አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.3K subscribers
18K photos
443 videos
23 files
3.07K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተቀማጭ የውጭ ምንዛሬ ክምችት መጠን 20 በመቶ ማደጉን ገለጸ

​የብር የመግዛት አቅም በገበያ እንዲወሰን ከተደረገ በኋላ የኢትዮጵያ ተቀማጭ የውጭ ምንዛሬ ክምችት መጠን 20 በመቶ ማደጉን እና ማዕከላዊ ባንኩ በጨረታ ለባንኮች ያቀረበው የውጭ ምንዛሬ 2.3 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በፋይናንስ ፎረም ላይ ገለጹ።

​የውጭ ምንዛሬ እና የትይዩ ገበያ ሁኔታ፦ የውጭ ምንዛሬ በገበያ ከተወሰነ በኋላ የመደበኛ እና የትይዩ (ጥቁር) ገበያ የዋጋ ልዩነት ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረበት 15.3 በመቶ ወደ 11–12 በመቶ ዝቅ ቢልም፣ ወደ ነጠላ አሃዝ ባለመውረዱ የተቀመጠው ግብ ገና እንዳልተሳካ ተጠቅሷል።

​የዋጋ ግሽበት እና የፖሊሲ ውጤት፦ የዋጋ ግሽበትን ወደ አንድ ዲጂት ለማውረድ የተያዘው ግብ አለመሳካቱ በውጭ ተጽዕኖ እንጂ በሀገር ውስጥ ፖሊሲ ውድቀት እንዳልሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማዕቀፍ ውጪ የሚካሄዱ ኢንቨስትመንቶች መንገድ እንዳይጀምሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

​የባንኮች ውህደት (Merger & Acquisition) ጥሪ፦ የባንኮች ተቀማጭ ገንዘብ ቢያድግም ክምችቱ ወጥ አለመሆኑን የጠቆሙት ገዢው፤ ጠንካራ የፋይናንስ ተቋማትን ለመፍጠር ትንንሽ ባንኮች በመዋሃድ እና በመሰብሰብ (Merger and Acquisition) መጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

​የህዝብ ኑሮ እና የኢኮኖሚ ሪፎርም፦ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ውጤት ከቁጥር ባለፈ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የእለት ተእለት ኑሮ እና ኪስ ላይ የሚታይ ለውጥ ማምጣት እንዳለበት ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤10👍4
በጋሞ ዞን ጠለፋና የመድፈር ሙከራ ፈጽሞ ድርጊቱን በቪዲዮ ቀርጾ በቲክቶክ ያሰራጨ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ጠለፋና የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ አስታወቀ።

ተከሳሹ መልካሙ ዳዊት የተባለ ሲሆን  የግል ተበዳይን  በመጥለፋ  ተበዳይዋን ወደ ጫካ በመውሰድ አስገድዶ ለመድፈር ሙከራ ማድረጉን ፖሊስ አስታውቋል።በተጨማሪም ድርጊቱን በቪዲዮ በመቅረፅ በቲክቶክ ላይ ማሰራጨቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ገፅታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተከሳሹን ከሠላምበር ከተማ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራውን አጠናቆ መዝገቡን ለአቃቤ ሕግ ማስረከቡን ፖሊስ አስታውቋል።አቃቤ ሕግም በተከሳሹ ላይ በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 587(1) እና 620(2) መሠረት ክስ በመመስረት የሰው፣ የሰነድና የቪዲዮ ማስረጃዎችን ለምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀርባል።
 
ተከሳሹ የቀረቡትን ማስረጃዎች ማስተባበል ባለመቻሉ፣ ፍርድ ቤቱ በሁለቱም ክሶች ጥፋተኛ መሆኑን በመወሰን 22 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላልፉን  ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍18❤12
ሰመራ ኤርፖርት‼️
በትናንትናው ዕለት በአፋር ክልል ዋና ከተማ ሰመራ አየር ማረፊያ (ኤርፖርት) ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረ የሚገልፁ መረጃዎች በስፋት ሲሰራጩ ቆይተዋል።

ሚድያችን በአካባቢው ካሉ ምንጮቹ እንዳረጋገጠው በሰመራ አየር ማረፊያ ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጥቃት የለም።

ይሁንና የድሮን ምት እንደሆነ በተገመተ ከባድ ጥቃት ምክንያት ከኤርፖርቱ በቅርብ ርቀት በሚገኘው የክልሉ መንግስት መቀመጫ ቤተ መንግስት ግቢ ወስጥ ዛሬ ምሽት 1:45 ገደማ ጥቃት መፈፀሙን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

ይህ ለክብር እንግዶች (VIP) እንዲሆን ታስቦ እየተሰራ ያለ ህንፃ ተመትቶ በእሳት መያያዙ የታወቀ ሲሆን ስለደረሰው ጉዳት እስካሁን አለመታወቁን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

"በቦታው ከፍተኛ የፀጥታ ሀይል ተሰማርቶ የክልል ፕሬዚዳንቱን የመጠበቅ ስራ እየተሰራ ነው፣ ወደ ቦታ ሰው እንዳይደርስ እየተከለከለ መሆኑንም አይተናል" በማለት አንድ ምንጫችን ማምሻውን ለመሰረተ ሚዲያ ተናግረዋል።
ኤርፖርቱ በመደበኛ ስራው ላይ ነው፣ በረራም አልተቋረጠም።
በዚህ መረጃ ዙርያ እስካሁን ከአፋር ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መረጃ የለም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤26👍4🕊3🤔1👌1👀1🤪1
አሜሪካን ያስደነገጠው የጋና መንግስት ውሳኔ‼️
የጋና መንግሥት ከወደ ዋሽንግተን የቀረበለትን የ109 ሚሊዮን ዶላር የጤና ድጋፍ ስምምነት "ብሔራዊ ክብርንና ሉዓላዊነትን ይነካል" ሲል ውድቅ አደረገ።
ኢትዮጵያ ይህንን ስምምነት መፈረሟ ይታወሳል።
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና ከአሜሪካ የጤና ድጋፍ ጀርባ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች "የሚያዋርዱ እና የአገሪቱን ሉዓላዊነት የሚጋፉ ናቸው" ብላለች።

በዚህም የቀረበላትን የ5 ዓመት ዕቅድ እንደማትቀበለው አስታውቃለች።

የጋናው ፕሬዚዳንት ጆን ማሃማ ካቢኔያቸው ስምምነቱን ውድቅ ማድረጉን ሲገልጹ ለአሜሪካ እጅ ላለመስጠት ምክንያት የሆኑትን ዋና ዋና ነጥቦች ይፋ አድርገዋል።

ስምምነቱ ጋና አጠቃላይ የዜጎቿን የሕክምና መረጃዎች ለዋሽንግተን እንድታስረክብ የሚያስገድድ አንቀጽ ይዟል።

አሜሪካ በዚሁ ፕሮግራም ሥር ወደ ጋና የምታስገባቸውን መድኃኒቶችና የሕክምና ቁሳቁሶች የጋና ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዳይመረምርና እንዳይፈትሽ የሚከለክል አ አሰራር ተካቶበታል ብለዋል።

አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ ብትገልጽም ጋና ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያ የራሷን በጀት አውጥታ እንድትመድብ መጠየቋ ቅሬታን ፈጥሯል።

ፕሬዚዳንት ማሃማ ሁኔታውን "አዋራጅ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን ጋና ይህ ድጋፍ ቢቀርባትም በራሷ አቅም መቆም እንደምትችል ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው በአክራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ ውዥንብር መፈጠሩን ጠቅሷል።

ኤምባሲው የቀረበው ጥያቄ የሕመምተኞችን ግላዊ ማንነት የሚያሳይ መረጃ ሳይሆን የፕሮግራሙን ውጤታማነት ለመለካት የሚያግዝ አጠቃላይ የጤና መረጃ ብቻ መሆኑን አስረድቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤51👍13👀5🫡4
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በድጋሜ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሰየሙ።

ላለፉት አመታት  አዲስ አበባን በከንቲባነት ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በድጋሜ ከንቲባ ሆነው በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ተሰይመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣44👍26❤8🙉6😢3🤷‍♂1👌1🤡1🤪1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ሹመት‼️
የደሴ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ፤  ጃንጥራር አባይን በመተካት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።
የአዲስ አበባ ካቢኔ አባላት

👉 አቶ ግርማ ሰይፉ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የከተማውን የካቢኔ አባላት ሹመት አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፦

1. አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ጥላሁን ከበደ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ ሃፍታይ ገ/እግዚአብሔር - በም/ ከንቲባ ማዕረግ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
5. ዶ/ር አህመዲን መሃመድ - የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ
6. ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ - የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ
7. ኢንጂነር አያልነሽ ኃብተማሪያም - የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ
8. ወ/ሪት ፂዮን ደረጀ (የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል) - የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ
9. ኢንጂነር ህይወት ፀጋዬ - የግንባታ ቁጥጥርና ፈቃድ ቢሮ ኃላፊ
10. ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ - የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ
11. ወ/ሮ ዚያዳ ካሚል - የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
12. አቶ ግርማ ሰይፉ - የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
13. አቶ ቢኒያም ምክሩ - ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
14. አቶ ሙሉቀን ታሪኩ - የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
15. ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ - የንግድ ቢሮ ኃላፊ
16. ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ - የጤና ቢሮ ኃላፊ
17. ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
18. አቶ አወሌ መሃመድ ኡመር - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
19. ዶ/ር ተፈራ ሞላ - የትራንስፖርት ቢሮ
20 ኢንጂነር አይሻ መሃመድ - የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
21. ኢንጂነር ሔለን ገመዳ - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ
22. ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ - የህፃናት ማህበራዊ ጉዳይና ሴቶች ቢሮ
23. አቶ ተስፋዬ ደጀኔ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
24. አቶ አሰግደው ወልደጊዮርጊስ - የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
25. አቶ መላኩ ታምሩ - የመሬት ልማት ቢሮ ኃላፊ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤25🤪7👍3🤔1🤣1
ጨርጨር‼️
መከላከያ ሠራዊት #ጨርጨር፣ #ሓደ_አልጋና #ወራባየን መቆጣጠሩ ታወቀ።
መከላከያ ሠራዊት #ጨርጨር፣ ሓደ አልጋ እና ወራባየን በቁጥጥር ሥር በማዋል በባቡር መስመሩ ወደ #ፋጫጋማ መድረሱ ተገለጸ።
የጨርጨር መስመር በተለይ የባቡር መስመሩን በመጠቀም ህወሓት ከባድ መሳሪያዎችን ጨምሮ ለማንቀሳቀስ የሚጠቀምበት ዋነኛ መስመር ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤23👍10🤪6🥱2✍1🥰1🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኤርትራ ሰራዊት ውጊያ ከፍቶብናል-አወል አርባ‼️
በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ የኤርትራ ሰራዊት ከህወሃት ሀይል ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ጥሶ ገብቶ በከባድ መሳሪያ ጭምር ጦርነት ከፍቶ ይገኛል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕስ መስተዳደር ሀጂ አወል አርባ ከክልሉ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል። በዚህ የተነሳ በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣15👍11❤10🤪6😢5😎4🎉2🕊1
በአዲስ አበባና አካባቢው ድሮን ማብረር ተከለከለ❗❗
በአዲስ አበባ እና አከባቢው ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ‼️
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የድሮንና ሌሎች ተመሳሳይ በራሪ አካላት አጠቃቀምን በተመለከተ ይፋ ባደረገው ማሳሰቢያ፤ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ በአዲስ አበባ እና አከባቢው ማንኛውንም አይነት ድሮን ለማብረር ፍቃድ አይሰጥም፡፡

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ እንዳመለከተው፤ እንደ ወትሮው ሁሉ በአዲስ አበባና አካባቢው የሚንቀሳቀሱ ድሮኖችንና ሌሎች ተመሳሳይ በራሪ አካላትን የሚቆጣጠር የተቀናጀ የጸረ-ድሮን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል፡፡

የተሰጠውን ማሰሰቢያ በመጣስ የሚነሱ እንዲሁም በየትኛውም አካባቢና ከፍታ የሚበሩ ድሮኖችን በመለየት፣ በመጥለፍ እና ወደ አስፈላጊው ቦታ በማሳረፍ እንዲሁም የአብራሪዎቹን ትክክለኛ መገኛ ቦታ በመለየትና በቁጥጥር ስር በማዋል ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20🤪14👍3🤣3👌1🫡1
መቐለ ከተማ‼️
በመቀሌ ከተማ በዛሬው ዕለት መስከረም 20/2019 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 አካባቢ በፍተሻ ኬላ አካባቢ በሚሊሻ እና በፍተሻ አካላት መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 7 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ አምስት ሰዎች መቁሰላቸውን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በርካታ የህግ ታራሚዎች መለቀቃቸው የታወቀ ሲሆን ወደ ጫካ ያልገቡ 15 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በባጃጅ ከተማዋን ለቀው እንደወጡ ምንጮቻችን ገልፀዋል።

Via :አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣18👍10❤8😢3
ሁለቱ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ ሁለት የአፋር ድርጅቶች፤ የኤርትራ መንግሥት ጦር ሰራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቆ መግባቱን አስታወቁ። ሁለቱ ድርጅቶች በየተናጠል ይፋ ባደረጉት መግለጫ፤ ኤርትራ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች፤ በሃገሪቱ ዉስጥ ያለዉን ግጭትንም በማባባስ ጉዳይ እጅዋ አለበት ሲሉ ከሰዋል።  የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ (EANC በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ) ቃል አቀባይ ዓሊ መሐመድ ዛሬ ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት የኤርትራ ጦር ኢትዮጵያ ግዛት መሥፈሩን ድርጅታቸዉ «ከዉስጥ» ካሉት ከኤርትራ መንግሥት ምንጮቹ ባገኘዉ መረጃ ጭምር ማረጋግጡን ለዶቼ ቬለ «DW » ዛሬ ተናግረዋል።ኢትዮጵያ የሚገኙት የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ኢብራሒም ሐሩን በበኩላቸዉ በተለይ በአፋር ክልል በሚደረገዉ ዉጊያ የኤርትራ ጦር መካፈሉን ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍13❤11🤪5🤔1🕊1🙈1
የድርድር ጥያቄ‼️
ህወሓት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከመንግሥት ጋር እንዲያደራድሩት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ተከታታይ ጥያቄ እያቀረበ መሆኑን በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሱሌይማን ደደፎ ገልፀዋል።
ህወሓት የድርድር ጥያቄ የሚያቀርበው የወታደራዊ ኃይል የበላይነት ሲወሰድበት በመሆኑ መንግሥት ሌላ ስህተት እንዳይሰራ በሚል በርካቶች ሀሳባቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪55❤8🥱7👍3🕊3🤷‍♂2🤡2🙏1💯1🤣1😡1
የኡጋንዳ ጦር ኃይል ዋና አዛዥ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም
ለተቀሰቀሰው ጦርነት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ ጥሪ አቀረቡ

* ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል

የኡጋንዳ ጦር ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ በኤክስ (X) ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በተቀሰቀሰው ግጭት ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ግጭቱ እንዳይባባስና በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

ጄኔራሉ አያይዘውም በፕሪቶሪያ የተፈጸመው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተከብሮ እንዲተገበር አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት በሁሉም ወገኖች ሊከበርና ሊጠበቅ እንደሚገባም በመልእክታቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣20❤9👍8🕊2🙏1👌1💔1🫡1
እረብቲ‼️
እራሱን የትግራይ ሰላም ሰራዊ(TPF) ብሎ የሚጠራውና ከመከላከያ ጋር አብሮ እየተዋጋ የሚገኘው ይህ ተዋጊ ሀይል በአፋር ግንባር እረብቲን ተቆጣጥሮ ወደ አብ ዓላ እየተጠጋ መሆኑን አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍20❤9🕊2🤪1
አዲስ ተላላፊ ቫይረስ በቻይና ተገኘ

​በቻይና የሚገኙ ተመራማሪዎች በኡካን በንክሻ አማካኝነት ወደ ሰው የሚተላለፍ ALTNV የተሰኘ አዲስ ቫይረስ ማግኘታቸውን አስታወቁ።

ቫይረሱ በቤጂንግ የፓቶጀንስ እና ባዮሴፍቲ ላቦራቶሪ ተመራማሪዎች የተገኘ ሲሆን፣ ውጤቱም በኒው ኢንግላንድ ሜዲካል ጆርናል ላይ ታትሟል።

​በጥናቱ ከተካተቱት 3,163 ታካሚዎች መካከል 10.4 በመቶ የሚሆኑት በቫይረሱ የተያዙ ሆነው ተገኝተዋል።

ዋነኛ ምልክቶቹም ከፍተኛ ድካም (84%)፣ የሆድ እና የምግብ ፍጨት ችግር (80%)፣ የደም ፕሌትሌት መቀነስ እና የጉበት ኢንፌክሽን ናቸው።

ALTNV ብቻ የያዛቸው ታካሚዎች ሙሉ በሙሉ ያገገሙ ቢሆንም፣ ከሌሎች ተመሳሳይ ቫይረሶች ጋር ደርበው የተያዙ ሰዎች ግን ለኩላሊት መድከም  እና ለሞት (18.4%) ተዳርገዋል።

​ተመራማሪዎቹ በ15 የቻይና ግዛቶች በተሰበሰቡ ኡካኖች ላይ ቫይረሱን ያገኙ ሲሆን፣ በሽታው ከሌሎች ጋር ስለሚመሳሰል ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ እንዲደረግ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15😢5👍3🥱2😱1🤣1👀1
አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን  መሥራች ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ አቶ አረጋ ከበደን የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት  አድርጎ በድጋሜ ሾሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣23❤9👍6🤩2🤡1😈1🤪1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የአማራ ክልል ምክር ቤት የቢሮ ኃላፊዎች ሙሉ ሹመት❗❗❗
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት በርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የቀረቡለትን ሹመቶች አጸደቀ። በዚህም መሠረት፡-

1. የሻለም ገዛኸኝ ዳምጠው (ዶ/ር) - ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ፣
2. ጥላሁን ፈንታው ተሾመ - ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ፣
3. መስፍን አበጀ ተፈራ (ዶ/ር) - ግብርና ቢሮ ኃላፊ፣
4. ጥላሁን ወርቅነህ ተክሌ - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣
5. ሞላ መልካሙ ከበደ (ዶ/ር) - ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
6. ዳኝነት ፈንታው መኮንን (ዶ/ር) - ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ፣
7. አታላይ ጥላሁን ጫኔ - ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ፣
8. ዶ/ር ጋሻው ሙጬ አለምነው - እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
9. እሸቱ የሱፍ አየለ (ዶ/ር) - ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣
10. አባይ መንግስቴ ሰላምሰው - ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፣
11. ባንቺአምላክ ገብረማርያም በላይ - ሲቪል ሰርቪስ እና ሰው ሃብት ቢሮ ኃላፊ፣
12. እንድሪስ አብዱ አሕመድ - ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ፣
13. አብዱልከሪም መንግሥቱ ይማም - ጤና ቢሮ ኃላፊ፣
14. መልካሙ ጸጋዬ ገላው - ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ፣
15. ኢብራሂም መሀመድ እንድሪስ (ዶ/ር) - ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
16. ሲሳይ ዳምጤ አበባይ - መሬት ቢሮ ኃላፊ፣
17. ጋሻው አወቀ ትኩዬ (ዶ/ር) - መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ፣
18. ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) - ፕላንና ልማት ቢሮ፣
19. ተስፋሁን ዓለምነው ይስማው - የአካበቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኃላፊ፣
20. ብርሃኑ ጎሹ አዘረፍ - ፍትህ ቢሮ ኃላፊ፣
21. ሃይሌ አበበ ብዙአየሁ - የማዕድን ቢሮ ኃላፊ፣
22. ስቡ ገበያው ታረቀ (ዶ/ር) - ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ፣
23. ብርቱካን ሲሳይ እንየው - ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሸመዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤23👍7🥱5😡4
አብዓላ‼️
ከመቀሌ በ50 ኪሎሜትር እርቀት ላይ የምትገኘውና በአፋርና ትግራይ አዋሳኝ ላይ የምትገኘው አብዓላ ከተማ በአፋር የፀጥታ ሀይሎች፣በትግራይ ሰላም ሰራዊት እና በመከላከያ ሰራዊት ከቀኑ 7:15 ቁጥጥር ስር መግባቷን በስፍራው የሚገኙ የአዩዘሀበሻ ምንጮች አረጋገጡ።
ምስል ከስፍራው።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍21🤪20❤15🕊1