የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን ሁለተኛውን የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ ጨረታ በመጭው መስከረም እንደገና እንደሚጀምር ካፒታል ጋዜጣ ከባለሥልጣኑ መስማቱን ጠቅሶ ዘግቧል። ባለሥልጣኑ ጨረታውን ለማውጣት የሚያስችለውን ቅድመ ጥናት እንዳጠናቀቀ ዘገባው ገልጧል። ባለሥልጣኑ ለሁለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ በተያዘው ዓመት መግቢያ ላይ ጀምሮት የነበረውን የጨረታ ሂደት ባለፈው ታኅሳስ ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጫለሁ ማለቱ ይታወሳል።የሁለተኛው ቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ ጨረታ ሂደት የተቋረጠው፣ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ኩባንያዎች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት እንደሆነ በወቅቱ ተገልጧል።
https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
👍2
በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች ከነገ በስቲያ ጀምሮ ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ!
በሳዑዲ አረቢያ በእስር ቤት እና በማዕከላት ውሰጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።16 የመንግስት ተቋማትን በአባልነት የያዘው ኮሚቴው ዜጎችን መመለስ ለመጀመር የተደረጉ የመጨረሻ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ዛሬ የገመገመ ሲሆን ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ ዜጎችን መመለሱ እንደሚጀምር ይፋ ሆኗል።
በውይይቱ እንደተገለፀው የበረራ፣ የማቆያ ማዕከላት ዝግጅት፣ የመገልገያ ቁሳቁስ፣ የምግብ እና መጠጥ አቅርቦት፣ የአልባሳት፣ የትራንስፖርት እንዲሁም የህክምና አገልግሎትን ለተመላሾች በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ በመቻል ረገድ የተደረጉ ዝግጅቶች በግብረ ሃይሉ አባላት ውይይት ተደርጎባቸዋል።የኮሚቴው ሰብሳቢ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዳሉት የመመለሱ ተግባር ተመላሽ ዜጎችን ካሉበት አምጥቶ እስከ መኖሪያ ቀያቸው የማድረስ ስራን የሚሸፍን ነው።
ይህንኑ ከመነሻው እስከ መድረሻው በተሳለጠ ቅብብሎሽ ለመፈፀም ተቋማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አምባሳደር ብርቱካን አሳስበዋል።ተመላሾች አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ክልሎች ከየማዕከላቱ ቶሎ በማንሳት ወደ መኖሪያቸው መውሰድ ያለባቸው በመሆኑ ያደረጉት ዝግጅትም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ክልሎቹ ያልተጠናቀቁ የዝግጅት ስራዎችን በቀሪ ቀናት እንዲያጠናቅቁ አሳስበዋል።በየጊዜው የቅበላ አቅምን በማሳደግ ዜጎችን ካሉበት አስቸጋሪ ሁኔታ ለማውጣት መንግሥት የተቻለውን ጥረት ማድረጉን እንደሚቀጥልም አምባሳደሯ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

👍2❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" ወያኔም አልቻለም፤ ብልፅግናም አልቻለም " - አቶ ጃዋር መሀመድ
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ከወራት በፊት ከእስር ከተፈቱ በኃላ በአደባባይ ንግግር ሲየደርጉ/ ሃሳባቸውን ሲገልፁ/ለሚዲያ ቃላቸውን ሲሰጡ አልተስተዋለም።
ባለፉት ቀናት በነበረው የፓርቲያቸው ጉባኤ ላይ ግን ንግግር አድርገዋል።
አቶ ጃዋር በንግግራቸው ሊበታትኗቸው የፈለጉ ኃይሎች ሁሉ ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ገልፀዋል።
አቶ ጃዋር መሀመድ " ' ይሄን ካላደረጋችሁ እናፈርሳችኋለን " ይሄን ወያኔም አልቻለም፣ ብልፅግናም አልቻለም። ሊበታትኑን በፍፁም አይችሉም። ኦሮሞን በፍጹም ማስፈራራት አይቻልም በፍጹም " ብለዋል።
"እኔ በራሴ ከኦፌኮ ከወጣክ ይሄን እናደርግልሃለን ፣ ይሄንን ካላደረክ እንደዚህ አናደርግም ብለውኛል " ያሉት አቶ ጃዋር " ሞተን እንገኛለን እንጂ ካመንበት ነገር ወደኋላ አንመለስም " ሲሉ ተደምጠዋል።
አክለው፥ " ብልፅግና ከግማሽ በላይ ኦነግን ወስዶት እንኳን ኦነግን ማፍረስ አልቻለም። ኦነግ ፈርሷል? አልፈረሰም " ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ ጃዋር፥ " ከቦረና፣ ከጉጂ የሚነሳውን ቅሬታ እንሰማለን፣ እንመካከራለን፣ እናስተካክላለን " ያሉ ሲሆን " እኔ ያልኩትን ካልወሰዳችሁ አርሲን ከዚህ አወጣለሁ፣ ሸዋን አወጣለሁ፣ ወለጋን ከዚህ አወጣለሁ ካልክ አንተ ነህ የምትወጣው እንጂ ጉጂም አርሲም አይወጡም " ሲሉ ተናግረዋል።
"እኔ OMN በነበርኩበት ሰዓት እንደዚህ አይነት ሙከራዎች ነበሩ " ያሉት አቶ ጃዋር " አንደዚህ ካላደረክ ከሀረርጌ የሚመጣውን ገንዘብ አንቆርጥብሃለን ከወለጋ የሚመጣውን ገንዘብ እንቆርጥብሃለን...ከቆረጣችሁ ትቆርጣላችሁ እንጂ የኦሮሞ አንድነት አይቆረጥም። ከተበታተንን እንበታተናለን እንጂ ወደኋላ አንመለስም" ብለዋል።
@ethiopian_reporter

👍4👎4
የእለተ ሰኞ አጫጭር መረጃዎች በሩሲያ-ዩክሬን ቀዉስ ዙሪያ
🇭🇺በሃንጋሪ የሚኖሩ ዜጎች በቡዳፔስት የዳኑቤ ወንዝ ዳርቻ ላይ 300 ጥንድ ያረጁ ጫማዎችን በማስቀመጠጥ በማሪፑል ቲያትር ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት ህይወታቸዉ ያለፉ ሰዎችን ዘክረዋል፡፡
🇺🇦በዩክሬን ያለው ጦርነት ከ63 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የመሰረተ ልማት ዉድመት ማድረሱን የኪየቭ ኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት ባወጣው አዲስ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ቢያንስ 4,431 የመኖሪያ ሕንፃዎች ፣ 92 ፋብሪካዎች እና መጋዘኖች እና 378 ትምህርት ቤቶች ጋር ዉድመት እንደደረሰባቸዉ ተገልጿል፡፡በተጨማሪም 12 አየር ማረፊያዎች እና ሰባት የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ዉድመት ከደረሰባቸዉ መካከል ናቸዉ፡፡
🇺🇦የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዝለንስኪ በወታደራዊ ጄኔራል ሰራተኞች ካልተገለጸ ወይም ካልተፈቀደ በቀር በወታደሮች እና በወታደራዊ መሳሪያዎች እንቅስቃሴ ላይ ዘገባ መስራት የሚገድብ ህግን ፈርመዋል ።
🇷🇺🇺🇦የሩስያ ወታደሮች ከቼርኖቤል የኒውክሌር ጣቢያ ወጣ ብሎ ከምትገኘዉ ከተማ ለቀው መውጣታቸው ተሰምቷል።ሮይተርስ እንደዘገበው ከንቲባ ዩሪ ፎሚቼቭ ወታደሮቹ “ሊሰሩት ያሰቡትን” ስራ አጠናቀው የስላቭች ከተማን ለቀው መውጣታቸውን ተናግረዋል።የሩሲያ ጦር ቅዳሜ ዕለት የስላቫትቺን ከተማ በመቆጣጠር ከንቲባውን ለአጭር ጊዜ አግተዉ ነበር።
🇺🇦በሰሜን ምዕራብ ዩክሬን በምትገኘው የቮልይን ግዛት በሆነችዉ በሉትስክ ከተማ የነዳጅ ማከማቻ ቦታ ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙ ተሰማ፡፡የቮልይን ግዛት ገዢ ዩሪ ፖሁሊያይኮ እንደተናገሩት ሚሳኤሉ የተተኮሰው ከቤላሩስ ግዛት እንደሆነ ገልጸዋል።
🇺🇸በኦስካር ከታጩት የዜማ ደራሲ ዳያን ዋረን፣ የባለፈው አመት የኦስካር ምርጥ ረዳት ተዋናይት ዩን ዩህ-ጁንግ እና የ"ሃሎዊን" ኮከብ ጄሚ ሊ ከርቲስ፣ ቤኔዲክት ኩምበርባች እና ጄሰን ሞሞአ ለዩክሬን ያላቸዉን አጋርነት በአካዳሚ አዋርድ ስነስርዓት ላይ አሳይተዋል፡፡
🇺🇸🇷🇺የሩሲያ ፕሬዝዳንት ከስልጣን እንዲለቁ ጥሪ አላደረኩም ሲሉ ባይደን አስተባበሉ፡፡የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባሳለፍነዉ ቅዳሜ በፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶ ባደረጉት ንግግር ፑቲን "በስልጣን መቆየት አይችሉም" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ሞስኮ በበኩሏ የሩሲያን መሪ የሚመርጡት የሩሲያ ዜጎች ናቸዉ በማለት ክሬምሊን የዋይትሀዉስ አለቃ የአእምሮ ጤና እንዲፈተሸ ጠይቃለች፡፡
🇩🇪ጀርመን የሩስያ ጥቃትን ለመከላከል የጸረ ሚሳኤል መሳሪያ ለመግዛት እያሰበች ነው ሲሉ ቻንስለር ኦላፍ ሾልስ ተናግረዋል ።በርሊን ምን ዓይነት የሚሳኤል መከላከያ መሳሪያ ለመግዛት እንዳሰበች ግን ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡
🇺🇦🇷🇺የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ አገልግሎት እንዳስታወቀዉ ሩሲያ ዩክሬንን ልክ እንደ ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ ለሁለት ለመከፋፈል እየሞከረች መሆኑን አስጠነቀቀቸ፡፡የሩስያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ምስራቃዊ እና ደቡባዊ የዩክሬንን ግዛቶች ከሌላው የሀገሪቱ ክፍል ለመለየት እየሞከሩ ነው ሲሉ የዩክሬን የስለላ ሃላፊ ኪሪሎ ቡዳኖቭ ተናግረዋል፡፡
🇬🇧ሩሲያ ዩክሬንን ከአለም አቀፍ የባህር ላይ ንግድ እየገለለች ነዉ ስትል ብሪታኒያ ተናግራለች፡፡ ዩክሬንን ከጥቁር ባህር ዳርቻ አግዳለች ሲል የብሪታኒያ የመከላከያ ጽህፈት ቤት ባወጣዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡
🇹🇷የሩሲያ እና የዩክሬን ተደራዳሪ ቡድኖች በቱርክ ኢስታንቡል ከተማ ለውይይት እንደሚገናኙ የቱርክ እና የሩሲያ ፕሬዝዳንቶች ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ስብሰባው በተያዘዉ ሳምንት የሚካሄድ እንደሆነ ቢነገርም ቀኑ ግን አልተገለጸም፡፡

👍5🔥1😁1
#መረጃ #ትኩረት
ለሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ማስፋፊያ ቤታቸው እንዲፈርስ የተደረጉ ሁለት ሰዎች ሞተዋል።
# ለ2 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል የሚባለው የሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ጉዳይ የነዋሪዎችን ብሶት አባብሷል!
# በከፍተኛ ጥንቃቄ የተቀረፀ ቪዲዮ ይለቀቃል!
/
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘደንት የሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ሳቢያ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ነዋሪ በምሬት ገለፀ፡፡ የባልደራስ አመራር አባላት በአካባቢው ሰሞኑን ባደረገው የመስክ ጉብኝት፣ በርካታ ሰዎች ተሰባስበው ያለውን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡
በአካባቢው ቀረፃ ስለማይቻል ሰወር ባለ ቦታ ላይ የተገናኙት የአመራር አባላቱና የአካባቢው ነዋሪዎች ያደረጉት ቆይታ በከፍተኛ ጥንቃቄ በቪዲዮ ተቀርጾ በጥንቃቄ ከአካባቢው እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
በሶስት ቀን ውስጥ ቤታቸውን እንዲለቁ የታዘዙት ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፣ “በድንገት እየመጡ ውጡ ሲሉን ከመካከላችን ሁለት ሰዎች ሞተዋል ” ብለዋል፡፡ ከመካከላቸውም የሐዘን ልብስ የለበሰች እንስት ያለውን ሁኔታ ተናግራ በቪዲዮ ተቀርፃለች፡፡
በነዋሪዎቹ አስተያየት፣ አሁን ለቢሮ ማስፋፊያ የተፈለገው ቦታ በጣም ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ለተባላለት ዓላማ ብቻ የተፈለገ ነው ለማለት እንደሚቸገሩ ተናግርዋል፡፡ “ ይህ ሁሉ መሬት ለአንድ ቢሮ ብቻ ያስፈልጋል ለማለት ያስቸግራል፡፡ ለምን እንደሆነ ባናውቅም፣ ይዞታቸውን ነው ማስፋፋት የፈለጉት፡፡ በዚህ ሂደት እኛ ደሀዎቹ እየተጨፈለቅን ነው ” ብለዋል፡፡
ስንታየሁ ቸኮል

👍10🤯5
#Update
የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ ወደ' ትግራይ ክልል' እንዲገባ የህወሓት ታጣቂዎች የያዟቸውን የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ሊወጡ ይገባል ሲል አስገነዘበ።
መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል መንግስት ግጭት የማቆም ውሳኔ ማሳለፉ ከትግራይ ክልል በኩልም በጎ ምላሽ መሰጠቱ ይታወሳል።
ነገር ግን ውሳኔ ከተላላለፈበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ምንም አይነት ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል ሊገባ እንዳልቻለ የክልሉ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።
ክልሉን ወክለው ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወት ፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ወደግጭት ማቆም እንዲደረስ ብዙ ጥረት አድርጓል፤ የባለፈው ሳምንት ስምምነት ዝም ብሎ የመጣ ስምምነት አይደለም ብዙ ጊዜ የተሰራበት ስምምነት ነው ብለዋል።
የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ክልሉ ለምን እንዳልገባ የተጠየቁት ፕ/ር ክንደያ ፤ ኃይላቸው በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች የእርዳታ መኪናዎች ስላልደረሱ ማወቅ እንዳልቻሉ ፤ ለምን እንዳልተላኩ መላክና ማሳለፍ የሚገባቸው አካላት ማብራሪ ሊሰጡ ይገባል ብለዋል።
ከባለፈው ሃምሌ ወር በየዕለቱ 100 የሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንደነበረባቸው የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ይገልፃሉ አሁን ያለው ችግር ሲታይ ፍላጎቱ ጨምሯል ሲሉ አስረድተዋል።
አሁን ያለው ግጭት ለማቆም እና ሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ የሚለው ውሳኔ ካልተሳካ ለረጅም ጊዜ ተዘጋግቶ መጠበቅ ስለማይቻል ሌላ አማራጭ እናያለን ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጠው ቃል ፤ እርዳታ ወደክልሉ እንዲገባ የህወሓት ኃይሎች ከያዟቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ሊወጡ ይገባል ብሏል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፤
" ... እነሱ ግጭት እናቆማለን ብለው አልነበር እንዴ ? ቀደም ብሎ መንግስት የትኛውም አይነት ትንኮሳ እንደማይፈፅም እና የትኛውም አይነት ግጭት ውስጥ እንደማይገባ አስቀምጧል።
በአንፃሩ እነሱ እርዳታው በቀላሉ ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርስ በጉልበት ከያዟቸው የአፋር ክልል ወረዳዎች መውጣት አለባቸው ብሎ አስቀምጧል። እስከዛሬ ድረስ ከ5 ወይም 6 ወረዳዎች አልወጡም።
እንደውም ትላንትና 'ኮኖባ' በሚባል ቦታ ከአፋር ሚሊሻ ጋር ጦርነት ነበር።
ለህዝቡ ካሰቡ ከያዙት ቦታ መውጣት እና መንገዱን ክፍት ማድረግ አለባቸው። ይሄን ሳያደርጉ መንግስት ሆን ብሎ ነው የሚለው ትክክል አይደለም "
👉 መጋሌ ፣
👉 ኤሬብቲ ፣
👉 በርሃሌ፣
👉 አብዓላ የተባሉ የአፋር ቦታዎችን የ " ህወሓት ኃይሎች " ተቆጣጥረው እንደሚገኙ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
" ... ይሄ በዋናነት እርዳታው የሚሄድበት የአስፓልት መንገድ ላይ ነው ያለው። ይሄንን መልቀቅ አለባቸው ይሄንን ሳይለቁ ' መንግስት እርዳታ አላቀረበም ' ብለው ቅሬታ ማቅረብ ሚችሉበት ምንም አይነት ሁኔታ የለም። ስለዚህ እርዳታው ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርስ ለህብረተሰቡ የሚያስቡ ከሆነ በጉልበት ከያዟቸው አካባቢዎች መልቀቅ ነው ያለባቸው፤ አካባቢውን ከግጭት ነፃ ነው ማድረግ ያለባቸው ። " ሲሉ ዶ/ር ለገሰ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ፤ እርዳታ ለማድረስ ያለውን ዝግጅቱነት በመተመለከተ 3 የነዳጅ እና 20 የእርዳታ እህል የጫኑ 23 መኪናዎች ቆመዋል (ከዚህ በፊት ሄደው በፀጥታ ችግር የተመለሱ) ፤ በተጨማሪ ሰመራ ላይ ከመጋዘን ለመጫን የሚጠባበቁ ትልልቅ ተሽከርካሪዎችም አሉ በአጠቃላይ 43 ተሽከርካሪዎች ናቸው መንገዱ ካልተከፈተ እና ግጭት ካልቆመ እርዳታ ሊሄድ አይችልም ብለዋል።
መንግስት የወሰነው ለሰብዓዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ እስከመቼ እንደሚቆየ የተጠየቁት ሚኒስትሩ ፤ " በመንግስት በኩል የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የለም። ህብረተሰቡ ወደ ተለመደው ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመጣ ነው መንግስት የሚፈልገው ፤ አካባቢውም ተረጋግቶ መጪውም ክረምት ስለሆነ እርሻውን እንዲያርስ መንግስት የሚፈልገው ከዛ ውጭ የሚደረግ ነገር ካለ እሱን በሂደት ይታያል። " ብለዋል።

👍9
አስቸኳይ ትኩረት ለዳንጉር በላያ እና ዙርያ!
በመተከል ዞን በዳንጉር ወረዳ በለያ ዙርያ ልዩ ስሙ አውጃቢስ ከፍተኛ የርስ በርስ ግጭት ተከስቶ በሰው እና ንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ያነጋገርናቸው የአካባቢው የአይን እማኞች ገልፀዋል። ይህ ግጭት ቀስበቀስ የብሔር ቅርፅ እየያዘ በመሆኑ በአስቸኳይ ካልቆመ አድማሱን አስፍቶ አላስፈላጊ ዋጋ እንዳያስከፍል መስጋታቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ የክልልና ፌዴራል መንግስት ሊደርስልን ይገባል ብለዋል።

👍2🔥2
በሀገር ውስጥ የዲ ኤን ኤ ምርመራ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ!
ከዚህ ቀደም ወደ ዉጭ ሀገር በመላክ ይሰጥ የነበረዉን አገልግሎት በሀገር ዉስጥ ለመስጠት ያስችላል የተባለለት ለወንጀል ምርመራ የሚያግዝ የዘረ-መል (ዲ ኤን ኤ) ምርመራ በሀገር ዉስጥ ለመጀመር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።አገልግሎቱ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ስለሚጀምረዉ ቴክኖሎጂው አተገባበር እና ስለሙከራው ውጤታማነት በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ለህዝብ መረጃ እንደሚሰጥ የፌደራል ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄላን ኢብራሂም ተናግረዋል።
ለወንጀል ምርመራ ስራ የሚያግዙ አዳዲስ የፎረንሲክ ምርመራ ማሽኖችን ወደ ሀገር አስገብቶ ጥቅም ላይ እያዋለ መሆኑን የገለጸዉ ፖሊስ ሌሎች አሰራሮቹንም በቴክኖሎጂ እያዘመነ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።ከዚህ በተጨማሪም የአቪየሽን ፖሊስ፣ የምድር ባቡር ፖሊስ፣ የዩኒቨርሲቲ ደህንነት ፖሊስ እንዲሁም በኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድርጎ የሚከታተል የፖሊስ ክፍሎች በአዲስ መልክ ተደራጅተዋል ነዉ የተባለው።

👍8
ዘመን ባንክ የማስተር ካርድ የክፍያ ሲስተምን መተግበር የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ!
ዘመን ባንክ ኤም ፒ ጂ ኤስ የተባለ የማስተር ካርድ ሲስተምን በማስጀመር ክፍያዎችን በቀጥታ መክፈል የሚያስችል ቴክኖሎጂን አስተዋውቋል።ይህንን ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀው ከማስተር ካርድ ጋር በመሆን ነው።ይህ የክፍያ ሲስተም ለአየር መንገድ እንዲሁም ለሆቴሎች ቅድሚያ አገልግሎት ክፍያ መፈጸም የሚያስችል ነው ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም የኦንላየን ግብይቶችን በቀጥታ መክፈል የሚያስችል ነው።ይህ የክፍያ ሲስተም በኢትዮጵያ ብርም መገበያየት የሚያስችልና የቀጥታ ክፍያ ንክኪን የሚቀንስ ነው።ኢኮሜርስ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ የመጣ ከመሆኑ አንጻር እንዲህ አይነት ቴክኖሎጂ ግብይቱን በአንድ ቦታ በመጨረስ እንዲቀላጠፍ ያደርጋል።

👍2🔥1
ከነገ ጀምሮ ዜጎቻችንን የመመለስ ስራ ይጀመራል ተብሏል!!
ለረጅም ጊዜያት ሲጠበቅ የነበረው በሳዑዲ አረቢያ በከፋ ስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ ነገ እንደሚጀመር ተገልጿል።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ አረቢያ ሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ወደ አገራቸው የመመለስ ሥራ እንደሚጀመር አስታውቋል።
ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከ7 እስከ 11 ባሉት ወራት ውስጥ ለመመለስ እንደታቀደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

🥰2👍1
አሜሪካ እና ፊሊፒንስ ግዙፍ የተባለዉን ወታደራዊ ልምምድ ጀመሩ
በአወዛጋቢው የደቡብ ቻይና ባህር ላይ ሁለቱ የረዥም ጊዜ አጋሮች ፊሊፒንስ እና ዩናይትድ ስቴትስ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ግዙፍ የተባለዉን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ከዚህ ቀደም ከአሜሪካ ጋር ያለዉን የጦር ልምምድ ለመሰረዝ እና ከቻይና ጋር ሊሰሩ እንደሚችሉ ሲዝቱ ቆይተዋል፡፡
ወደ 9,000 የሚጠጉ የፊሊፒንስ እና የአሜሪካ ወታደሮች ከሰኞ ጀምሮ በሉዞን ደሴት ላይ ለ12 ቀናት ልምምዳቸዉን ማድረግ የጀመሩ ሲሆን ልምምዱ ዓመታዊ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኙ የተነሳ ተቋርጦ ነበር።የፊሊፒንስ ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል አንድሬስ ሴንቲኖ በማኒላ በተካሄደው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን "ጥልቅ ጥምረት" የሚያንፀባርቁ የጦር ልምምድ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ሜጀር ጀነራል ጄይ ባርጌሮን በጦር ኃይሎቻቸው መካከል ያለው “ወዳጅነት እና መተማመን” “በአጠቃላይ ወታደራዊ ሥራዎች ላይ አብረው እንዲሳኩ ያስችላቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ልምምዱ የባህር ላይ ደህንነትን፣ የፀረ ሽብርተኝነት እና የሰብአዊ እርዳታ እና የአደጋ መከላከልን ያካትታል ተብሏል፡፡
የስድስት አመታት የስልጣን ዘመናቸው በሰኔ ወር የሚያበቃው ዱቴርቴ፣ ፊሊፒንስ ከዩናይትድ ስቴትስ ይልቅ ወደ ቻይና እንድታጋድል ሰርተዋል በሚል ትችት ይቀርብባቸዋል፡፡

👍4👎1
በአዲስ አበባ በ2014 የሙያ ብቃት ምዘና ከወሰዱ መምራን መካከል 1,600ዎቹ ማለፋቸው ተነገረ፡፡
ምዘናው ሁለት ዓይነት እንደሆነ የከተማዋ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዛሬ ባዘጋጀው መርኃ ግብር ላይ ሲነገር ተሰምቷል።የመጀመሪያው የጽሑፍ ምዘና ሲሆን ይህን ምዘና 1,835 መምህራን በዚህ ዓመት ወስደዋል ተብሏል።
የጽሑፍ ፈተናውን ከወሰዱ 1,835 መምህራን መካከል 1,600ዎቹ ለማህደረ ተግባር ፈተና መቅረባቸው ተጠቅሷል።እነዚህ በሙሉ የማህደረ ተግባር ፈተናውን አልፈው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርተፊኬት ማግኘታቸው ተነግሯል።የማህደረ ተግባር ምዘና የመምህሩን አጠቃላይ የተግባር እንቅስቃሴ የሚያሳይ ስርዓት እንደሆነ ተሰምቷል።
[Sheger FM]

👍4👏1
ቢሊየነሩ አብራሞቪች በኢስታንቡል የሰላም ንግግር ላይ ተገኝተዋል
ሮማን አብራሞቪች ተመርዘዋል የሚለዉ መረጃ ዉድቅ አድርጓል
ሩሲያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች በቱርክ አሸማጋይነት በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በተደረገው የሰላም ድርድር ላይ ታይተዋል።በኢስታንቡል በተደረገው ውይይት ላይ ሽምግልና ላይ ከሚገኙት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር ሲነጋገሩ ታይተዋል።
አብራሞቪች እና ሁለት የዩክሬን ተደራዳሪዎች በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ካካሄዱት ድርድር በኋላ የመመረዝ ምልክት ታይቆባቸዋል የሚል ሪፖርት ከወጣ ከሰዓታት በኋላ ነው የቢሊየነሩ ምስል ይፋ ተደርጓል፡፡ አብራሞቪች በሞስኮ እና በኪየቭ መካከል በሽምግልና ሚና ላይ ሳምንታት እንዳሳለፉ ይታወቃል።
የቼልሲው የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት የዓይን እና የቆዳ ህመም አጋጥሟቸው ነበር ቢባልም አሁን ግን አገግመዋል የሚል መረጃ ይፋ ሆኗል፡፡በዎል ስትሪት ጆርናል ዘገባ መሰረት ሮማን አብራሞቪች እና የዩክሬን ተደራዳሪዎች በሩሲያ አማካይነት ተመርዘዋል ቢልም የዩክሬን ፕሬዝዳንት ባለስልጣን ግን ሁለቱ ዩክሬናውያን ደህና እንደሆኑ እና መረጃዉ የውሸት ነው ብሏል።
ሆኖም ግን የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከውይይቱ ከሰዓታት በፊት በብሔራዊ ቲቪ እንደተናገሩት ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ የሚገኙ ባልደረቦቻቸው ምንም ነገር እንዳይበሉ እና እንዳይጠጡ መክረዋል።የኢስታንቡል ውይይት ማክሰኞ እለት በንግግር የከፈቱት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የተኩስ ማቆም እና የሰላም ጥሪ በማቅረብ "ግጭቱን ማራዘም ለማንም አይጠቅምም" ሲሉ ለሁለቱ ልዑካን ቡድን በዶልማባቼ ቤተ መንግስት ተናግረዋል፡፡
[Reporter ]

👍8🔥1🥰1
መርሳ ፋኖዎቿን አስመረቀች!
የመርሳ ከተማ ባለሽርጡ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ሰራዊት ወታደራዊ ስልጠናቸውን አጠናው ዛሬ ተመረቁ!
በአማራ ህዝብ አሰቃቂ ውድመት ያደረሰው የትግራይ ወራሪ ኃይል ያንገፈገፋቸው የመርሳ ባለሽርጥ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ሰራዊት ከሁለትወር በላይ ሲያካሂዱ የቆዩት ስልጠና አጠናቀው በመርሳ ሁለገብ ስታድየም በደማቅ ዝግጅት ዛሬ ተመረቁ፡፡

👍6🔥4👏1😁1
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ መጠን ይፋ አደረገ❗️
🔰የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ መጠን ይፋ አደረገ፡፡
🔰ቦርዱ ዛሬ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ያካሄደ ሲሆን÷ ለፓርቲዎች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ መጠንን ይፋ አድርጓል።
🔰የገንዘብ ድጋፉ ከዚህ ቀደም በፀደቀው መመሪያ ላይ በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት የተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
🔰ለ19 አገር አቀፍ እና 35 የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በድምሩ ለ54 ፓርቲዎች እስከ 789 ሺህ ብር የሚደርስ ድጋፍ እንደሚደረግ ከምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ፍርድ ቤት ዛሬ የአሶሴትድ ፕሬስ ዘጋቢዎች አሚር አማን እና ቶማስ እንግዳ እያንዳንዳቸው በ60 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል።
ሆኖም ችሎቱ ዘጋቢዎቹ ከአገር እንዳይወጡ እገዳ ጥሎባቸዋል። ፖሊስ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት ቢጠይቅም፣ ችሎቱ ግን የእስካሁኑ ምርመራ ለውጥ አላሳየም በማለት ነው የገንዘብ ዋስትናውን የፈቀደው። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ባለፈው ኅዳር ያሰራቸው፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮችን እና ታጣቂዎችን መስክ ወርደው በማነጋገር እና በተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረጽ ወደ ውጭ አገር መረጃዎችን ልከዋል በማለት ነበር።

👍6
❗️ፊንላንድ ኮሌጅ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሰው ተቋም ምንም አይነት የእውቅና ፈቃድ የለውም ተባለ
ፊንላንድ ኮሌጅ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሰው ተቋም ምንም አይነት የእውቅና ፈቃድ እንደሌለው የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ።
ፊንላንድ ኮሌጅ በሚል ስያሜ የእውቅና ፈቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ ያቀረበው ተቋሙ፣ ከባለሥልጣኑ የዕውቅና ፈቃድ ሳያገኝ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በአረካ ከተማና በሌሎች የክልሉ ከተሞች በርካታ ተማሪዎችን መዝግቦ እያስተማረ መሆኑ በተደረገው ማጣራት መረጋገጡን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገረሱ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
ባለሥልጣኑ በፊንላንድ ኮሌጅ በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ የሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ ተቀባይነት የሌለውና ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማስከበር እርምጃ በመውሰድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስቧል፡፡

የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚመለስ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የራያ ሕዝብ ተወካዮች ላቀረቡት ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የራያ ሕዝብ ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የራያ ሕዝብ ተወካዮች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የራያ ሕዝብ የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ያቀረቡ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ ምላሽ ሳያገኝ እንደቆየ አውስተዋል፡፡
ተወካዮቹ አያይዘውም የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ሞትን ጨምሮ ሌሎች በደሎች በራያ ሕዝብ ላይ ሲፈፀም የቆየ እንደነበረና በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ራያዎች ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ እና ንብረታቸውም ሲወድም እንደነበረ ተወካዮቹ በአካል ቀርበው አስረድተዋል፡፡
ጥያቄአችን ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ሲሉም ተወካዮቹ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሸገር በበኩላቸው ጥያቄውን ላቀረቡት የራያ የማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የራያ ሕዝብ ጥያቄው በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደ ከዚህ በፊቱ የሕዝብን ጥያቄ በኃይል ለማፈን የሚደረግ አላስፈላጊ ጫና ከሕገ መንግስቱ የሚቃረን ስለሆነ ተቀባይነት እንደሌለው የጠቆሙት አፈ ጉባዔው የሕዝብ ጥያቄ ሕግን መሠረት በማድረግ ምላሽ በመስጠት ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

👍24