A+ Tutorial Class Official
19.3K subscribers
424 photos
15 videos
169 files
61 links
📚 A+ Tutorial Class ለ መጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠቃሚ የሆነ አጋዥ ቲቶርያል በመስጠት እንዲሁም የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለግቢ ፈተናዎቻቼው የሚያግዟቸውን pdfs, ያለፉ አመታት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች Mid and Final Exams የሚያቀርብ ቻናል ነው።

እኛን ለማግኘት : በ @Aplus_support_Admin በኩል ማንኛውንም ጥያቄዎትን ሊያደርሱን ይችላሉ።
Download Telegram
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመትና በላይ ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን የመግቢያ ጊዜ መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት በምትማሩበት ግቢ (በደሴ ግቢ፣ በኮምቦልቻ ግቢ እና በልዕለ ህክምና ግቢ) ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

መስከረም 13/2019 ዓ.ም በቅጣት ምዝገባ ሲሆን፣ ትምህርት መስከረም 13/2019 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል።

በ2019 ዓ.ም ወደ ወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለምትመደቡ የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች፣ የሪሚዲያል ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ተምራችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ጥሪ ወደፊት ይደረጋል ተብሏል።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤11🎉1
🎓 የጥሪ ማስታወቂያ
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ እና ተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀናት መስከረም 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የምትመደቡ አዲስ ገቢ መደበኛ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተከታተላችሁና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች መግቢያ መስከረም 07 እና 08/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
😢10❤5😱1
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#AmboUniversity

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ እና ተከታታይ የቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ መስክረም 18-19/2019 ዓ.ም በመሆኑ በተጠቀሰው ቀናት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።

ለ 1ኛ ዓምውት ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ይገለፃል።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤2
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#ArsiUniversity

ለአርሲ ዩኒቨርሲቲ ነባር ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የምዝገባ ጊዜ መስከረም 9-10/2019 ዓ.ም እና ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 12/2019 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።

✔ 1ኛ ዓመት ለምትገቡ በቀጣይ ማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል።
✔ በ 2018 ዓ.ም በቆጂ ካምፓስ የነበራችሁ ተማሪዎች ወደ ዋናው ካምፓስ (Main Campus) የምትመጡ ሲሆን ፤ ሌሎች ተማሪዎች በሙሉ ባለፈው ዓመት ስትማሩ ወደነበረበት ካምፓስ የምትገቡ መሆኑን እናሳውቃለን።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤4
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#AksumUniversity

ለአክሱም ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ነባር ተማሪዎች በሙሉ፤

የዩኒቨርሲቲያችን ነባር መደበኛ ተማሪዎች፤ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 14 እና 15 2019 ዓ/ም ባለው የጊዜ ሰሌዳ መሆኑን አውቃችሁ፤ ከዚህ ቀደም ስትማሩበት በነበራችሁት ግቢ በአካል በመገኘት ሪፖርት በማድረግ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ እያሳወቅን፤ ከዚህ ውጭ ምንም ዓይነት ምዝገባ በውክልና የማይቻል መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

✔ በ2018 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በሬሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም ትምህርታችሁ ስትከታተሉ ቆይታችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፤ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን የምትገቡበት የመግቢያ ቀናት፤ በ2019 ዓ.ም አዲስ ከሚመደቡልን ተማሪዎች ጋር አብረን የምንጠራችሁ መሆናችንን አውቃችሁ በትዕግስት እንድትጠብቁ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናው ሬጅስትራር ፅ/ቤት!

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤1
📚Academic Excellence

📑የጥናት ችሎታና ልማድን በማዳበር ለትምህርታዊ ልእቀት መስራት    
(getting excellent by developing effective studying habits)

🎯ማጥናት ምንድነዉ?😊(What is Studying?)
  👉ጥናት ችሎታ ነዉ።(Studying is a skill.)
    ብዙዎቻችን በጣም ጎበዝ ተማሪ👨‍🏫👩‍🏫 የሆኑትን ስንመለከት በተፈጥሮ ያገኙ ነው የሚመስለን ነገር ግን አይደለም። ጥናት ችሎታ ነው፦ ማለትም የሚቻል ነገር ነው። ማጥናት እችላለሁ፥ ጎበዝ መሆን እችላለሁ ስኬታማ መሆን እችላለሁ። የምርጫ ጉዳይ ነው🤷‍♂። ይህ የዘመኑ አነቃቂ ንግግር እንዳይመስላችሁ ውጤታማ መሆን በውስጣችሁ አቅሙ እንዳለ ከማመን ነው የሚጀምረው።

👉ችሎታ ደግሞ በስራ የሚመጣ እንጂ የሚሰጥ ወይም አለኝ የምንለዉ - talent አይደለም።

👉ተማሪ በትምህርቱ ልቆ ለመገኘት የጥናት ችሎታዉን ማዳበር እና ልማዱ ማድረግ አለበት።
     (In order to be successful learn studying skills, practice them and develop effective study habits)

📘Good Study Habits

📝Good study habits include different skills:

      📌Time Management
(ጊዜን ባግባቡ መጠቀም)

🎯ጊዜአችሁ የከበረ ሃብታችሁ ነው። እናም ሰው ሀብቱን ለጥፋት ወይ ደግሞ ለመልካም ነገር እንደሚጠቀመው እናንተም ጊዜአችሁን ለማይጠቅማችሁ ነገር ወይ ደግሞ እራሳችሁን ለመገንባት ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።

🤔የጊዜ አጠቃቀም የሚያስፈልጋችሁ ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? በጣም ብዙ የሆነውን Task (ስራ) በአጭር ጊዜ መጨረስ ትችላላችሁ፥ ስለዚህም እንቅልፋችሁና ከሌሎች ጋር ያላችሁ ግኑኝነት አይዛባባችሁም። በጣም ብዙ ጊዜ ሚወስድባችሁን ነገር ለዩ! ለምሳሌ Social media📲 ሊሆን ይችላል።

      📌Self-discipline
(በስርዓት መመራት)

🎯ይሄ ለምን እንደሚያስፈልጋችሁ ልንገራችሁ፥ ለምሳሌ ግቢ እያላችሁ 2nd Semister Or 2nd Year ላይ ምናምን ስትደርሱ የግቢን ህይወት በደንብ ስለምትለምዱት ጥናቱን ምናምን ችላ የማለት እድል ይሰፋል። ስለዚህ ጥንቃቄ አድርጉ።

🎯እናም እንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ስትገቡ Self-discipline ያስፈልጋል። መዘናጋት አያስፈልግም። ከሌሎች ተማሪዎች ጋርም ጥሩ ተግባቢና ተጫዋች ነው መሆን ያለባችሁ።

      📌Concentration
(ማስተዋል)

ለጥናት እራሳችሁን ስታዘጋጁ ትኩረታችሁን ለመሰብሰብ እንዲረዳችሁ ስልክ ሳይለንት ማድረግ፥ ላይብረሪ መጠቀም፥ By the way ትኩረት የሚሰርቀው ስልክ፣ Social Media ምናምን ብቻ አይደለም። ለምሳሌ የሆነ ነገር ከሱቅ እንዲገዛ የላካችሁት ህፃን ልጅ መንገድ ላይ የሆነ ሰው ከረሜላ🍭 ወይ ብስኩት🧇 ቢያሳየው የተላከበትን ነገር ይረሳል። እናንተም እንዲህም እንዳትሆኑ☺️ ዙሪያችሁ ባለው ነገር ትኩረታችሁ እንዳይሰረቅ።

      📌Memorization (ማስታወስ)

ያነበባችሁትን ነገር ማስታወስ አለባችሁ። ከላስታወሳችሁ በቃ ዉሃ በላችሁ🙆‍♂ ያ ያጠናችሁት ሁሉ ከንቱና ጊዜ ማባከን ነበር። የማስታወስ አቅማችሁን ለመጨመር ደግሞ መደጋገም ያስፈልጋል።

      📌Organization (ማቀናጀት)

የምትሰሩት ነገር [Assignment; Exams; ሌሎች ቀጠሮዎች] እንዲህ ሲበዛባችሁ ሰማይ ምድሩ እንዳይዞርባችሁ😁 ተረጋግታችሁ To do list📝 አዉጥታችሁ የትኛውን ማስቀደም የትኛውን ደግሞ ማስከተል እንዳለባችሁ በማወቅ፣ በማቀናጀት ወደ ስራ መግባት ነው።

      📌Effort
(ትጋት/ጥረት)

" All things are difficult before They are easy "
        ~~Thomas Fuller

"እንቅልፋም መሆን የተቦጫጨቀ ልብስ ያለብሳል።" ብሏል ጠቢቡ ሰለሞን😊 ስለዚህ ስኬት ያለ ትጋት እንደማይመጣ ተረድታችሁ ሁሌ ትጉ መሆን አለባችሁ። ደግሞም የሆነ የሚደብር ሁኔታ ውስጥ የምትገቡበት፣ ሁሉ ነገር የሚያስጠላችሁ ጊዜ አለ😔። ያን ጊዜ እራሳችሁን ማበረታት እንጂ ተስፋ መቁረጥ የለባችሁም። ልትወደቁ ትችላላችሁ ግን ከወደቃችሁበት ትቢያችሁን አራግፋችሁ መነሳት አትዘንጉ🥰።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤17👍1
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#JimmaUniversity

ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች

✔ የምዝገባ ቀን መስከረም 11-12/2019 ዓ.ም

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤6
🌼🌻 መልካም አዲስ አመት የ A+ Tutorial ቤተሰቦች!

🌻🌼 በተሰማራችሁበት የትምህርት መስክ ሁሉ ፍሬያማ የምትሆኑበት አመት እንዲሆንላችሁ ፥ ጥረታችሁን ይባርክላችሁ።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤20🙏6🔥1
✅ በዚህ አመት ሳይኮሎጂ ኮርስን ከ A በታች የሚያመጣ አንድም የ A+ Tutorial ተማሪ አይኖርም።

✅ ጥንቅቅ ብለው የተዘጋጁ ፥ ያለምንም ተጨማሪ ነገር ለመረዳት ግልፅ ና ጊዜ የማይወስዱ ፥ ከሞጁሉ ኖቶች በላይ ከፍ ብለው የተዘጋጁ ፥ የፍሬሽማን ተማሪዎችን ጊዜ የሚቆጥቡ ቲቶርያሎች በአዲስ መልክ።

✅ በ አንድ ቻፕተር ላይ ብቻ ወደ 100 የሚደርሱ ከ 2013-2018 የግቢ ፈተናዎች ውስጥ ጥያቄዎች በጥንቃቄ ተመርጠው ለፈተና ከሚያዘጋጁ ከግልፅ ማብራሪያ ጋር።

✅ ተማሪዎች እያንዳንዱን Lesson ተምረው እንደጨረሱ ፥ እራሳቸውን የሚገመግሙበት በርካታ test your knowlede quiz ጥያቄዎች።

✅ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች አንፃር ደረጃቸውን የሚገመግሙበት Competitions።

🥳 Registration coming Soon, Stay tuned!

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤23
✅ የመጀመሪያው ሴሚስተር ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

🎯 ይህ መልዕክት ለዘንድሮ ለ 2019 ዓ.ም ፍሬሽማን ተማሪዎች ነው ፥ የፍሬሽማን የመጀመሪያውን ሴሚስተር ውጤት ግቢ ላይ ለምትቆዩበት አምስት ና ከዛ በላይ አመታት መሰረት ነው።

📍የመጀመሪያው ሴሚስተር ውጤት ፥ የምትገቡበትን ዲፓርትመንት ይወስናል። ከ አዲሱ ካሪኩለም  ትግበራ በሗላ ፥ የተማሪዎች የዲፓርትመንት ቅበላ ዋና መመዘኛው የፍሬሽማን ውጤት ነው። ፍሬሽማን 1st semester ላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጣ ተማሪ የሚፈልገውን ዲፓርትመንት መርጦ ይገባል። በተለይም ደግሞ እንደ Medicine, Anesthesia, Pharmacy ና ሌሎችም የጤና ዘርፎች ፥ እንደ Software engineering ና computer science ያሉ የ ቴክኖሎጂ ዘርፎች ፥ እንደ Law ያሉ የህግ ዘርፎች ብዙ ተማሪዎች ስለሚፈልጓቸው ፥ ከብዙ ተማሪዎች ጋ ፉክክር ስለሚኖር 1st semester ላይ ከፍተኛ ውጤት ካመጣችሁ እነዚህን ተፈላጊ ዘርፎች ታገኛላችሁ።

📍የ መጀመሪያው ሴሚስተር ውጤት የሚቀጥሉት የግቢ ቆይታችሁ ላይ ተፅዕኖ አለው። በተለይም ፍሬሽማን ላይ ከፍተኛ ውጤት(GPA) ካላችሁ ፥ ከፍሬሽማን በሗላ እንኳን ውጤት ቢወርድባችሁ ፥ ፍሬሽማን ላይ ያስመዘገባችሁት ውጤት ከፍ አድርጎ ያቆይላችሗል። ስለዚህ ፍሬሽማን ላይ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው።

✅ ስለዚህ አላማውን ትምህርት አድርጎ ዩኒቨርሲቲ የሚሔድ ተማሪ ፥ ይህን ሴሚስተር ሰግጦ ያንብብ። ስታነቡ ደግሞ በብልጠት አንብቡ ፥ እንደው ላይብረሪ ውስጥ እስከ ሌሊት 10 ሰአት ማንጋቱ ብቻውን በቂ አይደለም ፥ የመረጃ ሰው መሆን አለባችሁ ፥ ስታነቡ ፅንሰ ሀሳብ ተኮር መሆን አለባችሁ። ይኸ ማለት ይኸ ነው እያላችሁ ብቻ አትሸምድዱ ፥ ሞጅሉ ላይ ያሉ ኖቶችን ከስር መሰረቱ ለመረዳት ሞክሩ። የግቢያችሁን ያለፉ አመታትት ፈተናዎች በደንብ ስሩ ፥ በምን መልኩ መዘጋጀት እንዳለባችሁ ፍንጭ ይሰጧችሗል።

🎯 የተለያዩ አመታት የፍሬሽማን ኮርሶችን የተለያዩ ግቢዎችን ጥያቄ ተመልካቻለሁ ፥ አብዛሀኛዎቹ ግቢዎች ፈተናቸው መማሪያ ሞጁላችሁን መሰረት ያደረገ ነው። ስለዚህ መጀመሪያ ሞጁላችሁን ማንበብ ፥ ከሞጁሉ ሰፋ ያለ ተጨማሪ ማብራሪያ ደግሞ ለማግኘት Google መጠቀም አሪፍ ነው ፥ ጥሩ አድርጋችሁ search ካደረጋችሁ ግልፅ የሆኑ ማብራሪያዎችን ከነ ምሳሌያቸው ታገኛላችሁ ፥ even ፈተናዎች ሊወጡበትም ይችላሉ። ልክ አንድ part አንብባችሁ እንደጨረሳችሁ በዛ part ዙሪያ የወጡ የግቢዎችን ፈተና በደንብ መስራት።

📍የጊዜ አጠቃቀማችሁን ለማስተካከል ሞክሩ ፥ ግቢ እንደገባችሁ የመጀመሪያው ሳምንቱ ግቢውን መተዋወቅ ላይ ትኩረት አድርጉ። Orientation ይሰጣል እሱን ተከታተሉ ፥ የግቢውን አሰራር ለማወቅ ሞክሩ ፥ ላይብረሪውን ሆስፒታሉን መመገቢያ ካፌውን ክላሱን ዶርማችሁን ወዘተ scan የምታደርጉበት ሳምንት ለማድረግ ሞክሩ ፥ ከዛ በሗላ አብዛሀኛው ትኩረታችሁ ትምህርታችሁ ላይ ይሁን። በአንድ ጊዜ ሁሉንም አንብቤ ነካክቼ ካልጨረስኩ አትበሉ ፥ ቀስ በቀስ የሚያድግ የሚሻሻል ነገር እየሰራችሁ ሒዱ። ትምህርታችሁን ከስር ከስር አንብቡ ፥ ፈተና ሲደርስ አነባለሁ ብላችሁ አትተኙ ፥ እንደዛ ከሆነ ፈተና ሲደርስ ለማንበብ ብትሞክሩ ቴንሽኑ ራሱ አያስነብባችሁም ፥ ከቻላችሁ ፈተና ከመድረሱ በፊት አጠናቃችሁ የፈተና ሰሞን አዕምሯችሁን ነፃ አድርጋችሁ relax ለማድረግ ሞክሩ።

📍በተለይ ለፍሬሽማን ተማሪዎች ስለ ግቢ የተጋነነ መረጃ ነው የሚሰጣችሁ። ሌላ አለም እንደሆነ ተደርጎ ነው የሚነገራችሁ ፥ ግን ምንም የተለዬ ውስብስብ ነገር የለውም። በወሬ አትሸበሩ! አዲስ environment ነው ፥ አዲስ life style ነው ፥ አዲስ መምህራን ናቸው ፥ ከቤተሰብ ትርቃላችሁ ለህይወታችሁ ሐላፊነት የምትወስዱት እናንተ ናችሁ ወዘተ። ልዩነቱ ይኸ ነው ፥ ከዛ ውጪ ግቢ ማለት ይኸ ነው በዚህ ወጥቶ በዚህ ገብቶ የሚሏችሁን አትስሙ። ሌላው ትልቁ ነገር የጓደኛ ተፅዕኖ ከምታገኙት ነፃነት ጋ ተደማምሮ እያሳሳቀ ገደል እንዳይከታችሁ የአላማ ሰው ሁኑ ፥ በራሳችሁ አቋም እና እምነት ብቻ ተጓዙ።

🥳 በተረፈ ፍትት በሉ ፥ አትጨናነቁ ያላችሁን ህይወት enjoy አድርጉት ፥ እንወዳችሗለን በርቱ።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤31😢1
📌 የጥሪ ማስታወቂያ

🎯 ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ነባር የመደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚገቡበት ጊዜ ከመስከረም 21 እስከ 24 ቀን 2019 ዓ.ም. እንዲሆን ተወስኗል።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤14🔥2
✅ ማስታወሻ ፥ እዚህ ጋ ያሉት ተማሪዎች ከራሳቸው ልምድ በመነሳት ለፍሬሾች ያስተላለፉት መልዕክት ነው።

📚 ነባር ተማሪዎች “ግቢ ውስጥ በተለይም አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጥሩ ውጤት ያስመዘግቡ ዘንድ እንዴት እንዲያጠኑ ትመክራላቹህ? “ተብለዉ ለተጠየቁት ምን መልስ ሰጡ።

👨‍🏫 ተማሪ 1

📚 አንደኛ አመት ተማሪዎች ውጤታማ መሆን ከፈለጉ ከአሁኑ ሞጅሎችን በራሳቸው አረዳድ ማንበብ መጀመር አለባቸው እንጂ በዚህ ሰዓት ሌክቸረር እየጠበቁ መማር አያዋጣም ምክንያቱም ሌክቸረሮች ቀስ ብለው ማስተማር ይጀምሩና ልክ ሴሚስተሩ ሊያልቅ ሁለት ሳምንት ምናምን ሲቀረው የቀሩትን chapterች reading assigment ብለው ይሰጣሉ ይሄ ደግሞ አስተማሪ እየጠበቁ የሚያጠናውን ተማሪ ይበልጥ ይጎዳል።

🧑‍🏫 ተማሪ 2

📚 እኔ ለአድስ ገቢ ተማሪዎች የምሠጠው  ምክር በሚያነቡበት ግዜ በደንብ አድርገው ሀንድአውት ብቻ ቢያነቡ በእርግጠኝነት ጥሩ ውጤት ይሰራሉ ከሀንድአውትውጭ የሚወጣ ጥያቄ የለም በተለይ ፍሬሽማን ኮርስ ላይ እንደኔ ግንዛቤ ለብቻ በደንብ ማንበብእመርጣለሁ እየተጠያየቅን ብናነብ ይሻላል እሚሉ ተማሪዎች አሉ በእርግጥ ይህ ጥሩ ቢሆንም መጀመሪያ አንብቦ ከተረዳው ቡሀላ ቢጠያየቁ አሪፍ ነው ደግሞ በምታነቡ ግዜ ሞጅል ላይ ያለ ነገር ቀላል ነው ብላችሁ አትለፉ ዋጋ ያሥከፍላችዃል በፊት ተምሬዋለሁ አቀዋለሁ እሚባል ነገር በጣም ነው እሚጎዳው ምክንያቱም ኮርሱ ላይ ያሉት አብዛሀኞቹ ታች ክላሥ የተማራችሁት ሥለሆነ ቀላል ሊመሥላችሁ ይችላል ፈተና በምትሰሩበት ግዜ ደግሞ ጥያቄውን በደንብ ለመረዳት ሞክሩ ምክንያቱም አንድ ፊደል ታሥበላለች በተረፈ ማንበብ ነው በተለይ ፍሬሽማን ኮርስ ላይ እመረጣችሁት ፊልድ እንድትገቡ።

👨‍🏫 ተማሪ 3

📚 እኔ በተሳሳትኩበት እንዳትሳሳቱ ትንሽ ነገር ላካፍላችሁ።የምትፈልጉትን ነገር ማግኘት ትፈልጋላችሁ ፥ እንግዲያውስ ውጤት መስራት ያስፈልጋችኋል።

📌 አሁን ያላችሁበትን ጊዜ ተጠቀሙበት።Fresh man courseኦች ለማንበብ ብዙም አስቸጋሪ ስላልሆኑ ባላችሁ ጊዜ አየት አየት ብታደርጓቸው አይከፋም። ምክንያቱም ገና ክላስ ከመጀመሩ quize የሚል አስተማሪ አይጠፋም። በ quizeና በትናንሽ ፈተናዎች የተጠረቃቀመ ውጤት ጥቅሙ ያኔ ስታዩት ይገባችኋል።

ያላችሁበትንም ይሁን የሌላ ጊቢ ጥያቄዎች ከመስራት ወደኃላ እንዳትሉ። ጥቂት አንብባችሁ ብዙ ጥያቄ ብትሰሩ ታተርፋላችሁ....

🧑‍🏫 ተማሪ 4

📌 ይህ መልእክት አዲስ ለምትገቡ ተማሪዎች ነው እባካችሁ የያዛችሁትን fresh man program pdf አንብቡ በመጀመሪያው ሴሚስተር ለምትወስዱት 6 or 7 ኮርሶች 1 ወር አይሰጧችሁም የምሬን ነው እኛንም እያደረጉን ያለው ያንን ነው....እባካችሁ ትምህርት ሙድ ውስጥ ግቡ...እዚ መጥታችሁ ጊዜ አጠረኝ ሆዴን አመመኝ ብትሉ እመኑኝ ማንም አይሰማችሁም 5 እና ከዛ በላይ chapter ያላቸውን 6 ኮርሶች በ 1 ወር ከ 10 ቀን ባልሞላ ግዜ ውስጥ ነው እንድትወስዱ የምትገደዱት አስቡበት... ይህን ጊዜ ተጠቀሙበት...አመሰግናለው።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤20👏4