A+ Tutorial Class Official
19.2K subscribers
401 photos
15 videos
168 files
58 links
📚 A+ Tutorial Class ለ መጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠቃሚ የሆነ አጋዥ ቲቶርያል በመስጠት እንዲሁም የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለግቢ ፈተናዎቻቼው የሚያግዟቸውን pdfs, ያለፉ አመታት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች Mid and Final Exams የሚያቀርብ ቻናል ነው።

እኛን ለማግኘት : በ @Aplus_support_Admin በኩል ማንኛውንም ጥያቄዎትን ሊያደርሱን ይችላሉ።
Download Telegram
🔔 የታላቅ ምክር ለፍሬዎች....⬇️

✔️ ግቢ በየትኛውም ሰዓት ብትደርሱ ስለሚያስተናግዷቹህ በጭራሽ ቤርጎ እንዳትከራዩ ፤ በተለይ ከሩቅ ቦታ የምትመጡ ተማሪዎች ግቢው ስለሚረ'ዳቹህ ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳትዳረጉ ፤ ስርቆትም ሊኖር ስለሚችል ለብቻቹህ ከሆናቹህ ቤርጎ ባትከራዩ ፒስ ነው(በተለይ ሴቶች)

✔️ ከብዙ ወከባዎች ለመትረፍ ከፈለጋቹህ አንድ ቀን ቀደም ብላቹህ ግቢ ግቡ ማለት ግቢው በ29 ከጠራ እናንተ በ28 ግቡ ያስገቧቹሃል ፤ ቀደም ብሎ የሚመጣን ተማሪ አናስተናግድም የሚሉት ሳክስ ነው ፤ቀደም ብላቹህ ከመሄዳቹህ በፊት ግን ነባር ተማሪዎችን ለማንኛውም አናግሩ ።
 

✔️ ሻንጣ እንዳይቀያየርባቹህ የናንተን ሻንጣ የምትለዩበት መለያ ምልክት ይኑራቹህ ፤ ብዙ ሻንጣ ሊኖር ስለሚችል በስህተት እንዳይቀያየር (ለክፉም ለደጉ ግን ስልክ ቁጥር የሆነ ቦታ ላይ አስፍሩበት በወረቀትም ቢሆን....!)

✅ ግቢ በር ላይ ጥብቅ ፍተሻ ስለሚኖር ባለፈው የጠቀስኩላችሁን ነገሮች ይዛቹህ እንዳትመጡ ፤በስህተት ካመጣቹህ በር ላይ ይቀሟቹሃል ።
የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ቅርብ ቦታ አስቀምጡ ማለት ሻንጣ ውስጥ አታርጉት ፤ በር ላይ ቅድሚያ ስለምትጠየቁ ሁሉንም ዶክመንቶች በእጃቹህ ለመያዝ ሞክሩ ።

✅ ወንዶች ፀጉራችሁን ከልክ በላይ አታሳድጉ ቀለምም አትቀቡ ፤ የመጀመሪያ ቀናቶች ላይ ፀጉር ምናምን ሊባል ስለሚችል በተቻላቹህ ያህል እይታ ውስጥ የሚያስገባ የፀጉር style አይኑራቹህ(ምቺ ያስመታቹሃል....!)

✔️ ሴቶች አለባበስ ላይ ወጥ አትርገጡ ፤
አንዳንዶቻቹህ ለትምሮ የምትሄዱ እስከማትመስሉ ድረስ ትራቆታላቹህ ፥ የምር አይነፋም ይብራብሽ እርድናም አይደለም ( ለነገሩ ግቢ በር ላይም አይፈቱሽም ጥበቃዎች...!)

✔️ ግቢ ስትገቡ ፀባያቹህ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን ትዕግስተኛ መሆን አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ከማንም ጋር ብትጣሉ ካለምንም ማስተዛዘኛ የመባረር እድላቹህ ይሰፋል ።

✅ የጥላቻና የዘረኝነት ንግግሮችንም ይሁን አመለካከቶችን በፈጠራቹህ ጌታ ይሁንባቹህ እንዳትጠቀሙ ፤ የማንንም ስብዕና የሚነካ ንግግር በስህተት እንኳ እንዳትናገሩ ።

ግቢ ውስጥ ማንንም እንዳትንቁ ፤ እኔንም ጨምሮ ፤ ከየትኛውም ከተማ ልትመጡ ትችላላቹህ ግቢ ውስጥ እስካላቹህ ድረስ ግን እኩል ናቹህ ማለትም አትበላለጡም።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤20👍8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🚨በሶ ለውዝ ቆሎ ምናምን መርሳት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅት አድርጉ🥵።

🫵 ይህን ተላልፎ በሚገኝ ተማሪ አስተማሪ ና የማያዳግም እርምጃ እንደምንወስድ ከ ወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን" - የ ግቢ ካፌ

📱@Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😢12❤8👍4😱1
🎉 ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ እና መልስ ውደድር🙌

✅ ከ 125 በፊት ድሮ ድሮ ሳይኮሎጂ ራሱን የቻለ የሳይንስ ዘርፍ አልነበረም ፥ ነገር ግን በ ጀርመን ሀገር ሌብዚግ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት ጀርመናዊው Wilhelm Wundt(ዊልሔም ውንት) የሳይኮሎጂ ላቦራቶሪ አቋቋመ ፤ በዚህም ምክንያት ሳይኮሎጂ ራሱን ችሎ የሳይንስ ዘርፍ ሁኖ የራሱን የምርምር ስልቶች በመጠቀም ስለ ሰው ልጅ ባህሪ ና አዕምሮው ውስጥ ስለሚካሔድ የአስተሳሰብ ሒደት(mental process) አዳዲስ ጥናቶችን እና እድገቶችን አሳዬ።

👉 ጀርመናዊ የዘመናዊ ሳይኮሎጂ አባት ተብሎ የሚጠራው Wilhelm Wundt በ ሌብዚግ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ባለው የ ሳይኮሎጂ ቤተ-ሙከራ ውስጥ introspection የተባለ experiment በ ሰለጠኑ(train) ሰዎች ላይ በመስራት የሰዎችን የአዕምሮ ክፍሎች ለማወቅ ጥናት አድርጓል።

👉 የ Wilhelm Wundt ደቀ መዝሙር የነበረው ፤ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት ቲቸነር የ ውንት የ introspection ሀሳብን በማስፋት Structuralism Psychology ን መሰረተ። በዚህም ምክንያት የ Structuralism Psychology መስራቾች ውንት እና ቲቸነር ናቸው።

❓ ጥያቄ

☕️ Assume ውንት እና ቲቸነር ፤ ካፌ ውስጥ ቡና እየጠጡ አገኛችሗቸው። ውንት እና ቲቸነር ን ምን እያደረጋችሁ ነው ብላችሁ ብትጠይቋቸው ምን ብለው ይመልሱላችሗል❓

📤Hint : ቡና እየጠጣን ነው ብለው አይመልሱላችሁም።

✅ ቲቶርያሉ ላይ ገብታችሁ እየተማራችሁ ያላችሁ ልጆች መመለስ አትችሉም ፤ ሌሎቻችሁ መመለስ ትችላላችሁ።

🎁 መልሱን ጥሩ አድርጎ ያብራራ ተማሪ የ 150 ብር ካርድ ተሸላሚ ይሆናል።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10🔥4👍1
🚨 Important Updates Available.

🔥 የ A+ Tutorial የፍሬሽማን Application መማሪያ አፕ ላይ ተመዝግባችሁ እየተማራችሁ ያላችሁ ተማሪዎች Playstore ላይ በመግባት update አድርጉት⤵️

📱https://play.google.com/store/apps/details?id=com.aplus.depthabdre.tutorial

👏 ከ 2013-2018 ዓ.ም ድረስ የተለያዩ ግቢዎች ላይ የወጡ የ mid exam ጥያቄዎችን በቻፕተር በመከፋፈል ፥ በአንድ ቻፕተር ከ 100 በላይ ጥያቄዎች ለመረዳት ግልፅ በሆነ መንገድ ተብራርተው አፑ ላይ ተጭነዋል። በጥያቄዎቹ ማብራሪያዎች ላይ እያንዳንዱ የሞጅሉ ቻፕተር ገፅ በገፅ ተዳሰዋል።

🎉 ከ Worked Solutions በተጨማሪ በ አንድ lesson ብቻ ከ 30 በላይ ጥያቄዎች በ quiz መልክ ታኛላችሁ ፥ በአጠቃላይ በ አንድ ቻፕተር ከ 100 በላይ የ quiz ጥያቄዎች የተካተቱ ሲሆን ፤ በአንድ ቻፕተር
worked Solution + Quiz ከ 200 በላይ ጥያቄዎችን ታገኛላችሁ።

🥺 በየትኛውም ግቢ የምትመደቡ ተማሪዎች እነዚህን ጥያቄዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ስለምትፈተኗቸው ትኩረት ሰጥታችሁ ስሯቸው።

🔜 በቅርቡ በ A+ Tutorial የተዘጋጁ ከግቢ ፈተናዎቻችሁ ጋ በቀጥታ የሚገናኙ ፈተናዎችን ስለምንፈተናችሁ ያቀረብንላችሁን ቲቷርያል እና ፈተናዎች በደንብ ስሯቸው።

💡 ቅርፃወቸውን እየቀያዬሩ በዬአመቱ የሚወጡ ጥያቄዎች ከተለያዩ ግቢዎች በጥንቃቄ ተመርጠው ከነ ማብራያቸው የተዘጋጁ ሲሆን ፤ ለጥያቄዎቹ የቀረቡት ማብራሪያዎች ግቢ ላይ ፈተናን በምን መልክ መስራት እንዳለባችሁ የፈተና አሰራርን technique ን የሚያሳዩ ፥ የፈተና አሰራር system ን እግረ መንገዳችሁን እንዲታውቁ የሚያደርጉ ናቸው።

▶️በተጨማሪም የፍሬሽማን ሞጁሎችን በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችሉ ፥ ከ real world ጋ የሚገናኙ ፤ በቀጥታ ከ ህይወት ጋ የሚገናኙ ገላጭ ቲቶርያሎችን ስለሆነ ያዘጋጀንላችሁ የፍሬሽማን ኮርሶችን ለመረዳት ጊዜ ቆጣቢ እና ብዙ ነገር አቅላይ ናቸው ፤ ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች A+ Tutorial ላይ ለመማር ከ playstore ላይ አፑን በመመዝገብ ቲቶርያሎቹን ማግኘት ትችላላችሁ።

💬 ስለ ቲቶርያሉ መረጃ ለመጠዬቅ : @Aplus_support_Admin ን ይጠቀሙ።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤12🔥2
🎯 የጥሪ ማስታወቂያ

ጅማ ዪኒቨርሲቲ በ2019 አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎቹ ጥቅምት 4 እና 5 ጥሪ አድርጓል።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10😱1
📣 Exam Week.

🎉 በጣም አስፈላጊ በሆኑ topics ላይ ልትፈተኑ ነው።

🏆 ከ ሰኞ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በ A+ Tutorial የዘተጋጁ ፤ ከግቢያችሁ ፈተናዎች ጋ በቀጥታ የሚገናኙ ጥያቄዎችን እንፈትናችሗለን።

🐌 ሰኞ - General Psychology.

🔤 የፈተናው ይዘት - Chapter One Essence of Psychology.

🏃 Number of Questions - 20.

🔥 የ ጥያቄዎቹ ይዘት Case Study ና Conceptual ሲሆኑ ፤ ጥያቄዎች በቀጥታ የሚወጡ ሳይሆኑ ጥልቅ መረዳትን የሚጠይቁ ሲሆኑ ከሞጁሉ ከፍ ባለ መንገድ በጥልቀት ያቀረብንላችሁን ቲቶርያሎች መረዳታችሁን የሚገመግሙ ናቸው።

🚨 ከ 20 ው ጥያቄ 15 እና ከዛ በላይ የሚያመጣ ተማሪ በዬትኛውም ግቢ የሚወጡ የሳይኮሎጂ ቻፕተር 1 ጥያቄዎችን መስራት ይችላል።

😱 ማን ሰቃይ እንደሆነ የምንመለከትበት competitions ነው ፤ ጀግና የሆነ ተማሪያችን ልዩ ተሸላሚ ይሆናል።

⏰ ፈተናው የሚጀምረው ሰኞ ከምሽቱ 1:30 ሲሆን እስከ 4 ሰአት ድረስ መፈተን ትችላላችሁ።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10👏2
....ከታሪኬ ላካፍላችሁ❗️
#LifeSharing

ለሴቶች ብቻ (ወንዶች ተቀየሱ ...!)

📚 እህታችን ስለ ፍቅር መምክር አለብህ ብላ የሷን የፍሬሽነት ገጠመኟን አጫውታናለች ተከታተሏት።

★"ልጁን ለመጀመርያ ጊዜ እንዳየሁት ነበር ፍዝዝ ብዬ የቀረሁት ፡ ወድያው ከሱ ሌላ ወንድ ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ ነበር ድንዝዝ ያደረገኝ
ከዛም ምን ዲፕ እንደሚማር  ለማጣራት ሞከርኩ፥ ጓደኞቹንም አስቀድሜ ተዋወኩ  ሾለ ልጁ አብዝቼ ስጠይቃቸው አፍቅረሽው ነው ❓አሉኝ ።

📚 ብዙም ሳያንገራግሩ ስልክን ሰጡኝ  የሆነ ቀን library አብሮኝ ተቀምጦ የምሆነውን አሳጣኝ የምገባበት ሁላ ጠፋኝ ልጁ የኔን ነገር ሰምቶ መሰለኝ
ተገናኝተን እንድናወራ እድል ተፈጠረልን ከዛም ተገናኘን ፤ ሾለ ልሹ አወራኝ እኔ በሱ ፍቅር እብድ ልል ጫፍ ደርሼ ነበር እሱ ግን ቺክ እንዳለውና ይባስ ብሎ ሊያስተዋውቀኝም እንደሚችል ነግሮ ቅስሜን አንኮተኮተው ።  የዛን ሰሞን እንዴት እንደሆንኩ ማስታወስ ሁሉ አልፈልግም መማር እስኪያቅተኝ ድረስ ክላስ ምናምን መቅጣት ስራዬ ሆነ እና ሁሌም እሱን መፈለግና መኳተን ፤ ብቻ ብዙ ለፋሁ ።

📚 የሆነ ቀን መንገድ ላይ ተጋጨን  ከዛም *M ሰላም  ነሽ  ❓ አለኝ አስከትሎም ለምን እራት አልጋብዝሽም ❓ አለኝ  በዛ ፍጥነት እንደዛ ማለቱ ምንም አልመሰለኝም እንደውም ደስ ነበር ያለኝ coz ፍቅሩ ልቤን ደፍኖት ነበር ። ከዛም በጣም እንደሚያፈቅረኝ ነገረኝ ሁሌም እንገናኝ ምናምን ይለኝ ጀመር፤ ብዙ ጊዜም አብረን ተገናኘንም ።


❌ግን ለመጨረሻ ጊዜ ሾለ እሱ ማሰብ ያቆምኩት  እራት ጋብዞ መጠጥ ምናምን አጠጥቶ ሞቅ ሲለኝ ብሎም መስከሬን አውቆ ያን ምሽት እንደልቡ ተጫወተብኝ ። እና ሁሌም ለፍሬሽ ሴት ተማሪዎች መምከር የምፈልገው ማንኛውንም ወንድ እንዳያምኑ ነው፤ አብዛኛው ወንድ ምናልባትም ሁሉም ማለት በሚቻልበት ሁኔታ ሴትን ልጅ የሚፈልጉት ለስሜት እንደሆነ ብቻ እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ
ለየትኛውም የግቢ ወንድ ልባቸውን መስጠት እንደሌለባቸው ፤ ግቢ ውስጥ ፍቅር ምናምን ጭራሽ እንደማያስፈልግ አደራ ማለት እወዳለሁ ።

💬 ከኔ ደባሪ አጋጣሚ ብዙዎቻቹህ እንደምትማሩበት ተስፋ አደርጋለሁ ፤ አመሰግናለሁ"★

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤48👍3
📌መጀመሪያ ግቢ ስንደርስ ማን ጋር ነው ምንገናኘው  ❓


📚 ግቢ በር ላይ ከመኪና ኦር ከታክሲ እንደወረዳቹህ በመጀመሪያ የምታገኙት እንኳን ደህና መጣቹህ የሚል ፈገግ ያለ ፊት ነው ። ( like አስጌ ዴንዴሾ ) እዚህ ጋር መርሳት የሌለባቹህን ፤ ላገጠጠላቹህ በሙሉ ሻንጣ እንዳትሰጡ በተለይ መናሀሪያ የምትወርዱ ከሆነ በጣም ተጠንቀቁ አንገታቸው ላይ or ደረታቸው ላይ ባጅ ያጠለቁ እሱንም የዩንቨርሲቲው ማህተም ያለበት መሆኑን ቼክ አርጉ አንዳንድ ከተሞች ላይ በጣም የተደራጁና ረቀቅ ያሉ ሌቦች ስለሚኖሩ be take care. የትኛውም ግቢ አዲስ ተማሪዎች በሚገቡበት ቀን በር ላይ የተለየ ዝግጅት በማድረግ ጥብቅ ፍተሻ ይደረጋል ።

📚 ማንኛውም ተማሪ የያዘውን ሻንጣ ከፍቶ ሳያስፈትሽ እግሩ ወደ ግቢ አይገባም ። ከፍተሻው በተጨማሪ  ግን ሁሉም ተማሪ የዶርምና ብሎክ ቁጥር ማወቅ አለበት እሱም ከግቢ ውጭ ወይም ግቢ ውስጥ ይለጠፋል አንዳንዶች ግቢዎች ደግሞ ዌብሳይት ላይ አስቀድመው ይለቃሉ። የብሎክና ዶርም ቁጥራችሁን ካወቃቹህ ጓዛችሁንም ካስፈተሻቹህ በኋላ ቀጥታ የምትሄዱት ወደ ዶርም ነው ።(ነባር ተማሪዎች ብሎክ ድረስ ይሸኟቹሃል)
ብሎካቹህ ጋር ስትደርሱ ground ላይ የብሎክ ሃላፊው(ፕሮክተር) ቢሮ በመስኮት በኩል ዶርም ቁጥራችሁን፣ ስም፣ phone number እና ፎቶ በመስጠት ፈርማቹህ የዶርም ቁልፍ ትቀበላላቹህ ።( ቁልፍ የሚሰጠው ቀድሞ ለመጣ አንድ የዶርም አባል ብቻ ነው ከተቀደማቹህ ቁልፍ የተሰጠውን ዶርሜት ስልክ ቁጥር ተቀብላቹህ መደወል ነው ።) ዶርም ስትገቡ የመጀመሪያ ሰው ከሆናቹህ ያሻችሁን አልጋና ሎከር መርጣቹህ የመያዝ ሙሉ መብት አላቹህ ። ደስ ካላችሁም ትራስ ምናምን መቀያየር ችቡድ ሰባራ ከሆነ እሱንም መቀየር... ብቻ በዶርሙ ላይ የተመቻችሁን የግል ንብረት ማሽከርከር ትችላላቹህ coz ማንም በቦታው ላይ የለምና ።
ከተቀደማቹህ ግን ከቀደማቹህ ሰው ጋር ሳትጋፉ ያገኛችሁትን ፤ አደራ ግን እንዳትጨቃጨቁ።


📚 ሌላው ዶርም ስትገቡ አንሶላና ትራስ ጨርቅ ምናምን ሳትጠቀሙ ጋደም ማለት ቢያምራቹህ እንኳ እንዳተኙ coz ፎከታም ትሆኑብኛላቹህ(biology ላይ የተማራችሁትን አትርሱ fungus+virus) የዶርም ጣጣችሁን ከጨረሳችሁ ቀጥታ የምትሄዱት ወደ register ይሆናል (በስራ ሰዓት ብቻ) አመሻሽ ላይ ግቢ ከደረሳቹህ ለምዝገባ ስለማትደርሱ የዶርማችሁን ጣጣ ለመጨረስ ሞክሩ ለምዝገባው አታስቡ በነገታው መመዝገብ ትችላላቹህ ።

   ምዝገባ ቦታ ላይ ያለው process  ❓


📚 በመጀመሪያ ክላሰር ወረቀት ትገዙና የሚሰጣችሁን ፎርም ትሞላላቹህ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ኦሪጂናሉንና ኮፒውን ትጠየቁና ኦሪጂናሉ ይመለስላቹሃል ። ፎቶም ትጠየቃላቹህ
በሌላ መስኮት ደግሞ ID ምናምን ታወጣላቹ ከዛ ትንሽ ትንቀዋለሉና ትጨርሳላቹህ ። Above ሁለት ሺህ ተማሪ ምናምን በአንድ መስኮት ስለሚስተናገድ በጣም መጨናነቅ ይኖራል ቻል ማድረግ ነው ።

📚 ምዝገባ ከጨረሳቹህ መታወቂያ ከተቀበላቹ ዶርም ሂዳቹ ደስ ካላቹህ ተገልብጣቹህ ለጥ ማለት ትችላላቹህ ። አንዳንድ ግቢዎች ላይ መጨናነቁ በከፊል ሊቀንስ ይችላል ። አንዳንዶች ጋር ደግሞ ባስ ይላል ። ተማሪዎችም በተመሳሳይ መልኩ ይሆናል register ላይ ግን እንደፍሬሽ አይንከራተቱም ID ማሳደስ ብቻ ሌላው ነገር በሙሉ ተመሳሳይ ነው ።


ይሄ ካወቃችሁ ኮ አቤት በቃ ፍሬሽ ሳትሆኑ ግቢ ገባችሁ ማለት ነው ።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10👍7🔥2
የጥሪ ማስታወቂያ

✅ HaramayaUniversity

➡️ በ2019 ዓ.ም በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ቅድመ ምረቃ (Freshman) ተማሪዎች በሙሉ

✅ መግቢያ ቀን ከ ጥቅምት 05-08/2029 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች ፎቶውን ይመልከቱ።

@Aplustutorialofficial
❤5
#HawassaUniversity

በ2019 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 03-04/2019 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ማሳሰቢያ፤
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
1. የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
2. ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
3. አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
4. አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ፣ እና የስፖርት ትጥቅ

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡

@Aplustutorialofficial
❤7
🏆 Today's Competition - General Psychology Chapter One.

✅ There are 21 questions in total, including True/False and multiple-choice questions.
✅ The questions are directly related to your University exam.
✅ Since they focus on both concepts and case-based scenarios, take your time, stay focused, and think carefully before answering each question.
✅ You will have 1 minute for each question.

⚠️ Important: Getting answers from AI will result in complete removal from the tutorial.

✅Instead, enjoy the questions and use them as an opportunity to test your own knowledge and prepare yourself for the exam.

✅You can take the test anytime between 1:30 PM and 4:00 PM.

🏆 There will also be prizes for students who achieve the highest scores!

🔔 ከ ማታ 1:30 እስከ 4:00 ባለው ጊዜ ውስጥ መፈተን ትችላላችሁ ፤ ፈተናውን ለማግኘት Competion(🏆) ውስጥ በመግባት መፈተን ትችላላችሁ።

ያልተመዘገባችሁ የፍሬሽማን ተማሪዎች አፑ
ን ከ playstore ላይ በማውረድ ተመዝግባችሁ ፤ ከፍሬሽማን ጓደኞቻችሁ ጋ መወዳደር ዝግጅታችሀን መገምገም ትችላላችሁ📥

📱 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.aplus.depthabdre.tutorial

🎯 Good luck A+ Tutorial Families and do your best!

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤8
🔥 The competition has started.

ፈተናውን ለማግኘት competition ውስጥ ወይም የዋንጫ ምልክት 🏆 ያለበት ውስጥ ይግቡ። ረጋ ብላችሁ አስተውላችሁ ለመስራት ሞክሩ ፤ ጥያቄዎቹ ሸዋጅ ናቸው እንዲሁም የ case ጥያቄዎች ስላሉት ተረጋግታችሁ ለመስራት ሞክሩ።

⏰ ውደድሩ እስከ ማታ 4 ሰአት ይቆያል ፤ ከ 4 ሰአት በሗላ የጥያቄዎቹን መልስ እና explanation ማግኘት ትችላላችሁ።

@Aplustutorialofficial
❤7👏3
😲 ተደፈነ

🔥 ጨርቃቸውን ጥለው ያበዱ ጥያቄዎችን አዘጋጀንላችሁ ፤ ደፈናችሁት ትችላላችሁ👏።

👏 ዝግጅታችሁን በዚሁ ቀጥሉ ፤ ገና ግቢ ሳትገቡ እነዚህን ጥያቄዎች እንደዚህ ከሰራችሁ አትጠራጠሩ A+ የእናንተ ነው👌።

👉 አሁን የ ጥቄዎቹን መልስ ከነ ማብራሪያው psychology ኮርስ ውስጥ በመግባት Contests ውስጥ የሚለው ውስጥ በመግባት ማግኘት ትችላላችሁ።

🔥 ሮብ የ ሎጂክ Chapter 1 ፈተና ይኖራችሗል ፤ ስለዚህ ነገ Chapter 1 ቲቶርያልን ቅጥቅጥ አድርጋችሁ ተከታተሉ ፤ ከ 2013-2018 ድረስ chapter 1 ንን የተመለከቱ 110 ጥያቄዎችን ከነ ማብራሪያው አቅርበንላችሗል እነሱን በደንብ ስሩ ፤ Chapter 1ንን የተመለከቱ ወደ 100 ጥያቄዎች quiz አለ እሱንም ስሩ ፤ ከዛ ሮብ ማታ ትፈተናላችሁ።

🙌 ዘንድሮ እስከጥግ ድረስ አብረናችሁ እንጓዛለን።

@Aplustutorialofficial
👏14❤6