አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.3K subscribers
18K photos
443 videos
23 files
3.07K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አዲስ ተላላፊ ቫይረስ በቻይና ተገኘ

​በቻይና የሚገኙ ተመራማሪዎች በኡካን በንክሻ አማካኝነት ወደ ሰው የሚተላለፍ ALTNV የተሰኘ አዲስ ቫይረስ ማግኘታቸውን አስታወቁ።

ቫይረሱ በቤጂንግ የፓቶጀንስ እና ባዮሴፍቲ ላቦራቶሪ ተመራማሪዎች የተገኘ ሲሆን፣ ውጤቱም በኒው ኢንግላንድ ሜዲካል ጆርናል ላይ ታትሟል።

​በጥናቱ ከተካተቱት 3,163 ታካሚዎች መካከል 10.4 በመቶ የሚሆኑት በቫይረሱ የተያዙ ሆነው ተገኝተዋል።

ዋነኛ ምልክቶቹም ከፍተኛ ድካም (84%)፣ የሆድ እና የምግብ ፍጨት ችግር (80%)፣ የደም ፕሌትሌት መቀነስ እና የጉበት ኢንፌክሽን ናቸው።

ALTNV ብቻ የያዛቸው ታካሚዎች ሙሉ በሙሉ ያገገሙ ቢሆንም፣ ከሌሎች ተመሳሳይ ቫይረሶች ጋር ደርበው የተያዙ ሰዎች ግን ለኩላሊት መድከም  እና ለሞት (18.4%) ተዳርገዋል።

​ተመራማሪዎቹ በ15 የቻይና ግዛቶች በተሰበሰቡ ኡካኖች ላይ ቫይረሱን ያገኙ ሲሆን፣ በሽታው ከሌሎች ጋር ስለሚመሳሰል ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ እንዲደረግ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15😢5👍3🥱2😱1🤣1👀1
አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን  መሥራች ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ አቶ አረጋ ከበደን የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት  አድርጎ በድጋሜ ሾሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣23❤9👍6🤩2🤡1😈1🤪1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የአማራ ክልል ምክር ቤት የቢሮ ኃላፊዎች ሙሉ ሹመት❗❗❗
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት በርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የቀረቡለትን ሹመቶች አጸደቀ። በዚህም መሠረት፡-

1. የሻለም ገዛኸኝ ዳምጠው (ዶ/ር) - ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ፣
2. ጥላሁን ፈንታው ተሾመ - ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ፣
3. መስፍን አበጀ ተፈራ (ዶ/ር) - ግብርና ቢሮ ኃላፊ፣
4. ጥላሁን ወርቅነህ ተክሌ - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣
5. ሞላ መልካሙ ከበደ (ዶ/ር) - ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
6. ዳኝነት ፈንታው መኮንን (ዶ/ር) - ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ፣
7. አታላይ ጥላሁን ጫኔ - ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ፣
8. ዶ/ር ጋሻው ሙጬ አለምነው - እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
9. እሸቱ የሱፍ አየለ (ዶ/ር) - ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣
10. አባይ መንግስቴ ሰላምሰው - ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፣
11. ባንቺአምላክ ገብረማርያም በላይ - ሲቪል ሰርቪስ እና ሰው ሃብት ቢሮ ኃላፊ፣
12. እንድሪስ አብዱ አሕመድ - ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ፣
13. አብዱልከሪም መንግሥቱ ይማም - ጤና ቢሮ ኃላፊ፣
14. መልካሙ ጸጋዬ ገላው - ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ፣
15. ኢብራሂም መሀመድ እንድሪስ (ዶ/ር) - ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
16. ሲሳይ ዳምጤ አበባይ - መሬት ቢሮ ኃላፊ፣
17. ጋሻው አወቀ ትኩዬ (ዶ/ር) - መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ፣
18. ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) - ፕላንና ልማት ቢሮ፣
19. ተስፋሁን ዓለምነው ይስማው - የአካበቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኃላፊ፣
20. ብርሃኑ ጎሹ አዘረፍ - ፍትህ ቢሮ ኃላፊ፣
21. ሃይሌ አበበ ብዙአየሁ - የማዕድን ቢሮ ኃላፊ፣
22. ስቡ ገበያው ታረቀ (ዶ/ር) - ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ፣
23. ብርቱካን ሲሳይ እንየው - ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሸመዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤23👍7🥱5😡4
አብዓላ‼️
ከመቀሌ በ50 ኪሎሜትር እርቀት ላይ የምትገኘውና በአፋርና ትግራይ አዋሳኝ ላይ የምትገኘው አብዓላ ከተማ በአፋር የፀጥታ ሀይሎች፣በትግራይ ሰላም ሰራዊት እና በመከላከያ ሰራዊት ከቀኑ 7:15 ቁጥጥር ስር መግባቷን በስፍራው የሚገኙ የአዩዘሀበሻ ምንጮች አረጋገጡ።
ምስል ከስፍራው።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍21🤪20❤15🕊1
ሶስት አጫጭር መረጃዎች‼️
📌መከላከያ ሰራዊት ዛሬ መስከረም 21/2019 ዓ.ም ከቀኑ 7:15 ጀምሮ ማይጨው ከተማ መግባቱን ነዋሪዎቹ ገልፀውልናል።
📌መሆኒ ከተማ አቅራቢያ የነበሩ ሁለት የህወሓት ታንኮች ከጥቅም ውጪ ተደርገዋል።
📌በአፋር ኤረብቲ ግንባር የኤርትራ ሰራዊት አባላት ከህወሓት ሀይሎች ጋር በጋራ ሲዋጉ እንደነበር ከተደመሰሱ የሰራዊት አባላት ከተገኘው መታወቂያ ላይ ለማየት ተችሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19👍6🤪5🕊1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ሰበር መረጃ❗❗
ኢትዮጵያ በኤርትራ የሚገኘውን ኢምባሲዋን በመዝጋት በአዲስ አበባ ያሉ የሀገሪቱ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቅቀው እንዲወጡ አስጠነቀቀች‼️
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ኢትዮጵያ፣ በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲዘጋ እና የሀገሪቱ ዲፕሎማቶች ለቅቀው እንዲወጡ ወስናለች።

ሚኒስቴሩ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመችው ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ የጠብ አጫሪነት እና የትንኮሳ ድርጊቶች ምላሽ ለመስጠት በአስመራ፣ ኤርትራ የሚገኘውን ኤምባሲውን ለመዝጋት ወሰኛለሁ ብሏል።

አክሎም፤ በቪየና የተደረሰውን የዲፕሎማሲ ስምምነት በመጣስ ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት ፈጥረዋል የተባሉ አስር ኤርትራውያን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቅቀው እንዲወጡ  ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያላትን ታሪካዊ እና የህዝብ ትስስር እንደምታከብር የገለፀው ሚኒስቴሩ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፌታት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ባገረሸው ጦርነት ላይ የኤርትራ ወታደሮች በግልፅ እየተሳተፉ መሆኑን የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት ለአልጀዚራ መናገራቸው ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍29🤣12❤8👌1🕊1
አዲስ አበባ‼️
ትናንት በአዲስ አበባ የተሰማውን ፍንዳታ ተከትሎ አዩዘሀበሻ ከበርካታ ምንጮች ለማጣራት ሞክሯል።
ትናንት መስከረም 20/2019 ዓ.ም ከለሊቱ 6:20 እና 7:20 ላይ ሶስት ጊዜ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን ምንጮቻችን ለአዩዘሀበሻ አረጋግጠዋል።
ድሮኖቹ ትናንሽ እና አጥፍቶ ጠፊ የሚባሉት አነስተኛ ድሮኖች ናቸው።
አንደኛው መከላከያ ዋናው ቢሮ፣ሁለተኛው ቂርቆስ አራተኛው ሰፈር ሶስተኛው ቤተመንግሥት አከባቢ ነው።
በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፣ በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት አድርሰዋል።
መኪኖች በጣም ተጠጋግተው እንዳይቆሙ ምክረ ሃሳብ መሰጠቱን አሽከርካሪዎች ገልፀውልናል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍31❤21🤔7🤪3😱1🙉1
❗️አሁናዊ የጦርነት መረጃዎችን የምታገኙበት ፈጣን የመረጃ ቻናል ተከፈተ👇
https://t.me/addlist/rmM0bFFNbycwMTM0
👍4❤1
ሰበር ዜና‼️
ኢትዮጵያ የግብፅ ኤምባሲ ዲፕሎማትን ከሀገር እንዲወጡ አዘዘች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ለሚገኘው የግብፅ ኤምባሲ በላከው ይፋዊ ደብዳቤ አንድ የኤምባሲው ዲፕሎማት በአስቸኳይ ከሀገር እንዲወጡ ማዘዙን ደብዳቤው ያሳያል።

በጥቅምት 1 ቀን 2026 (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር) የተፃፈው ይህ ደብዳቤ፣ አህመድ ሞሀረም አህመድ ሱሊማን (Ahmed Moharam Ahmed Soliman) የተባሉ የግብፅ ኤምባሲ የዲፕሎማቲክ ባልደረባ በኢትዮጵያ መንግስት 'ፐርሶና ነን ግራታ' (persona non grata - ተቀባይነት የሌለው ግለሰብ) ተብለው መፈረጃቸውን ያስታውቃል።

በቪየና የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስምምነት መሰረት እርምጃው መወሰዱን የሚገልጸው ሰነዱ፣ ግለሰቡ ይህ ማስታወቂያ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት አርባ ስምንት (48) ሰዓታት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ሚኒስቴሩ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣13👍12❤11🕊3👌1🤪1