የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ዛሬ ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም ከአምስት ቀናት በኋላ ከራሺያ ተመልሰዋል።
ኢሳይያስ የደርሶ መልስ በረራቸውን ያደረጉት በአረብ ኢምሬትስ በተመዘገበ እና በROTANA JET አማካኝነት ቁጥጥር በሚደረግበት AIRBUS 319 በተባለ አውሮፕላን ነው።
@Addis_Reporter

❤11👍11🤪7🤷♂3🤡2🕊1
ኢራን «ወሰን የለሽ» ወታደራዊ ምላሽ ለመስጠት ማዘዟ ተሰማ
የኢራኑ ከፍተኛ መሪ ሞጅታባ ካሜኔይ ሀገራቸው ሊሰነዘርባት ለሚችል ለማንኛውም አዲስ ጥቃት «ያለ ምንም የጂኦግራፊያዊ ገደብ» እና በአፋጣኝ የሚሰጥ ከፍተኛ ወታደራዊ ምላሽ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ አስተላለፉ።
መሪው በይፋዊ የቴሌግራም ገጻቸው ባወጡት መግለጫ፦ ኃይሎቻቸው ሊሰነዘሩ የሚችሉ ጥቃቶችን ለማስቆም የምላሽ መስጫ ጊዜውን እና ሁኔታውን እራሳቸው እንደሚወስኑ አስታውቀዋል።
አሜሪካ እና እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ንብረቶቻቸው በኢራን የጦር ኃይሎች ኢላማ ስር እንዲገቡ፣ የወታደራዊ ጥቃት ስትራቴጂው በአስቸኳይ እንዲሻሻል አዝዘዋል።
ይህ የቴህራን ጠንካራ ማ ማስጠንቀቂያ የመጣው፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ አድሚራል ብራድ ኩፐር ጋር ተገናኝተው በኢራን ላይ ሊወሰዱ ስለሚችሉ ወታደራዊ አማራጮች ካደረጉት ምስጢራዊ ስብሰባ በኋላ ነው።
‘ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል’ እንደዘገበው ከሆነ፣ የዋሺንግተን ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ አዲስ እና መጠነ-ሰፊ የወታደራዊ ዘመቻ ዋዜማ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

👍12❤10🤣3
ትግራይ‼️
📌ሕወሓት ሌሊቱን በመቀሌ ከተማ በራሪ ወረቀቶችን ሲበትን እና በስልክ እንጨት ላይ 'ኦፕሬሽን ሃየሎም' የሚል ፅሁፍ ያለው ወረቀት ሲለጥፍ አድሯል።
📌ከዓዲግራት፣ ከውክሮ፣ ከሽሬ እስከ አኩሱም ያለው የቴሌኮሙኒኬሽን መስመር በቴክኒክ ችግሮች ምክንያት ተቋርጧል።

❤25🤣16🤪4👍3
ጥቆማ
ነገ የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል
ነገ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡-
ከጠዋቱ 2፡00-10፡30
👉🏾ጎፋ መከላከያ ካምፕ ፣ አሚጎ ፣ ጀሞ ሚካኤል ፣ መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ ፣ አቦ አደባባይ ፣ መካኒሳ አቦ ቤ/ክ ፣ ከፍያለው ህንጻ ፣ ከነማ መድሀኒት ቤት ድረስ እና አካባቢው፣
👉🏾ጎፋ ኮንዶሚየም ፣ ጎፋ መከላከያ ኮንዶሚንየም ፣ ጀርመን አደባባይ ፣ ቻይና ሪልእስቴት ፣ ሮያል ሴራሚክ ፣ ትግሬ ሰፈር፣ ባሌ ማህበር ፣ ዮቴክ ሪልእስቴት ፣ ፊውቸር ት/ቤት እና አካባቢው፣
👉🏾ፉሪ ፣ ኖክ ፣ ዋልያ ብረታ ብረት ፣ ካፒታል ሲሚንቶ ጀርባ፣ወለቴ ፣ ወለቴ ኢንዱስትሪ መንደር ፣ ኖክ ማደያ ፣ ባለወልድ እና አካባቢው፣
👉🏾ካራቆ፣ ረጲ ት/ቤት ፣ወሌ ኮንዶሚኒየም፣ ወለቴ ማርያም መውጫ፣ ወለቴ ቶታል፣ ወለቴ ኖክ ፣ ወጨጫ ማሪያም ፣ ወጨጫ ጎርጊስ ፣ካራ በከፊል ፣ አጃንባ ኮንዶሚየም ፣ ጥላሁን ከብት እርባታ ፣ ደግነት ኮንዶሚየም ፣ ኬላ እና አካባቢው፣
👉🏾ጉሙሩክ ፣ ቅመማ ቅመም ፣ ነጋ ቦንገር ፣ አደይ አበባ በከፊል ፣ ሳሪስ አዲስ ሰፈር እና አካባቢው፣
ከረፋዱ 4፡00-6፡00
👉🏾ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጎጃም በረንዳ ጫፍ ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና ፣ ቄጤማ ተራ፣ ፓስተር አደባባይ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ እና አካባቢው፣
👉🏾ዋሽንግተን ሆስፒታል ፣ ቦሌ ሚካኤል ኮንዶሚየም ፣ ቦሌ ሚካኤል ቤ/ ክ፣ 3ኛ በር ፣ 4ኛ በር ፣ 5ኛ በር ፣ 6ኛ በር ፣ ናቲ ሆቴል ፣ ጎርጎሪዎስ ቤ/ ክ ፣ መልካ ወከና ማህበር እና አካባቢው፣
👉🏾 ቡልቡላ ጊዮርጊስ ፣ ቡልቡላ ሰፈር በከፊል ፣ ሪሴንቲ ፣ሶማሌ ተፈናቃይ ሰፈር ፣ አየር መንገድ ራዳር ፣ ክሬቸር እና አካባቢው፣
👉🏾 ወሎ ሰፈር ፣ ኡራኤል፣ አዋሬ ቤተ መንግስት እና አካባቢው፣
ከጠዋቱ 3፡00-11፡00
👉🏾አዘዞ፣ ጎርጎራ፣ጣና፣ጎርጎራ ሪዞርት፣ ጯሂት፣ አንገርባ፣ ሳንጃ፣ ቀበሌ6፣7፣8፣9፣4፣5፣ክራክር፣ማሰሮ እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋጣል ፡፡
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ_አገልግሎት ገልፃል።

❤16👍7
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ኤርትራ ወታደሮቿን ታስወጣ-የፈረንሳይ አምባሳደር‼️
“በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የቀሩ የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ለቀው ይውጡ” ሲሉ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጥሪ አቀረቡ፡፡ በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቻርጅ ደ አፌይር የሆኑት አምባሳደር ሰብስቤ ባዴ አድቤብ በወቅታዊ ጉዳዮች ከ‹‹ዘ አፍሪካን ጋዜት›› ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ትላንት ለንባብ በበቃው ቃለ ምልልሳቸው ኤርትራ ወታደሮቿንና ከባድ መሳሪያዎችን ድንበር ጥሳ ማስገባቷን ገልፀው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን መንግስት ለመጣል የሚጥሩ የትግራይ አማፅያንን እየደገፈች መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አምባሳደር ሰብስቤ የኤርትራ ጦር በከባድ መሳሪያና በሜካናይዝድ ሀይል ታግዞ የኢትዮጵያን ድንበር በመጣስ ራማ፣ ሽራሮ፣ ባድመ፣ አዲግራትና ዛላምበሳ ኮሪደርን ጨምሮ በርካታ ቦታዎች ገብቶ እንደነበር ጠቅሰው በተጨማሪም ‹‹ወደድንበር ያፈገፈጉትን የህወሀት ታጣቂዎች እንደገና ለማደራጀት ጥረት አድርጓል›› ሲሉም ክስ አቅርበዋል፡፡ ምንም እንኳ ወታደራዊ ፍጥጫው እንዳለ ቢሆንም አምባሳደሩ በዚህ ቃለ ምልልሳቸው ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንደምትፈልግ ደጋግመው ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራ ወደውይይት እንድትገባ ጥሪ ማቅረቡን ጠቅሰውም ምንም አይነት አዎንታዊ ምላሽ እንዳልተገኘ አስረድተዋል፡፡
ሲናገሩም ‹‹አሁንም ቢሆን የኤርትራ ሀይሎች በኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ እነዚህ ወታደሮች በፍጥነትና ሙሉ በሙሉ ከግዛቷ እንዲወጡና ኤርትራ በአገራችን ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን እንድታቆም እንጠይቃለን›› ካሉ በኋላ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህንን የጠብ ጫሪነት ድርጊት እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ጋዜጣው እንደገለፀው ለዚህ የአምባሳደሩ አስተያየት የኤርትራን ምላሽ የጠየቀ ቢሆንም መልስ ለማግኘት አልቻለም፡፡

👍17🤪11❤9🥰1
«የተቃዋሚዎች ሕብረት የፌዴራል መንግሥት የጋራ ጠላት መሆኑን አውጃለሁ በማለት ትግሉን ማጠናከሩን አስታወቀ»
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ጋር ውጊያ ላይ የሚገኘው የ«ትብብር ለህልውና» ጥምረት፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች መብት ለማስጠበቅ በሚል የሚያደርገውን ሁለገብ ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጫው ማሳወቁ ተመላክቷል።
ሕብረቱ አዲስ መሠረቱን ይፋ ካደረገ በኋላ ባካሄደው የመጀመሪያ መደበኛ ስብሰባ ሒደት፣ አሁን ያለው የብልጽግና መንግሥት ለብሔሮችና ብሔረሰቦች ሰላም ከልብ እንደማይቆረቆር በመጥቀስ የሁሉም የጋራ ጠላት እንደሆነ መወንጀሉ ታውቋል።
በማኅበራዊ ሚዲያ በተሰራጨው እና ትብብሩ መግለጫ ባወጣበት የቪዲዮ መድረክ ላይ፤ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መሪ ዘመነ ካሴ መግለጫውን ያነበቡ ሲሆን፣ በጎናቸውም የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ተወካይ እና የህወሓቱ ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መታየታቸው ተገልጿል።
እንዲሁም በስብሰባው ላይ የደብረጽዮን ምክትል አቶ አማኑኤል አሰፋ በወታደራዊ ልብስ አሰናድተው መገኘታቸው እና የትግራይ ኃይሎች አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ፍሰሐ ኪዳኑ መሳተፋቸው ተመላክቷል።
ይህ ጥምረት መስከረም ወር አጋማሽ ላይ መመሥረቱ ከታወጀ ወዲህ፣ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ከተቀሰቀሱ ግጭቶች በኋላ መሪዎቹ በአንድ መድረክ ላይ በአካል ተገናኝተው ሲታዩ የመጀመሪያው መሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል።

👍28❤20🤣12🤪2🏆1🙈1
🚨 WW3 ፣ የሳይበር ጥቃት ወይስ አስከፊ የተፈጥሮ አደጋ ? ወይስ የተለመደ የአደጋ ዝግጁነት ?
ብሪታንያ ፣ ጃፓን እንዲሁም በርካታ የአውሮፓ አገራት መንግሥታት ዜጎቻቸው በድንገተኛ አደጋ ጊዜ ቢያንስ ለ72 ሰዓታት፣ አንዳንዶቹም እስከ አንድ ሳምንት የሚበቃ ምግብ፣ ውሃ፣ የመጀመሪያ እርዳታ መሣሪያዎች፣ ባትሪ፣ ፓወር ባንክና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በቤታቸው እንዲያዘጋጁ እያሳሰቡ ነው።
ማሳሰቢያዎቹ እንደ ጦርነት ፣ ሳይበር ጥቃትና የተፈጥሮ አደጋ ባሉ ሁኔታዎች የመብራት፣ የውሃና የመገናኛ አገልግሎቶች ሊቋረጡ እንደሚችሉ በመገመት እርዳታ እስኪደርስ ድረስ ቤተሰቦች ራሳቸውን እንዲችሉ ለማዘጋጀት የቀረቡ ናቸው።
ሆኖም እነዚህ የዝግጁነት ጥሪዎች በቅርቡ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት (WW3) ወይም ሌላ አስከፊ የዓለም አደጋ ይከሰታል የሚል ይፋዊ ማስጠንቀቂያ አይደሉም።
በብዙ አገራት የ72 ሰዓት ዝግጁነት ምክር የቆየ አሠራር ሲሆን የቅርብ ጊዜዎቹ ጥሪዎችም ነባር የዝግጁነት ማሳሰቢያዎችን የማደስና የማጠናከር እርምጃዎች ናቸው።
በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካው መከላከያ መስሪያ ቤት ዋና ዋና የጦር ሰፈሮች ያለ ውጭ ድጋፍ ለ90 ቀናት ያህል አስፈላጊ አገልግሎቶቻቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችል ዕቅድ እያዘጋጀ መሆኑን ፎክስ ኒውስ ዘግቧል። ዕቅዱ የሲቪል ሕዝብን ሳይሆን የወታደራዊ ተቋማትን የዝግጁነት አቅም ለማጠናከር የታቀደ ነው።

❤13👍6
አስገራሚ እውነታዎች ስለእንቅልፍ
• የሰው ልጅ የዕድሜውን አንድ ሦስተኛ የሚያሳልፈው በእንቅልፍ ነው። ይህም በአማካኝ 25 ዓመት ይሆናል።
• በቀን ከ7 ሰዓት በታች መተኛት የሰዎችን አማካኝ የመኖሪያ ዕድሜ ይቀንሳል።
• አላርም (የሚያነቃ ሰዓት) ከመፈጠሩ በፊት እንግሊዝ እና አየርላንድ ውስጥ ሰዎችን ከእንቅልፍ በመቀስቀስ የሚተዳደሩ ሠራተኞች ነበሩ። ሠራተኞቹ ማልደው ተነስተው በር እያንኳኩ ደምበኞችን ከእንቅልፍ ያስነሱ ነበር።
• ቀንድ አውጣ ያለማቋረጥ ለ3 ዓመት መተኛት ይችላል።
• ድመቶች የዕድሜያቸውን 70 በመቶ የሚያሳልፉት በእንቅልፍ ነው። ድመቶች በቀን እስከ 16 ሰዓት ይተኛሉ።
• አሜሪካን ለ1 ቀን ብቻ ያስተዳደሩት ፕሬዝዳንት ዴቪድ አቹሰን፤ ከ24 ሰዓት የስልጣን ዘመናቸው ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፉት በእንቅልፍ ነበር። ጊዜውም እ.ኤ.አ መጋቢት 4 ቀን 1894 ነው።
• ማይግሬን (ከባድ የራስ ምታት)፣ ዝቅተኛ የደም ግፊት እና የእንቅልፍ መቆራረጥ፣ የቅዥት ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው።
• በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ፓል ከርን የተባለ የሀንጋሪ ወታደር የፊት ግንባሩን በጥይት ተመቶ እንቅልፍ የሚቆጣጠረው የአይምሮው ክፍል ላይ ከባድ ጉዳት ይደርስበታል። በዚህም ወታደሩ ለ40 ዓመታት ያህል (ቀሪ ዕድሜውን) ያለ እንቅልፍ አሳልፏል።
• ቀጭኔዎች ንቁ ለመሆን በቀን ከ5 እስከ 30 ደቂቃ ብቻ መተኛት በቂያቸው ነው። ቀጭኔዎች በቀን በአማካኝ እስከ 5 ሰዓት ይተኛሉ።
• ሞርፊን የሚለው ቃል የመጣው ሞርፈስ ከተባለው የጥንት ግሪኮች የእንቅልፍ እና የህልም አምላክ ነው። ሞርፊን የከባድ በሽታዎች የህመም ማስታገሻ ሲሆን በታማሚዎች ላይም የእንቅልፍ ስሜት ይፈጥራል።
• ምሽት ላይ ካፌን ያላቸው እንደ ቡና ፤ ሻይ እና ኮካ ያሉ (የሚያነቃቁ) መጠጦችን መጠጣት ፤ አይምሯችን ሜላቶኒን የተባለውን የእንቅልፍ ሆርሞን የሚለቅበትን ጊዜ እንዲዘገይ ያደርገዋል። ይህም መደበኛውን የእንቅልፍ ስርዓት በአማክኝ እስከ 40 ደቂቃ ድረስ ያዛባል።
• የመተኛት ፍርሃት ሶምኒ ፎቢያ ይባላል።
• አብዛኛው ሰው አልጋ ላይ ከወጣ በኃላ በ7 ደቂቃ ውስጥ እንቅልፍ ይወስደዋል።
• ስራን በወቅቱ የማይሰሩ ሰዎች ለእንቅልፍ ችግር (ኢንሶምኒያ) የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው።
• በተደጋጋሚ በነውጥ (ሁከት) የተሞሉ ህልሞችን ማየት፤ እንደ ፓርኪንሰን (የሚያንቀጠቅጥ በሽታ) እና ድሜንሻ (የመርሳት በሽታ) ያሉ የአይምሮ ህመሞች ምልክት ሊሆን ይችላል።
• ህልም እያዩ ህልም መሆኑን መረዳት እና የህልሙን ትዕይንት በተወሰነ መልኩ መቆጣጠር መቻል ሉሲድ ድሪም ይባላል። በተለይ ቪዲዮ ጌም መጫወት የሚያዘወትሩ ሰዎች እንዲህ አይነት ህልሞችን በተደጋጋሚ ያያሉ።
• ከ80 በላይ በሳይንስ የተለዩ የእንቅልፍ ችግሮች አሉ።
• የዓለም ህዝብ ቁጥር አንድ የእንቅልፍ መስተጓጎል ምክንያት ኢንተርኔት ነው።
• ከመተኛታችን ከ2 ሰዓት በፊት ቴሌቭዥን ማየት እንዲሁም ስልክ እና ኮምፒዩተር መጠቀም እንቅልፍ ያስተጓጉላል።
• የሰው ልጅ በአማካኝ የዕድሜውን 6 ዓመት የሚያሳልፈው ህልም በማየት ነው።
• ዳክዬዎች የሚተኙት አንድ አይናቸው ሳይከደን ነው።
• ስሉዝ የተባሉት እንስሳቶች 80 በመቶ የሚሆነውን የዕድሜያቸውን ከፍል የሚያሳልፉት በእንቅልፍ ነው። ዓለም ላይ ቁጥር አንድ እንቅልፋም እና ዘገምተኛ እንስሳቶች ስሉዝዎች ናቸው።
• ከየብስ እንስሳቶች በሙሉ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ያላቸው ዝሆኖች ናቸው። ዝሆኖች በቀን እስከ 2 ሰዓት ብቻ ይተኛሉ።
• በእንቅልፍ ልብ የሚበሩ ወፎች አሉ። በተለይ ስደተኛ ወፎች (ወቅት እየጠበቁ ከሀገር ሀገር የሚጓዙ) አየር ላይ ለአጭር ጊዜ ያሸልባሉ።

❤24👍12
ቀን23/02/19 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 03 01 00 06
📞09 57 97 40 82
🔵የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
🔶ደመወዝ===150dollar
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ===10&12
🔵የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
🔶ደመወዝ===200-1000 dollar
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶 ልምድ===0-5አመት
🔶የት/ት ደረጃ= 12+
🔵position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
🔶ደመወዝ===13500+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የ/ት ደረጃ===10
🔵position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
🔶ደመወዝ===13000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ===8+
🔵positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
🔶ደመወዝ===15000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===አይጠይቅም
🔶የት/ደረጃ===6-12
🔵position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
🔶ደመወዝ-16000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ==8-12
🔵position===ሞዴል አሰልጥኖ
🔶ደመወዝ===15000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ===10
🔵potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
🔶ደመወዝ===15000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ0===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ==8-12
🔵position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
🔶ደመወዝ===14000
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🔵position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
🔶ደመወዝ===12000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0-1አመት
🔶የት/ትደረጃ ==8-12
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ የዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞09 57 97 40 82
📞 09 03 01 00 06
አድራሻ መገናኛ መተባበር
ህንፃ 4 ፎቅ ቢሮ ቁ B421
https://t.me/familyWorke
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 03 01 00 06
📞09 57 97 40 82
🔵የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
🔶ደመወዝ===150dollar
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ===10&12
🔵የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
🔶ደመወዝ===200-1000 dollar
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶 ልምድ===0-5አመት
🔶የት/ት ደረጃ= 12+
🔵position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
🔶ደመወዝ===13500+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የ/ት ደረጃ===10
🔵position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
🔶ደመወዝ===13000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ===8+
🔵positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
🔶ደመወዝ===15000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===አይጠይቅም
🔶የት/ደረጃ===6-12
🔵position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
🔶ደመወዝ-16000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ==8-12
🔵position===ሞዴል አሰልጥኖ
🔶ደመወዝ===15000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ===10
🔵potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
🔶ደመወዝ===15000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ0===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ==8-12
🔵position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
🔶ደመወዝ===14000
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0አመት
🔶የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🔵position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
🔶ደመወዝ===12000+
🔶ፆታ===ወ/ሴት
🔶ልምድ===0-1አመት
🔶የት/ትደረጃ ==8-12
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ የዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞09 57 97 40 82
📞 09 03 01 00 06
አድራሻ መገናኛ መተባበር
ህንፃ 4 ፎቅ ቢሮ ቁ B421
https://t.me/familyWorke
👍3❤2
ቅዱስ ሲኖዶስ በአርሲ ዞን በምእመናን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በማውገዝና ችግሩን ለመፍታት ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ እንዲያዝ መወሰኑን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን መርቲ እና ሸርካ ወረዳዎች በምእመናን ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ጥቃት በጽኑ ማውገዙን ገልጾ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከተው የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ጋር ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ እንዲያዝ ውሳኔ አሳለፈ።
ቅዱስ ሲኖዶስ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም. ባወጣው የሀዘን መግለጫ፤ በዞኑ መርቲ ወረዳ አንጋዳ ቀበሌ ጎራ ሲሊንጎ በተባለ ቦታ 14 ምእመናን፣ እንዲሁም በሸርካ ወረዳ ጠሬታ፣ ጮሌ እና ቢርቦ ቀበሌዎች 46 ምእመናን በጠቅላላው 60 ሰዎች ግፍ በተሞላበት ሁኔታ መገደላቸውን ጠቁሟል።
Via Addis Maleda

👍11❤8
አራት ኪሎ ግራም ጫት የሰረቀው ግለሰብ አራት አመት ከአስራ አንድ ወር እስራት ተፈረደበት።
በምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ኮቦልቻ ወረዳ ውስጥ አራት ኪሎ ግራም ጫት የሰረቀው የግለሠብ አራት አመት ከአስራ አንድ ወራት እስራት እንደተፈረደበት የምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ አስታውቋል።
የፖሊስ ዋና መምሪያው የኮምንኬሽን እና ሚዲያ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ካሲዬ አበበ ለብስራት እንደተናገሩት ተከሳሽ ከድር መሐመድ ኡመር የተባለው ግለሰብ በምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ኮቦልቻ ወረዳ ሐቢሶ ቀበሌ ውስጥ የአንዱ ዋጋ አስር ሺሕ ብር የሚያወጣ ጐሲፕ የተባለ እጅግ ውድ ጫት የሰው ግቢ በአጥር ዘሎ በመግባት አራት ኪሎ ሰርቆ ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ሊውል ችልዋል።
ተከሳሹ ግምቱ አርባ ሺሕ ብር የሚያወጣ ጫት ቆርጦ በአጥር ዘሎ ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ውሎ የምርመራ መዝገቡ ተጣርቶ በመጠናቀቅ ለአቃቢ እንደተላከ ገልፀዋል።
አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በስርቆት ወንጀል፣ ክስ የመሠረተ ሲሆን ክሱን የተመለከተው የኮቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ጥቅምት 20ቀን 2019 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ከድር መሐመድ አራት ኪሎ ግራም ጫት በመስረቁ በአራት አመት ከአስራ አንድ ወራት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ኢንስፔክተር ካሲዬ አበበ ጨምረው ገልፀዋል።ዳጉ

🤣19❤15🤩5👍3🤔2😢1
የክልል ፕሬዝዳንቶች ወታደራዊ ስልጠና
የክልል ፕሬዝዳንቶች ከህዳር 5/2019 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ወታደራዊ ስልጠና ሊገቡ መሆኑን ሰምተናል።
ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የፌዴራል አመራሮች በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ሲሆን በቀጣይ ዙር ወደ ማሰልጠኛ የሚላኩ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ አመራሮች ይኖራሉ።

🤪15❤14👍5🤣3
Forwarded from Basic 1
#Ads
😀 📱 😀 📱 LinkedIn😀 📱 😀 📱
✅ የሊንኪዲን አካውንት በረጅም ጊዜ አጋርነት መከራየት እንፈልጋለን።📱
📱 we have fair price , ማርኬቱን ያማከለ
✅ ከ 300+ በላይ እና ከአንድ አመት በላይ ( 2025 and before ) ተመራጭ ነው 📱
✅ አካውንትዎን ለእኛ ቢያከራዩን እኛ ደግሞ በታማኝነት እንከራያለን።መለያችን ታማኝነት ነው። 📱
✅ እኛ የምንከፍለው ሂሳብ ገበያውን በጣም ያማከለ ነው። 📱
📱 ማከራየት ከፈለጉ በዚህ ያግኙን @LinkedInethiorental 💬
channel = #Ads

channel = https://t.me/+Q8MUmu_sWzJhMDNk📣 📢
📣 📢
channel = #Ads
channel = https://t.me/+Q8MUmu_sWzJhMDNk
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍4❤2🥰1
የኢራኑ መሪ ትፅዛዝ ሰጡ‼️
የ #ኢራን የበላይ መሪ ወታደራዊ ኃይላቸው ለማንኛውም የ #አሜሪካ እና የ #እስራኤል ዛቻ «ያለ ጂኦግራፊያዊ ገደብ» ምላሽ እንዲሰጡ አዘዙ
አዲስ የተቀሰቀሰውን ቀጠናዊ ጦርነት ለማስቀረት የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በቀጠሉበት ወቅት፣ የኢራን የበላይ መሪ አያቶላህ ሞጅታባ ካመኒ የሀገሪቱ የታጠቁ ኃይሎች ከአሜሪካ ወይም ከእስራኤል ለሚሰነዘር ማንኛውም ዛቻ ያለ ምንም ጂኦግራፊያዊ ገደብ ወዲያውኑ ምላሽ እንዲሰጡ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ገልፃለች።

👍9❤8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሱዳን የተቃጠለው የኤርትራ ገንዘብ‼️
ቲኤን ኒውስ እንደዘገበው በሱዳን ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተዘዋወረ የሚገኝ አንድ የቪዲዮ ምስል፣ በእሳት እየነደደ ባለ አንድ ቤት ውስጥ በአብዛኛው ትላልቅ ኖቶች የሆኑ ከፍተኛ መጠን ያላቸው የኤርትራ የገንዘብ ኖቶች (ናቅፋ) አብረው ሲቃጠሉ ያሳያል።
የኤርትራ መንግስት በቅርቡ ዜጎች በእጃቸው የሚገኘውን የናቅፋ ገንዘብ በሙሉ ወደ ባንክ አካውንታቸው እንዲያስገቡ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል። የባንክ አካውንት የሌላቸው ዜጎችም አዲስ አካውንት እንዲከፍቱ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
ይህ የመንግስት እርምጃ በዋናነት በሱዳን እና በትግራይ አካባቢዎች ከባንክ ስርዓት ውጪ ተከማችቶ የሚገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ጥሬ ገንዘብ ወደ መደበኛው የባንክ ስርዓት ለመመለስ ያለመ መሆኑ ይገመታል።
ይሁን እንጂ ይህ የወጣው ቪዲዮ፣ አሁንም ቢሆን እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው ናቅፋ ከባንክ ስርዓት ውጪ ተደብቆ ወይም ተከማችቶ እንደሚገኝ ጠቋሚ ነው።
የኤርትራ ባለስልጣናት ከባንክ ውጪ ያለው የገንዘብ ክምችት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ካረጋገጡ፣ ከዚህ ቀደም ተጠቅመውበት ወደ ነበረው ጠንከር ያለ እርምጃ ሊገቡ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይኸውም አዳዲስ የገንዘብ ኖቶችን ወደ ገበያ በማስገባት አሮጌዎቹ ኖቶች ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ ማድረግ ሲሆን፣ ይህ እርምጃ ከባንክ ስርዓት ውጪ የተከማቸውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ዋጋ አልባ ሊያደርገው ይችላል።

❤21👍8🤪7
ፆረና‼️
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ፆረና በሚባል አካባቢ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 23 የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
መከላከያ ሰራዊት ሮኬት ጭምር እየተጠቀመ መሆኑን ገልፀውልናል።
Via : አዩዘሀበሻ

👍14❤12🤣5💔1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ሪፖርተር ታገደ‼️
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሪፖርተር ጋዜጣ እና ኦንላይን ስርጭት የምዝገባ ምስክር ወረቀትን ላልተወሰነ ጊዜ አገደ‼️
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሴንተር ኃ.የተ.የግል ማህበር ሥር የሚታተሙትን ሪፖርተር (አማርኛ)፣ ዘ ሪፖርተር (እንግሊዝኛ) ጋዜጦች እና የኢትዮጵያን ሪፖርተር ዲጂታል ፕላትፎርም የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከሰኞ፣ ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከህትመትና ከስርጭት ሙሉ በሙሉ ማገዱን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት ላለፈው አንድ ዓመት ባደረገው የይዘት ክትትል፣ በሚዲያ ተቋሙ ተደጋጋሚ የህግ እና የሙያ ስነ-ምግባር ጥሰቶች መፈጸማቸውን ባደረገው ማረጋገጫ ውሳኔው መተላለፉን ገልጿል።
እንደ ባለስልጣኑ መግለጫ፣ በጥሰት ከተለዩት ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የሚጻረሩ ይዘቶችን በተደጋጋሚ ማሰራጨት፣
በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አውድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያላቸውን ርዕሰ ጉዳዮች ከአርዕስት (Headline) ጀምሮ ማጮህ (Sensationalize ማድረግ)፣
ሀገራዊ መረጃዎችን ከአጠቃላይ አውዳቸው ውጪ በቁንጽል እይታ በመዘገብ በህብረተሰቡ ዘንድ ብዥታና ጥርጣሬ መፍጠር፣
በውጭ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝምና ዲፕሎማሲ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተዛቡ መረጃዎችን ማሰራጨት፣
የሀገር ገጽታንና ብሔራዊ ደህንነትን የሚጎዱ፣ እንዲሁም የህዝቦችን አብሮነት የሚያጠፉ ዘገባዎችን ማቅረብ፣
ሚዛናዊነት የጎደላቸውና በግል ፍላጎት ላይ ተመስርተው የተቋማትን ስም የሚያጠልሹ ዘገባዎችን ማሰራጨት ይገኙበታል።
ባለስልጣኑ አክሎ እንዳመለከተው፣ ላለፈው አንድ ዓመት ከተቋሙ ባለቤትና ዋና አዘጋጆች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ለማረም ቢሞከርም ምንም ዓይነት መሻሻል አልታየም።
በዚሁ መሰረት፣ ተቋሙ ህጋዊና ሙያዊ ግዴታዎቹን አሟልቶ እስኪያቀርብ ድረስ የምዝገባ ምስክር ወረቀቱ ታግዶ እንደሚቆይና ውሳኔው ከጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ በጥብቅ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።

❤22👍6🤩6😢1