🏘 40% ብቻ ከፍለው ቀሪውን 60% የቤቶን ቁልፍ እጆ ካስገቡ ቡኋላ የሚከፍሉት ልዩ እድል ከቴምር ሪልስቴት
🏘 ባለ 1 መኝታ ከ60 እስከ 71 ካሬ
🏘 ባለ 2 መኝታ ከ90 እስከ 105 ካሬ
🏘 ባለ 3 መኝታ ከ112 እስከ 145 ካሬ
🌴ቴምር ሪል እስቴት የማይደገም ዕድል በአዲስ ሳይት በመሀል መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ ይዞላቹ መቷል።
👉 እንዲሁም 100% ለሚከፍሉ ደምበኞች ደግሞ የ35% ታላቅ ቅናሽ ለውስን ቤቶች ቀድመው ቦታ ይያዙ
👉 ልብ ይበሉ ያለምንም የዋጋ ጭማሪ
👉ተጨማሪ ሼባ ማይልስ ይበረከትሎታል
ለበለጠ መረጃ
📞0942-16-42-62 ይደውሉ

❤3👍2
ቡና እና እርግዝና‼️
በእርግዝና ወቅት በቀን ከሁለት ስኒ ቡና በላይ መጠጣት የፅንስ ማቋረጥን ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቆመ።
በእርግዝና ወቅት ሙሉ ለሙሉ ቡና መጠጣት ባይከለከልም ከመጠን ያለፈ ሲሆን ግን በእናትየዉም ይሁን በህፃኑ ላይ የተለያዩ ችግሮችን እንደሚያስከትል ጥናቶች አመልክተዋል።
እንደየስኒው መጠን እና የቡናዉ ዉፍረት በዉስጡ የሚይዘዉ ካፊን የሚለያይ በመሆኑ ነፍሰጡር ሴቶች በቀን ከሁለት ስኒ ቡና በላይ ባይጠጡ ይመከራል ።
በእርግዝና ወቅት በቀን ዉስጥ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ቡና መጠጣት በተለይም የመጀመሪያዎቹ ሶስት እና አራት ወራት ላይ የማቅለሽለሽ ወይንም የሆድ ህመምን ሊያባብስ እንደሚችል ተገልጿል።
በእናትየዉ ላይ ከሚያሳድረዉ የጭንቀት ፣ የእረፍት ማጣት እና የእንቅልፍ ችግር በተጨማሪ የህፃኑን እድገትም እንደሚጎዳ ተጠቁሟል ። ቡና ዉስጥ ያለዉ ካፊን በማህፀን በኩል ወደ ፅንሱ የሚተላለፍ ሲሆን በእርግዝና ወቅትም ከፍተኛ መጠን ያለዉ ቡና መጠጣት የፅንስ ማቋረጥን ሊያስከትል እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ።
@Addis_Reporter

👍12❤7🤣1
ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ‼️
በዛሬው ዕለት 26 አውቶብሶች ከነዳጅ ወደ በተፈጥሮ ጋዝ ተለውጠው ስራ መጀመራቸው ታውቋል።
በቅርቡ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ 400 የከተማ አውቶቡሶች ከውጪ ይገባሉ ተብሏል።
ይህ እርምጃ የጉዞ ታሪፍን በግማሽ ያቃልላል ተብሏል።

❤14🤪13👍3
የኦሮሚያ መንግስት ለኦርቶዶክስ ምድራዊ ሲኦል ሁኗል
ከአርሲው ጥቃት ጋር ተያይዞ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች መታሰራቸው ተገለፀ
በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምስራቃዊ ዞን አርሲ-ሺርካ ወረዳ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ከተፈጸመ ወዲህ፣ የሟቾችን አስከሬን የቀበሩ እና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ወደ ጤና ተቋማት ወሰዱ የተባሉ ነዋሪዎች በአካባቢው አስተዳዳሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ። ነዋሪዎቹ እና የጥቃቱ ሰለባ ዘመዶች ለዶቼ ቬለ እንደገለጹት የአካባቢው ባለስልጣናት የተጎጂዎችን ዘመዶች "ምንም ምክንያት ሳይኖር" በማሰራቸው በአካባቢው ከፍተኛ ተቃውሞ እየተሰማ ነው።
ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም.በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምስራቃዊ ዞን አርሲ-ሺርካ ወረዳ ቢርቦና ጮሌ ቀበሌ በታጣቂዎች በተፈፀመው ጥቃት አብዛኞቹ ክርስቲያን የሆኑ ወደ 60 የሚጠጉ ንጹሃን ዜጎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል።
ጥቃቱን ተከትሎ በአካባቢው የክልሉ ጸጥታ አካላት በመሰማራታቸው አንጻራዊ ሰላም ያለ ቢመስልም ስጋቱ እንዳልተወገደ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ጥቃቱን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጠው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ራሱን ‘ፅምዶ’ ብሎ የሚጠራው ኃይል የብሔርና «የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር ያደረገው ጥፋት ነው» ያም ሆኖ ጥረቱ ከሽፋል ማለታቸው ይታወሳል።

😢30❤18👍5😡3✍1
ኢትዮጵያ Su-35 ማግኘቷ ግብፅ የቻይናውን J-10C ጀት ግዥ እንድታፋጥን ማስገደዱ ተገለፀ
አዲስ አበባ — ኢትዮጵያ የሩሲያ ሰራሽ Sukhoi-35 (Su-35) ዘመናዊ ተዋጊ ጀቶችን መታጠቋን ተከተሎ፣ ግብፅ የቻይናውን J-10C ተዋጊ ጀት ግዥ ለመፈጸም የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንድታፋጥን ማድረጉን በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው "ሚሊተሪ ዋች ሜጋዚን" ዘገበ።
እንደ ዘገባው ከሆነ፣ ግብፅ እ.ኤ.አ በ2018 ከሩሲያ Su-35 ጀቶችን ለመግዛት ተዋውላ የነበረ ቢሆንም ከአሜሪካ በደረሰባት የፖለቲካ ጫና ምክንያት ውሉን ለመሰረዝ ተገዳለች። ይህም በአሁኑ ወቅት የካይሮ አየር ሀይል ከአየር ወደ አየር የሚደረግ ውጊያ ላይ የሚመጥነው ዘመናዊ ተዋጊ ጀት እጥረት እንዲገጥመው አድርጎታል።
በአሁኑ ወቅት በግብፅ አየር ሀይል ጥቅም ላይ የሚገኙት የሩሲያው MiG-29M፣ የፈረንሳዩ Rafale እና የአሜሪካው F-16 ጀቶች ሲሆኑ፣ እነዚህም ከኢትዮጵያው Su-35 አቅም ጋር ሲነፃፀሩ ከአየር ወደ አየር በሚደረግ ውጊያ አነስተኛ አቅም ያላቸው መሆናቸው ተመልክቷል።
ይህንን የአየር ሀይል የቴክኖሎጂ ክፍተት ለመሙላት እና ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውዝግብ ጋር ተያይዞ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወታደራዊ የሃይል ሚዛን ለማስተካከል ግብፅ የቻይናውን J-10C ጀት ለመግዛት ያቀረበችውን ጥያቄ እያፋጠነች ይገኛል።

❤23🤣17👍4🤔2
በትግራይ ክልል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ቢያንስ 12 ሰዎች ተገደሉ
በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ዛሬ አርብ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ቢያንስ 12 ሰዎች መገደላቸውን የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ዘገባ አመላከተ። ዜና ወኪሉ የህክምና ምንጮችን እና የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው በጥቃቱ በርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሶል።
አንድ የዓይን እማኝ ለዜና ወኪሉ በሰጡት ቃል፤ ጥቃቱ የተፈጸመው ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ ተመቶ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ የነበረ እህልን በማንሳት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ግጭቶችን የሚከታተለው ኤሲኤልኢዲ (ACLED) የተሰኘው ተቋም ባወጣው መረጃ፤ ጥቃቱ በራማ ከተማ ሰላማዊ ሰዎችን በያዘ የ«አይሱዙ» ተሽከርካሪ ላይ የተፈጸመ መሆኑን ጠቁሟል። በጥቃቱ 12 ሰላማዊ ሰዎች ከመገደላቸው በተጨማሪ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች መጎዳታቸውን እና በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን አስታውቋል።
ተቋሙ አክሎ እንዳመለከተው፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና አጋሩ የትግራይ የሰላም ሀይል በማዕከላዊ ትግራይ ዞን ተንቤን የተለያዩ አካባቢዎችን ተቆጣጥረው በዚያም የድሮን ቅኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

😢11❤9👍2🤯1🙏1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
አሳዛኝ ዜና፡ አርቲስት አንተነህ ተኸርቁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ‼️ በበርካታ የኪነ-ጥበብ ሥራዎችና በስፖርት ዘርፍ በሚያሳየው ተሳትፎ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀው ወጣቱ አርቲስት አንተነህ ተኸርቁ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። አርቲስቱ ከዚህ ቀደም በጽኑ ታሞ በነበረበት ወቅት፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለ ምንም የዘርና የሃይማኖት ልዩነት ተባብሮለት አገግሞ ወደ ሥራው ተመልሶ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።…
«በወልቂጤ ዙሪያ በደረሰ ጥቃት አርቲስት አንተነህ ተኸርቁና ሌሎች አሽከርካሪዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ»
አርቲስት አንተነህ ተኸርቁ የዕለት ከዕለት ሥራውን ለማከናወን በነበረበት የኮሮላ ተሽከርካሪ ከጅማ የመጣች ደንበኛን ይዞ ከአዲስ አበባ ወደ ሰባት ቤት ጉራጌ (ወልቂጤ) በመጓዝ ላይ በነበረበት ወቅት ጥቃቱ ሰለባ ሆኗል።
በጉዞ ላይ እያለ ምሽት 4:30 አካባቢ የተሽከርካሪው ጎማ በመበላሸቱ የተሽከርካሪውን ጎማ ለመቀየር ወይም ለመጠገን ባቆመበት አቅራቢያ በነበሩ የታጠቁ አካላት ጥቃት እንደተፈጸመበት ተመላክቷል።
በትላንትናው ዕለት በተፈጸመው በዚህ አሳዛኝ ድርጊት አርቲስቱን ጨምሮ ሌሎች አሽከርካሪዎች ሕይወት ማለፉ የተገለጸ ሲሆን፣ በጉዞ ላይ ባሉ ንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ መሰል ጥቃቶችን ለማስቆም የጸጥታ መዋቅሮች የመንገድ ላይ ደህንነትንና ቁጥጥርን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማኅበረሰቡ ጥሪ ማቅረቡ ታውቋል።
ለሟቾች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እና ለአድናቂዎቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

💔26❤19👍3🤯1
#ሰበር መረጃ‼️
ብርጌድ ንሓመዱ የኢሳይያስ አፈወርቂን መንግሥት ለማስወገድ አብዮታዊ ትግል ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የኤርትራ ወጣቶች በሙሉ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ማዘዙን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
Via : አዩዘሀበሻ

👍30🤪9❤7
📣ምርት እና አገልግሎቶን በቅናሽ ያስተዋውቁ!!
➠ ሱቆች ➠ ሆቴሎች እና ሬስቶራንት
➠ ሽያጭ ➠ ቴሌግራም ቻናል
➠ ድርጅቶች ➠ የቲቪ ፕሮግራም
➠ ት/ቤቶች ➠ ስልጠናዎች
➠ ሆስፒታል ➠ ክሊኒኮች
➠ websites ➠ Events
➠ ሆቴሎች ➠ ፈርኒቸር ቤቶች
➠ ባዛር ➠ ዝግጅቶች እና ሌሎችንም
የድርጅታችሁን ወይም የሱቃችሁን ህጋዊነት በማረጋገጥ ምርትና አገልግሎቶን እንዲያስተዋውቁ እድሉን አመቻችተናል። በቻናላችን በማስተዋወቅ ለብዙዎች ይድረሱ... ትርፋማ እና ተመራጭ ይሁኑ።
ከታች ባሉት ሊንኮች ያነጋግሩን።
👉@Addis_reporter_bot

👍4❤3
ስለ ዲቪ-2027‼️
የአሜሪካ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል የተሰጠውን ውሳኔ ስላገደው፣ የ DV-2027 ዲቪ ሎተሪ ምዝገባ እንደታገደ ነው።
ዋና ዋና መረጃዎች:-👇
የፍርድ ቤት እገዳ፦ የታችኛው ፍርድ ቤት ዳኛ ምዝገባው በዚህኛው ህዳር ወር (November 1/2026) እንዲጀመር አዞ የነበረ ቢሆንም፣ የአሜሪካ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ግን ይህንን ትዕዛዝ አግዶታል።
የአሁኑ ሁኔታ፦ በአሁኑ ሰዓት ለDV-2027 ምንም ዓይነት የምዝገባ ሂደት እየተካሄደ አይደለም፤ እንዲሁም በይፋ የተቀመጠ የምዝገባ ቀን የለም።
ከማጭበርበር ይጠንቀቁ፦ ይፋዊው የዲቪ ሎተሪ ምዝገባ ሁልጊዜም ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆኑን እና ምዝገባው የሚካሄደው በአሜሪካ መንግስት ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ ብቻ መሆኑን ለማህበረሰቡ ያስታውሱ። ማንኛውም ደላላ ወይም ሶስተኛ ወገን ቪዛ ሊያሰጥ ወይም አስቀድሞ ሊያስመዘግብ አይችልም።
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት፦ የማህበረሰቡ አባላት ወደፊት የሚወጡ ይፋዊ መመሪያዎችን ወይም ማስታወቂያዎችን ለመከታተል የ U.S. Department of State Diversity Visa Portal ድረ-ገጽን እንዲከታተሉ ይመከራል።
ሁኔታዎች ከተቀየሩ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

❤18👍3😢1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ከሀገረ ስብከታቸው ተነሱ።
ብፁዕነታቸው ለ6 ወራት እስከ ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በየትኛውም ሀገረ ስብከት ሳይመደቡ በደብረ ሊባኖስ ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ተወስነው በሱባኤና በጸሎት እንዲቆዩ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳለፈ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉ ተገልጿል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ በሚመሩት ሀገረ ስብከት ላይ ከፍተኛ አስተዳደራዊና ቀኖናዊ ጥፋት ፈጽመዋል ያላቸው ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ላይ ቀኖናዊ ውሳኔ በማሳለፍ ለ6 ወራት እስከ ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በገዳም ተወስነው በሱባዔና በፀሎት እንዲቆዩ ወስኗል።
ቀደም ሲል ጉዳዩ በአጀንዳነት ተይዞ የአጣሪዎች ሪፖርት በንባብና በቪድዮ ለቅዱስ ሲኖዶስ መቅረቡ ተገልጿል።
በአጣሪ ልዑካን ከማስረጃዎች ጋር የቀረቡ፦
- የሰነድ ማስረጃዎች፣
- የሂሳብና ንብረት ቁጥጥር ሪፖርት ፣
- ከሊቀውንት ጉባኤ ፣ ከሕግ አገልግሎትና ከሕግ አማካሪ የቀረቡ የውሳኔ ሐሳቦች በቅደም ተከተል ከቀረቡ በኋላ የአህጉር ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ለተፈጠሩት ጥፋቶች በጉባኤው ፊት በአካል ቀርበው ይቅርታ ጠይቀዋል።
ትላንት ደግሞ የይቅርታ ጥያቄያቸውን በቀረቡት የቀኖና ጥሰቶች፣ የአስተዳደርና ፣ የአሠራር ክፍተቶች በመጥቀስ የይቅርታ ጥያቄዎቻቸውን ለምልዓተ ጉባኤው በጽሑፍ አቅርበዋል።
ምልዓተ ጉባኤውም ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ያቀረቡትን የይቅርታ ደብዳቤ በንባብ ከሰማ በኋላ በየርዕሰ ጉዳዩ ተገቢውን የቀኖና እና አስተዳደራዊ ውሳኔ ለመስጠት በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም ፦
1. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ለቀረቡባቸው የቀኖና ጉዳዮች እስከ ግንቦት 2019 ዓ.ም የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ድረስ በየትኛውም ሀገረ ስብከት ሳይመደቡ በደብረ ሊባኖስ ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም በጸሎትና በሱባኤ ተወስነው እንዲቆዩ፤
2. ብፁዕነታቸው ለአህጉረ ስብከት ማስረከብ ይገባቸው የነበሩ መኪኖችን ወደ ገዳም ከመሄዳቸው በፊት ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲያስረክቡ፤
3. ከሂሳብ ጋር በተያያዘው እስከ ግንቦት 2019 ዓ.ም የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በሚገባ ተጠርቶ እንዲቀርብ እና ውሳኔ እንዲያገኝ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል።
በሌላ በኩል፥ ቅዱስ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር) በያዙት ሀገረ ስብከት ላይ ደርበው የጋምቤላ ሀገረ ስብከትን እንዲመሩ ወስኗል።
ብፁዕነታቸው በአሁኑ ወቅት የምዕራብ ወለጋና ኢሉ አባቦራ ሀገረ ስብከትን በሊቀ ጳጳስነት እየመሩ ይገኛሉ።

❤16👍7🤣7🙏1🏆1
Forwarded from Basic 1
#Ads
😀 📱 😀 📱 LinkedIn😀 📱 😀 📱
✅ የሊንኪዲን አካውንት በረጅም ጊዜ አጋርነት መከራየት እንፈልጋለን።📱
📱 we have fair price , ማርኬቱን ያማከለ
✅ ከ 300+ በላይ እና ከአንድ አመት በላይ ( 2025 and before ) ተመራጭ ነው 📱
✅ አካውንትዎን ለእኛ ቢያከራዩን እኛ ደግሞ በታማኝነት እንከራያለን።መለያችን ታማኝነት ነው። 📱
✅ እኛ የምንከፍለው ሂሳብ ገበያውን በጣም ያማከለ ነው። 📱
📱 ማከራየት ከፈለጉ በዚህ ያግኙን @LinkedInethiorental 💬
channel = https://t.me/+4u1_Nb8yoKMxNTZk📣 📢
channel = https://t.me/+4u1_Nb8yoKMxNTZk
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍3❤1🥰1
16 አገልግሎቶችን ወደ «መሶብ አንድ ማዕከል» በማዘዋወር የእንግልትና የሙስና ስጋት ሊቀረፍ ነው አለ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ከሙስና የጸዳ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት የስመ-ንብረት ዝውውርን ጨምሮ 16 የመሬት ነክ አገልግሎቶችን ወደ «መሶብ አንድ ማዕከል» ማስገባቱን አስታወቀ።
ይህ አዲስ እርምጃ ደንበኞች ቀደም ሲል አገልግሎት ለማግኘት ያጋጥማቸው የነበረውን እንግልት፣ መዘግየትና አላስፈላጊ ተጨማሪ ወጪ በእጅጉ የሚቀንስ መሆኑ የአገልግሎት ማሻሻያ እና መሬት መረጃ ዘርፍ ከሰራተኞች ጋር ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ የውይይት ሰነድ ያቀረቡት የአገልግሎት ማሻሻያ እና መሬት መረጃ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ዲሪባ ግርማ እንደገለጹት፤ አገልግሎቶቹ ወደ «መሶብ አንድ ማዕከል» መግባታቸው የከተማዋን የመሬት አስተዳደር ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ በማድረግ የተያዘውን ትልቅ ግብ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ህብረተሰቡም የተሳለጠና ፈጣን አገልግሎት ለማግኘት ለዚሁ አላማ ወደተዘጋጁት የመሶብ አንድ ማዕከል መስኮቶች በመቅረብ ወይም የተዘረጉትን የዲጂታል አማራጮች በስፋት እንዲጠቀሙ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ አሰራሩ ህዝቡ በዘርፉ ያነሳ የነበረውን አጣዳፊ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚመልስ ታምኖበታል።

❤7👍5
የከፍተኛ መንግሥት ባለሥልጣናት በሁርሶ ወታደራዊ ሥልጠና ላይ ናቸው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የካቢኔ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚዎች በሁርሶ ወታደራዊ ማዕከል ሥልጠና እየተከታተሉ መሆኑን ገለጹ።

🤣44👍18❤8🤡5🤪2🤷♂1👀1
ቴምር ሪልእስቴት አዲስ ሳይት መገናኛ ቤል ቪው ሆቴል አጠገብ በ35% ቅናሽ ይዘን መጥተናል።
🏘 ባለ 2 መኝታ ከ90 እስከ 105 ካሬ
🏘 ባለ 3 መኝታ ከ112 እስከ 145 ካሬ
🏘 ፒንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 ካሬ
የሳይቱ ልዩ መገለጫ
✅ Top veiw መሆኑ
✅ ፔንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 የካሬ አማራጭ
✅40% ከፍላችሁ 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት
✅ ያለምንም ወለድ የሚከፈል
✅ የጫካ ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል
✅20% ቅድመ ክፍያ
✅35% ቅናሽ
🌴ቴምር ሪል እስቴት የማይደገም ዕድል በአዲስ ሳይት በመሀል መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ ይዞላቹ መቷል።
ለበለጠ መረጃ
📞0942-16-42-62 ይደውሉ
🏘 ባለ 2 መኝታ ከ90 እስከ 105 ካሬ
🏘 ባለ 3 መኝታ ከ112 እስከ 145 ካሬ
🏘 ፒንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 ካሬ
የሳይቱ ልዩ መገለጫ
✅ Top veiw መሆኑ
✅ ፔንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 የካሬ አማራጭ
✅40% ከፍላችሁ 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት
✅ ያለምንም ወለድ የሚከፈል
✅ የጫካ ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል
✅20% ቅድመ ክፍያ
✅35% ቅናሽ
🌴ቴምር ሪል እስቴት የማይደገም ዕድል በአዲስ ሳይት በመሀል መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ ይዞላቹ መቷል።
ለበለጠ መረጃ
📞0942-16-42-62 ይደውሉ
❤2👍2
የባሕር ኃይል አዛዡ፣ "ኢትዮጵያ ወደ ወደብ መመለሷ የማይቀር" ስለሆነ ከቀጠናው አገራት ጋር በቅርበትና በንግግር መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ጥሪ አቀረቡ‼️
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም. ፦ የኢትዮጵያ ወደ ባሕር በር ባለቤትነት የመመለስ ጉዳይ አይቀሬ በመሆኑ ከጎረቤት አገራት ጋር በቅርበት መሥራት እና በውይይት መመራራት አስፈላጊ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አዛዥ ምክትል አድሚራል ክንዱ ገዙ ገለጹ። አዛዡ ጥሪውን ያቀረቡት በቀጣናዊ የባሕር ላይ ደኅንነት ዙሪያ ጠንካራ ትብብርና ውይይት እንዲደረግ ባሳሰቡበት ወቅት ነው።
እንደ አገሪቱ መከላከያ ሠራዊት መረጃ፤ ምክትል አድሚራል ክንዱ ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ባዘጋጀው ቀጣናዊ የባሕር ደኅንነት የምክክር መድረክ ማጠቃለያ ላይ ነው።

❤16🤣10👍9🤪2
አሜሪካ በአርሲ በንጹሃን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዘች❗❗
በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በንጹሃን ዜጎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የታለሙ የግድያ ወንጀሎች ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠሩበት የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው በሰጠው መግለጫ፣ በሃይማኖት፣ በብሔር ወይም በፖለቲካ ምክንያት የሚፈጸሙ ማናቸውም ዓይነት ጥቃቶች ፈጽሞ ተቀባይነት የሌላቸውና ወዲያውኑ ሊቆሙ የሚገባቸው አስነዋሪ ድርጊቶች መሆናቸውን ገልጿል።
የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ አያይዞም፣ የተከሰተውን አሳዛኝ ሁኔታ ለመረዳት ጥረቶች እየተደረጉ ባለበት በዚህ ሰዓት፣ ማህበረሰቡን የበለጠ ሊያለያዩና ክፍፍል ሊፈጥሩ ከሚችሉ ነገሮች መቆጠብ እንደሚገባ አሳስቧል። በዜጎች ላይ የሚደርሱ እንዲህ ያሉ አስከፊ ጥቃቶች ዘግናኝ መሆናቸውን ጠቁሞ፣ በጉዳዩ ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማውም አስታውቋል።
በመጨረሻም የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ የኢትዮጵያ መንግሥት አፋጣኝ ማጣራት በማካሄድ፣ ወንጀሉን የፈጸሙ አካላትን ለሕግ እንዲያቀርብ ጥሪ አቅርቧል። የሰላምና የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እና ጥፋተኞች ተጠያቂ እንዲሆኑም አጽንኦት ሰጥቷል።

👍33❤13😡4🙏2