በአዲስ አበባ በ2014 የሙያ ብቃት ምዘና ከወሰዱ መምራን መካከል 1,600ዎቹ ማለፋቸው ተነገረ፡፡
ምዘናው ሁለት ዓይነት እንደሆነ የከተማዋ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዛሬ ባዘጋጀው መርኃ ግብር ላይ ሲነገር ተሰምቷል።የመጀመሪያው የጽሑፍ ምዘና ሲሆን ይህን ምዘና 1,835 መምህራን በዚህ ዓመት ወስደዋል ተብሏል።
የጽሑፍ ፈተናውን ከወሰዱ 1,835 መምህራን መካከል 1,600ዎቹ ለማህደረ ተግባር ፈተና መቅረባቸው ተጠቅሷል።እነዚህ በሙሉ የማህደረ ተግባር ፈተናውን አልፈው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርተፊኬት ማግኘታቸው ተነግሯል።የማህደረ ተግባር ምዘና የመምህሩን አጠቃላይ የተግባር እንቅስቃሴ የሚያሳይ ስርዓት እንደሆነ ተሰምቷል።
[Sheger FM]
https://t.me/ethiopian_reporter

👍4👏1
ቢሊየነሩ አብራሞቪች በኢስታንቡል የሰላም ንግግር ላይ ተገኝተዋል
ሮማን አብራሞቪች ተመርዘዋል የሚለዉ መረጃ ዉድቅ አድርጓል
ሩሲያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች በቱርክ አሸማጋይነት በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በተደረገው የሰላም ድርድር ላይ ታይተዋል።በኢስታንቡል በተደረገው ውይይት ላይ ሽምግልና ላይ ከሚገኙት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር ሲነጋገሩ ታይተዋል።
አብራሞቪች እና ሁለት የዩክሬን ተደራዳሪዎች በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ካካሄዱት ድርድር በኋላ የመመረዝ ምልክት ታይቆባቸዋል የሚል ሪፖርት ከወጣ ከሰዓታት በኋላ ነው የቢሊየነሩ ምስል ይፋ ተደርጓል፡፡ አብራሞቪች በሞስኮ እና በኪየቭ መካከል በሽምግልና ሚና ላይ ሳምንታት እንዳሳለፉ ይታወቃል።
የቼልሲው የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት የዓይን እና የቆዳ ህመም አጋጥሟቸው ነበር ቢባልም አሁን ግን አገግመዋል የሚል መረጃ ይፋ ሆኗል፡፡በዎል ስትሪት ጆርናል ዘገባ መሰረት ሮማን አብራሞቪች እና የዩክሬን ተደራዳሪዎች በሩሲያ አማካይነት ተመርዘዋል ቢልም የዩክሬን ፕሬዝዳንት ባለስልጣን ግን ሁለቱ ዩክሬናውያን ደህና እንደሆኑ እና መረጃዉ የውሸት ነው ብሏል።
ሆኖም ግን የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከውይይቱ ከሰዓታት በፊት በብሔራዊ ቲቪ እንደተናገሩት ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ የሚገኙ ባልደረቦቻቸው ምንም ነገር እንዳይበሉ እና እንዳይጠጡ መክረዋል።የኢስታንቡል ውይይት ማክሰኞ እለት በንግግር የከፈቱት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የተኩስ ማቆም እና የሰላም ጥሪ በማቅረብ "ግጭቱን ማራዘም ለማንም አይጠቅምም" ሲሉ ለሁለቱ ልዑካን ቡድን በዶልማባቼ ቤተ መንግስት ተናግረዋል፡፡
[Reporter ]

👍8🔥1🥰1
መርሳ ፋኖዎቿን አስመረቀች!
የመርሳ ከተማ ባለሽርጡ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ሰራዊት ወታደራዊ ስልጠናቸውን አጠናው ዛሬ ተመረቁ!
በአማራ ህዝብ አሰቃቂ ውድመት ያደረሰው የትግራይ ወራሪ ኃይል ያንገፈገፋቸው የመርሳ ባለሽርጥ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ሰራዊት ከሁለትወር በላይ ሲያካሂዱ የቆዩት ስልጠና አጠናቀው በመርሳ ሁለገብ ስታድየም በደማቅ ዝግጅት ዛሬ ተመረቁ፡፡

👍6🔥4👏1😁1
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ መጠን ይፋ አደረገ❗️
🔰የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ መጠን ይፋ አደረገ፡፡
🔰ቦርዱ ዛሬ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ያካሄደ ሲሆን÷ ለፓርቲዎች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ መጠንን ይፋ አድርጓል።
🔰የገንዘብ ድጋፉ ከዚህ ቀደም በፀደቀው መመሪያ ላይ በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት የተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
🔰ለ19 አገር አቀፍ እና 35 የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በድምሩ ለ54 ፓርቲዎች እስከ 789 ሺህ ብር የሚደርስ ድጋፍ እንደሚደረግ ከምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

👍2🔥1
ፍርድ ቤት ዛሬ የአሶሴትድ ፕሬስ ዘጋቢዎች አሚር አማን እና ቶማስ እንግዳ እያንዳንዳቸው በ60 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል።
ሆኖም ችሎቱ ዘጋቢዎቹ ከአገር እንዳይወጡ እገዳ ጥሎባቸዋል። ፖሊስ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት ቢጠይቅም፣ ችሎቱ ግን የእስካሁኑ ምርመራ ለውጥ አላሳየም በማለት ነው የገንዘብ ዋስትናውን የፈቀደው። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ባለፈው ኅዳር ያሰራቸው፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮችን እና ታጣቂዎችን መስክ ወርደው በማነጋገር እና በተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረጽ ወደ ውጭ አገር መረጃዎችን ልከዋል በማለት ነበር።

👍6
❗️ፊንላንድ ኮሌጅ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሰው ተቋም ምንም አይነት የእውቅና ፈቃድ የለውም ተባለ
ፊንላንድ ኮሌጅ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሰው ተቋም ምንም አይነት የእውቅና ፈቃድ እንደሌለው የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ።
ፊንላንድ ኮሌጅ በሚል ስያሜ የእውቅና ፈቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ ያቀረበው ተቋሙ፣ ከባለሥልጣኑ የዕውቅና ፈቃድ ሳያገኝ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በአረካ ከተማና በሌሎች የክልሉ ከተሞች በርካታ ተማሪዎችን መዝግቦ እያስተማረ መሆኑ በተደረገው ማጣራት መረጋገጡን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገረሱ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
ባለሥልጣኑ በፊንላንድ ኮሌጅ በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ የሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ ተቀባይነት የሌለውና ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማስከበር እርምጃ በመውሰድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስቧል፡፡

የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚመለስ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የራያ ሕዝብ ተወካዮች ላቀረቡት ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የራያ ሕዝብ ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የራያ ሕዝብ ተወካዮች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የራያ ሕዝብ የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ያቀረቡ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ ምላሽ ሳያገኝ እንደቆየ አውስተዋል፡፡
ተወካዮቹ አያይዘውም የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ሞትን ጨምሮ ሌሎች በደሎች በራያ ሕዝብ ላይ ሲፈፀም የቆየ እንደነበረና በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ራያዎች ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ እና ንብረታቸውም ሲወድም እንደነበረ ተወካዮቹ በአካል ቀርበው አስረድተዋል፡፡
ጥያቄአችን ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ሲሉም ተወካዮቹ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሸገር በበኩላቸው ጥያቄውን ላቀረቡት የራያ የማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የራያ ሕዝብ ጥያቄው በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደ ከዚህ በፊቱ የሕዝብን ጥያቄ በኃይል ለማፈን የሚደረግ አላስፈላጊ ጫና ከሕገ መንግስቱ የሚቃረን ስለሆነ ተቀባይነት እንደሌለው የጠቆሙት አፈ ጉባዔው የሕዝብ ጥያቄ ሕግን መሠረት በማድረግ ምላሽ በመስጠት ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

👍24
ኢትዮጵያን የሚመለከተው ኤስ3199 ረቂቅ ሕግ ተቀባይነት አግኝቶ ወደ አሜሪካ ሴኔት ተመራ!!
የአሜሪካ ሴኔት በኮሚቴ በኢትዮጵያ ሰላም እና ዲሞክራሲ ለማበረታታት በሚል የቀረበውን ረቂቅ ሕግ ተቀብሎ ወደ ሴኔቱ እንዲያልፍ አደረገ።
ይህ ኤስ3199 የተባለው በኢትዮጵያ ሰላም እና ዲሞክራሲ ማበረታታት ወይም The Ethiopia Peace and Democracy Promotion Act በሚል የቀረበው ረቂቅ ሕግ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እንዲሁም በጦርነት ተሳታፊ ናቸው በተባሉ ግለሰቦች ላይ ጠንከር ያለ ማዕቀብ ለመጣል የተዘጋጀ ነው።
የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ትናንት ማክሰኞ ምሽት መጋቢት 20/2014 ዓ.ም. ባደረገው ውይይት ረቂቅ ሕጉን ተቀብሎ ወደ ሴኔቱ እንዲቀርብ ወስኗል።
ይህን ረቂቅ ሕግ ለሴኔቱ ያስተዋወቁት የኒው ጀርሲው ሴናተር ሮበርት ሜንዴዝ ናቸው። ኤስ 3199 ረቂቅ ሕግ ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም. ለሴኔቱ ቀርቦ ለሴኔቱ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ተመርቶ ነው ውይይት ተደርጎበት ወደ ቀጣዩ ሂደት እንዲያልፍ የተደረገው።
ይህ ረቂቅ ሕግ ከዚህ በኋላ ለሙሉው ሴኔት ቀርቦ ሌላ ዙር ውይይት የሚደረግበት ሲሆን ሴኔቱ የሚያጸድቀው ከሆነ ለሕዝብ ተወካዮች ይቀርባል፣ የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቀብሎት ካለፈ በቀጠይነት ለፕሬዝዳንቱ ቀርቦ ፊርማቸውን ካኖሩበት ሕግ ሆኖ ተግባራዊ ይሆናል።
በተመሳሳይ ሌላ ኢትዮጵያ እና ኤርትራን የተመለከተ ረቂቅ ሕግ በአሜሪካ ምክር ቤት መተዋወቁ ይታወሳል።
ይህ ረቂቅ ሕግ ኤችአር 6600 የሚባል ሲሆን በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ከግጭት ጋር ተያይዞ ለደረሱ በደሎች ተጠያቂ ናቸው በተባሉ ግለሶች ላይ ማዕቀብ መጣል ያስችላል።
የኢትዮጵያ መንግሥት አጥብቆ የተቃወማቸው እነዚህ ረቂቅ ሕጎች በፕሬዝዳንት ባይደን የሚጸድቁ ከሆነ አሜሪካ በደኅንነት፣ በፋይናንስ/በኢንቨስትመንት እና በኢሚግሬሽን ጉዳዮች ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ትጥላለች።
ኤችአር 6600 ረቂቅ ሕግ በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 01/2014 ዓ.ም. ቀርቦ የነበረ ሲሆን፤ ረቂቅ ሕጉ ለምክር ቤቱ የውጭ ጉዳዮች፣ ፍትሕ፣ የፋይናንስ አገልግሎቶች እና ለጦር ኃይል አገልግሎቶች ተመርቷል።
ኤስ 3199 ረቂቅ ሕግ ይዘት ምንድነው?⁉️
በዚህ ረቂቅ ሕግ ላይ አሜሪካ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ግንባታ እና የሰብዓዊ መብት መከበርን እንደምትደግፍ ተመልክቷል። ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ለተከሰተ ግጭት መፍትሄ እና እርቅ ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፏን እንደምታደርግ ረቂቅ ሕጉ ያትታል።
ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የሚደረጉ የሰላም፣ የመረጋጋት እና የዲሞክራሲ ግንባታ ጥረቶችን በሚያደናቅፉ ግለሰቦች ላይ የንብረት እና የጉዞ እግድ ይተላለፍባቸዋል ይላል።
ይህ ረቂቅ ሕግ ሆኖ ከወጣ አሜሪካ ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ የጦር መሳሪያ አትልክም። በአሜሪካው "Better Utilization of Investments Leading to Development Act of 2018" መሠረት ዋሽንግተን በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ ፕሮጀክቶች ድጋፍ አታደርግም።
እንደ ኤችአር 6600 ሁሉ ኤስ3199 ረቂቅ ሕግ አሜሪካ ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ የምታደርገው የደኅንነት እና የፀጥታ ድጋፍ እንዲቋረጥ ይጠይቃል።
ከዚህ በተጨማሪም ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሚሰጡ ብድሮች ወይም የብድር ማራዘሚያዎች እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፎች እንዳይፈቀዱ አሜሪካ ተሰሚነቷን እና ድምጽ የመስጠት መብቷን ትጠቀማለች ይላል ረቂቅ ሕጉ።
እነዚህ ረቂቅ ሕጎች ኢትዮጵያውያንን የሚጎዱ እና ጦርነቱን ለማብቃት የሚደረጉትን የሰላም ጥረቶች የሚያደናቅፉ ከመሆናቸው በተጨማሪ በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ሙከራዎች ናቸው በማለት የኢትዮጵያ መንግሥት አጥብቆ ተቃውሟቸዋል።
እንዲሁም በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕጎቹ እንዳይጸድቁ ጥረትና የተቃውሞ ሰልፎች እያደረጉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የሕጎቹን መጽደቅ የሚደግፉ ኢትዮጵያውያንም ግፊት እያደረጉ ይገኛሉ።

👍6🥰1
#መረጃ! #ምንጃር!
ሽብርተኛዉ ኦነግ ሸኔ ምንጃር አውራጎዳና ገባ ግን አልወጣም ተባለ። የሽብር ቡድኑ ሁለት ፌደራል ፖሊስ እና አንድ የአካባቢው ንፁሀን ሰዉ ገድሏል።
በተጨማሪም በመሀል ከተማ ውስጥ ስድስት ሰው እንዳቆሰሉ ተገልጿል በስልጠና የዳበረ የምንጃር አውራጎዳና ነዋሪ የሽብር ቡድኑ እንደመግባት ቀላል ሳይሆንለት አስቀርቶታል።

👍8
በሳውዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ 498 ዜጎች ወደ አገር ቤት ተመለሱ!
በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለስ ጀምረዋል።
በዚሁ መሰረት በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው ዙር 498 ዜጎች ወደ አገር ቤት የተመለሱ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች በረራዎች ይኖራሉ ተብሏል።
https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለስ ጀምረዋል።
በዚሁ መሰረት በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው ዙር 498 ዜጎች ወደ አገር ቤት የተመለሱ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች በረራዎች ይኖራሉ ተብሏል።
https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
🥰2👍1
በጉራጌ ዞን በደረሰ የእሳት አደጋ 42 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለፀ!!
በቀቤና ወረዳ በሌንጫ ቀበሌ ልዩ ስሙ ፈረጀቴ ጎጥ ትናንት እኩለ ቀን ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ 35 የሳር ክዳን ቤቶች፣ 5 የቆርቆሮ ክዳን ቤቶችና 2 መስጂዶች በድምሩ 42 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ነው የተገለፀው።
2ቱ መስጂዶች በከፊል የወደሙ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በምርትና በሰብል ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱም ተጠቁሟል። በጥንቃቄ ጉድለት በአካባቢው የነበረውን ቁጥቋጦ ለማጥፋት በሚል የተለኮሰ እሳት በወቅቱ በነበረ ከፍተኛ ንፋስ ወደ አካባቢው በመዛመቱ ነው የእሳት አደጋው የደረሰው።
በእሳት አደጋው በቤትና ንብረት ላይ ከደረሰው ውድመት በተጨማሪም በእንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል። በእሳት አደጋው ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት በደረሰው አደጋ ለከፍተኛ ችግር በመጋለጥ ሜዳ ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።
በመሆኑም በጊዜያዊነትና በቋሚነት ለማቋቋም የወረዳውና የዞኑ አስተዳደር፣ የአካባቢው ተወላጅ ባለሃብቶች፣ ግብረሰናይ ድርጅቶችና መላው ህብረተሰብ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል። የቀቤና ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት በበኩሉ ወቅቱ ነፋሻማ በመሆኑ የወረዳው ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ገልጿል። ጉዳቱ የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ሁሉም ርብርብ ማድረግ እንደሚገባውም ፅህፈት ቤቱ መልእክቱን አስተላልፏል።

👍5😢1
በጥቆማ የተያዘ 46 ሺሕ ሊትር ዘይት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል ነው
መጋቢት 21/2014 (ሪፖርተር) በኅብረተሰቡ ጥቆማ በህገወጥ መንገድ በመኪና ተጭኖ የተያዘ ከ46 ሺሕ ሊትር በላይ ዘይት በመሰረታዊ ሸማች አማካኝነት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል መሆኑ ተገለፀ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር በመኪና ጥበቃ ላይ በተሰማሩ ነዋሪዎች ጥቆማ ከ2 ሺሕ 300 ካርቶን በላይ ዘይት ጭኖ የነበረ መኪና በኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል ተወርሶ በወረዳው መሰረታዊ ሸማች ማኅበር አማካኝነት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል መወሰኑን ወረዳው አስታውቋል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ትዝታ ነጋሽ ኅብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ተግባራትን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች:-

👍4❤1