አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.5K subscribers
17.4K photos
433 videos
23 files
3.02K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የአየር ጥቃት‼️
በራያ አላማጣ ወረዳ ፋጫ ቀበሌ የኢትዮጵያ አየር ሃይል በሚግ ጀት 5:35 አከባቢ ጥቃት መፈፀሙ ታወቀ።
ከዚህ በተጨማሪ በዋግኽምራ ዞን ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ 07 ድብርሳኤ፣ 02 ቲያ በተባለ ቦታ የአየር ጥቃት ተፈፅሟል።
ጥቃቱ ህወሃት የሚጠቀምባቸውን ከባድ መሳሪያዎች ያነጣጠረ መሆኑ ተሰምቷል።
ከአላማጣ ወደ ቆቦ መስመር ያለው ውጊያ የቀጠለ ሲሆን መከላከያ ከአላማጣ ከተማ ቅርብ እርቀት ላይ የምትገኘውን ዋጃ ከተማን መያዙን የአካባቢው ምንጮች ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍16❤12🤪7🕊4🤡2✍1👌1
የክፍያ ጭማሪ ተደረገ‼️
750 ብር የነበረው ብሔራዊ የድህረ ምረቃ ትም/ት መግቢያ ፈተና (NGAT) ክፍያ 3500 ብር ሆነ።
👉 500 ብር የነበረው የEXIT Exam ክፍያ 2000 ብር

👉 ለሙያ ብቃት ምዘና 3500 ብር የሚከፈል መሆኑን እንድታውቁት። ሌሎች ተጨማሪ የክፍያ ዝርዝሮች በደንብ ቁጥር 593/2018 ተዘርዝረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢48🤔8❤5👍4
ትናንት ጀምሮ በዋግኽምራ ሰቆጣ ከተማ ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ከባድ ውጊያ ሙሉ ለሙሉ ቆሟል።
በዚህ ውጊያ ከባድ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሷል። ሰቆጣ ከተማ መብራት መቋረጡን ነዋሪዎቹ ገልፀውልናል።
የህወሓት ተዋጊዎች ከሰቆጣ ከተማ ዙሪያ ወደ ሸንጎነ ሸሽተዋል ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤18👍10
ሂውማን ራይትስ ዎች፣ ነሐሴ 14 አጋማሽ ላይ በመቀሌ በመኖሪያ ግቢ ላይ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት እንደ "የጦር ወንጀል" ተቆጥሮ ሊመረመር ይገባል አለ።

ድርጅቱ፣ በጥቃቱ ሰባት ሕጻናትን ጨምሮ 13 ሰላማዊ ሰዎች ጉዳት እንደደረሠባቸው የጠቀሠው ድርጅቱ፣ በወቅቱ ምንም ዓይነት ወታደራዊ ዒላማ እንዳልነበርና ጥቃቱ "ሕገወጥ" እና "ማንንም ያልለየ" እንደነበር ገልጧል። ባለሥልጣናት ጥቃቱን ገለልተኛና ግልጽ በኾነ መንገድ እንዲመረምሩ፣ በድርጊቱ የተሳተፉት አካላትን ለሕግ እእንዲያቀርቡና ለተጎጂዎች በቂ ካሳ እንዲከፍሉ ድርጅቱ ጠይቋል።

ከመንግስት ወገን እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤25👍9🤩4😢3
በሰሜን ኢትዮጵያ በበርካታ ግንባሮች ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ በኩል፤ ከፌደራል እና ከክልል “አገናኞች” ጋር ግንኙነት እየተደረገ መሆኑን የአንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቃባይ ገለጹ።

ልዩ ልዑኩ በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአህጉራዊ እና ቀጠናዊ ድርጅቶች ጋር በቅርበት በመተባበር እየሰሩ መሆኑንም ቃል አቃባዩ ተናግረዋል።

የዋና ጸሀፊው ቃል አቃባይ ስቴፈን ዱጃሪች ይህን የተናገሩት፤ ትላንት አርብ መስከረም 15፤ 2019 በሰጡት ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ዱጃሪች በመግለጫቸው የጠቀሷቸው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ቻይናዊው ጉዋንግ ኮንግ፤ በመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተሾሙት በሐምሌ 2017 ዓ.ም. ነበር።

በተመድ የተለያዩ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ከ25 ዓመታት በላይ ያገለገሉት ኮንግ፤ አሁን ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ ለተባባሰው የጸጥታ ሁኔታ መፍትሔ የማፈላለግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኩ እያካሄዷቸው ያሉ ግንኙነቶች፤ “በፕሪቶሪያ ማዕቀፍ ስር የሚደረግ ውይይት እንዲቀጥል” የመደገፍ ሚና ያለው መሆኑን ቃል አቃባይ ዱጃሪች አስረድተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤24👍4
መርጌታ  ጌታቸው  የባህል መድህኒት ፈውስ  የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል

☞  ለመፍትሄ ሀብት
☞  ለህመም
☞  ለመስተፋቅር
☞  ቡዳ ለበላው
☞  ለገበያ
☞  ሚስጥር የሚነግር
☞  ለቀለም(ለትምህርት)
☞  ለመፍትሔ ስራይ
☞  ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞  ሌባ የማያስነካ
☞  ለበረከት
☞  ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞  ለግርማ ሞገስ
☞  መርበቡተ ሰለሞን
☞  ለዓይነ ጥላ
☞  ለሁሉ መስተፋቅር
☞  ጸሎተ ዕለታት
☞  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞  ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞  ለትዳር
☞  ለድምፅ
👉 0921007264 ይደውሉ መፍትሄ አለን
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🍀🌿🙏 መርጌታ  ጌታቸው  የባህል ህክምና ቀማሚ ከፈጣሪ በታች በተሰጠን ሰለሞናዊ ጥበባችን በአለም አቀፋ እዉቃና አግኝተን የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን🇪🇹።
📞09 21007264
📞09 21007264
👉 የብልት ማነስ

👉የመልፈስፈስ
👉ቶሎ የመጨረስ(የመርጨት) ችግር አለብዎት ባልሽስ አለበት

     ለበለጠ መረጃ
    👉በቴሌግራም ማውራት ለሚፈልግ ከታች ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇@Mgetachew23
በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሀለየ ይፌፅም                      
    🍀🌿 🙏በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር  ውጭም  ሆነ  ከአገር ውስጥ  መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን  
🍀🌿🙏ልብ ይበሉ  ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ

ራሳችሁን ከአጭበርባሪወች ጠብቁ!
🤣5❤4👍2😢1
በሰቆጣ ሌሊቱን ከባድ ውጊያ ሲደረግ አደረ ‼️
በዋግኽምራ ሰቆጣ ከተማ የህወሓት እንዲሁም የፋኖ ተዋጊዎች እንደገና ተደራጅተው ሰቆጣን ለመያዝ ትናንት መስከረም 16/2019 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ እስከ ንጋቱ 11:00 ሰዓት
ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ከባድ የተባለ ውጊያ አካሂደዋል።
ነዋሪዎቹ እጅግ አስፈሪና ከባድ ውጊያ ነው የተደረገው ያሉ ሲሆን ወደኋላ ጉዳ መጣያ ወደሚባል ቦታ በማፈግፈቻቸው አሁን ላይ  ውጊያው ቀንሷል ብለዋል።
መከላከያ አልፎ አልፎ ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ይገኛል ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢24❤12👍8🤣2👀1
በትግራይ ክልል የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ትናንት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ እንደማይሰራ፣ገንዘብ ማውጣትም ሆነ መላክ እንደተቸገሩ ገልፀውልናል።
ችግሩ እስኪፈታ :
-አዲስ አበባ ዋናው ብራንች
-ተፈራ ደገፌ
-ሲኤምሲ ብራች አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍12😢5❤3🤡2🤔1🤯1
ዜና ሹመት‼️
አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ኒውክለር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ❗
​ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ አብርሃም በላይን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ኒውክለር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው ሾመዋቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣34❤12👍6
እንኳን አደረሳችሁ!

የመስቀል በዓልን ለምታከብሩ መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! 

መልካም በዓል ይሁንላችሁ 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍26❤8🤔1
ብሔራዊ ባንክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወለድን አስቀድመው እንዳይከፍሉ አዘዘ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ በቅርቡ ባካሄደው የቁጥጥር ሥራ በአንዳንድ ተቋማት የጊዜ ተቀማጭ ሒሳብ ላይ ወለድን አስቀድሞ የማስላትና የመክፈል ሂደት መኖሩን ማረጋገጡን ገልጿል።

ተቋማቱ በመጀመሪያው ቀን ወለዱን አስልተው እንደሚከፍሉና ከዋናው ገንዘብ ጋር የማዳመር ሥራ እንደሚሰሩ ገልጾ ይህም የደንበኛን ሂሳብ ጊዜው ሳይደርስ ያለ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት እንዲጨምር የሚያደርግ ነው ብሏል።

ባንኩ ይህ አሠራር ገበያውን የሚያዛባ፣ ጤናማ ያልሆነ ውድድር የሚያባብስና የፋይናንስ ተቋማትን አሠራር የሚያዳክም መሆኑን አክሎ ገልጿል።

በዚህ መሠረትም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወለድን አስቀድሞ አስልቶ ለተቀማጭ ገንዘብ ባለቤቶች መክፈል፤ እና ወለድን ከዋናው ገንዘብ ጋር ጊዜው ከመድረሱ በፊት ማዋሃድ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ አስጠንቅቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍6❤3
«ውጊያው በድንበር ብቻ አይወሰንም» — ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

​የኢፌዴሪ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መንግሥት ለመጣል የተቋቋመውና «የህልውና ወዳጅነት» የሚባለው አዲስ ጥምረት ከቶ እንደማይሳካ አስታወቁ።

​ስለ ኤርትራ የተሰነዘረ ከሰሳ፦ ኤርትራ የሕወሓትን ቡድን እንደ ተኪ ኃይል (Proxy Force) በመጠቀም የሀብትና ቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን ፊልድ ማርሻሉ ተናግረዋል።

​የውጭ ኃይሎች ድጋፍ፦ ግብፅ፣ ሱዳን እና ኤርትራ ለሕወሓት ቡድን ድጋፍ እየሰጡ እንደሚገኙም አክለው ገልጸዋል።

​የሠራዊቱ አቅም እና የማስጠንቀቂያ መልእክት፦ የኢትዮጵያ ሠራዊት ማንኛውንም ጥቃት የመመከት ሙሉ አቅም እንዳለው የገለጹት ፊልድ ማርሻሉ፤ የጀመረው ውጊያ በድንበር አካባቢ ብቻ ተወስኖ እንደማይቀር አስጠንቅቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣32👍15❤11
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ በአንድ ክፍል ታስረው የነበሩ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች እና ምሁራን አርብ ጥር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ምሽት 11:00 ሰዓት ገደማ በማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ትዕዛዝ ወደተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው እንዲታሰሩ መደረጋቸው ተሰምቷል።

እስረኞቹ በኢሰመኮ አማካይነት የቀረበላቸውን የይቅርታ ቅድመ ሁኔታ የያዘ ሰነድ "አንፈርምም" በማለታቸው ምክንያት የተለያዩ ጫናዎችና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙባቸው እንደሚገኝ ተነግሯል።

በቃሊቲ የነበሩ ከ20 በላይ የህሊና እስረኞች ለእስር ምቹ ወደ ያልሆኑ ቦታዎች በመበታተን እንዲዛወሩ ተደርጓል።

ከእነዚህ እስረኞች መካከል ዶክተር ወንድወሰን አሰፋ በከባድ የህመም ስሜት ላይ እያሉ በምሽት ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተዛወሩ ሲሆን ከሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ተለይተው የጸጥታና የፖሊስ አባላት ብቻ ወደታሰሩበት "ዞን 6" እንዲገቡ ተደርጓል።

ዶክተር ወንድወሰን ካለባቸው የጤና ችግር፣ ከሁኔታው አስፈሪነትና ብቻቸውን ከመሆናቸው የተነሳ "ወደ ውስጥ አልገባም" በማለታቸው እስከ አሁን ድረስ በዞኑ ደጅ ላይ ተቀምጠው እንደሚገኙ ተረጋግጧል።
በጠባብ ቦታና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲቆዩ መደረጉ የጤና ሁኔታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እንዳካበበው ተገልጿል።

ለዚህ አስገዳጅ እርምጃ ምክንያቱን ሲጠይቁ "ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸውና ከኮሚሽነር ተክሉ የተሰጠ መመሪያ እንደሆነ ተጠቅሷል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ሌሎች የህሊና እስረኞችም ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸው ታውቋል።
አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ ዳዊት በጋሻው እና እሱባለው በለጠ ከባድ ወንጀል የፈጸሙና አስፈሪ እስረኞች ወደሚገኙበት በተለምዶ "ታንከር" ተብሎ ወደሚጠራው ማግለያ ቦታ እንዲገቡ ተደርገዋል።

በተጨማሪም ዶክተር ቴዎድሮስ ኃይለማሪያም እና ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው ከቃሊቲ ወደ ቂሊንጦ ዞን 4 የተዛወሩ ሲሆን ሚካኤል መላክ እና ሌሎች ሁለት እስረኞች ደግሞ ወደ አባ ሳሙኤል ማረሚያ ቤት ተወስደዋል።
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ አባይ ዘውዱ እና መንበር አለሙን ጨምሮ የሌሎች እስረኞች የገቡበት ቦታ እስካሁን አልታወቀም።

በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ መብትና ህክምና የማግኘት መብት በህግ የተጠበቀ በመሆኑ የዶክተር ወንድወሰን አሰፋ እና የሌሎች እስረኞች የጤና ሁኔታ በአስቸኳይ በተናጠል አካል እንዲጣራ ጥሪ ቀርቧል።

አግባብ ያላቸው አካላት የእስረኞቹን ህይወትና ደህንነት ለመጠበቅ አስቸኳይ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ፣ ከቤተሰቦቻቸውና ከህግ ጠበቆቻቸው ጋር እንዲገናኙ፣ እንዲሁም የተደረገበትን የዝውውር ህጋዊ መሰረት ግልጽ እንዲያደርጉ ጥሪ እየቀረበ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢15❤10👍4🤔2
ትግራይ ቴሌቪዥን ላይ የድሮን ጥቃት‼️
የህወሓት ልሳን የሆነው የትግራይ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ ዛሬ መስከረም 17/2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጥቃት ተፈፅሞበታል።
መቀሌ ከተማ ዓዲ ሺንድሁን በተባለው ሰፈር የሚገኘው የትግራይ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ በዛሬው ዕለት በድሮን ጥቃት ጉዳት እንደደረሰበት በስፍራው ከሚገኙ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን የቴሌቪዥን ጣቢያው መሰረዙን እና የትግራይ ቴሌቪዥንን በመረጃ ምንጭነት በመጠቀም መረጃ ማሰራጨት እንደሚያስጠይቅ ማሳወቁ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤33👍8😢6🤡5🍾1🫡1
❗️አሁናዊ የጦርነት መረጃዎችን የምታገኙበት ፈጣን የመረጃ ቻናል ተከፈተ👇
https://t.me/addlist/rmM0bFFNbycwMTM0
❤3🌚1
መከላከያ በሰቆጣ ግንባር ድል መቀናጀቱን ተከትሎ ነዋሪዎች በእንዲህ መልኩ ደስታቸውን መግለጻቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል

@Addis_News
@Addis_News
👍26🤣9❤3👀1🙈1