በጉራጌ ዞን በደረሰ የእሳት አደጋ 42 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለፀ!!
በቀቤና ወረዳ በሌንጫ ቀበሌ ልዩ ስሙ ፈረጀቴ ጎጥ ትናንት እኩለ ቀን ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ 35 የሳር ክዳን ቤቶች፣ 5 የቆርቆሮ ክዳን ቤቶችና 2 መስጂዶች በድምሩ 42 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ነው የተገለፀው።
2ቱ መስጂዶች በከፊል የወደሙ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በምርትና በሰብል ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱም ተጠቁሟል። በጥንቃቄ ጉድለት በአካባቢው የነበረውን ቁጥቋጦ ለማጥፋት በሚል የተለኮሰ እሳት በወቅቱ በነበረ ከፍተኛ ንፋስ ወደ አካባቢው በመዛመቱ ነው የእሳት አደጋው የደረሰው።
በእሳት አደጋው በቤትና ንብረት ላይ ከደረሰው ውድመት በተጨማሪም በእንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል። በእሳት አደጋው ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት በደረሰው አደጋ ለከፍተኛ ችግር በመጋለጥ ሜዳ ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።
በመሆኑም በጊዜያዊነትና በቋሚነት ለማቋቋም የወረዳውና የዞኑ አስተዳደር፣ የአካባቢው ተወላጅ ባለሃብቶች፣ ግብረሰናይ ድርጅቶችና መላው ህብረተሰብ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል። የቀቤና ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት በበኩሉ ወቅቱ ነፋሻማ በመሆኑ የወረዳው ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ገልጿል። ጉዳቱ የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ሁሉም ርብርብ ማድረግ እንደሚገባውም ፅህፈት ቤቱ መልእክቱን አስተላልፏል።
https://t.me/ethiopian_reporter

👍5😢1
በጥቆማ የተያዘ 46 ሺሕ ሊትር ዘይት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል ነው
መጋቢት 21/2014 (ሪፖርተር) በኅብረተሰቡ ጥቆማ በህገወጥ መንገድ በመኪና ተጭኖ የተያዘ ከ46 ሺሕ ሊትር በላይ ዘይት በመሰረታዊ ሸማች አማካኝነት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል መሆኑ ተገለፀ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር በመኪና ጥበቃ ላይ በተሰማሩ ነዋሪዎች ጥቆማ ከ2 ሺሕ 300 ካርቶን በላይ ዘይት ጭኖ የነበረ መኪና በኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል ተወርሶ በወረዳው መሰረታዊ ሸማች ማኅበር አማካኝነት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል መወሰኑን ወረዳው አስታውቋል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ትዝታ ነጋሽ ኅብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ተግባራትን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች:-

👍4❤1
የአማራ ክልል መንግሥት በወረራ የተያዙ ወረዳዎችን በተደራጀ ጥምር ጦር ማስለቀቅ እንደሚገባ አሳሰበ
የአማራ ክልል መንግሥት የሕወሓት ኃይሎች ‹‹ለዳግም ወረራ›› ይመጣሉ የሚል ሥጋት በመኖሩ ‹‹ጦርነቱ ተጠናቋል›› የሚል ሐሳብ እንደሌለውና በሕወሓት የተያዙ የክልሉ ወረዳዎችንም የተደራጀ ጦር በማሰለፍ ነፃ ማውጣት እንደሚገባ አሳሰበ፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ሕወሓት በያዛቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ለርሃብና ለሕክምና ዕጦት መዳረጋቸውን ለሕዝቡ ሲባል ሕወሓት በክልሉ ላይ የፈጸመው ‹‹ወረራ›› በፍጥነት ምላሽ ማግኘት አለበት የሚለውን ሐሳብ እንደሚጋሩ ተናግረዋል፡፡
መጋቢት 15 እና 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በተካሄደው የክልሉ ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር፣ አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔው ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት ይልቃል (ዶ/ር) በርካታ ወረዳዎች አሁንም በሕወሓት ቁጥጥር ሥር መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ዝቋላ፣ ፃግብጂ፣ አበርገሌ፣ አድርቃይና ጠለምት አከባቢዎች አሁንም ነፃ እንዳልወጡ በፕሬዚዳንቱ ከተጠቀሱ አከባቢዎች መካከል ናቸው፡፡

👍10🔥1
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ (ኢብባ) ለሲንቄ ባንክ የፕሬዝደንት ሹመት በልዩ ሁኔታ በሚል የሰጠው ይሁንታ ጥያቄ አስነሳ፡፡
ሲንቄ ባንክ በበኩሉ ኢብባ በልዩ ሁኔታ ብሎ መፍቀዱ ለምን እንደሆነ ግራ እንዳጋባው ጠቅሶ ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑን የጠየቀው በህጉ መሰረት ይሁንታ እንዲሰጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከሰሞኑ ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ ለሲንቄ ባንክ የፕሬዝደንትነት ሹመት ከባንኩ ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው የይሁንታ ምላሽ ደብዳቤ እንደጠቀሰው የአቶ ንዋይ መገርሳን ሹመት በልዩ ሁኔታ መፍቀዱን አስታውቋል፡፡
ይህ የኢብባ ውሳኔ በዘርፉ ያሉትን ባለሞያዎች ግራ ያጋባ ሆኖም ተስተውሏል፡፡“ተቆጣጣሪ ሁሉንም በሚያስተናግደው የህግ መሰረት መስራት ሲገባው ለምን በልዩ ሁኔታ ሲል መፍቀድ ፈለገ፡፡ ሁለት አይነት አሰራር ነው የታየው፤ ከጠንካራ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የማይጠበቅ ነው፣፣” ሲሉም ውሳኔውን ተችተዋል፡፡
ከኢብባ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ ሆኖም የሲንቄ ባንክ ፕሬዝደንት አቶ ንዋይ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።በምላሻቸውም የብሄራዊ ባንክ ደብዳቤ ግራ እንዳጋባቸው ገልፀው ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ የተጠየቀው በህጉ መሰረት ይሁንታ እንዲሰጥ ወይም እንዲከለክል ነው ለምን በልዩ ሁኔታ ፈቅጃለሁ እንዳለ እኔም ግራ ገብቶኛል ብለዋል፡፡በማከልም በኢብባ መመሪያ መሰረት በፕሬዝደንትነት ለመስራት የሚያበቃ በቂ የስራ ልምድ አለኝ በማለት አክለዋል፡፡
[Capital]

👍4
#EthioTelecom
ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች ልዩ ጥቅል ማቅረቡን ገለፀ።
ኢትዮ ቴሌኮም ለኮሌጅ እና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ የሆነ የተማሪ ጥቅል ማቅረቡን አሳውቋል።
በዚህም :
ወርሃዊ ፦
• ዋጋ 👉 34 ብር ፤ ጥቅል 👉 180 ደቂቃ (ጥሪ) ፤ ስጦታ 90 ደቂቃ (ጥሪ) + 100 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 64 ብር ፤ ጥቅል 👉 360 ደቂቃ (ጥሪ) ፤ ስጦታ 200 ደቂቃ (ጥሪ) + 150 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 42 ብር ፤ ጥቅል 👉 1 GB (ዳታ) ፤ ስጦታ 512 MB (ዳታ) + 100 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 82 ብር ፤ ጥቅል 👉 2 GB (ዳታ) ፤ ስጦታ 1.1 GB (ዳታ) + 150 መልዕክት ፤
ሳምንታዊ ፦
• ዋጋ 👉29 ብር ፤ 3 GB (ዳታ) መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ሳምንታዊው የዳታ ጥቅል እና ለደንበኞች የቀረቡት ስጦታዎች የሚያገለግሉት ከለሊቱ 6 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት መሆኑን አሳውቋል።
ተማሪዎች ተማሪነታቸውን የሚገልፅ " መታወቂያ " በመያዝ በኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከሎች በመቅረብ ጥቅሎቹን መግዛት ይችላሉ ተብሏል።

👍7👏2😱2🔥1
#AddisAbaba🪧
በአዲስ አበባ ከተማ ህገወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች እየተነሱ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02፣ 08፣ 10 እና 13 በህገ ወጥ መንገድ መሰረተ ልማት አውታሮች እና የዋና መንገድ ኤልክትሪክ ፖሎች ላይ የተሰቀሉ ህገ ወጥ የውጭ ማስታውቂያ ማንሳቱን አስታውቋል።
ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያዎች የተነሱባቸው ቦታዎች ፦
👉 ከሳህሊተ ምህረት እስከ የተባበሩት ግራ እና ቀኝ ፣
👉 ከተባበሩት እስከ ፍየል ቤት ፤
👉 ከፍየል ቤት እስክ ፊጋ
👉 ከተባበሩት እስከ አያት አደባባይ
👉 ከአያት አደባባይ እስከ ጣፎ አደባባይ ድረስ በግራና በቀኝ በኩል ተሰቅለው የነበሩ ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን አሳውቋል።
በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ከተሞች የተሰቀሉ ህገወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች የማንሳት ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
መረጃው የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ነው።

👍3🔥3
ከ100 በላይ ቤቶች በ12 ቀናት ውስጥ መቃጠላቸው ተገለጸ!
ከመጋቢት አንድ እስከ 12/2014 ባሉት ቀናት ውስጥ በምሥራቅ ወለጋ ሊሙ ወረዳ ሥር የሚገኙ ከ100 በላይ ቤቶች በታጣቂዎች መቃጠላቸውን አስተማማኝ ምንጮች ተናግረዋል።
ሥሜ እንይጠቀስ ያሉ የመረጃ ምንጫችን ከመጋቢት አንድ እስከ 12/2014 ባሉት ቀናት ብቻ ከ100 በላይ የሚሆኑ ቤቶች በታጣቂዎች ተቃጥለዋል ሲሉ ነው ገለጹት።
አስከትለውም፣ “የነዋሪዎቹን ቤት የሚያቃጥሉት ጁንታና ሸኔ ናቸው” ብለዋል። የሕወሓት አባሎች በአካባቢው ይኖሩ እንደነበር የገለጹት የመረጃ ምንጩ “መታወቂያቸው እየተቀየረላቸው ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው” ሲሉም ጠቁመዋል።
የሕወሓት ታጣቂዎችም ከሊሙ ወረዳ ወጣ ብለው ክልል ስድስት ድንበር ላይ በዴሳ እና መንደር ስምንት በሚባለው አካባቢ እንደሚገኙም ነው ግለሰቡ ያመላከቱት።

👍6👎1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
#መረጃ! #ምንጃር! ሽብርተኛዉ ኦነግ ሸኔ ምንጃር አውራጎዳና ገባ ግን አልወጣም ተባለ። የሽብር ቡድኑ ሁለት ፌደራል ፖሊስ እና አንድ የአካባቢው ንፁሀን ሰዉ ገድሏል። በተጨማሪም በመሀል ከተማ ውስጥ ስድስት ሰው እንዳቆሰሉ ተገልጿል በስልጠና የዳበረ የምንጃር አውራጎዳና ነዋሪ የሽብር ቡድኑ እንደመግባት ቀላል ሳይሆንለት አስቀርቶታል። https://t.me/ethiopian_reporter https:/…
#update
#MinjarShenkora📍
በምንጃር ሸንኮራ በተፈፀመ ጥቃት የሰው ህይወት አለፈ።
በወረዳው " አሞራ ቤት ቀበሌ " ላይ ታጣቂዎች ፈፀሙት በተባለው ጥቃት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ጥቃቱ ከኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ " አዉራ ጎዳና መንደር ትናንት ከሰዓት የተፈፀመ ሲሆን የሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ከሚል መረጃ ውጭ ምን ያህል የሚለው አልታወቀም።
ወረዳው ጥቃቱን ያደረሱ ታጣቂዎች ምናልባት ማንነታቸው ያልታወቁ " የፀረ ሰላም ኃይሎች " ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል።
የምንጃር ሸብኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ቦሰት ጥቃቱን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ፦
" ትላንትና መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ከኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ ልዩ ቦታዉ አዉራ ጎዳና ተብሎ በሚጠራ መንደር ላይ ታጣቂዎች በተደራጀ እንዱሁም በቡድንና በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ባደረሱት ጥቃት የሰዉ ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል " ብለዋል፡፡
በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸዉ ግለሰቦች በአረርቲ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና ወደ አዲስ አበባ ከተማ ተልከዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
" አካባቢዉ ለዓመታት የተለያዩ ትንኮሳዎች ይስተዋልበት ነበር ያሉት " አቶ ታደሰ ፤ " የትናንቱ ግጭት ግን መነሻዉ በግልፅ የማይታወቅ ፤ ምናልባትም ማንነታቸዉ በግልፅ ያልታወቁ ፀረ ሰላም ኃይሎች አቅደዉበት እና አካባቢዉን በማዉደም ነዋሪዎችን ለማፈናቀል አልመዉ የመጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል " ብለዋል፡፡
አቶ ታደሰ ቦሰት " ለጊዜዉ ማንነታቸዉ ያልታወቁ ታጣቂዎቹ ጥቃት ማድረሳቸዉን ተከትሎ ንፁሀን እንዳይጎዱ በተለይ ሴቶችን ህፃናትንና ነፍሰጡሮቹን ከስፍራዉ የማዉጣት ስራ ተሰርቷል " ያሉ ሲሆን " ቤት ንብረታቸዉን ትተዉ ወደ ጫካ የሸሹ በመኖራቸዉና ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ የስልክ ግንኙነት ባለመኖሩ ተጨማሪ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ማወቅ እንዳልተቻለ ገልፀዋል።
" ትናንትና አመሻሽ ከ12፡00 በኋላ በአካባቢዉ የፌደራል ፖሊስ በመግባቱና የማረጋጋት ስራ በመሰራቱ አሁን ጥቃቱ በቁጥጥር ስሮ ዉሏል " ብለዋል።
" የአካባቢዉን ሰላም ለማናጋት ከሁሉም ወገን የፀረ ሰላም ኃይሎች ሊኖሩ ይችላሉ " ያሉት አቶ ታደሰ ፤ " በማጥራት እና የጋራ ምክክር በማድረግ የአካባቢዉን ሰላም በዘላቂነት ለማስፈን በቀጣይ በትኩረት ሊሰራ የሚገባ ጉዳይ ነዉ " ብለዋል።
ወረዳው በትላንትናው ጥቃት አድራሾቹ " የማይታወቁ ፤ ፀረ ሰላም ኃይሎች " እያለ መጥራቱ ቅሬታ ያሳደረባቸው አካላት እንዲህ ያለው መሸፋፈን ይበልጥ ችግሩን ከማወሳሰብ በዘለለ ምንም አይነት ፋይዳ እንደሌለው አስገንዘበዋል።
ከዚህ በፊት በተለያዩ የሀገሪቱ ቦታዎች ለሚፈፀሙ ጥቃቶች " ማንነታቸው ያልተረጋገጠ፣ ፀረ ሰላም ኃይሎች " የሚሉ ቃላትን መጠቀም የተለመደ ነው።

😢7👍4🥰1
በእስራኤል ውስጥ አንድ ያልታወቀ ግለሰብ መትረየስ መሳሪን በመጠቀም ሰላማዊ ዜጎች ላይ ተኩስ ከፈተ ።
በከፈተው ተኩስ ቢያንስ 5 ሰዎች መሞታቸውን ተዘግበዋል ። ተኩስ የከፈተው ግለሰብም እዛው እርምጃ እንደተወሰደበት ከቦታው ያገኝነው መረጃ ያሳያል።

👍6👏3