይ የብሎክ ሃላፊው(ፕሮክተር) ቢሮ በመስኮት በኩል ዶርም ቁጥራችሁን፣ ስም፣ phone number እና ፎቶ በመስጠት ፈርማቹህ የዶርም ቁልፍ ትቀበላላቹህ ።( ቁልፍ የሚሰጠው ቀድሞ ለመጣ አንድ የዶርም አባል ብቻ ነው ከተቀደማቹህ ቁልፍ የተሰጠውን ዶርሜት ስልክ ቁጥር ተቀብላቹህ መደወል ነው ።) ዶርም ስትገቡ የመጀመሪያ ሰው ከሆናቹህ ያሻችሁን አልጋና ሎከር መርጣቹህ የመያዝ ሙሉ መብት አላቹህ ። ደስ ካላችሁም ትራስ ምናምን መቀያየር ችቡድ ሰባራ ከሆነ እሱንም መቀየር... ብቻ በዶርሙ ላይ የተመቻችሁን የግል ንብረት ማሽከርከር ትችላላቹህ coz ማንም በቦታው ላይ የለምና ።
ከተቀደማቹህ ግን ከቀደማቹህ ሰው ጋር ሳትጋፉ ያገኛችሁትን ፤ አደራ ግን እንዳትጨቃጨቁ።


📚 ሌላው ዶርም ስትገቡ አንሶላና ትራስ ጨርቅ ምናምን ሳትጠቀሙ ጋደም ማለት ቢያምራቹህ እንኳ እንዳተኙ coz ፎከታም ትሆኑብኛላቹህ(biology ላይ የተማራችሁትን አትርሱ fungus+virus) የዶርም ጣጣችሁን ከጨረሳችሁ ቀጥታ የምትሄዱት ወደ register ይሆናል (በስራ ሰዓት ብቻ) አመሻሽ ላይ ግቢ ከደረሳቹህ ለምዝገባ ስለማትደርሱ የዶርማችሁን ጣጣ ለመጨረስ ሞክሩ ለምዝገባው አታስቡ በነገታው መመዝገብ ትችላላቹህ ።

   ምዝገባ ቦታ ላይ ያለው process  ❓


📚 በመጀመሪያ ክላሰር ወረቀት ትገዙና የሚሰጣችሁን ፎርም ትሞላላቹህ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ኦሪጂናሉንና ኮፒውን ትጠየቁና ኦሪጂናሉ ይመለስላቹሃል ። ፎቶም ትጠየቃላቹህ
በሌላ መስኮት ደግሞ ID ምናምን ታወጣላቹ ከዛ ትንሽ ትንቀዋለሉና ትጨርሳላቹህ ። Above ሁለት ሺህ ተማሪ ምናምን በአንድ መስኮት ስለሚስተናገድ በጣም መጨናነቅ ይኖራል ቻል ማድረግ ነው ።

📚 ምዝገባ ከጨረሳቹህ መታወቂያ ከተቀበላቹ ዶርም ሂዳቹ ደስ ካላቹህ ተገልብጣቹህ ለጥ ማለት ትችላላቹህ ። አንዳንድ ግቢዎች ላይ መጨናነቁ በከፊል ሊቀንስ ይችላል ። አንዳንዶች ጋር ደግሞ ባስ ይላል ። ተማሪዎችም በተመሳሳይ መልኩ ይሆናል register ላይ ግን እንደፍሬሽ አይንከራተቱም ID ማሳደስ ብቻ ሌላው ነገር በሙሉ ተመሳሳይ ነው ።


ይሄ ካወቃችሁ ኮ አቤት በቃ ፍሬሽ ሳትሆኑ ግቢ ገባችሁ ማለት ነው ።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10👍7🔥2
የጥሪ ማስታወቂያ

✅ HaramayaUniversity

➡️ በ2019 ዓ.ም በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ቅድመ ምረቃ (Freshman) ተማሪዎች በሙሉ

✅ መግቢያ ቀን ከ ጥቅምት 05-08/2029 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች ፎቶውን ይመልከቱ።

@Aplustutorialofficial
❤5
#HawassaUniversity

በ2019 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 03-04/2019 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ማሳሰቢያ፤
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
1. የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
2. ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
3. አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
4. አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ፣ እና የስፖርት ትጥቅ

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡

@Aplustutorialofficial
❤7
🏆 Today's Competition - General Psychology Chapter One.

✅ There are 21 questions in total, including True/False and multiple-choice questions.
✅ The questions are directly related to your University exam.
✅ Since they focus on both concepts and case-based scenarios, take your time, stay focused, and think carefully before answering each question.
✅ You will have 1 minute for each question.

⚠️ Important: Getting answers from AI will result in complete removal from the tutorial.

✅Instead, enjoy the questions and use them as an opportunity to test your own knowledge and prepare yourself for the exam.

✅You can take the test anytime between 1:30 PM and 4:00 PM.

🏆 There will also be prizes for students who achieve the highest scores!

🔔 ከ ማታ 1:30 እስከ 4:00 ባለው ጊዜ ውስጥ መፈተን ትችላላችሁ ፤ ፈተናውን ለማግኘት Competion(🏆) ውስጥ በመግባት መፈተን ትችላላችሁ።

ያልተመዘገባችሁ የፍሬሽማን ተማሪዎች አፑ
ን ከ playstore ላይ በማውረድ ተመዝግባችሁ ፤ ከፍሬሽማን ጓደኞቻችሁ ጋ መወዳደር ዝግጅታችሀን መገምገም ትችላላችሁ📥

📱 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.aplus.depthabdre.tutorial

🎯 Good luck A+ Tutorial Families and do your best!

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤8
🔥 The competition has started.

ፈተናውን ለማግኘት competition ውስጥ ወይም የዋንጫ ምልክት 🏆 ያለበት ውስጥ ይግቡ። ረጋ ብላችሁ አስተውላችሁ ለመስራት ሞክሩ ፤ ጥያቄዎቹ ሸዋጅ ናቸው እንዲሁም የ case ጥያቄዎች ስላሉት ተረጋግታችሁ ለመስራት ሞክሩ።

⏰ ውደድሩ እስከ ማታ 4 ሰአት ይቆያል ፤ ከ 4 ሰአት በሗላ የጥያቄዎቹን መልስ እና explanation ማግኘት ትችላላችሁ።

@Aplustutorialofficial
❤7👏3
😲 ተደፈነ

🔥 ጨርቃቸውን ጥለው ያበዱ ጥያቄዎችን አዘጋጀንላችሁ ፤ ደፈናችሁት ትችላላችሁ👏።

👏 ዝግጅታችሁን በዚሁ ቀጥሉ ፤ ገና ግቢ ሳትገቡ እነዚህን ጥያቄዎች እንደዚህ ከሰራችሁ አትጠራጠሩ A+ የእናንተ ነው👌።

👉 አሁን የ ጥቄዎቹን መልስ ከነ ማብራሪያው psychology ኮርስ ውስጥ በመግባት Contests ውስጥ የሚለው ውስጥ በመግባት ማግኘት ትችላላችሁ።

🔥 ሮብ የ ሎጂክ Chapter 1 ፈተና ይኖራችሗል ፤ ስለዚህ ነገ Chapter 1 ቲቶርያልን ቅጥቅጥ አድርጋችሁ ተከታተሉ ፤ ከ 2013-2018 ድረስ chapter 1 ንን የተመለከቱ 110 ጥያቄዎችን ከነ ማብራሪያው አቅርበንላችሗል እነሱን በደንብ ስሩ ፤ Chapter 1ንን የተመለከቱ ወደ 100 ጥያቄዎች quiz አለ እሱንም ስሩ ፤ ከዛ ሮብ ማታ ትፈተናላችሁ።

🙌 ዘንድሮ እስከጥግ ድረስ አብረናችሁ እንጓዛለን።

@Aplustutorialofficial
👏14❤6
📣ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለፍሬሽማን ተማሪዎች ጥቅምት 4-5 የመግቢያ ጊዜ መሆኑን አሳውቋል።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤9
Forwarded from ⁵:⁸
Hello A+ team,
I hope you are all doing well. I am one of your students from Dilla University last year. I truly appreciate all the effort, dedication, and teaching skills you put into your work. Even though I feel I could have achieved even more because of your excellent teaching, I was very happy with my results in both semesters. Thank you so much😊
I also really enjoyed the way you teach all the different subjects. Your teaching style makes the lessons very interesting and easy to follow.
Thank you
❤12🔥3
🎉Natinael - One of the winners of yesterday's Tough Competition.

📣Listen to his experience of the A+ Tutoring Service.

📱@Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤8👏1
🏆 Today's Competition.

✅ Logic and Critical Thinking.

❤️ Content : Chapter One - Introduction to Philosophy.⤵️

✅ ጥያቄዎቹ በቀጥታ ከ ዩኒቨርሲቲዎች mid exam ጋ የሚገናኙ ናቸው ፤ የዛሬ ፈተና more conceptual ናቸው ፤ አንዳንዶቹ የሞጁላችሁን ደረቅ ንባብ መሰረት ያደረጉ ናቸው ፥ የ case ጥያቄ ብዙ የለበትም።

🥇 Chapter 1 ላይ የተለቀቀውን ቲቶርያል በደንብ ተከታተሉ።
🥈 ከ 2013-2018 ድረስ የተለያዩ ግቢዎች ላይ የወጡ Chapter 1 ን ብቻ የተመለከቱ 110 ጥያቄዎች ከነ ማብራሪያቸው አለ ፤ እሱን ተመልከቱ።
🥉 Chapter 1 ንን የተመለከቱ quizes ወደ 100 ጥያቄዎች አሉ እነሱን ስሩ።

ውድድሩ ማታ 1:30 ይጀምራል ፤ ከ 1:30 እስከ 4 ሰአት ባለው ጊዜ ውስጥ መወዳደር ትችላላችሁ።

🎉 ከ 1 እስከ 3 የሚወጡ ጀግና ተማሪዎቻችን ይሸለማሉ።

💡የ A+ Tutorial ተማሪዎች የ mid exam አብዛሀኞቹ ይዘቶቹን ግቢ ሳትገቡ ገና ቤታችሁ ሁናችሁ ጨርሳችሁ ነው የምትሔዱት።

🔜 በተጨማሪም በዚህ 4 ቀን ውስጥ አፑ ላይ የሚጨመሩ አዳዲስ ነገሮች ስላሉ ፤ stay active with us.

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤8👍7
🎯 የጥሪ ማስታወቂያ

📚 በ2019 ዓ.ም ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት  09 -10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ሙሉ መርጃውን ከላይ በምስሉ ተመልከቱ

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤9
💭 የካንፓስ የመጀመርያ አመት ቆይታ ......በትንሹ ❓

📚 ፍሬሽማን መሆን እንደእናንተ ስብዕና ይወሰናል ። የተለያየ ሰው የተለያየ experience ነው ያለው ። ግን ብዙዎች ጋር የሚኖረውን የፍሬሾች የጋራ ኑሮ ቆንፅለን ለማየት እንጥራለን ...!


💡 ናፍቆት .....!

📚 አንዳንድ ከቤታቸው ሱቅ ለመላክ ካልሆነ ወጥተው የማያቁ ልጆች ድንገት ከቤተሰብ ሲርቁ ምናምን አይችሉም ይነፋረቃሉ ...ከሰው ጋር የማይግባቡ ዝጋታም ልጆች ስላሉ እነሱም ... ለብቸኝነት ሲጋለጡ ሊከብዳቸው ይችላል ። አንድ ነገር እወቁ ከምትወዷቸው ሰዎች መለየት ይሄ የመጀመርያቹ ሊሆን ይችላል ግን ብርቅ አይደለም ...አቅፎ የሚያስተዛዝን ፤ ህመምን የሚጋራ ደስታን የሚካፈል ጓደኛ ቤተሰብ ወዳጅ መለየት በጣም ከባድ ነገር ነው ። ግን ቻሉት በህይወታችሁ ነፍ ግዜ ከምትወዷቸው የህይወት አጋጣሚ ይለያቹሃል ። ካንፓስም የምታገኟቸው ልጆች ከአመታት ውብ የጓደኝነት ቆይታ በኃላ ትለያያላችሁ ። ናፍቆት ያለ ነው ግን መቻል ነው ። በካንፓስ ጥሩ ጓደኛ ያዙ ...እስክትለምዱት ነው ። ከዛ ይለቃቹሃል ።


💡 ምግብ ....!

📚 እንደ እናትህ ውይ ልጄ ተነስ ቁርስ ብላ ና ትተኛለህ  አቡኪያዬ ...ምናምን የለም በጠዋት ተነስተህ ሰልፍ ካልወጣህ ሲሞረሙር ይውላል ካፌ ሊያልቅም ይችላል ....ሻይ በዳቦ ለመብላት ይሄ ያክል ሰልፍ ልትልም ትችላለህ ግን በመክሰስ ሰዓት 12 ስለሆነ ራት የሚገረሰው ችከላ ካደርክ ይሞረሙራል...ዳቦ ራሱ ስንት ጣዕሙ ..ከረሃብ ይሻላል ። ሩዝ ፤ ፍርፍር ...ስላለ አትቸጋገር ....ግን ጥሩ ነገር መብላት የለመደ ሰው....ወይኔ ግቢው ጥሩ ባልቴት  የሌለው ይመስል ..ጥቅል ጎመን ብለው ቀጭን ሾርባ ጎመን ጣል ጣል ያለበት ሊያቀርቡ ይችላሉ ...ታዲያ አሪፍ ነገር የለመደ አይችልም 2000 ብር አከባቢ ይገጨውና ውጪ ይበላል .... ምግቡ እንደ ካንፓሱ ነው  በተለይ በቅርቡ የተከፈቱ አርሲ ፤ ቦንጋ ምናምን ምንም አይልም ባህርዳርም አሪፍ ነው ። ሃሮማያማ በሳምንት አራቴ ነው ስጋ የምትግጡት ...ብቻ ብዙ ልጆች የጣፈጠ ነገር ለምደው እነደ ነገሩ የሚሰራው ምግብ አይጥማቸውም ።

💡 ጓደኛ መረጣ ...!

"ጓደኛ መረጣ ላይ መጠንቀቅ አለባችሁ ። በጣም መጥፎ ሰዎችም ጥሩ ልጆችም ይኖራሉ ። ከሱሰኛ ፤ ጨባሽ ፤ ዘረኛ ..ራቁ..በቢሊዮን ማይል ራቁ ...ከእናንተ ጋር የሚሄድ ሰው ፈልጋችሁ ከዶርም ውስጥ አንድ የልብ ጓደኛ በቂ ነው ። ታዲያ ምንም መጥፍ ባህሪይ ቢኖርባቸው ከዶርም ልጅ አትጣሉ ...ትቸገራላችሁ ተንከባክባችሁ ....ተከባብራችሁ በፍቅር አርጉት ...ጓደኛ ምርጫችሁን ተጠንቀቁ ዝም ብሎ ሲያነብ የሚውል የሚተሽንም ሰው አትጠጉ በቃ አራዳ ሆናችሁ ማንበብ ሲኖርበት የሚያነብ ፈታ ግድ ሲል የሚፍታታ ነገሮች የሚገቡ ምርጥዬ ሰው ፈልጉ ።

💡 ሱስ....

📚 በዙ ሰዎች ካንፓስ በጓደኛ ምክንያት ያልሆነ ነገር ውስጥ ይገባሉ ይሄ መሆን የለበትም ...ምንም ቢሆን ሱስ አለም እንዳትገቡ ...ያለባችሁ ችግር ይበቃል ... አንዳንዴ ግዜ ሊተርፋችሁ የምትሰሩት ታጡም ይሆናል ...ሱስ ከምትገቡ አንዷን/ዱን ጠብሳቹሁ ተጃጃሉ እሱ ይሻላል ... ጭራሽ ሱሰ ውስጥ ራሳችሁን እንዳታገኙ በርቱ ....!

💡 መወዛገብ ......!

📚 ከጠበቃችሁ በጣም የተለየ ነገር ሊገጥማችሁ ይችላል ....ያኔ ውዝግብግብ የተለመደ ነው ።ተሳስታችሁ የሰው ዶርም ከች ትሉም ይሆናል ።ብዙ ግዜ ልጆች እስኪለምዱ ድረስ እንዳይጠፋባቸው አንዴ ባዮት መንገድ ብቻ ነው የሚጓዙት ....ሌላ አጭር መንገድ ቢኖርም አይሄዱም በረጅመ ይሄዳሉ የፍሬሽ ነገር የተለመደ ነው ። በቃ በየስርቻው ሲዋሰቡ ፤ ትምህርት ብሎ መጥቶ አባቱን በሬ አሽጦ ፤ እናቱን ፆም አሳድሮ እሱ ጫት ቤት ፤ ቅምቀማ ስታዮት (2 or 3 ተማሪ እንዳይመስሏቹሁ ወደ ግማሽ የሚጠጋው ተማሪ  .)...በቃ ላይብረሪው ውስጥ 3 ሰው ብቻ ስታዮ ....ትደነግጣላችሁ ወይኔ ካንፓስ ልትሉም ትችላላችሁ ...!ለምግብ ሰልፍ ስታዮ ..ዋይፋይ ሰዎች ለሊት ሙሉ ሲጠቀሙ ስታዮ....በቃ ትወዛገባላችሁ ...ትምህርት ቤት ያላችሁ መሆኑ ትዝ የሚላችሁ ...የፈተና ሰሞን ነው ላይብረሪ 3 የነበረው ሰው መቀመጫ አጥቶ አንድ ወንበር  ለሁለት ተቀምጦ ስታዮ ...ዶርም አዳር ሲቸከል ስታዮ ይገባቹሃል ።

💡 የአስተማመር አይነት ....!.

📚 እንደ Highschol 40 ደቂቃ ሳይሆን 3 ሰዓት ሙሉ አንድ ሳብጀክት ትዳረቃላችሁ .....እሱም ደህና መመህር ካጋጠማችሁ ነው የሚገባችሁ ።  በቃሉ እየተጀነነ ሲያወራ የሚውል.... ኖት የሚቸከችክ  ...ደብተር ሁላ የሚያርም አለ ። የለመዳችሁት አይነት ...የመማር ማስተማር ሂደት ሲቀየር አትደናገጡ እንደ አየሩ መሆን ነው ። እስከትለምዱት ነው ።

💡 ወሲብ.......!

📚 ወሲብ ከባድ ነገር ነው ። እንኳን እንዲሁ ተለቃችሁ ወትሮም ....የporno ቪዲዮ ይታየዋል ለጉድ በቃ ። ሱሰኞች ካጋጠማችሁማ ዶርም ላይ ...በቃ ላይብረሪ ሁላ ወሲብ ይፈፀማል ......በጣም አስጠሊ ነገር ነው ።  ይሄ አይወራ እዛው እዮት .....

💡 ሙድ መያዝ .....❗️

📚 ፍሬሾች ገና ከመግባታችሁ ...የሲኒየሪዎች ነቆራ አይጣል በቃ ምንም ስለማታውቁ ...የማይሆ ነገር ሊነግራቹሁ ይችላል የመመዝገቢ ቦታ ጠይቃችሁ ሽንት ቤት ሊሊሉካችሁ ይችላሉ ። ግን አይደብራችሁ እናንተም በተራቹሁ አየር ስለምትይዙ ....ፈታ በሉበት እስክትለምዱ አየር አታብዙ አትኳትኑ ልጎብኝ እያላችሁ አታካሉ ወሬ ሰብስቡ መጀመርያ ። የመጀመርያ ምግብ ካፌ ማሰታወሻ ፎቶ አንሱት ።

📚 ሁሉንም አውርተን አንጨርሰውም ....በቃ የቀረ ካለ ግቢ ታዮታላችሁ ፥ ብዙ አትጨናነቁ አይዞን።

@Aplustutorialofficial
❤25🙏3