Abay Forum
3.53K subscribers
1.44K photos
239 videos
8 files
1.04K links
Download Telegram
2
የሒደቶች ውድቀት የዋናው ነገር ውድቀት ማረጋገጫ ነው!!

አንድን አገዛዛዊ ኹነት በጥቅሉ "አልቀበለውም" ብለህ ውድቅ ስታደርገው ፡ የጉዳዩን ዝርዝር ነገሮች እያቀረቡ "እርምት የሚፈልግ" በሚመስል መልኩ እንድታወራበት ማስቻል ለየት ያለ "የማስቀየሻ" እና "ተቀባይነት" መፍጠሪያ ዘዴ ይሆናል።
ዋናውን ነገር ከእነአፈጣጠሩ ውድቅ ብታደርገውም፡ ድርቅ ብሎ በሒደቶች ላይ እንድትሟገት ያደርግሃል።

ተቃውሞህን ከዋናው ነገር ወደዝርዝር ነገሮች "እርምት ፍለጋ" ያወርድብሃል!!

📍ዝርዝሮቹን የዋናው ጉዳይ ውድቀት ማረጋገጫ ማድረግህን አትዘንጋ !!

የግንዛቤ (perception) ወጥመዱ ያለው፥ "ይሕ ነገር ቢስተካከል፡ ዋናው ኹነትስ ባልከፋ.." ተብሎ እንዲታሰብ ማድረግ ነው።

(1)

[ "ምርጫው ተቀባይነት የለውም" ብለህ ውድቅ ካደረከው በኋላ ፡ አገዛዙ ግን ለፓርላማ ወንበር መርጦ በፈቀደላቸው ሰዎችና "ፓርቲዎች" ተገቢነት ላይ እንድታወራ ያደርግሃል። ውድቅ ያደረከው አጠቃላይ የ"ምርጫ" አጀንዳ ይረሳና በዝርዝር ሒደትቹ "ስሕተትነትና ተክክለኛነት" ላይ እንድትደክም ያደርግሃል]

ልዩ የማስቀየሻ ስልት ነው !!

(2)

["ራበን፡ ጥቅማችን ይከበር" ብለው ጥያቄ ያነሱ ሐኪሞችን ወይ ሌሎች ሠራተኞችን ፡ "አስተባባሪዎች"  ያላቸውን እየሰበሰበ በየእስር ቤቱ ይወረውርና፡ የሙያተኛው የጥያቄ አጀንዳ "ከራበንና ጥቅማችን ይከበር" ወደ "የታሠሩ ይፈቱልን፣ "Free mr X" ይዞራል። ትንሽ ጠብቆህ ይፈታቸውና "እንኳን ለቤትህ አበቃህ" ወደሚል "እፎይታ" ያዞርሃል]  

📍"የታሠረ ይፈታ" የሚለው የዋናው ጥያቄ ተከታይ ሒደት ፡ የዋናውን ጥያቄ ተገቢነት ማረጋገጫና የማስመለስ ትግል አቀጣጣይ ተደርጎ ስለማይታይ ነው!!

(3)
"አገራዊ ምክክር" እና ኮሚሽን ተብዬው "ውድቅ ነው" ብለህ እየተቃወምከው ሳለ፡ "የምክክር ተሳታፊዎች" ይልና 'በእነማን ናቸው?' ያደክምሃል፣ "አጀንዳ መረጣ" ይልና "በአጀንዳው ምንነት ላይ እንድትዋከብ ያደርግሃል።
ቀድሞውኑ "ውድቅ ነው ተቀባይነት የለውም" ያልከው ጉዳይ ቢሆንም፡ ቀጣይ ንትርክህ ባቀረበልህ ዝርዝር አጀንዳዎች ላይ  እንዲሆን ያደርጋል!!

📍የሒደት ዝርዝር አጀንዳዎች ቢስተካከሉ ዋናው ነገር ላይ የተስማማህ ይመስል በቅርንጫፍ አጀንዳዎች ያዋክብሃል።

🔑 መፍትሔው ፦ ከዚህ አይነት የማስቀየሻ አጀንዳ ወጥመድ በመጠንቀቅ፡ እያንዳንዱን ዝርዝር ሒደት፡ ዋናውን ኹነት ከጅምሩ ቀድመህ ለምን ተቀባይነት እንደነሳኸው ማሳያና አስረጂ  አድርጎ ማስኬድ ይገባል‼️
3