Advanced Freshman
32.8K subscribers
717 photos
11 videos
103 files
233 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

contact us: @EEG12bot
Download Telegram
አንዳንዶቻችሁ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባቿሀል👏
አንዳንዶቻችሁ ጥሩ ስኬት ላይ ደርሳችኋል😊

🌀ሌሎቻቹ ደግሞ ..… ውጤቱ እናንተ ባሰባችሁበት መንገድ አልሄደም 💔ግን እባካችሁ, ልባችሁ እንዲጎዳ አትፍቀዱ!! ራሳችሁን ለማሻሻል ሁለተኛ ዕድል አሁንም አለ-Remedial🫶

📖 አስታውሱ ይህ ፈተና ዉጤት የህይወት መጨረሻ አይደለም።ገና ረጅም ጉዞ አለ፣ ህልማችሁ አሁንም በህይወት አለ፣ እና ዋጋችሁ በወረቀት ላይ ካለው ቁጥር እጅግ የላቀ ነው🫶

🔜ምክንያቱም ከፊት ያለው መንገድ በአዲስ በሮች የተሞላ ነው እና የእናንተ ምርጥ ምዕራፎች ገና አልተጻፉም 🫴✍️💬

🔗 በመጨረሻም ትምህርት ሚኒስቴር የRemedial መግብያ ነጥብ እንዲሁም የዩንቨርስቲ ምደባ ስለሚያሳዉቅ አስፈላጊዉን መረጃ ተከታትለን ምናደርሳችሁ ይሆናል🤚

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
36🙏35🎉11💯8😢5👌5👍4😘3👏2
🎓በ2019 ፍረሽማን ተማሪ የሆናችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እስቲ አንዴ እጅ ወደ ላይ👋

ዘንድሮ በደምብ አርገን ፍረሽማን ላይ ደገፍገፍ እናረጋቿለን

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍99🫡47👏1916🙏10🤝3
Advanced Freshman pinned «በአጠቃላይ ዉጤታቹ ምን ይመስላል?»
#JalalGirma👏

የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ጃላል ግርማ በ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና 591. 6 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።

#ODA_SPECIAL_BOARDING_SCHOOL

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏7136👍13🔥7😢1🙏1
🎓Hello👋 2019 batch Freshman Students 🎓

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍8441😇30🙏29🫡27🥰17🤗17👏14😎12🔥5
13🫡7😇6🙏4👍3🆒1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎓 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2019 ዓ.ም ቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የወጣ ማስታወቂያ

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
8🙏5👍2
Advanced Freshman
ፍሬሽማንን የት ለመማር አሰባችሁ🤔
ከ Vote እንደተረዳነው ብዙ ልጆች AAU-Adis Ababa University መግባት እንደምትፈልጉ ተገንዝበናል።

ወደ አዲስ አበባ University ለመግባት ደግሞ የመግቢያ ፈተና እንደምትወስዱ ይታወቃል። ይህንን የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ ደግሞ መዘጋጀት አለባቹ።

ለዝግጅት እንዲሆናቹ አንድ ቻናል እንጠቁማቹ በዚህች በቀረችው ጥቂት ጊዜ ውስጥ እንድትዘጋጁ ይረዳችሁአል👍

👇👇
@UATpreparation
@UATpreparation
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
14🥰3🙏2
አሳዛኝ ዜና😔😭

12ኛ ክፍል ፈተና የወደቀች ልጅ ራሷን አጠፋች
ዛሬ በሲዳማ ክልል በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ዳዬ አንድት ሴት ልጅ ከ12ኛ (entrance) ተፈታኝ ባለማለፏ ምክንያት ተበሳጭታ #ቦኖራ ተብሎ በሚጠራው ጥልቅ ወንዝ ውስጥ እራሷን አጥፍታለች።
ነፍስ ይማር

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭443💔13122😢19😨11🙏10😱6👍3😇32🆒2
🟡በቅርቡ ኢንትራንስ የተፈተናቹ ተማሪዎች ከትንሽ ጊዜ በኃላ ዩኒቨርስቲ ምርጫ እንድትሞሉ ትጠየቃላቹ፡፡ 

🔶ዩኒቨርስቲ ለዓመታት የምትቆዩበት ስለሆነ ፤ ዩኒቨርስቲ ስትመርጡ እነዚህን ማወቅ አለባቹ:

1. የምትመርጧቸው ዩኒቨርስቲዎች የምትፈልጉት field/department እንደሚሰጡ ማወቅ አለባቹ ይሄ ዋነኛው ነው። መማር የምትፈልጉትን field/department  ካልወሰናቹ ካሁኑ shortlist አድርጓቸው፡፡

2. ስለዩኒቨርስቲው ትምህርት ጥራት በተለይ እናንተ መማር የምትፈልጉት field/department  በደንብ አጣሩ፡፡

3. የምትመርጧቸውን ዩኒቨርስቲዎች እና ከተማውን youtube ላይ እዩ ፤ እዛ ዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚማር ተማሪ ሰው በሰው ጠይቁ፡፡ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ወንድም / እህት ካላቹ ከእነሱ ጋር High school አብረው የተማሩ ሌላ ጊቢ የደረሳቸው ተማሪዎች ስለሚኖሩ እነሱ ሊያጠያይቁላቹ ይችላሉ፡፡

4. እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (AAU) በጣም ሀሪፍ የሚባሉ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በጣም ተፈላጊ የሆኑ department እንደ Medicine, Software Engineering መግባት በጣም ከባድ ነው፡፡ ውጤት በደንብ ካልሰራቹ በስተቀር በጣም ተፈላጊ የሆነ department የማግኘታቹ እድል ጠባብ ነው ፤ ስለዚህ የመጀመሪያ ምርጫቹ ያልሆነ department ውስጥ ልትመደቡ ትችላላቹ፡፡

5. ዩኒቨርስቲ ምርጫ ስትሞሉ ከክፍል ጓደኞቻቹ ወይም ዩኒቨርስቲ ከሚማር ወንድም/እህታቹ ጋር አብሯቹ ሙሉ። የምትሞሉት ዩኒቨርስቲ እንደየፍላጎታቹ እና እንደምታገኙት ውጤት ሊለያይ ይችላል። ግን አብሯቹ ያሉት ጓደኞቻቹ ወይም ወንድም/እህታቹ ስለ አንዳንድ ዩኒቨርስቲ መረጃ ሊኖራቸው ይችላል፡፡

6. የምትመርጧቸው ዩኒቨርስቲ ከከተማቹ ውጪ ከሆነ ፤ ስለከተማው ደህንነት እና ጸጥታ መረጃ አሰባስቡ፡፡

7. ዩኒቨርስቲው ያለበት ከተማ አየር ጸባይ ከግምት ውስጥ አስገቡ። አንዳንድ ተማሪዎች በጣም ሞቃታማ ቦታ ለዓመታት መኖር ሊያስቸግራቸው ይችላል!

🌐በተጨማሪም የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎችን አጠቃላይ መረጃ : የመጨረሻ placement እስክትሞሉበት ቀን ድረስ ገለፃ እናደርግላቿለን::

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
47👍7🥰4
የአምና የRemedial የመቁረጫ ነጥብ

➡️የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216

➡️የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204

➡️ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

➡️የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

➡️ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165

የዘንድሮዉ እስካሁን አለተገለፀም።አዲስ መረጃ ካለ የምናደርሳቹ ይሆናል።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN👍
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙏1510👍4
የተማሪዎች ቅሬታ‼️

ጉዳዩ፦ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እንደገና እንዲጣራ ስለመጠየቅ

ክቡራን የትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች፣እኛ የ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ስንሆን፣ የተሰጠን የፈተና ውጤት ከጠበቅነውና ከፈተናው በፊት ካደረግነው ዝግጅት ጋር በጣም የሚለያይ ሆኖ በማግኘታችን፣ ውጤታችን እንደገና በጥንቃቄ እንዲጣራልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ከእኛ መካከል Natural Science እና Social Science ተማሪዎች የምንገኝ ሲሆን፣ በNatural Science ዘርፍ Maths፣ Biology፣ Physics፣ SAT እና Chemistry፣ በSocial Science ዘርፍ ደግሞ SAT፣ Economics፣ Geography፣ History እና Maths በትጋት ተዘጋጅተን ፈተናውን ወስደናል።
ሆኖም ያገኘነው ውጤት ከጠበቅነው ውጤት ጋር በእጅጉ የሚለያይ በመሆኑ፣ የፈተና መልስ ወረቀቶቻችን፣ የተመዘገቡ ውጤቶች እና የውጤት ሂደቱ በድጋሚ በጥንቃቄ እንዲመረመሩልን እንጠይቃለን።
ይህ ጥያቄ የአንድ ተማሪ ብቻ ሳይሆን፣ ተመሳሳይ ችግር ያጋጠማቸውን ተማሪዎች በመወከል የቀረበ የጋራ ጥያቄ ነው። ስለሆነም ጉዳዩን በተለየ ትኩረት በመመልከት፣ ተገቢውን የውጤት ድጋሚ ምርመራ እንዲደረግልን እንጠይቃለን።

ስለዚህ ጥያቄያችንን በአግባቡ ተመልክታችሁ፣ የፈተና ውጤታችን በድጋሚ እንዲጣራ እና ትክክለኛው ውጤታችን እንዲረጋገጥልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ከአክብሮት ጋር።

Advanced Freshman ቻናል ለሚመለከተዉ አካል እንዲደርስ ጥረት ምናደርግ ይሆናል።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙏28760👍40
ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ በፍጥነት እንዲያከናውኑ እየተሠራ ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፥ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምልመላና ቅበላ ካከናወኑ በኋላ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም በፍጥነት ጥሪ እንዲያደርጉ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም እንዲጀምር መርሐ ግብር የተያዘ ሲሆን እሱን ለመጠበቅ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😢3427👍13🙏7
🌐Software የሚሰጡ ዩንቨርሲቲዎች ዝርዝር 🎓

🟡 Mekelle Universitiy
🟡 Gonder University
🟡 Bahirdar Universitiy
🟡 Debre-Markos Universitiy
🟡 Wollo University
🟡 Haremaya Universitiy
🟡 Jimma Universitiy
🟡 Bulehora Universitiy
🟡 Jigjiga Universitiy
🟡 Debre-Birhan Universitiy
🟡 Arbamich Universitiy
🟡 Wachamo Universitiy
🟡 Wolkite Universitiy
🟡 Adis Ababa University
🟡 AASTU ,ASTU
🟡 INJIBARA UNIVERSITY
🟡 Dire Dawa University

ቆየት ያለ list ስለሆነ ዘንድሮ update ሊኖር ይቻላል!


JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
33👍6🙏4👏1
#ጥቆማ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር (በመንግሥት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሐግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

መስፈርቶች
➻ በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው (COC) ያለፉ
➻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (UAT) ይወስዳሉ

የምዝገባ ጊዜ 👇
እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ድረስ

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://admission.aau.edu.et

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (UAT) ከጳጉሜን 02-04/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
16👍3🙏3
😎
በተደጋጋሚ ብዙ ልጆች የ Freshman Course ለምን አትሰጡንም እያላችሁን ትገኛላቹ👨‍🏫

🎓እንደ Advanced Freshman channel ላለፋት ተከታታይ አመታቶች ብዙ ተማሪዎችን በ Freshman ቆይታቸው ያማረ እንዲሆን ከፍተኛ እገዛ ስናደርግ ቆይተናል። በ2019 ዓ.ም ደግሞ በተሻለ እና ባማረ መልኩ እገዛችን ከእናንተ ጋር ይሆናል።

🎓ነገር ግን Placement አይታቹ እንድንጀምር አስበን ስለሆነ ሳትጨናነቁ በትእግስት ጠብቁን። ከትምህርታቹ ቀድሞ ብዙ ልታዉቋቸዉ እና ልትገነዘቧቸዉ የሚገቡ መረጃዎች ስላሉ እያንዳንዱን ነገር በሂደት የምናሳዉቃቹ ይሆናል። በእርግጥ በ Freshman ቆይታቹ ያለ አንዳች ሀሳብ ከ Advanced ጋር ጥሩ ቆይታን የምታደርጉ ይሆናል።ስለዚህ አሁን ላይ ቅድምያ መስጠት ላለባቹ ነገር ቅድሚያ ስጡ👋ግቢ ስትገቡ ጠንክረን እና ትኩረታችንን በሙሉ Freshman ላይ ስለምናደርግ ሀሳብ አይግባቹ🤗

በርቱልን እስከ መጨረሻዉ የግቢ ቆይታቹ ድረስ አብረናቹ ነን😊💪

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
52👍45🥰15👏9🔥7🙏7🕊3😇3🤗3
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ
============================
በ2019 ዓ.ም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና ኦንላይን (Online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡

የትምህርት መስኮች፡-

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ
- ኮምፒዩተር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ

አፕላይድ ሳይንስ
- አፕላይድ ባዮሎጂ
- አፕላይድ ኬሚስትሪ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፋርማሲ
- አፕላይድ ፊዚክስ
- አፕላይድ ጂኦሎጂ
- አፕላይድ ማቲማቲክስ

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ
- ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ

አፕላይድ ሳይንስ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፉድ ሳይንስና አፕላይድ ኒዩትሪሽን
- ጂኦሎጂ
- ባዮቴክኖሎጂ

የምዝገባ ጊዜ፡-
- ከነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡

የምዝገባ ቦታ፡
- የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡- በድህረ ገፃችን የምዝገባው ቀን ካበቃበት በኋላ እናሳውቃለን ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-
- በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-
· የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
· በቂ አመላካቾች የሌሉባቻው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡
· ለፈተና የሚቀርቡት የአመልካቾች ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡- www.aastu.edu.et ; www.astu.edu.et እንደአመቺነቱም በe-mail የሚገለፅ ይሆናል፡፡
· አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡
· ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡

· አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
· የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡
· በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል፡፡
· በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል፡፡
· በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
· በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከታች የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች እና ቴሌግራም ቻናላችንን መጎብኘት ይቻላል፡፡

www.astu.edu.et; www.aastu.edu.et

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
43👍8🔥2👏2🙏2