አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.3K subscribers
18K photos
443 videos
23 files
3.07K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በትግራይ ክልል በተደረገው ጦርነት ከተለያዩ ሀገራት የገቡና ከህወሓት የተማረኩ ድሮኖች፣ሚሳኤሎች፣ፀረ ተሽከርካሪዎች፣ ፀረ ታንኮችና የድሮን ተተኳሾች በመከላከያ ሰራዊት ለእይታ ቀርበዋል።
የተማረኩት ድሮኖች ብቻ ከ1 ሺህ በላይ እንደሆኑ ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍15🤪8❤5👌1
የታሸገ ውሃ ዋጋ ⬆️

የኢትዮጵያ መጠጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኅበር፣ በአዲስ አበባ ከተማ የሚሸጡ የተለያየ መጠን ያላቸው የታሸጉ ውሃዎችን (ከፋብሪካ እስከ ሸማች ያለውን) የ30 አምራቾች የመሸጫ ዋጋ ዝርዝር ለአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮው አሁንም የዋጋ ዝርዝራቸውን ገና ያላሳወቁ ቀሪ አምራቾች በአስቸኳይ እንዲያቀርቡ አሳስቦ ቁጥጥሩን እንደሚያጠናክር አስታውቋል።

ሸማቾችም ከዋጋ ጋር የተያያዘ ማንኛውም ቅሬታ ሲያጋጥማቸው በነፃ የስልክ መስመር 8588 እንዲጠቁሙ ጥሪ ቀርቧል።

(የውሃ አምራቾች ለአከፋፋዮች የሚያስረክቡበት ዋጋ / Factory Price ፣ የአከፋፋዮች የትርፍ ህዳግ / Agent Margin እንዲሁም አከፋፋዮች ለቸርቻሪ ነጋዴዎች የሚያስረክቡበት ዋጋ / Total Retailer Price ከላይ ተያይዟል)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍11❤7🤯3
በአዳማ ከተማ ስድስት እግርና ሁለት ራስ ያላት ድንቅ ግልገል ፍየል ተወለደች።

⚫ ፍየሏ በሁለቱም አፏ መጥባት ትችላለች!

በአዳማ ከተማ ሁለት ራስ፣ ሁለት አፍ፣ ስድስት እግር እንዲሁም ሁለት የብልት አካላት በአንድ ላይ የያዘች ግልገል ፍየል ተወልዳለች።

ግልገሏ በሁለቱም አፏ አተት የመጠባት አቅም እንዳላት የተገለጸ ሲሆን ከዚች ግልገል ጋር አብራ የተወለደችው ሁለተኛዋ መንታ ግን በተፈጥሮአዊ የአካላት መዋቅር የተወለደች ናት።

በአዳማ ከተማ ግብርና ጽሕፈት ቤት የእንስሳት ጤና ቡድን መሪ ዶክተር ደሪቤ ሀይሉ ስለ አጋጣሚው በሰጡት ሙያዊ ማብራሪያ፣ እንዲህ ዓይነቱ የሰውነት አካላት መደራረብ የሚከሰተው በእንስሳቱ የእርግዝና ወቅት የመንታ እንቁላል ክፍፍል ሂደት ከ12 እስከ 17 ባሉት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሳይለያይ ሲቀር እንደሆነ ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤯16❤7🤪3🤔2😱2👍1🌚1
የኩላሊት ጠጠር እንዳለባችሁ የሚያሳዩ 5 ምልክቶች

1. ከባድ ህመም
• በቀኝ ወይም በግራ ጀርባችሁ ላይ ድንገተኛ እና ከባድ ህመም የሚሰማችሁ ከሆነ። ይህ ህመም ከጎድን አጥንታችሁ በታች የሚሰማ ሲሆን ወደታችኛው ሆድ ሊሰራጭ ይችላል።

2. በሽንት ውስጥ ደም ካስተዋላችሁ
• በሽንት ውስጥ ደም መኖር ጠጠሩ በኩላሊት ትቦዎች  ውስጥ አልፎ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ያሳያል።

3. ቶሎ ቶሎ መሽናት
• ከተለመደው በላይ ወደ ሽንት ቤት መመላለስ እና ለመሽናት መፈለግ የኩላሊት ጠጠር ከፊኛ አጠገብ እንደሚገኝ ያሳያል።

4. ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
• በጣም ከባድ ህመም ሲኖር ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ይሰማችኋል።

5. ትኩሳት
• ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት በኩላሊት ዉስጥ ኢንፌክሽን መፈጠሩን ያሳያል።

እነዚህን ምልክቶች ካያችሁ ወደ ህክምና በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራ ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍20❤14
ፓስተር ፖል ማኬንዚ በ191 ሰዎች ግድያ የ200 ዓመታት እስራት ተበየነባቸው

በኬንያ ተከታዮቻቸውን ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት በሚል በረሃብ እንዲያልቁ ያደረጉት የ191 ሰዎችን ህይወት ያጠፉት የኑፋቄ ቡድን መሪ ፖል ማኬንዚ የ200 ዓመታት እስራት ተፈረደባቸው።

ፍርድ ቤቱ በማኬንዚ ላይ በግድያ ወንጀል የ100 ዓመት እንዲሁም በርሃብ በማስገደል ወንጀል የ100 ዓመት በድምሩ የ200 ዓመታት እስራት በይኖባቸዋል።

ከተገደሉት ሰዎች መካከል ከአንድ ግለሰብ ውጭ ሁሉም ሕፃናት እንደነበሩ የተገለጸ ሲሆን ከእርሱ ጋር የተከሰሱ 28 ተባባሪዎችም እስከ 160 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

ማኬንዚ እ.ኤ.አ. በ2023 በሻካሆላ ደን ውስጥ ከ400 በላይ አስከሬኖች በጅምላ ተቀብረው ከተገኙ በኋላ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ዳኛ ዲያና ሞቻቼ ውሳኔውን ሲያስተላልፉ ድርጊቱ ታቅዶ የተፈጸመ አሰቃቂ ጭካኔ መሆኑን ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20👍4😢1
«የኢሳያስ አገዛዝ ለኢትዮጵያና ለትግራይ ከባድ የደኅንነት ስጋት ነው!» — ጀኔራል ፃድቃን‼️

ሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ፣ በኤርትራ በኩል የሚመጣው የደኅንነት ስጋት ዘላቂ መፍትሔ ሊያገኝ እንደሚገባ ገለጹ።

እንደ ጀኔራሉ ግምገማ፣ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው አገዛዝ ሲዳከም ለጊዜው ዝም የሚልና ዳግም አቅም እንዳገኘ ሲሰማው ወደ ግጭት የሚመለስ አካሄድ አለው።

ይህ አካሄድ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነትና ለትግራይ መረጋጋት ከባድ ስጋት እንደሆነ የገመገሙት ጀኔራሉ፣ የኢሳያስ አመራር መወገድንም ለዘላቂ መፍትሔ አስፈላጊ እርምጃ አድርገው አቅርበዋል።

ጉዳዩን ለመፍታት የሚወሰደው አቅጣጫ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚወስነው መሆኑንም ከTBS ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ ጠቅሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣21❤11👍7
Forwarded from Naty
🎈CMC ከሳፋሪ ትምህርት ጀርባ አዲስ ሳይት ከቴምር ፕሮፐርቲስ

☎️ ለበለጠ መረጃ 09-82-15-16-64 ይፍጠኑ ።

     ✅  100% ለከፈለ 30% በነፃ ነው

👉 ስቱዲዮ ( ቡልጋሪያ እና አዋሬ ላይ)
👉 ባለ 1 መኝታ 73 ካሬ
👉 ባለ 2 መኝታ 112 እና 123 ካሬ
👉 ባለ 3 መኝታ ከ 125 ካሬ እስከ 145 ካሬ

ዋጋ እና አከፋፈል
☑️ስቱዲዮ 40 ካሬ
          ጠቅላላ ክፍያ = 5 ሚሊዮን ብር
       ቅድመ ክፍያ 20%= 1 ሚሊዮን ብር
   🔑 100% ለሚከፍል=  3.5 ሚሊዮን ብር

☑️ ባለ 1 መኝታ 73 ካሬ
          ጠቅላላ ክፍያ = 7.6 ሚልዮን ብር
        ቅድመ ክፍያ 20% = 1.5 ሚልዮን
    🔑100% ለሚከፍል=5.3 ሚሊዮን ብር

☑️  ባለ 2 መኝታ 112 ካሬ
         ጠቅላላ ክፍያ = 11.7 ሚልዮን ብር
       ቅድመ ክፍያ 20% = 2.3 ሚልዮን ብር
   🔑100% ለሚከፍል=  8.2 ሚሊዮን ብር

☑️  ባለ 2መኝታ 123 ካሬ
       ጠቅላላ ክፍያ = 12.9 ሚልዮን
       ቅድመ ክፍያ 20% = 2.5 ሚልዮን ብር
🔑100% ለሚከፍል =  9 ሚሊዮን ብር

☑️ ባለ 3 መኝታ 125 ካሬ
     ጠቅላላ ክፍያ= 13.1 ሚሊዮን ብር
       ቅድመ ክፍያ =  2.6 ሚሊዮን ብር
🔑100% ለሚከፍ = 9.1 ሚሊዮን ብር

☑️ ባለ 3 መኝታ 145 ካሬ
         ጠቅላላ ክፍያ= 15.2 ሚሊዮን ብር
          ቅድመ ክፍያ = 3 ሚሊዮን ብር
🔑100% ለሚከፍል= 10.6 ሚሊየን ብር

     ቀሪ ክፍያ
👉 ያለ ምንም ዋጋ ጭማሪ
👉 ከወለድ ነፃ አከፍፈል
👉 በግንባታ ሂደት የሚከፈል

WhatsApp=https://wa.me/message/Z5LFLDJBTZUDK1

Telegram = @Temerr34

   ☎️ 09-82-15-16-64
❤6👍2
“ስልጣኔን በመልቀቅ ህይወቴን ለክርስቶስ እሰጣለሁ!” – የኡጋንዳ ጦር አዛዥ ሙሁዚ ካይኔሩጋባ

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ ከፍተኛ ኃላፊነታቸው በቅርብ ወራት ውስጥ ለመልቀቅና ሕይወታቸውን ለክርስቶስ ለማዋል ያላቸውን ዕቅድ ይፋ አድርገዋል።

ጄነራል ሙሁዚ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት፣ “የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው። እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ። በጥቂት ወራት ውስጥ ይህንን ቢሮ ለብቁ ወታደራዊ መኮንን አስረክባለሁ፤ ከዚያም ሕይወቴን ለክርስቶስ እሰጣለሁ” ብለዋል። 

ጄነራሉ ከኃላፊነታቸው መልቀቅ በኋላ ከሕዝብ እይታ ሙሉ በሙሉ እንደማይሰወሩ የገለጹ ሲሆን፣ በተጨማሪም በኡጋንዳ የመከላከያ ኃይል (UPDF) ውስጥ የሚያገለግሉ ወታደሮች ደመወዝ ወደ 2 ሚሊዮን የኡጋንዳ ሺሊንግ እንዲያድግ ጥሪ አቅርበዋል። የወታደሮች የመኖሪያ ሁኔታና ደመወዝ ማሻሻል ከቀጣይ ትኩረቶቻቸው መካከል መሆኑንም ጠቁመዋል። 

ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ ሲሆኑ፣ በመጋቢት 2024 የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ ሆነው ተሾሙ። በወታደራዊ አመራርና በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያስተላልፏቸው መልእክቶች በአፍሪካ ክልላዊ ፖለቲካ ውስጥ ተደጋጋሚ ትኩረት የሚስቡ ሰው ናቸው። 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣21❤16👍8🤷‍♂2
«የሚመጡት 8 ሳምንታት በህይወታችን ውስጥ በጣም አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ!»
የቀድሞው የኋይት ሀውስ የጦርነት አማካሪ እና የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሮበርት ፔፕ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላለፉ።

እንደ ኤክስፐርቱ ገለፃ ከሆነ አሜሪካ እና አለማችን በጥልቅ «የግጭት መባባስ ወጥመድ» ውስጥ እየገቡ ይገኛሉ።
ይህንን አለም አቀፍ ስጋት ከጫፍ ያደረሱት ሶስት ዋና ዋና አደገኛ ሁኔታዎች በአንድ ላይ መገናኘታቸው ተገልጿል።

የመጀመሪያው በከፍተኛ ፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ የሚከናወነው የስልጣን ሽግግር እና የአገር ውስጥ አለመረጋጋት ነው። ሁለተኛው ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ ከኢራን ጋር እንዲሁም በምስራቅ አውሮፓ ከሩሲያ እና ዩክሬን ጋር የተያያዙ ወታደራዊ ግጭቶች ወደ ከፋ የክልላዊ እና አለም አቀፋዊ ጦርነት የመሸጋገር ከፍተኛ ስጋት ናቸው።

በሶስተኛ ደረጃ፣ በሀያላን ሀገራት የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃቶች አለም አቀፍ ወታደራዊ ግጭትን በቀላሉ ሊቀሰቅሱ ይችላሉ ተብሎ ይታመናል።

ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው በታዋቂው «The Diary Of A CEO» ፖድካስት ላይ በተደረገ ቃለ-መጠይቅ ሲሆን፣ የጂኦ-ፖለቲካ ተንታኞች ሁኔታውን በጥብቅ እየተከታተሉ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤22👍9😢1
በዛሬው ዕለት ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም በስለላ ክትትል 7 የህወሓት አመራሮች መያዘቸው ተገለፀ።
📋 የተያዙ መሪዎች ዝርዝር፡

1️⃣ አቶ ተ/ብርሃን ተስፋለም - የቀድሞ የሰላም እና የደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበረ።

2️⃣ አቶ ገብረፃዲቅ ገብረስላሴ - የትግራይ ክልል ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበረ።

3️⃣ አቶ ተስፋዬ አባዲ- የትግራይ ክልል የሰላም እና ደህንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበረ።

4️⃣ አቶ ገረኪዳን - ቀደም ሲል በማዕከላዊ እና ደቡብ ምዕራብ ዞኖች የፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው አገልግለዋል፤ ከጡረታ በኋላ በትግራይ ክልል የሰላም፣ የደህንነት፣ የመረጃ እና የክትትል ቢሮ ነበሩ።

5️⃣ አቶ ወልዱ መስፍን - የጦር መሳሪያ መምሪያ ኃላፊ፣ የትግራይ ክልል ሚሊሻ ጽ/ቤት የነበሩ።

6️⃣ ኪዳኔ ግሪማይ - የትግራይ ክልል ሚሊሻ የመረጃ እና የክትትል ቢሮ አስተባባሪ የነበሩ።

7️⃣ አቶ አማኑኤል - በትግራይ ክልል የቀድሞ የእስር ቤት አሽከርካሪ የነበረ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤11👍8🤔3🤷‍♂2
የኤሌክትሪክ መኪናዎን ባትሪ ሳያውቁት እየጎዱት ይሆን?እንዳይበላሽብዎ ማወቅ ያለብዎት 4 ወሳኝ ሚስጥሮች!

በአሁኑ ጊዜ በመንገዶቻችን ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች (EVs) በብዛት ማየት የተለመደ ሆኗል።

የኤሌክትሪክ መኪና ሲኖረን የነዳጅ መኪና ላይ እንደምናደርገው ዘይት መቀየር፣ ፕለግ ማፅዳት ወይም የሞተር ጥገና የለም ብለን ልንዘናጋ እንችላለን። ነገር ግን ፍፁም ጥገና አያስፈልጋቸውም ማለት አይደለም!

መኪናችን ለብዙ ዓመታት በሙሉ አቅሙ እንዲያገለግለን እና የመኪናው ውዱ አካል የሆነው ባትሪ እንዳይበላሽብን እነዚህን 4 ቀላል ነገር ግን ወሳኝ ጥንቃቄዎች ማወቅ አስፈላጊ ነው።

የመጀመሪያውና ዋናው ነገር የባትሪ ቻርጅ አጠቃቀማችን ነው። ባትሪው ሙሉ በሙሉ 0% እስኪሆን አቃጥሎ መጠቀምም ሆነ ሁልጊዜ 100% ሞልቶ ረጅም ጊዜ እንዲቆይ ማድረግ ዕድሜውን በእጅጉ ያሳጥራዋል።

የመኪና ባለሙያዎች የሚመክሩት የባትሪውን መጠን ሁልጊዜ ከ20% እስከ 80% ባለው ክልል ውስጥ አቆይቶ መጠቀም የባትሪውን ጤንነት ለረጅም ጊዜ እንደሚጠብቅ ነው።

ሁለተኛው የብሬክ ሲስተም ፍተሻ ነው። የኤሌክትሪክ መኪኖች ፍጥነት ሲቀንሱ ኃይል ወደ ባትሪው የሚመልስ (Regenerative braking) ቴክኖሎጂ ስላላቸው የብሬክ ፓዳቸው በፍጥነት አይበላሽም።

ነገር ግን ይህ ማለት የብሬክ ዘይት እና የዲስክ አቧራ ፍተሻ አያስፈልግም ማለት ስላልሆነ በየጊዜው ማሳየት ተገቢ ነው።

ሶስተኛው ደግሞ የባትሪ ማቀዝቀዣ ፈሳሽ (Coolant) ነው። ባትሪዎች በሚሞሉበትም ሆነ ረጅም መንገድ በሚነዱበት ጊዜ ከፍተኛ ሙቀት ያመነጫሉ።

ይህንን ሙቀት የሚቆጣጠረው ማቀዝቀዣ ፈሳሽ መጠኑ በቂ መሆኑን እና መፍሰስ አለመኖሩን ዘወትር ማረጋገጥ መኪናውን ከከፍተኛ አደጋ ይታደጋል።

አራተኛውና አብዛኛው ሰው ትኩረት የማይሰጠው የጎማ እንክብካቤ ነው። የኤሌክትሪክ መኪኖች ባትሪ ስላላቸው ከተራ መኪና በክብደት ይበልጣሉ፤ በተጨማሪም ረገጥ ስናደርጋቸው የሚሰጡት ድንገተኛ ከፍተኛ ጉልበት (Instant Torque) ጎማቸው በፍጥነት እንዲያልቅ ያደርገዋል።

ስለዚህ የጎማ አየር ግፊትን በየጊዜው ማስተካከል እና ጎማዎችን ቦታ ማቀያየር (Rotation) ማድረግ የጎማውን ዕድሜ ያራዝማል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍15❤8
በመቀሌ ጠንከር ያላ ፍተሻ እየተደረገ ነው‼️
ህወሃት በተለያዩ አካባቢዎች ደብቋቸው የነበሩ ወታደራዊ ትጥቆች በፍተሻ እየተገኙ ነው። ህዝቡ ጥቆማ በመስጠት እየተባበረ መሆኑን የከተማዋ ምንጮች ገልፀዋል።
ህወሃት በከተማዋ ለጦርነት ካከማቻቸው መሣሪያና ተተኮሾች በተጨማሪ የመገናኛ ራዲዮኖችም ይገኙበታል።
ከዚህ ጎን ለጎን በከተመዋ በሌብነት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በሕዝቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19👍2