: ከህሊናህና ከመንፈሳዊ አማካሪህ ሳትመክር ምንም ነገር አትወስን ፤ አጥርተህ ሳትሰማ ቃል አትግባ ። መከራ ካልደረሰ
በቀር ባል በሌለበት ቤት ውስጥ ከሚስቲቱ ጋር ብቻህን አትቀመጥ ።
:የሚበልጥህ ልኩራብህ እንዳይልህ ፣ ያነሰህ ልድረስብህ ብሎ እንዳያጠፋህ የሀብትህን ልክ እንዳታወራ ፤ በገዛ አፍህ ባንዱ
ትከብራለህ ባንዱ ትቀላለህና ።
:በጣም በማክበርህ እንዳታመልከው ፤ በጣም በመናቅህ እንዳታዋርደው ሠው እንዳንተ መሆኑን እወቀው ።
:የእኔ መናገር ምን ይለውጣል? ብለህም ስህተትን አትለፍ ፤የእኔ አስተዋፅኦ ምን ይጠቅማል ? ብለህም ስጦታህን አትጠፍ ።
:መልካም ቃል ከስጦታ ይበልጣልና መልካም ቃል ተናገር ፤ ማንኛውም ስጦታ ከልመና ወንበር አያስነሣም ።
የተስፋ ቃል ግን እንደሚያስነሣ አውቀህ ለሰዎች የተስፋ ቃል ስጣቸው ።
:ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን አይጨርስም ።
ዕውቀትህን የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን ያሳይሃል ።
አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት ፣ ሰውነትህን ለመግዛት ትዕግስት ፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት ያስፈልግሃል ። ለህሊናህ እረፍት ግን እምነት ያሻሃል ።
ተከታይ ለማበጀት ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ ይልሃል።
:አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል ።
ዘመን እኔና አንተ ነን ፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን የለም ።
:መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል ።
ትክክለኛም ውሳኔ ከመልካም ምክር ነውና..!!
@Addis_Reporter

❤31👌7👍5💯1🏆1
መሳሪያው የመጣው ከግብፅ ነው-ጄኔራል ገብረ አድሃና‼️
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን የጦርነት መንገድ በመቃወም ወደ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
ሜ/ጄኔራል ገበረ አድሃና ከ ኤንቢሲ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ንግግር ህወሃት የታጠቃቸው መሳሪያዎች መነሻቸው ግብጽ መሆኑን ተናግረዋል።
መሳሪያዎቹ የሚገቡት ከግብፅ በቀጥታ የገቡ አሉ፣እንደገና ከግብፅ በኤርትራ እና በሱዳን በኩልም የገቡ አሉ ብለዋል።
ህወሓት እነዚህን መሳሪያዎች ተርክቦ ድሮን ጭምር ለሌሎች ታጣቂዎች ሲያከፋፍል እንደነበር አውቃለሁ ብለዋል።

🤪14❤9👍5😢1🤣1
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ300 ሺህ በላይ ቪዛዎችን ሰረዘ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከጥር 2025 ጀምሮ ባሉት ጊዜያት ከ300,000 በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ቪዛዎችን መሰረዙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህ ጥብቅ እርምጃ በዋናነት ብሔራዊ ደህንነትን ለማስጠበቅ የታለመ ቢሆንም፣ የትችት ሰለባ ሆኗል።
በተለይም ወግ አጥባቂው ተንታኝ ቻርሊ ኪርክ መገደልን ተከትሎ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ሐሳብ የሰጡ እና በጋዛ ጦርነት ዙሪያ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የተሳተፉ የውጭ ዜጎች ቪዛዎች መሠረዛቸው ከፍተኛ መነጋገሪያ ፈጥሯል።
የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ይህ እርምጃ የሐሳብ ነፃነትን የሚጻረር እና ስደተኞችንና አነስተኛ ማህበረሰቦችንዒላማ ያደረገ አደገኛ አካሄድ ነው ሲሉ በጥብቅ እየተቹ ይገኛሉ።
አስተዳደሩ በበኩሉ ሀገሪቱን የሚቃወሙ ወይም ሕግ የሚተላለፉ አካላት ላይ የሚደረገው ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

❤9👍3🤔3
ልዩ መረጃ‼️
በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ኤርትራ መጠየቋ ተሰማ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ኬንያ ከመጓዛቸው ቀደም ብሎ October 18/2026
የኤርትራ ባለስልጣናት ወደ ናይሮቢ ተጉዘው እንደነበር ተረጋግጧል።
የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የማነ ገብረአብ ከቀናት በፊት ወደ ናይሮቢ ተጉዘው እንደነበር የዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አሕመድ የማሹጃ ቀንን ለማክበር በእንግድነት ተጋብዘው በትናንትናው እለት ወደ ኬንያ ማምራታቸው ይታወቃል።
እንደ ምንጮቹ ገለጻ ሁለቱ የኤርትራ ቁልፍ ባለስልጣናት ወደ ኬንያ የተጓዙት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውይይት እንዲጀመር ኬንያን ሎቢ ለማድረግ ነው ተብሏል። ሻብያ በሁለቱ አገራት ውጥረት ኬንያ እንድታደራድር ፍላጎት እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፤ በድንበሩ ላይ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ፍላጎቱን መግለጹ ታውቋል።
ኤርትራ ከሁለቱ አገራት መካከል ባሉ የድንበር አካባቢዎች የሰላም አስከባሪ ኃይሎች እንዲሰማሩ ሀሳብ አቅርባለች። ይህም ከአልጀርስ ስምምነት በኋላ ውጥረትን ለማርገብና ጦርነትን ለመከላከል እንደተደረገው ዓይነት እርምጃ ነው። ሆኖም፣ ኢትዮጵያ ይህንን ሀሳብ መቀበል ወይንም አለመቀበሏን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።

❤17🤣15👍4🤔1
ቴምር ሪልእስቴት 📌 አዲስ ሳይት🎯 መገናኛ ቤል ቪው ሆቴል አጠገብ በ35% ቅናሽ ይዘን መጥተናል።
የሳይቱ ልዩ መገለጫ
✅ Top veiw
✅ ፔንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 የካሬ አማራጭ
✅40% ከፍላችሁ 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት
✅ ያለምንም ወለድ የሚከፈል
✅ የጫካ ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል
✅20% ቅድመ ክፍያ
✅35% ቅናሽ
#ያስታውሱ፦
📌ቀድመው ለሚመጡ ውስን ደንበኞች 40% ቅድመ ክፍያ ከፍላችሁ ቀሪውን 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበትን አከፋፈል አቅርበናል
📌100%ሲከፍሉ የ35% ቅናሽ ያገኛሉ።
ለበለጠ መረጃ በ📞09-42-16-42-62

❤4👍2
#ጎረቤት ሀገር ኬንያ ከ245 ዶላር በታች ገቢ ለሚያገኙ ዜጎቿ የግብር ቅናሽ ማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ህግ አዘጋጀች‼️
ብሔራዎ የጀግኖች ቀንን ያከበረችው ጎረቤት ሀገር ኬንያ ለተቀጣሪ ሰራተኞቿ የግብር ቅናሽ ማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ህግ አዘጋጅለች፡፡ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንዳሉት አዲሱ ረቂቅ አነስተኛ ገቢ የሚያገኙ ኬንያዊንን ለመደገፍ ምንግስታቸው የግብር ቅናሽ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
ረቂቅ ህጉ የምግብ፣ ትራንስፖርት እና ምግብ ወጪ መናር የተቸገሩ ዝቅተኛ ገቢ በማግኘት ላይ ያሉ ተቀጣሪ ሰራተኞችን ለመደገፍ ያለመ መሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡
በተጨማሪም የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስት ኬንያዊያን ቋሚ ንብረት እንዲያፈሩ ለማበረታታት የንብረት ግብር ቅናሽ ለማድረግ እቅድ መያዙ ሲገለጽ በተለይም በንብረት ስም ዝውውር ወቅት እስከ አንድ ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወይም 7 ሺህ 700 ዶላር እና ከዛ በታች ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ዝውውር ለሚፈጽሙ ዜጎች ከግብር ነጻ እንዲሆኑም የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡ ይህ ረቂቅ ህግ ኬንያዊያን የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የኬንያን ድጅታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን ለማፋጠን ከውጭ ወደ ኬንያ በሚገቡ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ ቅናሽ ለማድረግ መታቀዱንም ፕሬዝዳንት ሩቶ ተናግረዋል፡፡

❤41👍11😢1🤝1
በደቡብ ጎንደር ዞን በድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ትናንት ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ የድሮን ጥቃት መሰንዘሩን ነዋሪዎች ገለጸዋል።
የዓይን እማኞች ጥቃቱ በሰና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ መፈጸሙን ሲናገሩ፤ ሌሎች በበኩላቸው ጥቃቱ በትምህርት ቤቱ አቅራቢያ ማነጣጠሩን ጠቁመዋል።
በድሮኑ ጥቃት ሳቢያ ስለደረሰው የሰውም ሆነ የንብረት ጉዳት እስካሁን በውል የታወቀ ነገር የለም።

❤13👍10😢10
ጎረቤት ሀገር ኬንያ ከ245 ዶላር በታች ገቢ ለሚያገኙ ዜጎቿ የግብር ቅናሽ ማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ህግ አዘጋጀች‼️
ብሔራዎ የጀግኖች ቀንን ያከበረችው ጎረቤት ሀገር ኬንያ ለተቀጣሪ ሰራተኞቿ የግብር ቅናሽ ማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ህግ አዘጋጅለች፡፡
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንዳሉት አዲሱ ረቂቅ አነስተኛ ገቢ የሚያገኙ ኬንያዊንን ለመደገፍ ምንግስታቸው የግብር ቅናሽ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
ረቂቅ ህጉ የምግብ፣ ትራንስፖርት እና ምግብ ወጪ መናር የተቸገሩ ዝቅተኛ ገቢ በማግኘት ላይ ያሉ ተቀጣሪ ሰራተኞችን ለመደገፍ ያለመ መሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡
በተጨማሪም የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስት ኬንያዊያን ቋሚ ንብረት እንዲያፈሩ ለማበረታታት የንብረት ግብር ቅናሽ ለማድረግ እቅድ መያዙ ሲገለጽ በተለይም በንብረት ስም ዝውውር ወቅት እስከ አንድ ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወይም 7 ሺህ 700 ዶላር እና ከዛ በታች ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ዝውውር ለሚፈጽሙ ዜጎች ከግብር ነጻ እንዲሆኑም የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡
ይህ ረቂቅ ህግ ኬንያዊያን የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የኬንያን ድጅታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን ለማፋጠን ከውጭ ወደ ኬንያ በሚገቡ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ ቅናሽ ለማድረግ መታቀዱንም ፕሬዝዳንት ሩቶ ተናግረዋል፡፡
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
ብሔራዎ የጀግኖች ቀንን ያከበረችው ጎረቤት ሀገር ኬንያ ለተቀጣሪ ሰራተኞቿ የግብር ቅናሽ ማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ህግ አዘጋጅለች፡፡
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንዳሉት አዲሱ ረቂቅ አነስተኛ ገቢ የሚያገኙ ኬንያዊንን ለመደገፍ ምንግስታቸው የግብር ቅናሽ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
ረቂቅ ህጉ የምግብ፣ ትራንስፖርት እና ምግብ ወጪ መናር የተቸገሩ ዝቅተኛ ገቢ በማግኘት ላይ ያሉ ተቀጣሪ ሰራተኞችን ለመደገፍ ያለመ መሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡
በተጨማሪም የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስት ኬንያዊያን ቋሚ ንብረት እንዲያፈሩ ለማበረታታት የንብረት ግብር ቅናሽ ለማድረግ እቅድ መያዙ ሲገለጽ በተለይም በንብረት ስም ዝውውር ወቅት እስከ አንድ ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወይም 7 ሺህ 700 ዶላር እና ከዛ በታች ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ዝውውር ለሚፈጽሙ ዜጎች ከግብር ነጻ እንዲሆኑም የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡
ይህ ረቂቅ ህግ ኬንያዊያን የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የኬንያን ድጅታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን ለማፋጠን ከውጭ ወደ ኬንያ በሚገቡ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ ቅናሽ ለማድረግ መታቀዱንም ፕሬዝዳንት ሩቶ ተናግረዋል፡፡
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤33👍5
የተከራዮች ቅሬታ‼️
የአዲስ አበባ ተከራዮች በመንግስት ቁጥጥር መላላት ላይ ቅሬታ አቀረቡ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ተከራዮች ከቤት ኪራይ ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ እየደረሰባቸው ባለው ከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና የተነሳ ምሬታቸውንና ቅሬታቸውን በከፍተኛ ድምጽ እየገለጹ ይገኛሉ።
መንግስት የኪራይ ገበያውን ለማረጋጋት እና የዋጋ ጭማሪውን ለመገደብ ያስቻለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ አውጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ ቢሞክርም በመሬት ላይ ያለው ተጨባጭ እውነታ ግን ከተቀመጠው ህግ ሙሉ በሙሉ ያፈነገጠ እንደሆነ ተከራዮች ያስረዳሉ።
እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ ከሆነ፣ አብዛኛዎቹ አከራዮች የተደነገገውን የ11.5% ዓመታዊ የጭማሪ ጣሪያ ወደ ጎን በመተው ኪራይን በከፍተኛ መጠን እየጨመሩ ሲሆን ይህንን አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆኑትን ተከራዮች ደግሞ «ቤቱን ልሸጠው ነው» ወይም «የራሴ ዘመድ ሊኖርበት ነው» በሚሉ የተለያዩ ምክንያቶች ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ እንዲለቁ እያስገደዷቸው እንደሚገኙ ቅሬታ አቅራቢዎች ምሬታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።ይህ በእንዲህ እንዳለ የከተማዋ ተከራዮች በመንግስት መዋቅር ላይ ያላቸውን ጠንካራ ቅሬታ እያነሱ ሲሆን በተለይም በየወረዳውና በየክፍለ ከተማው ህጉን የሚጥሱ አካላትን በአግባቡ የሚከታተል፣ የሚቆጣጠር እና የተከራዩን መብት የሚያስከብር ጠንካራ አስፈጻሚ አካል ባለመኖሩ ህጉ ጥርስ እንደሌለው አንበሳ ሆኗል ሲሉ ይተቻሉ።ከዚህ በተጨማሪ የደላላዎች መበራከትና የኮሚሽን ጥቅምን ለማሳደግ የሚደረገው ያልተገባ የዋጋ ማጋነን ገበያውን ይበልጥ እንዳናጋውና ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ለጎዳና እና ለከፍተኛ እንግልት እየዳረገው እንደሚገኝ በምሬት ይገልጻሉ።
በአንጻሩ አከራዮች በሀገሪቱ ካለው አጠቃላይ የኑሮ ውድነት እና የቤት ጥገና እቃዎች ዋጋ መጨመር አንጻር የኪራይ ገደቡ የንብረት ባለቤትነት መብታቸውን የሚጋፋ እንደሆነ ቢከራከሩም፣ ነዋሪዎች ግን መንግስት በአስቸኳይ በመሬት ላይ ያለውን ቁጥጥር በማጠናከር ከቤት አልባነትና ከማህበራዊ ቀውስ እንዲታደጋቸው በፅኑ በመጠየቅ ላይ ናቸው።

👍20❤14😢3
አርሰናል ከባየር ሙኒክ ሜዳ ላይ ነጥብ ይዞ ወጣ
የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ መርሃ ግብር ተጠባቂ ጨዋታ በጀርመን አሊያንዝ አሬና ተካሄዷል።
አርሰናል ከአስተናጋጁ ባየር ሙኒክ ጋር አቻ በመለያየት ጠቃሚ ነጥብ ይዞ መመለስ ችሏል።
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ አርሰናሎች በኤቤሬቺ ኢዜ ጎል ቀዳሚ መሆን ችለው ነበር።
ይሁን እንጂ ዴቪስ ባስቆጠራት ግብ ባየር ሙኒክ አቻ መሆን ችሏል።
በሁለተኛው አጋማሽ አስተናጋጆቹ በሃሪ ኬን የፍጹም ቅጣት ምት መሪነቱን ቢረከቡም፣ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ደቂቃዎች ሲቀረው ዲክላን ራይስ ያስቆጠራት ድንቅ ግብ የአርሰናልን አቻ ውጤት አረጋግጣለች።
በዚህም መሰረት ጨዋታው ባለበት 2 አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ሁለቱም ክለቦች ነጥብ ተጋርተዋል።

❤21👍10🤣2
ቦይንግ 737 MAX 10 አውሮፕላን የመጨረሻ የምስክር ወረቀት አገኘ
የአሜሪካ ፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር ለቦይንግ 737 MAX 10 አውሮፕላን የመጨረሻ የምስክር ወረቀት በመስጠት አውሮፕላኑን ለአየር መንገዶች ማስረከብ እንዲጀመር ፈቃድ ሰጥቷል።
ለዓመታት የዘለቀውን ማረጋገጫ የማግኘትን ሂደት ያጠናቀቀው ቦይንግ የ737 MAX ተከታታይ አውሮፕላኖች ትልቁን ሞዴል ለደንበኞቹ ለማስረከብ የነበረውን ዋነኛ እንቅፋት ማስወገዱን አስታውቋል።
አውሮፕላኑ ከአውሮፓው ኤርባስ ጋር የሚያደረገውን የገበያ ውድድር ለማጠናከር ወሳኝ ነው ተብሏል።
ቦይንግ የአውሮፕላኑን ርክክብ በ2020 ለመጀመር አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የቴክኒክ ችግሮችና የቁጥጥር ሂደቶች ምክንያት ለዓመታት ተራዝሟል።
እያንዳንዱ አውሮፕላንም ተጨማሪ የበረራ ብቃት ፈቃድ ከተሰጠው በኋላ ብቻ ነው መንገደኞችን ማጓጓዝ የሚችለው።
Via:- ሮይተርስ

❤6👍3
የሚዋጥ የወሊድ መከላከያ መድሀኒትን መጠቀም ለጡት ካንሰር ያጋልጣል ተባለ
የጡት ካንሰር በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ደረጃ በአንደኝነት በተለይም የሴቶችን ህይወት እየቀጠፈ ያለ በሽታ ነው ፡፡
የጡት ካንሰር በአብዛኛው ሴቶችን የሚያጠቃ እንደሆነና በዋናነት የሚተላለፈው በቤተሰብ ከእናት ወደ ልጅ ቢሆንም ሌላው ተጋላጭነትን የሚጨምሩ መንገዶች ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮልን አዘውትሮ መጠቀም አለመውለድ እና አለማጥባት እንደሆኑ ለብስራት ሬዲዮ የተነናገሩት በወራቤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቤተሰብ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ሔርሜላ አየለ ናቸው፡፡
በተጨማሪም ለወሊድ መከላከያ ተብሎ የሚወሰደውን የሚዋጥ መድሀኒት መጠቀም እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ ከ40 ዓመት በላይ መሆን ለበሽታው ተጋላጭ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡በሽታው በዋናነት ጎልቶ የሚታየው ከአርባ ዓመት በላይ ቢሆንም አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ስርጭቱ እየጨመረ በመምጣቱ ከ30 ዓመት ጀምሮ ላሉ ሴቶች የቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
አብዛኛውን ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋለው ትልቁ ችግር ከረፈደ በኋላ ማለትም በሽታው ወደ ሌላ ሰውነት ክፍሎች ከተሰራጨ በኋላ እና ሰውነታቸውም ተጎድቶ አቅም ከሳጣቸው በኋላ ወደ ህክምና ተቋማት መድረስ እንደሆነ የህክምና ባለሙያው ገልፀዋል፡፡
በሽታው ግን በጊዜ ከተደረሰበት እና ወደ ሳንባ፣ ወደ ጉበት፣ ወደ አጥንት እና ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሳይሰራጭ እባጩን ባለበት ከተገኘ ቀዶጥገና ተሰርቶ እና የጨረር ህክምና ወስዶ የመዳን እድሉ 90 በመቶ እእደሆነ ተናግረዋል።
ለካንሰር ህክምና የሞኖግራፊ ምርመራ ተመራጭ አንደሆነ እና በተለያዩ ሀገራት ይህንን መሳሪያ ይጠቀማሉ፡፡ ነገር ግን በመካከለኛ እና በዝቅተኛ በሆኑ ሀገራት የአለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው መስፈርት አካላዊ የጡት ምርመራ በማድረግ ምርመራው እንደሚሰጥ አብራርተዋል።
በምርመራውም በጡት ውስጥ ከ2 ሴንቲሜትር ጀምሮ ያለ እባጭ ማግኘት ዶ/ር ሔርሜላ አየለ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

❤11👍4🤪2
ቴምር ሪልእስቴት አዲስ ሳይት መገናኛ ቤል ቪው ሆቴል አጠገብ በ35% ቅናሽ ይዘን መጥተናል።
🏘 ባለ 2 መኝታ ከ90 እስከ 105 ካሬ
🏘 ባለ 3 መኝታ ከ112 እስከ 145 ካሬ
🏘 ፒንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 ካሬ
የሳይቱ ልዩ መገለጫ
✅ Top veiw መሆኑ
✅ ፔንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 የካሬ አማራጭ
✅40% ከፍላችሁ 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት
✅ ያለምንም ወለድ የሚከፈል
✅ የጫካ ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል
✅20% ቅድመ ክፍያ
✅35% ቅናሽ
🌴ቴምር ሪል እስቴት የማይደገም ዕድል በአዲስ ሳይት በመሀል መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ ይዞላቹ መቷል።
ለበለጠ መረጃ
📞0942-16-42-62 ይደውሉ

❤6👍2
ሞያሌ‼️
በሞያሌ ከተማ እንደገና በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች ወደ ኬንያ በመሰደድ ላይ ናቸው።
በኦሮሚያ እና በሱማሌ ክልሎች አወሳሰን ምክንያት በሞያሌ ከተማ ትላንት ረጋ ብሎ የነበረው ግጭት ዛሬ ማለዳ እንደገና መቀስቀሱ ተገለጸ።
ከስፍራው ያገኘናቸው የመረጃ ምንጮች እንደጠቆሙት፣ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ የሚሰማ ሲሆን፣ የከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ቆሟል።
በከተማዋ ባለው የአስፓልት መንገድ ግራና ቀኝ በሱማሌ እና በኦሮሞ ተከፍሎ በሚገኘው የሞያሌ ከተማ፣ የይገባኛልና የባለቤትነት ጥያቄን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ይህ ግጭት ከቀበሌ ሁለት ተነስቶ አሁን ላይ በሙሉ ከተማዋ ውስጥ ተስፋፍቶ ይገኛል።
የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ከተማዋ የገቡ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ተኩሱን ማስቆም እንዳልተቻለ ታውቋል።
ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ እንዲሁም ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡት ዋና ዋና መንገዶች ሙሉ በሙሉ ዝግ ሆነዋል።
የግጭቱን መበርታት ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ ኬንያ ሞያሌ በመሻገር ላይ ይገኛሉ።

❤22😢6👍4😎1😡1
የ #ኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ምዘና ደረጃ አሁንም አሽቆለቆለ‼️
የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት (WJP) ይፋ ባደረገው የ2026 የሕግ የበላይነት መረጃ ጠቋሚ መሰረት፣ የኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት አፈጻጸም አሁንም ማሽቆልቆሉ ተመልክቷል። በዚህም መሠረት አገሪቱ ከ143 አገሮች መካከል 133ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። አዲሱ ግምገማ ሀገሪቱ ደረጃዋ ለበርካታ ዓመታት መሽቆልቆሉን መቀጠሉን ይፋ በማድረግ ከዓለም አቀፍ እና ከሰሃራ በታች ካሉ አፍሪካ አገሮች ደረጃ ግርጌ መቀመጧን አመላክቷል።
ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ይፋ የሆነው የ2026 መረጃ ጠቋሚ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአምባገነንነት አዝማሚያ እየሰፋ መምጣቱን፣ በአስፈጻሚ አካል ላይ የሚደረጉ የቁጥጥር ገደቦች መዳከማቸውን፣ የዳኝነት ነፃነት መቀነሱን እና በመሠረታዊ ነፃነቶች ላይ የሚደረጉ ገደቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕግ የበላይነት እንዲሸረሸር አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት (WJP) ሲያስጠነቅቅ መቆየቱን ተከትሎ የወጣ ነው።

👍16❤8😢3
ከ600 ሺሕ ብር በላይ የዳኝነት ክፍያ ይጠየቅበት የነበረው የመሬት ይዞታ ማስለቀቅ አገልግሎት ነፃ ተደረገ ‼️
እንደ ጉዳዩ ይዘት 600 ሺሕ ብርና ከዚያ በላይ የዳኝነት ክፍያ ይጠየቅበት የነበረው የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ነፃ መደረጉን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ አስታወቀ፡፡
አገልግሎቱ ነፃ የተደረገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ እንደገና ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 13/2018 ተግባራዊ መደረግ በመጀመሩ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ፕሬዚዳንት አቶ ኦልያድ ሥዩም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትንና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን ወጥቶ የነበረውን አዋጅ ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1161/2011 መሠረት በማድረግ፣ እንደገና የወጣው ደንብ ቁጥር 13/2018፣ እንዲሁም ላለፉት 24 ዓመታት ሥራ ላይ የነበረውንና ክፍተቶች የነበሩበትን ደንብ ቁጥር 30/1994 የሚተካ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀድሞው ደንብ መሠረት የመሬት ይዞታና ካሳ ጉዳዮችን የተመለከተ ቅሬታ ያለው አንድ ባለ ጉዳይ ለይግባኝ ሰሚ ጉባዔው ሲያቀርብ የዳኝነት ክፍያ እንዲከፍል ይደረግ እንደነበር፣ በአሁኑ ወቅት ግን ለልማት ብሎ ይዞታውን የሚለቅ ሰው፣ ይዞታውን ከመልቀቅ አልፎ ለዳኝነትም ክፍያ የሚጠየቅ ከሆነ የመክፈል አቅም እንደማይኖረው ከግምት በማስገባት ቅሬታውን በነፃ እንዲያቀርብ መደረጉን ተናግረዋል።

❤16👍8🤪3
ሞያሌ ትኩረት ይፈልጋል‼️
በከባድ መሣሪያ ተኩስ ልውውጥ ሳይቀር የታጀበው #በሞያሌ የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ ሶስት ተጨማሪ ወረዳዎች ተስፋፋ
#በኦሮሚያ ክልል #ቦረና ዞን በምትገኘው የድንበር ከተማ ሞያሌ፣ የሶማሌ ክልል ሰንደቅ ዓላማ በመሰቀሉ ሳቢያ በተፈጠረ ውዝግብ እና ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም. የአንድ የ13 ዓመት ታዳጊ ልጃገረድ ህይወት ማለፉን ተከተሎ የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል የጸጥታ ኃይሎች መካከል የከባድ መሣሪያ ተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል።
ከረቡዕ ምሽት ጀምሮ ሲጋጋል የቆየው ውጥረት በሐሙስ ዕለት ወደ የለየለት ግጭት የተቀየረ ሲሆን፣ በደቡብ ኦሮሚያ በሚገኙ ጉሚ ኤልዳሎ፣ ዋጪሌ እና አሬሮ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ጭምር መስፋፋቱንነዋሪዎች እና የአካባቢው የጸጥታ ኃላፊዎች ገልጸዋል።
የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ግጭቱ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም ከማለዳው 11:30 ገደማ በነማለብ፣ ጫሙቅ፣ ቦሌ፣ ቀበሌ 01 እና ዋቆ ዶጎ በተባሉ በርካታ አካባቢዎች ተቀስቅሷል።
የሞያሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዋቆ ሁሴን እንደገለጹት፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ሰንደቅ ዓላማ ለመስቀል ያደረገው ሙከራ፣ የ13 ዓመቷ ዲቆ ጃታን አጋ መገደል እና ማክሰኞ ምሽት በአንድ የከተማዋ ኃላፊ ላይ “የግድያ ሙከራ ሊፈጸም ነው” በሚል የተሰራጨ ያልተረጋገጠ አሉባልታ ለግጭቱ መባባስ ምክንያት ከሆኑት መካከል ይጠቀሳሉ ብለዋል።

❤20👍4
ወረራ አልፈፀምኩም-ኤርትራ‼️
‹‹በኢትዮጵያ ላይ ወረራ እንደፈፀምን የሚገለፀው ክስ ሙሉ በሙሉ የተፈጠረ ውሸት ነው›› ሲል የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ‹‹በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ›› በሚል ዛሬ ዘለግ ያለ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በዚህ መግለጫው ‹‹የኤርትራ ሉአላዊ ግዛት ለስምምነት ወይንም ለድርድር አይቀርብም›› ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ‹‹ለስትራቴጂያዊ አላማ አስፈላጊ ነው›› በሚል የኤርትራን ሉአላዊ ድንበር ለመውረርና ለመጣስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ እየተባባሰ ለመጣው አለመረጋጋትና ቀውስ ‹‹በኢትዮጵያ ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ሆነ ተብሎ ለአመታት የፈፀመ የጂኦ ፖለቲካ ጥቃት ውጤት ነው›› በማለት ክስ ያቀረበው መግለጫው ይህም በወታደራዊ ዛቻ፣ ዲፕሎማሲያዊ ጠላትነት፣ በኢኮኖሚ ማስፈራሪያና በገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ጨምሮም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ‹‹ሁሉም ወገኖች›› ወይንም ‹‹ሁሉም አካላት›› መረጋጋትን እንዲያሳዩና ውጥረቱን እንዲያረግቡ በሚል የሚቀርበውን ጥሪ ‹‹ህጋዊነት የጎደለውና ለዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጎጂ ነው›› በማለት ገልፆታል፡፡ እንዲህ አይነት መግለጫዎች ሉአላዊነቱን የሚከላከልንንና ጥቃት ፈፃሚውን እኩል የሚያስቀምጡ መሆናቸውን ጠቅሶምነ ለተጨማሪ ሀላፊነት የጎደለው ድርጊት በር እንደሚከፍቱ አሳስቧል፡፡ በማስከተልም ‹‹ኤርትራ ወረራ ፈፅማለች የሚለው ክስ ሙሉ በሙሉ የተፈጠረ ውሸት ነው፡፡ ይህ መሰረት የለሽ ክስ ተጠያቂነትን ለማምለጥ፣ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማታለልና የተጀመሩ የግዛት ማስፋፋት ምኞቶችን ህጋዊ ለማድረግ የተደራጀ የመረጃ ጦርነት አካል ነው›› ብሏል፡፡

❤20🤣8👍4🕊1