አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.3K subscribers
18K photos
443 videos
23 files
3.07K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በአዲስ አበባና አካባቢው ድሮን ማብረር ተከለከለ❗❗
በአዲስ አበባ እና አከባቢው ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ‼️
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የድሮንና ሌሎች ተመሳሳይ በራሪ አካላት አጠቃቀምን በተመለከተ ይፋ ባደረገው ማሳሰቢያ፤ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ በአዲስ አበባ እና አከባቢው ማንኛውንም አይነት ድሮን ለማብረር ፍቃድ አይሰጥም፡፡

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ እንዳመለከተው፤ እንደ ወትሮው ሁሉ በአዲስ አበባና አካባቢው የሚንቀሳቀሱ ድሮኖችንና ሌሎች ተመሳሳይ በራሪ አካላትን የሚቆጣጠር የተቀናጀ የጸረ-ድሮን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል፡፡

የተሰጠውን ማሰሰቢያ በመጣስ የሚነሱ እንዲሁም በየትኛውም አካባቢና ከፍታ የሚበሩ ድሮኖችን በመለየት፣ በመጥለፍ እና ወደ አስፈላጊው ቦታ በማሳረፍ እንዲሁም የአብራሪዎቹን ትክክለኛ መገኛ ቦታ በመለየትና በቁጥጥር ስር በማዋል ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20🤪14👍3🤣3👌1🫡1
መቐለ ከተማ‼️
በመቀሌ ከተማ በዛሬው ዕለት መስከረም 20/2019 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 አካባቢ በፍተሻ ኬላ አካባቢ በሚሊሻ እና በፍተሻ አካላት መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 7 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ አምስት ሰዎች መቁሰላቸውን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በርካታ የህግ ታራሚዎች መለቀቃቸው የታወቀ ሲሆን ወደ ጫካ ያልገቡ 15 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በባጃጅ ከተማዋን ለቀው እንደወጡ ምንጮቻችን ገልፀዋል።

Via :አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣18👍10❤8😢3
ሁለቱ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ ሁለት የአፋር ድርጅቶች፤ የኤርትራ መንግሥት ጦር ሰራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቆ መግባቱን አስታወቁ። ሁለቱ ድርጅቶች በየተናጠል ይፋ ባደረጉት መግለጫ፤ ኤርትራ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች፤ በሃገሪቱ ዉስጥ ያለዉን ግጭትንም በማባባስ ጉዳይ እጅዋ አለበት ሲሉ ከሰዋል።  የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ (EANC በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ) ቃል አቀባይ ዓሊ መሐመድ ዛሬ ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት የኤርትራ ጦር ኢትዮጵያ ግዛት መሥፈሩን ድርጅታቸዉ «ከዉስጥ» ካሉት ከኤርትራ መንግሥት ምንጮቹ ባገኘዉ መረጃ ጭምር ማረጋግጡን ለዶቼ ቬለ «DW » ዛሬ ተናግረዋል።ኢትዮጵያ የሚገኙት የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ኢብራሒም ሐሩን በበኩላቸዉ በተለይ በአፋር ክልል በሚደረገዉ ዉጊያ የኤርትራ ጦር መካፈሉን ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍13❤11🤪5🤔1🕊1🙈1
የድርድር ጥያቄ‼️
ህወሓት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከመንግሥት ጋር እንዲያደራድሩት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ተከታታይ ጥያቄ እያቀረበ መሆኑን በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሱሌይማን ደደፎ ገልፀዋል።
ህወሓት የድርድር ጥያቄ የሚያቀርበው የወታደራዊ ኃይል የበላይነት ሲወሰድበት በመሆኑ መንግሥት ሌላ ስህተት እንዳይሰራ በሚል በርካቶች ሀሳባቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪55❤8🥱7👍3🕊3🤷‍♂2🤡2🙏1💯1🤣1😡1
የኡጋንዳ ጦር ኃይል ዋና አዛዥ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም
ለተቀሰቀሰው ጦርነት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ ጥሪ አቀረቡ

* ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል

የኡጋንዳ ጦር ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ በኤክስ (X) ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በተቀሰቀሰው ግጭት ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ግጭቱ እንዳይባባስና በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

ጄኔራሉ አያይዘውም በፕሪቶሪያ የተፈጸመው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተከብሮ እንዲተገበር አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት በሁሉም ወገኖች ሊከበርና ሊጠበቅ እንደሚገባም በመልእክታቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣20❤9👍8🕊2🙏1👌1💔1🫡1
እረብቲ‼️
እራሱን የትግራይ ሰላም ሰራዊ(TPF) ብሎ የሚጠራውና ከመከላከያ ጋር አብሮ እየተዋጋ የሚገኘው ይህ ተዋጊ ሀይል በአፋር ግንባር እረብቲን ተቆጣጥሮ ወደ አብ ዓላ እየተጠጋ መሆኑን አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍20❤9🕊2🤪1
አዲስ ተላላፊ ቫይረስ በቻይና ተገኘ

​በቻይና የሚገኙ ተመራማሪዎች በኡካን በንክሻ አማካኝነት ወደ ሰው የሚተላለፍ ALTNV የተሰኘ አዲስ ቫይረስ ማግኘታቸውን አስታወቁ።

ቫይረሱ በቤጂንግ የፓቶጀንስ እና ባዮሴፍቲ ላቦራቶሪ ተመራማሪዎች የተገኘ ሲሆን፣ ውጤቱም በኒው ኢንግላንድ ሜዲካል ጆርናል ላይ ታትሟል።

​በጥናቱ ከተካተቱት 3,163 ታካሚዎች መካከል 10.4 በመቶ የሚሆኑት በቫይረሱ የተያዙ ሆነው ተገኝተዋል።

ዋነኛ ምልክቶቹም ከፍተኛ ድካም (84%)፣ የሆድ እና የምግብ ፍጨት ችግር (80%)፣ የደም ፕሌትሌት መቀነስ እና የጉበት ኢንፌክሽን ናቸው።

ALTNV ብቻ የያዛቸው ታካሚዎች ሙሉ በሙሉ ያገገሙ ቢሆንም፣ ከሌሎች ተመሳሳይ ቫይረሶች ጋር ደርበው የተያዙ ሰዎች ግን ለኩላሊት መድከም  እና ለሞት (18.4%) ተዳርገዋል።

​ተመራማሪዎቹ በ15 የቻይና ግዛቶች በተሰበሰቡ ኡካኖች ላይ ቫይረሱን ያገኙ ሲሆን፣ በሽታው ከሌሎች ጋር ስለሚመሳሰል ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ እንዲደረግ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15😢5👍3🥱2😱1🤣1👀1
አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን  መሥራች ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ አቶ አረጋ ከበደን የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት  አድርጎ በድጋሜ ሾሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣23❤9👍6🤩2🤡1😈1🤪1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የአማራ ክልል ምክር ቤት የቢሮ ኃላፊዎች ሙሉ ሹመት❗❗❗
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት በርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የቀረቡለትን ሹመቶች አጸደቀ። በዚህም መሠረት፡-

1. የሻለም ገዛኸኝ ዳምጠው (ዶ/ር) - ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ፣
2. ጥላሁን ፈንታው ተሾመ - ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ፣
3. መስፍን አበጀ ተፈራ (ዶ/ር) - ግብርና ቢሮ ኃላፊ፣
4. ጥላሁን ወርቅነህ ተክሌ - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣
5. ሞላ መልካሙ ከበደ (ዶ/ር) - ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
6. ዳኝነት ፈንታው መኮንን (ዶ/ር) - ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ፣
7. አታላይ ጥላሁን ጫኔ - ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ፣
8. ዶ/ር ጋሻው ሙጬ አለምነው - እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
9. እሸቱ የሱፍ አየለ (ዶ/ር) - ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣
10. አባይ መንግስቴ ሰላምሰው - ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፣
11. ባንቺአምላክ ገብረማርያም በላይ - ሲቪል ሰርቪስ እና ሰው ሃብት ቢሮ ኃላፊ፣
12. እንድሪስ አብዱ አሕመድ - ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ፣
13. አብዱልከሪም መንግሥቱ ይማም - ጤና ቢሮ ኃላፊ፣
14. መልካሙ ጸጋዬ ገላው - ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ፣
15. ኢብራሂም መሀመድ እንድሪስ (ዶ/ር) - ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
16. ሲሳይ ዳምጤ አበባይ - መሬት ቢሮ ኃላፊ፣
17. ጋሻው አወቀ ትኩዬ (ዶ/ር) - መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ፣
18. ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) - ፕላንና ልማት ቢሮ፣
19. ተስፋሁን ዓለምነው ይስማው - የአካበቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኃላፊ፣
20. ብርሃኑ ጎሹ አዘረፍ - ፍትህ ቢሮ ኃላፊ፣
21. ሃይሌ አበበ ብዙአየሁ - የማዕድን ቢሮ ኃላፊ፣
22. ስቡ ገበያው ታረቀ (ዶ/ር) - ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ፣
23. ብርቱካን ሲሳይ እንየው - ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሸመዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤23👍7🥱5😡4
አብዓላ‼️
ከመቀሌ በ50 ኪሎሜትር እርቀት ላይ የምትገኘውና በአፋርና ትግራይ አዋሳኝ ላይ የምትገኘው አብዓላ ከተማ በአፋር የፀጥታ ሀይሎች፣በትግራይ ሰላም ሰራዊት እና በመከላከያ ሰራዊት ከቀኑ 7:15 ቁጥጥር ስር መግባቷን በስፍራው የሚገኙ የአዩዘሀበሻ ምንጮች አረጋገጡ።
ምስል ከስፍራው።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍21🤪20❤15🕊1
ሶስት አጫጭር መረጃዎች‼️
📌መከላከያ ሰራዊት ዛሬ መስከረም 21/2019 ዓ.ም ከቀኑ 7:15 ጀምሮ ማይጨው ከተማ መግባቱን ነዋሪዎቹ ገልፀውልናል።
📌መሆኒ ከተማ አቅራቢያ የነበሩ ሁለት የህወሓት ታንኮች ከጥቅም ውጪ ተደርገዋል።
📌በአፋር ኤረብቲ ግንባር የኤርትራ ሰራዊት አባላት ከህወሓት ሀይሎች ጋር በጋራ ሲዋጉ እንደነበር ከተደመሰሱ የሰራዊት አባላት ከተገኘው መታወቂያ ላይ ለማየት ተችሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19👍6🤪5🕊1