አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.9K subscribers
17.6K photos
434 videos
23 files
3.04K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የግብፅ አቻቸው አብደል ፈታህ አልሲሲ ባቀረቡላቸው ጥሪ መሠረት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ ካይሮ ገብተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣29👍12💯4💔3❤2👌2🤔1🎉1
መቐለ‼️
መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ሰራዊት መቀሌ ከተማ መግባታቸው ተገለፀ።
ይህን ተከትሎ ዛሬ ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ የህወሓት ሰራዊት ከመቐለ ከተማ በሁሉም አቅጣጫዎች ወጥተው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ ከስፍራው የተገኘው መረጃ አመላከተ።

የህወሐት ሰራዊት በዋናነት የመቐለ - ሓውዜን - ዕዳጋዓርቢ የመስመሮችን እየተጠቀመ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፣ ማንኛውም አመራር እንዳይቀር በተደረገ ጥብቅ ሰው በሰው ቁጥጥር እንቅስቃሴው እየተመራ ይገኛል።

በተጨማሪም የዚሁ እንቅስቃሴ አካል በሆኑት የዓድዋ፣ አክሱም እና ራማ ከተሞች በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የሰው ስብስብና ጥልቅ እንቅስቃሴ እንደሚታይ ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤28👍12🤪10🎉1🤣1
በመቀሌ ከተማ ዘረፋ አስደንጋጭ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ‼️
በመቀሌ ከተማ የመንግሥት እና የግል ንብረቶች ላይ ከፍተኛ ዝርፊያ እየተፈፀመ መሆኑ ታወቀ።
ከትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ፣የፕሬዝዳንት ቢሮ...ሁሉም ማለት ይቻላል የመንግስት ቢሮዎች እና የግል ነጋዴዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተዘረፉ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
በተለይ በህግ ጥላ ስር የነበሩና ከእስር ቤት የወጡ ግለሰቦች በከፍተኛ ሁኔታ ዘረፋ እየፈፀሙ ነው ተብሏል።
ተቋማት ያለ ጠባቂ በመቅረታቸው ዘረፋው መባባሱንም AFP ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15😢7👍5👀2🥰1
“ሕወሓት በሀገር ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽሟል”

የትግራይ የሰላም ተልዕኮ አስተባባሪ ሌተናንት ኮሎኔል ገብረዋሕድ ኃይሉ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን ከውጭ ኃይሎችና ከሀገር ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመተባበር በሀገር እና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽሟል። የቡድኑ የ30 ዓመታት የፖለቲካ ውድቀት ትግራይን የጦርነት አውድማ በማድረግ ሕዝቡን በማያባራ የኢኮኖሚ ውድቀት፣ የሥነ ልቦና ስቃይ እና ማኅበራዊ ውጥንቅጥ ውስጥ እንደከተተው ተመላክቷል።

በትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ምስቅልቅል የቡድኑን የባንዳነት እና የፖለቲካ ከንቱነት የሚያሳይ መሆኑን ያስታወቁት ሌተናንት ኮሎኔሉ፣ ሕዝቡ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ የከፈለው መስዋዕትነት ወደ ባርነት መቀየሩን ገልጸዋል። ይህንን የቁልቁለት ጉዞ ለመቀልበስ ከዜሮ በመነሳት የፖለቲካ ምኅዳሩን፣ የሲቪል ማኅበራትን እና የሥነ ልቦና ግንባታን እንደ አዲስ መጀመር የግድ እንደሚል አጽንኦት ተሰጥቷል።

በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የትግራይ ለውጥ ኃይልና የፌደራል መንግሥት የየበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው ተጠቁሟል። የትግራይ ሕዝብ የሚመጥነውን መሪ በዲሞክራሲያዊ መንገድ መምረጥ እንዲችል ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች እና ወጣቶች መለያየትን በመተው የጋራ መድረክ እንዲፈጥሩ ጥሪ ቀርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤23🤣13👍11🤯2💯1🤪1😎1
🚨 የሀገር መከላከያ ሠራዊት መቀሌን አልፎ ወደ ኤርትራ ድንበር ጉዞ መጀመሩ ተገለፀ

​የሀገር መከላከያ ሠራዊት መቀሌ ከተማን አልፎ ወደ ኤርትራ ድንበር የሚወስዱ መስመሮችን በመያዝ ጉዞውን መቀጠሉ እና ከተማዋን ከዝርፊያ የመጠበቅ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተሰምቷል።

​የቦታዎች ቁጥጥር፦ የመከላከያ ሠራዊቱ ከመቀሌ በኋላ ሳፊያ እና አዲ አከል የተባሉ አካባቢዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን፣ ሀገረ ሰላምን ጨምሮ ከመቀሌ የሚያስወጡ ዋና ዋና መንገዶችን መያዙ ተነግሯል።

​የኤርትራ ድንበር እንቅስቃሴ፦ የመከላከያ ሠራዊቱ እንቅስቃሴውን ወደ ኤርትራ አቅጣጫ በሚወስዱ የድንበር መስመሮች በኩል አጠናክሮ መቀጠሉ ተመላክቷል።

​የተቋማት ጥበቃ ስምሪት፦ የመከላከያ ልዩ ዘመቻ ኃይል ከትግራይ የሰላም ኃይል ጋር በመቀናጀት የመቀሌ ከተማ ተቋማትን ከዝርፊያና ከውድመት ለመጠበቅ ስምሪት አድርገው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍46❤30🤪25🤣2🕊1🫡1
❗️Breaking
በሰሜን ኢትዮጵያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና ውጥረት አዲስ መረጃ ወጣ 👇👇
https://t.me/addlist/rmM0bFFNbycwMTM0
👍9❤2
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ለሌላቸው ግብር ከፋዮች የሽግግር መመሪያ ይፋ አደረገ
​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 የበጀት ዓመት የግብር ማሳወቂያ ወቅት የሂሳብ መዝገብ ማቅረብ ላልቻሉ የደረጃ «ሀ» እና «ለ» ግብር ከፋዮች የሚያገለግል የማስተናገጃ መመሪያ ይፋ አደረገ። ቢሮው መስከረም 2019 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ እንደገለጸው፣ ይህ አሰራር ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ የሚሰራ ጊዜያዊ የሽግግር መፍትሔ ነው።
​መመሪያው የተዘጋጀው በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 እና በነባር አዋጆች መሰረት መዝገብ መያዝ ግዴታ ቢሆንም፣ ከግብር ከፋዮች በቀረቡ የሥራ ባህሪ ቅሬታዎች ምክንያት ነው። በዚህም መሰረት፡-
​ከመንግስት ጋር ውል ያላቸው፡- የትምህርት ቤት መጋቢ እናቶች፣ የፅዳት፣ የቆሻሻ አሰባሰብ እና ገፀ-ምድር ማስዋብ ማህበራት ዓመታዊ የክፍያ ሰነድ በማቅረብ በደንብ ቁጥር 410/2009 ሠንጠረዥ «ሐ» መሠረት ግብራቸው ይሰላል። የሸገር ዳቦ አከፋፋዮች ተጨማሪ ንግድ ካላቸው፣ ተጨማሪው ስራ ብቻ ተለይቶ ግብር ይጣልበታል።
​በትርፍ ህዳግ የሚስተናገዱ፡- የጫኝና አውራጅ፣ የኤሌክትሪክ ምሰሶ ቆፋሪዎች፣ የጥበቃ ማህበራት እና የታክሲ ታራ አስከባሪዎች የሂሳብ መዝገብ ባያቀርቡም ለዘርፉ በተቀመጠው የትርፍ ህዳግ መሰረት ግብራቸው ይወሰናል።
​የሙያ ፈቃድ ያላቸው እና የኪራይ ገቢዎች፡- ጠበቆች፣ የኢንሹራንስ ወኪሎችና ገማቾች እንዲሁም መዝገብ የሌላቸው የንግድና መኖሪያ ኪራይ ገቢ ያላቸው አካላት 35 በመቶው እንደ ወጪ ተይዞላቸዋል፤ በቀረው 65 በመቶ ገቢያቸው ላይ ግብር ይከፍላሉ።
​የትራንስፖርት ዘርፍ እና ያደጉ ግብር ከፋዮች፡- በትራንስፖርት የተሰማሩ ደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች የ57 በመቶ የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ ተደርጎላቸው በደረጃ «ለ» ቀመር የሚያሳውቁ ሲሆን፣ በአዲሱ አዋጅ ወደ ደረጃ «ሀ» ያደጉትም በደረጃ «ለ» አሰራር እንዲስተናገዱ ተወስኗል።
​ይህ አሰራር ለ2018 የበጀት ዓመት ብቻ የሚያገለግል ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች ለቀጣይ ዓመት መዝገብ ለመያዝ የቃል-መሐላ እንደሚፈፅሙና የሰነድ አለመያዝ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚጣስባቸው ቢሮው አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍4😢3
ሁለት መረጃዎች‼️
📌ኤርትራ ከዞን በታች ያሉ የትግራይ አመራሮች ወደ ኤርትራ እንዳይገቡ ወስናለች።
📌ዛሬ መስከረም 23/2019 ዓ.ም ኤርትራ በአዲግራት አቅጣጫ የሜካናይዝድ ጦሩን በከፍተኛ ሁኔታ እያንቀሳቀሰች መሆኑ ተረጋግጧል።
በርካታ የህወሓት ታጣቂዎችም ወደ አዲግራት ገብተዋል። አዲግራት ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን መዘገባችን ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍11🤪7🙊1
ለሻዕቢያ በእጥፍ ምላሽ ይሰጠዋል-ዶ/ር አብርሃም‼️
በሰሞኑ ውጊያ የሻዕቢያ ሰራዊት መሳሪያ ይዞ፣ግንባር ወስዶ፣የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ ከህወሓት ጋር አብሮ ተዋግቷል። በርካታ መሳሪያ ተማርኳል፣ የሞቱም አሉ።
ሻዕቢያ ለዚህ ተግባሩ በእጥፍ ምላሽ ይሰጠዋል፣የአንድን ሀገር መንግስት ከባንዳ ጋር አብሮ መውጋት ምን ሊያስከትል እንደሚችል በምላሹ ያገኘዋል'ሲሉ ዶክተር አብርሃም በላይ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍34🤣18❤14🤪3😎2🕊1🫡1
መርጌታ  ጌታቸው  የባህል መድህኒት ፈውስ  የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል

☞  ለመፍትሄ ሀብት
☞  ለህመም
☞  ለመስተፋቅር
☞  ቡዳ ለበላው
☞  ለገበያ
☞  ሚስጥር የሚነግር
☞  ለቀለም(ለትምህርት)
☞  ለመፍትሔ ስራይ
☞  ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞  ሌባ የማያስነካ
☞  ለበረከት
☞  ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞  ለግርማ ሞገስ
☞  መርበቡተ ሰለሞን
☞  ለዓይነ ጥላ
☞  ለሁሉ መስተፋቅር
☞  ጸሎተ ዕለታት
☞  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞  ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞  ለትዳር
☞  ለድምፅ
👉 0921007264 ይደውሉ መፍትሄ አለን
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🍀🌿🙏 መርጌታ  ጌታቸው  የባህል ህክምና ቀማሚ ከፈጣሪ በታች በተሰጠን ሰለሞናዊ ጥበባችን በአለም አቀፋ እዉቃና አግኝተን የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን🇪🇹።
📞09 21007264
📞09 21007264
👉 የብልት ማነስ

👉የመልፈስፈስ
👉ቶሎ የመጨረስ(የመርጨት) ችግር አለብዎት ባልሽስ አለበት

     ለበለጠ መረጃ
    👉በቴሌግራም ማውራት ለሚፈልግ ከታች ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇@Mgetachew23
በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሀለየ ይፌፅም                      
    🍀🌿 🙏በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር  ውጭም  ሆነ  ከአገር ውስጥ  መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን  
🍀🌿🙏ልብ ይበሉ  ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ

ራሳችሁን ከአጭበርባሪወች ጠብቁ!
❤5👍2🥱2🤷‍♂1
ግብጽ "ከደሙ ንጹህ ነኝ" ስትል ለአፍሪካ ህብረት ምላሽ ሰጠች

የአፍሪካ ኅብረት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ግብጽ ውጥረትን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ባወጣው መግለጫ ላይ ግብጽ  ተቃውሞዋን ገልጻለች። የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን እንደተናገሩት፣ የኅብረቱ ጥሪ ግብጽን በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት እና በውስጣዊ ቀውስ ውስጥ በግድ ጎትቶ ለማስገባት ያለመ ነው ሲሉ ወቅሰዋል። ግብጽ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ውስጥ ምንም ዓይነት እጅ እንደሌላትና የኅብረቱ መግለጫ እንዳስገረማት የመንግሥት የዜና አውታሯ ዘግቧል።

የአፍሪካ ኅብረት ይህንን የሰላምና ማረጋጋት ጥሪ ያቀረበው በቀጠናው ውስጥ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ውጥረት በነገሠበት ወቅት ነው። ጥሪው የተላለፈው ኢትዮጵያና ግብጽ አንዳቸው የሌላኛቸውን ዲፕሎማቶች ማባረራቸውን፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ የኤርትራ 10 ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ውስጥ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ተከትሎ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12🤣6👍5🤔3🤪1
መቀሌን ለቀናል-ህወሓት‼️
ህዝባችን ላይ ሊፈፀሙ ከሚችሉ ጥቃቶች በመስጋት መቀሌን ለቀን ወጥተናል ሲል ህወሓት አስታወቋል።

ሰማዩ የእኛም እንደሆነ በዚያው ይቀጥላል፣ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብሏል።

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ እንዲሁም በአፋር ክልል ለተፈፀሙ የድሮን ጥቃቶች ህወሓት ሀላፊነት ወስዷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣67❤14👍5🤔3
”ጦርነቱ አጭር ይሆናል፤ ተቃዋሚ ኃይሎችም
ክፉኛ ይሸነፋሉ” የዩጋንዳ ጦር ዋና አዛዥ

የዩጋንዳ ጦር  ዋና አዛዥ ጄኔራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ በኤክስ (X) ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሚመራውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት (ENDF) “በአፍሪካ ካሉ ጠንካራ ሠራዊቶች አንዱ” ሲሉ ገልጸውታል።

ጄኔራል ሙሆዚ አክለውም፣ “በወንድሜ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሚመራው የኢትዮጵያ  መከላከያ ሠራዊት በአፍሪካ ካሉ ጠንካራ ሠራዊቶች አንዱ ነው። ጦርነቱ አጭር ይሆናል፤ ተቃዋሚ ኃይሎችም ክፉኛ ይሸነፋሉ” በማለት መልዕክታቸውን አስፍረዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪39❤33🤣8👍4🫡2👌1😎1
ስልክ መስራት ጀምሯል‼

ለቀናት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት በመቀሌ ከተማ በዛሬው ዕለት ዳግም መስራት መጀመሩ ተሰምቷል።

ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ የሞባይል የስልክ ጥሪ ድምፅ እና የሞባይል ዳታ (ኢንተርኔት) አገልግሎት በአሁኑ ሰዓት መስራት ጀምሯል።

የአገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ የመመለስ አሁንም በስፋት እየተሰራ ነው ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤27👍6🙏1👌1
ቴምር ሪልእስቴት  📌 አዲስ ሳይት🎯 መገናኛ ቤል ቪው ሆቴል አጠገብ በ35%  ቅናሽ ይዘን መጥተናል።
የሳይቱ ልዩ መገለጫ
✅ Top veiw
✅ ፔንት ሃውስ ከ209 ካሬ እስከ 351 የካሬ አማራጭ
✅40% ከፍላችሁ 60% ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት
✅ ያለምንም ወለድ የሚከፈል
✅ የጫካ ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል
✅20% ቅድመ ክፍያ
✅35% ቅናሽ

#ያስታውሱ፦
📌ቀድመው ለሚመጡ ውስን ደንበኞች 40% ቅድመ ክፍያ ከፍላችሁ ቀሪውን 60% ቁልፍ ስትረከቡ  የምትከፍሉበትን  አከፋፈል አቅርበናል
📌100%ሲከፍሉ የ35% ቅናሽ ያገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ በ📞09-42-16-42-62
❤4👍1💯1🙉1
መቐለ‼️
📌ዛሬ ለሊቱን በመቀሌ ከተማ ዘረፋ ላይ ተሰማርተው በነበሩ ግለረቦች ላይ ከፍተኛ ዘመቻ ተካሂዷል።
TPF እና መከላከያ በሌሊት መጋዘኖችን ሲሰብሩ፣ ሳንጃ እና መሳሪያ ታጥቀው በቡድን ሲጓዙ በነበሩ በርካታ ዘራፊዎች ላይ ከባድ ተኩስ ልውውጥ ተደርጓል።
በመጨረሻም በርካታ ሌቦች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ባጃጆች ​​ተይዘዋል።

📌በትግራይ ክልል ለ10 ቀን ያህል ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት መስራት ጀምሯል።
📌 መከላከያ ሠራዊት እና TPF ከመቀሌ ወደ አጉላዕ እና ውድሮ እያቀና ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤28👍8🤪2👌1
የባንክ አገልግሎት‼️
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የባንክ አገልግሎቶችን በሚቀጥለው ሳምንት ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤22👍7🙏4🤪2🥰1👌1
ሰበር❗

ኤርትራ ፀረ ድሮን መትከሉ ታወቀ

ኤርትራ በአክሱም እና አድዋ አካባቢ ፀረ ድሮን መትከሉ ታወቀ።ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የመካናይዝድ ጦሩን በከፍተኛ ሁኔታ እያስጠጋ ይገኛል።

አሜሪካ ዛሬ ባወጣችው አስቸኳይ መግለጫ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ የሚደረግ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆም እና ሁሉቱ ሀገራት በሰከነ መንገድ ጉዳዩን እንዲመለከቱ ጥሪ አቅርባለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤27🤪14👍3🙉3🕊2👀2😢1💔1
የበጎ አድራጎት ፈርጡ አቶ ወንዱ በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

​የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

እድሜያቸው በሰባዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የሚገኘው አቶ ወንዱ በካንሰር ያጡትን የልጃቸውን ማቲዎስን ስም በመሰየም እ.ኤ.አ. በ2004 ፋውንዴሽኑን ከመሰረቱበት ጊዜ ጀምሮ፣ ደሞዝ ከሚከፈላቸው የመንግሥት የኃላፊነት ቦታቸው በፈቃደኝነት በመልቀቅ ህይወታቸውን ሙሉ ለበጎ አድራጎት ሰጥተዋል።

​ፋውንዴሽኑ ላለፉት 22 ዓመታት ከ5,000 በላይ የካንሰር ህሙማንና ቤተሰቦቻቸውን የህክምና፣ የትራንስፖርት፣ የምግብና የሥነ-ልቦና ድጋፍ አድርጓል። በተጨማሪም በአገር አቀፍ ደረጃ የካንሰርና የትምባሆ ቁጥጥር ፖሊሲዎች እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከታቸው ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ዘጠኝ ያህል ታላላቅ ሽልማቶችን አግኝተዋል።

​በቅርቡ በኮላንጂዮካርሲኖማ (የሐሞት ቧንቧ ካንሰር) ታመው በህክምና ላይ ነበሩ።

የቀብር ስነ-ስርዓታቸው ዝርዝር መረጃ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢27❤11💔4👍3🫡2🙏1
በረራ‼️
በትግራይ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ በመጪው ሳምንት ረቡዕ ወይም ሀሙስ ወደ መቀሌ በረራ ሊጀመር እንደሚችል ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍20🤣11❤6🤪1