Advanced Freshman
32.8K subscribers
717 photos
11 videos
103 files
234 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

contact us: @EEG12bot
Download Telegram
😎
በተደጋጋሚ ብዙ ልጆች የ Freshman Course ለምን አትሰጡንም እያላችሁን ትገኛላቹ👨‍🏫

🎓እንደ Advanced Freshman channel ላለፋት ተከታታይ አመታቶች ብዙ ተማሪዎችን በ Freshman ቆይታቸው ያማረ እንዲሆን ከፍተኛ እገዛ ስናደርግ ቆይተናል። በ2019 ዓ.ም ደግሞ በተሻለ እና ባማረ መልኩ እገዛችን ከእናንተ ጋር ይሆናል።

🎓ነገር ግን Placement አይታቹ እንድንጀምር አስበን ስለሆነ ሳትጨናነቁ በትእግስት ጠብቁን። ከትምህርታቹ ቀድሞ ብዙ ልታዉቋቸዉ እና ልትገነዘቧቸዉ የሚገቡ መረጃዎች ስላሉ እያንዳንዱን ነገር በሂደት የምናሳዉቃቹ ይሆናል። በእርግጥ በ Freshman ቆይታቹ ያለ አንዳች ሀሳብ ከ Advanced ጋር ጥሩ ቆይታን የምታደርጉ ይሆናል።ስለዚህ አሁን ላይ ቅድምያ መስጠት ላለባቹ ነገር ቅድሚያ ስጡ👋ግቢ ስትገቡ ጠንክረን እና ትኩረታችንን በሙሉ Freshman ላይ ስለምናደርግ ሀሳብ አይግባቹ🤗

በርቱልን እስከ መጨረሻዉ የግቢ ቆይታቹ ድረስ አብረናቹ ነን😊💪

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
52👍45🥰15👏9🔥7🙏7🕊3😇3🤗3
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ
============================
በ2019 ዓ.ም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና ኦንላይን (Online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡

የትምህርት መስኮች፡-

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ
- ኮምፒዩተር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ

አፕላይድ ሳይንስ
- አፕላይድ ባዮሎጂ
- አፕላይድ ኬሚስትሪ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፋርማሲ
- አፕላይድ ፊዚክስ
- አፕላይድ ጂኦሎጂ
- አፕላይድ ማቲማቲክስ

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ
- ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ

አፕላይድ ሳይንስ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፉድ ሳይንስና አፕላይድ ኒዩትሪሽን
- ጂኦሎጂ
- ባዮቴክኖሎጂ

የምዝገባ ጊዜ፡-
- ከነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡

የምዝገባ ቦታ፡
- የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡- በድህረ ገፃችን የምዝገባው ቀን ካበቃበት በኋላ እናሳውቃለን ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-
- በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-
· የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
· በቂ አመላካቾች የሌሉባቻው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡
· ለፈተና የሚቀርቡት የአመልካቾች ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡- www.aastu.edu.et ; www.astu.edu.et እንደአመቺነቱም በe-mail የሚገለፅ ይሆናል፡፡
· አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡
· ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡

· አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
· የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡
· በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል፡፡
· በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል፡፡
· በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
· በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከታች የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች እና ቴሌግራም ቻናላችንን መጎብኘት ይቻላል፡፡

www.astu.edu.et; www.aastu.edu.et

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
43👍8🔥2👏2🙏2
🖊 የ2019 Freshman ተማሪዎች በመጀመርያ እና በሁለተኛ ሴሚስተር የሚወስዷቸው 20 ኮርሶች:-

📌 First Semester

📚communicative English
📚Geography
📚physcholgy
📚Logic And critical Thinking
📚Physical Fitness
📚general physics
📚Economics
📚Maths for natural.
📚Maths for social


📌Second Semester

📚Inclusiveness
📚Introduction to Emerging Technology
📚 Anthropology
📚 Global Trend
📚 Civic and Moral Education
📚 General Chemistry
📚 General Biology
📚 Entrepreneurship
📚 Histroy of ethiopia and horn africa
📚 Applied Mathematics I
📚 Communicative English 2

🎓 እነዚህ በ የዮኒቨርስቲዎች ለፍሬሽማን ተማሪዎች የሚሰጡ ኮርሶች ናቸው ፤ እንደየ ግቢዎች የመጀመርያ እና ሁለተኛ ሴሚስተር የሚሰጡት ይለያያሉ ፤ አንዳንድ ግቢዎች መጀመርያ ሴሚስተር የሚሰጠው ሌሎች ጋር በሁለተኛ ሴሚስተር ሊሰጥ ይችላል።

በተረፈ እኛም ስለምናግዛቹ ሀሳብ እንዳይገባቹ🤗። 4GPA ማምጣት የሚፈልግ ጠንክሮ ከእኛ ጋር ዝግጅቱን ያደርጋል💪


JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
57🙏15👍9🔥1🕊1
ሰበር ዜና‼️ የ2018 ሪሜዲያል ውጤት ተለቋል

የ ሬሜዲያል ዉጤት Offical ተለቋል
Link:-https://result.ethernet.edu.et

@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
32🔥5🥰4😇2
Advanced Freshman
ሰበር ዜና‼️ የ2018 ሪሜዲያል ውጤት ተለቋል የ ሬሜዲያል ዉጤት Offical ተለቋል Link:-https://result.ethernet.edu.et @ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
የRemedial ተማሪዎች ቅሬታ


እኛ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዩኒቨርሲቲዎች የምንገኝ የ2018 ዓ.ም የሬሜዲያል (Remedial) ተማሪዎች ስንሆን፣ የትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው የፈተና ውጤት ላይ የገጠመን ከፍተኛ ችግር እንዲሰማልን እንፈልጋለን።
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የNatural Science ተማሪዎች ውጤት ሙሉ በሙሉ Disqualified የተደረገ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም በወሎ፣ አርባምንጭ፣ ሚዛንቴፒ፣ ደብረብርሃን፣ ሰመራ፣ ባህርዳር፣ወልቂጤ፣ ኦዳ ቡልቱም ፣ ጎንደር ደግሞ የNatural እና Social Science ተማሪዎችም ውጤት ላይ ተመሳሳይ ችግሮችና የተጋነኑ Disqualified/ዝቅተኛ ውጤቶች አጋጥመውናል።
ይህ በብዙ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ በአንድ ላይ መከሰቱ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረብን ሲሆን፣ የቴክኒክ ወይም የሲስተም ስህተት ሊሆን እንደሚችል እናምናለን። በመሆኑም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጉዳዩን በአስቸኳይ መርምሮ እስታንዳርድ ማስተካከያ እንዲያደርግልን ድምፃችን ሆናችሁ ታሰሙልን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።

የ 2018 የሬሜዲያል ተማሪዎች

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5234🙏12
🧳በ 2019 ግቢ ለምትገቡ ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ላይ ይሄን የምንላችሁን ስሙ❗️

🧑‍🎓 በዚህ ሰሞን ሁላችሁም ውጤታችሁን አይታችኋል። ሆኖም ውጤት መጥቶላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች ፣ «የትኛውን University ልምረጥ?» የሚለው ጉዳይ ነው አሳሳቢ ነው።

📍በቀጣዩ ሳምንትም የUniversity ምደባ ሙሉ ተብላቹህ በት/ቤቶቻችሁ ትጠራላችሁ!!

🤔 ዩኒቨርሲቲ አምስት ና ከዛ በላይ አመታቶችን የምታሳልፉበት ነው ፥ ህይወትን በራሳችሁ መንገድ ከ 0 የምትጀምሩበት ነው። ስለዚህ የሚቀጥሉት አምስት ና ከዛ በላይ አመታት የምትኖሩበትን ቦታ በጥንቃቄ መምረጥ ያስፈልጋል።

የትኛው ዩኒቨርሲቲ እና ምን አይነት Department መግባት እንዳለባችሁ በጥንቃቄ ማሰብ አለባችሁ። ይህን ለማድረግ ደግሞ እነዚህን ነገሮች አስቡባቸው፤

1. መግባት የምትፈልጉትን Department ለዩ

በጣም የሚስባችሁ የትኛው የትምህርት አይነት እንደሆነና ወደፊት ምን መስራት እንደምትፈልጉ ለራሳችሁ ግልጽ ማድረግ።

ለምሳሌ website, mobile apps የመሣሠሉት ላይ መስራት የምትፈልጉ ከሆነ፣  እነዚህን ትምህርት የሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎችን መምረጥ ትችላላችሁ ፤ like Software, computer science ,it department ያላቸውን።

2. ዩኒቨርሲቲው በቡዙ ነገሮች የተሻለ መሆኑን አረጋግጡ

ዩኒቨርሲቲው ጥሩ ስም ካለውና ጥራት ያለው ትምህርት የሚሰጥ ከሆነ አሪፍ ነው። በተለይ ደግሞ እናንተ የምትፈልጉት department  ምን ያህል ጥራት እንዳለው ማረጋገጥ አለባችሁ።

መምህራኖቹ ጥሩ እውቀትና ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው።

ቤተ መጽሐፍት፣Computer class፣ wifi፣ የላብራቶሪ መሳሪያዎችና ሌሎች ነገሮች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መሟላት አለባቸው።

  3. አቅማችሁን እወቁ

እንደ አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር  ያሉ ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተፈላጊ የሆኑ Departመንቶች ላይ ለመግባት ፍክክር አለ። ምክንያቱም ብዙ ጎበዝ ተማሪዎች ከ እነዚ ዩኒቨርቲዎች ስለሚኖሩ እና አብረዋችሁ ስለሚወዳደሩ ውጤታችሁ(GPA) ከፍ ያለ መሆን አለበት።

ስለዚህ የትምህርት ፍላጎታችሁን ብቻ ሳይሆን ውጤታችሁንም እና አቅማችሁንም እያያችሁ የሚመጥናችሁን ዩኒቨርሲቲ መምረጥ አለባችሁ።

ለምሳሌ Adiss Ababa ላይ Software ለመግባት Gpa ከ 3.97 ጀምሮ መስራት ሊጠበቅባችሁ ይችላል፤ እንደ Debre brihan diredawa የመሣሠሉት ደግሞ ከ 3.5፣  3.7 ጀምሮ ሰርታችሁ መግባት ትችላላችሁ።

ይሄ ብዙ ተማሪዎች የሚሸወዱበት ነው በትኩረት በደንብ አስቡበት፤ አቅማችሁን እወቁ!

...ሌሎች የሰላም ሁኔታ የመሣሠሉት እንዳሉ ሆነው እነዚህን ነገሮች በማሰብ ምርጫ አድረጉ።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN 👍
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
39🙏9🥰3👍2