#ካስተዋልኩት
ቤት ሲሰራ አስተውላቹ ከሆነ አንድ ነገር መመልከት ትችላላቹ በተለይ በእንጨት የሚሰራ ቤት።
በእንጨት ቤት ሲሰራ ሁሉም እንጨቶች ቀጥ ያሉ አይደሉም የተጣመሙ አሉ ነገር ግን የተጣመሙትን አይጥሏቸውም ይልቅ ያቃኑታል። ለማቃናት ሚጠቀሙት አንድ መንገድ ነው። የተጣመመ እንጨት ካለ የተጣመመውን እንጨት በማምጣት በተጣመመበት ቦታ እስከ ግማሽ ድረስ(ሙሉ በሙሉ አይደለም) በመጋዝ ይቆርጡታል ከዛን በቆረጡት ክፍተት አነስ ያለ ታኮ ነገር ያስገቡና ቀጥ ያረጉታል ያኔ እንጨቱ ቤት ለመስራት ይውላል።
ህይወትንም እንዲ እንመልከተው በህይወታችን የጠመመ ነገር ይኖራል ልክ ያልሆነ ነገር ታዲያ ይሄ ነገር ልክ እንዲሆን የተስተካከለ ህይወት እንዲኖረን የተቃና እንዲሆን እንደ እንጨቱ እየተጎዳንም ቢሆን ማጣት የሚገባን ነገር ይኖራል። ህይወታችንን የተቃና ለማረግ መስተካከል ያለበት ነገር ይኖራል ምንም ነገር ዝም ብሎ አይቃናም ዋጋ ያስከፍለናል። እንደ እንጨቱ በመቁረጥ በተቆረጠም ቦታ ታኮ ነገር እንደሚገባው ሁሉ ከህይወታችን ማውጣትና ባወጣነው ቦታ መተካት ያለብን ነገር ይኖራል። ያ ነገር ሊያሳዝነን ይችላል ነገር ግን ማወቅ የሚገባን ለትንሹ ሀዘን ብለን ትልቁን ደስታችንን ማጣት የለብንም። ህይወትህን እንዲጣመም ያረገውን ነገር እያዘንክም ቢሆን ከህይወትህ አውጣ ከዛን ሚያቃናህን ነገር ተካ።
#ለትናንሽ ደስታ ትልቁ ህይወትህን አታበላሽ መልቀቅ ካለብህ እያዘንክም ቢሆን ልቀቀው
#babi
ከ Yoseph
@amazing_generation
የደስታ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏

#SimonSinek
❝The WHY exists in the part of the brain that controls feelings and decisionmaking but not language. WHATs exist in the part of the brain that controls rational thought and language.❞
~Simon Sinek
🤍~💎~🤍~💎~🤍~💎~🤍️

#በየቀኑ ወደ ህልምህ አንድ እርምጃ ተጠጋ
ትልቅ ህልም አለህ ከሌለህ አሁአሁንኑኑ ህልምህን ወስን ከዛን ወደህልምህ ሁሉ ጊዜ አንድ እርምጃ ተጠጋ። ህልምህ ጋ በአንዴ ዘለህ አደርስም ይልቅ ሂደት ያስፈልገዋል። ሁሌ ቀኑ ሳያልቅ ወደ ህልምህ አንድ እርምጃ ቅረብ ነገ ሁለት ታረገዋለህ ከዛን ከተወሰነ ወራት ወይም አመታት በዋላ እራስህን ህልም ጋ ታገኘዋለህ። ሂደትን አክብር ይሄ ሂደት ተራ ነው ብለህ አትዝለለው የዛሬ ሂደት ለነገ ህልምህ አስፈላጊ ነው። ቢራቢሮን ብታይ እንደምታየው ከማማሩ በፊት ሂደት ነበረው እንቁላሉ በሂደት ሁሌም ለውጥ እያረገ እራሱን ቢራቢሮ ሆኖ ያገኘዋል አንተም ዛሬ ካልበረርኩ ወደ ህልሜም ካልደረስኩ አትበል ይልቅ በየቀኑ ወደ ህልምህ ቅረብ።
በትንሹ በቀን 1% ወደ ህልምህ ቅረብ በአመት አሁን ካለህበት 37% እራስህን ወደ ህልምህ ቀርበህ ታገኘዋለህ።
በቀን ለህልምህ ሚጠቅምህን መፅሐፍ 20 ገፅ አንብብ በአመት 7300 ገፅ ታነባለህ ያ ማለት በትንሹ አንድ መፅሐፍ 300 ገፅ ቢኖረው የምታነበው መፅሐፍ 25 መፅሐፍ ታነባለህ።
ታዲያ በየቀኑ ምታረገው ነገር ተደምሮ ወደ ህልምህ ያደርስሀል አንድ ቀን ደርሳለው ሳይሆን ወደ ህልም በየቀኑ ጉዞ አረጋለው በል።
#ዛሬ የምታረገው ነገር ሁሉ ነገህን ለመስራት ነው።

I respect people that tell me the truth, no matter how hard it is.
#babi
ከ Yoseph
@amazing_generation
የደስታ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
#babi
#babi
ከ Yoseph
@amazing_generation
የደስታ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
#babi
🔰ቤተሰቦች እንኳን ለአድዋ ድል በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
🔰የአድዋ ጦርነት ( አማርኛ ፡ የዓለድዋ ታሪክ ፤ ትግርኛ ፡ ውግእ ዓድዋ ፤ ጣልያንኛ ፡ battaglia di Adua ፣ also spelled Adowa ) የመጀመርያው ኢታሎ-ኢትዮጵያ ጦርነት ከፍተኛ ጦርነት ነበር። የኢትዮጵያ ጦር የጣሊያን ወራሪ ጦርን ድል ያደረገው እሑድ መጋቢት 1 (እንደ አውሮፖውያን አቆጣጠር ፤በኛ ደግሞ የካቲት 23)ቀን 1896 ዓ.ም በአድዋ ከተማ አቅራቢያ ነበር ። ወሳኙ ድል የጣሊያን መንግሥት የቅኝ ግዛት ግዛቷን በአፍሪካ ቀንድ ለማስፋፋት የጀመረችውን ዘመቻ አከሸፈ ። በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ የአውሮፓ ኃያላን ከሞላ ጎደል ሁሉንም አፍሪካን ቀርጾ ነበር.የበርሊን ኮንፈረንስ ; አሁንም ነፃነታቸውን ያስጠበቁት ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ብቻ ናቸው። አድዋ የፓን አፍሪካኒዝም ቀዳሚ ምልክት ሆና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አስከብሮ እስከ ሁለተኛው ኢታሎ-ኢትዮጵያ ጦርነት ድረስ ከአርባ ዓመታት በኋላ ነበር።
#በቅንነት ሼር ይደረግ🙏
@amazing_generation
#babi
Yoseph

#ትምህርት
ትምህርት ሁላችንም እንደምንስማማው የሒሳብ የቋንቋ የፊዚክስ... እውቀታችንን ይቀይርልናል ነገረ ግን ህይወታችንን አቀይርበትም። እንዴት? ልትሉ ትችላላችው ተምሬ ስራ ይዛለው ከዛን ብር አገኛለው በብሩ ቤተሰቦቼን ደግፍለውና ወዘተ ልትሉ ትችላላችው ነገር ግን ትምህርት ህይወትን አይቀይርም ሳትማሩ በፊት የምትኖሩትን ህይወት ተምራችሁም ትደግሙታላችው ለውጥ በትምህርት አታመጡም ስኬታማ መሆንም አችሉም እራሳችሁን ቀይራችው ሀገራችሁን አቀይሩበትም ምክንያቱም ከትምህርት በፊት መቅደም ያለበት ነገር አለ።
#እራስን ማወቅ እራስ ላይ መስራት እራስን ማወቅ የእውቀት ሁሉ መሰረት ነው በትምህርት እራስን መቀየር የለም እራስን በማወቅ ግን ከራስ አልፎ ሀገርን አለምን መቀየር ይቻላል። በኢትዮጵያ ሀገራችን ላይ የተማረ ብዙ ሀይል አለ ነገር ግን እስካሁን ኢትዮጵያ ለምን አልተቀየረችም ቢባል እራሱን የሚያቅ እራሱ ላይ የሚሰራ ጠፍቶ ነው። እራስህን ስታውቅ የት መሄድ እንዳለብህ ምን መስራት እንዳለብህ ስኬትን እንዴት ወደራስህ እንደምታመጣ ትረዳለህ ያ ማለት ግን ትምህርት አይጠቅምም አይደለም እያልኩ ያለውት የለውጥ መሰረት አይደለም ትምህርት መማርህ ብቻ የመለወጥህ ወደ ስኬት የመሄድህ ዋስትና አይሆንም። ይልቅ እራስህ ላይ ስራ እራስህን እወቅ በትምህርት ቤት የማታገኘውን የህይወት ትምህርት እንደ ተመራማሪ ተመራምረህ ከሌላውም ተሞክሮ ወስደህ እወቅ።
#ማይም ማለት የቀለም ትምህርት ያልተማረ ሳይሆን እራሱን ሳያቅ የሚኖር ነው።

Topic: ራስን የማሳደግ ስልጠና ምርቃት
Time: Mar 6, 2022 08:00 PM Dubai
Join Zoom Meeting
https://us05web.zoom.us/j/88146799884?pwd=elNrdTZOemdEMzlrSlUzbDlva3o4QT09
Meeting ID: 881 4679 9884
Passcode: 12345678
ማሳሰቢያ ትክክለኛ ስም ይጠቀሙ!!
@Amazing_Generation

በኦንላይን ለ3 ወራት ራስን ማሳደግ በሚል ርዕስ:-
➱ ዓላማ መቅረፅ
➱ የጊዜ አጠቃቀም
➱ የመግባባት ችሎታ
➱ በራስ መተማመን
ስልጠናዎችን በትክክል የወሰዱ ሰልጣኞች ምርቃት መርሐ ግብር ነው።
https://t.me/Denq_Hiwot
Contact ➱ @DH_Office
Topic: ራስን የማሳደግ ስልጠና ምርቃት
Time: Mar 6, 2022 08:00 PM
ለመካፈል በነፃ👇ይህንን👇 ተጭነው ይግቡ👇👇

#የማንነትህ_መለኪያ_ስኬት_አይደለም
“በቅርጫ ኳስ ጨዋታ ዘመኔ 9 ሺህ ኳሶችን ሞክሬ ስቼአለሁ፡፡ 300 ውድድሮችን ተሸንፌአለሁ፡፡ ባስቆጥረው ቡድኔን ለዋንጫ የሚያበቃውን ኳስ እንድወረውር አምነው ሰጥተውኝ ስቼ አውቃለሁ፡፡ በሕይወቴ ደግሜና ደጋግሜ ወድቄአለሁ፡፡ ለዚህ ነው ስኬታማ የሆንኩት” - Michael Jordan
አብዛኛው ሰው ውስጡን የሚነዳው አንድ ጥማት አለው፡፡ ይህ ጥማት የተመሰከረለትና ጥንቅቅ ያለ ስኬታማ ሆኖ ለመታየት ያለው ጥማት ነው፡፡ “እንደዚህ ባደርግ፣ ይህኛውና ያኛው ነገር ቢኖረኝ፣ እዚያኛው ደረጃ ብደርስ ኖሮ … እረካና ሙሉ ስኬት ውስጥ እገባ ነበር” የሚል የውስጥ ጩኸት በብዙ ሰዎች ውስጥ ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ስለዚህም፣ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ጥማት ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግና የትኛውንም ድንጋይ ከመፈንቀል አይመለሱም፡፡
የዚህ አመለካት ምንጩ፣ “ሙሉ ማንነት እንዲኖረኝ በኑሮዬ ስኬታማ መሆን አለብኝ” የሚለው አመለካከት ነው፡፡ የዚህ አመለካከትና የሕይወት ዘይቤ ውጤቱ ደግሞ “ስውር” ፍርሃት ነው፡፡ ሙሉ ማንነት እንዲኖረው ስኬታማ መሆን እንዳለበት ያመነ ሰው አለመሳካትን፣ ስህተትንና መውደቅን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ የሚሰራው ማንኛውም ስራ ስኬታማ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ከማንነቱ ዋጋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ባለማወቁ ምክንያት ለብዙ ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ያጋልጣል፡፡
የአንድ ሰው ማንነት የሚለካው በተሳካለትና ባልተሳካለት ነገር ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ሩጫ ማቆሚያ፣ ለውድድሩም መጨረሻ የለውም፡፡ ይህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤና አመለካከት የሚያስከትለው ዋነኛ መዘዝ የመውደቅ ወይም ስኬት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ከዚህ የተዛባ የማንነት መመዘኛ ቀውስ ለመውጣት በስኬት ላይ ያለንን አመለካከት መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡
1. ስኬት ዘርፈ-ብዙ ነው
ለምሳሌ፣ አንድ ሰው በስራው ወይም በንግዱ አለም የተዋጣለት ሆኖና ያሰበው ደረጃ ደርሶ፣ በማሕበራዊውም ሆነ በቤተሰባዊው ኑሮው የተበላሸ ሁኔታ ውስጥ ራሱን ሊያገኘው ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጤንነቱን ችላ ብሎ እውቀትን ወይም ንብረት ሲሰበስብ የሚኖር ሰው በቀኑ መጨረሻ “ስኬታማ ነኝ” ብሎ እንዲናገር የሚያደርገው ነገር ምንድን ነው? ስለዚህም፣ ስኬት የብዙ መሰረታዊና አስፈላጊ እውነታዎች ጥርቅም ነች እንጂ አንድ ገጽታ ብቻ የላትም፡፡
2. ስኬት የሂደት ጉዳይ ነው
ስኬት የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን የሂደት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬት፣ “አንድ ደረጃ ካልደረስኩ አልረጋጋም” ማለት ሳይሆን ጉዞውን በመጀመራችንና በሂደት ላይ በመሆናችን መርካትና መረጋጋት ማለት ነው፡፡ ዘርፈ-ብዙ የሆነው የስኬት ምስጢር ዘርፈ-ብዙ የሆነ ጥረትና ትጋት ይጠይቃል፡፡ ስኬታማ ሰው በሁሉም አቅጣጫ በአንድ ጊዜ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ነው ብሎ ማሰብ ከእውነት እንድንርቅ ያደርገናል፡፡
3. ስኬት ተለዋዋጭ ነው
ትናንት ቀለል ያለው ሁኔታ ዛሬ ከበድ ሲል፣ ዛሬ የጨመረው ሁኔታ ነገ ሊቀንስ፣ ዛሬ የተነሳሳውና የጋለው ፍላጎት ነገ ቀዝቀዝ ሊል ይችላል፡፡ እንደ ሁኔታውና እንደ እለቱ ስሜት ጥረቱን የሚቀያይር ሰው እንደዚያው አይነት ውጤትን ያተርፋል፡፡ እንደ እለቱ ሁኔታና ስሜት ሳይሆን ከዓላማው አንጻር የሚሰራ ሰው ደግሞ ከዚያው አንጻር ስኬታማ ይሆናል፡፡ ይህ በፍጹም የማይለወጥ ሕግ ነው፡፡
#babi
መልካም ቀን ይሁንላችሁ

አንድ ሺህ መስታወቶች
ያንተ ተጽዕኖ እስከ ምን ድረስ ይመስልሃል? አስተሳሰብህ ኑሮህ ላይ፤ ጤንነትህ
ላይ፤ ከሰዎች ጋር ያለህ ግንኙነት ላይ፤ ሃብትህም ላይ፤ ምን ያህል ድርሻ አለው
ብለህ ትገምታለህ ?ብዙዏችን እራሳችን (በተለይም አስተሳሰባችን) የራሳችን
ህይወት ላይ ያለውን ትልቅ ተጽዕኖ አናውቅም። ጥቂቶች ግን ይህንን ሚስጥር
ስለሚያውቁ፤ አስተሳሰባቸውን በመሞረድ አይምሮዋቸው ከተለመደው በላይ
እንዲያገለግላቸው ሲያደርጉ እና ህይወታቸው እንደ ተዓምር ሲቀየር ይታያል። ይህ
አርዕስት ሰፊ ነው…….ለዛሬ አለምን የምናይበትን መነጸር የሚያስቀይረንን ታሪክ
አገኘሁና እንዲህ አሰናዳሁት።
በድሮ ጊዜ አንድ መንደር ውስጥ በመስታወቶች የተሰራ አንድ ዝነኛ ቤት ነበር።
በመንደሩ የሚኖሩ ሁለት ውሾች ወሬውን ይሰሙና ቤቱን ለመጎብኘት
ይጓጓሉ።በመጀመሪያ አንደኛው ውሻ በደስታ ጓግቶ ወደ መንደሩ ሄደ፤ ጭራውን
በደስታ እያወዛወዘ በመስታወት ወደ ተሰራው ቤት ገባ። ቤቱ እንደተባለውም
በሺህ መስታወቶች የተገነባ ነበር። ውሻው በደስታ እያለከለከ፤ ጭራውን በሃሴት
እያስጨፈረ….ሲገባ …ሌሎች አንድ ሺህ ውሾች በደስታ እያለከለኩ፤ እንደሱ
ጭራቸውን እያስጨፈሩ ተቀበሉት። ለደቂቃ በመስታወቱ ከሚመለከቱት ውሾች
ጋር ሲስስቅ እየሳቁ….ሲዘል እየዘለሉ አብረው አሳለፉ…….ወደ ቤቱ ሲመለስም
“በጣም ደስ የሚል ቤት ነው…….ሁሉም በደሰታ የሚጨፍርበት …..አዘውትሬ
መምጣት አለብኝ” ብሎ ለራሱ ቃል ገባ
በሌላ ቀን ሌላኛው ውሻ……በመስታወት የተሰራውን ቤት ሊጎበኝ ወደ መንደሩ
ተጓዘ። ይህኛው ውሻ እንደመጀመሪያው ውሻ ደስተኛ አልነበረም…..ተናካሽ እና
በሆነው ባልሆነው የሚያንባርቅ ነበር። ከመንደሩ ደርሶ ወደ መስታወቱ ቤት
ሲዘለቅም፤ ልክ እንደሱ የተኮሳተሩ አንድ ሺህ ውሾችን በመስታወቱ ውስጥ
ተመለከተ፤ በንዴት ሲጮህ እነሱም ይጮሃሉ…..ሊናከስ ሲሞክር በመስታወቱ
ውስጥ ያሉት ልክ እንደሱ ሊናከሱ ይሞክራሉ….ቤቱን ጥሎ በንዴት ወጣ “ምን
አይነት የአውሬ ቤት ነው ሁለተኛ እዚህ ቤት አልመጣም” ብሎ እያጉረመረመ ወደ
ቤቱ ተመለሰ።
ሁለቱም ውሾች በሺህ መስታወቶች ውስጥ የተመለከቱት የራሳቸውን ምስል
ነው። በመስታወቶቹ ውስጥ የተመለክቱት የራሳቸውን ማንነት እና አመለካከት
ነው። ባህሪያቸው ግን ይለያያል። ባህሪያቸው በመለያየቱ አጋጣሚያቸው ተለያየ፤
በቤቱ የነበራቸው ልምድ ተለያየ፤ አለም እንደ አመለካከታቸው አስተናገደቻቸው
(የመስታወት ቤቱ እንደ ጸባያቸው አይደል የቀበላቸው?)
እኒህ ውሾች የኛ ተምሳሌቶች ናቸው። በሺህ መስታወት የተገነባው ቤት ደግሞ
አሁን እየኖርንባት ያለችው አለም። ህይወት ልክ እንደ መስታወት ናት፤ ስንስቅላት
ትስቅልናለች፤ ስንጮህባት ትጮህብናለች። በዙሪያችን ከምናያቸው ውስጥ ብዙ
ልንለውጣቸው የምንሻው ነገሮች ይኖራሉ። ግን እንዴት መለወጥ ይቻላል?……
መልሱ አይቻልምም ይቻላልም ነው። ከእኛ ውጪ ያለውን ነገር መለወጥ
ባንችልም፤ አመለካከታችንን ከለወጥን ግን ሁሉም ነገር ይለወጣል።
አመለካከታችንን ስንለው፤ በውጪ የምናያቸው ነገሮች ሁሉ መልካቸውን
ይለውጣሉ።
እንደመጀመሪያው ውሻ ደስተኛ መሆን ከቻልን፤ ዙሪያችን በመልካም ነገሮች
ይከበባል። ለሳቃችን ሳቅ ይመለስልናል፤ ለምስጋናችን ምሰጋና ፤ ለአክብሮታችን
አክብሮት፤ ለደግነታችን ደግነት ይመለስልናል (ሁሌም ባይሆን በአባዛኛው፤
ምክንያቱም እዚህ ምድር ላይ ፍጹም የሆነ ነገር ስለሌለ) ። እንደ ሁለተኛው ውሻ
ኑሯችን በፀለምተኝነት የተሞላ ከሆንም፤ እንደዛው። ለንዴታችን ንዴት
ይመለስልናል፤ ለግልምጫችን ግልምጫ፤ ለሃዘናችን ሃዘን፤ ለንቀታችነ ንቀት፤
ለመጥፎ ምኞታችን መጥፎ ምኞት።ህይወት ዘመናዊውን ንግድን እስካሁን
አልለመደችም። የምትገበያየው “በልውውጥ ገበያ ነው” የሰጠናትን ያህል
ትሰጠናለች።
ማንኛውንም ነገር ለመለወጥ ስናስብ መጀመሪያ ከፊታችን በመስታወት ውስጥ
ከምናየው ሰው እንጀምር።
((( ሚስጥር አደራው)))
ሸጋ ቀን🙏🙏
#Babi
@amazing_generation
#Yoseph

#ልዩነታችን_ዉበታችን
ሁላችን ምናዉቀዉን መሶብ እንደ ምሳሌ እንዉሰድና መሶብን እንደምታዉቁት ወጥ(ተመሳሳይ) ቀለም ወይም ብዙ አይነት ቀለም እንዲኖረዉ ተደርጎ ይሰራለ ታዲያ ከሁለቱ የቱ ያምራለ ቢባል መልሳችን በትክክለኛነት ብዙ አይነት ቀለም ያለዉ ነዉ፡፡
በወጥ(በተመሳሳይ) ቀለም የተሰራ ቀይ መሶብ ቢኖርና በሌላ በኩለ ደግሞ በብዙ አይነት ቀለም (ቀይ አረንጓዴ ነጭ ቢጫ…) ቢኖረን ዉበት ያለዉ በብዙ አይነት ቀለም የተሰራዉ ነዉ ብለናል ነገር ግን ብቻዉን የተሰራዉ ቀይ መሶብ ያላማረዉ ቀይ በመሆኑ ሳይሆነ ብቻዉን ስለሆነ ነዉ፡፡ ከብዙ አይነት ቀለም ጋር ሲመጣ አማረበት ታዲያ የቀዩ ዉበት አረንጓዴ ቢጫ ነጭ መኖሩ ነዉ የቢጫም ዉበት ቀይ ነጭ አረንጓዴ ምኖሩ ነዉ የአረንጓዴና ነጭ ዉበትም ሌሎች መኖራቸዉ ነዉ፡፡
ልዩነታችን ዉበታችን ነዉ የአማራ ባህል ዉበቱ የኦሮሞ ባህል የደቡቡ ባህል የትግሬ ባህል የሃረሩ… ስላል ነዉ የኦሮሞም እንደዛዉ ሌሎች በመኖራቸዉ ዉብ ሆነ ደቡብንም የትግራይንም የአፋርንም የጋቤላንም… ብቶስዱ ዉበታችዉ ሌላ ባህል መኖሩ ነዉ፡፡ እንደ መሶቡ ጋቤላ ብቻዉን ዉብ አይደለም ዉብቱ ከሌሎች ጋር መደባለቁ ነዉ፡፡
ስናጠቃልለዉ የኔ ቋንቋ ባህል ከሌሎች ዉብ ነዉ አትበል ያንተ ቋንቋ ባህል ዉብ የሆነዉ ሌላ ባህልና ቋንቋ ስላለ ነዉ፡፡ የትኛዉም ባህል አያምርም ወይም ዉብ ነዉ አይባልም ምክንያቱም ዉበቱም አለማማሩም ያለዉ በአንድነትና በመልያየት ዉስጥ ስለሆነ ስለዚህ አንድነትን ከመረጥን ዉበት አለን፡፡
#SHARE
#babi
@amazing_generati
on

እውነተኛ ነፃነት የህሊና ነፃነት ነው። የህሊና ነፃነት ደግም እውነትን በማወቅና በመኖር ነፃ ከወጣ አዕምሮ በቻ የሚገኝ ፀጋ ነው።
ሕይወት ሚጥሚጣ የበዛባት ብጫቂ እንጀራ ናት።
የአምፖል ውበቱ ከውስጡ የሚወጣው ብርሃኑ ነው።
በሚቃጠልበት ጊዜ ለምንም የማይጠቅም፣ የማንንም አይን የማይስብ በቀላሉ የሚሰበር ተራ ብርጭቆ ነው የሚሆነው ።
የሰውም ውበት ከውስጡ በሚፈልቀው የደስታ ፋናና የተስፋ ጨረር እንጂ በፊቱ ቅርጽና በሰውነቱ አሰካክ ብቻ አይደለም።👍
#SHARE
#babi
@amazing_generation
#Yoseph
🙏🙏

chology
#በራስ_መተማመንን (Self Confidence)
ለማሳደግ የሚረዱ አስር ሙያዊ ምክሮች
ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ
ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ
እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው።
ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ
ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ
ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው
ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ።
1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)።
የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ
አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት
የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም
አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ
ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን
እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም
በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት
ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና
ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ
ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ።
2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)።
አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች
ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም
ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ
ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው
በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ።
3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)።
በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ
መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች
የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም
በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ
ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች
ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል።
4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial)
ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ።
ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም
ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ።
5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude)
ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት
ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ
እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ። ምን ያህል እርቀት እንደመጡም ለመገንዘብ ይረዳዎታል፣ ወደ
ቀጣዩ ደረጃ ወደ ስኬት ለመሄድም በእጅጉ ያነሳሳዎታል።
6. ለሌሎች ሰዎች ስለ ጥሩ ስራቸው አድናቆትን ይለግሱ (Complement others)።
ስለራሳችን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ማጣጣል እና በጀርባቸው ላይ
መጥፎ ነገር መሸረብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለማቋረጥ ሌሎች ሰዎችን
የማመስገን ልማድ ይኑርዎት። ከሰዎች ጀርባ መጥፎ ነገር መመኘት ወይም መጠንሰስን
አስወግደው በሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አድናቆትን ለመግለፅ ይሞክሩ። በሂደቱ ውስጥም በጣም
ይወደዳሉ፣ በዚህም በራስ መተማመን ይገነባሉ ። በሌሎች ውስጥ ምርጡን በመፈለግና
በመመስከር በተዘዋዋሪ ምርጡን ወደ ራስዎ ዘንድም ያመጣሉ።
7. ከፊት ረድፍ ይቀመጡ (Sit in the front row)
ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ጽ / ቤቶች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ብዙ ሰዎች መጨረሻ
ለመቀመጥ ይጥራሉ። ምክንያቱም በቀላሉ መታየቱ ያስፈራቸዋል። ይህም በራስ መተማመን
ማጣትን ያሳያል። በፊተኛው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዎስኑ ይህንን ያለፈቃድ የሚመጣ ፍርሃት
አሸንፈው በራስ መተማመንዎን መገንባት ይችላሉ። በተጨማሪም ከዋናው ፊት ለፊት
ለሚነጋገሩ ሰዎች በይበልጥ ግልጽ ይሆናሉ።
8. ሃሳብዎን ይግለፁ (Speak up)
በቡድን ውይይቶች ወይም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሁኔታ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን
ከመግለፅ ይቆጠባሉ። ምክንያቱም ሰዎች ከንግግራቸው ተነስተው እንዳይገምቷቸው ስለሚፈሩ
ነው። ይህ ፍርሃት ትክክል አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ከምናስበው ይልቅ የሰውን ሃሳብ
የመቀበል ፍላጎት አላቸው። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ፍራቻ የተጠቁ ናቸው።
በእያንዳንዱ የቡድን ውይይት ቢያንስ አንድ ጊዜ ለመናገር ጥረት በማድረግ የተሻለ የህዝብ
ንግግር ክህሎት እንዲያዳብሩ ፣ ይበልጥ በራስ መተማመን እንዲኖርዎት እና በእኩዮችዎ ዘንድ
መሪነትን እና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ያደርግዎታል።
9. ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልምድዎ ይሁን (Work out)
ልክ እንደ አለባበስ አይነት፣ አካላዊ ብቃት በራስ መተማመን ዘንድ ከፍተኛ ሚና አለው።
ቅርጽዎ እንደተበላሸ ከተሰማዎት በሌሎች ዘንድ ዝቅ ተደርጎ የመታየት እና ሌሎችን መማረክ
አለመቻል ስሜት ይሰማዎታል። አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረግ አካላዊ ገጽታዎን ያሻሽላሉ፣
ኃይልን ያገኛሉ፣ ለአዎንታዊ ስራም ይነሳሳሉ።
10. የሚያደርጉት አስተዋፅዎ ላይ ያተኩሩ (Focus on contribution)
ብዙውን ጊዜ እኛ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንጂ የሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና በሌሎች ላይ
ስለሚመጣው ጥሩ ለውጥ አናስብም። ስለራስዎ ማሰብ ካቆሙ እና ለተቀረው ዓለም ላይ
ለውጥ እንዲመጣ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ (መዋጮ) ላይ ካተኮሩ፣ ያሉብዎት ጉድለቶች
አያስጨንቁዎትም። ይህ በራስ መተማመንን ይጨምራል እናም በከፍተኛ ተነሳሽነት እና
ውጤታማነት እንዲሳተፉ ያስችልዎታል። ለዓለም ጥሩ እያደረጉ በሄዱ መጠን የግል ስኬት እና
እውቅናንም እየተጎናፀፉ ይሄዳሉ።
#babi
@amazing_generation
#babi
ሰናይ ምሽት🙏🏿🙏🏿

ማንም ሰዉ በፍፁም መፍራትህን እንዳያዉቅ! ተኩላዎች መፍራትህን ከሰዉነትህ እንቅስቃሴ ያዉቃሉ፡፡ ምንም ያህል ብትፈራም፣ ማንም ሰዉ ፊት እንደፈራህ ሆነህ አትቁም! ቆፍጠን ብለህ ጠንከር ብለህ ድምፅህን ረጋ አድርገህ አይንህን ቀስ አድርገህ አንቀሳቅስ፡፡
• ሰዎችን ትንሽ አርቃቸዉ፡፡ ማንንም አትመን፡፡ ወደራስህ ህይወት በጣም ካስጠጋሃቸዉ ማንነትህን በደንብ አብጠርጥረዉ ስለሚያዉቁ መናቅ ይጀምራሉ፡፡
ስለዚህ መስመር አስምር...ሰዎች ስላንተ ትንሽ ብቻ ካወቁ አክብረዉህ ይኖራሉ፡፡ ስላንተ ያላቸዉ መረጃ አነስተኛ ሲሆን የቀረዉን ነገር በራሳቸዉ ሃሳብ ዉስጥ በሚፈጥሯቸዉ ነገሮች ሲፈልጉ ይሙሉት፡፡
• ወሳኝ ከምትለዉ ሰዉ በስተቀር ያገኘኸዉን ሁሉ ዝም ብለህ ወደቤትህ አትዉሰድ፡፡ ሰዎች በተፈጥሮ ቤትህን ሲያዉቁ አንተነትህን በቀላሉ መግለፅ አይከብዳቸዉም፡፡ ምን አልባትም ሲያወሩ ትደርስባቸዉ ይሆናል!
• ስለዚህ ሰዎችን በዉጪ አግኝ... ቢዝነስም ይሁን ሌላ ማንኛዉም ነገር በዉጪ ጨርስ፡፡ ከምንም በላይ ለራስህ ዋጋ ስጥ! ለማንም ለምንም በቀላሉ የምትገመት ሰዉ አትሁን ይኸዉ ነዉ!
• ሰዎች በብዙ ነገር ማንነትህን ይፈታተኑታል፡፡ ስለዚህ 'ለምን ተፈተንኩ?'ብለህ አትቆጣ፡፡አትናደድ፣ሃይልህን አትጨርስ...ብቻ ለሚመጣዉ ነገር እራስህን አዘጋጅ፡፡
አንዳንድ ነገሮች ፈፅመህ ካልጠበከዉ መንገድ እየጎረፈ ሲመጣ ታያለህ፡፡የዛኔ እንደምንም ብለህ እራስህን አረጋጋ፡፡ ከአምስትና አስር አመት በኋላ ያለህበት ነገር ምን ያህል ተፅእኖ ያሳድርብሃል? ብዙ ነገሮች ለጊዜዉ ብቻ የሚያስቆጡ ስለሆኑ በእርጋታ አሳልፋቸዉ፡፡
• ሁል ጊዜ ለሰዎች ክብር ይኑርህ፡፡ቢያጠቁህም እነሱን ለማጥቃት መልሰህ ጦርነት አትክፈት...ባህሪያቸዉን ወይም ከላይ ያለዉን ማንነታቸዉን አታጥቃዉ ነገር ግን የዉስጥ ሃሳባቸዉን አትቀበል፡፡
ዋናዉን የልብ ፍላጎታቸዉን ብቻ ቀይ ስጠዉ! ይህን የምታደርገዉ ግን በተረጋጋ ማንነት ዉስጥ መሆን ቢችል ጥሩ ነዉ፤ ነገሮችን ከግራም ከቀኝም የማየት አቅም ስለሚኖርህ የበሰለ ዉሳኔ መወሰን አያቅትህም፡፡
• ከማን ጋር እንደምትዋጋ እወቅ፡፡ ልታሸንፍ የምትችለዉን ጦርነት ብትመርጥ ይሻልሃል ያለበለዚያ ብዙ ነገር ይበለሻሻል፡፡
ምሳሌ ልስጥህ፡ አንድ ጓደኛዬ ከሴት ጓደኛዉ ጋር ተጣላና መደባደብ ጀመረ፡፡ ከሁለተኛ ፎቅ ላይ እቃዉን ሁሉ እያወጣች መወርወር ጀመረች፡፡ፊቱን ሞነጫጭራ ሞነጫጭራ አዲሱን የቀለበት መንገድ ዲዛይን ፊቱ ላይ ሳለችዉ፡፡ እሱም አልተዉም ብሎ ደበደባት፡፡
#SHARE
#babi
@amazing_generaton

አነቃቂ ጥቅሶች
📖ሰዎች ምክንያታዊ ያልሆኑና ራስ ወዳድ
ናቸው።ለማንኛውም ሰውን ውደድ
,
📖ጥሩ ብትሰራ ሰዎች ስውር ፍላጎት ስላለው ነው
ይሉሀል።ለማንኛውም ጥሩ ሁን
,
📖ስኬታማ ብትሆን የውሸት ጓደኛና የእውነት ጠላት
ታፈራለህ።ለማንኛውም ስኬታማ ሁን
,
📖ዛሬ የሰራኸው ጥሩ ነገር ነገ
ይረሳብሀል።ለማንኛውም ጥሩ ሁን
,
📖ሀቀኛና የዋህ ብትሆን ደካማ ጎንህን
ሊጠቀሙብህ ይፈልጋሉ። ለማንኛውም ሀቀኛና
የዋህ ሁን
,
📖ለአመታት የገነባኸው በአንድ ለሊት ሊናድ
ይችላል ።ለማንኛውም ገንባ
,
📖ሰዎች የእውነት እርዳታህ ያስፈልጋቸው ይሆናል
ነገር ግን በምላሹ ሊያጠቁህ
ይፈልጋሉ።ለማንኛውም እርዳ
,
📖ያለህን ምርጡን ነገር ለአለም ስጥ እናም
ጀርባህን ልትመታ ትችላለህ።ለማንኛውም ምርጡን
ነገርህን ለአለም ስጥ
#SHARE
#babi
@amazing_generati
on
#Yoseph
ሸጋ ቀን🙏🙏
📖ሰዎች ምክንያታዊ ያልሆኑና ራስ ወዳድ
ናቸው።ለማንኛውም ሰውን ውደድ
,
📖ጥሩ ብትሰራ ሰዎች ስውር ፍላጎት ስላለው ነው
ይሉሀል።ለማንኛውም ጥሩ ሁን
,
📖ስኬታማ ብትሆን የውሸት ጓደኛና የእውነት ጠላት
ታፈራለህ።ለማንኛውም ስኬታማ ሁን
,
📖ዛሬ የሰራኸው ጥሩ ነገር ነገ
ይረሳብሀል።ለማንኛውም ጥሩ ሁን
,
📖ሀቀኛና የዋህ ብትሆን ደካማ ጎንህን
ሊጠቀሙብህ ይፈልጋሉ። ለማንኛውም ሀቀኛና
የዋህ ሁን
,
📖ለአመታት የገነባኸው በአንድ ለሊት ሊናድ
ይችላል ።ለማንኛውም ገንባ
,
📖ሰዎች የእውነት እርዳታህ ያስፈልጋቸው ይሆናል
ነገር ግን በምላሹ ሊያጠቁህ
ይፈልጋሉ።ለማንኛውም እርዳ
,
📖ያለህን ምርጡን ነገር ለአለም ስጥ እናም
ጀርባህን ልትመታ ትችላለህ።ለማንኛውም ምርጡን
ነገርህን ለአለም ስጥ
#SHARE
#babi
@amazing_generati
on
#Yoseph
ሸጋ ቀን🙏🙏