http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25809:“40-ዓመት-በህክምና-ያገለገለችውን-እናቴን-ቀጥቅጠው-ገደሉብኝ”
Addisadmassnews
“40 ዓመት በህክምና ያገለገለችውን እናቴን ቀጥቅጠው ገደሉብኝ” - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news

የማይሽር ቁስል ይዣለሁ፤ መንግስት ደሜን ይመልስልኝ
(ሀኪም ሰራዊት ተረፈ፤ የዓለም ማያ ከተማ ነዋሪ)

http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25806:“ለ57-ዓመት-ለፍቼ-ያፈራሁት-ሀብት-ወድሞ-ያለ-መጦሪያ-ቀርቻለሁ”-ወ-ሮ-ሽቶ-ተገኝ፤
Addisadmassnews
“ለ57 ዓመት ለፍቼ ያፈራሁት ሀብት ወድሞ ያለ መጦሪያ ቀርቻለሁ” (ወ/ሮ ሽቶ ተገኝ፤) - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news

እኔ የ70 ዓመት አዛውንት ነኝ፤ በአለም ማያ 01 ቀበሌ ላለፉት 57 ዓመታት ኖሬያለሁ:: አግብቼ ንብረት አፍርቼበታለሁ፤ ከሰውም ጥሩ ፍቅር አለኝ፡፡ ምንም በማ...
http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25805:“17-የልጅ-ልጅ-ባየሁበት-ከተማ-ነው-ይህ-ሁሉ-መከራ-የደረሰብኝ”
Addisadmassnews
“17 የልጅ ልጅ ባየሁበት ከተማ ነው ይህ ሁሉ መከራ የደረሰብኝ” - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news

መጦሪያዬን፣ እምነቴን፣ ተስፋዬን ተነጥቄ ቁጭ ብያለሁ
(አቶ አበባው ከበደ፤ የአለማያ ከተማ ነዋሪ)

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 10 አዳዲስ ሹመቶች ሰጡ
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት 10 ሹመቶችን ሰጥተዋል።
በዚሁ መሰረት፦
1. ዶ/ር ቀንዓ ያደታ- የመከላከያ ሚኒስትር
2. ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
3. ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
4. ኢንጂነር ታከለ ኡማ- የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር
5. አቶ ተስፋዬ ዳባ- ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
6. አቶ ዮሐንስ ቧያለው – የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
7. አቶ ንጉሡ ጥላሁን – የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር
8. አቶ እንደአወቅ አብቴ – የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር
9. አቶ ፍቃዱ ጸጋ – ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
10. ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማርያም – በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ በመሆን መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ
የፌደራል አቃቤ ህግ የነበሩት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፤ የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በዛሬው እለት
ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ነው የምክትል ከንቲባነት ሹመቱን ያፀደቀው።
ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ሃላፊነቶችና የአዳማ ከንቲባ በመሆን ያገለገሉት ወ/ሮ አዳነች፤ የለውጡን መምጣት ተከትሎ የፌዴራል ገቢዎች ሚኒስትር
እንዲሁም የመጀመሪያዋ ሴት የፌደራል አቃቤ ህግ ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
ወ/ሮ አዳነች በተለይ የገቢዎች ሚኒስትር ሳሉ በተሾሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ በግብር አሰባሰብ ባስመዘገቡት አመርቂ ውጤት ከመንግስት አድናቆትን ማግኘታቸው
አይዘነጋም፡፡
ላለፉት ሁለት ዓመታት አዲስ አበባን በምክትል ከንቲባነት ያገለገሉትን ኢንጂነር ታከለ ኡማን በመተካት ነው ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተሾሙት፡፡ ጠ/ሚኒስትር
ዐቢይ አህመድ፤ የኢንጂነር ታከለ ኡማን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትርነት ሹመት ጨምሮ በዛሬው ዕለት 10 አዳዲስ ሹመቶችን እንደሰጡ የጠ/ሚኒስቴር
ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

በሻሸመኔ በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ቦምብ በወረወረ
የኦነግ ሸኔ አባል ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
በሻሸመኔ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የጸጥታ ስራን በማከወን ላይ በነበሩ ጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ቦምብ በወረወረ የኦነግ ሸኔ አባል ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ ገለፀ። ዛሬ ከጠዋቱ አንድ ሰአት ተኩል አካባቢ በሻሸመኔ ከተማ 01 ወይም አዋሾ ቀበሌ አካባቢ የጸጥታ ሀይሎች አካባቢያዊ ቅኝት ሲያደርጉ ነው ከድር ቱሌ የተባለ ግለሰብ የእጅ ቦምብ ወርውሮ ሊያመልጥ ሲል እርምጃ የተወሰደበት።
በዚህም የተጠርጣሪው ህይወት ሲያልፍ ቦምብ ከተወረወረባቸው የጸጥታ ሀይሎች መካከል በአንዱ ላይ ጉዳት ደርሶ ፣በመልክ ኦዳ ሆስፒታል ክትትል እየተደረገለት መሆኑን ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል፡፡ የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ፥ ከተጠርጣሪው እጅ ተጨማሪ የጦር መሳሪያ መገኘቱን አስታውቋል።
ከድር ቱሌ የተባለው ይህ ተጠርጣሪ መታወቂያው የአርሲ ዞን ሸርካ ወረዳ ነዋሪ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን፥ ሁለት ሞባይል፣ ገንዘብና ትጥቅ መያዣ ቀበቶ ይዞ ነበር ተብሏል። የከተማው ፖሊስ መምሪያ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል እንዲሁም ከፌደራል ፖሊስና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል፤ እንደ ፋና ዘገባ፡፡ የሻሸመኔ ከተማ አሁን ላይ ወደ ቀድሞ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች ሲሆን፥ ከዚህ ቀደም ለወደሙና ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ የማድረጉ ተግባርም ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል፡፡
የከተማዋ ነዋሪ ከጸጥታ አካሉ ጋር ተናቦ እየሰራ ባለው ስራ በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ያለው ፖሊስ፤ የተዘረፉ ንብረቶችም እየተመለሱ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 23,035 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1,829 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 37,665 ደርሷል። በሌላ በኩል 377 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ስሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 13,913 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማለዳ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ካርቱም፣ ሱዳን አቅንተዋል። የሽግግሩ ሚሊተሪ ምክር ቤት ሊቀመንበር ከሆኑት ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሀን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ውይይት ያካሂዳሉ። (የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)
http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25765:“ለምጣዱ-ሲባል-አይጧ-ትለፍ”
አዲስ አድማስ
“ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ”
ገጣሚና ፀሐፌ ተውኔት መንግሥቱ ለማ፤ “በግጥም ሃሳብን ለመግለጽ” በሚል ርዕስ የፃፉትን ታሪክ ወደ ስድ ንባብ ስንቀይረው የሚከተለውን ስነ ተረት ይመስላል፡፡ አንድ ገጣሚ ያጋጠመውን እንዲህ ሲል ተረከ፡- የሚተርከው ለአንድ ፈላስፋ ነው፡፡ “ከዕለታት አንድ ቀን፣ አንድ ንጉስና ንግስቲት ቤተ መንግሥታቸው ውስጥ ይኖሩ ነበረ፡፡ እስካሁን ልጅ አልወለዱም፡፡ መንግሥቱን የሚመራና ዙፋኑን የሚወርስ ልጅ ለማፍራት…
የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብሱን ሊቀይር ነው
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫን አስመልክቶ ለሁለት ቀናት ሲያካሄድ የነበረው ግምገማ ዛሬ ተጠናቋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ እንደሚቀየርና ጉዳዩን አስመልክቶ በመጪው ቅዳሜ ሰፊ ማብራሪያ በኮሚሽኑ እንደሚሰጥ በዚሁ ወቅት ለኢዜአ ገልጸዋል።
ለደንብ ልብሱ መቀየር አሁን ያለው የደንብ ልብስ በቀላሉ የሚገኝ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነ ምግባር ችግር የተባበሩ ፖሊሶች ልብሱን ለብሰው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በምክንያትነት ጠቅሰዋል።
በዚህም የደንብ ልብሱን በመልበስ የሚፈጸሙ ወንጀሎችና ዝርፊያዎች መበራከታቸውን ነው ያስታወቁት።
በሌላ በኩል በ2013 ዓ.ም አዳዲስ የፖሊስ ዘርፎች በሙከራ ደረጃ ወደ ሥራ ሊገቡ እንደሆነ ኮሚሽነር እንዳሻው አያይዘው ገልጸዋል። (Ethiopia News Agency)