አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.5K subscribers
17.8K photos
440 videos
23 files
3.05K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ሎሚ እና ጨው ለማይግሬን ህመም የመፍትሄ አማራጭ

የሄልዚ ላይፍ ላንድ ድረ-ገጽ ዘገባ እንደሚለው፣ ይህ ውህድ የራስ ምታት ህመምን በቶሎ ለማስታገስ የሚረዳው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦

1. የጨው ሚና (ሴሮቶኒን ሆርሞን)
ጨው ጭንቀትን በማስወገድ ደስታ እንዲሰማን የሚያደርገውን ሴሮቶኒን የተሰኘ ሆርሞን መመረትን ይጨምራል።

ጭንቀት ደግሞ ለከባድ የራስ ምታት ህመም (ማይግሬን) መነሻ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ በመሆኑ፣ የጨው መጠቀሚያው ይህንን መነሻ ለመቀነስ ይረዳል።

2. የአጠቃቀም ዘዴ

የሁለት ሎሚ ጭማቂ እና የተፈጨ የሎሚ ቅርፊትን ከሁለት ማንኪያ ጨው ጋር አድባልቆ በቀዝቃዛ ስፍራ ማስቀመጥ።

ከዚያም ከተወሰነ ውሃ ጋር ቀላቅሎ መጠጣት።

ይህ ውህድ በሶስት ደቂቃ ውስጥ ከህመሙ ለማገገም ይረዳል ተብሏል።

አስፈላጊ ማስጠንቀቂያ

ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም ያለባቸው ሰዎች ጨው ችግሩን ስለሚያባብሰው ይህንን ውህድ እንዳይጠቀሙበት ዘገባው አጥብቆ ይመክራል።

የማይግሬን መነሻ ምክንያቶች

ዘገባው ከባድ የራስ ምታት (ማይግሬን) ህመም እንዲከሰት የሚጠቅሳቸው ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦

🔹ጭንቀት

🔹አደንዛዥ እፆችን መጠቀም

🔹የምግብ እጥረት

🔹የሆርሞን አለመመጣጠን

🔹የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት

የራስ ምታት የሚከሰተው በአዕምሮ ውስጥ የሚገኙ ትልልቅ የደም ስሮች ሲያብጡና ሲሰፉ ነው። ይህ የደም ስሮች እብጠት በዙሪያቸው የሚገኙ ነርቮች የተለያዩ ንጥረ ነገሮች እንዲለቁ ያደርጋል። እነዚህ የተመረቱ ንጥረ ነገሮች የአዕምሯችን ለህመም ያለውን ስሜት ይጨምሩታል። ህመሙ ቀስ በቀስ የሚጨምር ሲሆን፣ ከእንቅልፍ ስንነሳ የሚበረታ ከሆነ ከፍተኛ የህመም ደረጃ ላይ መድረሱን ያመላክታል።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍4🙏1
​🚨 «የአሜሪካ የኮንግረስ መራጮች ለአጋማሽ ዘመን ምርጫ የመጨረሻ ክርክሮችን ያደረጉ ሲሆን፣ በብዙዎች ትኩረት የሳበው የምርጫ ውድድር በምቺጋን እና ካሊፎርኒያ መጧጧፉ ተሰማ»

​አሜሪካውያን መራጮች ለአጋማሽ ዘመን ምርጫ ዋዜማ በነበረው ሰኞ እለት የመጨረሻ የፖለቲካ ክርክሮችን እና ቅስቀሳዎችን ያደረጉ ሲሆን፣ ፖለቲካዊ ውጥረቶች ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተመላክቷል።

​በምቺጋን ግዛት አብዱል ኤል-ሳይድ ወደ የህግ አውጪው ምክር ቤት የሚመረጥ የመጀመሪያው ሙስሊም አባል ለመሆን ያደረገው ሩጫ ከፍተኛ ትኩረት ከሳቡት ክስተቶች መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

​በሌላ በኩል በካሊፎርኒያ ግዛት የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፍትሕ ዲፓርትመንት በምርጫው ሂደት ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ያደረገውን ጥረት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጉ ታውቋል።

​ይህ ወሳኝ ምርጫ በሁለቱም ፓርቲዎች መካከል ያለውን የሥልጣን ሚዛን የሚወስን እና በቀጣዮቹ ዓመታት በዋሺንግተን የሚኖሩ ፖሊሲዎችን ቅርጽ የሚያስይዝ በመሆኑ ዓለም አቀፍ ትኩረት ስቦ መክረሙ ተመላክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍6❤4🤣1
ቀን24/02/19 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 03 01 00 06
📞09 57 97 40 82
📣የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseptionn
    🇪🇹ደመወዝ===150dollar
    🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
    🇪🇹ልምድ===0አመት
    🇪🇹የት/ት ደረጃ===10&12
📣የስራ አይነትNGO ግማሽ ቀን ሙሉ ቀን
    🇪🇹ደመወዝ===200-600 dollar
    🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
   🇪🇹ልምድ===0-5አመት
    🇪🇹የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ
📣position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
     🇪🇹ደመወዝ===13500+
     🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
     🇪🇹ልምድ===0አመት
     🇪🇹የ/ት ደረጃ===10
📣position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
    🇪🇹ደመወዝ===13000+
    🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
    🇪🇹ልምድ===0አመት
    🇪🇹የት/ት ደረጃ===8+
📣positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
     🇪🇹ደመወዝ===15000+
     🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
     🇪🇹ልምድ===አይጠይቅም
     🇪🇹የት/ደረጃ===6-12
📣position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
     🇪🇹ደመወዝ-15000+
     🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
     🇪🇹ልምድ===0አመት
     🇪🇹የት/ት ደረጃ==8-12
📣position===ሞዴል አሰልጥኖ
      🇪🇹ደመወዝ===15000+
      🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
      🇪🇹ልምድ===0አመት
      🇪🇹የት/ት ደረጃ===10
📣potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
     🇪🇹ደመወዝ===15000+
     🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
     🇪🇹ልምድ0===0አመት
     🇪🇹የት/ት ደረጃ==8-12
📣position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
     🇪🇹ደመወዝ===14000
     🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
     🇪🇹ልምድ===0አመት
     🇪🇹የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
📣position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
🇪🇹ደመወዝ===12000+
🇪🇹ፆታ===ወ/ሴት
🇪🇹ልምድ===0-1አመት
🇪🇹የት/ትደረጃ ==8-12
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ የዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞09 57 97 40 82
     📞 09 03 01 00 06
     አድራሻ መገናኛ መተባበር
     ህንፃ 4 ፎቅ ቢሮ ቁ B421
https://t.me/familyWorke
❤5👍3
አሜሪካ ጥቃት ፈፀመች‼️
በሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙ የኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች በአሜሪካ ድብደባ ተፈጸመባቸው‼️

​አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ በሚገኘው የቀሽም ደሴት (Qeshm Island) የኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የተወሰነ የአየር ጥቃት ማድረሷን ይፋ አድርጋለች።
​የአሜሪካ የሰራዊት ባለስልጣናት እንደገለፁት፣ ድብደባው በስልታዊ የውሃ መንገዱ ላይ በሚንቀሳቀሱ የአሜሪካ ወታደራዊ ሀብቶች ላይ ስጋት ደቅነው በነበሩ የመሬት-ወደ-አየር (surface-to-air) ሚሳይል ማስወንጨፊዎች ላይ ያነጣጠረ ራስን የመከላከል እርምጃ ነው።

​የኢራን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን በበኩላቸው ህዳር 2/2026 ቀን በደሴቲቱ ላይ በርካታ ከፍተኛ ፍንዳታዎች መከሰታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት ሁለት የጦር አውሮፕላኖች በሰማይ ላይ ሲያንዣብቡ መመልከታቸውን ገልጸዋል።
​የፔንታጎን ምንጮች ጥቃቱ ወሰን ያለው እና ወደ ሰፊ ቀጠናዊ ጦርነት የማያመራ መሆኑን ቢገልፁም፣ እስካሁን ስለደረሰው የሰው እና ቁሳቁስ ጉዳት ሙሉ መረጃ አልወጣም።

​ይህ ወታደራዊ እርምጃ ለዓለም አቀፍ የነዳጅ እና የኃይል አቅርቦት ቁልፍ በሆነው በሆርሙዝ ወሽመጥ የደህንነት ስጋት ምክንያት በዋሽንግተን እና ቴህራን መካከል ያለው ውጥረት በከፍተኛ ደረጃ በጨመረበት ወቅት የተከሰተ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤9👍1
Forwarded from Basic 1
#Ads

😀📱😀📱LinkedIn😀📱😀📱

✅የሊንኪዲን አካውንት በረጅም ጊዜ አጋርነት መከራየት እንፈልጋለን።📱

📱 we have fair price , ማርኬቱን ያማከለ
✅ ከ 300+ በላይ እና ከአንድ አመት በላይ ( 2025 and before ) ተመራጭ ነው 📱
✅ አካውንትዎን ለእኛ ቢያከራዩን እኛ ደግሞ በታማኝነት እንከራያለን።መለያችን ታማኝነት ነው። 📱
✅ እኛ የምንከፍለው ሂሳብ ገበያውን በጣም ያማከለ ነው።  📱
📱 ማከራየት ከፈለጉ በዚህ ያግኙን @LinkedInethiorental 💬

channel = #Ads

😀📱😀📱LinkedIn😀📱😀📱

✅የሊንኪዲን አካውንት በረጅም ጊዜ አጋርነት መከራየት እንፈልጋለን።📱

📱 we have fair price , ማርኬቱን ያማከለ
✅ ከ 300+ በላይ እና ከአንድ አመት በላይ ( 2025 and before ) ተመራጭ ነው 📱
✅ አካውንትዎን ለእኛ ቢያከራዩን እኛ ደግሞ በታማኝነት እንከራያለን።መለያችን ታማኝነት ነው። 📱
✅ እኛ የምንከፍለው ሂሳብ ገበያውን በጣም ያማከለ ነው።  📱
📱 ማከራየት ከፈለጉ በዚህ ያግኙን @LinkedInethiorental 💬

channel = https://t.me/+Q8MUmu_sWzJhMDNk 📣📢
        
                                  📣📢
        
                                 
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤3👍2🥰1💯1
ትግራይ‼️
የህውሃት አርሚ-15 ዋና አዛዥ ኮሎኔል ኃይለሥላሴ አሰፋ (ወዲ ፈጠነ) እና የሎጂስቲክስ ኃላፊው ኮሎኔል ካሕሳይ ተኽሉ (ወዲ መርጋ) በትናንትናው ዕለት ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም በአዲግራት ዙሪያ በተደረገ ውጊያ ከሙሉ ስታፎቹ ጋር መማረካቸው ታውቋል።
መገናኛ ሬዲዮ፣ ዲሽቃ እና ሌሎች የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን ለመከላከያ ሰራዊት አስረክበዋል።
የወዲ ፈጠነ ምክትል በውጊያ ወቅት ተሰውቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤11🤣7👍3🤪1
ደቡብ ወሎ የተቀሰቀሰው ውጊያ‼️
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ሀይሎች መካከል ካለፉት አምስት ቀናት ጀምሮ ከባድ ውጊያ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።ይህንን ውጊያ ተከትሎ የደሴ-ወልዲያ መንገድ ከትናንት ጀምሮ እንደተዘጋ ታውቋል፡፡

በውጫሌ ከተማ ከቅዳሜ ጀምሮ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በከባድ መሳሪያዎችና በድሮን የታገዘ ውጊያ ሲካሄድ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረውናል።

ትናንት ሰኞ በከተማዋ ልዩ ሥሙ "ዳንካ ሚካኤል" በተባለ ሥፍራ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶች እንደተፈጸሙና ሆኖም በወቅቱ በንጹሃን ላይ የደረሠ ጉዳት ስለመኖሩ በእርግጠኝነት ለመናገር እንደማይችሉ ነዋሪዎቹ ገልጸውልናል።

በሌላ በኩል፤ በሀብሩ ወረዳ ውርጌሳ እና ጊራና ገጠራማ አካባቢዎችም በሁለቱ ወገኖች መካከል ውጊያ መቀጠሉን ተረድተናል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤7👍2
ኢትዮ-ሱዳን‼️
ኢትዮጵያ በድንበር ከተማዋ አሶሳ የሚገኘውን የሱዳን ቆንስላ እንዲዘጋ ማዘዟና ዲፕሎማቲክ ሰራተኞቹም በ48 ሰዓታት ውስጥ እንዲወጡ መመሪያ መስጠቷን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ሱዳን ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ግዛት በሚነሱ ድሮኖች ጥቃት እየተፈፀመብኝ ነው የሚል አቤቱታ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ለዲፕሎማቶች አሳውቃለች።
ኢትዮጵያ እነዚህን ውንጀላዎች በተደጋጋሚ ውድቅ አድርጋለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤9👍3
የታሸጉ ውሃዎች የአከፋፋዮች እና የቸርቻሪ  የመሸጫ ዋጋ  ይፋ ሆኗል በዚህም ሁለት ሊትር  ከ40 እስከ 50 እንዲሸጥ ተተምኗል

በአዲስ አበባ ከተማ የታሸጉ የውሃ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በተመለከተ የታሸገ ውሃ አምራቾች በማህበራቸው በኩል ለአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አሳውቀዋል።

በሸማቾች ጥበቃ አዋጅ 813/2006 ማንኛውም ነጋዴ የሚሸጣቸውን ምርቶች ዋጋ በሚታይ ቦታ የመለጠፍ/ለሸማቾች የማሳወቅ ግዴታ የሚጥልበት እንደመሆኑ መጠን ዋጋቸውን ያላሳወቁ የውሃ አምራች ፋብሪካዎች በሁለት ቀናት ውስጥ ዋጋ እንዲያሳውቁ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አሳውቋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የታሸገ ውሃ አምራቾች  ጋር በተደረሰው የጋራ መግባባት መሠረት የመሸጫ ዋጋቸውን ያሳወቁ ፋብሪካዎችን እንዲሁም ማህበሩን አመስግነዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በአዋጁ መሠረት የመሸጫ ዋጋቸውን ያላሳወቁ የውሃ አምራች ድርጅቶች ውሃዎችን በመዲናዋ መቸርቸር እንደማይችሉ ገልፀው በተሰጠው የጊዜ ገደብ እንዲያሳውቁ አሳስበዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ገለፃ በመዲናችን አዲስ አበባ ውሃ በቦቴ እያዞሩ የሚሸጡ ድርጅቶችን በተመለከተ በቅርቡ ከአዲስ አበባ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ጋር በመነጋገር መፍትህ እንደሚሰጥበት አሳውቀዋል።

በመጨረሻም የታሸጉ ውሃዎች ዝርዝር ዋጋ ከዚህ ልጥፍ ጋር የተያያዘ ሲሆን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የቁጥጥር ሠራተኞች ፋብሪካዎቹ ባሳወቁት ዋጋ መሠረት ሽያጭ እየተፈፀመ መሆኑን የመከታተል ስራ እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤6👍1
በ2019 የተጠናከረ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚኖር ይጠበቃል - ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ስምንተኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡

በዚሁ ወቅት ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንዳነሱት÷ በሲሚንቶ ምርት፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨትና በብረታብረት ምርቶች ላይ የታዩ መሻሻሎች በአጠቃላይ የኢንዱስትሪ ዘርፉ ንቁ እንቅስቃሴ እንደሚኖረው ይጠቁማሉ፡፡

የአገልግሎት ዘርፍ ዋና ዋና አመላካቾች ማለትም የቱሪስት ፍሰት፣ የአየር ትራንስፖርት፣ የብድር አቅርቦት መሻሻሎች ዘርፉ የበለጠ እንደሚያድግ ማሳያ እንደሆኑ ገልጸዋል።

እንዲሁም የወርቅ ወጪ ንግድ፣ የካፒታልና የጥሬ እቃ ምርቶች ገቢ ንግድ እድገቱን እንደሚያጠናክሩም አብራርተዋል።

መሰረታዊ ገንዘብ በመስከረም ወር 2019 መጨረሻ 87 ነጥብ 2 በመቶ ዓመታዊ እድገትን እንዳስመዘገበ በማንሳት፤ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው 72 ነጥብ 6 በመቶ አንጻር ጭማሪ እንዳሳየ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላላ የገንዘብ አቅርቦት ዓመታዊ እድገት ባለፈው ዓመት ከነበረው 33 ነጥብ 2 በመቶ አሁን ላይ 40 ነጥብ 2 በመቶ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ይህም ከሚጠበቀው የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር ከፍተኛ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

የባንኮች የሩብ ዓመቱ የተቀማጭ ገንዘብ ክምችት 85 ነጥብ 4 በመቶ፤ አጠቃላይ የብድር ክምችት ደግሞ 4 ነጥብ 6 በመቶ ዓመታዊ እድገት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡

የበጀት ፖሊሲ ስርዓት ጥንቃቄ የተሞላበት፣ ከብሔራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ እንዲሁም ከአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አጀንዳ ጋር የተናበበ እንደነበር አመልክተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤1🤪1