A+ Tutorial Class Official
19.3K subscribers
414 photos
15 videos
168 files
59 links
📚 A+ Tutorial Class ለ መጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠቃሚ የሆነ አጋዥ ቲቶርያል በመስጠት እንዲሁም የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለግቢ ፈተናዎቻቼው የሚያግዟቸውን pdfs, ያለፉ አመታት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች Mid and Final Exams የሚያቀርብ ቻናል ነው።

እኛን ለማግኘት : በ @Aplus_support_Admin በኩል ማንኛውንም ጥያቄዎትን ሊያደርሱን ይችላሉ።
Download Telegram
#ጥቆማ

🎉 ለ 2019 ፍሬሽማን ተማሪዎች በሙሉ

🎓 90%+ የ ዲፓርትመንት ቅበላ ፥ የፍሬሽማን ተማሪዎች አሪፍ Grade ሰርተው ወደሚፈልጉት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ከፍተኛ አስተዋዕፆ አበርክቷል።

📚 በስኬታማነቱ የተመሠከረለት አዲሱ የፍሬሽማን ካሪኩለም ሲመሠረት አብሮ የተመሠረተ፥ ከአምስት አመታት በላይ ያስቆጠረ የቲቶሪያል ድርጅት ነው - A+ Tutorial Class ይባላል❗️

❗ ከምሥረታው ጀምሮ በየአመቱ ብዙ ሺ የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ና የኮሌጅ ተማሪዎችን አስተምሯል።

✔️ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ከ 3.7 - 4.0  እንዲያያስመዘግቡ ትልቅ አስተዋዕፆ አበርክቷል ፥ በተጨማሪም ብዙ ሺዎች ወደሚፈልጉት ዲፓርትመንት እንዲገቡ በማድረግ ትልቅ ሚና ተጫዉቷል።

✔️ ለ ዘንድሮ ለ 2019 ፍሬሽማን ተማሪዎችን ተቀብሎ ምቹ በሆነ ና ለመረዳት ግልፅ በሆኑ በአማርኛ እንግሊዝኛ በተብራራ ኖት ፤ በቪድዮ  ና በ Diagram የተብራሩ ቲቶሪያሎችን ያስተምራል።

✔️ በእያንዳንዱ ኮርስ በቀጥታ ለፈተና የሚያዘጋጁ በርካታ ጥያቄዎችን ያቀርባል ፣ ከ 2013 እስከ 2018 በተለያዩ ግቢዎች ላይ የወጡ Mid and Final Exam ጥያቄዎች ተመርጠው ከነ ማብራሪያቸው ይቀርባሉ ፥ ተማሪዎች እያንዳንዱን Lesson ተምረው እንደጨረሱ በ quiz መልክ ራሳቸውን ይገመግማሉ።

🖥 የ A+ Tutorial የፍሬሽማን መማሪያ አፕሊኬሽን ከ playstore ላይ በማውረድ መመዝገብ ይችላሉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.aplus.depthabdre.tutorial

❔ለጥያቄ : @Aplus_support_Admin

ይፋዊ ቻናላችን በመቀላቀል ተጨማሪ የፍሬሽማን መረጃዎችን ያግኙ👇

@Aplustutorialofficial
         
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤20🔥2
👉 ካሁን በፊት ከነበሩ ፍሬሽማን ተማሪዎቻችን የተሰጠ ምስክርነት።

😴 "ሎጂክ 100+ ነው ያመጣሁት" ብሎናል ወንድማች።

🙌 በዚህ አመት ደግሞ A+ Tutorial ላይ የተመዘገበ ተማሪ ሎጂክን ከ A በታች አያመጣም ፥ ያለ ምንም ተጨማሪ reference የፍሬሽማን ሞጁልን ደስ ብሏችሁ ከ real life አገናኝተን ቀለል አድርገን እናስተምራችሗለን።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial

Š A+ Tutorial Class.
👍7👏4❤2🙏2
✅ ይህ መልዕክት ከ AASTU ተማሪ ለ 2019 ፍሬሽማኖች ነው ፥ በደንብ ስሙት!

👨‍🏫 "በ AASTU የ Software engineering ተማሪ ሲሆን ፥ A+ Tutorial በመቀላቀሌ Software engineering ለመግባት አስችሎኛል።" ይላል ተማሪ ነብዩ።

📖 ፈተናዎችን ያማካለ መማሪያ ሞጁላችሁን በቀላሉ እና ግልፅ በሆነ መንገድ ማስተማር መለያችን ነው።

📍ስለ ቲቶርያሉ ማንኛውም ጥያቄ ካላችሁ ፥ @Aplus_support_Admin ላይ ያናግሩን።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤17👍2🔥2
A+TutorialLogicExam (1).pdf
503.2 KB
📣 የፍሬሽማን ዝግጅት የጀመራችሁ ተማሪዎች ፥ ራሳችሁን በእነዚህ ጥያቄዎች ፈትሹ። ያልጀመራችሁ save አድርጋችሁ አስቀምጡት ግቢ ስትገቡ ይጠቅማችሗል።

💡Logic ን የሚወስድ ማንኛውም ፍሬሽማን ይህን pdf መመልከት አለበት።

✅ በየትኛውም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እነዚህን ጥያቄዎች ትፈተኑታላችሁ።  እነዚህን ጥያቄዎች ሁላችሁም በትኩረት ስሯቸው❗️

✔️Chapter two questions with their respective explained answers.

✏️ Number of questions - 62.

📚 የ ቻፕተር 2 ሞጁል እያንዳንዱ ገፅ በነዚህ ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ ተዳሷል።

👉 ለ Mid Exam ፈተናችሁ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ጥያቄዎች ና ማብራሪያዎች ናቸው።


📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤12👏2🎉2
📢 የዶርም ህይወት በጥቂቱ እናጋራቹ

🔠 ግቢ ውስጥ ከምንም በላይ ደስ የሚልና የማይረሱ ብዙ ክስተቶችን የምናሳልፈው በዶርም ህይወታችን ውስጥ ሲሆን በቆይታችንም እጅግ በጣም ብዙ አይነት ትምህርቶችን እንማራለን ።(የቀለም ትምህርት አላልኩም)

🏠 በብዙ ግቢዎች የሎከር በተወሰነ መልኩ አለ ፡ እናም በሎከር እጥረት ምክንያት አንድ ሎከር ለሁለትና ከዛም በላይ በመጠቀም ደስ የሚል መተሳሰብም አለ ፤ ባንፃሩ ደግሞ የዶርም ጭቅጭቅም በብዙ ነገራቶች ይፈጠራል ገና ከጅምሩ በሎከርና በአልጋ ምርጫ የሚጨቃጨቅ ተማሪ አይጠፋም ።

🏠 ሎከር ላይ ያለው ንትርክ ቀድሞ የያዘው ተማሪ ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ አልደበልም በማለት ሲሆን የአልጋው ግን ብዙ ጊዜ ከታች ያሉትን አልጋዎች ፍለጋ የሚፈጠር ሹኩቻ ነው ። ከላይ ያሉት አልጋዎች የመብራት ብርሃን💡 ስለሚያስቸግርና አንዳንድ ተማሪዎችም ስለማይፈልጉ or ስለማይመቻቸው ይመስለኛል (ሎከር ላይ ያለው ነገር በስምምነት ይፈታል ከቻላቹ ለመቅደም ሞክሩ ከተቀደማቹ ደግሞ አምባጓሮ ሳትፈጥሩ በpeace....)

✔️ ዶርም ውስጥ በምትኖሩበት ጊዜ ከተለያዩ ተማሪዎች ጋር ስለምትኖሩ ፀባያችሁን በጣም መግራት ይጠበቅባቹሃል ። ለምሳሌ በአንድ ዶርም ውስጥ 8 ተማሪ ቢኖር ከሰባቱም ተማሪ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፀባይ ላይኖረን ይችላል ።
ያንተ ፀባይ የቱንም ያህል አሪፍ ቢሆን ምንም ደስተኛ የማይሆን የዶርም አባል ሊኖር ይችላል ። በዚህ ጊዜ ከኛ የሚጠበቀው እንደዛ አይነት ተማሪዎችን ለማስደሰት መፍጨርጨር አልያም በንዴት እነሱን ፊት መንሳት ሳይሆን ባለንበት ጥሩ ፀባይ ለመፅናት መሞከር ነው ።

💔 ተመልከቱ እንግዲህ ከሰባት ተማሪ ጋር ሆኖ ሰባት አይነት ፀባይ መቻል እንዴት እንደሚከብድ ? ዋናው love❤️ ነው ብላቹህ የምታምኑ ከሆነ ግን ለሀያ ምናምን መኖርም አይከብዳችሁም ።

🔠 ዶርም ላይ

🌗በጣም ሀይማኖተኛ
🌗በጣም ነጭናጫ
🌗በጣም ሱሳም
🌗ከፊል ዘረኛ
🌗በጣም ዝርክርክ
🌗በጣም ተጠራጣሪ
🌗መቼም የማያወራ (ልጉም)
🌗ለሰከንድ ዝም ማለት የማይችል (BBC).....

👋 እና ሌሎችንም የመሳሰሉትን አይነት ተማሪዎች ያጋጥሙሃል/ሻል የናንተም የሆነ type of ፀባይ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው ።

🎧 እናም ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎችንም አይነት ፀባይ ያላቸውን ተማሪዎች እንደ አመጣጣቸው ማስተናገድ ይኖርባቹሃል ማለት ነው ።

🎮 አንዳንዴ ደግሞ ደባሪ ነገሮችንም ልታስተናግድ ትችላላችሁ ። ለምሳሌ አንድ የዶርም አባል ቅዳሜን አክባሪ ከሆነ ጨብሶ በመምጣት ቁም ስቅላችሁን ያሳያቹሃል (ቅዳሜ የመጠጥ 🍻ቀን ናት ብለው ስለሚያስቡ ነው) እናም የጨበሰው ወይም የጨበሰችው ተማሪ ዶርም ውስጥ በብዙ አይነት መልኩ አዛ ያደርጓቹሃል ።

🤮 ሻታ በርግደው የዶርሙን ንፅህና በማስዋብ (ምን ማድረግ ይሻላል🥹? ማልቀስም አይሻልም😭 ...ማለት ከዚህ ላይ ነው)

👽 በተኛችሁበት ብርድ ልብስ በመግፈፍ
ከአልጋ ለማስወረድ በመታገል

😡 ሳትፈልጉ በስካር ቅላፄ ዘፈን መጋበዝ (ወይኔ በላቸው ...እስክትሉ)

⚡ሌሎችንም like this የመሳሰሉትን የስካር  አመሎችን ሊያሳዩ ስለሚችሉ በተቻላቹ አቅም ስካራቸው እስኪለቃቸው በትዕግስት በመቻል እንዴትም ጊዜዋን ማሳለፍ ይጠበቅባችዋል ።

📣ከላይ የተጠቀሱ ነገሮች ወንዶችን ብቻ የሚመለከቱ አይደለም ከወንዶች ባልተናነሰ መልኩ የሴቶች በሽታ ነው ።

©️Hahu Students

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤18👏8😢1🎉1
🔔 በተለይ የ ፍሬሽማን ተማሪዎች ግቢ ላይ በአቻ ግፊት ተፅዕኖ ይጠመዳሉ ፥ ሲኒዬሩ ተማሪ ያሳለፈውን የፍሬሽማን ህይወት አጋርቷችሗል ፥ ምክሩንም ሰጥቷችሗል ፥ በደንብ አንብቡት📥

"ሰላም😇 L እባላለሁ የDireDawa 3rd year ተማሪ ነኝ👱‍♂። በዚህ አመት ወደ ግቢ ለሚገቡ ተማሪዎች የምመክረው ነገር ስላለኝ ነው። በመጀመሪያ ወደ ግቢ ስመጣ ከቤተሰብ የተደረገልኝ ሽኝት እና በግቢ የነበረው አቀባበል ደስ ይል ነበር።😍😍 ከዚያ ስሜን አስመዝግቤ Dorm ምናምን ካገኘን በኃላ ከዶርም ልጆችጋ ምናምን ተዋወኩኝ የተወሰኑት የዶርም ልጆች Seniorኦች ነበሩ፣ እና ተዋወቅን እንደኔው ደግሞ እዛ ዶርም አዲስ ገቢ የነበረ ልጅ አለ ከእሱጋ😍 በደንብ Pis ሆንን። ከዚያም በሚቀጥሉት ቀናት ትምህርት እስኪጀምር ድረስ ግቢው ውስጥ ዞር ዞር እያልን እንጎበኝ ነበር። ብቻ በአጠቃላይ 1st semister የነበረው ሙድ፣ ያሳለፍነው time ገራሚ ነበር። በዚሁ ገጠመኜን ልንገራችሁ😢ግቢ ገብተን Cafe ምግብ ለመብላት ከመሄዳችን በፊት የሆነ የዶርማችን Senior ልጅ እንዲህ አለን (ለእኔና ለጓደኛዬ)። ሰሃን🍛 ስትወስዱ (የግቢ cafe ውስጥ ሰሃን ተሰልፈን እየወሰድን ነው የምንበላው) በየሰሃኑ ላይ የተማሪው ስም ስለተፃፈ እናንተም ስማችሁ ያለበትን ነው የምትወስዱት አለን፣ ከዚያ እሺ ብለን cafe ሰአቱ ሲደር ሄድን...then after ስማችንን ሰሃኖቹን እየገለበጥን እንፈልጋለን፥ ሰዎቹና ተማሪዎች ምን ሆነው ነው ብለው ይስቁብናል😂😂😂

ምን ሆናችሁ ነው? ሲሉን ስማችን ያለበትን ሰሃን እየፈለግን🙆‍♂🙆‍♂😁😁😁 የምን ስም ነው አሉን፥ በዚያ ሁሉ ተማሪ ውስጥ አፈርን...never forget that day😂 የዶርማችን ልጅ ሰራልን🙆‍♂

በመቀጠል ወደ ቁምነገሩ ስመጣ 1st sem ላይ አሪፍ ግሬድ አመጣሁ 3.8፥ ነገር አንድ ያልነገርኳችሁ ነገር በዶርማችን የነበሩት ተማሪዎ ሲጃራ ምናምን የሚያጨሱ ነበሩ፣ እኔ ብዙ ጊዜ ዶርም ስለሆነ ማነበው ልክ ዶርም ስገባ የዶርሙ ሽታ ሲጃራ ብቻ ነው 😞😞የመጀመሪያ ሰሞን እኛ ፊት አያጨሱም ነበር። ከዚያ በኃላ ግን እነሱም ምንም አይመስላቸውም። እንዳልኳችሁ እኔ ዶርም ስለሆነ ማነበው ሽታው ተፅዕኖ እያሳደረብኝ መጣ ከዚያም Library እየሄድኩ ማንበብ ጀመርኩ ግን ያው በጊዜ ስለሆነ ምገባው ስገባም እነሱ ከጓደኞቻቸው ጋር እየቃሙና እያጨሱ ነው። እኔም ጓደኛዬን ተደብቄ እነሱም በሌሉበት ከእነሱ ላይ የተረፈውን እነሱ መሬት ላይ የጣሉትን አንስቼ አጨስኩ (that was my first time) ትን ብሎኝ ልሞት ነበር😭 ፈጣሪ አተረፈኝ🙏፥ እያልኩ እያልኩ ቀስበቀስ ለመድኩት ለራሴ እየገዛው ዶርም ውስጥ ማጨስ ጀመርኩኝ። ከቀድሞ በበለጠ ብዙ ጊዜዬን ለብቻዬ ዶርም ማሳለፍ ጀመርኩኝ። የድብርት ስሜት ውስጥ ገባሁ 🤕እኔው ብቻ ከሁሉ ኃጢያተኛ እንደሆንኩኝ ይሰማኝ ጀመር።😓

ከዚያ እንድ ቀን እንዲህ ሆነ እያጨስኩኝ ጓደኛዬ ድንገት መጣብኝ (ማታ ይመጣል ብዬ አልገመትኩም ነበር lib. ይሆናል ብዬ ነበር ያሰብኩት) ከዚያ ድንግጥ አልኩኝ።😨 እሱ በጣም ጥሩ ባህሪ የነበረው ልጅ ነበር፣😍 ይሄ ነገር በእሱም ተፅዕኖ ሊያመጣበት እንደሚችል አስቀድሞ አውቆ ስለነበር ብዙ ጊዜውን ውጪ ነበር ሚያሳልፈው። እኔንም እንደዛ ይለኝ ነበር። ከዚያ ልክ ሲጃራ በእጄ ይዤ ሲያየኝ የሚያንቋሽሸኝ ምናምን መስሎኝ ነበር ነገር ግን እሱ መጣና ሲጃራውን ከእጄ ላይ ወስዶ መሬት ላይ ጥሎት። በስሜ ጠራኝና #ይሄ_ላንተ_አይመጥንም አለኝ። ከዚያ ወሰደኝና ግቢ ውስጥ ያለ ምንብ ቤት (Launge) ሄድንና ብዙ መከረኝ፣ አበረታኝ ምናምን። Wow ከዚያ የሚገርም የደስታ ስሜት ተሰማኝ🥰 ከዚያም ሁኔታውን አመቻችተን ወደ ሌላ ዶርም አሰቀየርን። ብዙ ሳልሰምጥ አምላኬ በጓደኛዬ (ወንድሜ)😍 በኩል ታደገኝ።

ምንም እንኳ ያ ልምምድ ትንሽ Challenge ቢያረገኝም፤ ጓደኛዬ ያለው ነገር ሁሌ ትዝ ሲለኝ እበረታለሁ፦ ይሄ ላንተ አይመጥንም  Wow🥳 አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ፣ ትምህርቴም ከልጆች ጋር ያለኝም ቅርርብ ወደ ድሮ ተመልሷል። አምላክ ይመስገን። እናም ጠቀለል ሳረገው ላስተላልፍላችሁ የፈለኩት #አብራችሁ_የምትውሉትን ጓደኛ፥ Environment ምረጡ። እንዲሁም የማይመጥናችሁ ስፍራ አትገኙ። እናንተ አላማ ያላችሁ ትልቅ ሰው ናችሁ የወረደው ቦታ ለእናንተ አይመጥንም።

ደህና ሁኑ መልካም የትምህርት ዘመን☺️ L from DDU"

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤49👍14🎉3🔥1
🗓️የ 2019 ፍሬሸማኖች ዝግጅት ጀምሩ📥

📩 የዩኒቨርሲቲ ምደባ ቀድሞ ይፋ የሆነ
ቢሆንም፦ 90%+ ግቢዎች ግን እስካሁን
ለፍሬሸማኖች ጥሪ አላደረጉም።

📢 ግቢ አልተጠራንም ብላችሁ ግን
አትዘናጉ፤ ከአሁኑ ዝግጅቶችን ለማድረግ
ሞክሩ። ምክንያቱም ግቢ ስትገቡ ሳታስቡት
Mid and Final Exam ቶሎ ነው
የሚደርሰው። ከክላስ ዶርም ከዶርም ካፌ
ከካፌ ላይብረሪ ህይወታችሁ በዚህ Circle
ውስጥ ስለሆነ የሚሆነው ሳታስተውሉት
ጊዜው ይፈጥናል፥ ፈተናችሁ ቶሎ ይደርሳል።

✔️መማሪያ ሞጁለችሁ ላይ የምታገኙት ኖት
በጣም basic ነገር ነው። ዝርዝር የሆኑ ሰፊ
የሆኑ ማብራሪያዎችን ሞጁሉ ላይ አታገኙም።
ያ ማለት ሞጁሉን ማንበብ ብቻውን ኮርሱን
ለመረዳት በቂ አይደለም። ከሞጁሉ ይዘት
ከፍ ባለ መንገድ መረዳት ስለሚጠበቅባችሁ
detail የሆኑ ነገሮችን በራሳችሁ የተለያዩ
material ሎችን refer ማድረግ
ይጠበቅባችኋል።

🚨 መምህራኖቻችሁ በአንድ ክላስ አንድ
ቻፕተር ሊጨርሱ ይችላሉ። ያ ማለት ያንን
ቻፕተር in detail ለመረዳት ጫናው
የሚያርፈው እናንተ ላይ ነው። ግቢ ከገባችሁ
በኋላ ከምትጣደፉ ቢያንስ አሁን ላይ
የኮርሶቻችሁን የመጀመሪያ ቻፕተሮች ይዘቶች
ለመመልከት ሞክሩ፥ ትንሽ ትንሽ ቢሆን
ለማንበብ ሞክሩ።

❓ ማንበብ ማለት ደግሞ ሶስት ሰአት
ቁጭ ብሎ አንድ ቻፕተር መጨረስ ማለት
አይደለም ፥ እያንዳንዱን topic ከስር
መሰረቱ እየተረዳችሁ በዝርዝር እያወቃችሁ
በጥቂቱ የሚያድግ ቋሚ ና የማይጠፋ መረዳ
ግንዛቤ መያዝ ማለት ነው። ስለዚህ ስታነቡ
በጥልቀት ከስር መሰረቱ ለመረዳት ሞክሩ።

📈 ካነበባችሁ በኋላ ደግሞ ራሳችሁን
በጥያቄ ፈትሹ ፥ የፈተና አወጣጥ
ስታይሎችን በደንብ ለመረዳት ሞክሩ።
ስለዚህ አትዘጉ ከአሁኑ ትንሽ ትንሽ ነገር
ቢሆንም ጀምሩ ግቢ ስትገቡ የበለጠ
ያቀልላችኋል።

🎉 የ A+ Tutorial የፍሬሽማን መማሪያ App ከ playstore ላይ በማውረድ የፍሬሽማን ኮርሶችን ቀለል ባለ መንገድ መረዳት ይቻላል⤵️

📱https://play.google.com/store/apps/details?id=com.aplus.depthabdre.tutorial

💬ስለ A+ Tutorial መረጃ ለማግኘት :
@Aplus_support_Admin

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤22🔥1🥰1👏1
Hurley - A Concise Introduction To Logic 13th ed 2018.pdf
10.6 MB
💡Freshman Reference Book⤵️

🔤 "Hurley - A concise introduction To Logic."

💡13th Edition.

🥺 ባለፈው የዚህን መፅሀፍ 11 th edition አጋርተናችሁ ነበር ፥ ይህ ደግሞ 13th edition ነው።

⤴️ ይህ መፅሀፍ በአንድም በሌላም መንገድ ይጠቅማችሗል እና አጫጭር ppt ከማንበብ ጠለቅ ያለ ለመረዳት ይህን መፅሀፍ አሪፍ ነው።

🚨ፍሬሽማን ላይ ሎጂክ ኮርስ ለእናንተ አዲስ ስለሆነ ይህን መፅሀፍ እንደ ማጣቀሻ ብትጠቀሙት ና እዚህ መፅሀፍ ላይ ያሉ ጥያቄዎችን መመስራት ለሎጂክ ውጤታችሁ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤13🔥1
#LifeSharing

"📚 ሰላም ተማሪዎች👋 ዜድ ነኝ ከ#ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ; አዲስ ዩኒቨርሲቲ ለምትገቡ ሴት እህቶቼ ከማውቀው አንፃር ትንሽ ምክር ልመክር አሰብኩ።

📚 ሁለተኛ ዓመት እያለሁ ነበር ከዶርም ልጆች ጋር አሪፍ የሚባል ጓደኝነት ነበረን። ከአንዷ ልጅ ጋር አንድ class ነበርን። መካከለኛ ተማሪ ነበረች ፤ አሁን ትምህርቱን መናገር አልፈልግም ብቻ የሆነ ኮርስ #incomplete ሆነባት።ግን አንድም ቀን ቀርታ አታውቅም።አስተማሪውን አናገርነው  ምንም አላለም በቃ ስልክሽን ስጪኝና እናውራ አላት።

📚 በነጋታው ደወለላት እና ለምን incomplete እንደሆነ ስትጠይቀው አሁን አይመቸኝም ከግቢ ስወጣ እዚህ ቦታ እንገናኝ አላት። የምር በጣም ደነገጥን።በቃ ተስፋ ቆረጠች ምክንያቱም እንደምትጫር ታውቃለችና። እንገናኝ ያላት ቦታ ልትሄድ ወሰነች። እኛ(የ ዶርም ጓደኞቿ) እንዳትሄድ ከለከልናት።በጣም መከርናት። የአንድ ተምሮ ያልተማረ ሰው መጫወቻ እንዳትሆን በሚል አሰላስለን ....

📚  በኋላ እቅድ አወጣን።ሲደውልልሽ #record አርጊው አልናት። በመጀመሪያ በጣም ፈርታ ነበር ከዛ ግን ተስማማች።ከሁለት ቀን በኋላ ደውላ ብዙ እንዲያወራ ገፋፋችውና ዘባረቀ። "አንቺ እኮ ቆንጆ ነሽ ለማንም ተራ ተማሪ አትገቢም.....ካልተስማማሽ ወደ ቤተስቦችሽ  ተጭረሽ ትሄጃለሽ.... grade report ላደርግ ስልሆነ ቶሎ ወስነሽ ደውዩ!" አላት። ...first step ተሳካልን።

📚 ከዛ ግቢ ያለው የሴቶች ጉዳይ ለመሄድ አስበን ነበር ግን ምንም መፍትሄ እንደማይሰጡ ስለምናውቅ ተውነውና ቀጥታ ፖሊስ ጣቢያ ሄድን። #record ያደረግነውን እና ሁለት ምስክር ቀረብን።ግቢ ተመልሰን ደወለችለትና እንደተስማማች ነገረችው። እዚህ ሆቴል ብቻሽን እንገናኝ አላት።...ወደ 11 ሰአት ነበር ስንወጣ ለፖሊሶቹ ደውለን ቦታውን ነገርናቸው። እሷ ቀድማ ነበር የደረሰችው ሲቪል ፖሊሶቹም ወዲያው ደርሱ።

📚 ሰውየው መጥቶ ትንሽ እንዳወሩ ክፍል እንያዝ ማለት ጀመረ።እጅ ከፍንጅ ነው የተያዘው።ቃል አላወራም በቃ በድንጋጤ ደነዘዘ።ከዛ ውጤትም ተስትካከለላት አሁንም አብረን አለን (dorm ብንለያይም)

📚 ይህን ስፅፈው የምር በራሳችን ኮራን ፤ በቃ ሕይወቷ የዳነ ያክል ነው የተሰማኝ።

📚 እባክሽን እህቴ ለእንደዚህ አይነቱ አስተማሪ(አስተማሪ ለማለት ይከብዳል) እጅ እንዳትሰጪ...በፍፁም!!! መውሰድ ያልብሽን እርምጃ ሁሉ ተጠቀሚ።ደፋር መሆን አለብሽ።አንቺ የማንም ተራ ሰው መጫወቻ አይደለሽም።የምር በጣም ይፀፅትሻል።አለም ላይ infinite እድሎች አሉሽ ውዴ።ይህ ተራ ነገር ነው።
#ለነሱም ፈጣሪ ልቦና ይስጣቸው ሌላ ምን ይባላል🤷‍♀::"

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤38👏16🥰4🤩2
Audio
#LifeSharing

📚 ሜሮን ትባላለች ከ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ።

📚 በመጀመሪያው ሴሚስተር 3.8 ነው ያመጣቺው።

✅ ውጤት መስራት ግዴታ ነው ትላለች ሜሮን ፥ ካልሆነ ጊዜ ማባከን ነው ትላለች።

📚 "ፍሬሾች በጣም ብር እናባክናለን" "ስለዚህ አዲስ ገቢ ፍሬሾች ብር አጠቃቀም ላይ ጎበዝ ሁኑ ትለናለች" ሜሮን።

📚 "ፍሬሽማን ኮርስ አንድ አመት ጊዜ ማባከኛ ነው ምንም የተለየ ዕውቀት አይጨምርም ፤ ግቢ ላይ ውጤት ካልሰራን ዕድሜ ማቀጠል ነው" እያለች ነው ሜሮን እስኪ እንስማት።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤13
🔔 የታላቅ ምክር ለፍሬዎች....⬇️

✔️ ግቢ በየትኛውም ሰዓት ብትደርሱ ስለሚያስተናግዷቹህ በጭራሽ ቤርጎ እንዳትከራዩ ፤ በተለይ ከሩቅ ቦታ የምትመጡ ተማሪዎች ግቢው ስለሚረ'ዳቹህ ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳትዳረጉ ፤ ስርቆትም ሊኖር ስለሚችል ለብቻቹህ ከሆናቹህ ቤርጎ ባትከራዩ ፒስ ነው(በተለይ ሴቶች)

✔️ ከብዙ ወከባዎች ለመትረፍ ከፈለጋቹህ አንድ ቀን ቀደም ብላቹህ ግቢ ግቡ ማለት ግቢው በ29 ከጠራ እናንተ በ28 ግቡ ያስገቧቹሃል ፤ ቀደም ብሎ የሚመጣን ተማሪ አናስተናግድም የሚሉት ሳክስ ነው ፤ቀደም ብላቹህ ከመሄዳቹህ በፊት ግን ነባር ተማሪዎችን ለማንኛውም አናግሩ ።
 

✔️ ሻንጣ እንዳይቀያየርባቹህ የናንተን ሻንጣ የምትለዩበት መለያ ምልክት ይኑራቹህ ፤ ብዙ ሻንጣ ሊኖር ስለሚችል በስህተት እንዳይቀያየር (ለክፉም ለደጉ ግን ስልክ ቁጥር የሆነ ቦታ ላይ አስፍሩበት በወረቀትም ቢሆን....!)

✅ ግቢ በር ላይ ጥብቅ ፍተሻ ስለሚኖር ባለፈው የጠቀስኩላችሁን ነገሮች ይዛቹህ እንዳትመጡ ፤በስህተት ካመጣቹህ በር ላይ ይቀሟቹሃል ።
የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ቅርብ ቦታ አስቀምጡ ማለት ሻንጣ ውስጥ አታርጉት ፤ በር ላይ ቅድሚያ ስለምትጠየቁ ሁሉንም ዶክመንቶች በእጃቹህ ለመያዝ ሞክሩ ።

✅ ወንዶች ፀጉራችሁን ከልክ በላይ አታሳድጉ ቀለምም አትቀቡ ፤ የመጀመሪያ ቀናቶች ላይ ፀጉር ምናምን ሊባል ስለሚችል በተቻላቹህ ያህል እይታ ውስጥ የሚያስገባ የፀጉር style አይኑራቹህ(ምቺ ያስመታቹሃል....!)

✔️ ሴቶች አለባበስ ላይ ወጥ አትርገጡ ፤
አንዳንዶቻቹህ ለትምሮ የምትሄዱ እስከማትመስሉ ድረስ ትራቆታላቹህ ፥ የምር አይነፋም ይብራብሽ እርድናም አይደለም ( ለነገሩ ግቢ በር ላይም አይፈቱሽም ጥበቃዎች...!)

✔️ ግቢ ስትገቡ ፀባያቹህ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን ትዕግስተኛ መሆን አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ከማንም ጋር ብትጣሉ ካለምንም ማስተዛዘኛ የመባረር እድላቹህ ይሰፋል ።

✅ የጥላቻና የዘረኝነት ንግግሮችንም ይሁን አመለካከቶችን በፈጠራቹህ ጌታ ይሁንባቹህ እንዳትጠቀሙ ፤ የማንንም ስብዕና የሚነካ ንግግር በስህተት እንኳ እንዳትናገሩ ።

ግቢ ውስጥ ማንንም እንዳትንቁ ፤ እኔንም ጨምሮ ፤ ከየትኛውም ከተማ ልትመጡ ትችላላቹህ ግቢ ውስጥ እስካላቹህ ድረስ ግን እኩል ናቹህ ማለትም አትበላለጡም።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤20👍8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🚨በሶ ለውዝ ቆሎ ምናምን መርሳት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅት አድርጉ🥵።

🫵 ይህን ተላልፎ በሚገኝ ተማሪ አስተማሪ ና የማያዳግም እርምጃ እንደምንወስድ ከ ወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን" - የ ግቢ ካፌ

📱@Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😢12❤8👍4😱1
🎉 ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ እና መልስ ውደድር🙌

✅ ከ 125 በፊት ድሮ ድሮ ሳይኮሎጂ ራሱን የቻለ የሳይንስ ዘርፍ አልነበረም ፥ ነገር ግን በ ጀርመን ሀገር ሌብዚግ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት ጀርመናዊው Wilhelm Wundt(ዊልሔም ውንት) የሳይኮሎጂ ላቦራቶሪ አቋቋመ ፤ በዚህም ምክንያት ሳይኮሎጂ ራሱን ችሎ የሳይንስ ዘርፍ ሁኖ የራሱን የምርምር ስልቶች በመጠቀም ስለ ሰው ልጅ ባህሪ ና አዕምሮው ውስጥ ስለሚካሔድ የአስተሳሰብ ሒደት(mental process) አዳዲስ ጥናቶችን እና እድገቶችን አሳዬ።

👉 ጀርመናዊ የዘመናዊ ሳይኮሎጂ አባት ተብሎ የሚጠራው Wilhelm Wundt በ ሌብዚግ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ባለው የ ሳይኮሎጂ ቤተ-ሙከራ ውስጥ introspection የተባለ experiment በ ሰለጠኑ(train) ሰዎች ላይ በመስራት የሰዎችን የአዕምሮ ክፍሎች ለማወቅ ጥናት አድርጓል።

👉 የ Wilhelm Wundt ደቀ መዝሙር የነበረው ፤ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት ቲቸነር የ ውንት የ introspection ሀሳብን በማስፋት Structuralism Psychology ን መሰረተ። በዚህም ምክንያት የ Structuralism Psychology መስራቾች ውንት እና ቲቸነር ናቸው።

❓ ጥያቄ

☕️ Assume ውንት እና ቲቸነር ፤ ካፌ ውስጥ ቡና እየጠጡ አገኛችሗቸው። ውንት እና ቲቸነር ን ምን እያደረጋችሁ ነው ብላችሁ ብትጠይቋቸው ምን ብለው ይመልሱላችሗል❓

📤Hint : ቡና እየጠጣን ነው ብለው አይመልሱላችሁም።

✅ ቲቶርያሉ ላይ ገብታችሁ እየተማራችሁ ያላችሁ ልጆች መመለስ አትችሉም ፤ ሌሎቻችሁ መመለስ ትችላላችሁ።

🎁 መልሱን ጥሩ አድርጎ ያብራራ ተማሪ የ 150 ብር ካርድ ተሸላሚ ይሆናል።

📱 @Aplustutorialofficial
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10🔥4👍1