A+ Tutorial Class Official
19.4K subscribers
451 photos
15 videos
171 files
68 links
📚 A+ Tutorial Class ለ መጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠቃሚ የሆነ አጋዥ ቲቶርያል በመስጠት እንዲሁም የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለግቢ ፈተናዎቻቼው የሚያግዟቸውን pdfs, ያለፉ አመታት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች Mid and Final Exams የሚያቀርብ ቻናል ነው።

እኛን ለማግኘት : በ @Aplus_support_Admin በኩል ማንኛውንም ጥያቄዎትን ሊያደርሱን ይችላሉ።
Download Telegram
📣 Debre Markos University

በ2018 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 14 እና 15/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የየ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡

በ2018 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደ ፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡

@Aplustutorialofficial
❤9👍4
#Woldia University

በ 2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከትምህርት ሚኒስቴር ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አድስ ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲያችን በመደበኛ መርሀ ግብር የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎችና በ 2017 ዓ.ም 1ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር በተለያዩ ምክንያቶች መልሶቅበላ/Withdrawal በመሙላት ያቋረጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 17--18/2018 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በአካል ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታደርጉ እያሳወቅን በምዝገባ ወቅት፡

የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ካርድ ኦርጅናልና ኮፒ፣

ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪቢት ኦርጅናልና ኮፒ፣

አራት 3X4 የሆኑ ጉርድ ፎቶ ግራፎች

የሌሊት አልባሳት እና የስፓርት ትጥቅ አሟልታችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ አናስተናግድም፡፡

ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች መማር ማስተማር ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን እንገልፃለን፡፡

@Aplustutorialofficial
❤10
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429.pdf
2.6 MB
🔷 Logic and Critical Thinking.

🔷 Freshman Module.

📚 በሳይንስ ና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር(MoSHE) የተዘጋጀው የ Logic and Critical Thinking ኮርስ መማሪያ መፅሀፍ ነው። ሴሚስተሩን ሙሉ በዚህ ሞጁል መሰረት እንማራለን።

© A+ Tutorial Class.
a-concise-introduction-to-logic-hurley-7th-ed2.pdf
3.3 MB
🔶 Hurley - A Concise introduction to Logic

🔷 7th edition

🔶 እጅግ በጣም ጠቂሚ የሆኑ ኖቶች ና ጥያቄዎች ያሉት የ Logic and Critical Thinking አጋዥ መፅሀፍ ሲሆን የግቢ መምህራኖች የሚጠቀሙት የ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውጤት እንዲሰቅሉ የሚያደርግ ብቸኛው መፅሀፍ ነው።

© A+ Tutorial Class.
Hurley - A Concise Introduction To Logic 13th ed 2018.pdf
10.6 MB
🔶 Hurley - A Concise introduction to Logic

🔷 13th Edition , Latest Edition.

🔶 እጅግ በጣም ጠቂሚ የሆኑ ኖቶች ና ጥያቄዎች ያሉት የ Logic
and` Critical Thinking አጋዥ መፅሀፍ ሲሆን የ ግቢ መምህራኖች የሚጠቀሙት የ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውጤት እንዲሰቅሉ የሚያደርግ ብቸኛው መፅሀፍ ነው።

© A+ Tutorial Class.
❤16👏1
Frances_Howard_Snyder,_Daniel_Howard_Snyder,_Ryan_Wasserman_The.pdf
10 MB
📚The Power of Logic

📚እንደ Hurley አይነት ጥሩ መፅሐፍ ነው!

📚 ለፍሬሽማን ተማሪዎች

©A+ Tutorial Class
❤3
📣DebreTaborUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች በቅርቡ በሂሳብ ትምህርት ላይ የውጤት ማስተካከያ ስለተደረገ በድጋሜ በትምህርት ሚኒሰቴር ውጤት ማሳዎቂያ ፔጅ ላይ ውጤታችሁን ቼክ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ትምህርት አዲስ የምትመደቡ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር ምደባችሁን ይፋ እንዳደረገ ጥሪ በሌላ ማስታዎቂያ ይደረግላችኋል ተብሏል፡፡

@Aplustutorialofficial
❤2😢2
📣 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ እና በ2017 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች ቅበላና ምዝገባ ሐሙስና ዓርብ ጥቅምት 13 እና 14 ቀን 2018 ዓ/ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ሰኞ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ/ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በዚህ መሠረት በ2017 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በ2017 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት በተማራችሁበት ካምፓስ እንዲሁም በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ኩልፎ (Kulfo Campus)፣ አባያ (Abaya Campus)፣ ጫሞ (Chamo Campus) እና ዋናው ግቢ (Main Campus) የተመደባችሁ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙ ኩልፎ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ እና ዋናው ግቢ ካምፓሶች፤ ሳውላ ካምፓስ (Sawula Campus) የተመደባችሁ ተማሪዎች ደግሞ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል እየቀረባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉና ምዝገባ እንድትፈጽሙ እንገልጻለን፡፡

በዩኒቨርሲቲው አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ከታች የተመለከተውን ሊንክ በመጫን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መለያ ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ሊንክ፡- https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement

ማሳሰቢያ፡-

1ኛ) ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ እንዲሁም አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

2ኛ) ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት


@Aplustutorialofficial
❤12👍1
#DebreBerhanUniversity

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የተቋሙ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም  መሆኑን አሳውቋል።

በዚህም በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ውጤት ያመጣችሁና ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ በዋናው ግቢ፤ በ2017 ዓ.ም የማካካሻ ትምህርታችሁን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች ትምህርታችሁን ስትከታተሉ በነበራችሁበት ካምፓስ በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@Aplustutorialofficial
❤4👍1
#DireDawaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 15 እና 16/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3X4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ የብሔራዊ መታወቂያ/ፋይዳ (National ID)
➫ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@Aplustutorialofficial
❤14
#BahirDarUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች፣ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም የተከታተላችሁና ወደ Freshman Program ለመግባት የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ባወጣው የመንግሥት ስኮላርሽፕ (በወጭ መጋራት) የተመዘገባችሁ እና በግላችሁ ከፍላችሁ በመደበኛው መርሐግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር ያመለከታችሁ በሙሉ የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦

➫ ስማችሁ ከ A - Men የሆናችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሰላም ግቢ ፤ ስማችሁ ከ Meq - Z የሆናችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በፔዳ ግቢ

➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ግሻ አባይ (ይባብ) ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በተለያየ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@Aplustutorialofficial
❤17
የጥሪ ማስታወቂያ

📣 Jimma University

መግቢያ ቀናት ጥቅምት 13-14, 2018.

Check https://portal.ju.edu.et for details.

@Aplustutorialofficial
❤14
📣 አምቦ ዩኒቨርስቲ

በ2018 ዓ.ም ወደ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ በ2018 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲያችን አዲስ የተመደባችሁ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም በዩኒቨርሲቲያችን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነዉ ጥቅምት 17-18/2018 ዓ.ም በመሆኑ በተጠቀሱት ቀናት ብቻ የማህበራዊ ሳይንስ መስክ በዋና ካምፓስ፣ የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ በሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ በአካል በመገኘት እንዲሁም ኦንላይን በ estudent.ambou.edu.et ማመልከቻና ሙሉ መረጃ ሞልታችሁ እንድትመዘገቡ እናሳዉቃለን።

ማሳሰቢያ፡- ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ስትመጡ:-
➢ የ8ኛ ክፍል ስርቲፊኬት፤ ከ9-12ተኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፤ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርቲፊኬት (ዋናዉን እና 1 ፎቶ ኮፒ) እንዲሁም 3\*4 የሆነ 4 ፎቶግራፍ
➢ አንሶላ፤ ብርድልብስ፤ ትራስልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ።
➢ ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።

ሬጅስትራር ጽ/ቤት

@Aplustutorialofficial
❤11
#WOLKITE_University
በ2018 ዓ.ም ለመደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ይመለከታል
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሬጅስትራር ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት በዩኒቨርሲቲው እንዲገቡ በመንግስት የተመደቡ ተማሪዎችን እና የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና (EHEEE) ያለፉ ተማሪዎች ምደባ ስራ መጠናቀቁን ያስታውቃል፡፡
በመሆኑም ወደ ዩኒቨርሲቲው የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች ከጥቅምት 15 እስከ 16/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ሪፖርት እንድታደርጉ ጥሪ ያቀርባል፡፡ በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርሲቲው ያልተመዘገበ ተማሪ የመመዝገብ መብቱ የሚቋረጥ መሆኑን ያስታውቃል፡፡
ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
* የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤት
* የ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
* የ8ኛ ክፍል የድጋፍ ደብዳቤ
* 3x4 መጠን ያላቸው አራት (4) ጉርድ ፎቶግራፎች
* ለመኝታ እና ለግል አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች ይዘው መምጣት
* የብሔራዊ መታወቂያ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN number) ዋናውና ኮፒው ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
ማሳሰቢያ፡ ዩኒቨርሲቲው ለሁሉም አዲስ ገቢ ተማሪዎች መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል፡፡
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራር ጽ/ቤት

@Aplustutorialofficial
❤9🎉1
#Wolayita_sodo_university

በ2017 ዓ.ም. በአቅም ማሻሻያ (ሪሜዲያል) መርሀ-ግብር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም. በአንደኛ አመት ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መደበኛ ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 21 እና 22፣ 2018 ዓ.ም. እንዲሁም በቅጣት ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 24፣ 2018 ዓ.ም. ሲሆን ለምዝገባ ስትመጡ

1. የ8ተኛ ክፍል ካርድ ዋናውን እና የማይመለስ አንድ ኮፒ፣
2. ከ9 እስከ 12ተኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
3. 3X4 የሆኑ ስምንት (8) ጉርድ ፎቶግራፎች፣
4. የትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ በተመደባችሁበት ካምፓስ በአካል በመገኘት ምዝገባ እንድታከናውኑ እናሳውቃለን።

@Aplustutorialofficial
❤8🎉1
#WolloUniversity

በ2018 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እና በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ተምራችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች መግቢያ ቀናት ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮምቦልቻ ግቢ
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በደሴ ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ሁለት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@Aplustutorialofficial
❤6🔥3🙏1
Forwarded from є𝔭𝔥𝔯𝔢𝔪.𝔨
Bro endt nachew zare yemetahun le misgana new betam enamesegnaln A+ tutorial ...be universitye koyta endt lihon new beye sasb ande yenant bateseb yenber wedenant gabzegni ena temzegebku hulum nger alga balga honelgni betam enamesegnachiwaln Camus kelal endihonln kefetari betachi enante nachiw ene ye BAHIRDAR UNIVERSITY temari new Finally kemfelgew dep't yalemnm sekeken gebchalew fetari yebarkachiw!!🤝

Bene bekul demo lalochinm wedenant invite lemadrg kal egebalew enant teleyalachihu keberulgni🙏
❤16