Adebabay Media
4.15K subscribers
1.84K photos
97 videos
39 files
1.61K links
በወገንተኝነት፣ በጊዜአዊ ጥቅም እና አጋርነት ብቻ የሚደረግ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ጋዜጠኝነት ጥቅም እንደሌለው በመረዳት ዕውቀትና መረጃ ላይ የተመረኮዘ፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ፣ ሀገርንና ወገንን በመጥቀም ላይ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍ ባለ ብዙ ቋንቋዎች ሚዲያ፤ ቤተሰባችን ስለሆኑ እናመሰግናለን። በFacebook/YouTube (@adebabaymedia) ይመልከቱን። www.adebabay.com
Download Telegram
ዛሬ ሰኞ በምሥራቅ አርሲ 3 ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ፣ ሕዝቡ እየሸሸ ነው
=====
(EOTCMK TV ኅዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም)

ዛሬ ኅዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ልዩ ቦታው ጠለታ ቅዱስ ገብርኤል በተባለ አካባቢ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ገደማ ሦስት ኦርቶዶክሳውያን በአውድማ ላይ እህል እየወቁ ባሉበት በጥይት ተደብድበው በግፍ መገደላቸው ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመላክታል ።

ከተገደሉት ምእመናን መካከል ዲ/ን ኢዮብ እጅጉ፣ ጥላሁን ቦጌ እና ሕፃን ጻድቃኔ ሠራዊቱ የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን ይገኙበታል ።

ሥርአተ ቀብራቸው በጠለታ ቅዱስ ገብረኤል ቤተክርስቲያን ዛሬ ኅዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ ተፈጽሟል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በነበሩ የኦርቶዶክሳውያኑ አፈናና ግድያን በተመለከተ መረጃ አቀብላችኋ በሚል ምክንያት የአካባቢው ወጣት ምእመናን ወዳልታወቀ ሥፍራ ታስረው እየተወሰዱ እንደሚገኝ ምእመናኑ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በሥፍራው ላይ የጸጥታ ሓይል ቢኖርም ኢ-ሰብአዊ ድርጊቱ ፣ አፈናና ግድያውም ተባብሶ መቀጠሉን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ወደ ሆነው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እና የዞኑ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ የእጅ ስልክ ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት ሴቶች እና ሕጻናት አካባቢውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታም እየሸሹ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

Mahibere Kidusan Broadcast Service - ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት
😢11
ኦርቶዶክሳያውን ተክደዋል
======
( ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ )
"ኦርቶዶክሳውያን ተለይተው አልተገደሉም" የሚለው የነቀሲስ ታጋይ ታደለ መግለጫ የኦርቶዶክሳውያን ግድያ እንዲቀጥል የተፈቀደበት ደብዳቤ አድርጌ ወስጄያለሁ።

ይህንን ጽሑፍ በምጽፈበት በዚህ ቅጽበት ከአርሲ ጀጁ ወረዳ የኮለባ ማርያም ክርስቲያኖች የቤት እንስሶቻቸውን (ማለትም በሬ፣ ፍየል፣ በግ፣ አህያ ወዘተ) በመያዝ ከነቤተሰባቸው ከአካባቢው በመሸሸ ወደ ጀጁ ከተማ፥ አቦምሳ ከተማ፣ ስሬ እና ወደ ሌሎች አካባቢዎች በመሰደድ ላይ ናቸው።

ኅዳር 1 (Nov. 10/2025) በምሥ/አርሲ የተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች
======
➠ ዲያቆን ኢዮብ እጅጉ
➠ ወጣት ጥላሁን ቦጋለ
➠ ሕጻን ጻድቃን ሠራዊት
😢232🤯2🤔1
ምነው ምነው መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ:- በኢ/ኦ/ተ/ቤ ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ኃላፊ
===========
(ከ ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ )
ክቡር መልአከ ሰላም፣
** የክርስቲያኖችን ፍጅት "ተራ ሞት" አደረጋችሁት።
** የተጨፈጨፉ ክርስቲያኖች፣ ቁስላቸው ገና ያልጠገገ ቁስለኞች፣ የለፉበት ሰብላቸው አሁን በዚህ ሰዓት እየተዘረፈ ያሉ ገበሬዎች፣ ከሴቶችና ሕጻናት ጋራ ወደ ከተማ የተሰደዱ አማኞች ዕንባቸው አርሲን እያጠበ "በሃይማኖቱ ተለይቶ አደጋ የደረሰበት የለም" አላችሁት።
** በነዚህ ዓመታት እንኳን የፈረሰ መስኪድ፣ ጫፉ የተነካ የሙስሊም ንብረት አለ?
** በየቦታው የሚገነቡት የእምነት ቤቶች የነማን ናቸው? የተዘጋውና ጽላቱ ወደ ከተማ የተሰበሰበው የማን ቤተ እምነት ነው?
** በዚህ ወቅት ከቤቱ የተፈናቀለ የሌላ እምነት ተከታይ አግኝታችኋል?
** ከተማ ከተማውን ከመጓዝ ባሻገር፣ አባ ገዳዎችን፣ ሃዸ ሲንቄዎችን ከማናገር ባሻገር የራሳችንን ካህናትና ምዕመናን ለብቻ አግኝታችኋል? ሰይፍ አንገታቸው ላይ የተሳለ ወገኖች ያለ ፍርሃት እንዲናገሩ ሁኔታዎች ተመቻችተዋል?
** በዚህ የጥድፊያ "ምርመራ" ኦርቶዶክሱን በሃይማኖትህ ምክንያት አልምትህም ብለን ደሙን ደመ ከንቱ ፣ ሞቱን ሞተ ከለባት ማድረጋችን ሳያንስ ለወደፈቱም ጩኸቱ እንዳይሰማ አፉን ዘግተን አልተመለስንም?
** ምነው ምነው መልአከ ሰላም? የሰማዕታቱ ደም እንደ አቤል ደም ይጣራል፣ ይጮኻል።
=====
** "በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።" (ራእይ 6፥10)
😢255👏1
ቀጣዩ ጊዜ የከፋ የክርስቲያኖች ፍጅት || በመሪዎቻቸው የተካዱት የምሥ/ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን
የኦሮራ (ኮሎራዶ ግዛት) የሕዝብ ተመራጭ ስለ አርሲ ተናገሩ፣ ለፕ/ት ትራምፕ መልዕክት ላኩ
======
( ከቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ )
"በኢትዮጵያ በተለይም በአርሲ ዞን ያሉ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ያጋጠመውና የጅምላ ግድያ እና መፈናቀል አሳዛኝ ዘገባዎች በጣም አሳሳቢ ሆኗል። ሰዎችን በእምነታቸው እና በብሄራቸው ምክንያት ዒላማ ማድረግ ተቀባይነት የለውም።" (የሕዝብ ተመራጩ አምሳሉ ካሣው በደብዳቤአቸው)
++++++
የመልእክቱ ሙሉ ቃል ይህ ነው።

++++
AMSALU KASSAW
Aurora City Council Member
At-Large

PUBLIC STATEMENT

As a community member and elected official, I am deeply concerned by the heartbreaking reports coming out of Ethiopia, where Orthodox Christians in the Arsi Zone are facing mass killings and displacement. Targeting people because of their faith and ethnicity is unacceptable. Humanity must come before hate. Respect, tolerance, and the protection of human rights should never be compromised.

I have contacted President Trump’s Special Advisor directly to bring attention to this crisis, including the increasing tension between Ethiopia and Eritrea. Diplomacy must lead — not war.

Silence is not an option when lives are at risk. The international community must act now to prevent further tragedy and protect innocent civilians. We must stand for peace, justice, and the dignity of every human life.

Amsalu Kassaw
Aurora City Council Member At-Large

https://www.amsaluforaurora.com/
X (Twitter): @ams_kas
👍19👏9
የኔዘርላንድ የፓርላማ አባል ስለ አርሲ የኦርቶዶክሶች ጭፍጨፋ ተናገሩ
=====
(ከ ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ )
Dutch MP in the Netherlands, Don Ceder of the ChristenUnie, urges action after deadly attacks on Ethiopian Orthodox Christians amid ongoing violence in East Arsi, Oromia region, of Ethiopia.

Dutch MP Don Ceder has pressed the Dutch government to address violence against Ethiopian Orthodox Christians in East, Arsi, Oromia, highlighting ongoing conflict and alleged abuses, and urging international action to protect these communities.

His request is significant because it underscores the humanitarian and political dimensions of religious persecution within a polarized conflict, and it calls for concrete government engagement to safeguard civilians and pressure responsible actors.
======
CC
Mahibere Kidusan Broadcast Service - ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/ Adebabay የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት / EOTC His Holiness Secretariat Office Inter Religious Council of Ethiopia @highlight Mahibere Kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ማኅበረ ካህናት ዘሰሜን አሜሪካ - Mahibere Kahinat U.S. Department of State Oromia Police Commission U.S. Embassy Addis Ababa Union of Orthodox Journalists of America Amnesty International Africa United Nations
👍176
በኢትዮጵያ የወንጀል መርማሪ እና ሪፖርት አቅራቢነት ኃላፊነት የማን ነው??
=======
(ይርጋለም ብርሃኑ Yirgalem Birhanu እንደጻፈው)
በኢትዮጵያ የወንጀል መርማሪ እና ሪፖርት አቅራቢነት ኃላፊነት የማን ነው? የሃይማኖት ተቋማት እንዴት የከባድ ወንጀል አጣሪ እና ሪፖርት አቅራቢ ይሆናሉ? የሀገሪቱ ሕግ በዚህ ጉዳይ ምን ይል ይሆን? ቀሳውስት፣ ሼክ እና ፓስተር እንዴት ሆኖ የወንጀል ሪፖርት ያቀርባሉ? በምን ሙያቸው?

እኔ በምኖርበት ሀገር የሰዎች ግድያ ሲፈፀም በመጀመሪያ ደረጃ የአካባቢው ፖሊስ፣ የሀገር ግዛቱ ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ አንድ ላይ ወንጀል የተፈፀመበት ቦታ ላይ ሆነው መግላጫ ይሰጣሉ። በፌደራል FBI (Federal Bureau of Investigation) መሪነት የወንጀል መርማሪ ቡድን እንደሚቋቋም ለሕዝቡ ይገለፃል። በሒደት የደረሱበትን የምርመራ ደረጃ ውጤት በየጊዜው እየወጡ መግለጫ ይሰጣሉ። በመጨረሻ ወንጀል ፈጻሚ አካል በሕግ ቁጥጥር ሥር ከዋለ ወደ ፍርድ ቤት ይቀርባል።

በአርሲ እየተካሄደ ያለው ፍጅት እንዴት የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ድርጅት የወንጀል ሪፖርት ያቀርባል? ይህንን ለማድረግ የሀገሪቱ ሕግ ይፈቀድለት ይሆን? ተቋሙ የወንጀል ምርመራ ሪፖርት ለማቅረብስ ሙያዊ ብቃት አለው?
11👍5
ይድረስ ከሌ/ጄ/ል ድሪባ መኮንን፤ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
========
የዛሬ ዝግጅታችን፣ ለኦሮሚያ ፖሊስ ትልቁ አለቃ ጥሪአችንን የምናስተላልፍበት፣ የቤት ሥራ የምንለዋወጥበት የተግባር መርሐ ግብር ይሆናል። የነዚህ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሥራ ስልኮቻቸውና ሌሎች መገኛ መንገዶቻቸውን እንለዋወጣለን። ሕዝበ ክርስቲያኑ የነርሱን ጥበቃ በተነፈገበት እና ለመፍጫፊዎች ተላልፎ በተሰጠበት ሁኔታ እነርሱም መተኛት የለባቸውም፣ ሕሊናቸውም (ትንሹ እግዚአብሔር የሚባለው) በጸጸት ብዛት እረፍት ሊያገኝ አይገባውም።
12👍3
የዛሬ ዕለታዊ ሪፖርት አለን:- ክርስቲያን እየገ*ደ*ሉ በሰላም መኖር አይቻልም
======
( ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ )
** የአርሲ ጭፍጨፋ ዜና ዋይት ሐውስም፣ ኔዘርላንድ ፓርላማም ደርሷል፤ ይቀጥላል
** ከጭፍጨፋው ጀርባ ያሉ ባለሥልጣናት ስምና ፎቶ ይዘናል፤
** እጃቸው በክርስቲያኖች ደም ለጨቀየ ባለ ሥልጣናት መጥፎ ዜና ነው፤
**እጃቸው በክርስቲያኖች ደም የጨቀየ ባለ ሥልጣናት የዘረፉትን ሀብት የማይበሉበት ወጥመድ ነው የምናዘጋጅላቸው፤
** እጃቸው በክርስቲያኖች ደም የጨቀየ ባለ ሥልጣናት ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም።
=====
👍266
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ብዙ መርዝ የሚያከሸፍ ንግግር።
======
ዲ/ን ጫላ፣ ቃለ ሕይወት ያሰማህ።
28👍6
ጭፍጨፋውን ለማስቆም፤ ሕዝቡን በአካል ለመጎብኘት፣ ወንጀሉን ለዓለም ለመንገር
=====
የዛሬ ሳምንታዊ የውይይት ጠረጴዛችን "ጭፍጨፋውን ለማስቆም፤ ሕዝቡን በአካል ለመጎብኘት፣ ወንጀሉን ለዓለም ለመንገር" መደረግ ባለባቸው ነገሮች ዙሪያ እንወያያለን። ተግባራዊ የሆነ ነገር፤ በአቅማችን ልንሠራው ስለምንችለው ነገር አቅጭ እቅጩን እናነሣለን።

** በዋሺንግተን ዲሲ = 8 PM ላይ

** ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ Abel Gashe እና Teklemichael Ab Sahlemariam

++++ አደባባይ ሚዲያን ለማግኘት ..... +++
👉 በ YouTube
https://www.youtube.com/adebabaymedia
👉 በቲክቶክ
https://adebabaymedia
👉 በ Facebook
https://facebook.com/adebabaymedia
👉 በ Telegram
https://t.me/adebabaymedia
👉 በ Twitter
https://twitter.com/adebabaymedia

አደባባይ ሚዲያ፦ የሁላችን ስለሆነች ኢትዮዽያ!!!
ከ2ቱ ግንባር ቀደም ተግባራት አንዱ:- ክርስቲያኖቹን በአካል መጎብኘት
======
(ከ ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ )
ከ6 ቀናት በፊት የምሥ/አርሲን ጉዳይ በተመለከተ 2 ዋና ተግባራት ላይ ነው መሥራት ያለብን ብዬ ነበር።
፩/ ጭፍጨፋውን ማስቆም፣
፪/ ክርስቲያኖቹን በአካል ሄዶ መጎብኘት፣ ማጽናናት፣ ማጽናት።
++++++
** ቤተ ክህነቱ ምዕመናኑን ለመጎብኘት ሐዋርያዊ ጉዞ ያደርጋል ብለን ነበር፤ የሚሆን አይመስልም።
** ሌሎች መንፈሳዊ ማኅበራትና ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም የክርስቲያኖች ወቅታዊ ሁኔታ የሚገዳቸው በሙሉ በጋራ ሐዋርያዊ ጉዞ ሊያዘጋጁ ይችላሉ ወይ ብለን ጠይቀን ነበር። ያውም ከ6 ቀናት በፊት።

https://www.facebook.com/share/p/1G1JzfFVL7/

** ለዚህ ጥያቄ በጎ ምላሽ የሚሆን ግሩም መልዕክት ከሊቀ ሊቃውንት ቀለመ ወርቅ ቢራራ ቲክቶክ ላይ በማግኘቴ ደስ አለኝ።
** ስለዚህ በሀገር ቤት የምትገኙ ወገኖቻችን፣ በራሳችሁ አነሣሽነት እና አስተባባሪነት፣ ይህንን ሐዋርያዊ ጉዞ ማዘጋጀት ትችላላችሁ? ምን ይመስላችኋል?
=====

ከስድስት ቀናት በፊት ያቀረብሁት ተማጽኖ የሚከተለው ነበር፦
+++++
2 ነገር ላይ ብንረባረብ (ምሥራቅ አርሲ)
=======
( ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ )
1. ግድያው እንዲቆም ማድረግ (ግንባር ቀደም ዓላማ 1)
+++--
** ከክልሉ መንግሥት እና ከዞኑ ጋራ ፊት ለፊት መነጋገር የሚችለው ቤተ ክህነቱ ነበር፣
** ብፁዕ አባታችን አቡነ ናትናኤል "ምን እናድርግ?" ላሉት መልስ ይሆናል፣
( Cc የሚኒሶታና አካባቢው ሀገረ ስብከት )
** በዚህ ጊዜ ቅ/ሲኖዶስ በየቀኑ ነበር መሰብሰብ የነበረበት፣
** ብፁዕ አቡነ ያሬድ "ቅ/ሲኖዶሱ በሀገረ ስብከቴ እየደረሰ ባለው የክርስቲያኖች ፍጅት ምክንያት አስቸኳይ ጉባዔ ይቀመጥልኝ" ይበሉ አባታችን፣
** በውጪ ሀገራት የምንገኝ ሁላችን የክርስቲያኖች ግድያ እንዲያቆም ለዓለም ተቋማት ሳናሰልስ እንጩህ፣

2. የነፍስ አድን ጉዞ ወደ ምሥራቅ አርሲ (ግንባር ቀደም ዓላማ 2)
++++++++
** ምዕመናንም ካህናትም ጳጳሳትም በጋራ፣ በሕብረት ወደ ቦታው እንዲሄዱ፣ የወደቀውን እንዲያነሡ፣ የሞተውን እንዲቀብሩ፣ የቆሰለውን እንዲጠግኑ፣ የተሰደደውን እንዲመልሱ፣ ያዘነውን እንዲያጽናኑ፤
** የጉዞ ማኅበራት የእናንተ ሙያ በዚህ ይለካ፣
** የሰንበት ት/ቤት አንድነቶች ለዚህ ጊዜ ልትሆኑን ይገባል፤
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
** ለአርሲ ቅርብ የሆኑ ከተሞች አጥቢያዎችና ከተሞች ወገኖቻችሁን ሄዳችሁ ጎብኙ ፤
++++
** ለዚህ ሁሉ ግን የክልሉ መንግሥት በሩን መክፈት፣ ጥበቃ ማድረግ ሲችል ነው።
** "ክልላችን ሰላም ነው አትምጡብን" በሚለው የሰሞኑ ፕሮፓጋንዳ መቀጠል አያዋጣውም፣
** ወንጀልን መደበቅ ትልቅ ወንጀል ነው::
=====

@highlight Adebabay
Mahibere Kidusan Broadcast Service - ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት
የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት / EOTC His Holiness Secretariat Office
Mahibere Kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
ማኅበረ ካህናት ዘሰሜን አሜሪካ - Mahibere Kahinat
Inter Religious Council of Ethiopia
Kesis Melaku Terefe
@highlight
11