አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.7K subscribers
17.7K photos
437 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አርሰናል ከባየር ሙኒክ ሜዳ ላይ ነጥብ ይዞ ወጣ

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ መርሃ ግብር ተጠባቂ ጨዋታ በጀርመን አሊያንዝ አሬና ተካሄዷል።

አርሰናል ከአስተናጋጁ ባየር ሙኒክ ጋር አቻ በመለያየት ጠቃሚ ነጥብ ይዞ መመለስ ችሏል።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ አርሰናሎች በኤቤሬቺ ኢዜ ጎል ቀዳሚ መሆን ችለው ነበር።

ይሁን እንጂ ዴቪስ ባስቆጠራት ግብ ባየር ሙኒክ አቻ መሆን ችሏል።

በሁለተኛው አጋማሽ አስተናጋጆቹ በሃሪ ኬን የፍጹም ቅጣት ምት መሪነቱን ቢረከቡም፣ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ደቂቃዎች ሲቀረው ዲክላን ራይስ ያስቆጠራት ድንቅ ግብ የአርሰናልን አቻ ውጤት አረጋግጣለች።

በዚህም መሰረት ጨዋታው ባለበት 2 አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ሁለቱም ክለቦች ነጥብ ተጋርተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤21👍10🤣2
ቦይንግ 737 MAX 10 አውሮፕላን የመጨረሻ የምስክር ወረቀት አገኘ

የአሜሪካ ፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር ለቦይንግ 737 MAX 10 አውሮፕላን የመጨረሻ የምስክር ወረቀት በመስጠት አውሮፕላኑን ለአየር መንገዶች ማስረከብ እንዲጀመር ፈቃድ ሰጥቷል።

ለዓመታት የዘለቀውን ማረጋገጫ የማግኘትን ሂደት ያጠናቀቀው ቦይንግ የ737 MAX ተከታታይ አውሮፕላኖች ትልቁን ሞዴል ለደንበኞቹ ለማስረከብ የነበረውን ዋነኛ እንቅፋት ማስወገዱን አስታውቋል።

አውሮፕላኑ ከአውሮፓው ኤርባስ ጋር የሚያደረገውን የገበያ ውድድር ለማጠናከር ወሳኝ ነው ተብሏል።

ቦይንግ የአውሮፕላኑን ርክክብ በ2020 ለመጀመር አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የቴክኒክ ችግሮችና የቁጥጥር ሂደቶች ምክንያት ለዓመታት ተራዝሟል።
 
እያንዳንዱ አውሮፕላንም ተጨማሪ የበረራ ብቃት ፈቃድ ከተሰጠው በኋላ ብቻ ነው መንገደኞችን ማጓጓዝ የሚችለው።

Via:- ሮይተርስ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤6👍3
የሚዋጥ የወሊድ መከላከያ  መድሀኒትን መጠቀም ለጡት ካንሰር ያጋልጣል ተባለ

የጡት ካንሰር በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ደረጃ  በአንደኝነት በተለይም የሴቶችን ህይወት እየቀጠፈ ያለ በሽታ ነው ፡፡

የጡት ካንሰር በአብዛኛው ሴቶችን የሚያጠቃ እንደሆነና በዋናነት የሚተላለፈው በቤተሰብ ከእናት ወደ ልጅ  ቢሆንም ሌላው ተጋላጭነትን የሚጨምሩ መንገዶች ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮልን አዘውትሮ መጠቀም አለመውለድ እና  አለማጥባት እንደሆኑ ለብስራት ሬዲዮ የተነናገሩት በወራቤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቤተሰብ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ሔርሜላ አየለ  ናቸው፡፡

በተጨማሪም ለወሊድ መከላከያ ተብሎ የሚወሰደውን የሚዋጥ መድሀኒት መጠቀም እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ ከ40 ዓመት በላይ መሆን ለበሽታው ተጋላጭ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡በሽታው በዋናነት ጎልቶ የሚታየው ከአርባ ዓመት በላይ ቢሆንም አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ስርጭቱ እየጨመረ በመምጣቱ ከ30 ዓመት ጀምሮ ላሉ ሴቶች የቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋለው ትልቁ ችግር ከረፈደ በኋላ ማለትም በሽታው ወደ ሌላ ሰውነት ክፍሎች ከተሰራጨ በኋላ እና  ሰውነታቸውም ተጎድቶ አቅም ከሳጣቸው በኋላ ወደ ህክምና ተቋማት መድረስ እንደሆነ የህክምና ባለሙያው ገልፀዋል፡፡

በሽታው ግን በጊዜ ከተደረሰበት እና ወደ ሳንባ፣ ወደ ጉበት፣ ወደ አጥንት እና ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሳይሰራጭ እባጩን ባለበት ከተገኘ ቀዶጥገና ተሰርቶ እና የጨረር ህክምና ወስዶ የመዳን እድሉ 90 በመቶ እእደሆነ ተናግረዋል።
 
ለካንሰር ህክምና የሞኖግራፊ ምርመራ ተመራጭ አንደሆነ እና በተለያዩ ሀገራት ይህንን መሳሪያ ይጠቀማሉ፡፡ ነገር ግን በመካከለኛ እና በዝቅተኛ በሆኑ ሀገራት የአለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው መስፈርት አካላዊ የጡት ምርመራ በማድረግ ምርመራው እንደሚሰጥ አብራርተዋል።
 
በምርመራውም በጡት ውስጥ ከ2 ሴንቲሜትር ጀምሮ ያለ እባጭ ማግኘት ዶ/ር ሔርሜላ አየለ  ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤11👍4🤪2
ቴምር ሪልእስቴት አዲስ ሳይት መገናኛ ቤል ቪው ሆቴል አጠገብ በ35%  ቅናሽ ይዘን መጥተናል።

🏘 ባለ 2 መኝታ ከ90 እስከ 105 ካሬ
🏘 ባለ 3 መኝታ ከ112 እስከ 145 ካሬ
🏘 ፒንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 ካሬ

የሳይቱ ልዩ መገለጫ
✅ Top veiw መሆኑ
✅ ፔንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 የካሬ አማራጭ
✅40% ከፍላችሁ 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት
✅ ያለምንም ወለድ የሚከፈል
✅ የጫካ ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል
✅20% ቅድመ ክፍያ
✅35% ቅናሽ

🌴ቴምር ሪል እስቴት የማይደገም ዕድል በአዲስ ሳይት በመሀል መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ ይዞላቹ መቷል።

ለበለጠ መረጃ
📞0942-16-42-62 ይደውሉ
❤6👍2
ሞያሌ‼️
በሞያሌ ከተማ እንደገና በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች ወደ ኬንያ በመሰደድ ላይ ናቸው።
በኦሮሚያ እና በሱማሌ ክልሎች አወሳሰን ምክንያት በሞያሌ ከተማ ትላንት ረጋ ብሎ የነበረው ግጭት ዛሬ ማለዳ እንደገና መቀስቀሱ ተገለጸ።

ከስፍራው ያገኘናቸው የመረጃ ምንጮች እንደጠቆሙት፣ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ የሚሰማ ሲሆን፣ የከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ቆሟል።

በከተማዋ ባለው የአስፓልት መንገድ ግራና ቀኝ በሱማሌ እና በኦሮሞ ተከፍሎ በሚገኘው የሞያሌ ከተማ፣ የይገባኛልና የባለቤትነት ጥያቄን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ይህ ግጭት ከቀበሌ ሁለት ተነስቶ አሁን ላይ በሙሉ ከተማዋ ውስጥ ተስፋፍቶ ይገኛል።

የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ከተማዋ የገቡ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ተኩሱን ማስቆም እንዳልተቻለ ታውቋል።

ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ እንዲሁም ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡት ዋና ዋና መንገዶች ሙሉ በሙሉ ዝግ ሆነዋል።
የግጭቱን መበርታት ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ ኬንያ ሞያሌ በመሻገር ላይ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤22😢6👍4😎1😡1
የ #ኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ምዘና ደረጃ አሁንም አሽቆለቆለ‼️

የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት (WJP) ይፋ ባደረገው የ2026 የሕግ የበላይነት መረጃ ጠቋሚ መሰረት፣ የኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት አፈጻጸም አሁንም ማሽቆልቆሉ ተመልክቷል። በዚህም መሠረት አገሪቱ ከ143 አገሮች መካከል 133ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። አዲሱ ግምገማ ሀገሪቱ ደረጃዋ ለበርካታ ዓመታት መሽቆልቆሉን መቀጠሉን ይፋ በማድረግ ከዓለም አቀፍ እና ከሰሃራ በታች ካሉ አፍሪካ አገሮች ደረጃ ግርጌ መቀመጧን አመላክቷል።

ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ይፋ የሆነው የ2026 መረጃ ጠቋሚ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአምባገነንነት አዝማሚያ እየሰፋ መምጣቱን፣ በአስፈጻሚ አካል ላይ የሚደረጉ የቁጥጥር ገደቦች መዳከማቸውን፣ የዳኝነት ነፃነት መቀነሱን እና በመሠረታዊ ነፃነቶች ላይ የሚደረጉ ገደቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕግ የበላይነት እንዲሸረሸር አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት (WJP) ሲያስጠነቅቅ መቆየቱን ተከትሎ የወጣ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍16❤8😢3
ከ600 ሺሕ ብር በላይ የዳኝነት ክፍያ ይጠየቅበት የነበረው የመሬት ይዞታ ማስለቀቅ አገልግሎት ነፃ ተደረገ ‼️
እንደ ጉዳዩ ይዘት 600 ሺሕ ብርና ከዚያ በላይ የዳኝነት ክፍያ ይጠየቅበት የነበረው የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ነፃ መደረጉን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ አስታወቀ፡፡
አገልግሎቱ ነፃ የተደረገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ እንደገና ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 13/2018 ተግባራዊ መደረግ በመጀመሩ ነው፡፡ 
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ፕሬዚዳንት አቶ ኦልያድ ሥዩም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትንና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን ወጥቶ የነበረውን አዋጅ ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1161/2011 መሠረት በማድረግ፣ እንደገና የወጣው ደንብ ቁጥር 13/2018፣ እንዲሁም ላለፉት 24 ዓመታት ሥራ ላይ የነበረውንና ክፍተቶች የነበሩበትን ደንብ ቁጥር 30/1994 የሚተካ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀድሞው ደንብ መሠረት የመሬት ይዞታና ካሳ ጉዳዮችን የተመለከተ ቅሬታ ያለው አንድ ባለ ጉዳይ ለይግባኝ ሰሚ ጉባዔው ሲያቀርብ የዳኝነት ክፍያ እንዲከፍል ይደረግ እንደነበር፣ በአሁኑ ወቅት ግን ለልማት ብሎ ይዞታውን የሚለቅ ሰው፣ ይዞታውን ከመልቀቅ አልፎ ለዳኝነትም ክፍያ የሚጠየቅ ከሆነ የመክፈል አቅም እንደማይኖረው ከግምት በማስገባት ቅሬታውን በነፃ እንዲያቀርብ መደረጉን ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍8🤪3
ሞያሌ ትኩረት ይፈልጋል‼️
በከባድ መሣሪያ ተኩስ ልውውጥ ሳይቀር የታጀበው #በሞያሌ የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ ሶስት ተጨማሪ ወረዳዎች ተስፋፋ

#በኦሮሚያ ክልል #ቦረና ዞን በምትገኘው የድንበር ከተማ ሞያሌ፣ የሶማሌ ክልል ሰንደቅ ዓላማ በመሰቀሉ ሳቢያ በተፈጠረ ውዝግብ እና ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም. የአንድ የ13 ዓመት ታዳጊ ልጃገረድ ህይወት ማለፉን ተከተሎ የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል የጸጥታ ኃይሎች መካከል የከባድ መሣሪያ ተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል።

ከረቡዕ ምሽት ጀምሮ ሲጋጋል የቆየው ውጥረት በሐሙስ ዕለት ወደ የለየለት ግጭት የተቀየረ ሲሆን፣ በደቡብ ኦሮሚያ በሚገኙ ጉሚ ኤልዳሎ፣ ዋጪሌ እና አሬሮ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ጭምር መስፋፋቱንነዋሪዎች እና የአካባቢው የጸጥታ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ግጭቱ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም ከማለዳው 11:30 ገደማ በነማለብ፣ ጫሙቅ፣ ቦሌ፣ ቀበሌ 01 እና ዋቆ ዶጎ በተባሉ በርካታ አካባቢዎች ተቀስቅሷል።

የሞያሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዋቆ ሁሴን እንደገለጹት፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ሰንደቅ ዓላማ ለመስቀል ያደረገው ሙከራ፣ የ13 ዓመቷ ዲቆ ጃታን አጋ መገደል እና ማክሰኞ ምሽት በአንድ የከተማዋ ኃላፊ ላይ “የግድያ ሙከራ ሊፈጸም ነው” በሚል የተሰራጨ ያልተረጋገጠ አሉባልታ ለግጭቱ መባባስ ምክንያት ከሆኑት መካከል ይጠቀሳሉ ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20👍4
ወረራ አልፈፀምኩም-ኤርትራ‼️
‹‹በኢትዮጵያ ላይ ወረራ እንደፈፀምን የሚገለፀው ክስ ሙሉ በሙሉ የተፈጠረ ውሸት ነው›› ሲል የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ‹‹በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ›› በሚል ዛሬ ዘለግ ያለ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በዚህ መግለጫው ‹‹የኤርትራ ሉአላዊ ግዛት ለስምምነት ወይንም ለድርድር አይቀርብም›› ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ‹‹ለስትራቴጂያዊ አላማ አስፈላጊ ነው›› በሚል የኤርትራን ሉአላዊ ድንበር ለመውረርና ለመጣስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ እየተባባሰ ለመጣው አለመረጋጋትና ቀውስ ‹‹በኢትዮጵያ ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ሆነ ተብሎ ለአመታት የፈፀመ የጂኦ ፖለቲካ ጥቃት ውጤት ነው›› በማለት ክስ ያቀረበው መግለጫው ይህም በወታደራዊ ዛቻ፣ ዲፕሎማሲያዊ ጠላትነት፣ በኢኮኖሚ ማስፈራሪያና በገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት እንደሆነ አስታውቋል፡፡

ጨምሮም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ‹‹ሁሉም ወገኖች›› ወይንም ‹‹ሁሉም አካላት›› መረጋጋትን እንዲያሳዩና ውጥረቱን እንዲያረግቡ በሚል የሚቀርበውን ጥሪ ‹‹ህጋዊነት የጎደለውና ለዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጎጂ ነው›› በማለት ገልፆታል፡፡ እንዲህ አይነት መግለጫዎች ሉአላዊነቱን የሚከላከልንንና ጥቃት ፈፃሚውን እኩል የሚያስቀምጡ መሆናቸውን ጠቅሶምነ ለተጨማሪ ሀላፊነት የጎደለው ድርጊት በር እንደሚከፍቱ አሳስቧል፡፡ በማስከተልም ‹‹ኤርትራ ወረራ ፈፅማለች የሚለው ክስ ሙሉ በሙሉ የተፈጠረ ውሸት ነው፡፡ ይህ መሰረት የለሽ ክስ ተጠያቂነትን ለማምለጥ፣ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማታለልና የተጀመሩ የግዛት ማስፋፋት ምኞቶችን ህጋዊ ለማድረግ የተደራጀ የመረጃ ጦርነት አካል ነው›› ብሏል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20🤣8👍4🕊1
በባንክ ሂሳባቸው የሚታየውን ያልተገለጸ ከፍተኛ ገንዘብ "የእቁብ ነው" በማለት ምክንያት ለሚያቀርቡ ግለሰብ ግብር ከፋዮች ጥብቅ ማስረጃ ማቅረብ አስገዳጅ የሚያደርግ የዴስክ ኦዲት ማስፈጸሚያ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ይፋ አድርጓል።

• የተሟላ የሂሳብ መዝገብ ለማያቀርቡ የይዘት ፈጣሪዎች ከጠቅላላ ገቢያቸው ላይ 15 በመቶ ግብር ተቀናሽ ይደረጋል።

• ለዲጂታል ይዘት አመንጪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት አመንጪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክሱ ባለስልጣን የመላክ ግዴታ አለባቸው ተብሏል፡፡

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2018 የግብር ዓመት የታክስ ሂሳብ መግለጫዎች ግብርን ለማሳወቅ ሲቀርቡ የግብርና ታክስ አሰባሰብ ሂደቱን ይበልጥ ውጤታማ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ለማድረግ የሚያስችል የዴስክ ኦዲት (Desk Audit) ማስፈጸሚያ(Guideline) ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

​ቢሮው ባወጣውና ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተመለከተው ሰነድ ፣ በተለይም የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች የሚያቀርቧቸውን የሂሳብ መዛግብት በጥራትና በፍትሐዊነት ለመመርመር እንዲሁም ባለፉት ዓመታት የታዩ ክፍተቶችን ለማረም ማስፈጸሚያው ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብሏል።

በ2017 በጀት ዓመት የታክስ ሂሳብ መግለጫዎች ላይ በተደረገ ግምገማ፣ በርካታ ግብር ከፋዮች አጥጋቢ ያልሆነ የገቢ ማስታወቂያ በማቅረብ ቢሊዮን ብር የሚገመት ገቢ አሳንሰው ማስታወቃቸው መረጋገጡን ጠቅሶ፤ ይህን መሰል ህገ-ወጥ አሰራርና የገቢ ማሳነስን ለመግታት ወጥ የሆነ የኦዲት ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋቱን አስረድቷል።

በማስፈጸሚያ ሰነዱ ውስጥ ከተካተቱ ነጥቦች መካከል በባንክ ሂሳባቸው የሚታየውን ያልተገለጸ ከፍተኛ ገንዘብ "የእቁብ ነው" በማለት ምክንያት ለሚያቀርቡ ግለሰብ ግብር ከፋዮች ጥብቅ ማስረጃ አስገዳጅ ማድረግ አንዱ ነው።

ግብር ከፋዮቹ :-

- የእቁብ ሰብሳቢና ዳኛ የተፈረመበት ማስረጃ፣

- የእቁብተኞች ዝርዝር፣

- የእቁብ ደብተር፣ እንዲሁም እቁቡ በዕጣ ወይም በግዢ መገኘቱን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ካልቻሉ ገንዘቡ እንደ ንግድ ገቢ ተቆጥሮ ግብር ይጣልበታል።

የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ (ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም) ከሚያገኙት ማስታወቂያና ስፖንሰርሺፕ በተጨማሪ፣ ከተከታዮች በቀጥታ ሥርጭት (Live streaming) ወቅት የሚሰጡ ስጦታዎችና ስታሮች (Gifts/Stars)፣ የብዙሃን የገንዘብ ድጋፍ (Crowdfunding) እና የደንበኝነት ክፍያዎች (Membership Fees) ግብር እንደሚከፈልባቸው ተመላክቷል።

የተሟላ የሂሳብ መዝገብ ለማያቀርቡ የይዘት ፈጣሪዎች ከጠቅላላ ገቢያቸው ላይ 15 በመቶ ግብር ተቀናሽ ይደረጋል።

ለዲጂታል ይዘት አመንጪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች (platforms) ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት አመንጪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክሱ ባለስልጣን የመላክ ግዴታ አለባቸው ተብሏል፡፡

ልኳንዳ ቤቶች የሚያቀርቡት የሽያጭ መጠን ከቄራዎች በሚገኝ የ3ኛ ወገን የዕርድ መረጃ (የታረዱ ከብቶች ብዛትና ዓይነት) በሲስተም ተመሳክሮ ኦዲት ይደረጋል።

ስጋ ቤቱ ካሳወቀው ሽያጭ በላይ እንስሳትን ያሳረደ ሆኖ ከተገኘ፣ ልዩነቱ በአካባቢው የገበያ ዋጋ ተሰልቶ ወደ ሽያጭ እንዲለወጥና ግብር እንዲከፈልበት ይወሰናል።

የስራ ተቋራጮች በሂሳብ መዝገባቸው የሚያስመዘግቧቸው ወጪዎች ፕሮጀክቱ ካለበት የግንባታ ምዕራፍ ጋር የሚፈተሹ ሲሆን ለማሳያነትም፦

° በቁፋሮ ደረጃ ላይ ላለ ፕሮጀክት ከፍተኛ የሲሚንቶና የብረት ወጪ፣ ወይም

° በፊኒሺንግ (ማጠናቀቂያ) ላይ ላለ ህንፃ የኤክስካቫተር እና የአፈር ገልባጭ መኪና ኪራይ ወጪ ተደርጎ ከቀረበ ተቀባይነት እንደማያገኝ ተገልጿል።

ህንፃ አከራዮች ከእርጅና ቅናሽ ወጪ በፊት ያለውን ትርፍ ገንዘብ ከንግዱ አውጥተው በግል ለመጠቀም የሚያቀርቡት መከራከሪያም ገደብ ተበጅቶለታል።

በተጨማሪም የህንፃው የተከራየበትና ያላለቀ ክፍሎች፣ እንዲሁም ባዶ የሆኑት ወይም ለግል አገልግሎት የዋሉት ክፍሎች በካሬ ሜትር በግልጽ በማስረጃ መለየት እንዳለባቸው ታዟል።

መኪና አስመጪዎች ለእያንዳንዱ የተሸጠ መኪና የቆረጡት የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ እና ወደ ባንክ ገቢ የተደረገበት ቀንና የገንዘብ መጠን ካልተጣጣመ፣ በወቅቱ የገበያ ዋጋ ጥናት መሰረት ግብር እንዲከፍሉ ይደረጋል።

​ቢሮው ያወጣው ይህ ዝርዝር ማስፈጸሚያ (Guideline) ፣በግብር ከፋዮች ዘንድ በተለያዩ የሂሳብ ማጭበርበሪያ ዘዴዎች ይሸሸጉ የነበሩ ገቢዎችን በመረጃና በቴክኖሎጂ አስደግፎ ወደ ታክስ መረቡ ለማስገባት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍4
ቀን 13/02/19 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 03 01 00 06
📞09 57 97 40 82
🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
    ✨ደመወዝ===150dollar
    ✨ፆታ===ወ/ሴት
    ✨ልምድ===0አመት
    ✨የት/ት ደረጃ===10&12
🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
    ✨ደመወዝ===200-600 dollar
    ✨ፆታ===ወ/ሴት
   ✨ ልምድ===0-5አመት
    ✨የት/ት ደረጃ= ዲፕ ድግሪ
🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
     ✨ደመወዝ===13500+
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ===0አመት
     ✨የ/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
    ✨ደመወዝ===13000+
    ✨ፆታ===ወ/ሴት
    ✨ልምድ===0አመት
    ✨የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ብስኩት ፋብሪካ
    ✨ደመወዝ===14500
    ✨ዖታ===ወ/ሴት
   ✨ልምድ===0አመት
   ✨የት/ት=== ደረጃ-10+
🇪🇹positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
     ✨ደመወዝ===15000+
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ===አይጠይቅም
     ✨የት/ደረጃ===6-12
🇪🇹position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
     ✨ደመወዝ-15000+
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ===0አመት
     ✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ሞዴል አሰልጥኖ
      ✨ደመወዝ===15000+
      ✨ፆታ===ወ/ሴት
      ✨ልምድ===0አመት
      ✨የት/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ፕላስቲክ ፋብሪካ
     ✨ደመወዝ===12500+
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ===0አመት
     ✨የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
     ✨ደመወዝ===15000+
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ0===0አመት
     ✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
     ✨ደመወዝ===14000
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ===0አመት
     ✨የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🇪🇹position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
✨ደመወዝ===12000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0-1አመት
✨የት/ትደረጃ ==8-12
🇪🇹position👉አምፖል ማምረት
   ✨ደመወዝ===13,000
   ✨ፆታ===ወ/ሴት
   ✨ልምድ===0አመት
   ✨የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ሹፌር
    ✨ደመወዝ 14-22000
    ✨ፆታ===ወ
    ✨ልምድ=2አመት
    ✨የት/ት ደረጃ===ህዝብ1/ደረቅ/2/3/
🇪🇹position👉አካውንታት
   ✨ደመወዝ=14500+
   ✨ፆታ===ወ
   ✨ልምድ===0-5አመት
   ✨የት/ት ደረጃ===digree
🇪🇹position👉ሆስተስ
   ✨ደመወዝ===25000
   ✨ፆታ=/ሴት
   ✨ልምድ===0-አመት
   ✨የት/ት ደረጃ10-12
🇪🇹position👉ቴሌ ማርኬተር ሽያጭ
    ✨ደመወዝ===13500
    ✨ፆታ===ወ/ሴት
    ✨ልምድ===0-1አመት
    ✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ቀለም ፍብሪካ
    ✨ደመወዝ===16000
    ✨ዖታ===ወ/ሴት
    ✨ልምድ===አይጠይቅም
    ✨የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹position👉 ጫኝ አውራጅ
     ✨ደመወዝ===10000+
     ✨ዖታ===ወ/
     ✨ልምድ===0-አመት
     ✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ማናጀር ለሆቴል
    🔶ደመወዝ===18,000
    ✨ፆታ===ወ/ሴት
    ✨ልምድ===0-2
    ✨የት/ት ደረጃ===digree
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ ነዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞09 57 97 40 82
     📞 09 03 01 00 06
     አድራሻ መገናኛ መተባበር
     ህንፃ 4 ፎቅ ቢሮ ቁ B421
https://t.me/familyWorke
❤6👍2
ቻይና በመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች‼

በቻይና ቲቤት ግዛት በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 0 ማግኒቲዩድ የመሬት መንቀጥቀጥ
መከሰቱ ተገለፀ።
አደጋው የተከሰተው በሰሜናዊ ቲቤት ላሳ ከተማ 400 ኪሎ ሜትር ገደማ  ርቆ ነው ተብሏል።

በአደጋው የደረሰ የንብረት ውድመትም ሆነ  የሰው ህይወት መጥፋት እስካሁን የወጣ ዝርዝር መረጃ ባይወጣም የሰዎች መፈናቀል ግን ተስተውሏል።

ይሁን እንጂ የመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት ሊኖረው ስለሚችል የሚመለከታቸው አካላት ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ ይገኛሉ።

የነፍስ አድን ሰራተኞች እና የእሳት አደጋ ቡድኖች ወደ ስፍራው ተሰማርተው የረድኤት ስራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውም ተሰምቷል።

የቻይናውባለስልጣናት የመሬት መንቀጥቀጡ በቲቤት መከሰቱን ከማሳወቅ ባለፈ፣ የአደጋውን ሁኔታ አላብራሩም ።

ነገር ግን ወደ 7 ማግኒቲዩድ የሚጠጉ የመሬት መንቀጥቀጦች ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርሱ  ዥንዋን ጠቅሶ ቮይስ ኦፍ ኤምሬትስ አስነብቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤7👍5
የእቁብ ነው የሚል ማታለያ አይሰራም‼️
በባንክ ሂሳባቸው የሚታየውን ያልተገለጸ ከፍተኛ ገንዘብ "የእቁብ ነው" በማለት ምክንያት ለሚያቀርቡ ግለሰብ ግብር ከፋዮች ጥብቅ ማስረጃ ማቅረብ አስገዳጅ የሚያደርግ የዴስክ ኦዲት ማስፈጸሚያ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ይፋ አድርጓል።

• የተሟላ የሂሳብ መዝገብ ለማያቀርቡ የይዘት ፈጣሪዎች ከጠቅላላ ገቢያቸው ላይ 15 በመቶ ግብር ተቀናሽ ይደረጋል።

• ለዲጂታል ይዘት አመንጪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት አመንጪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክሱ ባለስልጣን የመላክ ግዴታ አለባቸው ተብሏል፡፡

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2018 የግብር ዓመት የታክስ ሂሳብ መግለጫዎች ግብርን ለማሳወቅ ሲቀርቡ የግብርና ታክስ አሰባሰብ ሂደቱን ይበልጥ ውጤታማ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ለማድረግ የሚያስችል የዴስክ ኦዲት (Desk Audit) ማስፈጸሚያ(Guideline) ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

​ቢሮው ባወጣውና ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተመለከተው ሰነድ ፣ በተለይም የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች የሚያቀርቧቸውን የሂሳብ መዛግብት በጥራትና በፍትሐዊነት ለመመርመር እንዲሁም ባለፉት ዓመታት የታዩ ክፍተቶችን ለማረም ማስፈጸሚያው ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብሏል።

በ2017 በጀት ዓመት የታክስ ሂሳብ መግለጫዎች ላይ በተደረገ ግምገማ፣ በርካታ ግብር ከፋዮች አጥጋቢ ያልሆነ የገቢ ማስታወቂያ በማቅረብ ቢሊዮን ብር የሚገመት ገቢ አሳንሰው ማስታወቃቸው መረጋገጡን ጠቅሶ፤ ይህን መሰል ህገ-ወጥ አሰራርና የገቢ ማሳነስን ለመግታት ወጥ የሆነ የኦዲት ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋቱን አስረድቷል።

በማስፈጸሚያ ሰነዱ ውስጥ ከተካተቱ ነጥቦች መካከል በባንክ ሂሳባቸው የሚታየውን ያልተገለጸ ከፍተኛ ገንዘብ "የእቁብ ነው" በማለት ምክንያት ለሚያቀርቡ ግለሰብ ግብር ከፋዮች ጥብቅ ማስረጃ አስገዳጅ ማድረግ አንዱ ነው።

ግብር ከፋዮቹ :-

- የእቁብ ሰብሳቢና ዳኛ የተፈረመበት ማስረጃ፣

- የእቁብተኞች ዝርዝር፣

- የእቁብ ደብተር፣ እንዲሁም እቁቡ በዕጣ ወይም በግዢ መገኘቱን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ካልቻሉ ገንዘቡ እንደ ንግድ ገቢ ተቆጥሮ ግብር ይጣልበታል።

የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ (ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም) ከሚያገኙት ማስታወቂያና ስፖንሰርሺፕ በተጨማሪ፣ ከተከታዮች በቀጥታ ሥርጭት (Live streaming) ወቅት የሚሰጡ ስጦታዎችና ስታሮች (Gifts/Stars)፣ የብዙሃን የገንዘብ ድጋፍ (Crowdfunding) እና የደንበኝነት ክፍያዎች (Membership Fees) ግብር እንደሚከፈልባቸው ተመላክቷል።

የተሟላ የሂሳብ መዝገብ ለማያቀርቡ የይዘት ፈጣሪዎች ከጠቅላላ ገቢያቸው ላይ 15 በመቶ ግብር ተቀናሽ ይደረጋል።

ለዲጂታል ይዘት አመንጪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች (platforms) ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት አመንጪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክሱ ባለስልጣን የመላክ ግዴታ አለባቸው ተብሏል፡፡

ልኳንዳ ቤቶች የሚያቀርቡት የሽያጭ መጠን ከቄራዎች በሚገኝ የ3ኛ ወገን የዕርድ መረጃ (የታረዱ ከብቶች ብዛትና ዓይነት) በሲስተም ተመሳክሮ ኦዲት ይደረጋል።

ስጋ ቤቱ ካሳወቀው ሽያጭ በላይ እንስሳትን ያሳረደ ሆኖ ከተገኘ፣ ልዩነቱ በአካባቢው የገበያ ዋጋ ተሰልቶ ወደ ሽያጭ እንዲለወጥና ግብር እንዲከፈልበት ይወሰናል።

የስራ ተቋራጮች በሂሳብ መዝገባቸው የሚያስመዘግቧቸው ወጪዎች ፕሮጀክቱ ካለበት የግንባታ ምዕራፍ ጋር የሚፈተሹ ሲሆን ለማሳያነትም፦

° በቁፋሮ ደረጃ ላይ ላለ ፕሮጀክት ከፍተኛ የሲሚንቶና የብረት ወጪ፣ ወይም

° በፊኒሺንግ (ማጠናቀቂያ) ላይ ላለ ህንፃ የኤክስካቫተር እና የአፈር ገልባጭ መኪና ኪራይ ወጪ ተደርጎ ከቀረበ ተቀባይነት እንደማያገኝ ተገልጿል።

ህንፃ አከራዮች ከእርጅና ቅናሽ ወጪ በፊት ያለውን ትርፍ ገንዘብ ከንግዱ አውጥተው በግል ለመጠቀም የሚያቀርቡት መከራከሪያም ገደብ ተበጅቶለታል።

በተጨማሪም የህንፃው የተከራየበትና ያላለቀ ክፍሎች፣ እንዲሁም ባዶ የሆኑት ወይም ለግል አገልግሎት የዋሉት ክፍሎች በካሬ ሜትር በግልጽ በማስረጃ መለየት እንዳለባቸው ታዟል።

መኪና አስመጪዎች ለእያንዳንዱ የተሸጠ መኪና የቆረጡት የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ እና ወደ ባንክ ገቢ የተደረገበት ቀንና የገንዘብ መጠን ካልተጣጣመ፣ በወቅቱ የገበያ ዋጋ ጥናት መሰረት ግብር እንዲከፍሉ ይደረጋል።

​ቢሮው ያወጣው ይህ ዝርዝር ማስፈጸሚያ (Guideline) ፣በግብር ከፋዮች ዘንድ በተለያዩ የሂሳብ ማጭበርበሪያ ዘዴዎች ይሸሸጉ የነበሩ ገቢዎችን በመረጃና በቴክኖሎጂ አስደግፎ ወደ ታክስ መረቡ ለማስገባት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19👍8
ቴምር ሪልእስቴት አዲስ ሳይት መገናኛ ቤል ቪው ሆቴል አጠገብ በ35%  ቅናሽ ይዘን መጥተናል።

🏘 ባለ 2 መኝታ ከ90 እስከ 105 ካሬ
🏘 ባለ 3 መኝታ ከ112 እስከ 145 ካሬ
🏘 ፒንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 ካሬ

የሳይቱ ልዩ መገለጫ
✅ Top veiw መሆኑ
✅ ፔንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 የካሬ አማራጭ
✅40% ከፍላችሁ 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት
✅ ያለምንም ወለድ የሚከፈል
✅ የጫካ ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል
✅20% ቅድመ ክፍያ
✅35% ቅናሽ

🌴ቴምር ሪል እስቴት የማይደገም ዕድል በአዲስ ሳይት በመሀል መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ ይዞላቹ መቷል።

ለበለጠ መረጃ
📞0942-16-42-62 ይደውሉ
❤5👍2
የህክምና ባለሙያዎች የህክምና ስህተት የመመርመር እና ዉሳኔ የመስጠት ሀላፊነት ለከተማዋ ጤና ቢሮ ተሰጠ

ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት ተግባራት ወደ አዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተካቷል።

ቢሮዉ በዛሬዉ እለት በሰጠዉ መግለጫ እንዳስታወቀው ፤የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፍቃድ ፤  የጤና ተቋት ብቃት ማረጋገጥ አገልግሎት እና  የጤና ባለሙያዎች  ሥነ-ምግባር  እና  የህክምና ስህተት የሚመረምር እና ውሳኔ የሚሰጥ ወይም የሜዲኮ ሌጋል   አገልግሎት ከባለስልጣኑ  ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ  ተላልፈዋል ።

ቢሮው  ተግባሩን ተረክቦ አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ  ግብዓቶችን  በማሟላት ፣ አደረጃጀቶችን  እንዲሁም ቀደምብሎ ስራውን  ሲሰሩ የነበሩ  ባለሙያዎች ወደ ጤና  ቢሮው  በመዛወር አስፈላጊውን ቅድመ  ዝግጅት  መጠናቀቁን ዶክተር ዮሐንስ ጫላ  በሰጡት መገለጫ ተናግረዋል ፡፡

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን በአካል ቀርቦ ለማግኘት  ከጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም  ጀምሮ ፒያሳ በሚገኘው የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ህንጻ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው  የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ  የተለመደውን አገልግሎት ማግኘት የሚቻል  መሆኑም  በመግለጫዉ ተነግሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15👍2
📣ምርት እና አገልግሎቶን በቅናሽ ያስተዋውቁ!!

➠ ሱቆች       ➠ ሆቴሎች እና ሬስቶራንት
➠ ሽያጭ       ➠ ቴሌግራም ቻናል
➠ ድርጅቶች   ➠ የቲቪ ፕሮግራም
➠ ት/ቤቶች    ➠ ስልጠናዎች
➠ ሆስፒታል    ➠ ክሊኒኮች
➠ websites  ➠ Events     
➠ ሆቴሎች      ➠ ፈርኒቸር ቤቶች
➠ ባዛር          ➠ ዝግጅቶች እና ሌሎችንም

የድርጅታችሁን ወይም የሱቃችሁን ህጋዊነት በማረጋገጥ  ምርትና አገልግሎቶን እንዲያስተዋውቁ እድሉን አመቻችተናል። በቻናላችን በማስተዋወቅ ለብዙዎች ይድረሱ... ትርፋማ እና ተመራጭ ይሁኑ።

ከታች ባሉት ሊንኮች ያነጋግሩን።

👉@Addis_reporter_bot
❤3👍3