#መረጃ #ትኩረት
ለሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ማስፋፊያ ቤታቸው እንዲፈርስ የተደረጉ ሁለት ሰዎች ሞተዋል።
# ለ2 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል የሚባለው የሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ጉዳይ የነዋሪዎችን ብሶት አባብሷል!
# በከፍተኛ ጥንቃቄ የተቀረፀ ቪዲዮ ይለቀቃል!
/
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘደንት የሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ሳቢያ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ነዋሪ በምሬት ገለፀ፡፡ የባልደራስ አመራር አባላት በአካባቢው ሰሞኑን ባደረገው የመስክ ጉብኝት፣ በርካታ ሰዎች ተሰባስበው ያለውን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡
በአካባቢው ቀረፃ ስለማይቻል ሰወር ባለ ቦታ ላይ የተገናኙት የአመራር አባላቱና የአካባቢው ነዋሪዎች ያደረጉት ቆይታ በከፍተኛ ጥንቃቄ በቪዲዮ ተቀርጾ በጥንቃቄ ከአካባቢው እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
በሶስት ቀን ውስጥ ቤታቸውን እንዲለቁ የታዘዙት ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፣ “በድንገት እየመጡ ውጡ ሲሉን ከመካከላችን ሁለት ሰዎች ሞተዋል ” ብለዋል፡፡ ከመካከላቸውም የሐዘን ልብስ የለበሰች እንስት ያለውን ሁኔታ ተናግራ በቪዲዮ ተቀርፃለች፡፡
በነዋሪዎቹ አስተያየት፣ አሁን ለቢሮ ማስፋፊያ የተፈለገው ቦታ በጣም ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ለተባላለት ዓላማ ብቻ የተፈለገ ነው ለማለት እንደሚቸገሩ ተናግርዋል፡፡ “ ይህ ሁሉ መሬት ለአንድ ቢሮ ብቻ ያስፈልጋል ለማለት ያስቸግራል፡፡ ለምን እንደሆነ ባናውቅም፣ ይዞታቸውን ነው ማስፋፋት የፈለጉት፡፡ በዚህ ሂደት እኛ ደሀዎቹ እየተጨፈለቅን ነው ” ብለዋል፡፡
ስንታየሁ ቸኮል
https://t.me/ethiopian_reporter

👍10🤯5
#Update
የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ ወደ' ትግራይ ክልል' እንዲገባ የህወሓት ታጣቂዎች የያዟቸውን የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ሊወጡ ይገባል ሲል አስገነዘበ።
መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል መንግስት ግጭት የማቆም ውሳኔ ማሳለፉ ከትግራይ ክልል በኩልም በጎ ምላሽ መሰጠቱ ይታወሳል።
ነገር ግን ውሳኔ ከተላላለፈበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ምንም አይነት ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል ሊገባ እንዳልቻለ የክልሉ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።
ክልሉን ወክለው ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወት ፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ወደግጭት ማቆም እንዲደረስ ብዙ ጥረት አድርጓል፤ የባለፈው ሳምንት ስምምነት ዝም ብሎ የመጣ ስምምነት አይደለም ብዙ ጊዜ የተሰራበት ስምምነት ነው ብለዋል።
የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ክልሉ ለምን እንዳልገባ የተጠየቁት ፕ/ር ክንደያ ፤ ኃይላቸው በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች የእርዳታ መኪናዎች ስላልደረሱ ማወቅ እንዳልቻሉ ፤ ለምን እንዳልተላኩ መላክና ማሳለፍ የሚገባቸው አካላት ማብራሪ ሊሰጡ ይገባል ብለዋል።
ከባለፈው ሃምሌ ወር በየዕለቱ 100 የሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንደነበረባቸው የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ይገልፃሉ አሁን ያለው ችግር ሲታይ ፍላጎቱ ጨምሯል ሲሉ አስረድተዋል።
አሁን ያለው ግጭት ለማቆም እና ሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ የሚለው ውሳኔ ካልተሳካ ለረጅም ጊዜ ተዘጋግቶ መጠበቅ ስለማይቻል ሌላ አማራጭ እናያለን ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጠው ቃል ፤ እርዳታ ወደክልሉ እንዲገባ የህወሓት ኃይሎች ከያዟቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ሊወጡ ይገባል ብሏል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፤
" ... እነሱ ግጭት እናቆማለን ብለው አልነበር እንዴ ? ቀደም ብሎ መንግስት የትኛውም አይነት ትንኮሳ እንደማይፈፅም እና የትኛውም አይነት ግጭት ውስጥ እንደማይገባ አስቀምጧል።
በአንፃሩ እነሱ እርዳታው በቀላሉ ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርስ በጉልበት ከያዟቸው የአፋር ክልል ወረዳዎች መውጣት አለባቸው ብሎ አስቀምጧል። እስከዛሬ ድረስ ከ5 ወይም 6 ወረዳዎች አልወጡም።
እንደውም ትላንትና 'ኮኖባ' በሚባል ቦታ ከአፋር ሚሊሻ ጋር ጦርነት ነበር።
ለህዝቡ ካሰቡ ከያዙት ቦታ መውጣት እና መንገዱን ክፍት ማድረግ አለባቸው። ይሄን ሳያደርጉ መንግስት ሆን ብሎ ነው የሚለው ትክክል አይደለም "
👉 መጋሌ ፣
👉 ኤሬብቲ ፣
👉 በርሃሌ፣
👉 አብዓላ የተባሉ የአፋር ቦታዎችን የ " ህወሓት ኃይሎች " ተቆጣጥረው እንደሚገኙ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
" ... ይሄ በዋናነት እርዳታው የሚሄድበት የአስፓልት መንገድ ላይ ነው ያለው። ይሄንን መልቀቅ አለባቸው ይሄንን ሳይለቁ ' መንግስት እርዳታ አላቀረበም ' ብለው ቅሬታ ማቅረብ ሚችሉበት ምንም አይነት ሁኔታ የለም። ስለዚህ እርዳታው ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርስ ለህብረተሰቡ የሚያስቡ ከሆነ በጉልበት ከያዟቸው አካባቢዎች መልቀቅ ነው ያለባቸው፤ አካባቢውን ከግጭት ነፃ ነው ማድረግ ያለባቸው ። " ሲሉ ዶ/ር ለገሰ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ፤ እርዳታ ለማድረስ ያለውን ዝግጅቱነት በመተመለከተ 3 የነዳጅ እና 20 የእርዳታ እህል የጫኑ 23 መኪናዎች ቆመዋል (ከዚህ በፊት ሄደው በፀጥታ ችግር የተመለሱ) ፤ በተጨማሪ ሰመራ ላይ ከመጋዘን ለመጫን የሚጠባበቁ ትልልቅ ተሽከርካሪዎችም አሉ በአጠቃላይ 43 ተሽከርካሪዎች ናቸው መንገዱ ካልተከፈተ እና ግጭት ካልቆመ እርዳታ ሊሄድ አይችልም ብለዋል።
መንግስት የወሰነው ለሰብዓዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ እስከመቼ እንደሚቆየ የተጠየቁት ሚኒስትሩ ፤ " በመንግስት በኩል የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የለም። ህብረተሰቡ ወደ ተለመደው ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመጣ ነው መንግስት የሚፈልገው ፤ አካባቢውም ተረጋግቶ መጪውም ክረምት ስለሆነ እርሻውን እንዲያርስ መንግስት የሚፈልገው ከዛ ውጭ የሚደረግ ነገር ካለ እሱን በሂደት ይታያል። " ብለዋል።

👍9
አስቸኳይ ትኩረት ለዳንጉር በላያ እና ዙርያ!
በመተከል ዞን በዳንጉር ወረዳ በለያ ዙርያ ልዩ ስሙ አውጃቢስ ከፍተኛ የርስ በርስ ግጭት ተከስቶ በሰው እና ንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ያነጋገርናቸው የአካባቢው የአይን እማኞች ገልፀዋል። ይህ ግጭት ቀስበቀስ የብሔር ቅርፅ እየያዘ በመሆኑ በአስቸኳይ ካልቆመ አድማሱን አስፍቶ አላስፈላጊ ዋጋ እንዳያስከፍል መስጋታቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ የክልልና ፌዴራል መንግስት ሊደርስልን ይገባል ብለዋል።

👍2🔥2
በሀገር ውስጥ የዲ ኤን ኤ ምርመራ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ!
ከዚህ ቀደም ወደ ዉጭ ሀገር በመላክ ይሰጥ የነበረዉን አገልግሎት በሀገር ዉስጥ ለመስጠት ያስችላል የተባለለት ለወንጀል ምርመራ የሚያግዝ የዘረ-መል (ዲ ኤን ኤ) ምርመራ በሀገር ዉስጥ ለመጀመር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።አገልግሎቱ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ስለሚጀምረዉ ቴክኖሎጂው አተገባበር እና ስለሙከራው ውጤታማነት በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ለህዝብ መረጃ እንደሚሰጥ የፌደራል ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄላን ኢብራሂም ተናግረዋል።
ለወንጀል ምርመራ ስራ የሚያግዙ አዳዲስ የፎረንሲክ ምርመራ ማሽኖችን ወደ ሀገር አስገብቶ ጥቅም ላይ እያዋለ መሆኑን የገለጸዉ ፖሊስ ሌሎች አሰራሮቹንም በቴክኖሎጂ እያዘመነ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።ከዚህ በተጨማሪም የአቪየሽን ፖሊስ፣ የምድር ባቡር ፖሊስ፣ የዩኒቨርሲቲ ደህንነት ፖሊስ እንዲሁም በኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድርጎ የሚከታተል የፖሊስ ክፍሎች በአዲስ መልክ ተደራጅተዋል ነዉ የተባለው።

👍8
ዘመን ባንክ የማስተር ካርድ የክፍያ ሲስተምን መተግበር የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ!
ዘመን ባንክ ኤም ፒ ጂ ኤስ የተባለ የማስተር ካርድ ሲስተምን በማስጀመር ክፍያዎችን በቀጥታ መክፈል የሚያስችል ቴክኖሎጂን አስተዋውቋል።ይህንን ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀው ከማስተር ካርድ ጋር በመሆን ነው።ይህ የክፍያ ሲስተም ለአየር መንገድ እንዲሁም ለሆቴሎች ቅድሚያ አገልግሎት ክፍያ መፈጸም የሚያስችል ነው ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም የኦንላየን ግብይቶችን በቀጥታ መክፈል የሚያስችል ነው።ይህ የክፍያ ሲስተም በኢትዮጵያ ብርም መገበያየት የሚያስችልና የቀጥታ ክፍያ ንክኪን የሚቀንስ ነው።ኢኮሜርስ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ የመጣ ከመሆኑ አንጻር እንዲህ አይነት ቴክኖሎጂ ግብይቱን በአንድ ቦታ በመጨረስ እንዲቀላጠፍ ያደርጋል።

👍2🔥1
ከነገ ጀምሮ ዜጎቻችንን የመመለስ ስራ ይጀመራል ተብሏል!!
ለረጅም ጊዜያት ሲጠበቅ የነበረው በሳዑዲ አረቢያ በከፋ ስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ ነገ እንደሚጀመር ተገልጿል።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ አረቢያ ሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ወደ አገራቸው የመመለስ ሥራ እንደሚጀመር አስታውቋል።
ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከ7 እስከ 11 ባሉት ወራት ውስጥ ለመመለስ እንደታቀደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

🥰2👍1
አሜሪካ እና ፊሊፒንስ ግዙፍ የተባለዉን ወታደራዊ ልምምድ ጀመሩ
በአወዛጋቢው የደቡብ ቻይና ባህር ላይ ሁለቱ የረዥም ጊዜ አጋሮች ፊሊፒንስ እና ዩናይትድ ስቴትስ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ግዙፍ የተባለዉን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ከዚህ ቀደም ከአሜሪካ ጋር ያለዉን የጦር ልምምድ ለመሰረዝ እና ከቻይና ጋር ሊሰሩ እንደሚችሉ ሲዝቱ ቆይተዋል፡፡
ወደ 9,000 የሚጠጉ የፊሊፒንስ እና የአሜሪካ ወታደሮች ከሰኞ ጀምሮ በሉዞን ደሴት ላይ ለ12 ቀናት ልምምዳቸዉን ማድረግ የጀመሩ ሲሆን ልምምዱ ዓመታዊ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኙ የተነሳ ተቋርጦ ነበር።የፊሊፒንስ ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል አንድሬስ ሴንቲኖ በማኒላ በተካሄደው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን "ጥልቅ ጥምረት" የሚያንፀባርቁ የጦር ልምምድ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ሜጀር ጀነራል ጄይ ባርጌሮን በጦር ኃይሎቻቸው መካከል ያለው “ወዳጅነት እና መተማመን” “በአጠቃላይ ወታደራዊ ሥራዎች ላይ አብረው እንዲሳኩ ያስችላቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ልምምዱ የባህር ላይ ደህንነትን፣ የፀረ ሽብርተኝነት እና የሰብአዊ እርዳታ እና የአደጋ መከላከልን ያካትታል ተብሏል፡፡
የስድስት አመታት የስልጣን ዘመናቸው በሰኔ ወር የሚያበቃው ዱቴርቴ፣ ፊሊፒንስ ከዩናይትድ ስቴትስ ይልቅ ወደ ቻይና እንድታጋድል ሰርተዋል በሚል ትችት ይቀርብባቸዋል፡፡

👍4👎1
በአዲስ አበባ በ2014 የሙያ ብቃት ምዘና ከወሰዱ መምራን መካከል 1,600ዎቹ ማለፋቸው ተነገረ፡፡
ምዘናው ሁለት ዓይነት እንደሆነ የከተማዋ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዛሬ ባዘጋጀው መርኃ ግብር ላይ ሲነገር ተሰምቷል።የመጀመሪያው የጽሑፍ ምዘና ሲሆን ይህን ምዘና 1,835 መምህራን በዚህ ዓመት ወስደዋል ተብሏል።
የጽሑፍ ፈተናውን ከወሰዱ 1,835 መምህራን መካከል 1,600ዎቹ ለማህደረ ተግባር ፈተና መቅረባቸው ተጠቅሷል።እነዚህ በሙሉ የማህደረ ተግባር ፈተናውን አልፈው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርተፊኬት ማግኘታቸው ተነግሯል።የማህደረ ተግባር ምዘና የመምህሩን አጠቃላይ የተግባር እንቅስቃሴ የሚያሳይ ስርዓት እንደሆነ ተሰምቷል።
[Sheger FM]

👍4👏1
ቢሊየነሩ አብራሞቪች በኢስታንቡል የሰላም ንግግር ላይ ተገኝተዋል
ሮማን አብራሞቪች ተመርዘዋል የሚለዉ መረጃ ዉድቅ አድርጓል
ሩሲያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች በቱርክ አሸማጋይነት በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በተደረገው የሰላም ድርድር ላይ ታይተዋል።በኢስታንቡል በተደረገው ውይይት ላይ ሽምግልና ላይ ከሚገኙት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር ሲነጋገሩ ታይተዋል።
አብራሞቪች እና ሁለት የዩክሬን ተደራዳሪዎች በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ካካሄዱት ድርድር በኋላ የመመረዝ ምልክት ታይቆባቸዋል የሚል ሪፖርት ከወጣ ከሰዓታት በኋላ ነው የቢሊየነሩ ምስል ይፋ ተደርጓል፡፡ አብራሞቪች በሞስኮ እና በኪየቭ መካከል በሽምግልና ሚና ላይ ሳምንታት እንዳሳለፉ ይታወቃል።
የቼልሲው የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት የዓይን እና የቆዳ ህመም አጋጥሟቸው ነበር ቢባልም አሁን ግን አገግመዋል የሚል መረጃ ይፋ ሆኗል፡፡በዎል ስትሪት ጆርናል ዘገባ መሰረት ሮማን አብራሞቪች እና የዩክሬን ተደራዳሪዎች በሩሲያ አማካይነት ተመርዘዋል ቢልም የዩክሬን ፕሬዝዳንት ባለስልጣን ግን ሁለቱ ዩክሬናውያን ደህና እንደሆኑ እና መረጃዉ የውሸት ነው ብሏል።
ሆኖም ግን የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከውይይቱ ከሰዓታት በፊት በብሔራዊ ቲቪ እንደተናገሩት ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ የሚገኙ ባልደረቦቻቸው ምንም ነገር እንዳይበሉ እና እንዳይጠጡ መክረዋል።የኢስታንቡል ውይይት ማክሰኞ እለት በንግግር የከፈቱት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የተኩስ ማቆም እና የሰላም ጥሪ በማቅረብ "ግጭቱን ማራዘም ለማንም አይጠቅምም" ሲሉ ለሁለቱ ልዑካን ቡድን በዶልማባቼ ቤተ መንግስት ተናግረዋል፡፡
[Reporter ]

👍8🔥1🥰1
መርሳ ፋኖዎቿን አስመረቀች!
የመርሳ ከተማ ባለሽርጡ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ሰራዊት ወታደራዊ ስልጠናቸውን አጠናው ዛሬ ተመረቁ!
በአማራ ህዝብ አሰቃቂ ውድመት ያደረሰው የትግራይ ወራሪ ኃይል ያንገፈገፋቸው የመርሳ ባለሽርጥ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ሰራዊት ከሁለትወር በላይ ሲያካሂዱ የቆዩት ስልጠና አጠናቀው በመርሳ ሁለገብ ስታድየም በደማቅ ዝግጅት ዛሬ ተመረቁ፡፡

👍6🔥4👏1😁1
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ መጠን ይፋ አደረገ❗️
🔰የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ መጠን ይፋ አደረገ፡፡
🔰ቦርዱ ዛሬ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ያካሄደ ሲሆን÷ ለፓርቲዎች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ መጠንን ይፋ አድርጓል።
🔰የገንዘብ ድጋፉ ከዚህ ቀደም በፀደቀው መመሪያ ላይ በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት የተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
🔰ለ19 አገር አቀፍ እና 35 የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በድምሩ ለ54 ፓርቲዎች እስከ 789 ሺህ ብር የሚደርስ ድጋፍ እንደሚደረግ ከምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ፍርድ ቤት ዛሬ የአሶሴትድ ፕሬስ ዘጋቢዎች አሚር አማን እና ቶማስ እንግዳ እያንዳንዳቸው በ60 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል።
ሆኖም ችሎቱ ዘጋቢዎቹ ከአገር እንዳይወጡ እገዳ ጥሎባቸዋል። ፖሊስ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት ቢጠይቅም፣ ችሎቱ ግን የእስካሁኑ ምርመራ ለውጥ አላሳየም በማለት ነው የገንዘብ ዋስትናውን የፈቀደው። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ባለፈው ኅዳር ያሰራቸው፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮችን እና ታጣቂዎችን መስክ ወርደው በማነጋገር እና በተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረጽ ወደ ውጭ አገር መረጃዎችን ልከዋል በማለት ነበር።

👍6
❗️ፊንላንድ ኮሌጅ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሰው ተቋም ምንም አይነት የእውቅና ፈቃድ የለውም ተባለ
ፊንላንድ ኮሌጅ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሰው ተቋም ምንም አይነት የእውቅና ፈቃድ እንደሌለው የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ።
ፊንላንድ ኮሌጅ በሚል ስያሜ የእውቅና ፈቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ ያቀረበው ተቋሙ፣ ከባለሥልጣኑ የዕውቅና ፈቃድ ሳያገኝ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በአረካ ከተማና በሌሎች የክልሉ ከተሞች በርካታ ተማሪዎችን መዝግቦ እያስተማረ መሆኑ በተደረገው ማጣራት መረጋገጡን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገረሱ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
ባለሥልጣኑ በፊንላንድ ኮሌጅ በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ የሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ ተቀባይነት የሌለውና ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማስከበር እርምጃ በመውሰድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስቧል፡፡

የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚመለስ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የራያ ሕዝብ ተወካዮች ላቀረቡት ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የራያ ሕዝብ ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የራያ ሕዝብ ተወካዮች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የራያ ሕዝብ የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ያቀረቡ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ ምላሽ ሳያገኝ እንደቆየ አውስተዋል፡፡
ተወካዮቹ አያይዘውም የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ሞትን ጨምሮ ሌሎች በደሎች በራያ ሕዝብ ላይ ሲፈፀም የቆየ እንደነበረና በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ራያዎች ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ እና ንብረታቸውም ሲወድም እንደነበረ ተወካዮቹ በአካል ቀርበው አስረድተዋል፡፡
ጥያቄአችን ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ሲሉም ተወካዮቹ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሸገር በበኩላቸው ጥያቄውን ላቀረቡት የራያ የማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የራያ ሕዝብ ጥያቄው በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደ ከዚህ በፊቱ የሕዝብን ጥያቄ በኃይል ለማፈን የሚደረግ አላስፈላጊ ጫና ከሕገ መንግስቱ የሚቃረን ስለሆነ ተቀባይነት እንደሌለው የጠቆሙት አፈ ጉባዔው የሕዝብ ጥያቄ ሕግን መሠረት በማድረግ ምላሽ በመስጠት ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

👍24
ኢትዮጵያን የሚመለከተው ኤስ3199 ረቂቅ ሕግ ተቀባይነት አግኝቶ ወደ አሜሪካ ሴኔት ተመራ!!
የአሜሪካ ሴኔት በኮሚቴ በኢትዮጵያ ሰላም እና ዲሞክራሲ ለማበረታታት በሚል የቀረበውን ረቂቅ ሕግ ተቀብሎ ወደ ሴኔቱ እንዲያልፍ አደረገ።
ይህ ኤስ3199 የተባለው በኢትዮጵያ ሰላም እና ዲሞክራሲ ማበረታታት ወይም The Ethiopia Peace and Democracy Promotion Act በሚል የቀረበው ረቂቅ ሕግ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እንዲሁም በጦርነት ተሳታፊ ናቸው በተባሉ ግለሰቦች ላይ ጠንከር ያለ ማዕቀብ ለመጣል የተዘጋጀ ነው።
የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ትናንት ማክሰኞ ምሽት መጋቢት 20/2014 ዓ.ም. ባደረገው ውይይት ረቂቅ ሕጉን ተቀብሎ ወደ ሴኔቱ እንዲቀርብ ወስኗል።
ይህን ረቂቅ ሕግ ለሴኔቱ ያስተዋወቁት የኒው ጀርሲው ሴናተር ሮበርት ሜንዴዝ ናቸው። ኤስ 3199 ረቂቅ ሕግ ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም. ለሴኔቱ ቀርቦ ለሴኔቱ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ተመርቶ ነው ውይይት ተደርጎበት ወደ ቀጣዩ ሂደት እንዲያልፍ የተደረገው።
ይህ ረቂቅ ሕግ ከዚህ በኋላ ለሙሉው ሴኔት ቀርቦ ሌላ ዙር ውይይት የሚደረግበት ሲሆን ሴኔቱ የሚያጸድቀው ከሆነ ለሕዝብ ተወካዮች ይቀርባል፣ የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቀብሎት ካለፈ በቀጠይነት ለፕሬዝዳንቱ ቀርቦ ፊርማቸውን ካኖሩበት ሕግ ሆኖ ተግባራዊ ይሆናል።
በተመሳሳይ ሌላ ኢትዮጵያ እና ኤርትራን የተመለከተ ረቂቅ ሕግ በአሜሪካ ምክር ቤት መተዋወቁ ይታወሳል።
ይህ ረቂቅ ሕግ ኤችአር 6600 የሚባል ሲሆን በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ከግጭት ጋር ተያይዞ ለደረሱ በደሎች ተጠያቂ ናቸው በተባሉ ግለሶች ላይ ማዕቀብ መጣል ያስችላል።
የኢትዮጵያ መንግሥት አጥብቆ የተቃወማቸው እነዚህ ረቂቅ ሕጎች በፕሬዝዳንት ባይደን የሚጸድቁ ከሆነ አሜሪካ በደኅንነት፣ በፋይናንስ/በኢንቨስትመንት እና በኢሚግሬሽን ጉዳዮች ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ትጥላለች።
ኤችአር 6600 ረቂቅ ሕግ በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 01/2014 ዓ.ም. ቀርቦ የነበረ ሲሆን፤ ረቂቅ ሕጉ ለምክር ቤቱ የውጭ ጉዳዮች፣ ፍትሕ፣ የፋይናንስ አገልግሎቶች እና ለጦር ኃይል አገልግሎቶች ተመርቷል።
ኤስ 3199 ረቂቅ ሕግ ይዘት ምንድነው?⁉️
በዚህ ረቂቅ ሕግ ላይ አሜሪካ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ግንባታ እና የሰብዓዊ መብት መከበርን እንደምትደግፍ ተመልክቷል። ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ለተከሰተ ግጭት መፍትሄ እና እርቅ ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፏን እንደምታደርግ ረቂቅ ሕጉ ያትታል።
ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የሚደረጉ የሰላም፣ የመረጋጋት እና የዲሞክራሲ ግንባታ ጥረቶችን በሚያደናቅፉ ግለሰቦች ላይ የንብረት እና የጉዞ እግድ ይተላለፍባቸዋል ይላል።
ይህ ረቂቅ ሕግ ሆኖ ከወጣ አሜሪካ ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ የጦር መሳሪያ አትልክም። በአሜሪካው "Better Utilization of Investments Leading to Development Act of 2018" መሠረት ዋሽንግተን በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ ፕሮጀክቶች ድጋፍ አታደርግም።
እንደ ኤችአር 6600 ሁሉ ኤስ3199 ረቂቅ ሕግ አሜሪካ ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ የምታደርገው የደኅንነት እና የፀጥታ ድጋፍ እንዲቋረጥ ይጠይቃል።
ከዚህ በተጨማሪም ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሚሰጡ ብድሮች ወይም የብድር ማራዘሚያዎች እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፎች እንዳይፈቀዱ አሜሪካ ተሰሚነቷን እና ድምጽ የመስጠት መብቷን ትጠቀማለች ይላል ረቂቅ ሕጉ።
እነዚህ ረቂቅ ሕጎች ኢትዮጵያውያንን የሚጎዱ እና ጦርነቱን ለማብቃት የሚደረጉትን የሰላም ጥረቶች የሚያደናቅፉ ከመሆናቸው በተጨማሪ በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ሙከራዎች ናቸው በማለት የኢትዮጵያ መንግሥት አጥብቆ ተቃውሟቸዋል።
እንዲሁም በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕጎቹ እንዳይጸድቁ ጥረትና የተቃውሞ ሰልፎች እያደረጉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የሕጎቹን መጽደቅ የሚደግፉ ኢትዮጵያውያንም ግፊት እያደረጉ ይገኛሉ።

👍6🥰1
#መረጃ! #ምንጃር!
ሽብርተኛዉ ኦነግ ሸኔ ምንጃር አውራጎዳና ገባ ግን አልወጣም ተባለ። የሽብር ቡድኑ ሁለት ፌደራል ፖሊስ እና አንድ የአካባቢው ንፁሀን ሰዉ ገድሏል።
በተጨማሪም በመሀል ከተማ ውስጥ ስድስት ሰው እንዳቆሰሉ ተገልጿል በስልጠና የዳበረ የምንጃር አውራጎዳና ነዋሪ የሽብር ቡድኑ እንደመግባት ቀላል ሳይሆንለት አስቀርቶታል።

በሳውዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ 498 ዜጎች ወደ አገር ቤት ተመለሱ!
በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለስ ጀምረዋል።
በዚሁ መሰረት በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው ዙር 498 ዜጎች ወደ አገር ቤት የተመለሱ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች በረራዎች ይኖራሉ ተብሏል።
https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለስ ጀምረዋል።
በዚሁ መሰረት በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው ዙር 498 ዜጎች ወደ አገር ቤት የተመለሱ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች በረራዎች ይኖራሉ ተብሏል።
https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
🥰2👍1
በጉራጌ ዞን በደረሰ የእሳት አደጋ 42 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለፀ!!
በቀቤና ወረዳ በሌንጫ ቀበሌ ልዩ ስሙ ፈረጀቴ ጎጥ ትናንት እኩለ ቀን ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ 35 የሳር ክዳን ቤቶች፣ 5 የቆርቆሮ ክዳን ቤቶችና 2 መስጂዶች በድምሩ 42 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ነው የተገለፀው።
2ቱ መስጂዶች በከፊል የወደሙ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በምርትና በሰብል ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱም ተጠቁሟል። በጥንቃቄ ጉድለት በአካባቢው የነበረውን ቁጥቋጦ ለማጥፋት በሚል የተለኮሰ እሳት በወቅቱ በነበረ ከፍተኛ ንፋስ ወደ አካባቢው በመዛመቱ ነው የእሳት አደጋው የደረሰው።
በእሳት አደጋው በቤትና ንብረት ላይ ከደረሰው ውድመት በተጨማሪም በእንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል። በእሳት አደጋው ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት በደረሰው አደጋ ለከፍተኛ ችግር በመጋለጥ ሜዳ ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።
በመሆኑም በጊዜያዊነትና በቋሚነት ለማቋቋም የወረዳውና የዞኑ አስተዳደር፣ የአካባቢው ተወላጅ ባለሃብቶች፣ ግብረሰናይ ድርጅቶችና መላው ህብረተሰብ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል። የቀቤና ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት በበኩሉ ወቅቱ ነፋሻማ በመሆኑ የወረዳው ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ገልጿል። ጉዳቱ የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ሁሉም ርብርብ ማድረግ እንደሚገባውም ፅህፈት ቤቱ መልእክቱን አስተላልፏል።

👍5😢1