አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.8K subscribers
17.7K photos
437 videos
23 files
3.05K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ጄኔራል ታደሰ ወረደ የጦርነቱ ተሳታፊ❓‼️
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የትግራይ ኃይሎች ዋና አዛዥ የነበሩት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ አሁን ከመንግስት ጋር ጦርነት የገጠመውን የትግራይ ተዋጊ ኀይል በማደራጀት የመሪነት ሚና እንደነበራቸው ሰነዶች አረጋገጡ።
በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም. በሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ተፈርሞ የወጣው ባለ 18 ገፅ «የትግራይ ፀጥታ ኃይል አባላት መብትና ተጠቃሚነት ደንብ» ሠራዊቱን ትጥቅ እንዲፈታ የሚያደርግ ሳይሆን፤ቋሚና የተደራጀ ወታደራዊ ተቋም አድርጎ የሚያጸና ደንብ ነበረ፡፡
ደንቡ ተዋጊዎች ወደ ትግሉ የተቀላቀሉበትን ጊዜ መሠረት በማድረግ የከተማ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ይሰጣል። ከጥቅምት 24 እስከ ሰኔ 21 ቀን፤ 2013 ዓ.ም. የተቀላቀለ 200 ካ/ሜ፣ ከሰኔ 22/2013 እስከ ታህሳስ 30/2014 ዓ.ም. የተቀላቀለ 175 ካ/ሜ፣ እንዲሁም ከጥር 1/2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ደንቡ መጽደቅ ጊዜ የነበረ ተዋጊ 140 ካ/ሜ የመሬት መብት ያገኛል። ይህ አሰራር የትግራይ ኃይልን እንደ መደበኛ የክልል ወይም የሀገር ሠራዊት በመቁጠር የይዞታ ዋስትና የሚሰጥ ነው።
ለሠራዊቱ አባላትና ለቤተሰቦቻቸው በየደረጃው ነፃ የሕክምና አገልግሎት ፤ ነፃ ወይም በመንግሥት የሚሸፈን የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት፤በዓመት ሁለት ጊዜ የደንብ ልብስ፣ ጫማና ካልሲ፤ በዓመት አንድ ጊዜ ቲሸርትና አንሶላ፤ በየሁለት ዓመቱ ብርድ ልብስና ምንጣፍ አቅርቦትን ያካትታል፡፡
ህወሓት ጌታቸው ረዳ ከጊዜያዊ አስተዳደርነት ተነስቶ ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሆን ለፌደራል መንግሥቱ ግፊት ሲያደርግ የነበረው ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የህወሓትን ሀሳብ ደጋፊ ለመሆናቸው ማሳያ ነው ተብሏል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤28🤣15👍6
የኢራን እና የእስራኤል ጦርነት ድጋሚ የመጀመር እድሉ እየሰፋ ይገኛል።
የኢራን የመከላከያ ሚኒስትር አዚዝ ናስርዛዴህ “ጣቶቻችን በቃታ ላይ ናቸው፣ ከእስራኤል ጋር ለሚደረገው ጦርነት ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተናል” ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤14👍3🤔2
🎈 በየወሩ 1ፐርሰንት (1%) ብቻ በመክፈል  የሱቅ ባለቤት ይሁኑ!!!

💫 የአዲስ አመት ስጦታ ከቴምር ሪልስቴት!!

✅ገበያ በሚደራባቸው…
       ⚫️ሳርቤት
       ⚫️ቡልጋሪያ እና 
       ⚫️ገላን

✅በተመጣጣኝ ዋጋ በእውነተኛ ቅናሽ እና
ከወለድ ነጻ አከፋፈል፤ ስርዓት የሚታወቀው
ቴምር ሪልስቴት

🔔 በ2019 ተጨማሪ ብስራት ይዞ ብቅ ብሏል!

✅25 በመቶ ቅድመ ክፍያ
✅ለ24 ወራት በየወሩ የሱቁን ዋጋ 1 በመቶ ብቻ መክፈል ነው!
✅ቀሪውን ክፍያ በ4 የግንባታ ምዕራፎች ሳይጨናነቁ ይከፍላሉ!

✅ቴምር የህልምዎን ማረፊያ በአዲስ አበባ አራቱም አቅጣጫ እየገነባ ነው!

☑️ የእርስዎ ትልቁ ህልም ቋሚ አድራሻ ስለሚያስፈልገው ምርጫዎን ብቻ ይንገሩን!
በፈለጉት አካባቢና ካሬ ንግድ ሳይጀምሩ የሚያተርፉባቸው ሱቆች አሉን!

☎️ለበለጠ መረጃ 09-42-16-42-62  ይደውሉልን
👍3❤1
ከስልክ ስክሪን የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን በጤናችን ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ምንድን ነው?
 
በጨለማ ክፍል ውስጥ አልጋ ላይ ሆኖ ረጅም ሰዓታት የሞባይል ስልክ ብርሃንን መመልከት ለዓይን ብዥታ፣ ለከፍተኛ የዓይን ድካም እና ለዘላቂ የእንቅልፍ መዛባት እንደሚያጋልጥ የጤና ባለሙያዎች አስጠነቀቁ።
 
በሳይንሳዊ እና ህክምና መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፡ ከስልኮችና ዲጂታል ስክሪኖች የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን (Blue Light) አእምሮ የእንቅልፍ ሆርሞን የሆነውን ሜላቶኒን (Melatonin) እንዳያመነጭ እንቅፋት ይፈጥራል። ይህ ሁኔታ በተለይ ማታ ማታ ስልክ የሚያበዙ ሰዎችን ለአእምሮ ድካም እና ለተዛባ የእንቅልፍ ዘይቤ ያጋልጣል።
 
እነዚህ ሁኔታዎች በየቀኑ በሚደጋገሙበት ወቅት የዓይን መድረቅ፣ የራስ ምታት እና የዕይታ መቀነስ ችግሮች እንደሚከሰቱ በህክምና ዘገባዎች ተመልክቷል።
 
የህክምና ባለሙያዎች እንደሚያስገነዘቡት ከሆነ ማታ ለመተኛት ሲዘጋጁ ስልኮችን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ወይም ከዓይን እይታ ማርቅ አስፈላጊ ነው። እንዲሁም የሞባይል ስልኮች ላይ የሚገኘውን የዓይን ጥበቃ (Night Light / Blue Light Filter) ሁነታን መጠቀምና ከመተኛት ከ30 ደቂቃ በፊት ስክሪን አለመመልከት መልካም እንደሆነ ተመልክቷል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19😢4👍3🤪1
የትብብር ለህልውና ሀይሉ የማርኮ ሩቢዮ ስለ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውጥረት ሲናገሩ የታጠቁ ሀይሎችን ከ“ተገንጣይ” እና ከ“ሽብር” ጋር ማዛመዳቸውን አወገዘ፡፡
 
የፌዴራል መንግሥቱን በመቃወም በታጠቁ እና በፖለቲካ ድርጅቶች የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና ጥምረት፤ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ የኢትዮጵያን ግጭት ከ”ተገንጣይ” እና ከ “ሽብር” ተግባር ጋር አያይዘው የሰጡትን አስተያየት አውግዟል።
 
ዋሽንግተን ለግጭቱ ተመጣጣኝና ሚዛናዊ አቀራረብ እንዲኖራትም ጥሪ አቅርቧል።
 
ጥምረቱ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎቹ በአፍራሽ ዓላማዎች የተነሱ ወይም አገርን ለመበተን የታለመ ስልት የሌላቸው መሆናቸውን አስታውቋል።
 
ይልቅስ ድርጊቶቹ የመንግሥት አካላት የጥቅምት 2015 ዓ.ም የፕሪቶሪያ ስምምነትን ጨምሮ ለሰላማዊ መፍትሔ የተደረጉ ጥረቶችን ውድቅ ካደረጉ በኋላ የተወሰዱ የራስን የመከላከል እርምጃዎች መሆቸውን ገልጿል።
ጥምረቱ ዋና ዓላማው ሁሉን አቀፍ ዲሞክራሲያዊ ሽግግርን ማመቻቸት፣ ሰላምና መረጋጋትን መመለስ እና ኢትዮጵያውያን የአገሪቱን ፖለቲካዊ መፃኢ ዕድል በራሳቸው እንዲወስኑ ማስቻል መሆኑን ገልጿል።
 
በመንግሥት ወታደራዊ ተቋማት ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን እንደ ሽብርተኝነት መፈረጁንም የተቃወመው ጥምረቱ፣ እንዲህ አይነቱ አተረጓጎም የግጭቱን እውነተኛ ገጽታ እንደሚያዛባው አብራርቷል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍12❤10🤣7
አርሲ‼️
በአርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ እና በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች የሚገኙ ክርስቲያኖች ተገ*ደሉ።
​1️⃣ኛ. ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም በሺርካ ወረዳ
1. ጌቱ አሰፋ የተባለ ግለሰብ የእርሻ ሥራ(አዝመራ) ላይ እያለ የተገ*ደለ ሲሆን፣ ሃምሳ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው በታጣቂዎች ተወስደዋል። ይህ ወንጀል የተፈጸመውም በቀን 7 ሰዓት ላይ ነው።

​በተጨማሪም በቀን 7/02/2019 ዓ.ም. እንደገና በሺርካ ወረዳ ለሊት በሄላ ዘንባባ ቀበሌ፦
1. ​አቶ ዘውዴ ኃብቴ
2. ​ወ/ሮ አስራሱ ተስፋዬ ተገድ*ለዋል።
​በተጨማሪም፦
1. ​አቶ ፍርዴ አሰፋ
2. ​አቶ ገናና አሰፋ
3. ​አቶ እፋ ዘነበ
4. ​አቶ አስናቀ ዘውዴ
5. ​ወ/ሮ ወጋየሁ መርሻ በታጣቂዎች ተወስደዋል/ታግተዋል)
​
እንዲሁም፦ ካህን/ቀሲስ/ ናርዶስ አሰፋ ጉዳት ደርሶበት (ተቆስለው) በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል።

2️⃣ኛ. በአርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ
​ጥቅምት 5/2019 ዓ.ም.፦
1. ​አቶ ዘነባ ነጋሽ
2. ​አቶ ሳሙኤል ዋሌ
3. ​አቶ ብሩህ አበራ ተገድ*ለዋል።
​በአርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች በተደጋጋሚ በሚከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ምዕመናን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተ*ገደሉ፣ ከቀያቸው እና ከንብረታቸው እየተፈናቀሉ እንዲሁም ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን ገልጿል።
​አርሲ ሀገረ ስብከት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢50❤5👍5🙏1
የስጋ ቤቶች ደንበኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ታወቀ፡ የ“No More ስጋ” ዘመቻ ውጤት እያስገኘ እንደሆነ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን ከልክ ያለፈ የስጋ ዋጋ ጭማሪ በመቃወም በማህበራዊ ሚዲያዎች የተጀመረው “የስጋ ዋጋ ይቀንስ - No More ስጋ” የቦይኮት ንቅናቄ በዋና ከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ አቀባበል በማግኘት ላይ ይገኛል።

በተለይም በቲክቶክ እና በፌስቡክ መድረኮች በስፋት እየተሰራጨ የሚገኘው ይህ የዲጂታል እምቢተኝነት፣ ሸማቾች የሉካንዳ ቤቶችን የዋጋ ጭማሪ ለመቃወም የወሰዱት ቀጥተኛ እርምጃ ሆኗል። በአንዳንድ ታዋቂ የስጋ ቤቶች የ1 ኪሎ ግራም ስጋ ዋጋ እስከ 6 ሺህ ብር መድረሱ የህብረተሰቡን ቅሬታ ወደ ተግባራዊ ቦይኮት እንዲቀየር አድርጎታል።

ትናንት እና ዛሬ በተደረጉ የመስክ ማጣራቶች

1. ቀደም ሲል በከፍተኛ ዋጋ ጥሬ ስጋ በሚሸጡ ታዋቂ የሉካንዳ ቤቶች አካባቢ የታየው የደንበኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።

2. የቦይኮት እርምጃው በተግባር ውጤት ማሳየት መጀመሩን የተመለከቱ ነዋሪዎች፣ የሸማቾች አንድነት ከተጠናከረ የገበያ ግፊት በመፍጠር ዋጋውን ወደ መደበኛ ደረጃ ማመለስ እንደሚቻል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

3. የስጋ ፍጆታን ሙሉ በሙሉ ወይም ለጊዜው ያቆሙ ዜጎች በሰውነታቸው ውስጥ የፕሮቲን እጥረት እንዳይከሰት ስጋን በሌሎች ከፍተኛ ፕሮቲን ባላቸው ምግቦች መተካት እንዳለባቸው ባለሙያዎች መክረዋ።

ስጋን መተካት የሚችሉ ዋና ዋና የፕሮቲን ምንጮች፦

1 ምስር፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽምብራ፣ አኩሪ አተር (Soybeans) እና ሎቢዮ

2. እንቁላል፣ አይብ፣ እርጎ እና ወተት

3. አሳ እና የዓሳ ውጤቶች

4. የኦቾሎኒ ቅቤ፣ የሱፍ ፍሬ፣ የኑግ ፍሬ እና የተለያዩ ለውዞች

5. Mushrooms ስፒናች እና ብሮኮሊ እንዲበሉ ተመክሯል::

ይህ በህብረተሰቡ አብሮነት እየተመራ ያለው የቦይኮት ዘመቻ፣ ሸማቾች በገበያው ላይ ያላቸውን የመደራደር አቅም ያሳየ ትልቅ ማሳያ ነው።

ገበያን ማረጋጋት የሁሉም ወገን ኃላፊነት በመሆኑ፣ ነጋዴዎችም የህዝቡን አቅም ያገናዘበ ፍትሃዊ የዋጋ ተመን ሊከተሉ ይገባል።

ጉርሻ page

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤42👍20🤣4
"አያዋጣችሁም" አብይ ለሻብያ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሕግደፍ መልእክታቸውን አስተላለፉ። ጠቅላዩ ከኢትዮጵያ ቴልቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ኤርትራ "ከነጻነት በኋላ" መቆርቆዟን አውስተዋል። ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል በነበረችበት ወቅት ከ300 በላይ የኢንዱስትሪ ተቋማት እንደነበሯት አውስተው አሁን ግን ያ ሁሉ እንደሌለ ገልጸዋል። ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ ሻብያ የተከተለው ፖሊሲ እንደሆነ ተችተዋል።

"ሕግደፍ በውስጥ ጉዳይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ በጎረቤቶቹ የውስጥ ጉዳይ በተለይም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በመግባት ፀብ አጫሪ ድርጊት መፈጸሙን" ገልጸዋል። "ይህ ጉዳይ ለሻብያ አያዋጣውም፤ በዚህ ከቀጠለ እና ጎረቤታችንነትን አምኖ የማይቀበል ከሆነ እጅግ እጅግ የከፋ ነገር ይደርስበታል፤ አያዋጣችሁም" በማለት አስጠንቅቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣20👍16❤5🙈1😎1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡-
✅  ከጠዋት 2፡00 – 09፡30
👉  6ኪሎ ዪኒቨርስቲ፣ መነን፣ ሀምሌ 19 ፓርክ፣ አሜሪካ ኢምባሲ፣ ስፔን ኢምባሲ፣ ሽሮሜዳ ኪዳነ ምህረት እና አካባቢው፣
  
✅  ከጠዋቱ 02፡00 – ምሽት 11፡30
👉 መድሀኒያለም ት/ቤት ጀርባ፣ መድሀኒያለም ኮንዶሚኒየም፣ ሩፋኤል፣ ፊናንስ፣ ቦናት፣ ሸጎሌ ቴሌ፣ አንበሳ ጋራጅ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል ጀርባ፣ ውሃ ጋኑ አካባቢ (ጎማ አደባባይ ) እና አካባቢው፣
➡️ 18 ማደያው ጋር፣ ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምርሄንሲቭ ት/ቤት እና አካባቢው፣ ኮልፌ መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ በከፊል፣ ሎሚ ሜዳ፣ ኢንዱስትሪ መንደርእና አካባቢው፣ 
👉 ልደታ፣ ብሪሞ ሜዳ፣ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ ድረስ፣ ጦርኃይሎች ምድር ሀይል ግቢ፣ ልደታ ፍርድ ቤት፣ደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ እና አካባቢው ፣
➡️ ጎፋ ገብርኤል አካባቢ፣ ጎፋ ገብርኤል አደባባይ፣ ሶፊያ ሞል፣ ቄራ፣ ገብርኤል ታቦት ማደሪያ፣ አልማዝዬ ሜዳ፣ ጎፋ መብራት ሀይል ኳስ ሜዳው ጋር (ታክሲው ተራ ጋር)፣መስቀል ክትፎ እና አካባቢው ፣
👉 ለገጣፎ፣ ማሚቴ መንደር፣ ስታዲየም ጀርባ፣ ወጣቶች ፣ ለገዳዲ፣500 መንደር፣ 44 ማዞሪያ፣ አበባ መንደር፣ ድሬ ሸኮሩ፣ ለገዳዲ ውሃ ማጣሪያ እና አካባቢው ፣
➡️ ካራቆሬ፣ ረጲ ት/ቤት ፣ ወሌ ኮንዶሚኒየም፣ ወለቴ ማርያም መውጫ፣ ወለቴ ቶታል፣ ወለቴ ኖክ ድረስ ፣ ወጨጫ ማሪያም፣ ወጨጫ ጊዮርጊስ፣ ካራ በከፊል እና አካባቢው ፣
👉 አጃምባ ኮንዶሚኒየም፣ ጥላሁን ከብት እርባታ እስከ ደግነት ኮንዶሚኒየም፣ ኬላ ድረስ፣ ፉሪ፣ አለምገና፣ ሰበታ፣ ዲማ፣ ሜታ፣ ክሬቸር፣ ኪዳነ ምህረት እና አካባቢው ፣
👉ጥሩ መናፈሻ፣ አባዶ ኮንዶሚኒየም በከፊል፣ ኦዞን ት/ቤት፣ ሰበታ ከተማ ፣ አቀበና ውሃ ማምረቻ ፣ዲማ ሆስፒታል እና አካባቢው ፣

✅  ከጠዋቱ 4፡00 – 9፡00
➡️ሴቶች አደባባይ፣ አድዋ ኮንዶሚኒየም፣ ብርሀን እና ሰላም ማተሚያ ፊት ለፊት፣ የካ ወረዳ 6፣ እንደራሴ ኮንዶሚኒየም፣ ብርሀን ጎህ ት/ቤት፣ መለስ ፋውንዴሽን፣ ጨርጨር ስጋ ቤት፣ ዳሽን ተራራ እና አካባቢው፣ 

✅  ከጠዋት 12፡00 – 3፡00
👉 ጎተራ፣ ላንቻ፣ ግሎባል፣ ሪቼ፣ ጨርቆስ በከፊል፣ ደንበል በከፊል፣ ይመቸም ፍየል ቤት፣ሀዲድ ገበያ፣ መስከረም ማዞሪያ አካባቢ የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ያሳውቃል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤7👍3
መርጌታ  ጌታቸው  የባህል መድህኒት ፈውስ  የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል

☞  ለመፍትሄ ሀብት
☞  ለህመም
☞  ለመስተፋቅር
☞  ቡዳ ለበላው
☞  ለገበያ
☞  ሚስጥር የሚነግር
☞  ለቀለም(ለትምህርት)
☞  ለመፍትሔ ስራይ
☞  ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞  ሌባ የማያስነካ
☞  ለበረከት
☞  ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞  ለግርማ ሞገስ
☞  መርበቡተ ሰለሞን
☞  ለዓይነ ጥላ
☞  ለሁሉ መስተፋቅር
☞  ጸሎተ ዕለታት
☞  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞  ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞  ለትዳር
☞  ለድምፅ
👉 0921007264 ይደውሉ መፍትሄ አለን
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🍀🌿🙏 መርጌታ  ጌታቸው  የባህል ህክምና ቀማሚ ከፈጣሪ በታች በተሰጠን ሰለሞናዊ ጥበባችን በአለም አቀፋ እዉቃና አግኝተን የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን🇪🇹።
📞09 21007264
📞09 21007264
👉 የብልት ማነስ

👉የመልፈስፈስ
👉ቶሎ የመጨረስ(የመርጨት) ችግር አለብዎት ባልሽስ አለበት

     ለበለጠ መረጃ
    👉በቴሌግራም ማውራት ለሚፈልግ ከታች ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇@Mgetachew23
በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሀለየ ይፌፅም                      
    🍀🌿 🙏በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር  ውጭም  ሆነ  ከአገር ውስጥ  መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን  
🍀🌿🙏ልብ ይበሉ  ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ

ራሳችሁን ከአጭበርባሪወች ጠብቁ!
❤3👍3
የፈረንሳዩ ካርፉር የችርቻሮ ንግድ ኩባንያ በኢትዮጵያ ከሕዳር 29 ቀን ጀምሮ በይፋ ስራ እንደሚጀምር ተገለጸ

የፈረንሳዩ ችርቻሮ ንግድ ኩባንያ የሆነው ካርፉር ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ከሚድሮክ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ከሆነው ኩዊንስ ሱፐርማርኬት ጋር የፍራንቻይዝ እና የአቅርቦት ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

በዚህ ስምምነት መሰረትም የኩዊንስ ሱፐርማርኬት ምርቶች እና ሱቆችን በካርፉር ብራንድ የመቀየር ስራዎች በመካሄድ ላይ ሲሆኑ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ስራውን የሚጀምረው ከህዳር 29 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

አሁን ላይ ኩዊንስ ሱፐርማርኬት 15 ሱፐርማርኬቶች ያሉት ሲሆን በሁለቱ ተቋማት ስምምነት መሰረትም የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ኮፕ 2027 ድረስ የካርፉር ሱፐርማርኬቶች ቁጥርን ወደ 31 የማድረስ እቅድ ተይዟል፡፡

ስምምነቱ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኢትዮጵያ ያለውን ሰፊ የግብርና ምርት ልምድ በመጠቀም እንደ ቡና፣ ሻይ፣ ቅመማ ቅመም፣ አበቦች እና ትኩስ ፍራፍሬዎችን ወደ ካርፎር ዓለም አቀፍ የችርቻሮ መረብ ለማስገባት እድል እንደሚፈጥለትም ይጠበቃል።

ካርፉር በዓለም ዙሪያ ከ40 በላይ ሀገራት ከ15,000 በላይ መደብሮች ያሉት ሲሆን፣ በ2024 ብቻ 94.6 ቢሊዮን ዩሮ ሽያጭ ያስመዘገበ ግዙፍ ኩባንያ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍12❤6
ቀን 10/02/2019
📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣
አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ
09 03 01 00 06/09 57 97 40 82
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ:# NGO በሁሉም ዘርፍ
🍇የት/ደረጃ /ዲፕሎማ / ድግሪ
🍇የስራ ልምድ ፡- 0አመት
🍇ደሞዝ:- 25000_50000
🍇ፆታ:-   ወ/ሴ
🍇የሰራ ቦታ  አአ/ክልል
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራው  መደብ =- የሰው ሀይል አስተዳደር
🍇የትምርት ደረጃ / ድግሪ
🍇ጾታ ወ/ሴ
🍇የስራ ልምድ 0-3
🍇ደሞዝ 10000+27000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራው መደብ =- ሆስተስ
🍇የትምርት ደረጃ 10 +
🍇ጾታ ሴት
🍇የስራ ልምድ 0 አመት
🍇ደሞዝ 15000 / 25000+
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራው መደብ =-ኢንጅነሪንግ
🍇የትምርት ደረጃ/ ድግሪ
🍇የስራ ልምድ 0/2
🍇ጾታ ወንድ /ሴት
🍇ደሞዝ 18000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራው መደብ /ሆቴል ሱፐርባይዘር
🍇የስራ ልምድ ፡- 1/3 አመት
🍇ደሞዝ:-  13000/25000
🍇ፆታ:-   ወ/ሴ
🍇የሰራ ቦታ  አአ/
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ ፡ ስልክ ኦፕሬተር 
🍇የት ደረጃ ፡ 10/12/ዲፕ
🍇ጾታ ሴ/ወ
🍇የስራ ልምድ ፡ 0 -አመት 
🍇ደሞዝ ፡ 16000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ:-ሹፌር ደ/1/2ህ/1/2ሞተረኛ
🍇የሰራ ልምድ :- 2-10አመት
🍇የት/ት ደረጃ :- 8/10/12
🍇ደሞዝ:- 7000_19000
🍇ፆታ :- ወንድ
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ:- ትኬተር/ኦፊስላይ
🍇የሰራ ልምድ :- 0አመት
🍇የት/ት ደረጃ :- 10/12/ዲፕሎማ
🍇ደሞወዝ   :- 9000~14,000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ፦ሽያጭ /ለፈርኒቸር
🍇የት/ደረጃ፦10/12/diploma/
🍇ደሞዝ:-8000_20000+
🍇የስራ ልምድ: 0አመት
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ :markting
🍇የት ደረጃ ፡- degree 
🍇የስራ ልምድ ፡- 0~3አመት
🍇ደሞዝ :-13000+
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ ፡ Accountant
🍇የት ደረጃ ፡ Degree/"Dip
🍇ፆታ: ሴ
🍇የስራ ልምድ ፡ 0 - 8አመት
🍇ደሞዝ ፡  8,000-35,000 
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ ፡ IT
🍇የት/ደረጃ ፡-  degree /dip
🍇የስራ ልምድ ፡- 0 -2አመት
🍇ፆታ:- ሴ/ወ
🍇ደሞዝ:- 8000-15000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ፦ካሸር
🍇የት/ደረጃ፦10 +
🍇የሰራ ልምድ 0~3 አመት
🍇ደሞዝ:- 7000-14000
🍇ፆታ፦ሴ
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ፦/መምህር በሁሉም
🍇የት/ደረጃ፦ዲፕልማ / ዲግሪ
🍇የስራ ልምድ: 0~2አመት
🍇ደሞዝ:- 10000+20000
🍇ፆታ፦ሴት/ወንድ
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራው መደብ ቡቲክ ሴልስ
🍇የት ደረጃ ፡ 8
🍇ፆታ: ሴ
🍇የስራ ልምድ ፡ 0-1
🍇ደሞዝ :8000-20,000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራው መደብ =- የጥፍር እና አይላሽ
🍇የትምርት ደረጃ 8+
🍇የስራ ልምድ 0 -1 አመት
🍇ደሞዝ 20000+
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራው መደብ=- ፀሀፊ
🍇የትምርት ደረጃ ዲፕሎም
🍇የስራ ልምድ ያላት
🍇ፆታ ሴት
🍇ደሞዝ 8000/25000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራው አይነት =- ዱቄት ፋብሪካ ሁለገብ
🍇የትምርት ደረጃ 8/10/12
🍇የስራ ልድ 0 አመት
🍇ፆታ ሴት/ወንድ
🍇ደሞዝ 17000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራው መደብ =- ከስተመር ሰርቢስ
🍇የትምርት ደረጃ 8/10/12
🍇የስራ ልምድ 0 አመት
🍇ጾታ ሴት
🍇ደሞዝ 10000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ፦ሼፍ ዋና / እረዳት
🍇የት/ደረጃ፦ ሰርተፍኬት/
🍇ደሞዝ:-9000-40000
🍇ፆታ፦ወንድ/ሴት
🍇የስራ ልምድ ፡ 0_5አመት
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ ፡ ሶፍት ፋብሪካ እሸጋ
🍇የት ደረጃ ፡ 8+
🍇ጾታ ሴ/ወ
🍇የስራ ልምድ ፡ 0
🍇ደሞዝ ፡  16000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ ፡ ሞባይል ቤት ሴልስ
🍇የ/ት ደረጃ ፡-8
🍇ጾታ ሴት
🍇የስራ ልምድ ፡- 0 /2አመት
🍇ደሞወዝ :- 10000+ኮምሽን
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ ፡ reception
🍇የት ደረጃ ፡ 10/12
🍇የስራ ልምድ ፡ 0-2
🍇ደሞዝ 8000/15000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ፦ ፍተሻ ፅዳት ለባንክ
🍇የት/ደረጃ፦8/12
🍇 የሰራ ልምድ 0 አመት
🍇ደሞዝ:- 5000
🍇የስራ ቦታ: በሰፈር አቅራብያ
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇የስራ መደብ ፡ ጉዳይ አስፈፃሚ ፖስተኛ
🍇የት ደረጃ ፡ 10/12/"Dip
🍇ፆታ: ሴ/ወ
🍇የስራ ልምድ ፡ 0-2አመት
🍇ደሞዝ ፡  15000
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
🍇ሀውስ ኪፒግ
🍇የት ደረጃ ፡ 8+
🍇የስራ ልምድ ፡ 0-1አመት
🍇ደሞዝ ፡ 7000+
🍇🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢
ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇
አድራሻ:-  መገናኛ መተባበር ህንጻ 4 ኛ
ፎቅ ቢሮ ቁ B421 👇👇👇👇👇
         ☎️ 09 57 97 40 82
         ☎️ 09 03 01 00 06
               09 97 47 03 84
❤6👍4🤯1👌1
ህወሃት ላይመለስ ሄዷል-ጄ/ል ታደሰ ወረደ‼️
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በወቅታዊ የትግራይና የሀገሪቱ የፖለቲካ እና የደህንነት ሁኔታዎች ላይ ከአውራ አምባ ታይምስ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

​የእገታው ሂደት እና የተፈጠረው ውዝግብ
​ጀነራል ታደሰ ወረደ በቃለ መጠይቁ ወቅት በቅርቡ ስለገጠማቸው እገታ ሂደት ዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል፦
​የእገታው አጀማመር፦ ሌሊት በቁጥጥር ስር ለማዋል የተደረገው ሙከራ ተገቢ እንዳልነበር እና በፖሊስ ሽፋን የመጡ አካላት እንደነበሩ ገልጸዋል።
​የተወሰደው እርምጃና ዝውውር፦ ከቤት ከተወሰዱ በኋላ በኤች ዜድ (HZ) ሆቴል እንዲቆዩ መደረጉን፣ በመቀጠልም በአክሱም፣ አድዋ እና ራማ አቅጣጫዎች እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ ተናግረዋል።
​የውሳኔው አካላት፦ ውሳኔውን ያሳለፉትና ያስፈጸሙት ይፋዊ የነበረው መንግስታዊ መዋቅር ሳይሆን፣ በፖለቲካ እና በሚሊተሪ ስብስብ የተዋቀረ “የአቋቋምት ኮሚቴ” እና ራዲካል አካላት እንደሆኑ ጠቁመዋል።

​ከመከላከያ ሰራዊት ጋር የተደረገ ግንኙነት፦ ከራማ ከተማ በመውጣት ከአድበራና ከአሮህ መካከል ከአገኘው የመከላከያ ሰራዊት አባላትና አመራሮች ጋር በሰላም መገናኘታቸውን አብራርተዋል።

​በእሳቸው ላይ ለሚነሱ ወቀሳዎችና ዘመቻዎች የተሰጠ ምላሽ
​በተለያዩ ማህበራዊና መደበኛ ሚዲያዎች በጀነራል ታደሰ ወረደ ላይ ለሚሰነዘሩ ቅሬታዎችና ጥርጣሬዎች የተሰጡ ምላሾች፦
​የህወሓት ሃይል በማደራጀትና ደንብ በማውጣት ሂደት፦ በወቅቱ የተሰሩ ስራዎች በሙሉ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ እና ከካቢኔው አሰራር ጋር የተያያዙ እንደነበሩ ገልጸዋል።

​የአቋም ልዩነቶችና ተቃውሞዎች፦ በየደረጃው በነበሩ ውሳኔዎች ላይ የነበራቸው ተቃውሞና ልዩነት በሰነድና በሪኮርድ የተያዘ መሆኑን አብራርተዋል።

​የጦር መሳሪያዎች ምዝገባና አመጣጥ፦ በስልጣን ዘመናቸው የተከናወኑ የደህንነት ስራዎች ግልጽ እንደነበሩና ከእሳቸው እውቅና ውጪ በድብቅ የተሰሩ ነገሮች ካሉ ማጣራት እንደሚቻል ገልጸዋል።
​ስለ ህወሓት የወደፊት እጣ ፈንታ እና የሽግግር ወቅት
​ጀነራል ታደሰ ወረደ ስለ ድርጅቱ ህልውና እና ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፦

​የህወሓት የፖለቲካ ማብቂያ፦ ህወሓት በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ማብቂያው ላይ እንደሚገኝና ድርጅቱን በሰላም ማሳረፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።
​ለድርጅት ህልውና የሚከፈል መስዋዕትነት ማብቃት አለበት፦ “ህወሓት ከሌለ ትግራይ የለችም” የሚለው አስተሳሰብ የተሳሳተ መሆኑንና ድርጅቱ ሳይኖርም ትግራይ እንደምትቀጥል አስረድተዋል።
"ሰራዊቱም ከሞተ ጋር መሞት የለበትም የTPLF አመራሮች አንድ የተሳካላቸው ነገር ቢኖር፣ ድርጅቱን ወደ መቃብር አውርደውታል፣ላይመለስ ሄዷል" ብለዋል።
​የወጣቱ እና የአዲሱ ትውልድ ድርሻ፦ አመራሩ ከወጣቱ ትውልድ ጋር መቆራረጡን ጠቅሰው፣ የትግራይ ህዝብና አዲሱ ትውልድ የራሱን እድልና ህልም መቅረፅ እንዳለበት አሳስበዋል።
​የሰላም አስፈላጊነት፦ ህዝቡ ተጨማሪ ጦርነትና ውድመት መሸከም የማይችል በመሆኑ ትኩረቱ በፖለቲካዊና በሰላማዊ መፍትሔዎች ላይ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19🤪10👍4
ሀሰተኛ መረጃ‼️
ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ የሚለው መረጃ ሀሰተኛ መረጃ ነው።
​የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ ተሹመዋል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የቆየው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀና ሀሰተኛ መረጃ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍10🤣9
ቴምር ሪልእስቴት  📌 አዲስ ሳይት🎯 መገናኛ ቤል ቪው ሆቴል አጠገብ በ35%  ቅናሽ ይዘን መጥተናል።
የሳይቱ ልዩ መገለጫ
✅ Top veiw
✅ ፔንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 የካሬ አማራጭ
✅40% ከፍላችሁ 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት
✅ ያለምንም ወለድ የሚከፈል
✅ የጫካ ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል
✅20% ቅድመ ክፍያ
✅35% ቅናሽ

#ያስታውሱ፦
📌ቀድመው ለሚመጡ ውስን ደንበኞች 40% ቅድመ ክፍያ ከፍላችሁ ቀሪውን 60% ቁልፍ ስትረከቡ  የምትከፍሉበትን  አከፋፈል አቅርበናል
📌100%ሲከፍሉ የ35% ቅናሽ ያገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ በ📞09-42-16-42-62
❤2👍2
በታሸጉ ምግቦችና በአመጋገብ ሥርዓት ለውጥ ህፃናት ለስኳር ህመም ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸው ተገለፀ

የታሸጉ ምግቦችና ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ልምድ በህፃናትና በወጣቶች ላይ የጤና ችግሮችን እያባባሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ማህበር አስታውቋል።

የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ኤርሚያስ ገብረማርያም ከብሰራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ በታሸጉ ምግቦች እና በአመጋገብ ስርዓት መለዋወጥ ሳቢያ ህፃናት እና እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ ያሉ አዋቂዎች ለስኳር ህመም ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል።


ከፍተኛ የውሃ ጥም፣ በተደጋጋሚ መሽናት፣ የመራብ ስሜት መጨመር፣ ድካምና ያልታሰበ የሰውነት ክብደት መቀነስ የዓይነት 1 የስኳር ህመም ዋና ዋና ምልክቶች ስለሆኑ፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች እነዚህን ምልክቶች በልጆቻቸው ላይ ሲያስተውሉ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመውሰድ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ተነግሯል።

ስለሆነም ህፃናት ከታሸጉ ምግቦችና ስኳር ከበዛባቸው መጠጦች ይልቅ በአትክልት፣ በፍራፍሬ፣ በጥራጥሬና በሌሎች ገንቢ ምግቦች ላይ የተመሰረተ ሚዛናዊ አመጋገብ እንዲኖራቸው ማበረታታት እንደሚገባ ማህበሩ ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም የበሽታውን ምልክቶች ማወቅ፣ በጊዜ ምርመራ ማድረግና ተገቢውን ህክምና ማግኘት በህፃናትና በወጣቶች ጤና ላይ የሚደርሱ ከባድ ጉዳቶችን ለመቀነስ ወሳኝ መሆኑን የስኳር ህመማን ማህበር የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ኤርሚያስ ጨምረው  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤5