Addis Admass
11.3K subscribers
7K photos
65 videos
20 files
2.03K links
የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
=====
አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx
ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv

የእርስዎና የቤተሰብዎ
Download Telegram
የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ
በአዲስ አበባ 102 ህገ-ወጥ ሽጉጦችና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

በአዲስ አበባ ከተማ 102 ህገ-ወጥ ሽጉጦችና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች መያዙን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ጀይላን አብዲ እንደተናገሩት፤ በመዲናዋ በተለምዶ ኮልፌ 18 ማዞሪያ እና ሰሜን ማዘጋጃ’ በሚባሉ አካባቢዎች ተጠርጣሪው ግለሰብ በተከራይዋቸው ቤቶች ውስጥ ነው ህገወጥ መሳሪያዎቹ የተያዙት።
በተደረገው ፍተሻም 102 ሽጉጦች 399 ጥይቶችና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያ እቃዎች መያዛቸው ታውቋል፡፡
ተጠርጣሪው በሰጡት ቃል መሳሪያዎቹ መነሻቸውን ሱዳን አድርገው በጎንደር በኩል አዲስ አበባ እንደገቡም የተናገሩ ሲሆን ግለሰቡ ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው።
ህገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች አብዛኛውን ጊዜ ቤት በመከራየት ወንጀሉን እንደሚፈጽሙ ጠቅሰው፤ ከዚህ አንጻር አከራዮች ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜና በኦሮሚያ ክልል ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ድጋሜ ሁከት ለመቀስቀስ የሚጥሩ አካላት እንዳሉ አቶ ጀይላን ተናግረዋል።
እነዚህ አካላት በዋናነት ምስሎችን ‘በፎቶ ሾፕ’ በማቀናበርና ከለውጡ በፊት የተደረጉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አሁን እንደተከናወኑ በማስመሰል ህዝብን እያደናገሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
በመሆኑም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ይህን እኩይ ተግባር ሊገነዘብ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

(FBC)
የአዲስአበባ ከተማ ምክርቤት የሁለት ቢሮ ሃላፊዎችን ሹመት አፅድቋል
በዚህ መሰረት:-
1.ወ/ሪት ፋይዛ መሐመድ ኡመር- የባህል ቱሪዝም እና ኪነጥበብ ቢሮ
2.ወ/ሪት ሓዳስ ኪዱ ትዓራ - የሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል ምንጭ -ከንቲባ ፅ/ቤት
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለኢ/ር ታከለ ኡማ የዕውቅና ሽልማት አበረከተ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ላከናወኗቸው ውጤታማ ስራዎች የዕውቅና ሽልማት አበርክቷል።
ምክር ቤቱ ኢንጂነር ታከለየዕውቅና ሽልማቱ ያበረከተላቸው ÷ የሚሰሩ ስራዎች የከተማዋ ነዋሪዎችን ያማከለ እንዲሆን በማድረግ በኩል ውጤታማ ስራዎችን በማከናወናቸው ፣አስታዋሽ አጥተው ለዘመናት የተዘነጉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማዕከል ያደረጉ
ስራዎችን በመስራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ መሆኑ ተገልጿል። (FBC)
ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
***************
ባለፉት አሥራ አንድ ቀናትከ46 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከሀገር ለማስወጣት እና ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞችና በየደረጃው ባሉ የፀጥታ አካላት በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 9.2 ሚሊዮን ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ስማርት ስልኮች በሞያሌ እና በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲሁም 8.2 ኪ.ግ የሚመዝን የብር ጌጣጌጥ እና 1500 ኪ.ግ መጠን ያለው ካናቢስ ተብሎ የሚጠራ አደንዛዥ ዕፅ ሞያሌ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በሚሌ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ 9.2 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልባሽ ጨርቆችና ሺሻ ተይዘዋል፡፡
የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት፣ ሲጋራ፣ መድኃኒት በሌሎች የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች የተያዙ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ናቸው፡፡ ኮምቦልቻ፣ ጋላፊ፣ ሑመራ፣ ያቤሎ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ፣ ጅግጅጋ እና ቦምባስ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከተያዙባቸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ይገኙበታል፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር
በአዲስ አበባ የተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ የአውሮፕላን በረራዎችን አስተጓጎለ

በዛሬው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ሳቢያ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ሊያርፉ የነበሩ አውሮፕላኖች በሌሎች የአውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ ተደረገ።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፥ አብዛኛው የከተማዋ ክፍልም በጉም ተሸፍኖ ነው የዋለው።
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ የአውሮፕላን በረራዎችን በማስተጓጎል ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው መረጃም፥ “ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ አውሮፕላኖቻችን በአቅራቢያ ወደሚገኙ የአየር ማረፊያዎች ተመልሰው እንዲያርፉ ተደርጓል” ብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚሕ ምክንያት ለተከሰተው መጉላላት ይቅርታ በመጠየቅም፤ ሁኔታውን እየተከታተለ ተጨማሪ መረጃ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጿል። (FBC)
የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ20 ሺህ አለፉ!!!
30-bert.gif
70.5 KB
የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ