ህወሃት ላይመለስ ሄዷል-ጄ/ል ታደሰ ወረደ‼️
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በወቅታዊ የትግራይና የሀገሪቱ የፖለቲካ እና የደህንነት ሁኔታዎች ላይ ከአውራ አምባ ታይምስ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
የእገታው ሂደት እና የተፈጠረው ውዝግብ
ጀነራል ታደሰ ወረደ በቃለ መጠይቁ ወቅት በቅርቡ ስለገጠማቸው እገታ ሂደት ዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል፦
የእገታው አጀማመር፦ ሌሊት በቁጥጥር ስር ለማዋል የተደረገው ሙከራ ተገቢ እንዳልነበር እና በፖሊስ ሽፋን የመጡ አካላት እንደነበሩ ገልጸዋል።
የተወሰደው እርምጃና ዝውውር፦ ከቤት ከተወሰዱ በኋላ በኤች ዜድ (HZ) ሆቴል እንዲቆዩ መደረጉን፣ በመቀጠልም በአክሱም፣ አድዋ እና ራማ አቅጣጫዎች እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ ተናግረዋል።
የውሳኔው አካላት፦ ውሳኔውን ያሳለፉትና ያስፈጸሙት ይፋዊ የነበረው መንግስታዊ መዋቅር ሳይሆን፣ በፖለቲካ እና በሚሊተሪ ስብስብ የተዋቀረ “የአቋቋምት ኮሚቴ” እና ራዲካል አካላት እንደሆኑ ጠቁመዋል።
ከመከላከያ ሰራዊት ጋር የተደረገ ግንኙነት፦ ከራማ ከተማ በመውጣት ከአድበራና ከአሮህ መካከል ከአገኘው የመከላከያ ሰራዊት አባላትና አመራሮች ጋር በሰላም መገናኘታቸውን አብራርተዋል።
በእሳቸው ላይ ለሚነሱ ወቀሳዎችና ዘመቻዎች የተሰጠ ምላሽ
በተለያዩ ማህበራዊና መደበኛ ሚዲያዎች በጀነራል ታደሰ ወረደ ላይ ለሚሰነዘሩ ቅሬታዎችና ጥርጣሬዎች የተሰጡ ምላሾች፦
የህወሓት ሃይል በማደራጀትና ደንብ በማውጣት ሂደት፦ በወቅቱ የተሰሩ ስራዎች በሙሉ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ እና ከካቢኔው አሰራር ጋር የተያያዙ እንደነበሩ ገልጸዋል።
የአቋም ልዩነቶችና ተቃውሞዎች፦ በየደረጃው በነበሩ ውሳኔዎች ላይ የነበራቸው ተቃውሞና ልዩነት በሰነድና በሪኮርድ የተያዘ መሆኑን አብራርተዋል።
የጦር መሳሪያዎች ምዝገባና አመጣጥ፦ በስልጣን ዘመናቸው የተከናወኑ የደህንነት ስራዎች ግልጽ እንደነበሩና ከእሳቸው እውቅና ውጪ በድብቅ የተሰሩ ነገሮች ካሉ ማጣራት እንደሚቻል ገልጸዋል።
ስለ ህወሓት የወደፊት እጣ ፈንታ እና የሽግግር ወቅት
ጀነራል ታደሰ ወረደ ስለ ድርጅቱ ህልውና እና ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፦
የህወሓት የፖለቲካ ማብቂያ፦ ህወሓት በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ማብቂያው ላይ እንደሚገኝና ድርጅቱን በሰላም ማሳረፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ለድርጅት ህልውና የሚከፈል መስዋዕትነት ማብቃት አለበት፦ “ህወሓት ከሌለ ትግራይ የለችም” የሚለው አስተሳሰብ የተሳሳተ መሆኑንና ድርጅቱ ሳይኖርም ትግራይ እንደምትቀጥል አስረድተዋል።
"ሰራዊቱም ከሞተ ጋር መሞት የለበትም የTPLF አመራሮች አንድ የተሳካላቸው ነገር ቢኖር፣ ድርጅቱን ወደ መቃብር አውርደውታል፣ላይመለስ ሄዷል" ብለዋል።
የወጣቱ እና የአዲሱ ትውልድ ድርሻ፦ አመራሩ ከወጣቱ ትውልድ ጋር መቆራረጡን ጠቅሰው፣ የትግራይ ህዝብና አዲሱ ትውልድ የራሱን እድልና ህልም መቅረፅ እንዳለበት አሳስበዋል።
የሰላም አስፈላጊነት፦ ህዝቡ ተጨማሪ ጦርነትና ውድመት መሸከም የማይችል በመሆኑ ትኩረቱ በፖለቲካዊና በሰላማዊ መፍትሔዎች ላይ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
@Addis_Reporter

❤28🤪13👍7
ሀሰተኛ መረጃ‼️
ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ የሚለው መረጃ ሀሰተኛ መረጃ ነው።
የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ ተሹመዋል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የቆየው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀና ሀሰተኛ መረጃ ነው።

🤣21👍15❤5
ቴምር ሪልእስቴት 📌 አዲስ ሳይት🎯 መገናኛ ቤል ቪው ሆቴል አጠገብ በ35% ቅናሽ ይዘን መጥተናል።
የሳይቱ ልዩ መገለጫ
✅ Top veiw
✅ ፔንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 የካሬ አማራጭ
✅40% ከፍላችሁ 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት
✅ ያለምንም ወለድ የሚከፈል
✅ የጫካ ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል
✅20% ቅድመ ክፍያ
✅35% ቅናሽ
#ያስታውሱ፦
📌ቀድመው ለሚመጡ ውስን ደንበኞች 40% ቅድመ ክፍያ ከፍላችሁ ቀሪውን 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበትን አከፋፈል አቅርበናል
📌100%ሲከፍሉ የ35% ቅናሽ ያገኛሉ።
ለበለጠ መረጃ በ📞09-42-16-42-62

❤4👍4
በታሸጉ ምግቦችና በአመጋገብ ሥርዓት ለውጥ ህፃናት ለስኳር ህመም ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸው ተገለፀ
የታሸጉ ምግቦችና ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ልምድ በህፃናትና በወጣቶች ላይ የጤና ችግሮችን እያባባሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ማህበር አስታውቋል።
የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ኤርሚያስ ገብረማርያም ከብሰራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ በታሸጉ ምግቦች እና በአመጋገብ ስርዓት መለዋወጥ ሳቢያ ህፃናት እና እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ ያሉ አዋቂዎች ለስኳር ህመም ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል።
ከፍተኛ የውሃ ጥም፣ በተደጋጋሚ መሽናት፣ የመራብ ስሜት መጨመር፣ ድካምና ያልታሰበ የሰውነት ክብደት መቀነስ የዓይነት 1 የስኳር ህመም ዋና ዋና ምልክቶች ስለሆኑ፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች እነዚህን ምልክቶች በልጆቻቸው ላይ ሲያስተውሉ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመውሰድ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ተነግሯል።
ስለሆነም ህፃናት ከታሸጉ ምግቦችና ስኳር ከበዛባቸው መጠጦች ይልቅ በአትክልት፣ በፍራፍሬ፣ በጥራጥሬና በሌሎች ገንቢ ምግቦች ላይ የተመሰረተ ሚዛናዊ አመጋገብ እንዲኖራቸው ማበረታታት እንደሚገባ ማህበሩ ጥሪ አቅርቧል።
በተጨማሪም የበሽታውን ምልክቶች ማወቅ፣ በጊዜ ምርመራ ማድረግና ተገቢውን ህክምና ማግኘት በህፃናትና በወጣቶች ጤና ላይ የሚደርሱ ከባድ ጉዳቶችን ለመቀነስ ወሳኝ መሆኑን የስኳር ህመማን ማህበር የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ኤርሚያስ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

❤17👍5😢2
በመቐለ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ በቅርቡ ይጀመራል
በመቐለ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አካላት ጋር ውይይት መካሄዱን የከተማዋ ከንቲባ ዶ/ር ሽሻይ አስታወቁ።
ከንቲባው እንዳሉት፣ ከኮሪደር ልማቱ ጋር በተያያዘ ትናንት ከሰዓት በኋላ የተካሄደው ውይይት የመጀመሪያ ዙር ሲሆን፣ የልማት ሥራው በቅርቡ ወደ ተግባር እንደሚገባ ገልጸዋል።
በመቐለ ከተማ የኮሪደር ልማቱ በፍጥነትና በጥራት እንዲከናወን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥብቅ መመሪያ መስጠታቸውም ተገልጿል።

🤣31❤26👍3😡2🤷♂1🤪1
ዲቪ ሊጀመር ነው‼
የ2027 የአሜሪካ ዲቪ አገልግሎት በፈረንጆቹ NOV 01/2026 እንደሚጀምር የታወቀ ሲሆን እስከ NOV 30/2026 ድረስ መሙላት ይቻላል።
የአሜሪካ መወሰኛ ፍርድ ቤት ዲቪ 2017 Nov 1/2026 ጀምሮ ዲቪ እንዲጀመር በመወሰን ለአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ማሳወቁ ታውቋል።
በውሳኔው መሰረት ስቴት ዲፓርትመንት October 29/2026 ሙሉ መረጃ ያወጣል።
ምን ምን ማሟላት ያስፈልጋል?
እንደተለመደው ዲቪ ለለመሙላት ሀይስኩልና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ የሚያስፈልግ ሲሆን ጉርድ ፎቶ እንዲሁም በዚህ አመት አዲስ የተጨመረው መስፈርት የታደሰ ፓስፖርት ግዴታ ናቸው።
ለመመዝገቢያ ክፍያ (registration fee) 1$ ያስፈልጋል።
ዲቪ 2026 ለደረሳቸው እድለኞች ኢምባሲዎች ቀጠሮ ማስያስዝ መጀመራቸውን ሰምተናል።

👍14🤪7❤3🥰1🎉1🙏1
ጠቃሚ ምክሮች❗
እስከመጨረሻው አንብቡት👇
📌በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል።
📌ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት
መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ።
📌የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም፣ ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።
📌ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ፣ምክርን አልሰማ ብትል ግን
በዋጋ እንደምትማር እወቀው፣ በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ።
📌 ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።
📌የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን
አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን
ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ።
የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ።
ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ።
ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ።
📌ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ
የመጣህበትን አትዘንጋ ።
📌የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ።
📌ካሳለፉት ሕይወት
ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ።
ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።
ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ።
ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ
የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።
📌ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ።
ላለው አትሩጥ ፣ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ።
📌ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ፣በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር።
📌ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።
ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው
አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣
ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው።
📌እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል። ጨካኝ
እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ
እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ
ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ
የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን
አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።
📌ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።
:በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።
📌የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።
📌ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!
:መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው።
📌ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል።
📌ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ።
📌እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው።
📌ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ።
📌ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም።
📌ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።
ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።
📌የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው።
📌ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም
ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።
:📌ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ
ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ
እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።:
ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን
አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።
📌እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።
📌ቂም አፍን የሚያመር ፣ ልብን የሚያነቅዝ ፣ ተግባርን የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ ሰው ቅያሜህን ግለጥለት ፤
ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ ።

❤26👌3👍2🥰1🙏1
: ከህሊናህና ከመንፈሳዊ አማካሪህ ሳትመክር ምንም ነገር አትወስን ፤ አጥርተህ ሳትሰማ ቃል አትግባ ። መከራ ካልደረሰ
በቀር ባል በሌለበት ቤት ውስጥ ከሚስቲቱ ጋር ብቻህን አትቀመጥ ።
:የሚበልጥህ ልኩራብህ እንዳይልህ ፣ ያነሰህ ልድረስብህ ብሎ እንዳያጠፋህ የሀብትህን ልክ እንዳታወራ ፤ በገዛ አፍህ ባንዱ
ትከብራለህ ባንዱ ትቀላለህና ።
:በጣም በማክበርህ እንዳታመልከው ፤ በጣም በመናቅህ እንዳታዋርደው ሠው እንዳንተ መሆኑን እወቀው ።
:የእኔ መናገር ምን ይለውጣል? ብለህም ስህተትን አትለፍ ፤የእኔ አስተዋፅኦ ምን ይጠቅማል ? ብለህም ስጦታህን አትጠፍ ።
:መልካም ቃል ከስጦታ ይበልጣልና መልካም ቃል ተናገር ፤ ማንኛውም ስጦታ ከልመና ወንበር አያስነሣም ።
የተስፋ ቃል ግን እንደሚያስነሣ አውቀህ ለሰዎች የተስፋ ቃል ስጣቸው ።
:ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን አይጨርስም ።
ዕውቀትህን የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን ያሳይሃል ።
አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት ፣ ሰውነትህን ለመግዛት ትዕግስት ፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት ያስፈልግሃል ። ለህሊናህ እረፍት ግን እምነት ያሻሃል ።
ተከታይ ለማበጀት ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ ይልሃል።
:አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል ።
ዘመን እኔና አንተ ነን ፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን የለም ።
:መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል ።
ትክክለኛም ውሳኔ ከመልካም ምክር ነውና..!!

❤31👌7👍5💯1🏆1
መሳሪያው የመጣው ከግብፅ ነው-ጄኔራል ገብረ አድሃና‼️
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን የጦርነት መንገድ በመቃወም ወደ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
ሜ/ጄኔራል ገበረ አድሃና ከ ኤንቢሲ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ንግግር ህወሃት የታጠቃቸው መሳሪያዎች መነሻቸው ግብጽ መሆኑን ተናግረዋል።
መሳሪያዎቹ የሚገቡት ከግብፅ በቀጥታ የገቡ አሉ፣እንደገና ከግብፅ በኤርትራ እና በሱዳን በኩልም የገቡ አሉ ብለዋል።
ህወሓት እነዚህን መሳሪያዎች ተርክቦ ድሮን ጭምር ለሌሎች ታጣቂዎች ሲያከፋፍል እንደነበር አውቃለሁ ብለዋል።

🤪14❤9👍5😢1🤣1
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ300 ሺህ በላይ ቪዛዎችን ሰረዘ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከጥር 2025 ጀምሮ ባሉት ጊዜያት ከ300,000 በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ቪዛዎችን መሰረዙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህ ጥብቅ እርምጃ በዋናነት ብሔራዊ ደህንነትን ለማስጠበቅ የታለመ ቢሆንም፣ የትችት ሰለባ ሆኗል።
በተለይም ወግ አጥባቂው ተንታኝ ቻርሊ ኪርክ መገደልን ተከትሎ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ሐሳብ የሰጡ እና በጋዛ ጦርነት ዙሪያ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የተሳተፉ የውጭ ዜጎች ቪዛዎች መሠረዛቸው ከፍተኛ መነጋገሪያ ፈጥሯል።
የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ይህ እርምጃ የሐሳብ ነፃነትን የሚጻረር እና ስደተኞችንና አነስተኛ ማህበረሰቦችንዒላማ ያደረገ አደገኛ አካሄድ ነው ሲሉ በጥብቅ እየተቹ ይገኛሉ።
አስተዳደሩ በበኩሉ ሀገሪቱን የሚቃወሙ ወይም ሕግ የሚተላለፉ አካላት ላይ የሚደረገው ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

❤9👍3🤔3
ልዩ መረጃ‼️
በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ኤርትራ መጠየቋ ተሰማ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ኬንያ ከመጓዛቸው ቀደም ብሎ October 18/2026
የኤርትራ ባለስልጣናት ወደ ናይሮቢ ተጉዘው እንደነበር ተረጋግጧል።
የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የማነ ገብረአብ ከቀናት በፊት ወደ ናይሮቢ ተጉዘው እንደነበር የዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አሕመድ የማሹጃ ቀንን ለማክበር በእንግድነት ተጋብዘው በትናንትናው እለት ወደ ኬንያ ማምራታቸው ይታወቃል።
እንደ ምንጮቹ ገለጻ ሁለቱ የኤርትራ ቁልፍ ባለስልጣናት ወደ ኬንያ የተጓዙት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውይይት እንዲጀመር ኬንያን ሎቢ ለማድረግ ነው ተብሏል። ሻብያ በሁለቱ አገራት ውጥረት ኬንያ እንድታደራድር ፍላጎት እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፤ በድንበሩ ላይ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ፍላጎቱን መግለጹ ታውቋል።
ኤርትራ ከሁለቱ አገራት መካከል ባሉ የድንበር አካባቢዎች የሰላም አስከባሪ ኃይሎች እንዲሰማሩ ሀሳብ አቅርባለች። ይህም ከአልጀርስ ስምምነት በኋላ ውጥረትን ለማርገብና ጦርነትን ለመከላከል እንደተደረገው ዓይነት እርምጃ ነው። ሆኖም፣ ኢትዮጵያ ይህንን ሀሳብ መቀበል ወይንም አለመቀበሏን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።

❤17🤣15👍4🤔1
ቴምር ሪልእስቴት 📌 አዲስ ሳይት🎯 መገናኛ ቤል ቪው ሆቴል አጠገብ በ35% ቅናሽ ይዘን መጥተናል።
የሳይቱ ልዩ መገለጫ
✅ Top veiw
✅ ፔንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 የካሬ አማራጭ
✅40% ከፍላችሁ 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት
✅ ያለምንም ወለድ የሚከፈል
✅ የጫካ ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል
✅20% ቅድመ ክፍያ
✅35% ቅናሽ
#ያስታውሱ፦
📌ቀድመው ለሚመጡ ውስን ደንበኞች 40% ቅድመ ክፍያ ከፍላችሁ ቀሪውን 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበትን አከፋፈል አቅርበናል
📌100%ሲከፍሉ የ35% ቅናሽ ያገኛሉ።
ለበለጠ መረጃ በ📞09-42-16-42-62
የሳይቱ ልዩ መገለጫ
✅ Top veiw
✅ ፔንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 የካሬ አማራጭ
✅40% ከፍላችሁ 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት
✅ ያለምንም ወለድ የሚከፈል
✅ የጫካ ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል
✅20% ቅድመ ክፍያ
✅35% ቅናሽ
#ያስታውሱ፦
📌ቀድመው ለሚመጡ ውስን ደንበኞች 40% ቅድመ ክፍያ ከፍላችሁ ቀሪውን 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበትን አከፋፈል አቅርበናል
📌100%ሲከፍሉ የ35% ቅናሽ ያገኛሉ።
ለበለጠ መረጃ በ📞09-42-16-42-62
❤4👍2
#ጎረቤት ሀገር ኬንያ ከ245 ዶላር በታች ገቢ ለሚያገኙ ዜጎቿ የግብር ቅናሽ ማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ህግ አዘጋጀች‼️
ብሔራዎ የጀግኖች ቀንን ያከበረችው ጎረቤት ሀገር ኬንያ ለተቀጣሪ ሰራተኞቿ የግብር ቅናሽ ማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ህግ አዘጋጅለች፡፡ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንዳሉት አዲሱ ረቂቅ አነስተኛ ገቢ የሚያገኙ ኬንያዊንን ለመደገፍ ምንግስታቸው የግብር ቅናሽ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
ረቂቅ ህጉ የምግብ፣ ትራንስፖርት እና ምግብ ወጪ መናር የተቸገሩ ዝቅተኛ ገቢ በማግኘት ላይ ያሉ ተቀጣሪ ሰራተኞችን ለመደገፍ ያለመ መሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡
በተጨማሪም የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስት ኬንያዊያን ቋሚ ንብረት እንዲያፈሩ ለማበረታታት የንብረት ግብር ቅናሽ ለማድረግ እቅድ መያዙ ሲገለጽ በተለይም በንብረት ስም ዝውውር ወቅት እስከ አንድ ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወይም 7 ሺህ 700 ዶላር እና ከዛ በታች ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ዝውውር ለሚፈጽሙ ዜጎች ከግብር ነጻ እንዲሆኑም የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡ ይህ ረቂቅ ህግ ኬንያዊያን የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የኬንያን ድጅታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን ለማፋጠን ከውጭ ወደ ኬንያ በሚገቡ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ ቅናሽ ለማድረግ መታቀዱንም ፕሬዝዳንት ሩቶ ተናግረዋል፡፡

❤41👍11😢1🤝1
በደቡብ ጎንደር ዞን በድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ትናንት ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ የድሮን ጥቃት መሰንዘሩን ነዋሪዎች ገለጸዋል።
የዓይን እማኞች ጥቃቱ በሰና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ መፈጸሙን ሲናገሩ፤ ሌሎች በበኩላቸው ጥቃቱ በትምህርት ቤቱ አቅራቢያ ማነጣጠሩን ጠቁመዋል።
በድሮኑ ጥቃት ሳቢያ ስለደረሰው የሰውም ሆነ የንብረት ጉዳት እስካሁን በውል የታወቀ ነገር የለም።

❤13👍10😢10
ጎረቤት ሀገር ኬንያ ከ245 ዶላር በታች ገቢ ለሚያገኙ ዜጎቿ የግብር ቅናሽ ማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ህግ አዘጋጀች‼️
ብሔራዎ የጀግኖች ቀንን ያከበረችው ጎረቤት ሀገር ኬንያ ለተቀጣሪ ሰራተኞቿ የግብር ቅናሽ ማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ህግ አዘጋጅለች፡፡
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንዳሉት አዲሱ ረቂቅ አነስተኛ ገቢ የሚያገኙ ኬንያዊንን ለመደገፍ ምንግስታቸው የግብር ቅናሽ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
ረቂቅ ህጉ የምግብ፣ ትራንስፖርት እና ምግብ ወጪ መናር የተቸገሩ ዝቅተኛ ገቢ በማግኘት ላይ ያሉ ተቀጣሪ ሰራተኞችን ለመደገፍ ያለመ መሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡
በተጨማሪም የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስት ኬንያዊያን ቋሚ ንብረት እንዲያፈሩ ለማበረታታት የንብረት ግብር ቅናሽ ለማድረግ እቅድ መያዙ ሲገለጽ በተለይም በንብረት ስም ዝውውር ወቅት እስከ አንድ ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወይም 7 ሺህ 700 ዶላር እና ከዛ በታች ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ዝውውር ለሚፈጽሙ ዜጎች ከግብር ነጻ እንዲሆኑም የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡
ይህ ረቂቅ ህግ ኬንያዊያን የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የኬንያን ድጅታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን ለማፋጠን ከውጭ ወደ ኬንያ በሚገቡ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ ቅናሽ ለማድረግ መታቀዱንም ፕሬዝዳንት ሩቶ ተናግረዋል፡፡
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
ብሔራዎ የጀግኖች ቀንን ያከበረችው ጎረቤት ሀገር ኬንያ ለተቀጣሪ ሰራተኞቿ የግብር ቅናሽ ማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ህግ አዘጋጅለች፡፡
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንዳሉት አዲሱ ረቂቅ አነስተኛ ገቢ የሚያገኙ ኬንያዊንን ለመደገፍ ምንግስታቸው የግብር ቅናሽ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
ረቂቅ ህጉ የምግብ፣ ትራንስፖርት እና ምግብ ወጪ መናር የተቸገሩ ዝቅተኛ ገቢ በማግኘት ላይ ያሉ ተቀጣሪ ሰራተኞችን ለመደገፍ ያለመ መሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡
በተጨማሪም የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስት ኬንያዊያን ቋሚ ንብረት እንዲያፈሩ ለማበረታታት የንብረት ግብር ቅናሽ ለማድረግ እቅድ መያዙ ሲገለጽ በተለይም በንብረት ስም ዝውውር ወቅት እስከ አንድ ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወይም 7 ሺህ 700 ዶላር እና ከዛ በታች ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ዝውውር ለሚፈጽሙ ዜጎች ከግብር ነጻ እንዲሆኑም የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡
ይህ ረቂቅ ህግ ኬንያዊያን የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የኬንያን ድጅታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን ለማፋጠን ከውጭ ወደ ኬንያ በሚገቡ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ ቅናሽ ለማድረግ መታቀዱንም ፕሬዝዳንት ሩቶ ተናግረዋል፡፡
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤33👍5
የተከራዮች ቅሬታ‼️
የአዲስ አበባ ተከራዮች በመንግስት ቁጥጥር መላላት ላይ ቅሬታ አቀረቡ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ተከራዮች ከቤት ኪራይ ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ እየደረሰባቸው ባለው ከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና የተነሳ ምሬታቸውንና ቅሬታቸውን በከፍተኛ ድምጽ እየገለጹ ይገኛሉ።
መንግስት የኪራይ ገበያውን ለማረጋጋት እና የዋጋ ጭማሪውን ለመገደብ ያስቻለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ አውጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ ቢሞክርም በመሬት ላይ ያለው ተጨባጭ እውነታ ግን ከተቀመጠው ህግ ሙሉ በሙሉ ያፈነገጠ እንደሆነ ተከራዮች ያስረዳሉ።
እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ ከሆነ፣ አብዛኛዎቹ አከራዮች የተደነገገውን የ11.5% ዓመታዊ የጭማሪ ጣሪያ ወደ ጎን በመተው ኪራይን በከፍተኛ መጠን እየጨመሩ ሲሆን ይህንን አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆኑትን ተከራዮች ደግሞ «ቤቱን ልሸጠው ነው» ወይም «የራሴ ዘመድ ሊኖርበት ነው» በሚሉ የተለያዩ ምክንያቶች ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ እንዲለቁ እያስገደዷቸው እንደሚገኙ ቅሬታ አቅራቢዎች ምሬታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።ይህ በእንዲህ እንዳለ የከተማዋ ተከራዮች በመንግስት መዋቅር ላይ ያላቸውን ጠንካራ ቅሬታ እያነሱ ሲሆን በተለይም በየወረዳውና በየክፍለ ከተማው ህጉን የሚጥሱ አካላትን በአግባቡ የሚከታተል፣ የሚቆጣጠር እና የተከራዩን መብት የሚያስከብር ጠንካራ አስፈጻሚ አካል ባለመኖሩ ህጉ ጥርስ እንደሌለው አንበሳ ሆኗል ሲሉ ይተቻሉ።ከዚህ በተጨማሪ የደላላዎች መበራከትና የኮሚሽን ጥቅምን ለማሳደግ የሚደረገው ያልተገባ የዋጋ ማጋነን ገበያውን ይበልጥ እንዳናጋውና ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ለጎዳና እና ለከፍተኛ እንግልት እየዳረገው እንደሚገኝ በምሬት ይገልጻሉ።
በአንጻሩ አከራዮች በሀገሪቱ ካለው አጠቃላይ የኑሮ ውድነት እና የቤት ጥገና እቃዎች ዋጋ መጨመር አንጻር የኪራይ ገደቡ የንብረት ባለቤትነት መብታቸውን የሚጋፋ እንደሆነ ቢከራከሩም፣ ነዋሪዎች ግን መንግስት በአስቸኳይ በመሬት ላይ ያለውን ቁጥጥር በማጠናከር ከቤት አልባነትና ከማህበራዊ ቀውስ እንዲታደጋቸው በፅኑ በመጠየቅ ላይ ናቸው።

👍20❤14😢3
አርሰናል ከባየር ሙኒክ ሜዳ ላይ ነጥብ ይዞ ወጣ
የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ መርሃ ግብር ተጠባቂ ጨዋታ በጀርመን አሊያንዝ አሬና ተካሄዷል።
አርሰናል ከአስተናጋጁ ባየር ሙኒክ ጋር አቻ በመለያየት ጠቃሚ ነጥብ ይዞ መመለስ ችሏል።
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ አርሰናሎች በኤቤሬቺ ኢዜ ጎል ቀዳሚ መሆን ችለው ነበር።
ይሁን እንጂ ዴቪስ ባስቆጠራት ግብ ባየር ሙኒክ አቻ መሆን ችሏል።
በሁለተኛው አጋማሽ አስተናጋጆቹ በሃሪ ኬን የፍጹም ቅጣት ምት መሪነቱን ቢረከቡም፣ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ደቂቃዎች ሲቀረው ዲክላን ራይስ ያስቆጠራት ድንቅ ግብ የአርሰናልን አቻ ውጤት አረጋግጣለች።
በዚህም መሰረት ጨዋታው ባለበት 2 አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ሁለቱም ክለቦች ነጥብ ተጋርተዋል።

❤21👍10🤣2
ቦይንግ 737 MAX 10 አውሮፕላን የመጨረሻ የምስክር ወረቀት አገኘ
የአሜሪካ ፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር ለቦይንግ 737 MAX 10 አውሮፕላን የመጨረሻ የምስክር ወረቀት በመስጠት አውሮፕላኑን ለአየር መንገዶች ማስረከብ እንዲጀመር ፈቃድ ሰጥቷል።
ለዓመታት የዘለቀውን ማረጋገጫ የማግኘትን ሂደት ያጠናቀቀው ቦይንግ የ737 MAX ተከታታይ አውሮፕላኖች ትልቁን ሞዴል ለደንበኞቹ ለማስረከብ የነበረውን ዋነኛ እንቅፋት ማስወገዱን አስታውቋል።
አውሮፕላኑ ከአውሮፓው ኤርባስ ጋር የሚያደረገውን የገበያ ውድድር ለማጠናከር ወሳኝ ነው ተብሏል።
ቦይንግ የአውሮፕላኑን ርክክብ በ2020 ለመጀመር አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የቴክኒክ ችግሮችና የቁጥጥር ሂደቶች ምክንያት ለዓመታት ተራዝሟል።
እያንዳንዱ አውሮፕላንም ተጨማሪ የበረራ ብቃት ፈቃድ ከተሰጠው በኋላ ብቻ ነው መንገደኞችን ማጓጓዝ የሚችለው።
Via:- ሮይተርስ

❤6👍3