ሞት አሻፈረኝ ያለው ታንዛኒያዊ !
በአፍሪማክስ ዘገባ መሠረት ስድስት ጊዜ ሞቶ ስድስት ጊዜ ሕይወት የዘራው ታንዛኒያዊው እስማኤል አዚዚ በማህበረሰቡ መገለል እንደደረሰበት ተናግሯል፡፡
አዚዚ እነዚህ ስድስት አደጋዎች የደረሱበት በሥራ ላይ፣ በጽኑ ወባ፣ በመኪና አደጋ፣ በእባብ ንክሻ፣ ጉድጓድ ውስጥ በመውደቅ እና በቤት ቃጠሎ ሳቢያ መሆኑን ይናገራል። ከእነዚህ ውስጥ በአንዱ አደጋ ሞቷል ተብሎ አስክሬን ማቆያ (ሬሳ ቤት) ውስጥ እንደነቃም ገልጿል።
ይሁን እንጂ በተደጋጋሚ ከሞት መነሳቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ፍርሃት ፈጥሮባቸው ነበር፤ አንዳንዶች መናፍስት ወይም አስማተኛ ነው ብለው በማሰባቸውም ተገልሏል። ይህ አስገራሚ ታሪክ በአብዛኛው በእስማኤል አዚዚ እና በአካባቢው ሰዎች ንግግር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ስድስቱንም የሞት ማረጋገጫዎች የሚያሳዩ ይፋዊ የሕክምና መዝገቦች ግን እስካሁን አልተገኙም።
@Addis_Reporter

❤28👍6🤯3👀3
ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ መስከረም 12 እስከ አርብ መስከረም 15፤ 2019 ድረስ ባሉት ቀናት፤ የኮረም እና አላማጣ ሆስፒታሎች ከ420 በላይ የጦርነት ቆስለኞችን መቀበላቸውን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (MSF) አስታወቀ።
በሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ሽረ ከተማ በሚገኘው ስሁል ሆስፒታል፤ ባለፈው አርብ ብቻ ከ300 በላይ በጦርነት የቆሰሉ ግለሰቦች መድረሳቸውንም ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ገልጿል።
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ዛሬ ሰኞ መስከረም 18፤ 2019 ባወጣው መግለጫ፤ አሁን ባለው “ወቅታዊ ሁኔታ” ምክንያት የአላማጣ ሆስፒታል እንቅስቃሴዎች መቋረጣቸውን ይፋ አድርጓል።
በዚሁ አካባቢ በጸጥታ ምክንያት የማህበረሰብ አገልግሎትም መቋረጡን ድርጅቱ አመልክቷል።
የግብረ ሰናይ ድርጅቱ “በጦርነት የቆሰሉ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸውን ተመልክቼባቸዋለሁ” ባላቸው ሆስፒታሎች፤ ሰራተኞቹን ተጨማሪ ድጋፍ እንዲሰጡ ማሰማራቱን አስገንዝቧል።
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በዛሬው መግለጫው፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉት ግጭቶች ምክንያት “ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል” ላላቸው ታካሚዎች የሚያስፈልጉ ድጋፎችን ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ እያቀረበ መሆኑንም ጠቁሟል።

❤11👍5🤯2🕊1
አበርገለ‼️
መከላከያ ሰራዊት አበርገሌን ለመቆጣጠር መቃረቡን በአከባቢው የሚገኙ ምንጮች ገለፁ። በአሁኑ ስዓት 03ቀበሌ ሳቃ በቅርብ ርቀት የምትገኘውን ቀበሌ ተቆጣጥሮ ወደ ዋና ከተማዋ ንየረ-አቑ ከተማ እያመራ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
ውጊያው ወደትግራይ ክልል እየገባ ይገኛል።
Via : አዩዘሀበሻ

👍35🤪12👌4❤3🎉1🙏1🕊1
#በኢትዮጵያ ግጭት በመስፋፋቱ ስድስት #የአሜሪካ #ሴናተሮች ማርኮ ሩቢዮ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጠየቁ‼️
#በትግራይ እንዲሁም በአጎራባች #አማራ እና #አፋር ክልሎች ግጭት ዳግም በመስፋፋቱ፣ ስድስት የአሜሪካ ሴናተሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና መስሪያ ቤታቸው ከኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት፣ ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና ተባባሪ ታጣቂ ቡድኖች ጋር በመነጋገር አዲስ ያንሰራራውን ግጭት በአስቸኳይ እንዲያስቆሙና ወገኖችን ወደ ድርድር እንዲመልሱ ጥሪ አቀረቡ።
የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ትናንት ሰኞ መስከረም 18/2019 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት፤ ሴናተር ጂን ሻሂን፣ ሴናተር ኮሪ ቡከር፣ ሴናተር ክሪስ ኩንስ፣ ሴናተር ጄፍ ሜርክሊ፣ ሴናተር ክሪስ ቫን ሆለን እና ሴናተር ቲም ካይን እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታ የሁለት ዓመቱን የትግራይ ጦርነት ያቆመውን የ2015ቱን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ገልጸዋል።

❤11👍3🤝2🤪2
ማይጨው‼️
በማይጨው ከባድ የተባለ የመድፍ ድብደባ እየተደረገ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
የመድፍ ድብደባው ትናንት የጀመረ ሲሆን ዛሬም ቀጥሏል ብለዋል። ትናንት ብቻ 11 ጊዜ የመድፍ ድብደባ ተፈፅሟል ያሉ ሲሆን ጥቃቱ የደረሰው በአደባባይ አካባቢ፣ ታደለ ሆቴል ጀርባ እንዲሁም በራያ ዩኒቨርሲቲ በር አካባቢ ሲሆን፣ ቁጥራቸው ያልታወቀ ንፁሃን ሲቪሎች መጎዳታቸው የከተማዋ ነዋሪዎች አድርሰውናል።
በራያ መሆኒ መስመር ውጊያው ቀጥሏል።

❤18👍8😢5🕊3
አላማጣ‼️
የህወሓት ወታደራዊ ማዕከል የነበረችው አላማጣ ከተማ ከሰሞኑ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር መግባቷን ተከትሎ
ከትግራይ ሰላም ሰራዊት እና ከፌዴራል ፖሊስ ውጭ ያሉ ሁሉም ታጣቂዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
የከተማዋን ሰላምና ደህንነትን የማስጠበቅ ኃላፊነት በዋናነት ለትግራይ ሰላም ሰራዊት እና ለፌደራል ፖሊስ መሰጠቱ ታውቋል።

❤18👍14🤪3😢1
የክልሎች መንግሥት ምስረታ‼️
ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር መጨረሻ የተደረገውን ሰባተኛውን ዙር ምርጫ ተከትሎ፤ የክልል ምክር ቤቶች መስራች ጉባኤያቸውን ማካሄድ ጀምረዋል። በዚህ ረገድ ቀዳሚ የሆነው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) ነው። ትላንት ሰኞ መስከረም 18 በአዳማ ከተማ ጉባኤውን ያደረገው ምክር ቤቱ፤ የክልሉን ፕሬዝዳንት እና ምክትሎቻቸውን በመምረጥ የአዲስ መንግስት ምስረታውን አከናውኗል።
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ነገ ረቡዕ መስከረም 20 በሚያደርገው መስራች ጉባኤ፤ በተመሳሳይ መልኩ የክልሉን አዲስ መንግስት ይመሰርታል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ምስረታ እና የመክፈቻ ጉባኤ የሚካሄደውም በዚሁ ቀን ነው።
ከነገ በስቲያ ሐሙስ ጉባኤያቸውን የሚያደርጉት የሲዳማ እና የአማራ ክልል ምክር ቤቶች፤ በዚያኑ ዕለት አዲስ መንግስት መስርተው ርዕሰ መስተዳደሮቻቸውን ይመርጣሉ። የሁለቱ ክልሎች ምክር ቤቶች ጉባኤዎች የሚካሄዱት በሀዋሳ እና ባህር ዳር ከተሞች ነው።
በስድስተኛው የምርጫ ዘመን በክልልነት የተመሰረቱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ምክር ቤቶች፤ ለሁለት ቀናት የሚቆይ መስራች ጉባኤያቸውን የሚያካሄዱት በተመሳሳይ ቀን ነው። በወልቂጤ፣ አርባ ምንጭ እና ታርጫ ከተሞች የሚካሄዱት የምክር ቤቶቹ ጉባኤዎች፤ ከሐሙስ መስከረም 21 እስከ አርብ መስከረም 22 ድረስ ይቆያሉ።
መጪውን አርብ ለጉባኤ ማካሄጂያነት የመረጡት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የሀረሪ ክልሎች፤ በዚሁ ቀን አዲሱ መንግስታቸውን በአሶሳ እና በሐረር ከተሞች ይመሰርታሉ። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መስራች ጉባኤ የሚካሄደውም አርብ መስከረም 22 ነው።
በተመሳሳይ ቀን መስራች ጉባኤውን የሚጀምረው የአፋር ክልል ምክር ቤት፤ በሰመራ ከተማ የሚያካሄደው ስብሰባ እስከ ቅዳሜ መስከረም 23 ድረስ እንደሚቆይ አስታውቋል። ምርጫ ባልተደረገበት ትግራይ ክልል፤ የምክር ቤት መስራች ጉባኤ አይካሄድም።

❤18👍3🤣2🤪1
ባሕር ዳር ❤️
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሴኔጋል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፏል።
በህዝብና ደጋፊው ፊት ከዓመታት በኋላ ጨዋታውን ያደረገው ብሔራዊ ቡድናችን ጥሩ እና አበረታች እንቅስቃሴ ቢያደርም የተገኙ እድሎችን ወደ ውጤት መቀየር ሳይችል ቀርቷል።
የባሕር ዳር ከተማ ህዝብ ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ከጨዋታው መጀመር አንስቶ ያሳየው ድጋፍ የሚደንቅ ነበር።
የባሕር ዳር ስታዲየም ጥራትም በበርካቶች አድናቆት አግኝቷል።

❤9👍7🙊5🤣3🥰1🤔1🌚1
24 የመማሪያ ክፍል መስኮቶችን የሰረቁ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ
በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ የቡሬ አቦ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍሎች 24 መስኮቶችን በመስረቅ የተከሰሱ ሦስት ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በእስራት መቀጣታቸው ተገልጿል።
የቡሬ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ያየህ አድገህ እንደገለፁት የትምህርት ቤቱ አመራሮችና የአካባቢው ሕብረተሰብ ለፖሊስ ባቀረቡት ጥቆማ መሠረት ፖሊስ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ ችሏል።
ተከሳሾቹ የሰረቁትን መስኮቶች በባጃጅ ጭነው ወደ አዊ ዞን ቲሊሊ ከተማ በመውሰድ ለቁራሌ ለመሸጥ ሲሞክሩ መሆኑን ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ታኅሣሥ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማድረጉን ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።
ፖሊስ በምርመራው ያገኘውን ማስረጃና የተያዙትን ንብረቶች በማስረጃነት በማቅረብ መዝገቡን ለቡሬ ወረዳ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ልኳል።በዚህም ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ተከሳሾች በቡሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኛ መሆናቸው በማስረጃ ከተረጋገጠ በኋላ በመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔ ተሰጥቷል።
በውሳኔውም ስንታየሁ ባንቴ፣ ስማቸው ፈንታሁን እና ምስጋናው አስማረ የተባሉት ሦስት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል። ሌላኛው ተከሳሽ ደግሞ የተሰረቀውን እቃ በመደበቅ ጥፋተኛ በመሆኑ የ1 ዓመት ከ3 ወር እስራት መፈረዱን ብስራት ሬዲዮ ከቡሬ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅ/ቤት የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

🤪13👍6❤5
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተቀማጭ የውጭ ምንዛሬ ክምችት መጠን 20 በመቶ ማደጉን ገለጸ
የብር የመግዛት አቅም በገበያ እንዲወሰን ከተደረገ በኋላ የኢትዮጵያ ተቀማጭ የውጭ ምንዛሬ ክምችት መጠን 20 በመቶ ማደጉን እና ማዕከላዊ ባንኩ በጨረታ ለባንኮች ያቀረበው የውጭ ምንዛሬ 2.3 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በፋይናንስ ፎረም ላይ ገለጹ።
የውጭ ምንዛሬ እና የትይዩ ገበያ ሁኔታ፦ የውጭ ምንዛሬ በገበያ ከተወሰነ በኋላ የመደበኛ እና የትይዩ (ጥቁር) ገበያ የዋጋ ልዩነት ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረበት 15.3 በመቶ ወደ 11–12 በመቶ ዝቅ ቢልም፣ ወደ ነጠላ አሃዝ ባለመውረዱ የተቀመጠው ግብ ገና እንዳልተሳካ ተጠቅሷል።
የዋጋ ግሽበት እና የፖሊሲ ውጤት፦ የዋጋ ግሽበትን ወደ አንድ ዲጂት ለማውረድ የተያዘው ግብ አለመሳካቱ በውጭ ተጽዕኖ እንጂ በሀገር ውስጥ ፖሊሲ ውድቀት እንዳልሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማዕቀፍ ውጪ የሚካሄዱ ኢንቨስትመንቶች መንገድ እንዳይጀምሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
የባንኮች ውህደት (Merger & Acquisition) ጥሪ፦ የባንኮች ተቀማጭ ገንዘብ ቢያድግም ክምችቱ ወጥ አለመሆኑን የጠቆሙት ገዢው፤ ጠንካራ የፋይናንስ ተቋማትን ለመፍጠር ትንንሽ ባንኮች በመዋሃድ እና በመሰብሰብ (Merger and Acquisition) መጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የህዝብ ኑሮ እና የኢኮኖሚ ሪፎርም፦ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ውጤት ከቁጥር ባለፈ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የእለት ተእለት ኑሮ እና ኪስ ላይ የሚታይ ለውጥ ማምጣት እንዳለበት ተናግረዋል።

❤10👍4
በጋሞ ዞን ጠለፋና የመድፈር ሙከራ ፈጽሞ ድርጊቱን በቪዲዮ ቀርጾ በቲክቶክ ያሰራጨ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ጠለፋና የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ አስታወቀ።
ተከሳሹ መልካሙ ዳዊት የተባለ ሲሆን የግል ተበዳይን በመጥለፋ ተበዳይዋን ወደ ጫካ በመውሰድ አስገድዶ ለመድፈር ሙከራ ማድረጉን ፖሊስ አስታውቋል።በተጨማሪም ድርጊቱን በቪዲዮ በመቅረፅ በቲክቶክ ላይ ማሰራጨቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ገፅታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተከሳሹን ከሠላምበር ከተማ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራውን አጠናቆ መዝገቡን ለአቃቤ ሕግ ማስረከቡን ፖሊስ አስታውቋል።አቃቤ ሕግም በተከሳሹ ላይ በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 587(1) እና 620(2) መሠረት ክስ በመመስረት የሰው፣ የሰነድና የቪዲዮ ማስረጃዎችን ለምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀርባል።
ተከሳሹ የቀረቡትን ማስረጃዎች ማስተባበል ባለመቻሉ፣ ፍርድ ቤቱ በሁለቱም ክሶች ጥፋተኛ መሆኑን በመወሰን 22 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላልፉን ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

👍18❤12
ሰመራ ኤርፖርት‼️
በትናንትናው ዕለት በአፋር ክልል ዋና ከተማ ሰመራ አየር ማረፊያ (ኤርፖርት) ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረ የሚገልፁ መረጃዎች በስፋት ሲሰራጩ ቆይተዋል።
ሚድያችን በአካባቢው ካሉ ምንጮቹ እንዳረጋገጠው በሰመራ አየር ማረፊያ ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጥቃት የለም።
ይሁንና የድሮን ምት እንደሆነ በተገመተ ከባድ ጥቃት ምክንያት ከኤርፖርቱ በቅርብ ርቀት በሚገኘው የክልሉ መንግስት መቀመጫ ቤተ መንግስት ግቢ ወስጥ ዛሬ ምሽት 1:45 ገደማ ጥቃት መፈፀሙን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
ይህ ለክብር እንግዶች (VIP) እንዲሆን ታስቦ እየተሰራ ያለ ህንፃ ተመትቶ በእሳት መያያዙ የታወቀ ሲሆን ስለደረሰው ጉዳት እስካሁን አለመታወቁን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
"በቦታው ከፍተኛ የፀጥታ ሀይል ተሰማርቶ የክልል ፕሬዚዳንቱን የመጠበቅ ስራ እየተሰራ ነው፣ ወደ ቦታ ሰው እንዳይደርስ እየተከለከለ መሆኑንም አይተናል" በማለት አንድ ምንጫችን ማምሻውን ለመሰረተ ሚዲያ ተናግረዋል።
ኤርፖርቱ በመደበኛ ስራው ላይ ነው፣ በረራም አልተቋረጠም።
በዚህ መረጃ ዙርያ እስካሁን ከአፋር ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መረጃ የለም።

❤26👍4🕊3🤔1👌1👀1🤪1
አሜሪካን ያስደነገጠው የጋና መንግስት ውሳኔ‼️
የጋና መንግሥት ከወደ ዋሽንግተን የቀረበለትን የ109 ሚሊዮን ዶላር የጤና ድጋፍ ስምምነት "ብሔራዊ ክብርንና ሉዓላዊነትን ይነካል" ሲል ውድቅ አደረገ።
ኢትዮጵያ ይህንን ስምምነት መፈረሟ ይታወሳል።
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና ከአሜሪካ የጤና ድጋፍ ጀርባ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች "የሚያዋርዱ እና የአገሪቱን ሉዓላዊነት የሚጋፉ ናቸው" ብላለች።
በዚህም የቀረበላትን የ5 ዓመት ዕቅድ እንደማትቀበለው አስታውቃለች።
የጋናው ፕሬዚዳንት ጆን ማሃማ ካቢኔያቸው ስምምነቱን ውድቅ ማድረጉን ሲገልጹ ለአሜሪካ እጅ ላለመስጠት ምክንያት የሆኑትን ዋና ዋና ነጥቦች ይፋ አድርገዋል።
ስምምነቱ ጋና አጠቃላይ የዜጎቿን የሕክምና መረጃዎች ለዋሽንግተን እንድታስረክብ የሚያስገድድ አንቀጽ ይዟል።
አሜሪካ በዚሁ ፕሮግራም ሥር ወደ ጋና የምታስገባቸውን መድኃኒቶችና የሕክምና ቁሳቁሶች የጋና ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዳይመረምርና እንዳይፈትሽ የሚከለክል አ አሰራር ተካቶበታል ብለዋል።
አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ ብትገልጽም ጋና ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያ የራሷን በጀት አውጥታ እንድትመድብ መጠየቋ ቅሬታን ፈጥሯል።
ፕሬዚዳንት ማሃማ ሁኔታውን "አዋራጅ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን ጋና ይህ ድጋፍ ቢቀርባትም በራሷ አቅም መቆም እንደምትችል ገልጸዋል።
በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው በአክራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ ውዥንብር መፈጠሩን ጠቅሷል።
ኤምባሲው የቀረበው ጥያቄ የሕመምተኞችን ግላዊ ማንነት የሚያሳይ መረጃ ሳይሆን የፕሮግራሙን ውጤታማነት ለመለካት የሚያግዝ አጠቃላይ የጤና መረጃ ብቻ መሆኑን አስረድቷል።

❤51👍13👀5🫡4
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በድጋሜ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሰየሙ።
ላለፉት አመታት አዲስ አበባን በከንቲባነት ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በድጋሜ ከንቲባ ሆነው በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ተሰይመዋል።

🤣44👍26❤8🙉6😢3🤷♂1👌1🤡1🤪1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ሹመት‼️
የደሴ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ፤ ጃንጥራር አባይን በመተካት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።
የአዲስ አበባ ካቢኔ አባላት
👉 አቶ ግርማ ሰይፉ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የከተማውን የካቢኔ አባላት ሹመት አፅድቋል።
በዚህም መሰረት፦
1. አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ጥላሁን ከበደ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ ሃፍታይ ገ/እግዚአብሔር - በም/ ከንቲባ ማዕረግ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
5. ዶ/ር አህመዲን መሃመድ - የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ
6. ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ - የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ
7. ኢንጂነር አያልነሽ ኃብተማሪያም - የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ
8. ወ/ሪት ፂዮን ደረጀ (የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል) - የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ
9. ኢንጂነር ህይወት ፀጋዬ - የግንባታ ቁጥጥርና ፈቃድ ቢሮ ኃላፊ
10. ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ - የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ
11. ወ/ሮ ዚያዳ ካሚል - የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
12. አቶ ግርማ ሰይፉ - የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
13. አቶ ቢኒያም ምክሩ - ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
14. አቶ ሙሉቀን ታሪኩ - የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
15. ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ - የንግድ ቢሮ ኃላፊ
16. ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ - የጤና ቢሮ ኃላፊ
17. ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
18. አቶ አወሌ መሃመድ ኡመር - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
19. ዶ/ር ተፈራ ሞላ - የትራንስፖርት ቢሮ
20 ኢንጂነር አይሻ መሃመድ - የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
21. ኢንጂነር ሔለን ገመዳ - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ
22. ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ - የህፃናት ማህበራዊ ጉዳይና ሴቶች ቢሮ
23. አቶ ተስፋዬ ደጀኔ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
24. አቶ አሰግደው ወልደጊዮርጊስ - የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
25. አቶ መላኩ ታምሩ - የመሬት ልማት ቢሮ ኃላፊ

❤25🤪7👍3🤔1🤣1
ጨርጨር‼️
መከላከያ ሠራዊት #ጨርጨር፣ #ሓደ_አልጋና #ወራባየን መቆጣጠሩ ታወቀ።
መከላከያ ሠራዊት #ጨርጨር፣ ሓደ አልጋ እና ወራባየን በቁጥጥር ሥር በማዋል በባቡር መስመሩ ወደ #ፋጫጋማ መድረሱ ተገለጸ።
የጨርጨር መስመር በተለይ የባቡር መስመሩን በመጠቀም ህወሓት ከባድ መሳሪያዎችን ጨምሮ ለማንቀሳቀስ የሚጠቀምበት ዋነኛ መስመር ነበር።

❤23👍10🤪6🥱2✍1🥰1🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኤርትራ ሰራዊት ውጊያ ከፍቶብናል-አወል አርባ‼️
በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ የኤርትራ ሰራዊት ከህወሃት ሀይል ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ጥሶ ገብቶ በከባድ መሳሪያ ጭምር ጦርነት ከፍቶ ይገኛል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕስ መስተዳደር ሀጂ አወል አርባ ከክልሉ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል። በዚህ የተነሳ በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል ብለዋል።

🤣15👍11❤10🤪6😢5😎4🎉2🕊1