Advanced Freshman
32.8K subscribers
717 photos
11 videos
103 files
234 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

contact us: @EEG12bot
Download Telegram
የተማሪዎች ቅሬታ‼️

ጉዳዩ፦ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እንደገና እንዲጣራ ስለመጠየቅ

ክቡራን የትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች፣እኛ የ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ስንሆን፣ የተሰጠን የፈተና ውጤት ከጠበቅነውና ከፈተናው በፊት ካደረግነው ዝግጅት ጋር በጣም የሚለያይ ሆኖ በማግኘታችን፣ ውጤታችን እንደገና በጥንቃቄ እንዲጣራልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ከእኛ መካከል Natural Science እና Social Science ተማሪዎች የምንገኝ ሲሆን፣ በNatural Science ዘርፍ Maths፣ Biology፣ Physics፣ SAT እና Chemistry፣ በSocial Science ዘርፍ ደግሞ SAT፣ Economics፣ Geography፣ History እና Maths በትጋት ተዘጋጅተን ፈተናውን ወስደናል።
ሆኖም ያገኘነው ውጤት ከጠበቅነው ውጤት ጋር በእጅጉ የሚለያይ በመሆኑ፣ የፈተና መልስ ወረቀቶቻችን፣ የተመዘገቡ ውጤቶች እና የውጤት ሂደቱ በድጋሚ በጥንቃቄ እንዲመረመሩልን እንጠይቃለን።
ይህ ጥያቄ የአንድ ተማሪ ብቻ ሳይሆን፣ ተመሳሳይ ችግር ያጋጠማቸውን ተማሪዎች በመወከል የቀረበ የጋራ ጥያቄ ነው። ስለሆነም ጉዳዩን በተለየ ትኩረት በመመልከት፣ ተገቢውን የውጤት ድጋሚ ምርመራ እንዲደረግልን እንጠይቃለን።

ስለዚህ ጥያቄያችንን በአግባቡ ተመልክታችሁ፣ የፈተና ውጤታችን በድጋሚ እንዲጣራ እና ትክክለኛው ውጤታችን እንዲረጋገጥልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ከአክብሮት ጋር።

Advanced Freshman ቻናል ለሚመለከተዉ አካል እንዲደርስ ጥረት ምናደርግ ይሆናል።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙏28760👍40
ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ በፍጥነት እንዲያከናውኑ እየተሠራ ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፥ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምልመላና ቅበላ ካከናወኑ በኋላ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም በፍጥነት ጥሪ እንዲያደርጉ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም እንዲጀምር መርሐ ግብር የተያዘ ሲሆን እሱን ለመጠበቅ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😢3427👍13🙏7
🌐Software የሚሰጡ ዩንቨርሲቲዎች ዝርዝር 🎓

🟡 Mekelle Universitiy
🟡 Gonder University
🟡 Bahirdar Universitiy
🟡 Debre-Markos Universitiy
🟡 Wollo University
🟡 Haremaya Universitiy
🟡 Jimma Universitiy
🟡 Bulehora Universitiy
🟡 Jigjiga Universitiy
🟡 Debre-Birhan Universitiy
🟡 Arbamich Universitiy
🟡 Wachamo Universitiy
🟡 Wolkite Universitiy
🟡 Adis Ababa University
🟡 AASTU ,ASTU
🟡 INJIBARA UNIVERSITY
🟡 Dire Dawa University

ቆየት ያለ list ስለሆነ ዘንድሮ update ሊኖር ይቻላል!


JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
33👍6🙏4👏1
#ጥቆማ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር (በመንግሥት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሐግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

መስፈርቶች
➻ በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው (COC) ያለፉ
➻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (UAT) ይወስዳሉ

የምዝገባ ጊዜ 👇
እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ድረስ

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://admission.aau.edu.et

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (UAT) ከጳጉሜን 02-04/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
15👍3🙏3
😎
በተደጋጋሚ ብዙ ልጆች የ Freshman Course ለምን አትሰጡንም እያላችሁን ትገኛላቹ👨‍🏫

🎓እንደ Advanced Freshman channel ላለፋት ተከታታይ አመታቶች ብዙ ተማሪዎችን በ Freshman ቆይታቸው ያማረ እንዲሆን ከፍተኛ እገዛ ስናደርግ ቆይተናል። በ2019 ዓ.ም ደግሞ በተሻለ እና ባማረ መልኩ እገዛችን ከእናንተ ጋር ይሆናል።

🎓ነገር ግን Placement አይታቹ እንድንጀምር አስበን ስለሆነ ሳትጨናነቁ በትእግስት ጠብቁን። ከትምህርታቹ ቀድሞ ብዙ ልታዉቋቸዉ እና ልትገነዘቧቸዉ የሚገቡ መረጃዎች ስላሉ እያንዳንዱን ነገር በሂደት የምናሳዉቃቹ ይሆናል። በእርግጥ በ Freshman ቆይታቹ ያለ አንዳች ሀሳብ ከ Advanced ጋር ጥሩ ቆይታን የምታደርጉ ይሆናል።ስለዚህ አሁን ላይ ቅድምያ መስጠት ላለባቹ ነገር ቅድሚያ ስጡ👋ግቢ ስትገቡ ጠንክረን እና ትኩረታችንን በሙሉ Freshman ላይ ስለምናደርግ ሀሳብ አይግባቹ🤗

በርቱልን እስከ መጨረሻዉ የግቢ ቆይታቹ ድረስ አብረናቹ ነን😊💪

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
52👍45🥰15👏9🔥7🙏7🕊3😇3🤗3
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ
============================
በ2019 ዓ.ም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና ኦንላይን (Online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡

የትምህርት መስኮች፡-

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ
- ኮምፒዩተር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ

አፕላይድ ሳይንስ
- አፕላይድ ባዮሎጂ
- አፕላይድ ኬሚስትሪ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፋርማሲ
- አፕላይድ ፊዚክስ
- አፕላይድ ጂኦሎጂ
- አፕላይድ ማቲማቲክስ

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ
- ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ

አፕላይድ ሳይንስ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፉድ ሳይንስና አፕላይድ ኒዩትሪሽን
- ጂኦሎጂ
- ባዮቴክኖሎጂ

የምዝገባ ጊዜ፡-
- ከነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡

የምዝገባ ቦታ፡
- የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡- በድህረ ገፃችን የምዝገባው ቀን ካበቃበት በኋላ እናሳውቃለን ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-
- በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-
· የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
· በቂ አመላካቾች የሌሉባቻው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡
· ለፈተና የሚቀርቡት የአመልካቾች ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡- www.aastu.edu.et ; www.astu.edu.et እንደአመቺነቱም በe-mail የሚገለፅ ይሆናል፡፡
· አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡
· ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡

· አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
· የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡
· በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል፡፡
· በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል፡፡
· በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
· በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከታች የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች እና ቴሌግራም ቻናላችንን መጎብኘት ይቻላል፡፡

www.astu.edu.et; www.aastu.edu.et

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
43👍8🔥2👏2🙏2
🖊 የ2019 Freshman ተማሪዎች በመጀመርያ እና በሁለተኛ ሴሚስተር የሚወስዷቸው 20 ኮርሶች:-

📌 First Semester

📚communicative English
📚Geography
📚physcholgy
📚Logic And critical Thinking
📚Physical Fitness
📚general physics
📚Economics
📚Maths for natural.
📚Maths for social


📌Second Semester

📚Inclusiveness
📚Introduction to Emerging Technology
📚 Anthropology
📚 Global Trend
📚 Civic and Moral Education
📚 General Chemistry
📚 General Biology
📚 Entrepreneurship
📚 Histroy of ethiopia and horn africa
📚 Applied Mathematics I
📚 Communicative English 2

🎓 እነዚህ በ የዮኒቨርስቲዎች ለፍሬሽማን ተማሪዎች የሚሰጡ ኮርሶች ናቸው ፤ እንደየ ግቢዎች የመጀመርያ እና ሁለተኛ ሴሚስተር የሚሰጡት ይለያያሉ ፤ አንዳንድ ግቢዎች መጀመርያ ሴሚስተር የሚሰጠው ሌሎች ጋር በሁለተኛ ሴሚስተር ሊሰጥ ይችላል።

በተረፈ እኛም ስለምናግዛቹ ሀሳብ እንዳይገባቹ🤗። 4GPA ማምጣት የሚፈልግ ጠንክሮ ከእኛ ጋር ዝግጅቱን ያደርጋል💪


JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
57🙏15👍9🔥1🕊1