አቤንኤዘር_Testimony ⚓️🎤
187 subscribers
60 photos
4 videos
1 file
22 links
ይህ የህያዋን ድምጽ ነው!
ግንዱ በቅርንጫፉ ህይወት ላይ የሰራውን የምናደምቅበት!
ለመጽናናት የሚሆኑ ድንቅ የህይወት ምስክርነቶች!
1ጴጥ 2:9 #በጎነቱን_መናገር!
@AmazingTestimony!
ምስክርነት👇👇👇 አላችሁ ፦
@NATI4MC
Download Telegram
እንደምን ቆይታችኋል ተወዳጆች። ካለፈው አርብ ጀምሮ በባሌ ሮቤ ዞን በሠልቃ ከተማ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ለወንጌል ተልዕኮ ከተወደዱ ወንድሞች ጋር ሄደን ነበር። እግዚአብሔር በዛ ስፍራ ድንቅ ነገርን አድርጓል።

👉 ነፍሳት ከጨለማ ወደ ብርሃን መጥተዋል። (10 ሰዎች ጌታ አግኝቷቸዋል)
👉 በከተማው ከሰለጠነው የጨለማ መንፈስ አርነትን ተቀብለዋል።
👉 ወጣት ሴትና ወንድ ልጆች በመንፈስቅዱስ እሳት ተጠምቀዋል።
👉 ወንጌል በኃይልና በስልጣን በከተማዋ የገበያ ቀን ተሰብኳል።

በትናንትናው ዕለት ከወንድሞቼ ጋር ተልዕኳችንን በድል ጨርሰን በሰላም ተመልሰናል። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን። (ናቲ ማራናታ)
ለእግዚአብሔር ደስታ መኖር ይሁንላችሁ!

👉 ሰማያዊውን ህይወት ለመኖር በምድር ላይ ለራስ ፍላጎት አለመኖር ወሳኝ ነው።
👉 የእግዚአብሔር ሐሳብ ከእኛ ሐሳብ ጋር ፈጽሞ የተለያየ ነው።
👉 እግዚአብሔርን አስደስቶ ለማለፍ በእርሱ ፈቃድ ስር ራስን ማስገዛት በጣም ወሳኝ ነገር ነው።

ለሐሳቡ በመሸነፍ ተባረኩ።
እግዚአብሔርን እሺ ማለት ይብዛላችሁ።

@AmazingTestimony
☝️☝️☝️join us☝️☝️☝️
#አቤንኤዘር_እግዚአብሔር_ረድቶናል!
"ህይወትን በክርስቶስ ተርጉማት ፤ እንዳንተ ደስተኛ ሰው በምድር ላይ አይኖርም!"

@AmazingTestimony
☝️☝️☝️join us☝️☝️☝️
#አቤንኤዘር_እግዚአብሔር_ረድቶናል!
እግዚአብሔር ከተመቻችሁ ስፍራ ለምን ያወጣችኋል? ከለመዳችሁት ቦታ ፈቀቅ ለምን ያደርጋችኋል? ከምትታወቁበት ክልል ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆናችሁበት አካባቢ ለምን ገለል ያደርጋችኋል???

የማታውቁትን እንድታውቁለት ነው! ባላችሁበት ስፍራ የሚገኘውን ዕውቀት ስለጨረሳችሁ ነው! እርሱን ብቻ እንድታምኑት ስለሚፈልግ ነው። የተሻለን ነገር ወደ ህይወታችሁ ሊያመጣ ስለወደደ ነው።

አትደንግጡ ፣ አትማረሩ ፣ ለምን አትበሉ ፣ አትዘኑ....አመስግኑ! ደስ ተሰኙ! ክብርን ስጡት! ደግሞም እወቁት!!!

“አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፤ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፤”
  — ዕንባቆም 3፥2

🔥 አስተውሉ ሁልጊዜ ማድረግ ያለብን እግዚአብሔር በዓመታት መካከል ከዘላለም ያሰበውን የእርሱን ፈቃድ በህይወታችን በሙላት እንዲያደርገው መፍቀድ ነው! እወዳችኋለሁ+ (ናቲ ማራናታ)
መጠጊያችሁ ማነው?🤔
መንገዳችሁን ለእግዚአብሔር አደራ ስጡ! "መንገድ" ማለት ታድያ የሰፈራችሁ ኮብል አልያም የከተማችሁ አስፓልት አይደለም😁!

👉 በራሱ ብቁ እንዳልሆነ የሚያምን ከእግዚአብሔር ጋር ይወዳጃል። ወደ እርሱ መጠጋጋት ደግሞ ከክፋት ሁሉ ያስመልጣል!
እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ከመልካም ነገር አይጎድሉም።

“ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም።”
— መዝሙር 34፥10

እርሱን ተማምነው የሚጠብቁትም ከድል ወደ ድል ይሻገራሉ። ህይወታችሁን በድል ውስጥ ለመምራት ከፈለጋችሁ ራሳችሁን በትልቁ ጌታ ላይ ጣሉት!!!
ዛሬ አመሻሹን ወደ አንድ የክርስቶስ ቤ/ክ የወጣቶች ፕሮግራምን ለመካፈል ተገኘሁ። የጸሎት ጊዜ እንዳለቀ መድረኩን የተቀበለው ወንድሜ ስለመንፈስቅዱስ ማለት የምትፈልጉት ነገር ካለ 1ደቂቃ እሰጣችኋለሁ አለና እጁን ያወጣ ሰው ባለመኖሩ ምንም እንኳን እንግዳ ሆኜ ብሄድም ስሜን ጠርቶ እስኪ የሆነ ነገር በለን አለኝ።

ድንገት መጠየቅ ያስደነግጣልም ደግሞም ደስ ይላል😁

እኔም እንዲህ አልኩኝ... "በሌሊት ማጥናት ፈልጋችሁ ባላችሁበት ክፍል መብራት / ብርሃን ባይኖር ማንበብም ሆነ መረዳት አትችሉም። ልክ እንዲሁ ኢየሱስን ካለ መንፈስቅዱስ መረዳት አትችሉም! መንፈሳዊ ምስጢርን ካለ መንፈስቅዱስ መረዳት አትችሉም!  ብርሃን የምታነቡትን እንድታዩት እንደሚያደርጋችሁና በማየታችሁ መረዳት እንደምትጀምሩ ሀሉ በመንፈስቅዱስ  በኩል ኢየሱስን መመልከት ብሎም መረዳት ትችላላችሁ። መንፈስቅዱስ ለእኔ ኢየሱስን የማይበት ብርሃኔ ነው።"

እውነት ነውኮ ተወዳጆች በመንፈስቅዱስ አማካኝነት ካልሆነ በቀር ኢየሱስን መረዳት ዘበት ነው።

መንፈስቅዱስ እንወድሃለን!

@AmazingTestimony
ማስለመድ

ልጄ ሆይ👸 እንድ ነገር ልንገርሽማ፥ እርግብ🕊 ሲጠመድ🗑 አይተሽ👀 ታውቂያለሽ?
መጀመሪያ የሚደረገው እኮ እሷን ካለችበት ሄዶ የሚያመጣት እና ይሄንን ሰፈር የሚያስለምዳት አንድ እርግብ🕊 ይዘጋጃል፣ በመቀጠልም እሷ ሰፈር ይላካል፤ በዚህን ጊዜ ነው እሷ የሚወዳት፥ የሚፈልጋት እና እርሷን ለማግኘት ዋጋ💰 የሚከፍል ያገኘች መስሏት ካሳደጋት እና በየእለቱ እየመገበ ጤንነቷን ከሚከታተለው ጌታዋ🕵ተለይታ በመሄድ ሌላን ሰፈር 'የምትለምደው'፤ የሚገርመው🤔 ነገር ሰፈሩን ከለመደች በኋላ፥ አንድ ቀን ተከትላው የሄደችውን እርግብ ተከትላ ወደእርሱ መኖሪያ ግቢ ትገባለች🕊🕊 እርሱ የሚበላውንም ምግብ ከአንድ ስፍራ ላይ ታያለች ስለሚርባትም አብራው ትበላለች፥ ያንን ሲያደርግላትም ያስብልኛል ብላ በጣም ልቧ ይነካል፥ ነገር ግን ድንገት ሳታውቀው የሆነ ነገር አብረው እንዳሉ ይከድናቸዋል🕊🕊፥ ወዲያውም ይጨልማል፤ የዛን ጊዜ ብቻ ነው ይሄ ሁሉ ነገር እሷን ለማጥመድ🗑 እንጂ ተወዳ እንዳልሆነ የምታውቀው:: ከዚያ በኋላማ አጥማጁ ይመጣና👣 ከወጥመድ አውጥቶ መጀመሪያ ክንፏን ወይ ይነጨዋል አለዚያም ደግሞ ያስረዋል:: በዚህን ጊዜ ተከትላው የነበረው እርግብ፥ ከጓደኞቹ ጋር ሲበር 🕊እርሷ መሬት ትቀራለች፥ መብረር እና ጌታዋ ህልም😴 እና ምኞት ይሆንባታል:: ያ ሁሉ የውሸት ፍቅር💔 ነበር!
አየሽ ይሄ የሆነው በአንድ ቀን አይደለም፤ ትንንሽ በሚመስሉ ነገሮች ድግምግሞሽ ነው! ይሄ የማጥመድ ስልት ምን ይባላል መሰለሽ፦
🚸'ማስለመድ'🚸::
ምንም ነገር ከለመድሽው ቀላል💁ይሆናል!
ልጄ ሆይ👩 አየሽ👉 የአንቺም ህይወት እንደእርግብ ነው ከሰፈርሽ ውጪ ይወስዱሻል፥ ቀጥሎም 'ያስለምዱሻል':: መጀመሪያ ግን የሚያስለምዱሽ ያለሰፈራቸው በመምጣት ፍቅር💗 የሚመስልን ሽንገላ እና ላንቺ ማሰብ የሚመስልን ወጥመድ ነው🕸፥ ቀጥሎም የእነርሱ ሰፈር ይወስዱሻል፡ እነዚህን ነገር ቀሎሽ እንድታደርጊው ደግሞ ደጋግመው የሚያውሩሽ ቃል አለ:
🕸'ችግር የለውም'🤷‍♀
🕸'አታካብጂ' 🤒
🕸'አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡
🕸ሞክሪው'🤑
🕸'እነእንትናም እኮ እንደዚህ ናቸው🤡፥ እንደዚህ እኮ ያደርጋሉ'👥 እና ሌሎችም የማጥመጃ ቃሎችን ይነግሩሻል::
💃🕺💃🕺💃🕺💃
የዚህ 'ጨዋታ' ትክክለኛ ስሙ "ወጥመድ"🕸 ነው።
                         💃🕺💃🕺💃🕺💃
እርግቧን በምግብ አድርገው ጨዋታ በማስመሰል ስበው ወጥመድ ውስጥ እንደከተቷት አንቺንም የሚስብ 👋ወጥመድ መክተቻ ጨዋታ ነው!
ልጄ እርግቤ ሆይ🕊 አጥማጁ🃏 ወፏ ምግቡን ብቻ አይታ ወጥመድ ውስጥ እንደምትገባ እንደሚያውቅ😆ሁሉ ሰይጣንም የዚህን እድሜሽን ስሜት ያውቀዋልና ክፉ ጓደኛን👭ማለትም የሚወዱሽ💑የሚመስሉ ነገር ግን አለማዊነት ውስጥ ዘፍቀው ለነገ ፀፀት😪🤦‍♀የሚያዘጋጁሽን ወደ አንቺ ያመጣል፤ ወደወጥመዱ ለማስገባት እንደዚህ አይነቶቹን ጓደኞች🤷‍♂ወደአንቺ ያመጣል! አንቺ ለይተሽ ልታውቂያቸው ይገባል አለዚያ እንደዚያች እርግብ አታለው ይወስዱሻል:: ከዚያ አንቺም እንደእርግቧ የተወደድሽ💕 መስሎሽ ትልቅ ስህተት ትሰሪያለሽ::
ምናልባት ደግሞ በቤተሰብሽ👪 እና በተለያየ የህይወት ክፍልሽ ያልተደሰትሽበት😞 ነገር እና ክፍተት ቢኖር እንኳን ወደፈጣሪሽ ፀልይ🙏 አምላክሽን አውሪው🗣 እርሱ ማንም ያልተረዳልሽን ይረዳል👆😏! ከቤትሽ/ ከቤተሰብሽ/ ህልምሽን😴 ከሚያስታውስ👈 ስፍራ አትራቂ🏃‍♀! ከፊልም ያገኘሁትን አንድ አባባል ልንገርሽ: "When children👼 are away🏃 from home too long🏘, they forget who they are." ልጆች ከቤታቸው(ከቤተሰባቸው) እርቀው ሲቆዩ ማንነታቸውን(ማን🤔 እንደሆኑ) ይረሳሉ::
የውሸታቸውን😋 ክፍተትሽን የሚሞሉ የሚመስሉ ነገር ግን ህይወትሽን ሙሉ ጎዶሎ እና አንካሳ የሚያደርጉ ክንፍሽን ነጭተው መቼም እንዳትበሪ🕊 አድርገው ሊያኖሩሽ ከሚፈልጉ ሰዎች እና ሱሶች🤒🍻 ራስሽን ጠብቂ! ህልም😴 እና ራዕይሽን🎯 እያጣጣለ ጭፈራ💃 እና ፊልም የሚጋብዝሽ🖥፥ አንድም ቀን ስለትምህርትሽ📚🎓 ሳያወራ ያለማቋረጥ ስለዝሙት💏 የሚያወራሽ ምን ፈልጎ ይመስልሻል? እመኚኝ ያንቺኑ ስሜት አነሳስቶ ሰፈሩ በመውሰድ👣 ባሪያ ሊያደርግሽ እና ወጥመዱ🗑 ውስጥ ሊያስገባሽ ነው! እርግቧ የሚበላ🌽 አይታ ነው፤ ልጄ እርግቤ ሆይ🕊 አንቺስ ምን ይታይሻል👀? የዛሬሽን ጥራጥሬ🌽 የሆነ ተራ ነገር ብቻ አይተሽ አትታለይ! አንቺ እኮ በጣም እሩቅ🛫 መሄድ የምትችዪ የሚያምር የአስተሳሰብ👌😇 እና የእድሜ ክንፍ ያለሽ ነሽ👸! አዎ
💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
አንቺ እኮ ብዙ ነገዎች ያሉት አዲስን ታሪክ መስራት የሚችል ትልቅ አቅም ውስጥሽ አለ!
💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
ልጄ ሆይ እባክሽን አርቀሽ እዪ👉👀! በስሜትሽ😊 ሳይሆን እውቀትሽን📒 ተጠቅመሽ ውስጥሽ ባለው ትልቅነት ተመልከቺ🔍! ስሜትሽ ሁሌም የሚያሳይሽ የቅርቡን ነው፥ አሁን ላይ ብቻ የሚያስደስትሽን😀፤ አንቺ ግን ከዚያም ያለፈ እምቅ ሃይል🔥 ያለው የውስጥ ጥንካሬ እና ውበት👌 አለሽ!
ልጄ እርግቤ ሆይ🕊 በቀሪው ወርቃማ💥 እድሜሽ በእራስሽ ክንፍ አየርሽ ላይ በፅናት መብረር🛩 ይሁንልሽ! በእድሜሽ ዘመን ሁሉ በሙሉ ክንፍ ብረሪ🕊! ጠላት👽መሻትሽንና ክንፍሽን አያግኝብሽ🚫!
አምላኬ አንቺን ሁሌም አየር🕊 ላይ ያሳየኝ! መሬት እና ወጥመድ🗑 አያግኝሽ! በጠላቶችሽም አትበልጪ💀🙌!
ኬቢ (fb)
በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥም!
"Prayer is not a presentation. Rather, it is communication."
(nati maranatha)
ምን ዓይነት ኑሮ እየኖራችሁ ነው?
በምን አይነት መንገድስ እየሄዳችሁ ነው?
አሁን ላላችሁበት የህይወት ስርዓት ሀላፊነት ትወስዳላችሁ? ወይንስ በቂ የምትሉት ምክንያት አላችሁ?
*
አንድ ነገር ልንገራችሁ
+++
ምንም ዓይነት ኃጢአት በማይታወቅበት የእግዚአብሔር መንግሥት በሙላት ባለበት በኤደን ገነት ውስጥ አዳም ኃጢአትን ሲሰራ
ርኩሰት በበዛበት የእግዚአብሔርን ቁጣ የጠራ የኃጢአት ልምምድ ባለበት ሰዶም ውስጥ ሎጥ የተጠበቀ ልጆቹም ድንግሎች ነበሩ
*
እናስተውል ካለንበት ቦታ ይልቅ ያለንበት ማንነት ላይ እናተኩር
+++
ቸርች ውስጥ ከመሆን እና ቸርች ከመመላለስ በላይ
በክርስቶስ መሆንን እና በአብ ፊት በፅድቅ መመላለስን እናብዛ
+++
በራሳችን ላይ እንስራ ላለመሆናችን ምክንያት አንፈልግ
+++
ገነት ጽድቅ ቢኖርም ኃጢአት አልታጣበትም
ሰዶምም የርኩሰት መንደር ቢሆንም ድንግሎች ነበሩበትና
+++

✍️ ዳንኤል ብርሃኑ
@AmazingTestimony
ይህን ያውቁ ኖሯል???

በአለማችን ታሪክ ውስጥ የሰው መወለድ ትልቅ ዜና ሆኖ አያውቅም! የሚገርም አዲስ ነገርም አይደለም መውለድና መዋለድ የፍጥረት ህግ ነውና።

የኢየሱስ መወለድ ግን ለምድርም ለሰማይም አግራሞትን የጫረ ነበር። መላእክት ዝም ማለት ያልቻሉበት የውልደቱን የምስራች ከሰው ቀድመው ያወጁበት ፤ ምንም ምድር ባትነቃም በእንግዶች ብዛት ለልዑሉ ስፍራ ባይገኝለትም ከሰው የተረሱት እረኞች በመላእክት የተበሰረውን ደስታ ለመስማት የቻሉበት በወቅቱ እንደዛሬው የተሰየመ ጤና ጣቢያ ይኑር አይኑር ባላውቅም በረት ለክብር የታደለበት በእንስሶች ሰፈር አዳኙ የተገኘበት ፤ ኮከብ ከሰማይ ድምቀት አልፎ እየተራመደ አቅጣጫ ጠቋሚ የሆነበት ሰብአሰገሎቹ ለገንፎ ሳይሆን ለስግደት ጉዞ የጀመሩበት ለንጉሱ የሚገባውን እጅ መንሻ ከስግደት ጋር ለህጻኑ የሰጡበት ፤ የጊዜው ገዢ በህጻን ንጉስ መወለድ ልቡ የተተረከከበት አስደናቂ የልደት ኩነቶች ናቸው።

“ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም።”
  — ኢሳይያስ 9፥1

ጭንቀት መጨነቅ የጀመረበት ጨለማ ስፍራ ሊያጣ የሆነበት አንገት ደፊው የሰው ልጅ ቀና አለቃ ነኝ ባዩ ጨለማ ደፋ ሊል መንገድ የተጀመረበት የጠላት ተራራ ሊደረመስ የድል ድማሚት የተቀበረበት ተጨቁነው ለነበሩ የጸሐይ ጮራ ሸክም ለከበደባቸው የነጻነት ዜና ሊሰማ ጉዞ የተጀመረበት ፤ በአጋንንት መንደር ሁካታ በሰው ልጆት ሰፈር እልልታ ሊሰማ አስጨናቂው ኃጢአት ተገፎ የሚጸንሰው ሞት ጨንግፎ ህይወት ለእያንዳንዱ ሊታደል ሰጪው ከሰማይ የወረደበት ድንቅ የሆነ የመወለድ እለት ነበር።

ተሾመ ፣ ቻላቸው እና መሰሎቹን ሳይሆን ባለብዙ ስም የሆነ ህጻን ድንቅ የሆነ መካር ፣ ኃያል የሆነ አምላክ ፣ ዘላለማዊ አባት ፣ የሰላም አለቃ የሆነ ለሰላሙ ፍጻሜ የሌለው "አዳኝ" የሚለውን ስም የያዘ ህጻን ስሙ ማንነቱ የሆነለት የእውነትም አዳኝ የሆነ ልዑል የተወለደበት እለት ነበር።

ይህን ያውቁ ኖሯል???

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምንኛ ታላቅ ነው! እኛም እንዲሁ ልጆቹ ነን።
1 ዮሐንስ 3:1


በእርግጥ ፍቅር ርካሽ አደለም! በፍጥረት ህግ ለሰው ፍቅር ለመስጠት አንዳች ግንኙነት አልያም መንደርደሪያ መንገድ የግድ ያስፈልጋል። የአብዛኛዎቻችን ግንኙነትም የተጠበቀ ነው። በዙሪያችን ላሉ መልካም ሰዎች ብቻ በእኛ ዘንድ ስፍራ እንዳላቸው ለማሳወቅ የምናደርጋት ጥቂት ነገር የፍቅራችን መግለጫ ሆና ትሰየማለች።

"አብ ግን እንዴት ፍቅርን የሚያክል ትልቅና ውድ ሃብት በእኛ ላይ አትረፍርፎ ለማፍሰስ ወደደ"? በእርግጥስ ተግብቶን ነውን???

አባት ፍቅሩን በህይወታህ/ሽ ላይ ሲያፈስ አንተ/ቺ ምንም አይነት ሰው ነበርክ/ሽ?
___ መልሱን ለእናንተ እተዋለሁ።

እግዚአብሔር ጋር የፍቅር ስስት የለም። ማንም ሊሰጥ በማይችለው ልክ ፍቅሩን ለሰው ልጆች ሁሉ ሰጥቷል። ጨለማ ፣ ኃጢአተኛ ፣ ሞት የሚገባው ፣ መቀጣት ያለበት ፣ የዘላለም ፍርድ የሚጠብቀው ፣ የእግዚአብሔር ቁጣ ተቀባይ...በጥቂቱ ይህ ነበር የእኛ ማንነት። ነገር ግን፦

ነገር ግን በምሕረቱ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ፣  በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው።
ኤፌሶን 2:4-5


በልጁ ውልደት ህያው የመሆናችን ዜና ተበስሯል ፣ የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን መንገዱ ተጀምሯል ፣ የፍቅርን ትርጉም አውቀናል ፣ ተስፋችን ለምልሟል። የተወለደው ቅዱስ ክብር ይገባዋል።

ማራናታ ፤ አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ና።
ራእይ 22:20


(ናቲ ማራናታ | ታህሳስ 28-2016)
"በሞተ ጊዜ: ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኃጢአት ሞቶአል፤ ነገር ግን በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖራል።”
— ሮሜ 6፥10

🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐

በቱሚም የአምልኮ ህብረት የተዘጋጀ
ልዩ የአምልኮ ምሽት


(💥 ልኑርልህ 💥)


የፊታችን እሁድ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ማራናታ አየርጤና አጥቢያ ቤተክርስቲያን

አድራሻ:- 📍
ከአየርጤና ወደ አለምባንክ በሚወስደው መንገድ ሜሪት አካዳሚ 50 ሜትር ገባ ብሎ


👉 ለበለጠ መረጃ 0947330001 ይደውሉ
Join us @mezmuroch1
👀 እይታችን ጌታችን ላይ ከሆነ የእውነት ምንም አያስደነግጠንም! አምነውት ያለፉ በህይወታቸው ይናገራሉ! እኔም በብዙ ትግል ውስጥ ሆኜ የሚናወጠው ባህርና የሚያስጨንቀው ነፋስ ከከፍታዬ እንዳይጥለኝ ፤ ተፍገምግሜ እንዳልወድቅና እንዳልሰጥም በልቤም በአፌም ከመንፈስ በሆነ የውስጥ ጩኸት ጌታዬን እንዲህ እያልኩት ነው።

👀 እንዳየውህ ልቅር! ሌላውን አልመልከት!
ሳይህ አምኜሃለሁ! አንተ መሆንህ ገብቶኝ የእውነት ተራምጃለሁ! በቃ እንዳየውህ ልቅር!!!

እንደዚህ ልባርካችሁ🖐

ስትጀምሩ ጌታን አይቶ መጀመር ይሁንላችሁ!
አይናችሁ አይታችሁ በጀመራችሁት በጌታ ላይ ተተክሎ ይቅር🖐

እኔና ከእኔ ጋር የሚስማሙ ሁሉ እንዲህ እንልሃለን እንዳየንህ እንቅር🙏
መዝሙረኛው ዳዊት በአንድ ወቅት ሊወጣ የማይችልበት የጥፋት ጉድጓድና መራመድ የማያስችል ረግረግ ውስጥ ገብቶ ነበር።

👀 የሰዎች እይታ ከገባበት ሁኔታ ወጥቶ ዳግም መቆም የሚችል አልመሰላቸውም ነበር።

🤔 ዳዊት ምንም እንኳን ጉድጓድና ረግረግ ውስጥ ቢሆንም አስቸኳይ የሆኑ አጭር መንገዶችን ከመጠቀም ይልቅ ማንም ሊቆይ በማይችልበት አጣብቂኝ ውስጥ ሆኖ እግዚአብሔር አምላኩን ይጠብቅ ነበር።

🗻 በስተመጨረሻም አምኖት የጠበቀው ጌታ ደረሰለትና ከነበረበት ሁኔታ አወጣው። ታሪኩን እንደገና አሳመረለት። ዳዊትም ከጉድጓዱና ከጭቃው ወጥቶ በዓለት ላይ ቆመ አረማመዱም ጸና።

📖 መዝ 40:1-3

🗣 በማይመቹ አጣብቂኝ ሁኔታዎች ውስጥ ብንሆንም እንኳን "በመቆየት" ውስጥ የሚገኘውን የእግዚአብሔርን እርዳታ ለመቀበል የቆረጥንና የተዘጋጀን ከሆንን እግዚአብሔር ዘንበል ብሎ ነገራችንን ይቀይራል። አንወጣም ካልንበት ውስጥ ወጥተን ዳግም እንራመዳለን እንጸናለን!

🙌 እግዚአብሔር ሆይ ጸንተው የጠበቁህ ፍጻሜያቸው አምሯልና ቆይተን ደጅ በመጥናት በአንተ የምንጎበኝና የምንጸና ሰዎች አድርገን! እንጠብቅህ😔🙏

@AmazingTestimony
👨‍🦳የእግዚአብሔር ባሪያ አብርሃም ከሎጥ ጋር ለመለያየት ሲወስን "በዕይታ" ምርጫ የተሻለውን ይወስድ ዘንድ በሩን ሁሉ ክፍት አደረገለት።

👀 ሎጥ አሻግሮ የተመለከተው ምድር ሁሉም ሰው ከ💯/💯 የሚሰጠው ገነት የመሰለ አረንጓዴ ምድር ነው ፤ ያም ጸናለት።

👨‍🦳 አብርሃም ግን ነገውን ከእግዚአብሔር ጋር ያየ ሰው ነበር። "ሎጥ ከተለየው በኋላ... እይ" 📖 ዘፍ 13:14 ብሎ እግዚአብሔር ለእርሱ ያየለትን ያሳየው ጀመር። በእርግጥ የሎጥ አይነት አረንጓዴ ምድር ባትሆንም እግዚአብሔር ለአብርሃም ያየለት ርስት ነበረች። ...

🙏እኔ አይን የትክክለኝነት መስፈርት የአንተን ጥሩ መራጭነት አምናለሁ።
👉 ብዙ ድምጾች የሚስማሙበት ስፍራ ከአንተ እይታ ከጓደለ ድንቄም ምርጫ ብዬ አጥለዋለሁ።

👀 በአይን ሚዛን ምድረበዳ በሆንም አንተ ለእኔ ካየኸው ይመቸኛል። በበረሃ ውስጥ በምቾትህ እኖራለሁ። ከላቤ ድካም በላይ በበጎነትህ አርፋለሁ።

🙌 በሚታየው ምድረበዳዬ ላይ የማምንህ ልምላሜዬ ነህ! ከማየው በላይ አንተን አምናለሁ።

🤗 የኔ አባት አንተ ካለህ የትም ፣ መችም ፣ እንዴትም ይሁን በምንም ብቻ ይመቸኛል!

😌 አንድ ነገር ብቻ እጠይቅሃለሁ ነገም የምታይልኝን እወድደው ዘንድ ጸጋህ ይርዳኝ!

@AmazingTestimony
🙍‍♂️ ዳዊት አንድ የተረሳና እዚህ ግባ የማይባል ሰው ነበር። በቤት ውስጥም አባቱ ረስቶት በጥየቃ የታሰበ ልጅ ነበር። ነገር ግን "ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይም" ብሎ ለነብዩ ሳሙኤል እንኳን ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ቃሉ ለሚሰማው ታላቅ ነብይ እግዚአብሔር የራሱን ልዩ መገለጫ ያብራራበት ሰው ነው።

🙍‍♂️ በዳዊት ህይወት ትልቁና ሌላኛው ምዕራፉ ነው የሚያስብለው ታሪክ ታላቁን ጎልያድን በመገንደስ መጣሉ ነው። የተረሳውና ማንም የማያውቀው ዳዊት በእርሱም ሆነ በሌሎች ወገኖች ዘንድ የሚወራ የየቀን ርዕስ መሆን ጀመረ።

🔆 ይህ ታሪክ እጅግ አስገራሚ የሆኑ ጥልቅና ታላላቅ የእግዚአብሔር ስራዎችን የተመለከትንበት ነው። የተናቀው ፣ የተተወው ሰው ዛሬ ስሙ በድፍን እስራኤል ናኘ።

💪 በጊዜው "ሳኦል ሺህ ዳዊት እልፍ ገደለ" እየተባለ ቢዘፈንለትም እርሱ ግን ያንን የእስራኤልን ስጋት በምን እንደጣለ ያውቃል። ሰዎች በእጁና በኮሮጆው የያዘውን ሲመለከቱ እሱ ግን ትክክለኛውን የኃይል ምንጭ የሆነውን እግዚአብሔርን ይመለከት ነበር።

🏋🏻‍♂️ ጎልያድ የወደቀው በጠጠሯ ኃይል ሳይሆን በተገለጠው ምስጢር ነው። እርሱም የእግዚአብሔር ስም።

📖 1ሳሙ 17:45

💪 እንደማሸንፍ እርግጠኛ የምሆነው በአንተ ነው።
🚶‍♂️ ከፊቴ የቆመውን ለመጋፈጥ የምደፍረውም በአንተ ነው።
🙌 አምኜ ውጊያ የምጀምረውም በአንተ ነው።
💀 ዘርሬ የምጥለውም በአንተ ነው።

አንተ የኔ ጌታ የድሌ ምስጢር ነህ!

ማንንም በምንም ላሸንፍ ፤ ስለ ድሉ ይህንን አውቃለሁ :- በስምህ አሸንፌአለሁ🙌

🤔 ይህ ስም ለትንሹ ለዳዊት በጎልያድ ፊት ከሰራ ፤ ዛሬም ለእኔ ለትንሹ በጎልያዶቼ ፊት ይሰራልኛል።

🙌 ስምህ ይቀደስ!

@AmazingTestimony