አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.3K subscribers
18K photos
443 videos
23 files
3.07K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አዲሱ የሲቪል ሰርቪስ መመሪያ‼️
18 መመሪያዎች፣ 70% ማለፊያ እና የ2 እርከን ደመወዝ ጭማሪ፡ አዲሱ የሲቪል ሰርቪስ ረቂቅ

*የመንግስት ሰራተኞች በስራ ለመቆየት እና የደረጃ እድገት ለማግኘት ምዘናዎችን እንዲያልፉ የሚያስገድዱ መመሪያዎች መዘጋጀታቸው ተገለጸ።የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግስት ሰራተኞችን በባህሪ፣ በክህሎት እና በአገልግሎት ለመመዘን የሚያስችሉ 18 መመሪያዎችን በቅርቡ አጽድቆ ወደ ስራ እንደሚያስገባ አስታውቋል።

መመሪያዎቹ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 ለማስፈጸም የተዘጋጁ ሲሆን ፦

👉የመንግስት ሰራተኞች የሰው ሃይል እቅድ አዘገጃጀትና አፈጻጸም፣

👉የመንግስት ሰራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ፣

👉የመንግስት ሰራተኞች የብቃት ምዘናና እውቅና፣

👉የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል ማሻሻያ አበል እና ክፍያ አፈጻጸም መመሪያዎች ከተዘጋጁት 18 ረቂቆች መካከል ይጠቀሳሉ ተብሏል።

በመመሪያው ረቂቅ ድንጋጌ መሰረት ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ በያዘው የስራ መደብ ላይ ለመቆየት፣ ከፍ ወዳለ የስራ ደረጃ ለማደግ፣ ከአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ወደ ሌላ ለመዘዋወርም ሆነ በአዲስ ለመቀጠር የግድ የቴክኒካልና የባህሪ ብቃት ምዘናዎችን መውሰድ ይጠበቅበታል።

መመሪያዎቹ ለውይይት በቀረቡበት መድረክ ላይ ማብራሪያ የሰጡት በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአስተዳደር ፍርድ ቤት ተጠሪ ዳኛ አቶ መስፍን ረጋሳ ማንኛውም ሰራተኛ በስራው ላይ ለመቆየት በባህሪያዊ፣ በቴክኒካል እና በተግባር ምዘናዎች በእያንዳንዳቸው ቢያንስ 70 ከመቶ ውጤት የማምጣት ግዴታ እንዳለበት ገልጸዋል።የባህሪ ምዘናው በዘልማድ አስተያየት ሳይሆን በሳይንሳዊ መስፈርቶች እንደሚከናወን የገለጹት አቶ መስፍን "የሚመዘኑት በዘልማድ ሃሳብ የምንሰጥባቸው 'ይቆጣል፣ ይበሳጫል' የመሳሰሉት ሳይሆኑ፣ በሳይንስ ተረጋግጠው የተለዩ ባህሪዎች ናቸው" ብለዋል።

አንድ ሰራተኛ በባህሪው እንዴት ሊመዘን ይችላል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ የሰጡት አቶ መስፍን ፦

"ለምሳሌ በአንድ መንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ለብቻ በመስራት የሚገኝ ውጤት የለም ባይባልም ግን በጣም አነስተኛ ውጤት ነው አንድ ሰራተኛ በቡድን የመስራት ችሎታን ማሳየት አለበት፤ ለዛም ጥረት ማድረግ አለበት። ምክንያቱም በቡድን ብዙ ስራዎችን መስራት ይቻላል፣ መተጋገዝ ይቻላል፣ እውቀትን ማሻገር ይቻላል ፣ ተተኪን ማፍራት ይቻላል ስለዚህ አንዱ በቡድን የመስራት ችሎታው አለው የለውም የሚለው የሚለካ፣ የሚታይ፣ የሚሰራ፣ ክፍተትንም ለማየት የሚያስችል የመመሪያ ድንጋጌ ነው ያለው" ብለዋል።

አክለውም "በቡድን በመስራት በሳይንስ ላይ በተመሰረተ ሁኔታ ክፍተት አለ የለም የሚለው ማጣራት ይቻላል የሚጎድል ክፍተት ካለ ያ ስልጠና ይሰጠዋል ምክንያቱም የቡድን ስራ ወይም ደግሞ በእንግሊዘኛው 'ቲም ቢልዲንግ' የሚለው የሳይንስ መንገድ ተተንትነው የተጻፉ ጽሁፍ እውቀቶች ስላሉ በዛ መሰረት እራሱን እንዲገነባ ይደረጋል ተምሳሌት፣ አርአያ መሆን፤ ይሄም ማንኛውም ሰው በስራ ልምዳችን አስተያየት ሊሰጥበት የሚችል ነው" ብለዋል።

በተጨማሪ "በህዝብ አገልግሎት ሲሰጥ ምንድነው የሚታዩት ሁኔታዎች? ስነ ስርዓቱ፣ ስነምግባሩ፣ ታዛዥ መሆኑ፣ የሚቀርቡለትን ሰነዶች የማረጋገጥ ችሎታው፤ እነዚህን በተመለከተ ማጣራት፣ መገምገም የሚቻል ነው"በማለት አስረድተዋል።

በተጨማሪም እስከ ወረዳ ድረስ ባሉ የሙያና የስራ መደቦች ላይ ምዘናውን ላለፈ ሰራተኛ የሚሰጠው የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለአምስት ዓመታት እንደሚያገለግል ተገልጿል።

ሰራተኛው ለመመዘን በመጀመሪያ ዙር የሚወስደውን ፈተና ማለፍ ካልቻለ የሚያሰራው ተቋም እንደገና በ6 ወር ውስጥ ሰራተኛውን አዘጋጅቶ ፈተና የመስጠት ግዴታ እንዳለበት በረቂቁ ላይ ሰፍሯል ተብሏል። አንድ ሰራተኛ ፈተናዎችን ማለፍ ካልቻለ እስከ ስንት ጊዜ ድረስ የመመዘኛ ፈተናን ይወስዳል የሚለውን በተመለከተ ግን መመሪያው በግልጽ አላብራራም።

የሰራተኞች ምዘና ተግባራዊ የሚደረገው ሰራተኛን ለመቀነስ ወይም ለማባረር ታስቦ ነው በሚል ለሚነሱ ቅሬታዎች ምላሽ የሰጡት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መኩሪያ ሃይሌ(ዶ/ር) ዋናው ጉዳይ ሰራተኛ መቀነስ እንዳልሆነ አብራርተዋል።ኮሚሽነሩ ሲያብራሩም "የኢትዮጵያ የህዝብ ብዛት 120 ሚሊዮን ሲሆን አሁን ያለው የመንግስት ሰራተኛ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ነው ገና ብዙ የመንግስት ሰራተኛ ትፈልጋለች ኢትዮጵያ ዋናው ቁም ነገር ሰራተኛው ተልዕኮውን በሚሸከም ደረጃ መሆን አለበት ስራውን መስራት የማይችል ከሆነ ችግሩ እዛ ጋር ይመጣል ስራውን መስራት የሚችል ሰራተኛ ግን እንደገና በብዙ ሚሊዮን የሚቀጠርበት እድል ነው እየመጣ ያለው" ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በምዘናው ከሚያስመዘግቡት ውጤት ጋር እንደሚያያዝ ተመላክቷል።

በዚሁ መሰረት በሶስቱም መመዘኛዎች ከ90 ከመቶ በላይ ላስመዘገበ ሰራተኛ እንደ የደመወዝ ስኬሉ ሁለት የእርከን ጭማሪ የሚደረግለት ሲሆን፤ ከ75 እስከ 90 ከመቶ ላመጣ ደግሞ የአንድ እርከን የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግለት በረቂቅ መመሪያው ተደንግጓል።ረቂቅ መመሪያው የሙያ እጥረት በሚታይባቸው የስራ መስኮች ላይ የጋራ ቅጥር እንዲፈጸም እድል የሚሰጥ አሰራርንም አካቷል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15👍6
ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ የነበሩ 6 ቁልፍ የህወሓት አመራሮች ተያዙ‼️
የቡድኑ አመራሮች በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም በራማ አካባቢ ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ ያሰቡ የቀድሞ የህወሃት ስድስት ቁልፍ አመራሮች ከተደበቁበት በርሃ በተሰጠ ጥቆማ መሠረት በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።

እነሱም
1ኛ = ተወልደ ብርሃን የክልል ሰላም እና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ የነበረ፤
2ኛ = ገ/ፃድቃን ገ/ስላሴ የክልሉ የሚሊሺያ ዘርፍ ሃላፊ የነበረ፤
3ኛ = ገ/ኪዳን ኪዳኑ የክልሉ የፀጥታ ዘርፍ መረጃ ሃላፊ የነበረ፤
4ኛ = አባዲ ገብሩ የክልል ፀጥታ ዘርፍ ምክትል ሃላፊ የነበረ፤

5ኛ = ወልዱ መስፍን የክልሉ ሚሊሺያ ፅህፈት ቤት ሠራተኛ የነበረ፤
6ኛ = አማኑኤል ዘርዑ ሹፌር ሲሆኑ በመከላከያ ተይዘዋል።
እነኝህ ሲቪል አመራሮች 04 ክላሽ፣ 05 ሽጉጥ፣ 01 ሳታላይት ስልክ እና 134,000 ( አንድ መቶ ሠላሳ አራት ሺህ ብር) ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤18👍11🤪3
🎈CMC ከሳፋሪ ትምህርት ጀርባ አዲስ ሳይት ከቴምር ፕሮፐርቲስ

☎️ ለበለጠ መረጃ 09-82-15-16-64 ይፍጠኑ ።

     ✅  100% ለከፈለ 30% በነፃ ነው

👉 ስቱዲዮ ( ቡልጋሪያ እና አዋሬ ላይ)
👉 ባለ 1 መኝታ 73 ካሬ
👉 ባለ 2 መኝታ 112 እና 123 ካሬ
👉 ባለ 3 መኝታ ከ 125 ካሬ እስከ 145 ካሬ

ዋጋ እና አከፋፈል
☑️ስቱዲዮ 40 ካሬ
          ጠቅላላ ክፍያ = 5 ሚሊዮን ብር
       ቅድመ ክፍያ 20%= 1 ሚሊዮን ብር
   🔑 100% ለሚከፍል=  3.5 ሚሊዮን ብር

☑️ ባለ 1 መኝታ 73 ካሬ
          ጠቅላላ ክፍያ = 7.6 ሚልዮን ብር
        ቅድመ ክፍያ 20% = 1.5 ሚልዮን
    🔑100% ለሚከፍል=5.3 ሚሊዮን ብር

☑️  ባለ 2 መኝታ 112 ካሬ
         ጠቅላላ ክፍያ = 11.7 ሚልዮን ብር
       ቅድመ ክፍያ 20% = 2.3 ሚልዮን ብር
   🔑100% ለሚከፍል=  8.2 ሚሊዮን ብር

☑️  ባለ 2መኝታ 123 ካሬ
       ጠቅላላ ክፍያ = 12.9 ሚልዮን
       ቅድመ ክፍያ 20% = 2.5 ሚልዮን ብር
🔑100% ለሚከፍል =  9 ሚሊዮን ብር

☑️ ባለ 3 መኝታ 125 ካሬ
     ጠቅላላ ክፍያ= 13.1 ሚሊዮን ብር
       ቅድመ ክፍያ =  2.6 ሚሊዮን ብር
🔑100% ለሚከፍ = 9.1 ሚሊዮን ብር

☑️ ባለ 3 መኝታ 145 ካሬ
         ጠቅላላ ክፍያ= 15.2 ሚሊዮን ብር
          ቅድመ ክፍያ = 3 ሚሊዮን ብር
🔑100% ለሚከፍል= 10.6 ሚሊየን ብር

     ቀሪ ክፍያ
👉 ያለ ምንም ዋጋ ጭማሪ
👉 ከወለድ ነፃ አከፍፈል
👉 በግንባታ ሂደት የሚከፈል

WhatsApp=https://wa.me/message/Z5LFLDJBTZUDK1

Telegram = @Temerr34

   ☎️ 09-82-15-16-64
👍4❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«የኢትዮጵያ የባህር ኃይል አዛዥ አሰብ በሰላም ካልተቻለ በኃይል ጭምር እንደሚመለስ ገለጹ»

​የኢትዮጵያ የባህር ኃይል አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲ እና በሰላማዊ መንገድ የምታደርገው ጥረት የማይሰራ ከሆነ፣ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የቀይ ባህር በር በኃይል ጭምር ወደ እናት ሀገሩ በመመለስ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ማረጋገጥ የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቀዋል።

​አዛዡ አክለውም ሕዝቡ በችግር፣ በረሃብ እና በደኅንነት ዋስትና እጦት እንዲሰቃይ ከማድረግ ይልቅ፣ በማንመርጠው እና በመጨረሻው አማራጭ ጭምር ተጠቅሞ የባህር በር ባለቤት ለመሆን ሠራዊቱ እና ሀገሪቱ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍45🤣17❤12🤔3🤪1😎1
ኢትዮጵያ የታጠቀችውን የአየር መከላከያ ቴክኖሎጂ ኢራንም በአስቸኳይ ጠየቀች‼️
የኢራን ከፍተኛው መሪ ሞጅታባ ኻመኔይ ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የተጻፈ አስቸኳይ የግል ደብዳቤ የያዘ የደህንነት ልዑክ ወደ ሞስኮ መላካቸው የተሰማ ሲሆን፣ የኢራን የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ጸሐፊ ሞህሰን ሪዛኢ በክሬምሊን በተካሄደው ከፍተኛ ውይይት የጠቅላይ መሪውን ደብዳቤ ለአስተላላፊነት አቅርበዋል።

ቴህራን ይህንን የላቀ የኤስ-400 (S-400) የአየር መከላከያ ስርዓት ከሩሲያ በአስቸኳይ እንድታስረክባት በጽኑ እየጠየቀች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፣ ኢትዮጵያ ቀደም ብላ ይህንኑ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እና የሱ-35 (Su-35) የጦር አውሮፕላኖችን ለመታጠቅ ስምምነት በመፈጸም የመከላከያ አቅሟን በከፍተኛ ደረጃ መገንባቷ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

የኢራን አስቸኳይ ጥያቄ የመጣው በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል በኩል በተሰነዘሩት አድማዎች የኢራን የአየር መከላከያ መዋቅር እና ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ከፍተኛ ጉዳት ካስተናገዱ በኋላ ነው።

እነዚህ ጥቃቶች የሀገሪቱን ዝቅተኛ እና ከፍተኛ ከፍታ የመከላከል አቅም ክፍተቶች ያጋለጡ ሲሆን፤ ስትራቴጂካዊ የኑክሌር፣ የወታደራዊ እና የመሪዎች ማዕከላት ለቀጣይ ጥቃቶች ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

ቴህራን ከዚህ ቀደም የቆዩ የሩሲያ ኤስ-300 ባትሪዎችን እና የሀገር ውስጥ አማራጮችን ስትጠቀም ብትቆይም፣ ዘመናዊውን ኤስ-400 ማግኘት የዒላማ ክትትል ክልሏን እንዲሁም የላቁ የጦር አውሮፕላኖችን፣ የክሩዝ ሚሳኤሎችን እና ፈጣን ጦር መሳሪያዎችን የመቋቋም አቅሟን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድገው ታምናለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪24❤12👍9🤔2
ሞያሌ‼️
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ)፤ በሞያሌው ግጭት ሳቢያ ወደ ኬንያ ለተሠደዱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አስቸኳይ ድጋፍ የሚውል 3 ሚሊዮን ዶላር መደበ። ተመድ፤ የገንዘብ ድጋፉ ለነፍስ አድን የሚውል የምግብ፣ የውሃ፣ የመጠለያና የጤና ድጋፍ ለሚያደርጉ የረድኤት ድርጅቶች እንደሚሠጥ ገልጧል። ተመድ፤ እስካሁን ወደ ኬንያዋ መርሳቢት ግዛት የተሠደዱት ኢትዮጵያዊያን ብዛት 50 ሺሕ ይሆናሉ ብሏል። ድርጅቱ የእርዳታ አሠጣጡን የሚያስተባብር ቡድን ወደ ሞያሌ ማሠማራቱን አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13👍4😢4🌚2🙏1🕊1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
 
ነገ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች

✅  ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡30
 
👉 ጎፋ ካምፕ፣ ሀዋርያው ቸርች፣ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን፣  መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ፣ ቆሬ አደባባይ፣ አሚጎ ኮንዶሚንየም፣ ፋና ት/ቤት እና አካባቢው፣
 
👉 ኮተቤ ኮሌጅ፣ መሳለሚያ፣ ኮተቤ አማኑኤል ሆስፒታል፣ ዘርፌ ቦኖ፣ ፍናን ዳቦ፣ ቀርሳ ሚካኤል እና አካባቢው፣
 
👉መነን፣ 6 ኪሎ ዩኒቨርስቲ፣ አሜሪካ ኢምባሲ ያሉ ቤቶች፣ ስፔን ኢምባሲ፣ ሽሮሜዳ፣ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት እና አካባቢው፣

👉አድማስ ዩኒቨርስቲ፣ ቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ፣ አርሴማ ቤተ-ክርስቲያን፣ ቃሊቲ 40/60 ኮንዶኒሚየም፣ ቃሊቲ ገብርኤል፣ ቃሊቲ ማረሚያ እና አካባቢው፣
 
👉 አርሴማ ቤተክርስቲያን፣ ጀርመን አደባባይ፣ ጀሞ ሚካኤል፣ አፍሪካ ህንጻ፣ ዱላ ማርያም፣ አንበሳ ጋራዥ እና አካባቢው፣
 
✅  ከጠዋቱ 2፡30 – 11፡30
 
👉ጎንደር - ደልጊ፣ አዘዞ፣ ሎዛ ቀበሌ፣ ኢንዱስትሪ ቪሌጅ 1፣2፣3፣4፣ ጠዳ እና አካባቢው፣
 
✅ከጠዋቱ 4፡30 – 6፡30
 
👉 ለገጣፎ፣ማሚቴ መንደር፣ 500 መንደር፣ ስታዲየም ጀርባ፣ ወጣቶች አካባቢ፣140፣ ለገዳዲ፣ ለገበሬ፣ 44 ማዞሪያ፣ አበባ መንደር፣ ድሬ ሸኮሩ፣ ለገዳዲ ውሃ ማጣሪያ እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
 
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤6👍3
ግብፅ እና ሱዳን በኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ጉዳቶች ላይ የጋራ ኮሚቴ አቋቋሙ፤ ካሳ እንጠይቃለን አሉ

ግብፅ እና ሱዳን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ነጠላ አሰራር በሁለቱ ታችኛዉ የናይል ተፋሰስ ሀገራት ላይ የሚያደርሰውን ቁሳዊ፣ ማህበራዊ እና አካባቢያዊ ጉዳቶች ለመመዝገብ እና ለመገምገም የጋራ ኮሚቴ ማቋቋማቸውን አስታወቁ።

የግብፅ የውሃ ሀብት እና መስኖ ሚኒስትር ሀኒ ሴዊላም በካይሮ የተካሄደውን የግብፅ እና የሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች የ2+2 ስብሰባ ማጠናቀቂያ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ኮሚቴው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የደረሱ ጉዳቶችን አጠቃላይ ይዘት በመመርመር ከኢትዮጵያ በኩል ካሳ ለመጠየቅ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ሁለቱ ሀገራት በጋራ መግለጫቸው የኢትዮጵያ ግድብ ያለ ህጋዊ አስገዳጅ ማዕቀፍ መሰራቱና መተዳደሩ ለሁለቱ ሀገራት ቀጣይ ስጋት መሆኑን በመጥቀስ፣ ኢትዮጵያ ነጠላ አካሄዷን ትታ ወደ አለም አቀፍ ህግ መርሆች እንድትመለስ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣39❤10😡7👍2💊2
የጤና አዳም ድብቅ ፈውስ እና የጎንዮሽ ጉዳቱ፡ ማወቅ የሚገቡን ወሳኝ እውነታዎች!

በባህላዊ ሕክምናችን እና በቡና ሥነ-ሥርዓታችን ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ጤና አዳም፣ ለብዙ በሽታዎች ፈውስ እንደሆነ ቢነገርለትም በተሳሳተ አጠቃቀም ምክንያት ከፍተኛ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል የሕክምና ባለሙያዎች ያሳስባሉ።

በውስጡ ሩቲን እና ኩዌርሴቲን የተባሉ ጠንካራ ፀረ-ብግነት እና ፀረ-ኦክሲዳንት ውህዶችን የያዘው ጤና አዳም የወር አበባ ቁርጠትን፣ የሆድ ህመምን እና ብግነትን በከፍተኛ ደረጃ የመቀነስ፣ የሆድ ትሎችን ለማስወገድ እና የምግብ መፈጨት ሥርዓትን የማስተካከል ኃይል አለው።

በተጨማሪም የደም ስሮችን ጥንካሬ በመደገፍ የደም ዝውውርን የሚያፋጥን፣ የደም ስኳር መጠንን ለመቆጣጠር የሚያግዝ እና ከሰውነት ውስጥ አላስፈላጊ ትርፍ ፈሳሾች እንዲወጡ የሚያደርግ ተክል ነው።

ጤና አዳም ከፍተኛ የመፈወስ አቅም እንዳለው ሁሉ ከፍተኛ የጎንዮሽ ጉዳቶች ስላሉት ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል። በተለይ እርጉዝ እናቶች የማህጸን ጡንቻዎችን ስለሚያናውጥ እና ፅንስ የመጨናገፍ አደጋ ስለሚያስከትል በፍጹም መጠቀም የለባቸውም።

እንዲሁም ጡት የሚያጠቡ እናቶች እና ሕፃናት ወደ ጡት ወተት ስለሚቀላቀል እና መመረዝን ሊያስከትል ስለሚችል አይመከርም። የተጠናከረ የጤና አዳም ዘይት ከፍተኛ የመመረዝ ባህሪ ስላለው የጉበት እና የኩላሊት ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ሲሆን ያልተጣራ ፈሳሹን ወይም ጭማቂውን አይን ውስጥ መጨመር የዓይን ቲሹዎችን በማቃጠል ለዓይነ ስውርነት ሊዳርግ ይችላል።

ጤና አዳምን በጥንቃቄ እና በልክ በመጠቀም ጤናችንን እንጠብቅ፤ ላልሰሙትም መረጃውን በማጋራት እንታደግ!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤34👍15
ቀን30/02/19 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 03 01 00 06
📞09 57 97 40 82
📣የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseptionn
    🇪🇹ደመወዝ===150dollar
    🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
    🇪🇹ልምድ===0አመት
    🇪🇹የት/ት ደረጃ===10&12
📣የስራ አይነትNGO ግማሽ ቀን ሙሉ ቀን
    🇪🇹ደመወዝ===200-600 dollar
    🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
   🇪🇹ልምድ===0-5አመት
    🇪🇹የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ
📣position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
     🇪🇹ደመወዝ===13500+
     🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
     🇪🇹ልምድ===0አመት
     🇪🇹የ/ት ደረጃ===10
📣position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
    🇪🇹ደመወዝ===13000+
    🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
    🇪🇹ልምድ===0አመት
    🇪🇹የት/ት ደረጃ===8+
📣positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
     🇪🇹ደመወዝ===15000+
     🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
     🇪🇹ልምድ===አይጠይቅም
     🇪🇹የት/ደረጃ===6-12
📣position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
     🇪🇹ደመወዝ-15000+
     🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
     🇪🇹ልምድ===0አመት
     🇪🇹የት/ት ደረጃ==8-12
📣position===ሞዴል አሰልጥኖ
      🇪🇹ደመወዝ===15000+
      🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
      🇪🇹ልምድ===0አመት
      🇪🇹የት/ት ደረጃ===10
📣potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
     🇪🇹ደመወዝ===15000+
     🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
     🇪🇹ልምድ0===0አመት
     🇪🇹የት/ት ደረጃ==8-12
📣position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
     🇪🇹ደመወዝ===14000
     🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
     🇪🇹ልምድ===0አመት
     🇪🇹የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
📣position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
🇪🇹ደመወዝ===12000+
🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
🇪🇹ልምድ===0-1አመት
🇪🇹የት/ትደረጃ ==8-12
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ የዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞09 57 97 40 82
     📞 09 03 01 00 06
     አድራሻ መገናኛ መተባበር
     ህንፃ 4 ፎቅ ቢሮ ቁ B421
https://t.me/familyWorke
❤5👍2
የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ እና የአዲሱ የምዘና አሠራር መረጃ‼️

​የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግሥት ሠራተኞችን በባህሪ፣ በቴክኒካል ብቃት እና በተግባር ለመመዘን የሚያስችሉ 18 መመሪያዎችን ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

​ከ 90% በላይ የሚያመጡ ሠራተኞች የ 2 እርከን የደመወዝ ጭማሪ ያገኛሉ።

​ከ 75% እስከ 90% የሚያመጡ ሠራተኞች የ 1 እርከን የደመወዝ ጭማሪ ያገኛሉ።

​በሥራ መደብ ለመቆየት፣ የደረጃ እድገት ለማግኘት፣ ለዝውውር እንዲሁም ለአዲስ ቅጥር የምዘና ፈተናውን ማለፍ ግዴታ ነው።

​በሦስቱም የምዘና ዓይነቶች ቢያንስ 70% ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

​የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱ ለ 5 ዓመታት የሚያገለግል ይሆናል።

​ምዘናውን ማለፍ ያልቻለ ሠራተኛ በተቋሙ ተዘጋጅቶ በ6 ወር ውስጥ ድጋሚ ፈተና እንዲወስድ ይደረጋል።

​ኮሚሽኑ አሠራሩ ሠራተኞችን ለመቀነስ ሳይሆን ብቃታቸውን ለማሳደግ እና የሕዝብ አገልግሎትን ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍16❤6🤔6
🎈CMC ከሳፋሪ ትምህርት ጀርባ አዲስ ሳይት ከቴምር ፕሮፐርቲስ

☎️ ለበለጠ መረጃ 09-82-15-16-64 ይፍጠኑ ።

     ✅  100% ለከፈለ 30% በነፃ ነው

👉 ስቱዲዮ ( ቡልጋሪያ እና አዋሬ ላይ)
👉 ባለ 1 መኝታ 73 ካሬ
👉 ባለ 2 መኝታ 112 እና 123 ካሬ
👉 ባለ 3 መኝታ ከ 125 ካሬ እስከ 145 ካሬ

ዋጋ እና አከፋፈል
☑️ስቱዲዮ 40 ካሬ
          ጠቅላላ ክፍያ = 5 ሚሊዮን ብር
       ቅድመ ክፍያ 20%= 1 ሚሊዮን ብር
   🔑 100% ለሚከፍል=  3.5 ሚሊዮን ብር

☑️ ባለ 1 መኝታ 73 ካሬ
          ጠቅላላ ክፍያ = 7.6 ሚልዮን ብር
        ቅድመ ክፍያ 20% = 1.5 ሚልዮን
    🔑100% ለሚከፍል=5.3 ሚሊዮን ብር

☑️  ባለ 2 መኝታ 112 ካሬ
         ጠቅላላ ክፍያ = 11.7 ሚልዮን ብር
       ቅድመ ክፍያ 20% = 2.3 ሚልዮን ብር
   🔑100% ለሚከፍል=  8.2 ሚሊዮን ብር

☑️  ባለ 2መኝታ 123 ካሬ
       ጠቅላላ ክፍያ = 12.9 ሚልዮን
       ቅድመ ክፍያ 20% = 2.5 ሚልዮን ብር
🔑100% ለሚከፍል =  9 ሚሊዮን ብር

☑️ ባለ 3 መኝታ 125 ካሬ
     ጠቅላላ ክፍያ= 13.1 ሚሊዮን ብር
       ቅድመ ክፍያ =  2.6 ሚሊዮን ብር
🔑100% ለሚከፍ = 9.1 ሚሊዮን ብር

☑️ ባለ 3 መኝታ 145 ካሬ
         ጠቅላላ ክፍያ= 15.2 ሚሊዮን ብር
          ቅድመ ክፍያ = 3 ሚሊዮን ብር
🔑100% ለሚከፍል= 10.6 ሚሊየን ብር

     ቀሪ ክፍያ
👉 ያለ ምንም ዋጋ ጭማሪ
👉 ከወለድ ነፃ አከፍፈል
👉 በግንባታ ሂደት የሚከፈል

WhatsApp=https://wa.me/message/Z5LFLDJBTZUDK1

Telegram = @Temerr34

   ☎️ 09-82-15-16-64
❤5👍2
እኔ ስሞት ገነት ነው የምገባው፤ ገሃነም መግባት ፈጽሞ አልፈልግም:ትራምፕ‼️

በትላንትና እለት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሲቢኤስ (CBS) «60 ሚኒትስ» ፕሮግራም ጋዜጠኛ ሮስ ዳውታት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ስለ ሃይማኖታዊ እምነታቸው እና ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት ያላቸውን አመለካከት ይፋ አድርገዋል።

እንደ CBS 60 ሚኒትስ ዘገባ በቃለ ምልልሱ ወቅት ጋዜጠኛው ከሞት በኋላ ምን እንደሚጠብቃቸው ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ እምነት እንዳላቸው ጠቅሰው «በንድፈ ሐሳብ ደረጃ ወደ ገነት እሄዳለሁ» ብለዋል። አክለውም ወደ ገሃነም መሄድ እንደማይፈልጉና ወደ ገነት እንደሚገቡ ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ሆኖም ውይይቱ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ይቅር ስለማለት ወደሚል ጥያቄ ሲሸጋገር ትራምፕ ያላቸው ምላሽ ትኩረት ስቧል። ወደ ገነት ለመግባት የፖለቲካ ጠላቶቻቸውን ይቅር ማለት ቢጠየቁ ማድረግ እንደሚችሉ ተጠይቀው፣ «የአንዳንዶቹን ጥፋት ይቅር ማለት አልችልም፤ አሁንም እጠላቸዋለሁ፡ ወደፊትም መጥላቴን እቀጥላለሁ» ሲሉ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣29❤9👍2🤡1
1ሺህ 584 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 584 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል፡፡

ወደ ሀገራቸው የተመለሱት 1ሺህ 432 ወንዶች ፣ 131 ሴቶች እና 21 ህፃናት ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 25ቱ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራ እየተሰራ እንደሆነ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እስካሁን ከ114 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤8👍4
#DillaUniversity

በ2019 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ህዳር 17 እና 18/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የምዝገባ ቦታ
ኦዳያኣ ግቢ በሚገኘው የሬጅስትራር ህንፃ ቁ. 609

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● መጠኑ 3×4 የሆነ አራት የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
● አንድ የሰነድ መያዣ ክላሰር፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍7❤4
ያለ ባለሙያ ምክር የቫይታሚን ዲ እንክብሎችን መውሰድ ለጤና አደጋ ሊዳርግ እንደሚችል ተገለጸ

ያለ ላብራቶሪ ምርመራና የባለሙያ ምክር የቫይታሚን ዲ ተጨማሪ እንክብሎችንና ጠብታዎችን መጠቀም ለጤና አደጋ ሊዳርግ እንደሚችል የስነ-ምግብ ባለሙያው አቶ ይስሐቅ ግርማ ተናግረዋል።

በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ የተዛቡ መረጃዎች ተጽዕኖ ሥር በመውደቅ የቫይታሚን ዲ እጥረት ሳይኖርባቸው ተጨማሪ እንክብሎችን የሚወስዱ ሰዎች መበራከታቸውም አሳሳቢ መሆኑን ጠቁመዋል።

የጉበትና የኩላሊት ችግር ያለባቸው ሰዎች ቫይታሚኑን በብዛት መውሰዳቸው ተጨማሪ የጤና ችግር ሊያስከትል እንደሚችልም አስረድተዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ያለ ምርመራና የባለሙያ ክትትል መድኃኒቶችን ከመውሰድ እንዲቆጠብ፣ የቫይታሚን ዲ መጠኑን በምርመራ እንዲያረጋግጥና በተመጣጠነ ምግብና ተገቢ የፀሐይ ብርሃን ተጋላጭነት ጤናውን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍2
የኮማንድ ፖስቱ መግለጫ‼️
📌በመቀሌ ከተማ ፈቃድ የሌለው የጦር መሳሪያ የያዙ ግለሰቦች ከህዳር 1 እስከ 3/2019 ዓ.ም ለመንግስት እንዲያስረክቡ ታዟል። ፍቃድ የሌለው መሳሪያ ይዘው በተገኙ ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል።
📌ፍተሻ:- ከጠዋቱ 12፡00 እስከ ምሽቱ 12፡00 ድረስ በከተማዋ ጥብቅ ፍተሻ ይካሄዳል፤ ለዚህ ማህበረሰቡ እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍15🤪10❤3
ሞያሌ‼️ moyale‼️
በሞያሌ ቆም ብሎ የነበረው ግጭት ትናንት ከለሊቱ 8:30 ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ከፍተኛ የተባለ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን ከነዋሪዎቹ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ግጭቱ ላለፉት አራት ቀናት ጋብ ብሎ ቆይቶ የነበረ ቢሆንም ከትናንት ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም ከለሊቱ 8:30 ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ መጀመሩን ገልፀውልናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍8❤5🕊2🤔1
ኢትዮጵያ 590  ግድቦችን ለመገንባት አቅዳለች

ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 24 ዓመታት ውስጥ በአባይ (ናይል)፣ በዋቢ ሸበሌ፣ በገናሌ፣ በዳዋ፣ በኦሞ፣ በባሮ፣ በቴክዜ እና በአዋሽ ዋና ዋና ወንዞች ላይ 40 ትላልቅ እና 300 መካከለኛ መጠን ያላቸው የሃይድሮ ኤሌክትሪክ እና የመስኖ ግድቦችን ለመገንባት አቅዳለች።

ሀገሪቱ በእነዚህ ወንዞች ገባሮች ላይ ቢያንስ 250 ተጨማሪ መካከለኛ እና ትናንሽ ግድቦችን ለመገንባትም አቅዳለች።

ይህ ታላቅ መርሃ ግብር በመላው ኢትዮጵያ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨትን፣ የመስኖ ስራዎችን፣ የውሃ አስተዳደርን እና የግብርና ልማትን ለማስፋፋት ያለመ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍37🤣26❤10🤪4⚡1👌1🙈1🤝1