የሃይማኖት አባቶችን የሚገድለው ማን ነው?
=====
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
በሀገራችን የተለያዩ ክፍሎች የሃይማኖት አስተማሪዎችን መግደል እየተበራከተ መጥቷል። ምሥራቅ አርሲን የመሳሰሉ የክርስቲያን ፍጅት የታወጀባቸውን ቦታዎች ማለቴ አይደለም። አንጻራዊ መረጋጋት አለባቸው በሚባሉ አካባቢዎች እንጂ። በቅርቡ በጎንደር ከተማ፣ በጠራራ ፀሐይ ኡስታዝ መሐመድ ዘይኑ የተባሉ የመስጂድ ኢማም፣ ተገ* ደሉ። ያውም ቤተሰባቸው ፊት። እንዲህ ያለው ነገር ዓለማውን ቶሎ ካልነቃንበት ከዚህም ከዚያም እያፈራረቁ በመግደል አንዱን በአንዱ ላይ ለማሥነሣት ሆን ተብሎ የሚሠራ ተንኮል ሰለባ ልንሆን እንችላለን። ትልቅ መረጋጋትና አስተውሎት የሚጠይቅ ጊዜ ላይ ነን። ለተገደሉት ወገኖች ሁሉ ዕረፍተ ነፍስ ያድልልን።
===========
የወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል አስተዳዳሪ ተገደሉ፤ ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ተፈጽሟል
==========
መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ):- የመልአከ ምሕረት አባ ዐይናለም አማረ /ቆሞስ/ ሥርዓተ ቀብር በወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ተፈፀመ፡፡
የወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት አባ ዐይናለም አማረ /ቆሞስ/ ዛሬ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊት በተፈጸመባቸው ጥቃት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ባስተላለፉት ቃለ ምእዳን መልአከ ምሕረት አባ ዐይናለም እግዚአብሔር በቆረጠው ቀን አርፈዋል፤ ነገር ግን በቀናቸው ለተጠሩት አገልጋይ መሞት ምክንያት የሆነ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር ብለዋል።
የቤተ ክርስቲያን ሀብት እንዳይባክን በመጠበቅና ሥርዓተ አምልኮቱ በአግባቡ እንዲፈጸም ሌት ተቀን ራሳቸውን ሰጥተው እያገለገሉና እየደከሙ ባለበት በቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ ከመኖሪያ ቤታቸው በጥይት ተመትተው ሕይታቸው በማለፉ መሪር ሐዘናቸውን ገልጠው ምእመናን አገልጋዮቹን እንዲጠብቅ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል።
መልአከ ምሕረት አባ ዐይናለም አማረ ነጻና ፊት ለፊት የሚናገሩ፣ ለልማትና ለቤተ ክርስቲያን እድገት በቆራጥነት ሠርተው የሚያሠሩ ትጉኅ እረኛ እንደነበሩም ብፁዕነታቸው መስክረዋል፡፡
===========
የመልአከ ምሕረት አባ ዐይንዓለም አማረ (ቆሞስ) አጭር የሕይወት ታሪክ
++++++
መልአከ ምሕረት አባ ዐይናዓለም አማረ (ቆሞስ) በስመ ክርስትናቸው ወልደ ጊዮርጊስ ከአባታችው ከአቶ አማረ ከእናታችው ከእማሆይ አስቴር ሻረው በ1958 ዓ.ም በጉባላፍቶ ወረዳ በቅሎ መፍለቂያ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ተወለዱ፡፡
እድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ በተለያዩ የአብነት ጉባኤ ቤቶች መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርትንና ቅዳሴን ተምረዋል፡፡
በተወለዱበት በቅሎ መፍለቂያ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመዓርገ ዲቁና አገልግሎትን የጀመሩ ሲሆን በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም በምናኔ ኑረዋል።
ወደአዋሳ በመሄድ ከብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መዓርገ ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ ወደካህናት ማሠልጠኛ በመግባትም ሥልጠና በመከታተል አጠናቅቀው ተመርቀዋል፡፡
መልአከ ምሕረት አባ ዐይናዓለም በሐረርና በጂጂጋ ለበርካታ ዓመታት በቅዳሴና በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል፡፡
አባ ዐይናዓለም ወደየመን በመሻገር በውጭ ሀገርም ሰፊ አገልግሎት የሰጡ ሲሆን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፈቃድ በዱባይ በቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪነት አገልግለዋል፡፡
በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ መልካም ፈቃድ ወደ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ተመልሰው በቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪነት፣ በአስፋ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ፈለገ አእምሮ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች፣ በመርሳ ቤዛ ብዙኀን ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያንና በወልዲያ ቲንፋዝ ደብረ በረከት ቅ/ጊዮርጊስ አብያተክርስቲያን በአስተዳዳሪነት አገልግለዋል፡፡
መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ዐይናለም አማረ ሕይወታቸው እስከአለፈበት ድረስ በወልዲያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል በአስተዳዳሪነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
በተወለዱ በ60 ዓመታቸው መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊት በተተኮሰባቸው ጥይት በሞተ ሥጋ ተለይተው ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና ከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና የወልዲያና አካባቢው የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት፣ ሕዝበ ክርስቲያንና የሥጋ ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡
የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ልዑል እግዚአብሔር የአባታችንን የወልደ ጊዮርጊስን ነፍስ በአጸደ ገነት እንዲያሳርፍልን፤ ለሥጋና ለመንፈስ ቤተሰቦቻቸውም መጽናናቱን እንዲሰጥልን ይመኛል፡፡
_______
(ምንጭ፦ https://www.facebook.com/EOTCNWD )

😢7❤2
በዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ሁለት መነኮሳት ሲገደሉ አንድ ረድዕ ቆስለዋል፡፡
(EOTCMK TV መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም)
በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በአድርቃይ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም በ480 ዓ.ዓ እንደተመሠረተ የሚነገርግለት ነው።
በገዳሙም ውስጥ በአሁኑ ሰዓት 700 የሚጠጉ ገዳማውያን መነኮሳት ይኖራሉ።
ለማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ በደረሰው መረጃ መሰረት በገዳሙ መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ታጣቂ ግለሰብ ከግብር አበሮቹ ጋር በመሆን በከፈተው የተኩስ እሩምታ የገዳሙ መነኮሳት መገደላቸው ታውቋል፡፡
በዚህም መሠረት አባ ወልደ ሰንበትና አባ ወልደ ትንሣኤ የተባሉ መነኮሳት ወዲያው ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን አባ ገብረ ማርያም የተባሉት ረድዕ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው በዛሬማ ከተማ በሕክምና ላይ መሆናቸውን የመረጃ ምንጫችን ነግረውናል።
የተገደሉት መነኮሳት ሥርዓተ ቀብራቸው በዕለቱ በገዳሙ ሥርዓት መሰረት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት መፈጸሙ ተገልጿል፡፡
የገዳሙ አባቶች በገዳሙ አጠገብ የዳጉሳ አውድማ ጥለው ባሉበት ወቅት ታጣቂ ግለሰብ አውድማው ድረስ በመምጣት "ከቤተ እግዚአብሔር አግብታችሁ ምግብ አብሉኝ" ብሎ መጠየቁ ለተኩሱ መነሻ መሆኑን በመረጃው ላይ ተነስቷል።
ነገር ግን ለሥራው የተመደቡ አባቶች "ከእንግዳ ማረፊያ ቤት ሆነህ መመግብ ትችላለህ፣ መነኩሴ ስላልሆንክ ወደ ቤተ እግዚአብሔር መግባት ግን አትችልም ምክንያቱም ሥርዓተ ገዳሙ አይፈቅድልህም" እንዳሉት በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።
ግለሰቡ በዚህም ተበሳጭቶ ለመተኮስ ሲሞክር "በሱባኤ ወቅት ግጭት መፍጠር አያስፈልግም" ብለው መነኮሳቱ ቢመክሩትም ገዳዩ ግለሰብ ስልክ ደውሎ አምስት ግብር አበሮቹን በመጥራት የተኩስ እሩምታ መክፈታቸውን ምንጫችን አስረድተዋል።
የመረጃ ምንጫችን እንደነገሩን ከሆነ ከዚህ በፊት ግለሰቡ ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም አንድ የቅዳሴ ተማሪ አግኝቶ በመውሰድ ለማስለቀቂያ ከቤተሰቦቹ 200 ሺሕ ብር ከተቀበለ በኋላ ደቀ መዝሙሩን ገድሎት መገኘቱ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም በወርኃ ጥቅምት 2018 ዓ.ም ከዳባት ወረዳ ለቀብር ወደ ገዳሙ የመጡ ምእመናንን ገዳዩ አግቶ 700 ሺሕ ብር ቢጠይቅም በሽምግልና ሊለቃቸው መቻሉን ከመረጃ ምንጫችን ለማወቅ ተችሏል።
በተመሳሳይም በጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በማይ ደንጎላ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጊዮርጊዮስ ስባረ አጽሙ በዓል ተከብሮ ዑደት በሚደረግበት ጊዜ ተኩስ ከፍቶ ዑደቱ ተቋርጦ ታቦተ ሕጉ ወደ መንበሩ መመለሱን ተገልጿል።
በአሁኑ ሰዓት ምንም አይነት የመንግሥት የፀጥታ አካላት በገዳሙ አካባቢ ባለመኖራቸው በመነኮሳቱ ዘንድ ከፍተኛ ሥጋት መፈጠሩን የመረጃ ምንጫችን ገልጸውልናል፡፡
©ማኅበረ ቅዱሳን

😢10❤1
አዲስ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ "ታ0ብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር" (The Magnificat)
=====
ውይይት ከደራሲው ከሊቀ ብርሃናት ቀሲስ ነህምያ ጌጡ ጋራ
=====
ውይይት ከደራሲው ከሊቀ ብርሃናት ቀሲስ ነህምያ ጌጡ ጋራ
የ“ዝም በል ዳያስጶራ” - አዋጅ፦ ከቤተ መንግሥት እስከ ቤተ እምነት
=========
(** እ.ኤ.አ በ2013፤ ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ ባለፈችበት ወቅት የተጻፈውን ይህንን ጽሑፍ ምንም ሳልጨመር ምንም ሳልቀነስ በድጋሚ ላጋራችሁ ወደድሁ። መልካም ንባብ)
++++++++
( ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ )
መግቢያ:-
በዚህ ሰሞን መቼም ከእግር ኳስ ውጪ ማውራት በሕማማት ስለ ቁርጥና ጥብስ እንደማውራት ሳይቆጠር አይቀርም። እኔም ብሆን ስለ እግር ኳሱ ማውራቱን መች ጠልቼው። በርግጥ ይኼ ሁሉ ወፈ-ሰማይ የስፖርት ተንታኝ በየኤፍ.ኤሙ ሲተችበት በሚውለው የተጫዋቾቻችን ብቃት፣ ጥራት፣ የኳስ ጥበብ፣ የሽልማት ዓይነት፤ የተጋጣሚዎቻችን ሁኔታ፣ የተጫዋቾቻቸው ዝና፣ ማን ከየትና ከየትኛው ክለብ እንደመጣ፣ አሰላለፋቸው እና ከኢትዮጵያ ጋር ሲገጥሙ ሊኖራቸው ስለሚችለው አያያዝ ለመተንተን ሙያውም መረጃውም የለኝም። (“ችሎታ የለኝም” አለማለቴ ይሰመርበት። ማን ይሞታል። መቸም “አልችልም” ማለት ጎጂ ባህል ሆኗል።) ቢያንስ የእንጀራ አገሮቻችን አሜሪካ እና ስዊዲን ስላፈሯቸው እና ለእናት አገራችን ኢትዮጵያ ስላበረከቷቸው ተጫዋቾቻችን መወያየት ይቻላል።
++++++
ኢትዮጵያውያን እንደ ጨው በመላው ዓለም ተበትነዋል። በብዙ ቦታዎች አንድ ትውልድ አልፎ ሁለተኛ ትውልድ ላይ ደርሷል። በቅርብ ከሚገኙት ኬንያና ሱዳን እስከ አረብ አገሮች፣ ከምዕራብ አውሮፓና ስካንዲኔቪያን አገሮች እስከ አሜሪካና አውስትራሊያ ድረስ ብዙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ። ከእነርሱ መካከል የአሜሪካ ሜኔሶታው ፉአድ ኢብራሒም እና የስዊዲኑ ዩሱፍ ሳላህ ተገኝተዋል። ፉአድ ኢትዮጵያ ተወልዶ አሜሪካ ያደገ፤ ዩሱፍ ደግሞ እዛው ስዊዲን ተወልዶ እዛው ያደገ እግር ኳስ ተጫዋች ነው። የብዙ ኢትዮጵያውያን የኋላ ማንነት ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ ልጆች ናቸው። አድገውና ለቁም ነገር ደርሰው አገራቸውን ለመወከል መብቃታቸው ደስ ይላል። “አለ ገና፣ ገና፣ አለ ገና” እንላለን።
ጣዕመ-ኢትዮጵያ፣ ባህለ-ኢትዮጵያ በቀዘቀዘባቸው ባህሎች መካከል አድገው በመጨረሻ አገራቸውን ለመወከል መቻላቸው ትልቅ ነገር ነው። ስለ ፉአድ ያነበብኩት አንድ ጽሑፍ ይህ ወጣት ለአሜሪካ እግር ኳስ ቡድን (ከ17 ዓመት በታች እንዲሁም ከ21 ዓመት ላሉት) ቢጫወትም የማታ ማታ ግን አገሩን ለመወከልና የአገሩን ማሊያ ለመልበስ መወሰኑን ያትታል። ስዊዲን እነ ኢብራሒሞቪችን (በአባቱ ቦስንያዊ) እና ታዋቂው ሔንሪክ ላርሰንን (አባቱ ከኬፕቬርዴ ናቸው) የመሳሰሉ ተጫዋቾችን በማሰለፏ እናውቃታለን። ዩሱፍም ተመሳሳይ በሆነ መልክ ተመሳሳይ ዕድል ሊያገኝ እንደሚችል እገምታለኹ። ነገር ግን ያንን ትቶ የአገሩን መለያ ለብሷል።
ዳያስጶራው ለረዥም ዓመታት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወደ አገሩ በመላክ አገሩን በቀጥታም በተዘዋዋሪም ሲደግፍ ቆይቷል። በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከዳያስጶራው የሚገኘው ገቢ አገሪቱ ከወጪ ንግድ ከምታገኘው በእጅጉ እንደሚበልጥ የዓለም ባንክ ጥናቶች በተደጋጋሚ አሳይተውናል። ከዚህ የቀጥታ ገንዘብ ርዳታ ባሻገር ትውልደ-ኢትዮጵያዊው በአገሪቱ አጠቃላይ ሕይወት ላይ በጎ ሱታፌ ማሳየቱ አገሩን ለሚወድ ወገን ሁሉ ትልቅ ተስፋ ነው። ዩሱፍና ፉአድ ለዚህ መልካም አብነቶች ይሆናሉ።
ዩሱፍና ፉአድ ወደ አገራቸው ሲመለሱ በዚያው መጠን ብዙ ኢትዮጵያውያን ወደ ዳያስጶራነት ጎራ እየተቀላቀሉ ነው። በዚህ ዓመት (2013 እ.ኤ.አ) መጀመሪያ ላይ በዋሺንግተን ዲሲ የተደረገ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ሐኪሞች ማኅበር ስብሰባ ተገልጿል እንደተባለው በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ዶክተሮች ይልቅ በውጪ የሚገኙት ቁጥር ይበልጣል። አዝማሚያውን ስንመለከተው ይኸው የዕውቀትና የአዕምሮ ስደት እንደሚቀጥል እርግጥ ነው። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ዋስትና ማጣት እና ፖለቲካዊ ነጻነት አለመኖር ነው። ከኢኮኖሚው በበለጠ ፖለቲካዊ ጫናው ለብዙው ወገናችን መሰደድ ምክንያት ነው የሚለው የብዙዎች እምነት ነው። በፖለቲካዊ ምክንያቶች የተሰደዱት ደግሞ በየወጡበት አገር ባላቸው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን መንግሥት ዘወትር መክሰስ ቀጥለዋል። በቅርቡም ይቆማል ተብሎ አይጠበቅም። ይህም ፉአድንና ዩሱፍን የመሳሰሉ ትልውደ ኢትዮጵያውያን በየሙያቸው ትውልድ አገራቸውን እንዳያገለግሉ እንቅፋት ይሆናል። በአገሪቱ ያለው የሰብዓዊ መብት ገፈፋ ሲሻሻል ዳያስጶራውም ተጠቃሚ ይሆናል። ዳያስጶራውን በጥቅማጥቅም ማባበል መጠነኛ ደጋፊ ያስገኛል፤ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት መጠበቅና ሕገ መንግሥቱን ማክበር ግን ሙሉ ድጋፍ ያስገኛል።
ዳያስጶራው በየሚኖርበት አገር የሚተነፍሰው ፖለቲካዊ፣ ሕሊናዊ፣ አካላዊ እና ሰብዓዊ ነጻነት ይኸው ነጻነት በአገሩ እንዲኖር በጎ ምኞት ይቀሰቅስበታል። ስለዚህ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በአገሩ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ይኮንናል፤ ተጽዕኖ ለመፍጠርም የማይወጣው ዳገት የማይወርደው ቁልቁለት የለም። ይህም የተለያየ አመለካከት መፍጠሩ አይቀርም። "ዳያስጶራው አክራሪ ነው” ከሚለው ጀምሮ “የአገሩን ነባራዊ ሁኔታ የማያውቅ” እንዲሁም “50 ዶላር ልኮ አገር ውስጥ ያለው ወጣት እንዲማገድ ይፈልጋል” ወዘተ ተብሎ ይቀርባል።
ሐሳቡ ቀደም ብሎ በመንግሥት ብቻ ተደጋግሞ ሲገለጽ የቆየ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ተርታ ዜጎችም በማኅበራዊ ድረ ገጾቻቸው ሲያስተጋቡት ይስተዋላል። በአጭር አባባል ለማቅረብ “ዳያስጶራ ዝም በል” ወይም “ዳያስጶራው ዝም እንዲል አድርጉት” የሚል አዋጅ የተነገረ ይመስላል።
በመጀመሪያ ደረጃ አንድን ዜጋ ከአገሩ ርቆ በመኖሩ ስለ አገሩ ያለውን ሐሳብ፣ በመንግሥቱ ላይ የሚኖረውን ቅዋሜ እና ለችግሮች የሚኖረውን መፍትሔ ከማቅረብ ሊከለክለው የሚችል ሕግ የለም። ስለ አገርህ ለመናገር በአገርህ መሬት መኖር አለብህ የሚል “የቀበሌ ትእዛዝ” የመሰለ ሐሳብ ውኃ አያነሣም። ነቢዩ ዳዊት ስለ ኢየሩሳሌም ሲናገር “ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” እንዳለው “እመሰ ረሳዕኩኪ ኢትዮጵያ ለትርስዐኒ የማንየ፣ ኢትዮጵያ ሆይ ብረሳኝ ቀኜ ትርሳኝ” የሚሉ ኢትዮጵያውያንን "እኮ ምን አግብቷችሁ?" ማለት ከስድብ ይልቅ ያማል።
ዛሬ ባንኖርባት ተወልደንባት አድገንባታል፤ ዘር ማንዘሮቻችን ኖረው አልፈውባታል። ክቡር አጥንታቸው ረግፎባታል። በየወቅቱ በሚመጣና በሚሄድ ሥልጣን የአንድ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱ አይገመገምም። ኢትዮጵያዊነትን ማንም ባለሥልጣን አልሰጠንም፣ ማንም ባለሥልጣንም አይነፍገንም። ከደርቡሽና ቱርክ፣ ጣሊያንና ግብጽ፣ ከሌሎችም ድንበር ገፊዎች ሲታገሉ በወደቁ ወገኖቻችን የቆመ ዜግነት እንጂ እንጀራ ፍለጋ፣ ነጻነት ፍለጋ እንደምንኖርባቸው አገሮች በወረቀት ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም። ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከወረቀት እና ከፖለቲካ ወገንተኝነት እንዲሁም ከየብሔረሰባዊ ማንነታችን በላይ ነው።
በሌላም በኩል ካየነው ስለ ሰብዓዊ መብት ለመናገር የግድ የዚያ አገር ዜጋ መሆን፣ በዚያ አገር መኖርም አይጠይቅም። ሰብዓዊ መብቱ እንዲጠበቅለት የሚፈልግ ማንም ሰው የሌላው ሰው መብት ሲጣስ አይደሰትም። ሌላው ሁሉ ታሪካዊ ሐተታ እንኳን ቢቀር በቅርቡ ዘመን የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ከኛ ሚሊሻ ጋር አብረው የተዋደቁልንን ኩባውያንን መስዋዕትነት እንደምናከብረው፣ ዕድሜ ዘመናቸውን በሴቶች (ፊስቱላ) ሕክምና ረገድ አገራችንን የጠቀሙትን ሐኪሞች እንደምናመሰግነው ሁሉ ለዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት የሚከራከሩትንም በዚሁ መነጽር ልንመለከታቸው ይገባል።

❤8👍3
በተጨማሪም የመንግሥትን አሠራር ማሔስ አገርን መተቸት አይደለም። መንግሥት የአገር መሪ እንጂ አገር አይደለም። ፓርቲና መንግሥትነት ከዘር ጋር በመቆራኘታቸው ፓርቲውን መተቸት የመጣበትን ዘር እንደመውቀስ ተደርጎ መቆጠሩም ትልቅ ስሕተት ነው። ፓርቲዎች በዓላማቸውና በአሠራራቸው መነቀስና መተቸት ግዴታቸው ስለሆነና በዘር ላይ የተመሠረተ የፓርቲ አወቃቀር እስካለ ድረስ ከፓርቲው ጀርባ ያለው ዘር ወቀሳው ለርሱ የተወረወረ አለመሆኑን ለመረዳት ብዙ ጥበብ አያስፈልገውም።
እንኳን የኢትዮጵያ መንግሥት በዲሞክራሲያዊነታቸው ወደር የማይገኝላቸው አገሮች የየጊዜው መንግሥታት ሳይቀሩ ከትችት አያመልጡም። ትችት መንግሥታቱን ከዓምባገነንነት የሚያተርፋቸው ፍቱን መድኃኒት ነው። ተቃዋሚዎችን፣ ፕሬሶችን፣ ጥቃቅን ስብስቦችን ሁሉ በመዋጥና በዓይነ ቁራኛ በመመልከት፣ ትችትን ሳይሆን ተቺውን በማፈን ጥሩ መንግሥት መሆን አይቻልም። “ልማት ላይ ነን አትንኩን” የሚል ፈሊጥ ወንዝ አያሻግርም። ጥያቄው ግድቡና ሕንጻው ላይ አይደለም። የዜጎችን ሰብዓዊ ሕንጻ እያፈረሱ የድንጋይ ሕንጻ እንሠራለን ማለት አይቻልም። ከግዑዝ ሕንጻ ሰብዓዊ ዜጋ ይቀድማል፤ ከግድብ ግንባታም መብት ይቀድማል።
በውጪ የሚገኘው ዜጋ የአገሩን ሁኔታ በትኩረት ለመከታተል ቴክኖሎጂው ትልቅ ዕድል ይሰጠዋል። አራት ኪሎ የተፈጠረው አቃቂ፣ አንዱ ክፍለ ሀገር የተሠራው ሌላው ክፍለ ሀገር ሳይረዳው ሳይሰማው፤ እረኛና አዝማሪ እንኳን ለዘፈኑና እንጉርጉሮው በራሱ ላይ ግላዊ-ሴንሰርሺፕ በጣለበት ዘመን፣ ከአንድ አፍ በሚወጣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚና ቁጥጥር የተደረገበት ወሬ አገር በሚተዳደርበት ጊዜ፣ አለመስማትን እና አለማወቅን (መንግሥታዊ የመረጃ ግርዶሽን) መታገል ሲገባ የሰማውንና ያወቀውን “እኮ ማን ስማ አለህ” ማለት አያዋጣም። ይህንን የሚለው አካል ነገሩ እንዳይሰማበት የፈለገው እንጂ ተጎጂው አለመሆኑም በቅጡ ይታወቃል።
ዳያስጶራውን አምርሮ የመጥላት እና በጅምላ ክፉ ስም የመስጠት ተደጋጋሚ ሙከራ ፍሬ ማፍራቱን ለማወቅ ተርታ ግለሰቦች እና ቤተ እምነቶች ሳይቀር ማንጸባረቅ የጀመሩትን ተመሳሳይ አመለካከት መመልከት ይገባል። የግለሰቦቹን እንኳን ለጊዜው ብናቆየው የአንዳንድ ቤተ እምነት አስተዳደሮችና መሪዎች ከውጪ የሚመጣላቸውን የአማኛቸውን ሐሳብ፣ ልክ እንደ መንግሥት፣ “አፍራሽ፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጥያቄ” አድርገው ሲመለከቱት ማየት እየተለመደ መጥቷል። ‘አጋጣሚ ነው ወይስ የተላለፈ አዋጅ አለ?" የሚያሰኝ ነው። የቤተ እምነት መሪዎች ሰማያዊውን መንግሥት መጠበቅ ትተው ምድራዊውን መንግሥት ለመጠበቅ ደፋ ቀና ሲሉ እነርሱን የሚከተላቸው ምእመን እንደሚመለከታቸው እንኳን ይዘነጉታል። እነርሱም ከምድራዊው ባለ ጉልበት ጋር ተደርበው “ውጪ ያላችሁት ዝም በሉልን፣ እንደፈቀድን እንሁን” ሲሉ አዋጃቸውንም በደህና ጊዜ የሚናገሩትንም ሰማያዊ ቃል የሚሰማቸው ጆሮ ያጣሉ። በርግጠኝነት ግን ማንም ዝም አይልም።
መልካም ዕድል ለእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድናችን!!!!
ይቆየን - ያቆየን
=====
(በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ በደቡብ አፍሪካ በተዘጋጀ ዓመት የተጻፈ)

❤4👍3
Forwarded from Adebabay Media
አዲስ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ "ታ0ብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር" (The Magnificat)
=====
ውይይት ከደራሲው ከሊቀ ብርሃናት ቀሲስ ነህምያ ጌጡ ጋራ
=====
ውይይት ከደራሲው ከሊቀ ብርሃናት ቀሲስ ነህምያ ጌጡ ጋራ
👍2
** መዝሙር ዘደብረ ዘይት
------------------
"እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ። ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ፤ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን። ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወስ ኲሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአነ ምድር ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበአዕላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእምኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት።" ( ቅዱስ ያሬድ)
===========
** ትርጒም፦
------------------
ጌታችን በደብረ ዘይት ተቀምጦ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው። እወቁ፤ እንዳያስቷችሁ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ብዙዎች በስሜ ይመጣሉ። ትዕግሥቱን ያዘወተረ እሱ ይድናል። የሰው ልጅ በሚመጣ ጊዜ የሰማያትና የምድር ኃይል ይናወጣል። ያንጊዜ የምድር ኃጥአን ሁሉ ያለቅሳሉ። ከእግዚአብሔር ታዞ በሚደረግ የመለከት መነፋት፣ በአዕላፍ መላእክት አጀብ፣ በትእዛዝና በቃል ጌታችን ከሰማይ ወደምድር ይወርዳል። በዚያች ሰዓት ከኃጢአት ሞት (በኃጢአት ከሚመጣ ፍርድ) ይማረን። የሰንበት ጌታ እሱ ሕይወትን የሚሰጥ ነውና።
===========
የ0ቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት (ደብረ ዘይት) የመዝሙር፣ ምንባባትና ምስባክ ግጻዌ
=========
** መዝሙር ዘደብረ ዘይት
------------------
እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወስ ኲሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአነ ምድር ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበአዕላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእምኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት።

** የዕለቱ ምስባክ
------------------
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ። (መዝ ፵፱፥፫/ 44፥3)
======
** ትርጒም፦
------------------
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፤
አምላካችን ዝም አይልም፤
እሳት በፊቱ ይነዳል።
=======
** የዕለቱ ወንጌል፦
------------------
++ ማቴ ፳፬፥፩ -፴፮ (24÷36)
** ቅዳሴ፦
------------------
++ ዘአትናቴዎስ
============

👍11❤5