ድንቅ ነን🎯Amazing Generation
100 subscribers
89 photos
13 videos
3 files
15 links
" #ደስተኛ

#ስኬታማ

#አስተዋይ
ወደ መሆን የሚወስድ ህብረት!!"

Contact
@Mikyas_Feleke
Download Telegram
እምነት ይኑርህ

በነገ ላይ ትልቅ እምነት ይኑርህ፣ ሁሉም ነገር የሚሳካልህ ከሰዎች በመብለጥህ አይደለም፣ እየወደክም እነፈየተነሳህም ባለማቀቋረጥህ እና በመፅናትህ ነው።

ወዳጆቼ ወደ ስኬታችሁ የምትደርሱት ባለመቆማችሁ ነው፣ ስለዚህ ወደፊት እንድትጓዙ ብርታት የሚሆናችሁ እምነት ይኑራችሁ!!

@Amazing_Generation
•አንዳንድ ሰዎች የተለየ የህይወት ጫወታ ይጫወታሉ፤ ሁሌም በህብረተሰቡ ዉስጥ የሚነገረን ሰዉ ስኬታማ ለመሆን ተምሮ ፡ዲግሪ ይዞ ፡አግብቶ ጥሩ ስራ ይዞ መኖር እንዳለበት ነዉ፡፡ ግን ህይወትን በሌላ ትምህርት፡ በሌላ ዲግሪ፡ በሌላ ስራ ይተዋወቋታል

• የሆነ ነገር ለማግኘት በፈለክ ቁጥር የበለጠ እየራቀህ ይሄዳል፡፡ በህይወቴ ከተረዳሁት ነገር ዉስጥ የፈለኩት ነገር ጥሎኝ ሲሄድ አይቻለሁ፡፡

• ሰዎች ህይወታቸዉን ሊያደላደሉ ሲጥሩ አያለሁ፡፡ ቦታ ካስያዙት በኋላ ሁሉም ነገር ወደነሱ እንደሚመጣ ያስባሉ ነገር ግን ይህ በገሃዱ አለም የማይሆን ነገር ነዉ፡፡

• ሰዎች የሚያወሩትን ሳይሆን የሚያደርጉትን አስተዉል፡፡ ሰዎች አቁስለዉኛል ምክንያቱም ተግባራቸዉን አተኩሬ ጊዜ ስላልሰጠሁት ዉስጤን አደሙት!

• ከሚሰጡት በላይ የሚቀበሉ ሰዎችን አትታገሳቸዉ፡፡ ከሚጠቅሙበት ነገር በበለጠ የሚጎዱበት ማንነታቸዉ የጎላ ሰዎችን ከህይወትህ ካላወጣሃቸዉ ውስጥህን እንደ'ብል'ይበሉታል

• ብዙ መሰናክሎች እራስህ የምትፈጥራቸዉ ናቸዉ፡፡ ማህበረሰቡ፣ ጓደኞቼ ወይም ቤተሰቦቼ መሰናክል እንደሆኑብኝ አምን ነበር ግን በመስታወት የማየዉ ማንነቴ እርስ በእርሱ ተሰነካክሏል፡፡

• ህይወት አጭር ናት፡፡ ሞት ደግሞ የማይቀር ጉዳይ ነዉ፡፡ ይህን ማሰብ ላትፈልግ ትችላለህ ግን አንድ ቀን ትሞታለህ፡፡ አንተ ብቻ ሳትሆን የምታየዉ ሰዉ ሁሉ ቀኑን ጠብቆ ይሞታል፡፡ ስለዚህ ሕይወትህን እስከ እንጥፍጣፊዋ ድረስ ኑርባት!

• ህይወትህ የሚወሰነዉ ትኩረት በሰጠኸዉ ነገር ላይ ነዉ፡፡ ይህ አለም ብዙ ክፋትና ሰይጣናዊነት የተንሰራፋበት ቦታ ነዉ፡፡

• ደስ የሚል ህይወት ከፈለክ የሚያምረዉና መልካም የሆነዉ ነገር ላይ አተኩር፡፡ አስጠሊታ ህይወት ከፈለክ ደግሞ በተቃራኒዉ የአለም ጨለማዉ ባህሪ ላይ አተኩር፡፡ ይህ ያንተ ምርጫ ይሆናል!

• ሁሉም ሰዉ ዉሸታም ነዉ፡፡ ሰዉ የየራሱ ምክንያት ቢኖረዉም አንዳንዱ ሌላዉ እንዳይጎዳ ፣አንዳንዱ ለማጭበርበር ሌላዉ ደግሞ እራሱን ለመሸወድ ይዋሻል




#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
💦እራስን መሆን ማለት እራሳችንን ከማንም ከምንም ጋር አለማመሳሰል።
እራስን መሆን ቀላል ነገር አይደለም፤ ነገር ግን ሌሎችን እንደመምሰል አይከብድም።

ሁላችንም ልዩ እንድንሆን ባይፈልግ ኖር
አምላክ ተመሳሳይ አድርጎ በፈጠረን ነበር።
ነገር ግን እኛን የሚመስል ፈጽሞ
አይደገምም።

ይህ #ልዩነታችንን_ማህበረሰብ_ወይም_
ልማድ_እየፈተነብን_ከብዙሃኑ_ጋር_ተመሳስለን_
ለመኖር_እራሳችንን_እናስጨንቀዋለን_ልነትን
በእጅጉ_እንፈራዋለን_ምክንያቱም_ተቀባይነት_እንድናገኝ_ስንል።
ያንተን ሳቅ ማንም አይስቀውም፤
ያንትን ንግግር ማንም ሊናገረው አይችልም፤
ያንተን ህልም ማንም ሊፈታው አይችልም፤
ያንተን ምግባር እንዳንተ የሚተገብር ማንምአይፈጠርም።

# ሌላውን_ለመምሰል_አትጣር ፤_ምንም_ያህል_ብናስመስል_ሌላውን_መሆን_አንችልም።
ሌሎችም እኛን መሆን አይቻላቸውም።
ሁሉም የሚያምርበት በልኩ የተሰፋውን
ሲለብስ ነው።
ሌላውን ለመምሰል መሞከር በሌላው ልክ የተሰፋን ልብስ ለብሰን እንዲያምርብን መጠበቅ
ነው።
# ከምንም_በላይ_ውበት_የሚገለጸው_
እራስን_በመሆን_ነው ።
📒📘📖📒📘📖📒📘📖📒📘📖📒
ለሰው ልጅ ስብዐናው መሰረቱ ነው ድጋፉችሁ አይለየን 👍


#babi

@amazing_generaton

#babi

#መልካም_ምሽት_ይሁንልን
#ጠቃሚ_የህይወት_ስንቅ
👉ሁላችንም የቻልነውን በመቋጠር እንለወጥ

📗ያለፈ ነገር አይቀዪርም ፣ ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው ፣ ካለፈው ነገርህ ተማር
እንጅ በፍፁም አታማርር ፣ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም
የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነትአይገልፅም ፣
ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው ፣ መልካም አድርግ ሌላውን
እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣
ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና ለሁሉም ጊዜ አለው ።

📒መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል ጊዜህ ሲደርስ
መኪናዎች ወይም ‘ፕሌን’ ትገዛለህ ፣ ያውም
ለመኖር አስፈላጊ
ከሆነ ፣ ደግሞም እንዴት እንደገዛው የት
ታውቃለህ ?
ተወው በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው ።
በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ
እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣
ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት
አይደለም ። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ
ከተጎዳው ሰው ጋ
ሁን ፣ አስተውል ።

📕ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣
በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውና
የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት
ስራ መስራት
ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤
አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው
፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ አንተም ጥቂትም ብትሆን
ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ ቁፋሮ ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ ምንድነው? ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው ፣ የድንጋይ ቅርፅ (ኮብልስቶን)
እየሰሩ መኖር ነው ፣ ምንድነው ??? እባክህ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣
በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው ።
:
📗አስተውል ፣ መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ
ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን አይደለም ፣ ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም
የመቀዪር ብቃት አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ
ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣አስተውል ።
መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር
እንዲገጥምህ ማመቻቸት
ነው ፣ መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም ።
:
📒የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ
ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን
ያጭዳል" የሚለውን ስታውስ ፣
ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣
ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ
አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም
የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ ።

📕ለራስህ ስትል መልካም ሁን ፣ በጎውንም አስብ።
ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም ።
አትፍረድ ፣ የመፍረድ ሃላፊነት በፍፁም የለህም ። ፍርድ የፈጣሪ ነው፣ ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል ፣ ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ
ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት ። የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል ።
:
📗ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣ አበረታታው ፣ እንደማይጠቅም አትንገረው ፣
ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ
አትሁን ። መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ ነው ። መልካም ጓደኛ ፣ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል ታድለሃል ። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ
መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ።

📒ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትን ፣ ሀዘንን
ያስከትላል ።
ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ ፣
መመለስ በማትችለው
ነገር ላይ አትወጠር ፣ የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ
። አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ ።

📕 ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር ።ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው ፣ "ያስከፍላል"ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ
። ደግ ሁኑ ፣ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ
በረከታቸው ሰላማቸው ልክ የለውም ።

📗ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ ፣ ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ
ሲርቅ ወይም
ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል ። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ
ናቸው ። በራስህ በአፈጣጠርህ ደስ ይበልህ ፣ውለህ
በመግባትህ ደስ ይበልህ ። በአለህ ትንሽ ነገር ደስ ይበልህ ።

📒ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ
አይኑርህ ። በመውደድ የተጠመደ ሰው
ለመጥላት ጊዜ የለውም።
እድሜህን በተመለከተ ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው ።
ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳዪኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው።
:
📕የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ
ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ።
ሰላምና ጤና ፣ ከመልካም አስተሳሰብና በጎ
ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ።




#babi

@amazing_generaton

#Yoseph



#መልካም_ምሽት_ይሁንልን
💧ህይወት ማለት...
.
ሕይወት ውጫዊ ሳትሆን ውስጣዊ ነች
የአንተ ዓለም የሚቀለሰው በምታስበው ነገር ነው፡፡በሌላ አነጋገር የፈጠርካት ዓለም በአእምሮ ውስጥ ያለው እምነት እና አመለካከት ውጤት ነች፡፡አታካች እና ፈተናው የበዛ የሕይወት
ውጣ ውረድ ውስጥ ከተዘፈቅክ መንስኤውን ለማወቅ ወደ ሌላ
ማማተር አይኖርብህም፡፡የገዛ አእምሮህ ላይ ጣትህን ቀስር፡፡
ወስጥህ በነውጥ ማዕበል ከፍ ዝቅ ባለ ቁጥር ውጪውም
አብሮ ከፍ ዝቅ ይላል፡፡ይህ የተራቀቀ ፍልስፍና አይደለም፡፡ደረቅ
ሀቅ እንጂ፡፡ በአአምሮህ ውስጠ ያለው እምነት ውጪውን አለም
አጥለልህ ፍርድ እንድትሰጥ ይረዳሃል ፡፡ቀይ መነጽር ካጠለቅ
ዓለም ሁሉ ቀይ በቀይ ይሆንብሃል፡፡
ቀለል ያለ ያልተወሳሰብ ሕይወት ለመምራት ከፈለግክ ምስጢሩ
ቅርብህ ነው ያለው፡፡የነውጥ ማዕከል የሆነውን አእምሮህን
በሚከተሉት ስምነት ነጥቦች አደብ ማስገዛት ጀምር፣

1. የሰለጠንከበትን ሐሳብ አጢን፡በአካባቢህ እና በማኅብረሰቡ
በተጫኑብህ አስተሳሰቦች ላይ ክፉኛ አትጣበቅ፡፡

2. ጨለምተኝነትን ከአእምሮህ ውስጥ ለአንዴ እና ለመጨረሻ
ጊዜ መንግለህ ጣለው፡የአእምሮህን ቅብዝብዝነት ፈር ማስያዝ
በቻልክበት ቅጽበት ጨለምተኝነት ከላይህ ላይ እንደጉም በኖ
ይጠፋል፡፡

3. ከሐሳብ ጋር ያለህን ቁርኝት ቁረጥ፡ከአልባሌ ሐሳቦች ጋር
ያለህን ዝምድና ማላላት ስትጀምር ሰላም እና ደስታ ወደእንተ
መፍሰሳቸውን ይቀጥላሉ፡፡
4. ቀለል ያለ ሕይውት ከአእምሮ ንፍቀ ክበብ ውጪ ነው
የሚፈጠረው፡ለነገሮች ደረጃ እያወጣ አበሳችንን የሚያስቆጥረን
አእምሮ ቀምበሩ ሲሰበር መንገዱ ሁሉ የተቀና፣ሁሉም ነገር
አልጋ በአልጋ ይሆንልናል፡፡

5. አሁንን ኑር፡እንደፔንዱለም እየተወዛወዝክ መናኛ ሐሳቦች
ላይ ከመባከን ሰልሰህ ወደ እውነተኛው የነፃነት ካምፕ፣ ወደ
የአሁን ቅጽበት ፊትህን መልስ፡፡

6. በአሁን ቅጽበት ውስጥ ሕይወት ገራገር እና ብሩህ ነች፡
የሕይወት ገራምነት የሚጋነነው በእዚህ ቅጽበት ውስጥ ብቻ
ነው፡፡

7. ሕይወትህን ቀላል ለማድረግ ደጋ መውጣት ቆላ መውረድ
አይጠበቅብህም፡ምንም አይነት ምትሃት ወይም ጥልቅ ፍልስፍና
አይሰፈልግህም፣ዝግጁ ስትሆኑ ሁሉም ነገር ይቀናል፡፡

8. በሕይወትህ ውስጥ ያጋጠሙህ አስከፊ ሁኔታዎች እና
አእምሮህ የማይነጣጠሉ ባልንጃራዎች ናቸው፡ ከአስከፊው
የሕይወት ገጽታ በላይ ለመሆን አእምሮህን እንደአሻህ
የምትናደበትን ልጓም ጨብጥ፡፡
በአሁን ቅጽበት ላይ እንኑር፡፡ይኽ የትምህርት ደረጃን፣የአእምሮ
ምጥቀትን፣የሃብት መጠንን
የሚጠይቅ ውስብስብ ሥራ
አይደለም፡፡ በእጃችን ላይ የተቀመጠ ቀላል ውሳኔን ነው የሚፈልገው፡፡




#babi

@amazing_generaton

#Yoseph

#መልካም_ምሽት_ይሁንልን
የትኛውም ያህል ራስን መውቀስ ያለፈውን ጊዜ አይቀይርም፣እና የትኛውም ያህል ጭንቀት የወደፊቱን ጊዜ አይቀይርም፡፡



#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
👉 አስተውል 👌👌
የዛሬው ማንነትህ የትላንት አስተሳሰብህ ውጤት ነው‼️‼️
ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ሐዘን፣ ማጣት፣ ድብርት፣ ብስጭት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ብቸኝነት……
ከነዚህ አንዱ እንኳን በኑሮህ ከገባ ህይወትህ ጎዶሎ ነው⁉️⁉️⁉️
በእርግጠኝነት ግን ህይወትህን ሠላም፣ ጤና፣ ደስታ፣ ፍቅር፣ ተስፋ፣ ስኬት…… የሞላበት ማድረግ ይቻላል‼️‼️‼️
አጋጣሚ የሚባል ነገር እንደሌለ
ልትረዳ ይገባል።
በዚህች ቅፅበት እንኳን ይህን
ፅሁፍ እያነበብክ ያለኸው በአጋጣሚ ይመስልሃል በፍፁም አይደለም ድብቁና ውስጣዊ ማንነትህ የልብህን ሀሳብ ለማስፈፀም ያለማቛረጥ ስለሚሰራ እንጂ።
"ሰው በልቡ እንዳሰበ እንደዚያው ነው"‼️ እንዲል
🗝 ያለምክንያት የምታየው፣ የምትሰማውና ወደ ህይወትህ የሚገባ አንዳችም ነገር የለም ‼️
በምንልክልህ መልዕክት አብረኸን ሁን የምትመኘውን ነገህን ዛሬ ላይ እንደምኞትህ ቅረፃት‼️

ጉዞህን ወደ ስኬት፣ ሠላም፣ጤና፣ ደስታ፣ ፍቅር፣ ባለፀግነት አድርግ

አስታውስ ህይወት ምርጫ ናት


#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
ሕሊና እንጂ መልክ አያስብም፡፡ አንደበት እንጂ መልክ አይናገርም፡፡
መልካምነት እንጂ መልክ ከሰው አያኖርም፡፡
ስነ ምግባር እንጂ መልክ አያስከብርም፡፡
እምነትና ፍቅር እንጂ መልክ ሞትን አያሻግርም፡፡ መልክ
የላይ ማንነትን እንጂ የውስጥ ሰብእናን አይገልጥም ፡፡
ፊት ቀልቶ ውስጥ ሊጠቁር፣ ውጪ አጊጦ ልብ ሊቆሽሽ ይችላል፡፡
እውነተኛ ፍቅር በአይን ሳይሆን በልብ ነው።




#babi

@amazing_generaton

#babi

#መልካም_ምሽት_ይሁንልን
ሰዎች ሲጀመር ስላንተ የሚያስቡት በጣም አልፎ አልፎ መሆኑን ብታውቅ ኖሮ ስለኔ ምን ያስባሉ? በሚል ጭንቀት ናላህን አታዞረውም ነበር።



#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
አስተዋይ ሁን፡፡አመስጋኝ ሁን፡፡አዎንታዊ አስተሳሰብ ይኑርህ፡፡እውነተኛ ሁን፡፡ደግ ሁን፡፡




#babi

@amazing_generaton

#Yoseph

#መልካም_ቀን_ይሁንልን
ልብህ የሚነግርህን ተከተል እንጂ አይኖችህን የሚነግሩህን አትከተል፡፡




#babi

@amazing_generaton

#Yoseph

#መልካም_ምሽት_ይሁንልን
መናገር ያለብህን በግዜው ተናገር። ማድረግ ያለብህን በግዜው አድርግ። ምክንያቱም ብዙ ነገሮች ሁለተኛ እድል አይሰጡም!!


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የሆሳዕና በዓል በቻናላችን ስም ተመኝተናል።


#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏

ሆሳዕና በአርያም
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም የጤና እንዲሆንላቹህ እንመኛለን

መልካም በዓል ለሁላችሁም

@amazing_generation


#Yoseph
መቼም ቢሆን ምንም አይነት አጋጣሚ ውስጥ ብትገባ ተስፋ አትቁረጥ። ቀጣዪ ቀን ላንተ የተሻለ እድል ይዞልህ ሊመጣ ይችላልና!!!



#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
ከዕለት ተዕለት ተግባርህ ውስጥ ምንም ነገር እስካልተቀየረ ድረስ በሂወትህ ለውጥ አጠብቅ:: ስኬት የለዕለት ተዕለት ተግባራት ውጤት ነው❗️❗️❗️



#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
ለመደሰት ትልቅ ነገር አትጠብቅ። በሂወትህ እያንዳንዷ ትንሽ በረከት ተደሰትባት!!!








#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
የሶቅራጠስ ጣፋጭና ወርቃማ አባባሎች: -

* ያልተፈተነ ሕይወት መኖር እርባና ቢስ ነው ።
* ልታስፈፅም የማትችለውን ትዕዛዝ አትዘዝ ።
* ራሱን በቅድሚያ ማንቀሳቀስ የቻለን ፣ ዓለምን እንዲያንቀሳቅስ ፍቀድለት ።
* እውነተኛ ጥበብ አለማወቅን ማወቅ ነው ።
* ብቸኛው ጥሩ ነገር ማወቅ ሲሆን ፣ ብቸኛው መጥፎ ነገር ደሞ መሀይምነት ነው ።
* ሐሰተኛ ቃላት በራሳቸው ብቻ ኃጢያት ሳይሆኑ ነፍስንም በሀጢያት ይመርዛሉ።
* በቅን ነት ስህተትህን የሚገልፁልህን እንጂ ቃልህንና ተግባርህን በሙሉ የሚያወድሱት ታማኝ አይምሰሉህ ።
* አንዳንዶች ለመኖር ሲበሉ ሌሎች ደሞ ለመብላት የሚኖሩ አሉ ።
* አላዋቂ መሆኔን በማወቄ ብልህ ነኝ።
* መልካም ሰውን በህይወትህ እያለም ሆነ ከሞተ በኋላ የሚጎዳው ነገር የለም።
* It is the richest who content with the least.
* ባለው ያልረካ የሚመኘውንም ቢያገኝም አይረካ ።
* ለራስህ ማሰብ ስትጀምር ራስህን ታገኘዋለህ።
* እውነተኛ ጥበብን የምናገኘው ስለሕይወት ፣ ስለአለምና
ስለራሳችን ብዙም እንደማናውቅ ስንገነዘብ ነው።
* በዚች ምድር ሁሉም ነገር ያልፋልና ስታገኝም ከልክ በላይ
አትፈንጥዝ ፣ ስታጣም አብዝተህ አትከፋ! ።
* ወደ ክብር የሚወስደው አቐራጩ መንገድ የምትመኘውን
ለመሆን መጣር ነው!።

____________________

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ

መልካም በዓል
🙏
#babi


@Amazing_Generation


#Yoseph
•ቤተሰቦችህ በምንም ነገር ልትተካቸዉ የማትችላቸዉ ልዩ ማንነቶችህ ናቸዉ፡፡

•የጤናህ ጉዳይ ከምንም ነገር በላይ ጠቃሚ ነዉ፡፡ የምትበላዉን ምግብ ምረጥ፣ ታትረህ ስራ፣ በህይወትህ አላማ ይኑርህ እንዲሁም ሃብትህን በብልሃት ያዘዉ፡፡

•ለራስህ ክብርና ስርአት አታመቻምች፡፡ ለማንም ሰዉ ብለህ የራስህን ክብር አትጣል፡፡ የራስህን መስመር አስምር፣ አይሆንም ማለትን ተማር ሲያስፈልግ ብቻ ማንነትህን ግለጽ፡፡

•የነፍሴ ክፋይ እና እዉነተኛ ፍቅር የሚባሉ የተቃራኒ ፆታ ግንኙነቶች በዘፈንናና በፊልም ታጅበዉ የሚኖሩ ነገር ግን ዉሸትና ግነት የሞላባቸዉ ሃሳባዊ ድርሰቶች መሆናቸዉን ተረዳ፡፡

•ከአምላክህ ቀጥሎ ለሕይወትህ ትኩረት መስጠት የምትችለዉ አንተ ራስህ መሆንህን እወቅ፡፡ ህይወትህን አትቀልድበት! መስራት ባለብህ ነገር ስራ..መዝናናት በሚኖርብህ ጊዜም እንዲሁ፡፡

•'አንዴና አንዴ' ብቻ እንደምትኖር አዉቀህ ጊዜህንና ጉልበትህን በማይጠቅም ቦታና ማንነት ዉስጥ አታባክነዉ፡፡


#babi

@amazing_generaton

#babi

#መልካም_ቀን_ይሁንልን
#በዙሪያህ_ያለው_ሁሉ_ጨለማ ከመሰለህ ወደ ቀልብህ ተመለስና እንደገና ተመልከት ምናልባት #ብርሀኑ_አንተ_ልትሆን_ትችላለህ




#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
በአንድ ትልቅ ባዛር ሱቅ ውስጥ እየተመላለስኩ እየገዛሁ ነበር ፣ አንድ ገንዘብ ተቀባይ ከአንድ ልጅ ጋር ሲነጋገር አየሁ ከ 5 ወይም ከ 6 ዓመት በላይ ሊሆን አይችልም ፡፡ ገንዘብ ተቀባዩ ይቅርታ አድርግልኝ ግን ይህንን አሻንጉሊት ለመግዛት በቂ ገንዘብ የለህም ፡፡ ከዚያ ትንሹ ልጅ ወደ እኔ ዞር ብሎ ጠየቀኝ ፣ አጎቴ ፣ በቂ ገንዘብ እንደሌለኝ እርግጠኛ ነህ?
የእርሱን ጥሬ ገንዘብ ቆጥሬ መለስኩ ፣ አሻንጉሊቴን ለመግዛት በቂ ገንዘብ እንደሌለህ ታውቃለህ ውዴ ፡፡ ትንሹ ልጅ አሁንም አሻንጉሊቱን በእጁ ይዞ ነበር ፡፡ በመጨረሻም ወደ እሱ ሄድኩኝ እናም ይህን አሻንጉሊት ለማን ሊሰጥ እንደፈለገ ጠየቅሁት ፡፡ እህቴ በጣም የምትወደው እና በጣም የምትፈልገው አሻንጉሊት ናት ፡፡ ለልደት ቀን ልሰጣት ፈለግሁ ፡፡ እዚያ ስትሄድ ለእህቴን እንድትሰጥልኝ አሻንጉሊቱን ለእናቴ መስጠት አለብኝ ፡፡ ይህን እያለ ዓይኖቹ በጣም አዘኑ ፡፡

እህቴ ከእግዚአብሄር ጋር ለመሆን ሄዳለች ፡፡ አባባ እማዬም በጣም በቅርቡ እግዚአብሔርን ማየት እንደምትችል ነግሮኛል ፣ ስለሆነም አሻንጉሊቱን እህቴ ጋር ልትወስድ ትችላለች ብዬ አሰብኩ ፡፡ ልቤ ሊቆም ተቃርቧል ፡፡ ትንሹ ልጅ ቀና ብሎ ወደ እኔ ተመለከተና ለአባዬ እማዬ እንዳትሄድ እንዲነግራት ነገርኩት ፡፡ ከገበያ ማዕከሉ እስክመለስ ድረስ እንድትጠብቀኝ እፈልጋለሁ ፡፡ ከዛም እሱ እየሳቀበት ያለበትን በጣም ጥሩ ፎቶ አሳየኝ ፡፡ ከዛ እህቴ እንዳትረሳኝ እናቴን ፎቶግራፌን ከእሷ ጋር ማንሳት እንደምፈልግ ነግሮኛል ፣ እናቴን እወዳታለሁ እና እሷም መሄድ የለባትም ብዬ ተመኘሁ ግን አባዬ ከእህቴ ጋር ለመሆን መሄድ አለባት አለኝ ፡፡

ከዚያ አሻንጉሊቱን በአሳዛኝ ዓይኖች እንደገና ተመለከተ ፣ በጣም በፀጥታ ፡፡ በፍጥነት የኪስ ቦርሳዬን ዘርግቼ ለልጁ ፡፡ ለአሻንጉሊት የሚሆን በቂ ገንዘብ ካለህ እንደገና ደግመን እንፈትሽ አልኩት እሱ እሺ እኔ በቂ አለኝ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ ከእሱ እይታ ውጭ ከገንዘቤ የተወሰነውን አክዬ እሱን መቁጠር ጀመርን ፡፡ ለአሻንጉሊት እና የተወሰነ ትርፍ ገንዘብ ነበር ፡፡
ትንሹ ልጅ ፣ በቂ ገንዘብ ስለሰጠኝ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ! ከዚያ ወደ እኔ ተመለከተ እና አክሎ ፣ እናቴ ለእህቴ እንድትሰጥ ይህንን አሻንጉሊት ለመግዛት በቂ ገንዘብ ማግኘቴን ለማረጋገጥ ለእግዚአብሄር ከመተኛቴ በፊት ትናንት ማታ ጠየኩ ፡፡ ሰማኝ! እንዲሁም ለእናቴ ነጭ ጽጌረዳ ለመግዛት በቂ ገንዘብ ማግኘት ፈልጌ ነበር ፣ ግን እግዚአብሔርን ብዙ ለመጠየቅ አልደፈርኩም ፡፡ ግን አሻንጉሊቱን እና ነጭ ጽጌረዳውን ለመግዛት በቂ ሰጠኝ ፡፡ እናቴ ነጭ ጽጌረዳዎችን ትወዳለች ፡፡

ከጀመርኩበት ጊዜ በተለየ ሁኔታ ገበያዬን ጨረስኩ ፡፡ ትንሹን ልጅ ከአእምሮዬ ማውጣት አልቻልኩም ፡፡ ከዛም ከሁለት ቀናት በፊት በአካባቢው አንዲት የዜና ወረቀት ላይ ትዝ ይለኛል ፣ በጭነት መኪና ውስጥ አንድ ሰካራም ሰው ጠቅሷል ፣ እሱም ወጣት ሴት እና ትንሽ ልጅ የተጫነችበትን መኪና ይመታል ፡፡ ትንሻ ልጃገረድ ወዲያውኑ ሞተች እናቱ በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ተኝታለች ፡፡

ወጣቷ ከኮማ ማገገም ስለማትችል ቤተሰቡ በህይወት ማቆያ ማሽን ላይ መሰኪያውን መሳብ መወሰን ነበረባቸው ፡፡ ይህ የትንሹ ልጅ ቤተሰብ ነበር? ከትንሽ ልጅ ጋር ከተገናኘን ከሁለት ቀናት በኋላ ወጣቱ ሴት እንደሞተች በዜና ወረቀቱ ላይ አነበብኩ ፡፡ እራሴን ማቆም አልቻልኩም ፡፡ ብዙ ነጭ ጽጌረዳዎችን ገዝቼ ከቀብርዋ በፊት ሰዎች ለማየት እና የመጨረሻ ምኞቶችን ለማድረግ የወጣት ሴት አስከሬን ወደ ተጋለጠበት የቀብር ስፍራ ሄድኩ ፡፡ እዚያ ነበረች ፣ በሬሳ ሣጥኗ ውስጥ በትንሽ ነጭ ፎቶ እና አሻንጉሊት በደረቷ ላይ ከተጫነች ጋር ቆንጆ ነጭ ጽጌረዳ በእጇ ይዛለች ህይወቴ ለዘላለም እንደተለወጠ እየተሰማኝ በእንባ እየተመለከትኩ ቦታውን ለቅቄ ወጣሁ ...

ትንሹ ልጅ ለእናቱ እና ለእህቱ የነበረው ፍቅር እስከ ዛሬ ድረስ መገመት ከባድ ነው ፡፡ እና በአንድ ሰከንድ ክፍል ውስጥ አንድ ሰካራም ሾፌር ይህን ሁሉ ወሰደበት

Moral of the story -ሕይወትን ማክበር ፣ ደንቦችን መከተል እና ባለመታዘዝ ፡፡ ሌላ ሰው ስህተቶችዎን እንዲከፍል እና እንዲሸከም አታድርጉ ፡፡ ሌሎችን በጭራሽ ሊተካ የማይችል ነገርን የሚያስከፍሉ ስህተቶችን አትሥሩ ፡፡ ሁል ጊዜ የእርዳታ እጅ ይኑረን እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እና ለሐዘን እጇችን ይርዘም ።
#babi

@amazing_generation
መልካም ቀን
#Yoseph


💚💛❤️