ድንቅ ነን🎯Amazing Generation
100 subscribers
89 photos
13 videos
3 files
15 links
" #ደስተኛ

#ስኬታማ

#አስተዋይ
ወደ መሆን የሚወስድ ህብረት!!"

Contact
@Mikyas_Feleke
Download Telegram
chology
#በራስ_መተማመንን (Self Confidence)
ለማሳደግ የሚረዱ አስር ሙያዊ ምክሮች
ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ
ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ
እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው።
ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ
ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ
ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው
ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ።
1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)።
የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ
አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት
የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም
አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ
ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን
እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም
በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት
ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና
ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ
ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ።
2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)።
አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች
ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም
ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ
ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው
በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ።
3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)።
በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ
መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች
የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም
በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ
ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች
ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል።
4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial)
ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ።
ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም
ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ።
5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude)
ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት
ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ
እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ። ምን ያህል እርቀት እንደመጡም ለመገንዘብ ይረዳዎታል፣ ወደ
ቀጣዩ ደረጃ ወደ ስኬት ለመሄድም በእጅጉ ያነሳሳዎታል።
6. ለሌሎች ሰዎች ስለ ጥሩ ስራቸው አድናቆትን ይለግሱ (Complement others)።
ስለራሳችን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ማጣጣል እና በጀርባቸው ላይ
መጥፎ ነገር መሸረብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለማቋረጥ ሌሎች ሰዎችን
የማመስገን ልማድ ይኑርዎት። ከሰዎች ጀርባ መጥፎ ነገር መመኘት ወይም መጠንሰስን
አስወግደው በሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አድናቆትን ለመግለፅ ይሞክሩ። በሂደቱ ውስጥም በጣም
ይወደዳሉ፣ በዚህም በራስ መተማመን ይገነባሉ ። በሌሎች ውስጥ ምርጡን በመፈለግና
በመመስከር በተዘዋዋሪ ምርጡን ወደ ራስዎ ዘንድም ያመጣሉ።
7. ከፊት ረድፍ ይቀመጡ (Sit in the front row)
ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ጽ / ቤቶች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ብዙ ሰዎች መጨረሻ
ለመቀመጥ ይጥራሉ። ምክንያቱም በቀላሉ መታየቱ ያስፈራቸዋል። ይህም በራስ መተማመን
ማጣትን ያሳያል። በፊተኛው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዎስኑ ይህንን ያለፈቃድ የሚመጣ ፍርሃት
አሸንፈው በራስ መተማመንዎን መገንባት ይችላሉ። በተጨማሪም ከዋናው ፊት ለፊት
ለሚነጋገሩ ሰዎች በይበልጥ ግልጽ ይሆናሉ።
8. ሃሳብዎን ይግለፁ (Speak up)
በቡድን ውይይቶች ወይም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሁኔታ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን
ከመግለፅ ይቆጠባሉ። ምክንያቱም ሰዎች ከንግግራቸው ተነስተው እንዳይገምቷቸው ስለሚፈሩ
ነው። ይህ ፍርሃት ትክክል አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ከምናስበው ይልቅ የሰውን ሃሳብ
የመቀበል ፍላጎት አላቸው። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ፍራቻ የተጠቁ ናቸው።
በእያንዳንዱ የቡድን ውይይት ቢያንስ አንድ ጊዜ ለመናገር ጥረት በማድረግ የተሻለ የህዝብ
ንግግር ክህሎት እንዲያዳብሩ ፣ ይበልጥ በራስ መተማመን እንዲኖርዎት እና በእኩዮችዎ ዘንድ
መሪነትን እና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ያደርግዎታል።
9. ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልምድዎ ይሁን (Work out)
ልክ እንደ አለባበስ አይነት፣ አካላዊ ብቃት በራስ መተማመን ዘንድ ከፍተኛ ሚና አለው።
ቅርጽዎ እንደተበላሸ ከተሰማዎት በሌሎች ዘንድ ዝቅ ተደርጎ የመታየት እና ሌሎችን መማረክ
አለመቻል ስሜት ይሰማዎታል። አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረግ አካላዊ ገጽታዎን ያሻሽላሉ፣
ኃይልን ያገኛሉ፣ ለአዎንታዊ ስራም ይነሳሳሉ።
10. የሚያደርጉት አስተዋፅዎ ላይ ያተኩሩ (Focus on contribution)
ብዙውን ጊዜ እኛ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንጂ የሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና በሌሎች ላይ
ስለሚመጣው ጥሩ ለውጥ አናስብም። ስለራስዎ ማሰብ ካቆሙ እና ለተቀረው ዓለም ላይ
ለውጥ እንዲመጣ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ (መዋጮ) ላይ ካተኮሩ፣ ያሉብዎት ጉድለቶች
አያስጨንቁዎትም። ይህ በራስ መተማመንን ይጨምራል እናም በከፍተኛ ተነሳሽነት እና
ውጤታማነት እንዲሳተፉ ያስችልዎታል። ለዓለም ጥሩ እያደረጉ በሄዱ መጠን የግል ስኬት እና
እውቅናንም እየተጎናፀፉ ይሄዳሉ።



#babi

@amazing_generation

#babi

ሰናይ ምሽት🙏🏿🙏🏿
ማንም ሰዉ በፍፁም መፍራትህን እንዳያዉቅ! ተኩላዎች መፍራትህን ከሰዉነትህ እንቅስቃሴ ያዉቃሉ፡፡ ምንም ያህል ብትፈራም፣ ማንም ሰዉ ፊት እንደፈራህ ሆነህ አትቁም! ቆፍጠን ብለህ ጠንከር ብለህ ድምፅህን ረጋ አድርገህ አይንህን ቀስ አድርገህ አንቀሳቅስ፡፡

• ሰዎችን ትንሽ አርቃቸዉ፡፡ ማንንም አትመን፡፡ ወደራስህ ህይወት በጣም ካስጠጋሃቸዉ ማንነትህን በደንብ አብጠርጥረዉ ስለሚያዉቁ መናቅ ይጀምራሉ፡፡

ስለዚህ መስመር አስምር...ሰዎች ስላንተ ትንሽ ብቻ ካወቁ አክብረዉህ ይኖራሉ፡፡ ስላንተ ያላቸዉ መረጃ አነስተኛ ሲሆን የቀረዉን ነገር በራሳቸዉ ሃሳብ ዉስጥ በሚፈጥሯቸዉ ነገሮች ሲፈልጉ ይሙሉት፡፡

• ወሳኝ ከምትለዉ ሰዉ በስተቀር ያገኘኸዉን ሁሉ ዝም ብለህ ወደቤትህ አትዉሰድ፡፡ ሰዎች በተፈጥሮ ቤትህን ሲያዉቁ አንተነትህን በቀላሉ መግለፅ አይከብዳቸዉም፡፡ ምን አልባትም ሲያወሩ ትደርስባቸዉ ይሆናል!

• ስለዚህ ሰዎችን በዉጪ አግኝ... ቢዝነስም ይሁን ሌላ ማንኛዉም ነገር በዉጪ ጨርስ፡፡ ከምንም በላይ ለራስህ ዋጋ ስጥ! ለማንም ለምንም በቀላሉ የምትገመት ሰዉ አትሁን ይኸዉ ነዉ!

• ሰዎች በብዙ ነገር ማንነትህን ይፈታተኑታል፡፡ ስለዚህ 'ለምን ተፈተንኩ?'ብለህ አትቆጣ፡፡አትናደድ፣ሃይልህን አትጨርስ...ብቻ ለሚመጣዉ ነገር እራስህን አዘጋጅ፡፡

አንዳንድ ነገሮች ፈፅመህ ካልጠበከዉ መንገድ እየጎረፈ ሲመጣ ታያለህ፡፡የዛኔ እንደምንም ብለህ እራስህን አረጋጋ፡፡ ከአምስትና አስር አመት በኋላ ያለህበት ነገር ምን ያህል ተፅእኖ ያሳድርብሃል? ብዙ ነገሮች ለጊዜዉ ብቻ የሚያስቆጡ ስለሆኑ በእርጋታ አሳልፋቸዉ፡፡

• ሁል ጊዜ ለሰዎች ክብር ይኑርህ፡፡ቢያጠቁህም እነሱን ለማጥቃት መልሰህ ጦርነት አትክፈት...ባህሪያቸዉን ወይም ከላይ ያለዉን ማንነታቸዉን አታጥቃዉ ነገር ግን የዉስጥ ሃሳባቸዉን አትቀበል፡፡

ዋናዉን የልብ ፍላጎታቸዉን ብቻ ቀይ ስጠዉ! ይህን የምታደርገዉ ግን በተረጋጋ ማንነት ዉስጥ መሆን ቢችል ጥሩ ነዉ፤ ነገሮችን ከግራም ከቀኝም የማየት አቅም ስለሚኖርህ የበሰለ ዉሳኔ መወሰን አያቅትህም፡፡

• ከማን ጋር እንደምትዋጋ እወቅ፡፡ ልታሸንፍ የምትችለዉን ጦርነት ብትመርጥ ይሻልሃል ያለበለዚያ ብዙ ነገር ይበለሻሻል፡፡


ምሳሌ ልስጥህ፡ አንድ ጓደኛዬ ከሴት ጓደኛዉ ጋር ተጣላና መደባደብ ጀመረ፡፡ ከሁለተኛ ፎቅ ላይ እቃዉን ሁሉ እያወጣች መወርወር ጀመረች፡፡ፊቱን ሞነጫጭራ ሞነጫጭራ አዲሱን የቀለበት መንገድ ዲዛይን ፊቱ ላይ ሳለችዉ፡፡ እሱም አልተዉም ብሎ ደበደባት፡፡


#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
አነቃቂ ጥቅሶች
📖ሰዎች ምክንያታዊ ያልሆኑና ራስ ወዳድ
ናቸው።ለማንኛውም ሰውን ውደድ
,
📖ጥሩ ብትሰራ ሰዎች ስውር ፍላጎት ስላለው ነው
ይሉሀል።ለማንኛውም ጥሩ ሁን
,
📖ስኬታማ ብትሆን የውሸት ጓደኛና የእውነት ጠላት
ታፈራለህ።ለማንኛውም ስኬታማ ሁን
,
📖ዛሬ የሰራኸው ጥሩ ነገር ነገ
ይረሳብሀል።ለማንኛውም ጥሩ ሁን
,
📖ሀቀኛና የዋህ ብትሆን ደካማ ጎንህን
ሊጠቀሙብህ ይፈልጋሉ። ለማንኛውም ሀቀኛና
የዋህ ሁን
,
📖ለአመታት የገነባኸው በአንድ ለሊት ሊናድ
ይችላል ።ለማንኛውም ገንባ
,
📖ሰዎች የእውነት እርዳታህ ያስፈልጋቸው ይሆናል
ነገር ግን በምላሹ ሊያጠቁህ
ይፈልጋሉ።ለማንኛውም እርዳ
,
📖ያለህን ምርጡን ነገር ለአለም ስጥ እናም
ጀርባህን ልትመታ ትችላለህ።ለማንኛውም ምርጡን
ነገርህን ለአለም ስጥ




#SHARE


#babi

@amazing_generati
on

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
#የዛሬ_ሳይኮዎ_መልክት
🕊#የወፏ_ምክር_[ወርቆቻችን _ወዴት_አሉ?]
🕊እንዲህ የሚባል የሀገራችን ተረት አለ። አንድ ሰው አንዲት ለዓይን በጣም የምታምር ወፍ ይይዝና በመዳፉ ጨምቆ ሊገድላት ሲል ከመሞቷ በፊት አንድ ወይም ሁለት ቃላት ትናገር ዘንድ እንዲፈቅድላት ጠየቀችው፡፡
እንዲህም አለችው(በወፍኛ ቋንቋ) ... “እባክህ ከመሞቴ በፊት ሦስት ጠቃሚ ምክሮችን ልሰጥህ እፈልጋለሁና አዳምጠኝ"፡፡
ሰውየውም ለማንኛውም ምክሩን መስማት አይከፋም በሚል እሽ አላት። እንዲህም አለችው

🕊."የመጀመሪያው ምክር ፦ #በእጅህ_ያለውን_ነገር_አትልቀቅ ፣ ምክንያቱም መልሰህ ላታገኘው ትችላለህና፡፡

🕊ሁለተኛው ምክር ፦ #ስለሆነውና_ስላለፈው_ነገር_ሁሉ በመበሳጨት_የነገ ሕይወትህን_ አታበላሽ፡፡”

🕊"ሦስተኛውስ?" አላት ሰውየው። ወፏም መለሰች ፦ “ሦስተኛው ምክር ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ካለቀቅኸኝ አልነግርህም፡፡” አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ሰውየው ሦስተኛውን ምክር ለመስማት በጣም ጓጉቶ ስለነበረ ወፏን ለቀቃት። ወፍዬም ብርርር ብላ ከአንድ ዛፍ ላይ ወጣችና እንዲህ አለችው።

🕊“በመጀመሪያ ምንድን ነበር ያልኩህ? ታስታውሳለህ?”
እርሱም “በእጅህ ያለውን ነገር አትልቀቅ ነበር ያልሺኝ፡፡” አላት፡፡ “ሁለተኛውስ?” ወፏ ጥያቄዋን ቀጠለች። “ስላለፈው ነገር በመቆጨት የነገ ሕይወትህን አታበላሽ ነው ያልሽኝ” አለ ሰውዬው።

🕊ወፊቱም እንዲህ አለችው “አየህ
ወዳጄ... የመከርሁህን ምክር አልተገበርኸውም። ለምን አታስተውልም? ምክርን ካልተገበሩት መስማት ምን ይጠቅማል? ገና ከአሁኑ ምክሬን ችላ ብለህ ባትለቀኝ ኖሮ ከሆዴ ውስጥ ለልጅ ልጆችህ የሚሆን ወርቅ ታገኝ ነበር፡፡ ግን 'በእጅህ ያለውን አትልቀቅ' የሚለውን ምክሬን ስላልተገበርኸው አመለጠህ፡፡

🕊አሁንም የሚጠቅምህ ሁለተኛውን ምክሬን መተግበር ብቻ ነው። ...ባለፈውና ባመለጠህ ዕድል እየተናደድህ የወደፊቱን ሕይወትህን አታበላሽ። እኔን ደግመህ እጅህ ለማስገባት እንደኔ መብረር ይጠበቅብሃል። መብረር ስለማትችልም አትይዘኝም።”....
ሰውዬው በጣም አዝኖ ቢያንስ ሦስተኛውን ምክር ለመናት። በመጨረሻም ወፏ እንዲህ አለችው።

🕊“ሦስተኛው ምክር የአንደኛውና የሁለተኛው ምክር ድምር ነው፡፡ አሁንም በእጅህ ያሉ ብዙ ወርቆች ስላሉ እንዳትጥላቸው አጥብቀህ ያዝ እንጅ ስላጣኸው ነገር በመበሳጨት ራስህን አታሳምም... አሁን እኔን እርሳና የእጅህን ወርቆች ፈልግ.... ደህና ሁን፡፡"
.............................
🕊የወፏ ምክር ሁላችንንም ይመለከታል። በተለይ ያለንበት ወቅት የጠቢባኑን ምክር ልናዳምጥበትም ልንተገብርበትም የሚገባ ነው። እጅግ ብዙ በእጃችን ላይ ያሉ ወርቆችን እንደዋዛ እየጣን::🕊🕊🕊🕊🕊🕊
#መልካም_ምሽት_ይሁንልን


#Babi



@amazing_generation



#Yoseph
እምነት ይኑርህ

በነገ ላይ ትልቅ እምነት ይኑርህ፣ ሁሉም ነገር የሚሳካልህ ከሰዎች በመብለጥህ አይደለም፣ እየወደክም እነፈየተነሳህም ባለማቀቋረጥህ እና በመፅናትህ ነው።

ወዳጆቼ ወደ ስኬታችሁ የምትደርሱት ባለመቆማችሁ ነው፣ ስለዚህ ወደፊት እንድትጓዙ ብርታት የሚሆናችሁ እምነት ይኑራችሁ!!

@Amazing_Generation
•አንዳንድ ሰዎች የተለየ የህይወት ጫወታ ይጫወታሉ፤ ሁሌም በህብረተሰቡ ዉስጥ የሚነገረን ሰዉ ስኬታማ ለመሆን ተምሮ ፡ዲግሪ ይዞ ፡አግብቶ ጥሩ ስራ ይዞ መኖር እንዳለበት ነዉ፡፡ ግን ህይወትን በሌላ ትምህርት፡ በሌላ ዲግሪ፡ በሌላ ስራ ይተዋወቋታል

• የሆነ ነገር ለማግኘት በፈለክ ቁጥር የበለጠ እየራቀህ ይሄዳል፡፡ በህይወቴ ከተረዳሁት ነገር ዉስጥ የፈለኩት ነገር ጥሎኝ ሲሄድ አይቻለሁ፡፡

• ሰዎች ህይወታቸዉን ሊያደላደሉ ሲጥሩ አያለሁ፡፡ ቦታ ካስያዙት በኋላ ሁሉም ነገር ወደነሱ እንደሚመጣ ያስባሉ ነገር ግን ይህ በገሃዱ አለም የማይሆን ነገር ነዉ፡፡

• ሰዎች የሚያወሩትን ሳይሆን የሚያደርጉትን አስተዉል፡፡ ሰዎች አቁስለዉኛል ምክንያቱም ተግባራቸዉን አተኩሬ ጊዜ ስላልሰጠሁት ዉስጤን አደሙት!

• ከሚሰጡት በላይ የሚቀበሉ ሰዎችን አትታገሳቸዉ፡፡ ከሚጠቅሙበት ነገር በበለጠ የሚጎዱበት ማንነታቸዉ የጎላ ሰዎችን ከህይወትህ ካላወጣሃቸዉ ውስጥህን እንደ'ብል'ይበሉታል

• ብዙ መሰናክሎች እራስህ የምትፈጥራቸዉ ናቸዉ፡፡ ማህበረሰቡ፣ ጓደኞቼ ወይም ቤተሰቦቼ መሰናክል እንደሆኑብኝ አምን ነበር ግን በመስታወት የማየዉ ማንነቴ እርስ በእርሱ ተሰነካክሏል፡፡

• ህይወት አጭር ናት፡፡ ሞት ደግሞ የማይቀር ጉዳይ ነዉ፡፡ ይህን ማሰብ ላትፈልግ ትችላለህ ግን አንድ ቀን ትሞታለህ፡፡ አንተ ብቻ ሳትሆን የምታየዉ ሰዉ ሁሉ ቀኑን ጠብቆ ይሞታል፡፡ ስለዚህ ሕይወትህን እስከ እንጥፍጣፊዋ ድረስ ኑርባት!

• ህይወትህ የሚወሰነዉ ትኩረት በሰጠኸዉ ነገር ላይ ነዉ፡፡ ይህ አለም ብዙ ክፋትና ሰይጣናዊነት የተንሰራፋበት ቦታ ነዉ፡፡

• ደስ የሚል ህይወት ከፈለክ የሚያምረዉና መልካም የሆነዉ ነገር ላይ አተኩር፡፡ አስጠሊታ ህይወት ከፈለክ ደግሞ በተቃራኒዉ የአለም ጨለማዉ ባህሪ ላይ አተኩር፡፡ ይህ ያንተ ምርጫ ይሆናል!

• ሁሉም ሰዉ ዉሸታም ነዉ፡፡ ሰዉ የየራሱ ምክንያት ቢኖረዉም አንዳንዱ ሌላዉ እንዳይጎዳ ፣አንዳንዱ ለማጭበርበር ሌላዉ ደግሞ እራሱን ለመሸወድ ይዋሻል




#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
💦እራስን መሆን ማለት እራሳችንን ከማንም ከምንም ጋር አለማመሳሰል።
እራስን መሆን ቀላል ነገር አይደለም፤ ነገር ግን ሌሎችን እንደመምሰል አይከብድም።

ሁላችንም ልዩ እንድንሆን ባይፈልግ ኖር
አምላክ ተመሳሳይ አድርጎ በፈጠረን ነበር።
ነገር ግን እኛን የሚመስል ፈጽሞ
አይደገምም።

ይህ #ልዩነታችንን_ማህበረሰብ_ወይም_
ልማድ_እየፈተነብን_ከብዙሃኑ_ጋር_ተመሳስለን_
ለመኖር_እራሳችንን_እናስጨንቀዋለን_ልነትን
በእጅጉ_እንፈራዋለን_ምክንያቱም_ተቀባይነት_እንድናገኝ_ስንል።
ያንተን ሳቅ ማንም አይስቀውም፤
ያንትን ንግግር ማንም ሊናገረው አይችልም፤
ያንተን ህልም ማንም ሊፈታው አይችልም፤
ያንተን ምግባር እንዳንተ የሚተገብር ማንምአይፈጠርም።

# ሌላውን_ለመምሰል_አትጣር ፤_ምንም_ያህል_ብናስመስል_ሌላውን_መሆን_አንችልም።
ሌሎችም እኛን መሆን አይቻላቸውም።
ሁሉም የሚያምርበት በልኩ የተሰፋውን
ሲለብስ ነው።
ሌላውን ለመምሰል መሞከር በሌላው ልክ የተሰፋን ልብስ ለብሰን እንዲያምርብን መጠበቅ
ነው።
# ከምንም_በላይ_ውበት_የሚገለጸው_
እራስን_በመሆን_ነው ።
📒📘📖📒📘📖📒📘📖📒📘📖📒
ለሰው ልጅ ስብዐናው መሰረቱ ነው ድጋፉችሁ አይለየን 👍


#babi

@amazing_generaton

#babi

#መልካም_ምሽት_ይሁንልን
#ጠቃሚ_የህይወት_ስንቅ
👉ሁላችንም የቻልነውን በመቋጠር እንለወጥ

📗ያለፈ ነገር አይቀዪርም ፣ ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው ፣ ካለፈው ነገርህ ተማር
እንጅ በፍፁም አታማርር ፣ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም
የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነትአይገልፅም ፣
ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው ፣ መልካም አድርግ ሌላውን
እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣
ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና ለሁሉም ጊዜ አለው ።

📒መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል ጊዜህ ሲደርስ
መኪናዎች ወይም ‘ፕሌን’ ትገዛለህ ፣ ያውም
ለመኖር አስፈላጊ
ከሆነ ፣ ደግሞም እንዴት እንደገዛው የት
ታውቃለህ ?
ተወው በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው ።
በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ
እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣
ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት
አይደለም ። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ
ከተጎዳው ሰው ጋ
ሁን ፣ አስተውል ።

📕ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣
በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውና
የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት
ስራ መስራት
ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤
አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው
፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ አንተም ጥቂትም ብትሆን
ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ ቁፋሮ ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ ምንድነው? ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው ፣ የድንጋይ ቅርፅ (ኮብልስቶን)
እየሰሩ መኖር ነው ፣ ምንድነው ??? እባክህ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣
በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው ።
:
📗አስተውል ፣ መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ
ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን አይደለም ፣ ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም
የመቀዪር ብቃት አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ
ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣አስተውል ።
መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር
እንዲገጥምህ ማመቻቸት
ነው ፣ መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም ።
:
📒የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ
ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን
ያጭዳል" የሚለውን ስታውስ ፣
ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣
ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ
አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም
የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ ።

📕ለራስህ ስትል መልካም ሁን ፣ በጎውንም አስብ።
ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም ።
አትፍረድ ፣ የመፍረድ ሃላፊነት በፍፁም የለህም ። ፍርድ የፈጣሪ ነው፣ ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል ፣ ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ
ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት ። የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል ።
:
📗ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣ አበረታታው ፣ እንደማይጠቅም አትንገረው ፣
ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ
አትሁን ። መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ ነው ። መልካም ጓደኛ ፣ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል ታድለሃል ። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ
መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ።

📒ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትን ፣ ሀዘንን
ያስከትላል ።
ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ ፣
መመለስ በማትችለው
ነገር ላይ አትወጠር ፣ የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ
። አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ ።

📕 ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር ።ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው ፣ "ያስከፍላል"ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ
። ደግ ሁኑ ፣ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ
በረከታቸው ሰላማቸው ልክ የለውም ።

📗ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ ፣ ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ
ሲርቅ ወይም
ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል ። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ
ናቸው ። በራስህ በአፈጣጠርህ ደስ ይበልህ ፣ውለህ
በመግባትህ ደስ ይበልህ ። በአለህ ትንሽ ነገር ደስ ይበልህ ።

📒ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ
አይኑርህ ። በመውደድ የተጠመደ ሰው
ለመጥላት ጊዜ የለውም።
እድሜህን በተመለከተ ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው ።
ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳዪኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው።
:
📕የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ
ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ።
ሰላምና ጤና ፣ ከመልካም አስተሳሰብና በጎ
ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ።




#babi

@amazing_generaton

#Yoseph



#መልካም_ምሽት_ይሁንልን
💧ህይወት ማለት...
.
ሕይወት ውጫዊ ሳትሆን ውስጣዊ ነች
የአንተ ዓለም የሚቀለሰው በምታስበው ነገር ነው፡፡በሌላ አነጋገር የፈጠርካት ዓለም በአእምሮ ውስጥ ያለው እምነት እና አመለካከት ውጤት ነች፡፡አታካች እና ፈተናው የበዛ የሕይወት
ውጣ ውረድ ውስጥ ከተዘፈቅክ መንስኤውን ለማወቅ ወደ ሌላ
ማማተር አይኖርብህም፡፡የገዛ አእምሮህ ላይ ጣትህን ቀስር፡፡
ወስጥህ በነውጥ ማዕበል ከፍ ዝቅ ባለ ቁጥር ውጪውም
አብሮ ከፍ ዝቅ ይላል፡፡ይህ የተራቀቀ ፍልስፍና አይደለም፡፡ደረቅ
ሀቅ እንጂ፡፡ በአአምሮህ ውስጠ ያለው እምነት ውጪውን አለም
አጥለልህ ፍርድ እንድትሰጥ ይረዳሃል ፡፡ቀይ መነጽር ካጠለቅ
ዓለም ሁሉ ቀይ በቀይ ይሆንብሃል፡፡
ቀለል ያለ ያልተወሳሰብ ሕይወት ለመምራት ከፈለግክ ምስጢሩ
ቅርብህ ነው ያለው፡፡የነውጥ ማዕከል የሆነውን አእምሮህን
በሚከተሉት ስምነት ነጥቦች አደብ ማስገዛት ጀምር፣

1. የሰለጠንከበትን ሐሳብ አጢን፡በአካባቢህ እና በማኅብረሰቡ
በተጫኑብህ አስተሳሰቦች ላይ ክፉኛ አትጣበቅ፡፡

2. ጨለምተኝነትን ከአእምሮህ ውስጥ ለአንዴ እና ለመጨረሻ
ጊዜ መንግለህ ጣለው፡የአእምሮህን ቅብዝብዝነት ፈር ማስያዝ
በቻልክበት ቅጽበት ጨለምተኝነት ከላይህ ላይ እንደጉም በኖ
ይጠፋል፡፡

3. ከሐሳብ ጋር ያለህን ቁርኝት ቁረጥ፡ከአልባሌ ሐሳቦች ጋር
ያለህን ዝምድና ማላላት ስትጀምር ሰላም እና ደስታ ወደእንተ
መፍሰሳቸውን ይቀጥላሉ፡፡
4. ቀለል ያለ ሕይውት ከአእምሮ ንፍቀ ክበብ ውጪ ነው
የሚፈጠረው፡ለነገሮች ደረጃ እያወጣ አበሳችንን የሚያስቆጥረን
አእምሮ ቀምበሩ ሲሰበር መንገዱ ሁሉ የተቀና፣ሁሉም ነገር
አልጋ በአልጋ ይሆንልናል፡፡

5. አሁንን ኑር፡እንደፔንዱለም እየተወዛወዝክ መናኛ ሐሳቦች
ላይ ከመባከን ሰልሰህ ወደ እውነተኛው የነፃነት ካምፕ፣ ወደ
የአሁን ቅጽበት ፊትህን መልስ፡፡

6. በአሁን ቅጽበት ውስጥ ሕይወት ገራገር እና ብሩህ ነች፡
የሕይወት ገራምነት የሚጋነነው በእዚህ ቅጽበት ውስጥ ብቻ
ነው፡፡

7. ሕይወትህን ቀላል ለማድረግ ደጋ መውጣት ቆላ መውረድ
አይጠበቅብህም፡ምንም አይነት ምትሃት ወይም ጥልቅ ፍልስፍና
አይሰፈልግህም፣ዝግጁ ስትሆኑ ሁሉም ነገር ይቀናል፡፡

8. በሕይወትህ ውስጥ ያጋጠሙህ አስከፊ ሁኔታዎች እና
አእምሮህ የማይነጣጠሉ ባልንጃራዎች ናቸው፡ ከአስከፊው
የሕይወት ገጽታ በላይ ለመሆን አእምሮህን እንደአሻህ
የምትናደበትን ልጓም ጨብጥ፡፡
በአሁን ቅጽበት ላይ እንኑር፡፡ይኽ የትምህርት ደረጃን፣የአእምሮ
ምጥቀትን፣የሃብት መጠንን
የሚጠይቅ ውስብስብ ሥራ
አይደለም፡፡ በእጃችን ላይ የተቀመጠ ቀላል ውሳኔን ነው የሚፈልገው፡፡




#babi

@amazing_generaton

#Yoseph

#መልካም_ምሽት_ይሁንልን
የትኛውም ያህል ራስን መውቀስ ያለፈውን ጊዜ አይቀይርም፣እና የትኛውም ያህል ጭንቀት የወደፊቱን ጊዜ አይቀይርም፡፡



#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
👉 አስተውል 👌👌
የዛሬው ማንነትህ የትላንት አስተሳሰብህ ውጤት ነው‼️‼️
ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ሐዘን፣ ማጣት፣ ድብርት፣ ብስጭት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ብቸኝነት……
ከነዚህ አንዱ እንኳን በኑሮህ ከገባ ህይወትህ ጎዶሎ ነው⁉️⁉️⁉️
በእርግጠኝነት ግን ህይወትህን ሠላም፣ ጤና፣ ደስታ፣ ፍቅር፣ ተስፋ፣ ስኬት…… የሞላበት ማድረግ ይቻላል‼️‼️‼️
አጋጣሚ የሚባል ነገር እንደሌለ
ልትረዳ ይገባል።
በዚህች ቅፅበት እንኳን ይህን
ፅሁፍ እያነበብክ ያለኸው በአጋጣሚ ይመስልሃል በፍፁም አይደለም ድብቁና ውስጣዊ ማንነትህ የልብህን ሀሳብ ለማስፈፀም ያለማቛረጥ ስለሚሰራ እንጂ።
"ሰው በልቡ እንዳሰበ እንደዚያው ነው"‼️ እንዲል
🗝 ያለምክንያት የምታየው፣ የምትሰማውና ወደ ህይወትህ የሚገባ አንዳችም ነገር የለም ‼️
በምንልክልህ መልዕክት አብረኸን ሁን የምትመኘውን ነገህን ዛሬ ላይ እንደምኞትህ ቅረፃት‼️

ጉዞህን ወደ ስኬት፣ ሠላም፣ጤና፣ ደስታ፣ ፍቅር፣ ባለፀግነት አድርግ

አስታውስ ህይወት ምርጫ ናት


#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
ሕሊና እንጂ መልክ አያስብም፡፡ አንደበት እንጂ መልክ አይናገርም፡፡
መልካምነት እንጂ መልክ ከሰው አያኖርም፡፡
ስነ ምግባር እንጂ መልክ አያስከብርም፡፡
እምነትና ፍቅር እንጂ መልክ ሞትን አያሻግርም፡፡ መልክ
የላይ ማንነትን እንጂ የውስጥ ሰብእናን አይገልጥም ፡፡
ፊት ቀልቶ ውስጥ ሊጠቁር፣ ውጪ አጊጦ ልብ ሊቆሽሽ ይችላል፡፡
እውነተኛ ፍቅር በአይን ሳይሆን በልብ ነው።




#babi

@amazing_generaton

#babi

#መልካም_ምሽት_ይሁንልን
ሰዎች ሲጀመር ስላንተ የሚያስቡት በጣም አልፎ አልፎ መሆኑን ብታውቅ ኖሮ ስለኔ ምን ያስባሉ? በሚል ጭንቀት ናላህን አታዞረውም ነበር።



#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
አስተዋይ ሁን፡፡አመስጋኝ ሁን፡፡አዎንታዊ አስተሳሰብ ይኑርህ፡፡እውነተኛ ሁን፡፡ደግ ሁን፡፡




#babi

@amazing_generaton

#Yoseph

#መልካም_ቀን_ይሁንልን
ልብህ የሚነግርህን ተከተል እንጂ አይኖችህን የሚነግሩህን አትከተል፡፡




#babi

@amazing_generaton

#Yoseph

#መልካም_ምሽት_ይሁንልን
መናገር ያለብህን በግዜው ተናገር። ማድረግ ያለብህን በግዜው አድርግ። ምክንያቱም ብዙ ነገሮች ሁለተኛ እድል አይሰጡም!!


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የሆሳዕና በዓል በቻናላችን ስም ተመኝተናል።


#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏

ሆሳዕና በአርያም
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም የጤና እንዲሆንላቹህ እንመኛለን

መልካም በዓል ለሁላችሁም

@amazing_generation


#Yoseph
መቼም ቢሆን ምንም አይነት አጋጣሚ ውስጥ ብትገባ ተስፋ አትቁረጥ። ቀጣዪ ቀን ላንተ የተሻለ እድል ይዞልህ ሊመጣ ይችላልና!!!



#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏
ከዕለት ተዕለት ተግባርህ ውስጥ ምንም ነገር እስካልተቀየረ ድረስ በሂወትህ ለውጥ አጠብቅ:: ስኬት የለዕለት ተዕለት ተግባራት ውጤት ነው❗️❗️❗️



#SHARE


#babi

@amazing_generaton

#Yoseph


ሸጋ ቀን🙏🙏