A+ Tutorial Class Official
19.3K subscribers
434 photos
15 videos
170 files
62 links
📚 A+ Tutorial Class ለ መጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠቃሚ የሆነ አጋዥ ቲቶርያል በመስጠት እንዲሁም የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለግቢ ፈተናዎቻቼው የሚያግዟቸውን pdfs, ያለፉ አመታት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች Mid and Final Exams የሚያቀርብ ቻናል ነው።

እኛን ለማግኘት : በ @Aplus_support_Admin በኩል ማንኛውንም ጥያቄዎትን ሊያደርሱን ይችላሉ።
Download Telegram
📢 በ 2019 ግቢ ለምትገቡ ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ላይ ይሄን የምንላችሁን ስሙ❗️

📢 በዚህ ሰሞን ሁላችሁም ውጤታችሁን አይታችኋል። ሆኖም ውጤት መጥቶላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች ፣ «የትኛውን University ልምረጥ?» የሚለው ጉዳይ ነው አሳሳቢ ነው።

📌 በቀጣዩ ሳምንትም የUniversity ምደባ ሙሉ ተብላቹህ በት/ቤቶቻችሁ ትጠራላችሁ!!

🤔 ዩኒቨርሲቲ አምስት ና ከዛ በላይ አመታቶችን የምታሳልፉበት ነው ፥ ህይወትን በራሳችሁ መንገድ ከ 0 የምትጀምሩበት ነው። ስለዚህ የሚቀጥሉት አምስት ና ከዛ በላይ አመታት የምትኖሩበትን ቦታ በጥንቃቄ መምረጥ ያስፈልጋል።

የትኛው ዩኒቨርሲቲ እና ምን አይነት Department መግባት እንዳለባችሁ በጥንቃቄ ማሰብ አለባችሁ። ይህን ለማድረግ ደግሞ እነዚህን ነገሮች አስቡባቸው፤

✅ 1. መግባት የምትፈልጉትን Department ለዩ

በጣም የሚስባችሁ የትኛው የትምህርት አይነት እንደሆነና ወደፊት ምን መስራት እንደምትፈልጉ ለራሳችሁ ግልጽ ማድረግ።

ለምሳሌ website, mobile apps የመሣሠሉት ላይ መስራት የምትፈልጉ ከሆነ፣  እነዚህን ትምህርት የሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎችን መምረጥ ትችላላችሁ ፤ like Software, computer science ,it department ያላቸውን።

✅ 2. ዩኒቨርሲቲው በቡዙ ነገሮች የተሻለ መሆኑን አረጋግጡ

ዩኒቨርሲቲው ጥሩ ስም ካለውና ጥራት ያለው ትምህርት የሚሰጥ ከሆነ አሪፍ ነው። በተለይ ደግሞ እናንተ የምትፈልጉት department  ምን ያህል ጥራት እንዳለው ማረጋገጥ አለባችሁ።

✅ መምህራኖቹ ጥሩ እውቀትና ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው።

✅ ቤተ መጽሐፍት፣Computer class፣ wifi፣ የላብራቶሪ መሳሪያዎችና ሌሎች ነገሮች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መሟላት አለባቸው።

✅  3. አቅማችሁን እወቁ

እንደ አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር  ያሉ ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተፈላጊ የሆኑ Departመንቶች ላይ ለመግባት ፍክክር አለ። ምክንያቱም ብዙ ጎበዝ ተማሪዎች ከ እነዚ ዩኒቨርቲዎች ስለሚኖሩ እና አብረዋችሁ ስለሚወዳደሩ ውጤታችሁ(GPA) ከፍ ያለ መሆን አለበት።

ስለዚህ የትምህርት ፍላጎታችሁን ብቻ ሳይሆን ውጤታችሁንም እና አቅማችሁንም እያያችሁ የሚመጥናችሁን ዩኒቨርሲቲ መምረጥ አለባችሁ።

ለምሳሌ Adiss Ababa ላይ Software ለመግባት Gpa ከ 3.97 ጀምሮ መስራት ሊጠበቅባችሁ ይችላል፤ እንደ Debre brihan diredawa የመሣሠሉት ደግሞ ከ 3.5፣  3.7 ጀምሮ ሰርታችሁ መግባት ትችላላችሁ።

ይሄ ብዙ ተማሪዎች የሚሸወዱበት ነው በትኩረት በደንብ አስቡበት፤ አቅማችሁን እወቁ!

...ሌሎች የሰላም ሁኔታ የመሣሠሉት እንዳሉ ሆነው እነዚህን ነገሮች በማሰብ ምርጫ አድረጉ።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤22👍4🙏3
✅ Theory የሆኑ ኮርሶችን ሞጁላችሁን ብቻ ትኩረት አድርጋችሁ አንብቡ።

📚 | የመጀመሪያ አመት በመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የ ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የምትወስዷቸው ኮርሶች ዝርዝር:

● Mathematics for Natural Science
● General Physics
● Geography of Ethiopia & The Horn
● Logic & Critical Thinking
● Communicative English Skill I
● General Psychology
● Physical Fitness

📖 | እስኪ አሁን ደግሞ እያንዳንዱን ኮርስ ወደ ጥልቁ ወርደን እንመልከት😊።

📚 || Mathematics for Natural Science

● አብዛኛዎቹ Chapteroch 11 ኛ እና 12ኛ ክፍል የተማራችኋቸው ናቸው። የተወሰነ Modification ነው ያለው።

🔸 በይበልጥ ፈተና ሲውጣ basic ነገር ነው የሚያወጡት፡ በፈተና ጊዜ module ማንበብ በጣም ወሳኝ ነገር ነው። Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳትገልጡ አደራ Definition, Properties, Exercises... በቃ module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course Outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል።

📚 || Logic and Critical Thinking

● ይህ 𝖼𝗈𝗎𝗋𝗌𝖾 ለናንተ አድስ ነው። ምክንያታዊነት እና ፍልስፍስና የትምህርቱ መሰረት ናቸው። የ 𝖼𝗈𝗇𝖼𝖾𝗉𝗍 ተማሪ ከሆናችሁ ትሰሩታላችሁ። ይህ ኮርስ በዋናነት የእናንተን የመረዳት ክህሎት ይጠይቃል። እጅግ በጣም በጣም ደስ የሚል ኮርስ ነው። ነገር ግን ጥልቅ ንባብ እና መረዳትን ይጠይቃል። እላይ ላዩን ማንበብ የለባችሁም።

🔸 ለማንኛውም ለ Logic and critical Thinking የሚያግዙ እጅግ በጣም ምርጥ አጋዥ መፅሀፎች አሉ።

❶ አንደኛው: Concise Introduction to Logic

❷ ሁለተኛው: freshman Logic

⓵ Concise Introduction to Logic የሚለው መፅሀፍ በጣም አሪፍ አድርጎ ያስረዳል። በጣም አሪፍ አሪፍ የሚባሉ እና ከበድ ያሉ ጥያቄዎችም አሉት።

□ የዚህን መፅሀፍ ጥያቄዎቹን ገብቷችሁ በአግባቡ ከሰራችሁ፣ በእርግጠኝነት ግቢ ላይ የሚወጣውን áˆá‰°áŠ“ ትሰሩታላችሁ። ምክንያቱም ከባድ የሚባሉ ጥያቄዎች መፅሀፉ ላይ አሉ። እንዳውም ከመፅሀፉ Exercise ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ፈተና ላይ ቀጥታ ያወጡታል። የግቢ መምህሮች በጣም የሚጠቀሙት መፅሀፍ ነው።

⓶ freshman Logic የሚለው መፅሀፍ ደግሞ የ logic ትምህርትን በቀላሉ እንድትረዱት ያደርጋል ምክንያቱም በ አማርኛ እየተረጎመ ስለሚያስረዳ። የትምህርቱን ፅንሰ ሀሳብ (Concept) በቀላሉ ለመረዳት freshman logic የሚለው መፅሀፍ በጣም ምርጥ ነው። በዛ ላይ እጅግ በጣም ደስ ደስ የሚሉ የ concept ጥያቄዎችም አሉት።

🔸 ስለዚህ እኛ የምንመክራችሁ:-

➀ አንደኛ:- መምህሩ የሚሰጣችሁን ኖት or Pdf በአግባቡ ማንበብ እንዲሁም መምህሩ ሲያስተምር በ ደንብ መከታተል ነው። ጥሩ አድርጎ የሚያስተምር መምህር ላያጋጥማችሁ ስለሚችል ነባር ተማሪዎችን ጠይቆ መረዳት።

➁ ሁለተኛው:- freshman logic የሚለውን መፅሀፍ ማንበብ፡ ምክንያቱም መፅሀፉ ላይ የቀረቡት ኖቶችን በቀላሉ ስለምትረዷቸው።

➂ ሶስተኛው:- Concise Introduction to Logic የሚለው መፅሀፍ ላይ ሄዳችሁ ጥያቄዎችን መፍለጥ። የሚገራርሙ ጥያቄዎች አሉት። ከዛ 𝖠 ታመጡና እርፍ😅።

📚 || Communicative English Skill I

● ይህ ኮርስ ላወቀበት ተማሪ የሚሰራ ኮርስ ነው። በውስጡ ምን ምን ይዟል መሰላችሁ:

🔹 Reading Skill (አንድ Passage) ይሰጣችኋል፡ በ passegu መሰረት ጥያቄ ይሰጣችኋል፣ Then የሆነ ማርክ% ታገኛላችሁ። እዚህ ጋ Reading Compression አሰራር ጎበዝ መሆን አለባችሁ ፥ Vocabulary ላይ ጎበዝ መሆን አለባችሁ። ችግሩ ብዙዎቻችን የ እንግሊዝኛ basement ስለሌለን ብዙዎቻችን እንግሊዝኛን መስራት እንቸገራለቸገራለኝን።

🔹 Grammar (Tense, Active and Passive voice, Conditional sentence, modal verbs etc) እነዚህን ነው የምትማሩት። ደግሞ ቀላል ናቸው።

📚 || Geography of Ethiopia & The Horn

● ለ Geography ም አዲስ አይደላችሁም። ነገር ግን ይህ ትምህርት አንዴ ተነቦ የሚተው አይደለም። በተፈጥሮው ይተናል ብል ይቀላኛል😁፡ ስለዚህ ብትችሉ ስታነቡ Note ያዙ ቀጣይ ስትደግሙት Notun ብቻ ማንበብ ነው የሚጠበቅባችሁ። ከ module ውጪ ፈተና አይወጣም።

◌ እንዳልኳችሁ ስለሚረሳ ቶሎ ቶሎ ሳይበዛ ከልሱት አንዳንዴ module ስታነቡት ደስ ላይል ሰለሚችል note እየያዛቹ ዋና ዋና ነጥቦቹን አንብቡ👍።

📚 || General Psychology

● ይህ ኮርስ በብዙ መልኩ አድስ ሊሆንባችሁ ይችላል። ይህን ትምህርት ለየት የሚያረገው በደምብ መረዳትን ይጠይቃል module ካነበባችሁ በቂ ቢሆንም module በደምብ የማያብራራው ሀሳብ ስለሚኖር Ai' ን መጠቀም በጣም ተመራጭ ነው።

◌ በይበልጥ ከ ምዕራፍ 3 ጀምሮ የ case ጥያቄ ስለሚበዛ በደምብ Exercise መስራት ይጠቅማቹሀል። በቀላሉ Google ላይ በ topicu ርዕስ worksheet search ብታረጉ or Gemini ላይ በመግባት በTopicu መሰረት ጥያቄዎቹን እነዲሰጣችሁ በመጠየቅ ከፈተናው ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ጥያቄዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።

🔹 General Psychology 11 ምዕራፎች ሲኖሩት ቢበዛ እስከ ምዕራፍ 8 ብትማሩት ነው አታስቡ።

📚 || General Physics

General Physics ላይ የምትማሩት ከ 11 እና 12 የተለየ ነገር የለውም ከናንተ የሚጠበቀው module ማንበብና á‹¨á‰°á‹ˆáˆ°áА refer አድርጋቹህ ጥያቆዎችን መስራት ነው እንጂ የተለየ አዲስ ነገር የለውም።

📚 || Physical Fitness

● ሜዳ ወጥታችሁ መሮጥ ነው😁። ስለዚህ የ ስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል፡ እንዳትረሱ😅። ይህ ኮርስ ውጤት የለውም ማለቴ ውጤት አይሰራለትም። pass 𝗈𝗋 fail ነው የምትባሉት።

🔸 Fail ካረጋችሁ ቀጣይ አመት Corsun በድጋሚ ለመዉሰድ ትገደዳላችሁ። ስለዚህ fail ላለማረግ እያንዳንዱን Class ተሳተፉት።

በተረፈ ያለፉ አመታት የግቢ ፈተናዎቻችሁን በደንብ ስሩ።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤31🔥1
Audio
#Life_sharing

🙌 የኛ ጀማ 3.8, 3.9 ና 4.0 የሚዘጋ ጀማ ነው። ዝቅተኛ ውጤት ማምጣት ያለባችሁ B+ ነው ፤ A- ና A ማምጣት አለባችሁ ይላል አብዱ።

📌 ግቢን በትንሹም ቢሆን እንደጠበኩት ነበር ፤ ግቢ ላይ የከበደኝ ነገር የካፌ ምግቡ ና ከቤተሰብ ተለይቶ መኖር ነው ይለናል አብዱ።

📌 የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ ጥሩ ውጤት ለመስራት ማንበብ ነው፤ ነገር ግን ያነበበ ሁሉ ጥሩ ውጤት አይሰራም። ግቢ ላይ ከማንበብ ጎን ለጎን መረጃ አፈንፋኝ መሆኑ የግዴታችን ነው ይለናል አብዱ።

📌 የምትፈልገትን ዲፓርትመንት ለማግኘት መስዋዕትነት መክፈል አለባችሁ ይላል አብዱ።

👉 "በብስለት ማንበቤ ፥ መረጃ ላይ ንቁ መሆኔ ፥ ከ ጓደኞቼ ጋ መረዳዳቴ ፥ A+ Tutorial Class መማሬ ፥ ለ ኮርሶቹ የተለያዬ ትኩረት መስጠቴ ፥ ለ አሉባልታ ወሬ ችላ ማለቴ የምፈልገውን ዲፓርትመንት እንዲገባ ረድቶኛል።"

👉 "ግቢ ስትገቡ የመጀመሪያውን ሁለት ሳምንት አታንብቡ። እነዚህን ሁለት ሳምንታት መረጃ በማነፍነፍና ና ጥሩ ጓደኛ በመተዋወቅ ማሳለፍ አለባችሁ ÷ ክላስ አትቅጡ" ይለናል አብዱራሒም።

ŠA+ Tutorial Class.
❤29😢1
Geography Module Final-1.pdf
2.9 MB
📚 በ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀው ፥ የፍሬሽማን ተማሪዎች መማሪያ ሞጁሎች ናቸው።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤13👏3
#LifeSharing

✅ ዲፓርትመንት ከገባን በሗላ ከምንሰራው ውጤት ይልቅ ፍሬሽማን ኮርስ ላይ የተሻለ ውጤት መስራት እንችላለን - የፂዮን ሀሳብ።

👩‍🎓ተማሪ ፂዮን ትባላለች።

📚 በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ናት! ያመጣችው ነጥብ አጠይቁኝ....🏆ጂፒኤዋ 3.8 ነው!

📚 የ ፂዮን የ ግቢ ተሞክሮ ፡ምክር እና ልምድ ለፍሬሽ ተማሪዎች።

📚 ተማሪዎች ካላወቁበት ግቢ የሚበላሹበት ቦታ ሊሆን ይችላል ግቢ ላይ የጓደኛ ተፅዕኖ ከባድ ነው ትለናለች ፅዮን።

📚 ፍሬሽማን ኮርስ ጥሩ ነው ስለብዙ ነገር እንድናውቅ ያደርገናል። የምንፈልገውን ዲፓርትመንት ለማግኘት ፍሬሽማን ኮርስ መስራት የግድ አለብን ብላናለች ፂዮን። ስሟት❗️

Š A+ Tutorial Class.
❤30👏2
📢 አዲስ ወደ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ ተማሪዎች ልታስተውሏቸው የሚገቡ  ነጥቦች ምንድናቸው?


✅ 1. የዩኒቨርሲቲ ካምፓስ አኗኗር ከነበራችሁበት አኗኗር የተለየ ስለሆነ ይህንኑ ተገንዝባችሁ የስነልቦና ዝግጅት አድርጉ። ለምሳሌ ከተለያዪ ቦታዎች ከሚመጡና ስድስትና ከዚያ ቁጥር በላይ ተማሪዎች ጋር በአንድ ዶርም መኖር ትጀምራላችሁ፤ በተገደበ ሰዓት ብቻ ትመገባላችሁ፤ለመመገብም ትሰለፋላችሁ! ወዘተ

✅ 2. አሉታዊ የሆነ የተለያየ ባህርይና ልምምድ ያላቸው ተማሪዎች ሲያጋጥሟችሁ ቆም ብላችሁ በማሰብ ራሳችሁን ጠብቁ! በአሉታዊ የአቻ ግፊት ተፅእኖ ውስጥ እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ

✅ 3. በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያሉ ፋሲሊቲዎችን ለማወቅ ሞክሩ፤ ቤተ- መፅሐፍት፤ መፀዳጃ ቦታዎች፤ የተማሪዎች ዲን ፅ/ቤት፣ ካፍቴሪያ፤ ክሊኒክ ወይም የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ የሚሰጥበት ክፍል፤ የግቢ ፓሊስ ወይም የፀጥታ ቢሮ፤ የስነልቦና ድጋፍ የሚሰጥበትን ቦታ ወዘተ እወቁ 🏠

✅ 4. በዶርም ውስጥ እናንተ  ከምትናገሩት  ቋንቋ እና ከመጣችሁበት  ባህል በመጠኑም ቢሆን የተለየ ቋንቋና ባህል ያላቸው ልጆች ስለሚኖሩ ሁሉንም አክብሮ ና ተግባብቶ መኖር አስፈላጊ መሆኑን ተረዱ

✅  5. ግጭቶች ድንገት ቢከሰቱ ሳትደናገጡ ራሳችሁን ከግጭት ስፍራ አርቁ፤ በማይመለከታችሁና ባልገባችሁ ጉዳይ ራሳችሁንም ሆነ ሌሎችን ከመጉዳት ተቆጠቡ

✅ 6. ዩኒቨርሲቲ የምትገቡበት ዋና  ዓላማ ትምህርት ለመማር ነው። አይኖቻችሁንና ልባችሁን ከዓላማችሁ ላይ አትንቀሉ

✅ 7. ትምህርት ከተጀመረ ሳምንት ጀምሮ መፅሐፍትን ማንበብ ፥ ክፍል ውስጥ የተማራችሁትን ማጥናት፤ ቤተ መፅሐፍት መግባት ጀምሩ! ፈተና እስኪቃረብ ድረስ ሳያጠኑ መዘግየት ፈፅሞ አይመከርም

✅ 8.  በመማር ሂደት ውስጥ በትምህርታችሁ ዝቅተኛ ውጤት ካስመዘገባችሁ ሳትደናገጡ " ለምን ዝቅተኛ ውጤት አመጣሁ?"  ብላችሁ ራሳችሁን በመጠየቅ በተለየ ሁኔታ ለማጥናት እና ትምህርታችሁን ለመከታተል ግብ እና እቅድ አውጡ፤ እሱንም ተግባራዊ አድርጉ፤ ቶሎ ተስፋ አትቁረጡ

✅ 9. ለሰላም፣ ለአብሮነት እና ለመተጋገዝ ራሳችሁን አዘጋጁ የቅርቡን ብቻ ሳይሆን ከዩኒቨርሲቲ ተመርቃችሁና በስራው ዓለም ተሰማርታችሁ የቤተሰብና የአገር አለኝታ ለመሆን ቆርጣችሁ ተማሩ

✅ 10. ዋና ስራችሁ ትምህርት መሆኑን ተገንዝባችሁ እጃችሁ የገባውን ስራ (ትምህርት) በሙሉ ሃይላችሁ ስሩት!!

✅ 11. በሚገጥማችሁ ከበድ ያሉ ችግሮች ቤተሰብን ማማከር አትዘንጉ

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤13🙏10👍4
ማንበብ + መረጃ 👀

👉 ግቢ ላይ ውጤት ለመስራት የተለያዩ Mechanisms አሉ። ዛሬ ልንነግራችሁ የምንፈልገው አንዱን ነው። እርሱም የመረጃ ተማሪ መሆን አለባችሁ።

ግቢ የቱንም ያህል ብታነብ ፡ ላይብረሪ ውስጥ ብትውል ብታድር ፡ ሺህ መፅሀፎችን ብታነቢ መረጃ ከሌለህ በለፋህበት ልክ ውጤት ላትሰራ ትችላለህ።  መረጃው  ምን አይነት ይሆን🤔?

📌 ለምሳሌ አንዳንድ ፈጣን  ተማሪዎች ከነሱ በፊት ያሉ ነባር ተማሪዎችን (senior) ይጠይቃሉ።

🤔 ለምሳሌ ነባር ተማሪዎች ያንን ኮርስ በሚወስዱበት ጊዜ ምን ምን መፅሀፍ ይጠቀሙ እንደነበር: ፈተናው ምን ይመስል እንደነበር፡ መምህራኖች ጥያቄ የሚያወጡበት መፅሀፍ ምን እንደነበር ይጠይቃሉ ፡ ከዛም: ፈተናውንም መፅሀፉንም ይቀበላሉ😉። ስለዚህ እናንተም ተፍ ተፍ ማለት አለባችሁ😁።

📌 ሌላኛው ደግሞ መምህሩ ክላስ ውስጥ በሚያስተምርበት ሰአት ፡ ይኸን part በደምብ አንብቡ ፡ ይሄን ያዙ ምናምን እያለ ፈተና የሚወጣበትን part ሊጠቁም ይችላል። ክላስ ካልገባህ ወይ ደግሞ ክላስ ውስጥ የምታንቀላፊ ከሆነ ፡ ተበላሽ😂። ስለዚህ ክላስ የገቡ ተማሪዎችን መምህሩ ምን ምን እንዳለ መጠየቅ😉።

🙋‍♂ ሀሳቤን ስጠቀልለው ፡ ግቢ ላይ ማንበብ ብቻውን አይጠቅምም። መረጃ አነፍናፊ መሆን አለባችሁ። ስለ ፈተናው አወጣጥ ፡ ፈተናው ምን part ላይ እንደሚያተኩር ፡ ፈተናው ምን መፅሀፍ ላይ ሊወጣ እንደሚችል ምናምን መረጃዎች ሾልከው ይወጣሉ ። ከቻላችሁ ያለፉ አመታት የእናንተ ግቢ የFreshman ፈተናዎችን ሁሉንም አንድ በአንድ ቅጥቅጥ አድርጋችሁ ስሩት:: በዩኒቨርሲቲ ዉስጥ መከታተል ካለባችሁ መረጃዎች አንዱ እና ዋነኛው ያለፉ አመታት ፈተናዎች ናቸው:: ስለዚህ ከንባብ በተጨማሪ መረጃ ላይም እኩል ትኩረት ይኑራችሁ።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤18👍1
Forwarded from đ”Źđ”˛đ”Şđ”˘đ”Ż
A+


የሀይ school ትምርት አለ ብየ ሄጄ ፣
ሁለት unit አለቀ ያውም በ1 period ምንም ሳልፅፍ በጄ ።


ማብራራት መተንተን ከሌለው ማስረዳት፣
A+ን እንጂ አንፈልግም ሌክቸር ይሂዱ ወደቤት ።


ያው ግጥሙም ባያምር ምንም ቃና ቢያጣ ፣
እንደ A ኘላሶች ያለ አስተማሪ ከወዴት ሊመጣ።




A+ እንወዳቹሀለን 🙏🙏🙏
❤23
Forwarded from Contact A+ Tutorial Class
ሰላም ሀዊ እባላለሁ የፍሬሽማን ተማሪ ነኝ እና የA+ ቲቶሪያል ተጠቃሚ ነኝ እና አስተያየት ለመስጠት ነበር እና የምር የምትሰጡት ቲቶሪያል በጣም አሪፍ ነው በጣም ነው የተመቸኝ ቀላልና ግልፅ በሆነ መንገድ ምንም ነገር ሳታስቀሩ ነው ምታስተምሩት እና በጣም ወድጄዋለው አቀራረባቹ በጣም አሪፍ ነው ፈጣሪ ይባርካቹ በርቱ በዚሁ ቀጥሉበት ለብዙዎች መድረስ አለባቹ ለብዙዎች ጠቃሚ ነው እናም አመሰግናለሁ መልካም ጊዜ።
🔥9❤2
Forwarded from Weza 10
ewnetwn nw milachu endet arge endemameseginachu alakim gin beka ye gid misganayen meglets silalebign beka enante complex yemimesil neger bekelalu simplify bemadreg freshmanin bekelalu endiwetaw argachgnal endihum feshman lay arif gpa(3.9) bemamtat yemifeligewn dept law megbat chiyalehu neger gin yihe misgana lenante beki nw biye alasibim kezim belay yigebachuhal bemeceresham keep it up biye abekahu 🙏
🙏8❤2
🎯 የ 2019 ፍሬሽማን ተማሪዎች ስለሚወስዷቸው ኮርሶች አጠር ያለ ገለፃ።

📌
Communicative English Skill I

📌 Emerging Technology

📌 Anthropology

📌 Economics

📌 Geography

📌  Maths(Social)

📌 Civics and Moral Education

📌 Global Trends

📌 Physical Fitness

🙌 አሁን ደግሞ ስለ እያንዳንዱ ኮርስ መጠነኛ የሆነ ገለፃ እናድርግ።

    🏹 Civics and Moral Education

📚 ዩኒቨርሲቲ ላይ የሚሰጠው የ Civics and Moral Education ኮርስ ፤ Highschool ና pre paratory ከሚሰጠው ኮርስ ጋ በፍፁም አይገናኝም። ግቢ ላይ ያለው የ Civics ኮርስ ለተማሪዎች የሚያስቸግር ከባድ ኮርስ ነው። ይህ ኮርስ በተለይ ስለ Ethics ና Morality ምንነት በስፋት ያትታል። ከ Ethics ጋ የተያያዙ የ ሞራል ፍልስፍናዎችን ና ንድፈሀሳቦችን በስፋት ይዳስሳል። በተለይ ስለ Normative ና non-normative Ethics, Teleological Ethics, Ethical Egoism and psychological Egoism, Altruism, Utilitarianism, Quality over quantity Ethics, Quantity over quality Ethics, Act and Rule Utilitarianism, Virtue Ethics, Meta Ethics በጣም በስፋት ይዳስሳል። እንዲሁም ደግሞ ስለ state, government ና citizenship ምንነት በስፋት ያጠናል በተለይ ስለ pluralist state, capitalist state, Leviathan state, Patriarchal state, minimal state, developmental state,social-democratic state, collectivized state, totalitarian state, religious state ና ስለ Citizenship በጣም በስፋት ያጠናል።

            🏹 Communicative English Skill I

ይህ ኮርስ የብዙ ተማሪዎችን ውጤት የሚያነሳ ነው እንግሊዝኛ ሞካሪ ከሆናችሁ። ነገር ግን የአምና ተማሪዎች ውጤታቸውን ዝቅ አድርጎባቸዋል።  በዚህ ኮርስ በዋናነት የምትማሩት 

🟢 Reading skill (  ልክ Entrance እንደተፈተናችሁ አይነት የ passage ጥያቄ ትፈተናላችሁ።)

🟢 Grammar( Tense , conditional sentence, Modal Verbs etc ትማራላችሁ።) mid exam, final exam እና CoC exam ላይ  passive and active voice እና conditional sentence ብዙ ጥያቄ ስለሚወጡ ትኩረት ሰጥታችሁ በማንበብ ተረዱት።)

🟢 Vocabulary - ከ አውዱ ተነስታችሁ የቃላቶችን ተመሳሳይ ና ተቃራኒ ትርጉም መፈለግ ነው። ብዙ ተማሪዎች ለመስራት ይቸገራሉ። ነገር ግን ወደ 5 የሚሆኑ ዘዴዎች አሉ በእነሱ መሰረት መስራት ነው። ፈተና ላይ በብዛት ይወጣል።

              🏹 Geography

📚 ግቢ ላይ የምትማሩት የ Geography ትምህርትም አዲስ አይደለም። በዋናነት የኢትዮጵያን እና የምስራቅ አፍሪካን መልክአምድራዊ ገፅታ ነው በዚህ ኮርስ የምትማሩት ። ነገር ግን ይህ ትምህርት አንዴ ተነቦ የሚተው አደለም በተፈጥሮው ይተናል ብል ይቀላኛል 🤷‍♂ ስለዚህ ብትችሉ ስታነቡ Note ያዙ ቀጣይ ስትደግሙት Note ብቻ ማንበብ ነው የሚጠበቅባቹ ከ module ውጪ ፈተና አይወጣም PPT እንደ Apetizer ውሰዱ 😂 እንዳልኳቹ ስለሚረሳ ቶሎ ቶሎ ሳይበዛ ከልሱት አንዳንዴ Module ስታነቡት ደስ ላይል ሰለሚችል Note እየያዛቹ ዋና ዋና ነጥቡን አንብቡ 👍::

              🎯 Maths (Social)

ከ መጠነኛ ለውጥ ( modification) ውጭ 11 እና 12 የተማራችሁት ነው። 📚 በይበልጥ ፈተና ሲውጣ Basic ነገር ነው የሚያወጡት Module ማንበብ ለዚ ግዜ በጣም ወሳኝ ነው Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳገልጡ አደራ Defintion , Properties , Exercises ..... module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል::

        🏹 Economics

📚 ግቢ ላይ ብዙ ሰቃይ ተማሪዎች Economics ን አይሰሩትም🙇‍♂። 3.7 or 3.8 ያላቸው ልጆች Economics ን B- ምናምን ነው የሚያመጡት። ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው ግቢ ላይ የ Economics ትምህርት ፈተናዎች ወይም ጥያቄዎች conceptual ናቸው። ስለዚህ Economics ን ስታነቡ አትሸምድዱ። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ሞክሩ ፡ ተግባራዊ እውነታውን ተረዱ። 

        🎯 Global Trends

📚ይህ ኮርስ ከስሙ እንደምትረዱት ፤ ፖለቲካዊ ቴክኖሎጂያዊ ና ኢኮኖሚያው  አለም አቀፍ ጉዳዮችን ይዳስሳል። በተለይ አለም አቀፍ ግንኙነት(International relation) ሳይንሳዊ ምንነትን ይዳስሳል። ሾለ አቀፍ ግንኙነት ንድፈ ሀሳቦችን ይዳስሳል በተለይ ሾለ Liberalism, Realism , Marxism ና Constructivism የተባሉ የፖለቲካ ርዕዮቶችን ይዳስሳል። እንዲሁም ሾለ Foreign Policy, National interest ና Globalization በሰፊው ይናገራል። 😁ይህ ኮርስ ለተማሪዎች የሚከብድ ኮርስ ነው።

💡 Emerging Technology.

📚 ይህ ኮርስ ለእናንተ አዲስ ነው ፥ ከስሙ እንደምትረዱት አዳዲስ እየመጡ ያሉ ና ወደፊት አለማችን ላይ ትልቅ Impact ያመጣሉ ተብለው የታሰቡ ቴክኖሎጂዎችን ትማራላችሁ። በዚህ ኮርስ ውስጥ ስለ Data and Science ፥ ስለ Artificial intelligence ፥ ስለ Augmented Reality ፥ ስለ Virtual Reality በስፋት የምትማሩት ይሆናል ፥ በዚህ በአጠቃላይ 7 ኮርሶችን የምትማሩ ይሆናል። ውጤት መስራት የምትችሉበት ኮርስ ስለሆነ ትኩረት ሰጥታችሁ መከታተል ነው ከእናንተ የሚጠበቀው።

            🏹 Physical Fitness

📚 ይህ ኮርስ ውጤት የለውም። ማለትም A, B+ ,C ምናምን ተብሎ Grade አይሰራለትም። pass or fail ነው የምትባሉት። ኳስ ሜዳ ወጥታችሁ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ነው የምትሰሩት ፡ ስለዚህ የስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል። attendance ካልቀራችሁ እና መምህሩ የሚያሰራችሁን ስፖርት ከሰራችሁ pass ትባላላችሁ ማለትም ታልፋላችሁ።

🥺 የ ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች first semester course እነዚህ ናቸው።

🙌  ማስታወሻ - አንዳንድ ኮርሶች ከ ግቢ ግቢ እንደሚለያዩ ግምት ውስጥ አስገቡ ❗️Social Science ሁናችሁ ፥ 1st semester ላይ ከ እነዚህ ኮርሶች መካከል የማትወስዷተው ሊኖሩ ይችላሉ።

🥳 በ A+ Tutorial Class እነዚህን ኮርሶች በጥሩ ሁኔታ እናስተምራለን።

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialoffical
❤18🙏2🔥1
🙌 በነገራችን ላይ የ ጂማ ዩኒቨርሲቲ ሎጂክ ኮርስን A- ና A ማምጣት ብርቅ ነው። የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሲኒዬር ተማሪ ለ ዘንድሮ ፍሬሾች መረጃ አጋቷል።

"👨‍🏫👩‍🏫ሰላም ውድ የ A+ ተማሪዎች እንዴት ናችሁ ስሜ ይቆይና የዘንድሮ የጅማ ዮኒቨርስቲ Social science Fresh ተማሪ እንዲሁም የA+ ተማሪ ነበርኩ እና ከነበረኝ የመጀመሪያ አመት ቆይታ ላካፍላችሁ እኔ የSocial ተማሪ ስለነበርኩ ልነግራችሁ የምችለው ስለ BECO እና ስለ Main campus ነው።

✅ 1) የአየር ፀባዮ ሞቃት ነው በተለይ ከ አዲስ አበባ ለምትሄዱ ልጆች ሙቀቱ እስኪለመድ ትንሽ ትቸገራላችሁ እና ይዛችሁ የምትሄጇቸውን ልብሶች ቀለል ቀለል ያሉ ቢሆኑ ይመረጣል ብርድልብሳችሁ ልሹ ሳሳ ያለ ይሁን ብዙ ልጆች confort ብርድልብስ ይዘው መተው break ላይ መልሰውታል  ይሄን ስል ግን ምንም ወፋፍራም ነገር አትያዙ ለማለት አደለም የሆነ ወቅት ላይ በጣም ቀዝቃዛ አየር ስለሚመጣ እንዲሁም ማታ Library ስታመሹ Jacket or ሹራብ ያስፈልጋችሗል ጠቅለል ሳረግላችሁ በብዛት ቀለል ያለ ልብስ ያዙ ማታ ላይ ቀዝቀዝ ማለቱ ስለማይቀር ሹራብ ምናምን ያዙ

✅ 2) ቀለል ቀለል ያሉ ልብሶች ፣በሶ፣ለውዝ፣ማር/ማርማራታ እንዲሁም ጅማ ኑሮ ከባድ ነው ማለት እቃ ላለማብዛት እዛው እገዛለሁ ብላችሁ ምንም ነገር ትታችሁ እንዳትመጡ እቃ ጅማ በጣም ዉድ ነው ሳሙና ላርጐ ሞዴስ ብቻ ያስፈልገኛል ምትሉትን ነገር ይዛችሁ ብትመጡ ባይ ነኝ😊

✅ 3) አቀባበል ቆንጆ ነበር ለregistration በተጠራን እለት በጊዜ ምዝገባችንን ጨርሰን Doorm ይዘናል እና ስለ Doorm ስናወራ Fresh ተማሪዎች የሚመደቡት BECO campus ነው ደስ የምትል ትንሽ የሀብታም ጊቢ ነው የምትመስለው🤭 በጣም ሰላማዊ ነው doormኦቹም ቆንጆ ናቸው አንድ Doorm ውስጥ ከ6-8 ሰው ይመደባል ዉሀ አትቸገሩም ለልብስ ለገላ ምናምን ለመጠጥ ግን ስለማይሆን የሚጠጣ ውሀ Cafe ስትሄዱ ሀይላንድ ይዛችሁ በመሄድ ከዛ እያመጣችሁ መጠጣት ትችላላችሁ
ሰለ ምግቡ ስናወራ ደሞ ለማጋነን ሳይሆን የምር ከሌላው ጊቢ በጣም የተሻለ ነው ምናልባት ጨጓራውን የሚያመው ሰው ሊቸገር ይችል ይሆናል እንጂ ሌላው ፀዴ ነው ያው እንደ ቤት ምግብ ባይሆንም ግን በጣም አሪፍ ምግብ ያቀርባሉ ከናንተ ሚጠበቀው ሰአታችሁን ጠብቃችሁ መሄይ ነው አንድ ደቂቃ ብታሳልፋ ሚያስገባችሁ የለም የምግብ ዝርዝሮቹ ምስር፣አተር ክክ፣ድፍን ምስር፣ሽሮ፣እሩዝ፣ቅንጬ እና ዜርፎር ናቸው።ደሞ የፍሬሽ ትልቁ ጥፋት ስንመጣ familyም ጐረቤትም ብር ስለሚሰጠን ካፌ ብዙ ተማሪ አይገባም በሗላ ታዲያ ያቺ ብር ስታልቅ መከራ ስለዚህ ካፌ(የካፌ ምግብ ማለት መንግስት የሚያቀርበው ምግብ ነው እሺ ካፌ ሲባል ሌላ እንዳይመስላችሁ)ተመገቡ አንዳንዴ ሽሮ ምናምን ሲሆን ወጣ እያላችሁ ብትበሉ ይሻላል ባይ ነኝ።

✅ 4) ጅማ 4 ካምፖሶች አሉት Main Campus,Agriculture Campus,Tecno Campus and Agaro Campus እና ፍሬሾች የሚመደቡት BECO የምትባለው ከ Main Campus ጋር በድልድይ የምትገናኝ ጊቢ ውስጥ ነው።

✅ 5) ሀይለኛ competition ነው ያለው በተለይ አሁን አሁን ወደ ጊቢ የሚሄዱት ተማሪዎች ቁጥር ትንሽ ስለሆነ ተማሪው እንዳለ ሰጋጭ ነው በዛ ላይ የጊቢው ፈተና በጣም ከባድ ስለሆነ ካልተጠና ውጤት አይታሰብም በተቻለ መጠን Fresh year ላይ life ምናምን ሚባለውን ነገር ወደጐን ተወት አርጐ ሰግጦ ማንበብ ነው የሚያዋጣው b/c ለጊቢ Life ገና ብዙ አመት አላችሁ በዛላይ የ መጀመሪያ አመት ውጤት በየአመቱ ምታመጡት ውጤት ላይ ስለሚደመር ውጤት በደንብ ስሩ።Department ለማግኘትም ቢሆን ውጤት ወሳኝ ነው ብዙ competition ስለሚኖር ውጤት በደንብ ካልሰራችሁ ምትፈልጉትን department ማግኘት አትችሉም።

✅ 6) አስተማሪ እንደገጠምሺኙ ነው በጣም ጥሩ አስተማሪ እንዳለ ሁሉ አስተምሬያለሁ ለማለት የሚገቡም አሉ ለምሳሌ ስሙን ባልጠቅስም Logic Course ያስተማረን መምህር🤦‍♂ ኮርሱ አዲስ መምህሩ በአግባቡ አያስተምር ብቻ ከባድ ነበር እንደዛም ሆኖ ግን A- አምጥቼ ነው ያለፍኩት ይህን ማሳካት የቻልኩትም በውቅቱ የ A+ ተማሪ ስለነበርኩ ነው don't take it as a promotion i told u the reality guys የምር በጣም ነው የተጠቀምኩባቸው እና ተመዝገቡ ማለት እፈልጋለሁ በዚሁ አጋጣሚ ሌላው እንደ Highschool አስተማሪ ላይ depend መሆን አያስፈልግም ጊቢ ላይ የሚያዋጣው በራስ መጣጣር ነው።

✅ 7) በተቻለ መጠን የመጀመሪያ አመት ላይ ሰርክላችሁን በትምህርት እና በቤተክርስቲያን(በጊቢ ጉባኤ፣ፌሎ……) ብትወስኑት የተሻለ ነው ጊቢ ላይፍ ምናምን ሚባለው ይደርሳል ብዙ ጊዜ አላችሁ ከሁሉም በፊት የመጣችሁበት አላማ ይቀድማ የጅማ ፈተናዎች ደሞ ስለሚከብዱ ወጥሮ ማንበብ ያስፈልጋል በተረፈ ጥሩ ጊዜ እንደሚኖራችሁ ባለ ሙሉ እምነት ነኝ መልካም የትምህርት ጊዜ

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤14👍7
#Placement

ማስታወቂያ
የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
 
✅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን ከነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ምርጫችሁን ት/ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ እራሳችሁ በመሙላት እንድታሳውቁ እንገልጻለን።

ማስፈንጠሪያ (Link)  đŸ‘‡
https://student.ethernet.edu.et/
ማሳሰቢያ፡-
v የህክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከ6 ወር በታች ህፃን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል።
 
የትምህርት ሚኒስቴር

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
👍4❤3
🙌 ፍሬሽማን ላይ ውጤት መስራት የሚያስፈልግበት መሰረታዊ ምክንያት

|| በአብዛኛዎቹ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ውድድር የሚደረግባቸው ዲፓርትመንቶች

🏢 First Generation ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በሌሎች የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ወደሚፈልጉት የትምህርት ዘርፍ ለመግባት የሚያደርጉት ውድድር እጅግ አታጋይ ነው። በተለይም በየዓመቱ ከፍተኛ GPA መቁረጫ ነጥብ የሚያስመዘግቡትን አራቱን ቀዳሚ ዲፓርትመንቶች እና የውድድሩን ምክንያት እንመልከት።

👨‍⚕️ Medicine

● የጤና ዘርፉ ያለውን ማህበራዊ ክብርና የተረጋጋ የሥራ ዕድል ተከትሎ፣ የፍሬሽማን ውጤታቸው ወደ 4.0 የተቃረበ እና የቅበላ ፈተናዎችን ያለፉ ተማሪዎች ብቻ የሚቀላቀሉት ዘርፍ ነው።

👨‍💻 Software Engineering

● በ Engineering ወይም በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በ Computing ሼር ከሚሰጡ ዘርፎች መካከል በየዓመቱ ቀዳሚውን cut off point á‹­á‹­á‹›áˆá˘ የቴክኖሎጂ ፍላጎት መጨመር እና የዲጂታል ኢኮኖሚው መስፋፋት የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

💻 Computer science

● በቴክኖሎጂው ዘርፍ ባለው ከፍተኛ የሥራ ፍላጎት፣ የርቀት ሥራ (Remote Work) ዕድሎች እና በራሳቸው የሶፍትዌር ፕሮጀክቶች መፍጠር የሚፈልጉ ተማሪዎች ቀዳሚ ምርጫ በመሆኑ ከፍተኛ GPA ይጠይቃል።

🧑‍⚖️ Law

● በሀገራችን ህግ (Law)ን መማር ትልቅ ክብር ያለው በመሆኑ፣ በማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቀዳሚ መዳረሻ ነው።

|| እነዚህ ዲፓርትመንቶች ከፍተኛ ውድድር የሚደረግባቸው በገበያው ላይ ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎት፣ በውስጣቸው በሚይዙት የተማሪዎች መጠን ገደብ እና በሚሰጡት ሰፊ የሙያ ዕድል ምክንያት ነው።

▢ እነዚህ ዲፓርትመንቶችን መግባት የሚወሰነው በፍሬሽማን ውጤታችሁ ነው። ስለዚህ ከአሁኑ በትክክል መዘጋጀት የህልማችሁን ዲፓርትመንት የመቀላቀል እድላችሁን በእጅጉ ያሳድጋል።

✅ እንደተለመደው A+ Tutorial Class የ 2019 ፍሬሽማን ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ጠቃሚ የሆነ ቲቶርያል ይሰጣችሗል።

📤 Contact us : @Aplus_support_Admin


🎯Join and Share
@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤14🔥2
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም ቅበላ የመግቢያ ፈተና ጳጉሜን 04/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

በ2019 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች የመግቢያ ፈተና ለመፈተን በኦንላይን የተመዘገባችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ጳጉሜን 04/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በመሆኑም ያመለከታችሁ በሙሉ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ መፈተን የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎቹ አሳውቀዋል።

ተፈታኞች በዕለቱ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያዎች መገኘት ይጠበቅባችኋል። የሞባይል ስልክ እንዲሁም ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አመልካቾች ለፈተና ስትቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የአድሚሽን ካርድ እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡

@Aplustutorialofficial
@Aplustutorialofficial
❤9