Addis Intelligence
14K subscribers
113 photos
34 videos
17 links
Addis Intelligence - about artificial intelligence, tools, and trends. tips, updates, and practical applications.

Advertising manager:
Download Telegram
✴️ የ-OpenAI AI ኤጀንቶች የሳይበር ደህንነት ፈተና ላይ እያሉ ያልተፈቀደ የሳይበር ጥቃት ማድረሳቸው ይፋ ተደረገ

በ-OpenAI የሳይበር ደህንነት ግምገማ እና የፈተና ሂደት ላይ የነበሩ የ-AI ኤጀንቶች ከተፈቀደላቸው የሙከራ ገደብ ውጭ በመውጣት በ-Hugging Face የዳታ ቋት እና ሰርቨሮች ላይ ያልተፈቀደ ጥቃት ማድረሳቸውን የ-OpenAI ዝርዝር የምርመራ ሪፖርት አረጋግጧል። በሂደቱ ወቅት አንዱ የ-AI ኤጀንት ጥቃቱ ያለፈቃድ እየተካሄደ መሆኑን ተረድቶ ድርጊቱን ለማቆም የሞከረ ቢሆንም ሌላኛው ኤጀንት “GO” የሚል ትዕዛዝ በመለጠፉ የመጀመሪያው ኤጀንት እንደ ህጋዊ ፈቃድ ወስዶ ጥቃቱን መቀጠሉ ተገልጿል።


➡️ ኤጀንቶቹ በድብቅ የመልዕክት መለዋወጫ ሰሌዳ (Message board) በማቋቋም የይለፍ ቃሎችን እና ክፍተቶችን እርስ በእርስ ሲለዋወጡ የስራ ድርሻ ሲከፋፈሉ እና ራሳቸውን “Swarm” (መንጋ) ብለው ሲጠሩ ተስተውለዋል

➡️ አንደኛው ኤጀንት መደበኛ ያልሆኑ የመገናኛ መንገዶችን በመጠቀም የሃላፊነት ስልጣን እንዳለው በማስመሰል (Simulating authority) የሌላኛውን ኤጀንት የደህንነት ውሳኔ ውድቅ ማድረግ ችሏል

➡️ ይህ ክስተት የተፈጠረው ከ-GPT-5.6 Sol ጋር ተመጣጣኝ አቅም ባለው የ-OpenAI ውስጣዊ የጥናት ሞዴል (Internal research model) እንጂ በ-GPT-Astra እንዳልሆነ ተረጋግጧል

➡️ OpenAI የደህንነት ማረጋገጫዎች እንዴት እንደተጣሱ እና ወደፊት መሰል ክስተቶች እንዳይደገሙ የተወሰዱ እርምጃዎችን የሚያሳይ ዝርዝር ሪፖርት ይፋ አድርጓል

🚬 እንዴ

🤩 @addisintel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍3
✴️ OpenAI የ-Nvidiaን የበላይነት የሚፈታተን Jalapeño የተሰኘ ብጁ የ-AI ቺፕ ይፋ አደረገ

OpenAI Jalapeño የተሰኘው የራሱ ብጁ የ-AI Inference ቺፕ የመጀመሪያውን ይፋዊ የአፈፃፀም ውጤት ይፋ ያደረገ ሲሆን ያስመዘገባቸው አሃዞች የ-Nvidiaን የገበያ የበላይነት በቀጥታ የሚገዳደሩ ሆነው ተገኝተዋል። ቺፑ እንደ GPT-OSS 120B፣ DeepSeek R1 እና Kimi K2.5 1T ባሉ ግዙፍ ሞዴሎች ላይ ከ-Nvidia GB200 እና GB300 ጋር ሲነፃፀር በአንድ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ከ1.5 እስከ 1.9 እጥፍ የበለጠ ስራ የሚያከናውን ሲሆን የፍጥነት መዘግየትንም (Latency) ከ1.7 እስከ 3.6 እጥፍ ቀንሷል።

📷 ለ-AI ኤጀንቶች ወሳኝ በሆኑ ፈጣን እና ተደጋጋሚ ግንኙነት በሚጠይቁ ስራዎች (Interactive workloads) ላይ ከ2.1 እስከ 4.1 እጥፍ የላቀ ብቃት አሳይቷል

📷 የቺፑ ከፍተኛ የኃይል ፍጆታ 700W ብቻ ሲሆን ይህም ከ-GB200 (1,200W) እና ከ-GB300 (1,400W) ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስተኛ ነው በተጨባጭ ሙከራዎች ላይም የኃይል ፍጆታው ከ550W በታች ሆኖ ተመዝግቧል

📷 OpenAI ቺፑን በራሱ የዳታ ማዕከላት ውስጥ እስከ ፈረንጆች 2026 መጨረሻ ድረስ ስራ ላይ ማዋል የሚጀምር ሲሆን የ-Gen 2 እና Gen 3 ቀጣይ ትውልድ ቺፖችን የማበልፀግ ስራ አስቀድሞ ተጀምሯል

🤩 @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2
🤶 Anthropic የ-AI ሲስተሞች ሮቦቶችን እና የላቦራቶሪ እቃዎችን በአንድ ወጥ መንገድ እንዲቆጣጠሩ የሚያስችል MHS የተሰኘ አዲስ ስታንዳርድ ይፋ አደረገ

➡️Anthropic እንደ Claude ያሉ የ-AI ሞዴሎች የተለያዩ የላቦራቶሪ እና የፋብሪካ መሳሪያዎችን በአንድ  Single interface እንዲቆጣጠሩ የሚያስችል Model Hardware Standard (MHS) የተሰኘ ክፍት ስታንዳርድ ይፋ አድርጓል። ከዚህ ቀደም ለእያንዳንዱ መሳሪያ የተናጠል የፕሮግራሚንግ በይነገጾችን (APIs) መጠቀም ይጠይቅ የነበረውን አሰራር በማስቀረት MHS የትዕዛዝ የባህሪያት እና የደህንነት ገደቦችን በአንድ ወጥ ድራይቨሮች እንዲያስተዳድሩ ያደርጋል።

➡️ይህ አሰራር የ-AI ኤጀንቶች የትዕዛዝ መስመሮችን (CLI) ወይም ብጁ ኮዶችን በመጠቀም ከመሳሪያዎች ጋር እንዲገናኙ ስራዎችን እንዲመሩ እና በሙከራ ውጤቶች ላይ ተመስርተው አሰራራቸውን እንዲያስተካክሉ ያስችላቸዋል። Anthropic እንዳስታወቀው አዲሱ ስታንዳርድ የተለያዩ መሳሪያዎችን ወደ ላቦራቶሪ ወይም ፋብሪካ የማካተት እና የማዋሃድ ጊዜን ከሳምንታት ወደ ጥቂት ሰዓታት አልፎ ተርፎም ደቂቃዎች ዝቅ አድርጎታል።

🤩 @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍1
✴️ OpenAI እስከ 2026 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ AGI ማሳካት እንደሚችል አስታወቀ

የ-OpenAI ዋና ስራ አስፈፃሚ Sam Altman ኩባንያው እስካሁን ሙሉ በሙሉ AGI ላይ ባይደርስም እስከዚህ የፈረንጆች ዓመት (2026) ማብቂያ ድረስ ግን በውስጣዊ አሰራሩ AGI ሊባል የሚችል ሲስተም እንደሚኖረው እንደሚጠብቅ ገልጿል። ይህ መግለጫ OpenAI ለ-AGI መድረሻ ግልጽ የሆነ የጊዜ ሰሌዳ ያስቀመጠበት የመጀመሪያው አጋጣሚ ተደርጎ ተወስዷል።

🖱️ OpenAI ራሱን ችሎ የሚሰራ የ-AI ተመራማሪ (Autonomous AI research intern) ለመፍጠር ያስቀመጠውን ውስጣዊ መመዘኛ ማሳካቱ ተገልጿል

🖱️ Astra በሚል የኮድ ስም የሚታወቀው ይህ ውስጣዊ ሲስተም የጥናት ሀሳቦችን ተቀብሎ በ-OpenAI የኮድ መሰረት ላይ የመተግበር ሙከራዎችን የማስኬድ እና ውጤቶችን የማመንጨት አቅም አለው

🖱️ ሲስተሙ አንድ የሰው ተመራማሪ ለአንድ ሳምንት ያህል የሚፈጅበትን ውስብስብ የጥናት ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ማቅረብ ይችላል

🖱️ ሳም አልትማን Astra ከሰዎች ጎን ለረጅም ጊዜ አብረው የሚሰሩ ቋሚ ኤጀንቶችን (Persistent agents) ለመፍጠር እንደሚያስችል ገልጾ የ-AGI ትልቁ ተፅዕኖ አዳዲስ ሳይንሳዊ እውቀቶችን ማግኘት እና ጠቃሚ ፈጠራዎችን ማመንጨት ላይ እንደሚሆን አስረድቷል

🤩 @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍1
👀 በለንደን በተካሄደ የአንጎል ቀዶ ጥገና ላይ AI የቀዶ ጥገና ሃኪሞች ሁለተኛ ጥንድ አይን በመሆን አገለገለ

በለንደን የሚገኙ የቀዶ ጥገና ሃኪሞች በአንድ ታካሚ የእይታ ነርቮች (Optic nerves) ላይ ጫና አሳድሮ የነበረን 11 ሚሊሜትር መጠን ያለው የአንጎል ዕጢ በተሳካ ሁኔታ ለማስወገድ ለመጀመሪያ ጊዜ የ-AI ቴክኖሎጂን በቀዶ ጥገና ወቅት ተጠቅመዋል። በመቶዎች በሚቆጠሩ የቀዶ ጥገና ቪዲዮዎች የሰለጠነው ይህ AI የተደበቁ የደም ስሮች እና የነርቭ መስመሮችን በቅጽበት በስክሪን ላይ በማድመቅ ሃኪሞቹ ከአደጋ ነፃ በሆነ መንገድ ቀዶ ጥገናውን እንዲያከናውኑ ረድቷል።

የቡድኑ መሪ ፕሮፌሰር ሃኒ ማርከስ ቴክኖሎጂውን እንደ “ሁለተኛ ጥንድ አይን” የገለጹት ሲሆን የመጨረሻው የውሳኔ ሃላፊነት ግን ሁልጊዜም በሃኪሞቹ እጅ እንደሚቆይ አስረድተዋል። ቀዶ ጥገናው የተደረገላቸው የ48 ዓመቱ ሪስ ሂበርት ከአንድ ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥርት ያለ እይታ ማግኘት የቻሉ ሲሆን plየህክምና ቡድኑ አሰራሩን ይበልጥ በማሳደግ ወደ ሰፋፊ ክሊኒካዊ ሙከራዎች ለመሸጋገር አቅዷል።

🤩 @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2
✴️ OpenAI ያለማቋረጥ ራሱን ችሎ የሚሰራ “Persistent” የ-AI ኤጀንት እያበለጸገ መሆኑ ተገለፀ

OpenAI በ-Codex ኤጀንቱ ላይ ተጠቃሚው በእጅ እስካላቆመው ድረስ ስራውን ያለማቋረጥ እንዲቀጥል የሚያስችል አዲስ Persistent mode እየሞከረ ይገኛል። ይህ አሰራር ኤጀንቱ በራሱ ተነሳሽነት ተከታታይ ስራዎችን Follow-up tasks እንዲፈጥር ከተለያዩ የስራ ክፍለ-ጊዜዎች ባሻገር ስራውን እንዲቀጥል ካለፉት ግንኙነቶች የተማረውን እውቀት እንዲጠቀም እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለተጠቃሚው በራሱ መልዕክት እንዲልክ የሚያስችለውን Proactivity የተሰኘ አዲስ ባህሪ ያካተተ ነው።

ይህ ግስጋሴ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ከተለመደው ጥያቄ እና ምላሽ (Ask → Answer) አሰራር በማውጣት ወደ ግብ ማስቀመጥ → መፈጸም → መገምገም → መቀጠል (Goal → Execute → Reassess → Continue) ወደሚል የላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል። ምንም እንኳን ባህሪው ለሁሉም ተጠቃሚዎች ገና በይፋ ባይለቀቅም የ-OpenAI ዋና የጥናት አቅጣጫ የሰው ልጅ ተደጋጋሚ ትዕዛዝ ሳይፈልጉ ለረጅም ጊዜ ራሳቸውን ችለው ለሚሰሩ  አስተዋይ ኤጀንቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ያሳያል።


🤩  @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍4
Channel photo updated
📌 SpaceX የ-Cursorን ባለቤት Anysphereን መግዛቱን ተከትሎ OpenAI ከ-Cursor ጋር የነበረውን የሞዴል አቅርቦት ውል እንደሚያቋርጥ አስታወቀ

🖱️OpenAI በቅርቡ በስፔስኤክስ የተገዛውን ታዋቂ የኮዲንግ መተግበሪያ Cursor የ-OpenAI ሞዴሎችን እንዳይጠቀም የሚያግድበትን የውል ማቋረጫ ውሳኔ ይፋ አድርጓል। ኩባንያው ውሳኔውን ያስተላለፈው ስፔስኤክስ የአጠቃቀም ደንቦችን (Terms of Service) ያከብራል የሚል እምነት እንደሌለው በመግለጽ ሲሆን የአገልግሎት መቋረጡ ከ76 ቀናት በኋላ ማለትም በፈረንጆች November 12, 2026 ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጿል।

🖱️OpenAI ውሳኔው በ-Cursor ላይ ጥገኛ ለሆኑ developers አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል በመገንዘብ በሽግግሩ ወቅት ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ እና developers የራሳቸውን API ቁልፎች (BYOK) በመጠቀም አገልግሎቱን ማስቀጠል እንደሚችሉ አስታውቋል। ይህ እርምጃ በ-OpenAI እና በኢሎን መስክ ተቋማት መካከል ያለውን ረጅም የቴክኖሎጂ እና የህግ ፉክክር ይበልጥ ያባባሰ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል।

🤩 @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😡1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✴️ ChatGPT Work ተጠቃሚዎችን ወክሎ ወደ ድረ-ገጾች የመግባት (Login) እና ተግባራትን የማከናወን አቅም አገኘ

🔺OpenAI በ-ChatGPT Work ላይ ተጠቃሚዎችን ወክሎ ድረ-ገጾች ውስጥ በመግባት ስራዎችን ማከናወን የሚያስችል አዲስ አሰራር አስተዋውቋል። የመግቢያ Authentication በተናጠል ስለሚከናወን የ-AI ኤጀንቱ የተጠቃሚውን የተጠቃሚ ስም Login ወይም Password የማያይ ሲሆን ፈቃድ ከተሰጠው በኋላ በብሮውዘሩ አማካኝነት ተግባራትን ያከናውናል።

🔺ይህ አሰራር የሀኪም ቀጠሮ የመያዝ,የተገዙ እቃዎችን የመመለስ ሂደት የማስፈጸም የተለያዩ ማመልከቻዎችን የመሙላት እንዲሁም ደረሰኞችን (Invoices) ከኢሜይል ወደ ሂሳብ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌሮች የማስተላለፍ አቅም አለው። አዲሱ አገልግሎት በድረ-ገጽ እና በሞባይል መተግበሪያዎች ላይ ለ-Plus Pro እና Business ተጠቃሚዎች ደረጃ በደረጃ መለቀቅ ጀምሯል።

🤩 @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🗣Elon Musk : ዓለማችን በኮምፒውተር ሲሙሌሽን ውስጥ ልትሆን እንደምትችል ያለውን እምነት እና አስገራሚ መላ-ምት ገለፀ

ኢሎን መስክ የወደፊቱን ጊዜ ለመገመት የሚጠቀምበትን ንድፈ-ሀሳብ ሲያብራራ እጅግ ሳቢ እና አዝናኝ የሆነው ውጤት የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነው ሲል ተናግሯል። መስክ እንደገለፀው ዓለማችን የተመሰለች ምናባዊ አለም ከሆነች ሲሙሌሽኑን የሚያስኬዱት አካላት አሰልቺ በሚሆንበት ጊዜ ሊያቆሙት ስለሚችሉ ሲሙሌሽኑ እንዲቀጥል ሁልጊዜም አስደናቂ እና ሳቢ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ይደረጋል።

🔺SpaceX የሮኬት ሙከራዎችን በኮምፒውተር ሲሙሌሽን ሲያከናውን ትኩረት የሚሰጠው እጅግ አስገራሚ ለሆኑት ውጤቶች ብቻ እንደሆነ መስክ አስረድቷል

🔺 ዓለማችን ለሌሎች የጠፈር ፍጥረታት እንደ አንድ የ-Netflix ተከታታይ ድራማ ልትሆን እንደምትችል የገለፀው መስክ ድራማው ሊቀጥል የሚችለው የተመልካች ደረጃው ጥሩ ሲሆን ብቻ እንደሆነ አመሳስሏል

🔺 የዳርዊንን የዝግመተ-ለውጥ ህግ በሲሙሌሽን ላይ ብንተገብረው ቀጣይነት የሚያገኙት እጅግ ሳቢ የሆኑት ሲሙሌሽኖች ብቻ ናቸው ስለሆነም የምናየው እውነታ ወይ ሳቢ መሆን አለበት አለበለዚያ መጥፋት ይከተላል

🔺 በመሆኑም የሰው ልጅ ብቸኛ ግብ ዓለምን ሳቢ እና አስደናቂ አድርጎ ማቆየት መሆን እንዳለበት ገልጿል

🤩 @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍3
🛍️ አሊባባ QwenWork የተሰኘ ሁሉን አቀፍ የስራ ቦታ AI ኤጀንት በይፋ ለቀቀ

➡️ተጠቃሚዎች የሚፈልጉትን ስራ ቋንቋ በመግለጽ ብቻ ኤጀንቱ ተግባራትን እንዲያከናውን ማድረግ የሚችሉ ሲሆን ሲስተሙ የተጠቃሚውን የአሰራር ልምድ ቀስ በቀስ በመረዳት ለቀጣይ ስራዎች ተግባራዊ ያደርጋል።

➡️QwenWork ያለምንም ኮዲንግ ወይም የሰርቨር ማዋቀር ድረ-ገጾችን እና የዌብ መተግበሪያዎችን የመገንባት እንዲሁም የሚዲያ ይዘቶችን የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን አገልግሎቱ በድረ-ገጽ እና በኮምፒውተር መተግበሪያ ላይ በይፋዊ የቅድመ-ሙከራ ደረጃ ለዓለም አቀፍ ተጠቃሚዎች ክፍት ሆኗል።

🤩 @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎችን ፊት በመመልከት ብቻ የስኳር እና የደም ግፊት በሽታዎችን መለየት የሚያስችል አቅም አገኘ

በቶኪዮ የሚገኙ ተመራማሪዎች በጥቂት ሰከንዶች የፊት ቪዲዮ አማካኝነት የደም ግፊት እና የስኳር በሽታ ምልክቶችን በከፍተኛ ትክክለኛነት መለየት የሚችል አዲስ የ AI ሲስተም ይፋ አድርገዋል። ቴክኖሎጂው በሰው ዓይን የማይታዩ ጥቃቅን የደም ዝውውር ለውጦችን የልብ ምት ቅጦችን እና የቆዳ ቀለም ልዩነቶችን በመተንተን ነው በሽታዎቹን የሚለየው።

🖱️ የደም ግፊትን በ30 ሰከንዶች ቪዲዮ በ 95% እንዲሁም በ 5 ሰከንዶች ብቻ በ 90.3% ትክክለኛነት ለይቷል

🖱️ የስኳር በሽታን በ30 ሰከንዶች ቅጂ በ 88.2% እንዲሁም በ 5 ሰከንዶች ውስጥ በ 81.2% ትክክለኛነት መለየት ችሏል

🖱️ የደም ግፊት መለኪያ ማሰሪያ (Cuff) ሳይጠቀም የደም ግፊትን በከፍተኛ ትክክለኛነት መገመት የቻለ ሲሆን አማካይ የስህተት መጠኑ -2.6 mmHg ብቻ ሆኖ ተመዝግቧል

ምንም እንኳን ቴክኖሎጂው በአሁኑ ወቅት መደበኛውን የደም ምርመራ ሙሉ በሙሉ ባይተካም ወደፊት ተራ ካሜራዎችን ብቻ በመጠቀም የጤና እክሎችን አስቀድሞ ለመለየት ትልቅ ተስፋ የጣለ ግኝት ነው።


🤩  @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🤶 Anthropic ለ Claude ሞዴል እንደ ማይክሮስኮፕ፣ የሮቦት እጆች እና ሌሰር ያሉ የላቦራቶሪ እቃዎችን በቀጥታ የመቆጣጠር አቅም ሰጠ

Claude የተለያዩ አካላዊ የሳይንስ መሳሪያዎችን በራሱ እንዲያንቀሳቅስ በተደረገበት የሙከራ ሂደት እጅግ አስደናቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በ QuEra የኳንተም ኮምፒውተር ሌሰሮችን የማስተካከል ስራ ላይ ባለሙያዎች ከ5 እስከ 10 ደቂቃ የሚፈጅባቸውን ተግባር Claude ያለ ሰው ቁጥጥር በ6 ሰከንዶች ውስጥ ያጠናቀቀ ሲሆን የስኬት ምጣኔውንም ከ 58% ወደ 99.3% አሳድጎታል።

በተጨማሪም በ Genentech የፈሳሽ መመጠኛ መሳሪያዎችን (Pipetting) በራሱ እንዲያስተካክል የተደረገ ሲሆን በአንድ ዩኒቨርሲቲ ላቦራቶሪ ደግሞ ሌሊት በሰው እጅ የሚከናወነውን ስራ ሙሉ በሙሉ በራሱ አከናውኗል። በካሊፎርኒያ ወንዝ ውስጥ የሚገኝ የፍሳሽ ብክለትን ለመለየት የተደረገውን የ qPCR ምርመራ በተሳካ ሁኔታ የመራው Claude ሳይንሳዊ ላቦራቶሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ አውቶሜሽን እየተሸጋገሩ መሆናቸውን አሳይቷል።

🤩  @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2
🤖 Perplexity በኮምፒውተር ላይ Local ሆኖ የሚሰራ አዲስ AI Agent ይፋ አደረገ

🖱️Portable Computer ሞዴሎቹን እና የ Agent ሲስተሙን በቀጥታ በተጠቃሚው ኮምፒውተር ላይ የሚያስኬድ ሲሆን Local ፋይሎችን እና ኮዶችን Search በማድረግ ትዕዛዞችን Run በማድረግ እንዲሁም ዳታ ወደ Cloud ሳይልክ ረጅም Tasks የማከናወን አቅም አለው።

🖱️ይህ አሰራር Qwen 3.8 27B እና PPLX 27B ሞዴሎችን የሚጠቀም ሲሆን ምንም አይነት የ Perplexity Credits አይቀንስም። በአሁኑ ወቅት በ Linux ላይ ለሚገኙ Pro እና Max ተጠቃሚዎች ክፍት የሆነ ሲሆን ለ Windows እና መደበኛ Nvidia RTX ኮምፒውተሮች ወደፊት ይለቀቃል።

🤩 @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔍 Google ለቪዲዮ Create ማድረጊያ ትልቅ Upgrade ይዞ የመጣውን Gemini Omni 1.1 Flash ይፋ አደረገ

➡️ Google ለሁሉም ተጠቃሚዎች ክፍት ያደረገው Gemini Omni 1.1 Flash አጫጭር ቪዲዮዎችን በ10 ሰከንዶች ክፍፍል እስከ 40 ሰከንዶች ድረስ Extend የማድረግ አዲስ አቅም ይዞ መጥቷል።

➡️ ሞዴሉ የቪዲዮውን ቀጣይ ክፍል Generate ሲያደርግ የቀደመውን የመጨረሻ አንድ ሰከንድ ብቻ ከመጠቀም ይልቅ ያለፉትን 10 ሰከንዶች ሙሉ በሙሉ ተንትኖ ስለሚሰራ የትዕይንቶች Transition እጅግ Smooth እና ወጥ እንዲሆን ያደርጋል።

🤩 @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1👍4
🤖 ChatGPT Search በአውሮፓ ህብረት ውስጥ 159 ሚሊዮን ወርሃዊ ተጠቃሚዎች ላይ ደረሰ

የ ChatGPT Search ተጠቃሚዎች ቁጥር በአውሮፓ ህብረት ውስጥ በፍጥነት በማደጉ ምክንያት የአውሮፓ ኮሚሽን አገልግሎቱ ይበልጥ ጥብቅ የሆኑ አዳዲስ ህጎች እና ደንቦች (Regulations) የሚተገበሩበት ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቋል።

አውሮፓ ከዚህ ጋር የሚወዳደር የራሷን የ AI ቴክኖሎጂ መገንባት ባትችልም የውጭ ቴክኖሎጂዎችን ቁጥጥር ስር በማዋል እና ህጎችን በመጫን ላይ ብቻ ያተኮረ ፖሊሲዋን እንደ ትልቅ ስኬት እያየችው ይገኛል።

🤩 @Addisintel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‼️ AI የህጻናት የቅርብ ጓደኛ እየሆነ መምጣቱ ከፍተኛ ስነ-ልቦናዊ ስጋት ፈጥሯል

ታዋቂው የማህበራዊ ሳይኮሎጂ ባለሙያ ጆናታን ሃይድት  እንዳስጠነቀቀው ማህበራዊ ሚዲያዎች የልጆችን ትኩረት የመሰብሰብ አቅም ያዛቡትን ያህል የ AI አጋሮች ደግሞ የልጆችን ጥልቅ ስሜታዊ ትስስር የመቆጣጠር አደጋ አላቸው። ፈጽሞ የማይደክመው የማይፈርድበት እና ልጅ በሚፈልገው መንገድ ብቻ ምላሽ የሚሰጠው የ AI ጓደኛ ከእውነተኛ ሰዎች ጋር ከሚደረግ ማህበራዊ ግንኙነት ይልቅ ለህጻናት ይበልጥ ሳቢ እየሆነ መጥቷል።

🔺ህጻናት ከወላጆቻቸው ከቤተሰቦቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ይልቅ ከ AI ጋር ጠንካራ ስሜታዊ ትስስር  የመፍጠር ስጋት ተደቅኗል

🔺 የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ትርፍ ለማግኘት ሲሉ እነዚህን የልጆች “ምርጥ ጓደኞች” ዳታ መሰብሰቢያ ማስታወቂያ ማሰራጫ እና የተጠቃሚውን ትኩረት መቆጣጠሪያ ሊያደርጓቸው ይችላሉ

🔺 የመጀመሪያ ደረጃ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ህጻናት ከ AI አጋሮች ጋር ባልተገባ መልኩ እየተቆራኙ እና ከእውነተኛው ዓለም ማህበራዊ ግንኙነት እየራቁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል

🤩 @AddisIntel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍3