በጥቆማ የተያዘ 46 ሺሕ ሊትር ዘይት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል ነው
መጋቢት 21/2014 (ሪፖርተር) በኅብረተሰቡ ጥቆማ በህገወጥ መንገድ በመኪና ተጭኖ የተያዘ ከ46 ሺሕ ሊትር በላይ ዘይት በመሰረታዊ ሸማች አማካኝነት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል መሆኑ ተገለፀ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር በመኪና ጥበቃ ላይ በተሰማሩ ነዋሪዎች ጥቆማ ከ2 ሺሕ 300 ካርቶን በላይ ዘይት ጭኖ የነበረ መኪና በኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል ተወርሶ በወረዳው መሰረታዊ ሸማች ማኅበር አማካኝነት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል መወሰኑን ወረዳው አስታውቋል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ትዝታ ነጋሽ ኅብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ተግባራትን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች:-
https://t.me/ethiopian_reporter

👍4❤1
የአማራ ክልል መንግሥት በወረራ የተያዙ ወረዳዎችን በተደራጀ ጥምር ጦር ማስለቀቅ እንደሚገባ አሳሰበ
የአማራ ክልል መንግሥት የሕወሓት ኃይሎች ‹‹ለዳግም ወረራ›› ይመጣሉ የሚል ሥጋት በመኖሩ ‹‹ጦርነቱ ተጠናቋል›› የሚል ሐሳብ እንደሌለውና በሕወሓት የተያዙ የክልሉ ወረዳዎችንም የተደራጀ ጦር በማሰለፍ ነፃ ማውጣት እንደሚገባ አሳሰበ፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ሕወሓት በያዛቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ለርሃብና ለሕክምና ዕጦት መዳረጋቸውን ለሕዝቡ ሲባል ሕወሓት በክልሉ ላይ የፈጸመው ‹‹ወረራ›› በፍጥነት ምላሽ ማግኘት አለበት የሚለውን ሐሳብ እንደሚጋሩ ተናግረዋል፡፡
መጋቢት 15 እና 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በተካሄደው የክልሉ ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር፣ አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔው ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት ይልቃል (ዶ/ር) በርካታ ወረዳዎች አሁንም በሕወሓት ቁጥጥር ሥር መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ዝቋላ፣ ፃግብጂ፣ አበርገሌ፣ አድርቃይና ጠለምት አከባቢዎች አሁንም ነፃ እንዳልወጡ በፕሬዚዳንቱ ከተጠቀሱ አከባቢዎች መካከል ናቸው፡፡

👍10🔥1
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ (ኢብባ) ለሲንቄ ባንክ የፕሬዝደንት ሹመት በልዩ ሁኔታ በሚል የሰጠው ይሁንታ ጥያቄ አስነሳ፡፡
ሲንቄ ባንክ በበኩሉ ኢብባ በልዩ ሁኔታ ብሎ መፍቀዱ ለምን እንደሆነ ግራ እንዳጋባው ጠቅሶ ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑን የጠየቀው በህጉ መሰረት ይሁንታ እንዲሰጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከሰሞኑ ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ ለሲንቄ ባንክ የፕሬዝደንትነት ሹመት ከባንኩ ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው የይሁንታ ምላሽ ደብዳቤ እንደጠቀሰው የአቶ ንዋይ መገርሳን ሹመት በልዩ ሁኔታ መፍቀዱን አስታውቋል፡፡
ይህ የኢብባ ውሳኔ በዘርፉ ያሉትን ባለሞያዎች ግራ ያጋባ ሆኖም ተስተውሏል፡፡“ተቆጣጣሪ ሁሉንም በሚያስተናግደው የህግ መሰረት መስራት ሲገባው ለምን በልዩ ሁኔታ ሲል መፍቀድ ፈለገ፡፡ ሁለት አይነት አሰራር ነው የታየው፤ ከጠንካራ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የማይጠበቅ ነው፣፣” ሲሉም ውሳኔውን ተችተዋል፡፡
ከኢብባ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ ሆኖም የሲንቄ ባንክ ፕሬዝደንት አቶ ንዋይ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።በምላሻቸውም የብሄራዊ ባንክ ደብዳቤ ግራ እንዳጋባቸው ገልፀው ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ የተጠየቀው በህጉ መሰረት ይሁንታ እንዲሰጥ ወይም እንዲከለክል ነው ለምን በልዩ ሁኔታ ፈቅጃለሁ እንዳለ እኔም ግራ ገብቶኛል ብለዋል፡፡በማከልም በኢብባ መመሪያ መሰረት በፕሬዝደንትነት ለመስራት የሚያበቃ በቂ የስራ ልምድ አለኝ በማለት አክለዋል፡፡
[Capital]

👍4
#EthioTelecom
ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች ልዩ ጥቅል ማቅረቡን ገለፀ።
ኢትዮ ቴሌኮም ለኮሌጅ እና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ የሆነ የተማሪ ጥቅል ማቅረቡን አሳውቋል።
በዚህም :
ወርሃዊ ፦
• ዋጋ 👉 34 ብር ፤ ጥቅል 👉 180 ደቂቃ (ጥሪ) ፤ ስጦታ 90 ደቂቃ (ጥሪ) + 100 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 64 ብር ፤ ጥቅል 👉 360 ደቂቃ (ጥሪ) ፤ ስጦታ 200 ደቂቃ (ጥሪ) + 150 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 42 ብር ፤ ጥቅል 👉 1 GB (ዳታ) ፤ ስጦታ 512 MB (ዳታ) + 100 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 82 ብር ፤ ጥቅል 👉 2 GB (ዳታ) ፤ ስጦታ 1.1 GB (ዳታ) + 150 መልዕክት ፤
ሳምንታዊ ፦
• ዋጋ 👉29 ብር ፤ 3 GB (ዳታ) መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ሳምንታዊው የዳታ ጥቅል እና ለደንበኞች የቀረቡት ስጦታዎች የሚያገለግሉት ከለሊቱ 6 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት መሆኑን አሳውቋል።
ተማሪዎች ተማሪነታቸውን የሚገልፅ " መታወቂያ " በመያዝ በኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከሎች በመቅረብ ጥቅሎቹን መግዛት ይችላሉ ተብሏል።

👍7👏2😱2🔥1
#AddisAbaba🪧
በአዲስ አበባ ከተማ ህገወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች እየተነሱ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02፣ 08፣ 10 እና 13 በህገ ወጥ መንገድ መሰረተ ልማት አውታሮች እና የዋና መንገድ ኤልክትሪክ ፖሎች ላይ የተሰቀሉ ህገ ወጥ የውጭ ማስታውቂያ ማንሳቱን አስታውቋል።
ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያዎች የተነሱባቸው ቦታዎች ፦
👉 ከሳህሊተ ምህረት እስከ የተባበሩት ግራ እና ቀኝ ፣
👉 ከተባበሩት እስከ ፍየል ቤት ፤
👉 ከፍየል ቤት እስክ ፊጋ
👉 ከተባበሩት እስከ አያት አደባባይ
👉 ከአያት አደባባይ እስከ ጣፎ አደባባይ ድረስ በግራና በቀኝ በኩል ተሰቅለው የነበሩ ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን አሳውቋል።
በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ከተሞች የተሰቀሉ ህገወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች የማንሳት ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
መረጃው የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ነው።

👍3🔥3
ከ100 በላይ ቤቶች በ12 ቀናት ውስጥ መቃጠላቸው ተገለጸ!
ከመጋቢት አንድ እስከ 12/2014 ባሉት ቀናት ውስጥ በምሥራቅ ወለጋ ሊሙ ወረዳ ሥር የሚገኙ ከ100 በላይ ቤቶች በታጣቂዎች መቃጠላቸውን አስተማማኝ ምንጮች ተናግረዋል።
ሥሜ እንይጠቀስ ያሉ የመረጃ ምንጫችን ከመጋቢት አንድ እስከ 12/2014 ባሉት ቀናት ብቻ ከ100 በላይ የሚሆኑ ቤቶች በታጣቂዎች ተቃጥለዋል ሲሉ ነው ገለጹት።
አስከትለውም፣ “የነዋሪዎቹን ቤት የሚያቃጥሉት ጁንታና ሸኔ ናቸው” ብለዋል። የሕወሓት አባሎች በአካባቢው ይኖሩ እንደነበር የገለጹት የመረጃ ምንጩ “መታወቂያቸው እየተቀየረላቸው ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው” ሲሉም ጠቁመዋል።
የሕወሓት ታጣቂዎችም ከሊሙ ወረዳ ወጣ ብለው ክልል ስድስት ድንበር ላይ በዴሳ እና መንደር ስምንት በሚባለው አካባቢ እንደሚገኙም ነው ግለሰቡ ያመላከቱት።

👍6👎1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
#መረጃ! #ምንጃር! ሽብርተኛዉ ኦነግ ሸኔ ምንጃር አውራጎዳና ገባ ግን አልወጣም ተባለ። የሽብር ቡድኑ ሁለት ፌደራል ፖሊስ እና አንድ የአካባቢው ንፁሀን ሰዉ ገድሏል። በተጨማሪም በመሀል ከተማ ውስጥ ስድስት ሰው እንዳቆሰሉ ተገልጿል በስልጠና የዳበረ የምንጃር አውራጎዳና ነዋሪ የሽብር ቡድኑ እንደመግባት ቀላል ሳይሆንለት አስቀርቶታል። https://t.me/ethiopian_reporter https:/…
#update
#MinjarShenkora📍
በምንጃር ሸንኮራ በተፈፀመ ጥቃት የሰው ህይወት አለፈ።
በወረዳው " አሞራ ቤት ቀበሌ " ላይ ታጣቂዎች ፈፀሙት በተባለው ጥቃት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ጥቃቱ ከኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ " አዉራ ጎዳና መንደር ትናንት ከሰዓት የተፈፀመ ሲሆን የሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ከሚል መረጃ ውጭ ምን ያህል የሚለው አልታወቀም።
ወረዳው ጥቃቱን ያደረሱ ታጣቂዎች ምናልባት ማንነታቸው ያልታወቁ " የፀረ ሰላም ኃይሎች " ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል።
የምንጃር ሸብኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ቦሰት ጥቃቱን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ፦
" ትላንትና መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ከኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ ልዩ ቦታዉ አዉራ ጎዳና ተብሎ በሚጠራ መንደር ላይ ታጣቂዎች በተደራጀ እንዱሁም በቡድንና በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ባደረሱት ጥቃት የሰዉ ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል " ብለዋል፡፡
በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸዉ ግለሰቦች በአረርቲ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና ወደ አዲስ አበባ ከተማ ተልከዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
" አካባቢዉ ለዓመታት የተለያዩ ትንኮሳዎች ይስተዋልበት ነበር ያሉት " አቶ ታደሰ ፤ " የትናንቱ ግጭት ግን መነሻዉ በግልፅ የማይታወቅ ፤ ምናልባትም ማንነታቸዉ በግልፅ ያልታወቁ ፀረ ሰላም ኃይሎች አቅደዉበት እና አካባቢዉን በማዉደም ነዋሪዎችን ለማፈናቀል አልመዉ የመጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል " ብለዋል፡፡
አቶ ታደሰ ቦሰት " ለጊዜዉ ማንነታቸዉ ያልታወቁ ታጣቂዎቹ ጥቃት ማድረሳቸዉን ተከትሎ ንፁሀን እንዳይጎዱ በተለይ ሴቶችን ህፃናትንና ነፍሰጡሮቹን ከስፍራዉ የማዉጣት ስራ ተሰርቷል " ያሉ ሲሆን " ቤት ንብረታቸዉን ትተዉ ወደ ጫካ የሸሹ በመኖራቸዉና ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ የስልክ ግንኙነት ባለመኖሩ ተጨማሪ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ማወቅ እንዳልተቻለ ገልፀዋል።
" ትናንትና አመሻሽ ከ12፡00 በኋላ በአካባቢዉ የፌደራል ፖሊስ በመግባቱና የማረጋጋት ስራ በመሰራቱ አሁን ጥቃቱ በቁጥጥር ስሮ ዉሏል " ብለዋል።
" የአካባቢዉን ሰላም ለማናጋት ከሁሉም ወገን የፀረ ሰላም ኃይሎች ሊኖሩ ይችላሉ " ያሉት አቶ ታደሰ ፤ " በማጥራት እና የጋራ ምክክር በማድረግ የአካባቢዉን ሰላም በዘላቂነት ለማስፈን በቀጣይ በትኩረት ሊሰራ የሚገባ ጉዳይ ነዉ " ብለዋል።
ወረዳው በትላንትናው ጥቃት አድራሾቹ " የማይታወቁ ፤ ፀረ ሰላም ኃይሎች " እያለ መጥራቱ ቅሬታ ያሳደረባቸው አካላት እንዲህ ያለው መሸፋፈን ይበልጥ ችግሩን ከማወሳሰብ በዘለለ ምንም አይነት ፋይዳ እንደሌለው አስገንዘበዋል።
ከዚህ በፊት በተለያዩ የሀገሪቱ ቦታዎች ለሚፈፀሙ ጥቃቶች " ማንነታቸው ያልተረጋገጠ፣ ፀረ ሰላም ኃይሎች " የሚሉ ቃላትን መጠቀም የተለመደ ነው።

😢7👍4🥰1
በእስራኤል ውስጥ አንድ ያልታወቀ ግለሰብ መትረየስ መሳሪን በመጠቀም ሰላማዊ ዜጎች ላይ ተኩስ ከፈተ ።
በከፈተው ተኩስ ቢያንስ 5 ሰዎች መሞታቸውን ተዘግበዋል ። ተኩስ የከፈተው ግለሰብም እዛው እርምጃ እንደተወሰደበት ከቦታው ያገኝነው መረጃ ያሳያል።
https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
በከፈተው ተኩስ ቢያንስ 5 ሰዎች መሞታቸውን ተዘግበዋል ። ተኩስ የከፈተው ግለሰብም እዛው እርምጃ እንደተወሰደበት ከቦታው ያገኝነው መረጃ ያሳያል።
https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
👍6👏3
ዩክሬን ሩሲያ ለዓመታት አጥብቃ ስትጠይቅ የነበረውን ጥያቄ ለማክበር መስማማቷ ተገለፀ!
የሩሲያ ልዑካን ቡድን መሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ እንዳሉት ዩክሬን የወደፊቱን ስምምነት ዋና መርሆች የያዘውን ረቂቅ አስረክባለች።
"ዩክሬን ማንኛውንም ህብረት ከመግባት ትታቀባለች።የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እና የውጭ ወታደራዊ ቡድንን አትተባበርም።የትኛውም ወታደራዊ ልምምድ የምታደርገው የሩሲያ ፈቃድ ሲኖር ብቻ ነው።" ብለዋል።
"ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኪየቭ ባለስልጣናት ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል" ሲሉ መናገራቸውን ራፕትሊ ዘግቧል።

👍6🔥2❤1
#Education_and_Training_Authority
"ሀምበርቾ ኮሌጅ" በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀስ ተቋም ምንም አይነት የእውቅና ፈቃድ #እንደሌለው የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል።
‘’ሀምበርቾ ኮሌጅ" ምንም አይነት የእውቅና ፈቃድ ሳያገኝ በአማራ ክልል በአዴት ከተማ እና በሌሎች የክልሉ ከተሞች በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎችን እያስተማረ መሆኑን ባካሄደው ማጣራት ማረጋገጡን ባለሥልጣኑ ጠቁሟል፡፡
ራሱን ‘’ሀምበርቾ ኮሌጅ’’ በማለት የሚጠራው ተቋም በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ እንዲያስተምር የተሰጠው የእውቅና ፈቃድ #የሌለው በመሆኑ የሚሰጠው ትምህርትም ሆነ የትምህርት ማስረጃ ተቀባይነት የሌለው እና ሕገ-ወጥ እንደሆነ ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡
በመሆኑም የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን የሕግ ማስከበር እርምጃ እንዲወስድ ባለስልጣኑ ጠይቋል፡፡

👍2👏1
43 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ከአራት የአውሮፓ ሀገራት ተባረሩ!
አራት የአውሮፓ ሀገራት 43 የሩሲያ ዲፕሎማቶች በስለላ ወንጅል ከጠረጠሯቸው በኋላ አባረዋል፡፡
ቤልጂየም ለ21 የሩስያ ዲፕሎማቶች ለብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ናቸው ብላ መናገሯን እና የሁለት ሳምንት ጊዜ መስጠቷን ሲጂቴን ዘግቧል፡፡የቤልጂየም ጎረቤት ኔዘርላንድስ በዲፕሎማሲያዊ ቪዛ በሀገሪቱ ውስጥ የነበሩትን 17 ሩሲያውያንን ማባረሯን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የአየርላንድ ሪፐብሊክም አራት "ከፍተኛ ባለስልጣናት" ግዛቷን ለቀው እንዲወጡ ጠይቃለች፤ ነገር ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ የተባረረበትን ምክንያት ግልጽ አላደረገም፡፡ቼቺያም አንድ ዲፕሎማት ከሀገሯ እንዲወጡ 72 ሰአታት ብቻ ሰጥታለች። በፕራግ የሚገኘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ያለውን የሩሲያ የስለላ መረጃ እየቀነስን ነው" ብሏል። ዲፕሎማቶቹን ያረሩት አራቱም ሀገራት የአውሮፓ ህብረት አባል ናቸው፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” መክፈቷን ተከትሎ በሩሲያ እና በአውሮፓ መካከል ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ ገብቷል፡፡ ሩሲያ ወደ ግጭት የገባቸውም የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ ሶቬት አባል ሀገራት እየተስፋፋ ነው ይህም ለደህንነቴ ያሰጋኛል በሚል ነበር፡፡ ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ግጭት ውስጥ ከገቡ በኋላ ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ሁሉንም አይነት ማእቀብ ጥለዋል፤እየጣሉም ነው፡፡ ሁለቱ ሀገራት ግጭቱን በሰላም ለመፍታት ድርድር ጀምረዋል፡፡

👍6🔥1
❗️❗️ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና ሕዝብ በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን የተቃጣበትን ጦርነት እየመከተና በጦርነቱ ምክንያት ከደረሱበት ሁለንተናዊ ጉዳቶች ለማንሰራራት ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል።
የአማራ ህዝብ የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ቀዳሚ የጥቃት ዒላማ በመሆኑ ወራሪ ቡድኑ በክልሉ ህዝብ ላይ ያላደረሰው ሰብአዊ ቀውስ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት አለ ተብሎ አይወሰድም። በዚህም ምክንያት የክልሉ መንግሥትም ሆነ መላው ሕዝብ መክፈል የማይገባውን ከፍተኛ መስዋዕትነት ተከፍሏል።
መሪው ፓርቲም ይህንን ነባራዊ ሁኔታ መነሻ ያደረገና መላውን የአማራ ሕዝብ ያሳተፈ ተጨባጭ የመፍትሔ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። በጦርነቱ የጉዳት ሰለባ የሆኑ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ከደረሰባቸው ስነ ልቡናዊ ጥቃት እንዲያገግሙ ጥረት ከማድረግ ጎን ለጎን የወደሙ ተቋማትና መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት የአደጋ ጊዜ አመራር እያረጋገጠ ይገኛል።
ይህ ተግባር ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተሳትፎ ውጭ የሚሳካ እንዳልሆነ የክልሉ መንግሥት ጽኑ እምነት አለው።
ምንም እንኳን ከወራሪው ኃይል ጋር በከፊል ጦርነት ውስጥ መሆናችን የሚዘነጋ ባይሆንም ጎን ለጎን በሕዝቦች መካከል በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጽናት የሚያስችሉ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና አያሌ የምክክር መድረኮችን እያከናወነ መሆኑም ይታወቃል።
ይሁን እንጂ አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ውላጅ የሆኑ ተስፈኛ ጽንፈኞችና አሸባሪዎች በአማራ ክልል ሕዝብ እና በአጎራባች ክልል ሕዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠርና የክልሉን ሕዝብ ማኅበራዊ እረፍት ለመንሳት በክልላችን አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ለማጫር ተንቀሳቅሰዋል፤ እየተንቀሳቀሱም ይገኛሉ።
እነዚህ የጥፋት ኃይሎች በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጃዊ ወረዳ በምንዋሰንባቸው የቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን በላያ እና አካባቢው፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በመልካ ጅሎና ሲናናጆ ቀበሌ እንዲሁም በማእከላዊ ጎንደር ዞን በአንድ አንድ አካባቢዎች በወንድማማቾችና እህትማማቾች መካከል በአንድነትና በፍቅር ለሺ ዘመናት አብሮ በኖረው የአማራ ሕዝብ መካከል እንዲሁም ከኦሮሞ እና ከጉሙዝ ሕዝብ ጋር የግጭት ሙከራ ያደረጉ ቢሆንም በአማራ እና በሁለቱም ክልሎች ህዝብ ሆደ ሰፊነት እና በጀግኖች የጸጥታ አካላት ተሳትፎ የጥፋት እና የእልቂት ፍላጎታቸው ሳይሳካ ቀርቷል፤ እንዲከሽፍም ተደርጓል።
ይህንን የጥፋት ሙከራ ለመቆጣጠርና ለመቅረፍ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከኦሮሚያ እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥታት ጋር ተባብሮ በመሥራት ላይ ይገኛል።
ይህ የጨነገፈ የጥፋት ተልእኮ ሙከራ ጽንፈኛና ፀረ ሰላም ኃይሎች ምን ያህል በተቀናጀና ተመጋጋቢ በሆነ መንገድ የአማራ ክልልን የግጭት ማእከል ለማድረግ አልመው እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ በተጨባጭ ያረጋግጣል።
ስለሆነም መላው የአማራ ክልል ሕዝብ ከውስጥም ሆነ ከውጭ በሕዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠር በህቡዕም ሆነ በገሃድ የሚንቀሳቀሱ የጽንፈኛ ኃይሎችን እኩይ ዓላማ በመረዳት እንደወትሮው ሁሉ ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ጽንፈኛና ፀረ ሰላም ቡድኖችን አደብ ለማስገዛት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና የህግ የበላይነትን የማስከበር መንግሥታዊ ስምሪት ሆን ተብሎ በሚለቀቅ የተሳሳቱ መረጃዎች ሕዝቡ ሳይወዛገብ በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀልን ለመከላከል የዜግነት ድርሻችሁን እንድትወጡ የክልሉ መንግሥት በአክብሮት ይጠይቃል።
በሌላ በኩል በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከጽንፈኛና ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ የጥፋት ትስስር በመፍጠር የአማራ ክልልን የቀውስ ሜዳ ለማድረግ፤ የክልሉን ሕዝብ ማኅበራዊ እረፍት ለመንሳት እንዳሁም የህዝባችንን ሰላምና የመልማት እድል በመንፈግ ከድህነት እንዳይወጣ ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀን የጠላት እቅድ በመፈጸምም ሆነ በማስፈጸም እኩይ ተግባር ውስጥ የተዘፈቃችሁ አካላት ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ የክልሉ መንግሥት በጥብቅ ያሳስባል።
ከየትኛውም ጠላት ጋር የምናደርገውን ትግል ከሰላም ወዳድ ወገኖቻችን ጋር በመተባበር አጠናክረን የምንቀጥል ሲሆን እዚህ እና እዚያ በመርገጥ የክልሉን ሕዝብ ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል በግልፅም ሆነ በህቡዕ የምትንቀሳቀሱ ኃይሎች ከዚህ እኩይ ድርጊታችሁ የማትታቀቡ ከሆነ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ማንኛውንም አይነት ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አበክሮ ያስጠነቅቃል።
በመጨረሻም የአማራ ክልል መንግሥት የክልሉን ልማትና የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሲል በሚወስደው ማንኛውም አይነት ህጋዊ እርምጃ መላው የክልሉ ሕዝብ ከመንግሥት ጎን እንዲቆም በድጋሚ የአክብሮት ጥሪውን ያሳተላልፋል።
በሕዝብ ስም እየነገዱ የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ቅርቃር ውስጥ ማስገባት የሕዝብ ፀርነት እንጂ ሕዝባዊነት አይደለም!
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ባህር ዳር

👍8
በኢትዮጵያ የአውሮፕላን ነዳጅ እጥረት መከሰቱ ተሰማ!
የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለ ሥልጣን የአውሮፕላን ነዳጅ ክምችት መጠን አስተማማኝ እንዳልሆነ ዋዜማ ሰምቻለሁ ብላለች። ይህንኑ ግምት ውስጥ በማስገባት ባለሥልጣኑ ሌሎች አየር መንገዶች ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመብረራቸው በፊት ከሌላ አገር ነዳጅ እንዲቀዱ በመምከር ላይ ነው። ባለሥልጣኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች እንዳይስተጓጎሉ የተለያዩ ርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ሆኖም ችግሩ በአጭር ጊዜ ይፈታል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል። በተያዘው ሩብ በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ካስገባችው 1 ሚሊዮን ቶን ነዳጅ ውስጥ የአውሮፕላን ነዳጅ 12 በመቶ ብቻ ነው።ሰሞኑን በበርካታ ከተሞች ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ተከስቷል።

👍6😁1
" አፋር ውስጥ ጦርነቱ ቀጥሎ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም ሊኖር አይችልም " - አቶ ሰዒድ ሙሳ ኢብራሒም (የኤሬብቲ ጎሣ መሪ)
አፋር ክልል ውስጥ የቀጠለው ጦርነት " ለሰብዓዊነት ሲባል በታወጀው ግጭት ማቆም ውሳኔ " ላይ አደጋ መደቀኑን ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።
ሮይተርስ ፤ አፋር ውስጥ ጦርነቱ መቀጠሉን 2 የሰብአዊ ርዳታ ሠራተኞች እንዳረጋገጡለት አስነብቧል።
በአፋር 6 ወረዳዎች በትግራይ ኃይሎች መያዛቸውን ዘገባው ገልጿል።
የአፋር ኤሬብቲ ጎሣ መሪ አቶ ሰዒድ ሙሳ ኢብራሒም ለሮይተርስ በሰጡት ቃል፥ " አፋር ውስጥ ጦርነቱ ቀጥሎ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም ሊኖር አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።
የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አህመድ ሃሪፍ ፤ በትግራይ ኃይሎች ተይዘዋል ካሉት 6 ወረዳዎች 2ቱ ውስጥ ጦርነቱ መቀጠሉን፤ በክልሉ መዳረሻ ላይም በከፍተኛ ሁኔታ የትግራይ ኃይሎች እየተበራከቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የህወሓት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት ቃል በተጠቀሱት አካባቢዎች ውጊያ የለም ሲሉ አስተባብለዋል።
በአፋር ክልል አቅራቢያ ተዋጊዎቻቸውን እያሰፈሩ ነው ስለመባሉ ግን ማስተባበያ አልሰጡም ሲል ሮይተርስ ገልጿል። (Reuters.com / Deutsche Welle)
በሌላ መረጃ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል።
አምባሳደር ጃኮብሰን ፤ አሜሪካ በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል የገለፁ ሲሆን አቶ አወል አርባ ህወሓት እያደረሰ ነው ያሉትን ስቃይ የዓለም ህብረተሰብ በፅኑ ሊያወግዘው ይገባል ብለዋል።

👍11