Addis Admass
11.3K subscribers
7K photos
65 videos
20 files
2.03K links
የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
=====
አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx
ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv

የእርስዎና የቤተሰብዎ
Download Telegram
http://addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25384:የኮሮና-ቫይረስ-ከተከሰተ-በኋላ-11ሺህ-8-መቶ-ስደተኞች-ወደ-ሀገር-ቤት-ተመልሰዋል የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ባሉት የ1 ወር ከሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ 11ሺህ 8 መቶ ኢትዮጵያዊያን ከስደት መመለሳቸውን አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታወቀ፡፡
አይኦኤም ስደተኞች እና የኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ጥረትን አስመልክቶ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ፤ ከመጋቢት 23 ቀን 2012 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2012 ባለው ጊዜ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው የተሰደዱ 11ሺህ 8 መቶ ኢትዮጵያውያን በየሀገራቱ አስገዳጅ እርምጃ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ብሏል፡፡
http://addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25386:ዘንድሮ-በክልሉ-ምርጫ-ከማካሄድ-ወደ-ኋላ-እንደማይል-ህወኃት-ገለፀ በዘንድሮ አመት ምርጫ ማካሄድ የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን ህወኃት በድጋሚ የገለፀ ሲሆን፤ በህወኃት አስተባባሪነት የተመሠረተው የፌደራሊስት ሃይሎች ጥምረት በበኩሉ፤ ምርጫው መራዘሙን እንደሚደግፍ አስታውቋል፡፡
ከሰሞኑ የህወኃት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረ ፂዮን ገ/ሚካኤል ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ “ህወኃት ምርጫን በሚመለከት የወሰደው አቋም ፖለቲካዊና ህገ መንግስታዊ ነው” ብለዋል፡፡
“በክልል ደረጃ ኮሮናን እየተከላከልን ምርጫውን በጥንቃቄ ማካሄድ እንችላለን፤ ምርጫውን በዘንድሮ አመት ማካሄድ ወሳኝ ጉዳይ ነው” ብለዋል ዶ/ር ደብረፂዮን፡፡
የፌደራል መንግስት ጉዳዩን በህገመንግስት ትርጉም ለማስተናገድ መሞከሩም ህገ መንግስታዊ ድጋፍ የለውም ሲሉ የተቃወሙት ሊቀ መንበሩ፤ ህገመንግስቱ የምርጫ ጊዜን አስመልክቶ የሚተረጐም ነገር የለውም፤ መፍትሔ የሚሆነው ፖለቲካዊ ውይይት ማድረግ ነው ብለዋል፡፡
http://addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25403:በቀጣዩ-ምርጫ-ብልጽግና-የማሸነፍ-ዕድል-የለውም-አቶ-ልደቱ-አያሌው የኢዴፓ አመራርና አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው፤ የኮቪድ ወረርሽኝ ከተጋታ በኋላ በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ በሚጠበቀው 6ኛው አገራዊ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ የማሸነፍ እድል እንደሌለው ባዘጋጁት የቅድመ ምርጫ ውጤት ግምትና ትንተና ሰነድ ላይ ጠቁመዋል፡፡
ከመስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ የሚፈጠረውን የሥልጣን ክፍተት ለመሙላት መፍትሄው ለ2 ዓመት የሚዘልቅ የሽግግር መንግስት ማቋቋም መሆኑን ሽንጣቸውን ገትረው የሚሟገቱት አቶ ልደቱ፤ ሃሳባቸው ውድቅ ተደርጎ ምርጫው የሚካሄድ ከሆነና በተዐምራዊ ምክንያት ሰላማዊ፣ ነጻና ፍትሐዊ መሆን ቢችል፣ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ካለው የፖለቲካ የኀይል አሰላለፍ አንጻር፣ ምርጫውን የትኛው የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ጎራ ሊያሸንፍ ይችላል? ለሚለው ጥያቄ፤ ‹‹የቅድመ -ምርጫ ውጤት ግምትና ትንተና›› መስጠት ጠቃሚ እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡
ከሁሉም ክልሎች በቀጣዩ ምርጫ የሚመጣውን ውጤት ወደ እርግጠኝነት በተጠጋ መጠን አስቀድሞ ለመገመት የሚቻለው በትግራይ ክልል ነው የሚሉት አቶ ልደቱ፤ በክልሉ ዋናው (ምናልባትም ብቸኛው) የምርጫ አጀንዳ የትግራይ ክልል ሉዓላዊነትና የህወሓት ህልውና መቀጠል እንደሚሆን ይጠቁማሉ፡፡
"ይህንን አጀንዳ ደግሞ ከህወሓት በተሻለ መጠን በአሁኑ ወቅት ሊያሳካ የሚችል ድርጅት አለ ተብሎ
addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25377:“ኮሮና-እስከ-መቼ? “ይህንን ማንም ሰው ሊተነብየው አይችልም!”

ከትናንት በስቲያ ከወደ ጄኔቫ አንድ ነገር ተሰማ…
“ኮሮና ቫይረስ ፈጽሞ ላይጠፋ ይችላል… አብረውን እንደሚኖሩት ሌሎች በሽታዎች ሁሉ፣ ኮሮናም አብሮን ሊቀጥል ይችላል” በማለት እቅጩን ተናገሩ - ዶ/ር ሪያን፡፡
የአለም የጤና ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶ/ር ማይክ ሪያን ከትናንት በስቲያ በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “ቫይረሱ መቼ ከአለማችን ላይ ሊጠፋ ይችላል?” ተብለው ሲጠየቁ የሰጡት ምላሽ ብዙዎችን ያስደነገጠ፣ ተስፋ ያስቆረጠና ግራ ያጋባ ነበር፡፡
በተለያዩ የአለማችን አገራት ከ100 በላይ የሚሆኑ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ምርምሮች እየተደረጉ እንደሚገኙ የጠቆሙት ዶ/ር ማይክ ሪያን፤ አለም በለስ ቀንቷት ክትባቱን ብታገኝ እንኳን ኮሮናን ላታጠፋው እንደምትችል ተናግረዋል - የመከላከያ ክትባት ከተገኘለት ረጅም ጊዜ ያለፈውንንና አሁንም ድረስ ከአለማችን ያልጠፋውን የኩፍኝ በሽታ እንደ አብነት በመጥቀስ፡፡
ጥቂት ቆይቶ ግን፤ አለቃቸው ሌላ የተሻለና የሚያጽናና ነገር ተናገሩ…
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1775 የላብራቶሪ ምርመራ ሰላሳ አምስት (35) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ ምሳ ሁለት (352) ደርሷል፡፡
http://addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25387:በሸርተቴ-ሞራል-ሰበራ "--የእኛ ህዝብ እኮ ይህን ሁሉ ዘመን የኖረው በባህላዊ ህክምና ነው! አሁንም ቢሆን እኮ…አለ አይደል…ምናልባትም ከአራት አምስተኛ በላይ ህዝባችን የሚጠቀመው ባህላዊ መድሀኒት ነው፡፡ ታዲያላችሁ… ለእኛ ሲሆን ነገርዬው ግልብጥብጥ የሚለው ለምንድነው! የእኛ የብዙ መቶ ዓመታት ባህላዊ እውቀቶች ለምንድነው ‘ህቅ፣ ህቅ’ የሚለን! የምር ያሳዝናል፡፡ --"
እንዴት ሰነበታችሁሳ!
ስሙኝማ …
addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25272:በዓልን-በብልህነትና-በጥንቃቄ "ደግሞላችሁ…ለጥሬ ሥጋ ወዳጆችም ሲባል የነበረውን ነገሬ ብሎ መመርመሩ ግድ ይላል፡፡ የጥሬ ሥጋ አምሮት የፈለገ እንቅልፍ ይንሳ፣ የፈለገ ሆድን ባር፣ ባር ያሰኝ…አለ አይደል… “እንዲህ ቢሆን እንዲህ ማድረግ ይቻላል፤” እየተባለ “ፕላን ቢ” ምናምን የሚመዘገብበት ጊዜ አይደለም፡፡ “ፕላን ቢ” ብሎ ነገር የለም፡፡"


እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ!
እንዴት ሰነበታችሁሳ!
ስሙኝማ…የኮንዶሚኒየም ኑሮ የበዓል ሰሞን ጭቅጭቅን ቀነሰው ወይስ እንዴት ነው ነገሩ!
አሁን አሁን በር አልፈው ጐረቤት ድረስ የሚሰሙ “የበዓል በጀት” ንትርኮች ስለማንሰማ ነው፡፡ የምር ግን…እንግዲህ ጨዋታም አይደል…ይሄ የዋዜማ ሰሞን ጭቅጭቅ እኮ…አለ አይደል…ለበዓል የሆነ “ቴስት” ነገር ይሰጠው ነበር፡፡ ልክ ነዋ…
“እኔ እንኳን ልቀርበው እንደሱ የሚያስጠላኝ ሰው የለም!”
addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25296:የ‘ክፉ-ቀን’-ክፉ-ነገር “-ጉድ እኮ ነው! ሰዋችን ለአንዲት ዶሮ ስምንት መቶና አንድ ሺህ ብር የሚጠየቀው ከሌላው የዓለም ህዝብ የተለየ እርግማን አለበት እንዴ! ለስደት የመን ድንበር በእግሯ ደርሳ፣ በእግሯ የተመለሰች የምትመስል ‘በግ’፤ ስድስትና ሰባት ሺህ ብር የሚጠየቅባት ውስጧ የተደበቀ ‘ጎልድ’ ‘ዳይመንድ’ ‘ሜርኩሪ’ ምናምን ነገር አለ እንዴ!?-”

እንዴት ሰነበታችሁሳ!
ልጁ የፊት መሸፈኛ እየሸጠ ነበር፡፡ የሆነ ሸለል ያለ ሰውዬ አቅራቢያ ከነበረ የኤሌክትሮኒክስ ሱቅ ይወጣል፡፡ ልጁን ዋጋውን ይጠይቀዋል፡፡
“ሠላሳ ብር፡፡”
ከዛላችሁ…እንድ ነጣ ያለውን ይቀበለውና ከትንሽዬ የፕላስቲክ ከረጢት አውጥቶ አገላብጦ ያየዋል፡፡ እናላችሁ…አገላብጦ ሲያይም በጣቶቹ ጫን፣ ጫን እያደረገ ነበር፡፡ ከዛ አንደኛውን አፍና አፍንጫው ላይ አድርጎ ይሞክረዋል፡፡ ከዛ ምን ቢያደርግ ጥሩ ነው… የሞከረውን አውልቆ ለልጁ ይመልስለትና ሌላ ቡኒ ቀለም ያለው መሸፈኛ ተቀብሎት፣ ሠላሳ ብሩን ይከፍልና ቆማ ወደነበረች ለክፉ የማትሰጥ መኪና ይገባል፡፡ ጉድ እኮ ነው!
addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25359:ተቃዋሚ-ፓርቲዎች-“የሽግግር-መንግስት”-ሃሳብ-ተቀባይነት-የለውም-አሉ በአገሪቱ ኮቪድ -19 መከሰቱን ተከትሎ ምርጫው በመራዘሙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው መራዘምና በመንግስት ቅቡልነት ዙሪያ የተለያዩ አቋም እያንፀባረቁ ሲሆን አብዛኞቹ “የሽግግር መንግስት” መቋቋም የሚለውን ሃሳብ ተቃውመውታል፡፡
“የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና ምርጫ 2012 በኢትዮጵያ ፣ ፖለቲካዊ ቅርቃርና አማራጭ የመውጫ መንገዶች” በሚል ርዕስ ባለ 11 ገጽ የመፍትሔ ሃሳቦች ሰነድ ያቀረበው ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ በህገ መንግስቱ ማዕቀፍ ስር ያሉ አማራጮችን ይዘረዝራል፡፡
ፓርቲው ፓርላማውን መበተን፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ የሚሉት አማራጮች በህገመንግስቱ ያሉ ቢሆንም፣ እነዚህ አማራጮች ከጥቅማቸው ጉዳታቸው እንደሚያመዝን ተንትኖ የሚገልፀው የፓርቲው ሰነድ፤ “መፍትሔው ህገመንግስታዊ ማሻሻያ ማድረግ ነው” ሲል ከእነትንታኔዎቹ ያቀርባል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3271 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ አራት (14) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ ስልሳ አምስት (366) ደርሷል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3460 የላብራቶሪ ምርመራ ሃያ አራት (24) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ (389) ደርሷል፡፡
http://addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25397:ከኮቪድ-19-በኃላ፤-ጉርብትናና-ወዳጅነት-በኢትዮጵያ-ስነ-ሰብዓዊ-ምልከታ-በተለይ ከ2000 ዓ.ም በኃላ ተወራራሽ፣ ተደጋጋፊ እና ተካካቢ በሆነው የኢትዮጵያ የባህል ባላ ላይ በፍጥነትና በብዛት አያሌ ቅጠሎች እያቆጠቆጡበት ይገኛሉ፡፡ የቤተሰብ፣ ትምህርት ቤት፣ ሀይማኖት እና መንግስዊ ተቋማት ቅርጻቸው ብቻ ሳይሆን እድገታቸውና ይዘታቸውም እየተቀያየረ መጥቷል፡፡ ቅርብ የነበሩ እሴቶች እሳት እንደነካው ፌስታል ሲጨማደዱና ባዳ ሲሆኑ፤ ሩቅ ያሉ የሚመስሉ ትውፊቶች ደግሞ መጤነትን ተሻግረው ባለድርሻ ሆነው አርፈዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት መስፋፋት፤ የመሰረተ ልማት መጎልበት እና የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች መበልጸግ ደግሞ ለውጡ ድንገቴና አቅጣጫ አልባ አድርገውታል፡፡
ባህላዊና ማህበራዊ ህይወትን ከሚለውጡ አበይት ኩነቶች መካከል ቴክኖሎጂ፣ በሽታ፣ ድርቅ፣ ጦርነት፣ ስደት እና ሌሎች ተጠቃሽ ምክኒያቶች ናቸው (Stroma Cole, 2008)፡፡ ኢትዮጵያም ከላይ ለተጠቀሱት ገፊ ክስተቶች እንግዳ አይደለችም፡፡ ሀገሪቱ ባሳላፈችው ረጅም የታሪክ ሀዲድ ላይ ስሟ ከረሀብ፤ ከጦርነት እና ከጠኔ ጋር ሲነሳና ሲጣል፤ ሲቦካና ሲጋጋር ኖሯል፡፡