አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.8K subscribers
15.7K photos
350 videos
21 files
2.94K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
🌧 ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ - ዝናብ ጥሏል 🌧

በታሪኳ እጅግ አስከፊ በሆነ ድርቅ ላይ የምትገኘው እና 4.5 ሚሊዮን ህዝቧ ለረሃብ የተጋለጠው ጎረቤታችን ሶማሊያ ዝናብ አግኝታለች።

በሀገሪቱ ብዙ ክፍሎች ላይ ዝናብ መጣሉን የሚገልፁ ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው።

አሁንም ከፍተኛ ደመና በተለያዩ ቦታዎች የሚታይ ሲሆን ብዙ ቦታዎች ተጨማሪ ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ይገመታል።

ዝናቡ ሲጠፋ የድርቅ አደጋ ፤ ዝናቡ ሲገኝ ደግሞ የጎርፍ አደጋው ያሳስባልና ነዋሪዎች በጎርፍ ከሚመጣው አደጋ እንዲጠነቀቁም መልዕክት እየተላለፈ ነው።

የሀገሬው ሰው በማህበራዊ ሚዲያው #አልሃምዱሊላህ እያለ ለፈጣሪው ምስጋናን እያቀረበ ነው።

ቪድዮ - ሃሩን ማሩፍ

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
👍1
◌ቀጣዩ የ2014 የዩኒቨርስቲ መግብያ ፈተና ( 12ኛ ክፍል ኢንትራንስ) ተማሪዎች ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል የተማሩትን የትምህርት ይዘት እንደሚያካትት የመረጃ ምንጮች ያመላከታሉ!

➛ከትምህርት ሚኒስተር ተጨማሪ መረጃ እየተከታተልን እናሳውቃችኋለን።

@ethiopian_reporter
@ethiopian_reporter
#Update
#የአማራ_ተማሪዎች_ማህበር

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ በሁሉም የአማራ ክልል ከተሞች ዛሬ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የሰላማዊ ሰልፍ ሳይካሄድ ቀርቷል።

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ም/ቤት ሰልፉ እውቅና እንዳልተሰጠው ገልጾ ነበር፡፡

በክልሉ በርካታ ከተሞች የጸጥታ ኃይል በመመደቡ ሰልፉ በተጠበቀው መልኩ አለመካሄዱን ሰምተናል፡፡

ይሁን እንጂ በተወሰነ መልኩም ቢሆን በባሕር ዳር፣ ደብረ ታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን እና ቆቦ ከተሞች የፈተናው ውጤት በድጋሜ እንዲታይ የሚጠይቁ ሰዎች ጥያቂያቸውን ዛሬ አሰምተዋል።

በሌላ በኩል ሰላማዊ ሰልፉን የጠራው የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ)፤ ሊቀመንበሩ እሸቱ ጌትነት እና ሌሎች አምስት አባላቱ መታሰራቸውን አሳውቆ ነበር።

ሊቀመንበሩን ጨምሮ አምስት አባላቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከእስር ተፈተዋል።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት በወላጆች፣ በተማሪዎች፣ በመምህራን እና በተቋማት ከፍተኛ ቅሬታና ውዝግብ ማስነሳቱ ይታወቃል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጉዳዩን የሚያጣራ 11 አባላት ያሉት ቡድን ወደ ትምህርት ሚኒስቴር የላከ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ እንዲራዘም ደብዳቤ መጻፉም አይዘነጋም፡፡


https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተጨማሪ የሳተላይት ምስሎች ይፋ ሆነዋል ❗️

⚡️ሩሲያ በዮክሬን ላይ በቀጠለችው ወታደራዊ እንቅሳቃሴዎች ምክንያት የወጡ አዲስ የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዮት የነዳጅ ዴፖ እና የቲቪ ማማን ሲያወድሙ የሚያሳዮ ምስሎች ይፋ ተደርገዋል።

⚡️Maxar's satellite images published on March 24-26 spotlight recent damage to a Ukrainian fuel storage facility in Kalinovka, burning buildings and damage to civilian infrastructure in Kiev, and the battle between Russian and Ukrainian forces for the city of Izyum in eastern Ukraine.

🎬 የምስል ዘገባ 🎬
   
💰 ፓኬጅ ከገዙ 2.64 ብር💰

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
1
የፕሬዝዳንት ባይደን የአእምሮ ጤና ሁኔታ ሊታይ ይገባል ሲል ክሬምሊን አስታወቀ❗️

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በትላንትናዉ እለት ቭላድሚር ፑቲን "በስልጣን ላይ መቆየት አይችሉም" ሲሉ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ሩሲያውያን የራሳቸውን ፕሬዝዳንት ይመርጣሊ ሲል የባይደንን ንግግር ክሬምሊን ውድቅ አድርጓል፡፡የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የባይደንን አስተያየት አስመልክቶ ለሮይተርስ እንደተናገሩት "የሩስያ ፕሬዝዳንት የሚመረጡት ሩሲያውያን ናቸዉ፤ ይህንን ባይደን አይወስኑም" ሲሉ ተናግረዋል።

ባይደንን በዋርሶ ባደረጉት ንግግር በሩሲያ “የአገዛዝ ለውጥ” እንዲደረግ ጥሪ አላቀረቡም ነገር ግን ነጥቡ “ፑቲን በጎረቤት ሀገራት ሆነ በቀጠናዉ ላይ ስልጣን እንዲጠቀሙ አይፈቀድላቸዉም” የሚል ንግግር ነዉ ሲል ዋይት ሀዉስ አስታዉቋል፡፡ፔስኮቭ ለኋይት ሀውስ ማብራሪያ ምላሽ ለመስጠት ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ባለፈው ወር የሩሲያው ፕሬዝዳንት ዩክሬንን ለመዉረር ትዕዛስ ካሳለፉ በኋላ ባይደን በፑቲን ላይ ግላዊ ጥቃቶችን መፈጸም አጠናክረዉ ቀጥለዋል፡፡ክሬምሊን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት የአእምሮ ጤና ሁኔታ መጠየቅ ያሻል ሲል አስታዉቋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ባይደን ፑቲንን “የጦር ወንጀለኛ” እና “ገዳይ አምባገነን” በማለት መፈረጃቸዉ ይታወሳል፡፡

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
#Breaking_news ❗️

በእስራኤል ጥቃት ተፈፀመ ❗️

በእስራኤል በሃደራ ከተማ ያልታወቁ ሰዎች #ተኩስ መክፈታቸው በምስል በወጣ መረጃ ተደግፎ ተዘግቦል። እስካሁን ሁለት ፖሊሶችን ጨምሮ አምስት ሰዎች ባጠቃላይ መቁሰላቸው ተዘግቧል። የሽብር ጥቃትን ከከፈቱን ሁለት በእስራኤል ህግ አስከባሪዎች ተመተው መገደላቸው ተዘግቧል።

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
👍3
ተዋናይ ዊል ስሚዝ ኦስካርስ በተሰኘው የፊልም ጥበብ የሽልማት መድረክ የሚስቱን ስም አንስቶ ያብጠለጠለውን ታዋቂውን ኮሜዲያን ክሪስ ሮክን በጥፊ ተማታ።

ክሪስ ሮክ፤ የዊል ስሚዝ ሚስት ጄዳ ፒንኬት ስሚዝን የፀጉር ቁርጥ በቀልድ ወረፍ ካደረገ በኋላ ነው ይህ የተከሰተው።ዊል ስሚዝ ከመቀመጫው በመነሳት ወደ መድረኩ አቅንቶ ክሪስ ሮክን በጥፊ አጋጭቶ ሲመለስ ብዙዎች ጉዳዩ ቀልድ ነው ብለው አስበው ነበር።ነገር ግን ወደ ወንበሩ ከተመለሰ በኋላ "የሚስቴን ስም በ. . . አፍህ አታንሳ" ብሎ ሲጮህ ነው ብዙዎች ተዋናዩ ማምረሩን የተረዱት።

ስሚዝ ከዚህ ብዙዎችን ካስበረገገ ድርጊት በኋላ የኦስካር ሽልማቱን ሲያነሳ ለድርጊቴ ይቅርታ በሉኝ ብሏል።"አካዳሚውን [ኦስካር ሸላሚው ኮሚቴ] እንዲሁም ለሽልማት የታጩ የተውኔት አጋሮቼን ይቅርታ መጠየቅ እሻለሁ" ሲል ተማፅኗል።

ዊል ስሚዝ፤ ኪንግ ሪቻርድ በተሰኘው ፊልም ላይ የቴኒስ ከዋክብቱን ቬነስና ሰሪና ዊሊያምስ አባት ሆኖ በመተወኑ ነው በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለስም የከበደውን የኦስካር ሽልማት ያገኘው።"ጥበብ የሕይወት ቅጂ ናት።ልክ እንደ ተወንኩት ሪቻርል ዊሊያምስ የእብደት ሥራ ሠርቻለሁ። ነገር ግን ፍቅር የእብድ ሥራ እንድትሠሩ ያደርጋችኋል።"

ባለቤቱ ፒንኬት ስሚዝ ከዚህ በፊት የፀጉር መነቀል የሚያስከትል አለፔሲያ የተሰኘ በሽታ እንዳለባት ተናግራ ነበር።የዊል ስሚዝ ጥፊ ሰላባ የሆነው ክሪስ ሮክ በሁኔታው እጅግ ተደናግጦ "በቴሌቪዥን ታሪክ እጅግ አስደናቂውን ክስተት ታድመናል" ሲል ተደምጧል።

Via Reporter

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
በሶማሌ ክልል የተከሰተውን ድርቅ መቋቋም እንደተቻለ የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

በሶማሌ ክልል ላለፉት ወራት በዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተው ድርቅ በተለይ በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ የክልሉ መንግስት ድርቁን ለመቋቋምና ህዝብና እንስሳትን ለመታደግ በሰራው ስራ ድርቁን መቋቋም እንደቻለ ገልጿል፡፡

አሁን ላይ የድርቅ አደጋ ጊዜ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝና በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች የበልግ ዝናብ መጣል መጀመሩን የገለጸው የክልሉ መንግስት፤ ድርቁን ለመቋቋም እንደተሰራው ሁሉ፣ በድህረ ድርቁ ወቅትም ጠንካራ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን ትላንት አመሻሹን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል፡፡

በክልሉ አካባቢዎች መዝነብ ከጀመረው የበልግ ዝናም በድርቁ የተጎዱ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግና በወንዞችና ተፋሰስ አከባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የጎርፍ አደጋዎች፣ ወረርሽኝና ተዛማጅ ጉዳዮች ለመከላከል ጠንካራ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውንም አክሏል፡፡

የክልሉ አደጋ ስጋት አመራርና የጤና ቢሮ አመራሮች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ወደ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በመውረድ አስፈላጊው ትብብርና ድጋፍ እንዲሰጡ የክልሉ መንግሥት ኮሚቴዎችን አዋቅሮ ማሰማራቱም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

የድርቅ አደጋውን ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥትና ህዝብ ጎን በመሆን የክልል መንግስታትና ህዝቦች፤ ባለሀብቶች፣ ግብረሰናይ ድርጅቶች እንዲሁም የፌዴራል መንግሥት ላደረጉት ድጋፍና ትብብር የክልሉ መንግሥት ምስጋና ማቅረቡን ከክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
👍1
በአማራ ክልል በጦርነቱ ጉዳት በደረሰባቸው አራት ዞኖች የሚገኙ ከ60 ሺህ በላይ ህጻናትን መንከባከብ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ!

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋና ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዞኖች የሚገኙና በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ከ60 ሺህ በላይ ህጻናትን መንከባከብ የሚያስችል ፕሮጀክት በደሴ ከተማ ይፋ ተደርጓል።ፕሮጀክቱ የአንድ ዓመት መርሃ ግብር ሲሆን፤ በአራቱ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች ላይ ይተገበራል ተብሏል።

ፓዝ ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ባደረገው የዳሰሳ ጥናት በአማራ ክልል ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ህጻናት በጦርነቱ ሳቢያ ክፉኛ መጎዳታቸውን ማረጋገጡን የፓዝ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ትርሲት ግርሻው ተናግረዋል። በአካባቢዎቹ የተደረገው ጦርነት በበርካታ ህጻናትና እናቶች ላይ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ማድረሱን የጠቆሙት ዳይሬክተሯ፤ መርሃ ግብሩ ከሰሜን ወሎ ዞን ግዳንና ራያ ቆቦ ወረዳዎች፣ ከደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ፣ ከዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዞን ሰቆጣ ዙሪያና ዳህና ወረዳዎች እንዲሁም ከሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ የሚተገበር መሆኑን አስረድተዋል።

በዚህም 60 ሺህ የሚደርሱ ህጻናትና ከ15 ሺህ በላይ የሚያጠቡና ነፍሰ ጡር እናቶች በቀጥታ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል። ከ446 ሺህ በላይ ህዝብ ደግሞ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።ይህ የቅድመ ልጅነት ዘመን እንክብካቤ መርሃ ግብር 500 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን፤ የገንዘብ ድጋፉን ያደረገው ቢግ ዊን ፊላንትሮፊ የተባለ ግብረ ሠናይ ድርጅት ነው።

በመሆኑም በአማራ ክልል የከፋ ጉዳት የደረሰባቸው በአራት ዞኖችና ስድስት ወረዳዎች የሚገኙ ህፃናትና እናቶች በዚሁ የክብካቤ በመርሐ ግብር መካተታቸውን ተናግረዋል።የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ያደታ፤ በኢትዮጵያ 59 በመቶ የሚሆኑ ህፃናት በዕድሜያቸው ልክ መድረስ ከሚገባቸው አካላዊና አዕምሯዊ ዕድገት ያልደረሱ ስለመሆናቸው ገልጸዋል።

ፓዝ ኢትዮጵያ የጀመረው የቅድመ ልጅነት ዘመን፣ የሚያጠቡና ነፍሰ ጡር እናቶች ክብካቤ መርሃ ግብር ውጤታማ እንዲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ መጠቆማቸውን ከደቡብ ወሎ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።በፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ወሎ ዞን ም/ አስተዳዳሪ ተስፋ ዳኛው በበኩላቸው፤ ፓዝ ኢትዮጵያ የቅድመ ልጅነት ዘመን እንክብካቤው ህፃናት በአካላቸው የጠነከሩ በአዕምሯቸው የጎለበቱ ሆነው እንዲያድጉ የሚያስችል በመሆኑ፤ በሚመለከታቸው የመንግስት መዋቅሮች ተገቢው ድጋፍና ክትትል ይደረጋለታል ብለዋል።

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
👍1
#AmharaRegion

በጦርነት ምክንያት በአማራ ክልል ፤ ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ባለው እጅግ የከፋ ችግር በርካታ ህፃት እና እናቶች ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፤ ይሄ በተደጋጋሚ ተገልጿል።

በችግር ላይ ላሉት ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም ካለው የከፋ ሁኔታ አንፃር ምንም ነው።

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለሴቶች እና ሕጻናት 3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት እና ለ300 እናቶች ደግሞ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አሚኮ ዘግቧል።

እንዲሁም በክልሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እስካሁን 200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ቢያደርጉም ከተከሰተው ችግር ስፋት ጋር የሚጣጣም ሆኖ አልተገኘም።

ችግሩንም መፍታት አልተቻለም።

መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፣ ባለሃብቶች በችግር ላይ ለወደቁ ወገኖች አሁንም ድጋፋቸው አጠናክሮ እንዲቀጥሉ እና ሕጻናትን እና እናቶችን መታደግ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።

ፎቶ ፦ አሚኮ

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
👍2
"ከኦነግ ጋር በጥምረት ሆነን ወደ ምርጫ ልንገባ ስንል የውላችንን ወረቀት ቀደው እስር ቤት ወረወሩን፣ብልፅግና ኡሁንም እንደ ህወሃት ሊከፋፍለን እየሞከረ ነው፣ይህ ለህወሃትም አላዋጣትም"

ጀዋር መሀመድ በኦፌኮ ጠ/ጉባኤ ላይ ከተናገረው የተወሰደ

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
ከፍተኛ ስርቆት በመዲናችን አዲስ አበባ ተፈጽሟል!

🔰ስርቆቱ የተፈጸመው የፌደራል ፖሊስ በለበሱ ሰዎች ነው ተብሏል

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጎሮ ሰፈራ ልዩ ቦታው ፖስታ ቤት መቲ ጋራዥ አካባቢ በቀን 11፣ 2014 ዓ.ም የቻይና ነጋዴዎች ተከራይተው ይሰሩበት የነበረው መጋዘን ላይ ከፍተኛ ስርቆት የተፈጸመው፡፡

በዚህ ስርቆት 418 ያህል ቴሌቪዥኖች የተሰረቁ ሲሆን ቁጥራቸው የማይታወቅ ላፕቶፕ ኮምፒተሮች የመኪና ባትሪዎች እንደዚሁም 63ሺህ ጥሬ ገንዘብ አብሮ መሰረቁን ነው ኢትዮ ኤፍ ኤም ያገኝው መረጃ የሚጠቁመው፡፡

እነዚህ ነጋዴዎች መጋዘኑን የተከራዩት ከአንድ ወር በፊት የነበረ ሲሆን ከቻይና በርካታ እቃዎችን እያስመጡ ለነጋዴዎች ያከፋፍሉበታል የነበረ መጋዘን ነው፡፡
አቶ መኮንን ድርጊቱን ያቀነባበሩት የጥበቃ ሰራተኞች ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ያላቸውን ግምት ያስቀመጡ ሲሆን አሁን ላይ እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል በለዋል፡፡

ቃላቸውን ለፖሊስ የሰጡት የጥበቃ ሰራተኞች በበኩላቸው ስርቆቱ የተፈጸመው የፌደራል ፖሊስ በለበሱ ሰዎች ነው ያሉት አቶ መኮነን ፣ከድርጊቱ መፈጸም በላይ የጸጥታ አካላት የሰጡት ምላሽ እንዳሳዘናቸው ነግረውናል፡፡

የቤት አከራዩ አቶ መኮንን ስርቆቱ በተፈጸመበት እለት መብራት ጠፍቶ እንደነበረ እና የአይሱዚ መኪና መጋዘን ውስጥ ገብቶ መጫኑን በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ጥቆማቸውን እንዳደረሱዋቸው ነግረውናል፡፡

via ፦ Ethio fm

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
በሳምንቱ መጨረሻ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተገለጸ!!

በአዲስ አበባ በሁለት ቀናት ውስጥ በተከሰቱ የእሳት አደጋዎች በንበረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ እሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡
አንደኛው የእሳት አደጋ የደረሰው በኦሮምያ ልዪ ዞን አሸዋ ሜዳ በንግድ ሱቆች ላይ የደረሰው ነው ተብሏል፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት አቶ ንጋቱ ማሞ እንደነገሩን ሌላኛው የእሳት አደጋ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት አወልያ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በአንድ መኖርያ ቤት ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሶስተኛው የእሳት አደጋ የተከሰተው ደግሞ በትላንትናው እለት በኦሮሚያ ልዩ ዞን አሸዋ ሜዳ በተመሳሳይ በንግድ ሱቆች ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ ሲሆን በነዚህ አደጋዎች ምክንያትም ከ2ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል ብለውናል፡፡

አደጋዎቹን ለመቆጣጠር 40ሺህ ሊትር ውሀ አገልግሎት ላይ መዋሉንም አቶ ንጋቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን እና ቭላድሚር ፑቲን ቀጣዩን የሩሲያ-ዩክሬን ድርድር በቱርክ ለማካሄድ ተስማሙ!!

የቱርክ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ሁለቱ መሪዎች እሁድ እለት የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን እና ስለ ሩሲያ – ዩክሬን ግጭት ወቅታዊ ሁኔታ እና የድርድር ሂደት መወያየታቸውን አስታውቋል፡፡

በውይይታቸውም ቀጣዩ የሩሲያ እና የዩክሬን የድርድር ሂደት በቱርክ ኢስታምቡል እንዲካሄድ ስምምነት ላይ መድረሳቸውም ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ለሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን፥ ቱርክ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የተኩስ አቁም እና የሰላም ስምምነት እንዲደረግ እና በአካባቢው ያለው የሰብአዊ ሁኔታ መሻሻል እንዳለበት ገልጸውላቸዋል።

የዩክሬን ተደራዳሪ ልዑካን ቡድን አባል የሆኑት ዴቪድ አራካሚያ ቀጣዩ ዙር የዩክሬን እና የሩሲያ የሰላም ድርድር በሚቀጥለው ሳምንት በቱርክ እንደሚካሄድ ግለጻቸውን ሺንዋ በዘገባው አስነብቧል፡፡

የሩሲያ ተደራራደሪ ቡድን መሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ በበኩላቸው የፊት ለፊት ድርድሩ በቀጣይ ሳምንት እንደሚደረግ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

የዩክሬን እና የሩሲያ ልዑካን ከየካቲት 28 ጀምሮ በቤላሩስ ሶስት ዙር የሰላም ድርድር ያደረጉ ሲሆን አራተኛውን የሰላም ድርድር ደግሞ በቪዲዮ ኮንፈረንስ አካሄደዋል።

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
በኤሌክትሪክ መስመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት በጭስ አባይና አካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋረጠ!

ከባህር ዳር ወደ ጭስ አባይ በሚሄደው 15 kV የኤሌክትሪክ አስተላለፊ መስመር በተለምዶ ቆሸ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 3 የእንጨት ምሰሶዎች በመጋዝ ቆርጦ በመጣል 720 ሜትር ባለ 95 ሚ.ሜ አልሙኒየም ሽቦ በሌቦች መሰረቁን የባህር ዳር ዲስትሪክት ኦፐሬሽን ስራአስኪጅ አቶ ውባለ አብጤ ገልፀዋል፡፡

በተፈፀመው ስርቆት ምክንያት በጭስ አባይ፣ሰባት አሚት ፣አንዳሳ እና በአካባቢው ባሉ ከተሞች ከ 18/7/2014 ዓ.ም ሌሊት 7፡40 ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል፡፡

ይህ መጋቢ መስመር ከላይ ከተገለፁት ከተሞች በተጨማሪ ለጥበበ ጊዮን ሪፈራል ሆስፒታል እና ለባህርዳር ማረሚያ ቤት ኤሌክትሪክ የሚሰጥ ሲሆን ሆስፒታሉና ማረሚያ ቤቱ ዛሬ በ19/7/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡30 ጀምሮ ጊዜያዊ መፍትሄ በመስጠት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

የባህር ዳር ዲስትሪክት ሰራተኞች አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ መሆናቸውንና ፤ ጉዳዩን የባህር ዳር ከተማ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ እየተከታተለውና አጥፊዎቹን ለመያዝ ጥረት እያደረገ መሆኑን የባህርዳር ዲስትሪክት ኦፐሬሽን ስራአስኪጅ አቶ ውባለ አብጤ ገልፀዋል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባበሰ ጥቷል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ እና በየደረጃው የሚገኝ የፀጥታ አካል ጉዳዩን በትኩረት በመመልከት በአካባቢው ለተዘረጉ የኤሌክትሪክ አውታሮች ጥበቃ እንዲያደርግና አጠራጣሪ ጉዳዮችንም ሲመለከት ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትና ለተቋማችን ጥቆማ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡

የአማራ ኤሌክትሪክ ኃይል

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter
👍1
ኢትዮ ሱዳን ድንበር ጦርነት
ዛሬ ሰባተኛ ቀኑን የያዘው የኢትዮ ሱዳን ድንበር ጦርነት በኢትዮጵያ ጦር በኩል ጥሩ ድሎች እየተገኘ ሲሆን ዛሬ አለው በሚባል አካባቢ ከሶስት በላይ የህወሓት ታጣቂዎች የሰሩት የኮንክሪት ምሽግ በከባድ መሳሪያ ከጥቅም ውጪ ሆኗል ተብሏል። የኢትዮጵያ ሰራዊት በረከትን ለመቆጣጠር በቅርብ ርቀት እንደሚገኝ ታውቋል፣ከ11 በላይ የህወሓት ታጣቂዎችም እጅ ሰጥተዋል። በርካታ መካናይዝድ ጦራቸውም ከጥቅም ውጪ ሆኗል፣በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ መንግሥት ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

https://t.me/ethiopian_reporter
https://t.me/ethiopian_reporter