አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.3K subscribers
17.3K photos
433 videos
23 files
3.02K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ህወሓት 4 አርሚዎችን አሰልፎ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ ላይ ያካሄደው ወታደራዊ እንቅስቃሴ በመክሸፉ 436 ታጣቂዎቹ መገደላቸውን መከላከያ ገለጸ‼️
የህወሓት ታጣቂ ቡድን 31ኛ፣ 26ኛ፣ 15ኛ እና 44ኛ የተባሉ አራት አርሚዎቹን ሙሉ በሙሉ በማሰለፍ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ የግዳጅ ቀጣና ላይ ያካሄደው ወታደራዊ ግስጋሴ በመክሸፉ፣ በተካሄደ የተቀናጀ የፀረ-ማጥቃት እርምጃ 436 አባላቱ ሲገደሉ 220 መቁሰላቸውን እና 44 ደግሞ መማረካቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።

የህወሓት ታጣቂዎች ከትናንት በስቲያ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ አቅጣጫ ካካሄዱት ወታደራዊ እንቅስቃሴ በኋላ፣ የተበታተኑ ኃይሎቻቸውን በማሰባሰብ ዳግም ወታደራዊ ግስጋሴ ማድረጋቸውን የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የአንድ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል አዲሱ በድሩ ገልጸዋል።

ብርጋዲየር ጀነራል አዲሱ እንደተናገሩት፤ ታጣቂ ቡድኑ በኮሩ የግዳጅ ቀጣና 31ኛ፣ 26ኛ፣ 15ኛ እና 44ኛ ብሎ የሚጠራቸውን አራት አርሚዎች ሙሉ በሙሉ አሰልፎ ተጨማሪ ማጥቃት ለመሰንዘር የሞከረ ቢሆንም፣ የኮሩ ክፍለ ጦሮች ባካሄዱት የተቀናጀ የመከላከልና የፀረ-ማጥቃት እርምጃ የቡድኑን እንቅስቃሴ ማክሸፍ ተችሏል።

በተካሄደው ወታደራዊ እርምጃ፤ 436 የታጣቂ ቡድኑ አባላት ሲገደሉ፤ 220 አባላት የቆሰሉ ሲሆን፣ 44 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ውለው ተማርከዋል ብሏል  ሠራዊቱ።

በተጨማሪም ከታጣቂ ኃይሉ ላይ በርካታ የጦር መሳሪያዎች እና የመገናኛ ሬዲዮዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል 4 ዲሽቃ፣ 18 መትረየስ፣ 6 ስናይፐር፣ 83 ክላሽንኮፍ ጠብመንጃ፣ 15 አይኮም የመገናኛ ሬዲዮ፣ 2 ዓይነት-77 ሬዲዮ እና 3 አርፒጂ ይገኙበታል ተብሏል።

እንዲሁም ከ5 ሺህ በላይ የመትረየስና 1,590 የዲሽቃ ጥይቶች፣ በርካታ ተተኳሾች እና የመሳሪያ አባሪ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዲየር ጀነራል አዲሱ በድሩ አክለው አብራርተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣16👍11❤10🥱2🕊1🙈1🤪1
ለመስቀል ደመራ በዓል ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶች

በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል፡፡

በዚህም መሰረት ከመስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ ከ5 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሐ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-

👉 22 ማዞሪያ ወደ መስቀል አደባባይ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች፣

👉 ከቦሌ ኤርፖርት ወደ መስቀል አደባባይ ደንበል ወይም ኦሎምፒያ ላይ እና ታች፣

👉 ከጎፋ ፣ በታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ፣

👉 ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለገሃር መብራት ፣

👉 ከለገሃር ቴሌ ወደ ስታዲየም ንግድ ባንክ ክቡ ህንጻ መስቀለኛ፣

👉 ከቸርቸል ጎዳና ፣ በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት፣

👉 ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መስቀለኛ፣

👉 ከካዛንቺስ መብራት ወደ መስቀለኛ መቅረዝ ሆስፒታል የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

በተጨማሪም ነገ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል፡፡

ሕብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና 990 ነፃ የስልክ መስመርን መጠቀም እንደሚችልም ተመላክቷል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤10👍6
ትናንት ጠዋት ጀምሮ በሰሜን ወሎ እና አፋር ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በ17 ግንባር ተቀስቅሶ የነበረው ውጊያ ዛሬ በአብዛኛው ግንባሮች ጋብ ያለ ሲሆን በተኩለሽ አቅጣጫ እስከዚህ ሰዓት ድረስ ውጊያ እየተደረገ ይገኛል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ለመከታተል ቻናላችንን ይቀላቀላሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤5👍4😢3
ምደባ ይፋ ሆነ።
 
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ።
 
በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ይችላሉ።
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement

ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ ተብሏል።
 
በሌላ በኩል፤ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።
 
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement  

እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሀውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍2
ሰቆጣ‼️
ዛሬ መስከረም 15/2019 ዓ.ም 11:00 ጀምሮ በዋግኽምራ ሰቆጣ ከተማ
-በመቀሌ መውጫ
-አዲስ አበባ ወይም ላሊበላ መውጫ
-እና ደሀና/አምደ ወርቅ መውጫ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ዝርዝር መረጃ እንደደረሰ ይቀርባል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤21😢11👍4🤣2
Update‼️
በትግራይ ክልል ሙሉ ለሙሉ የኔትወርክ አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ዘገባዎች ጠቁመው ነበር።

አሁን የደረሱን መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሽሬ፣አዲግራት እንዲሁም ሌሎች አካባቢዎች ላይ ከቀኑ 7:30 አካባቢ ጀምሮ መከፈቱን ነዋሪዎቹ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ሽሬ 7:00 ጀምሮ ኔትወርክ እና ዳታ ተመልሷል ብለዋል።
[አዩዘሀበሻ]

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍14❤6🤔1🙏1
ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው‼️
በሰሜን ወሎ ዋግኽምራ
ሰቆጣ ላይ መከላከያ ሰራዊትና የህወሓት ሀይሎች እጅግ ከፍተኛ የተባለ ውጊያ እያደረጉ ይገኛሉ።
በተለይ በወለህ መስመር፣ውቅር፣አማኑኤል መውጫ አካባቢው ላይ በዚህ ሰዓት (2:40) ከባድ የጨበጣ ውጊያ እያደረጉ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍18❤11🕊6👀5🤪3😢2💔2✍1😱1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው‼️ በሰሜን ወሎ ዋግኽምራ ሰቆጣ ላይ መከላከያ ሰራዊትና የህወሓት ሀይሎች እጅግ ከፍተኛ የተባለ ውጊያ እያደረጉ ይገኛሉ። በተለይ በወለህ መስመር፣ውቅር፣አማኑኤል መውጫ አካባቢው ላይ በዚህ ሰዓት (2:40) ከባድ የጨበጣ ውጊያ እያደረጉ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልፀዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Update‼️
የህወሓት አርሚ 22 ጦር ወደ ሰቆጣ ለመግባት 3 ጊዜ በመልሶ ማጥቃት ምሽቱን ሲደረግ የነበረው ከባድ የጨበጣ ውጊያ በመከላከያ ሰራዊት ብልጫ ተወስዶበታል።
አርሚ 22 ከባድ ኪሳራ ደርሶበት ወደ መሆኒ እየተመለሱ መሆኑን ምንጮቻችን ያረጋገጡ ሲሆን አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተኩሱ ቆሟል ብለዋል።
አሁን ላይ በአካባቢው የድሮን ቅኝት አለ።
Strive for peace🕊🕊🕊🕊

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍23🤪16🕊6❤5👌1
መርጌታ  ጌታቸው  የባህል መድህኒት ፈውስ  የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል

☞  ለመፍትሄ ሀብት
☞  ለህመም
☞  ለመስተፋቅር
☞  ቡዳ ለበላው
☞  ለገበያ
☞  ሚስጥር የሚነግር
☞  ለቀለም(ለትምህርት)
☞  ለመፍትሔ ስራይ
☞  ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞  ሌባ የማያስነካ
☞  ለበረከት
☞  ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞  ለግርማ ሞገስ
☞  መርበቡተ ሰለሞን
☞  ለዓይነ ጥላ
☞  ለሁሉ መስተፋቅር
☞  ጸሎተ ዕለታት
☞  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞  ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞  ለትዳር
☞  ለድምፅ
👉 0921007264 ይደውሉ መፍትሄ አለን
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🍀🌿🙏 መርጌታ  ጌታቸው  የባህል ህክምና ቀማሚ ከፈጣሪ በታች በተሰጠን ሰለሞናዊ ጥበባችን በአለም አቀፋ እዉቃና አግኝተን የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን🇪🇹።
📞09 21007264
📞09 21007264
👉 የብልት ማነስ

👉የመልፈስፈስ
👉ቶሎ የመጨረስ(የመርጨት) ችግር አለብዎት ባልሽስ አለበት

     ለበለጠ መረጃ
    👉በቴሌግራም ማውራት ለሚፈልግ ከታች ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇@Mgetachew23
በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሀለየ ይፌፅም                      
    🍀🌿 🙏በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር  ውጭም  ሆነ  ከአገር ውስጥ  መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን  
🍀🌿🙏ልብ ይበሉ  ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ

ራሳችሁን ከአጭበርባሪወች ጠብቁ!
🤪9🤣3👍2❤1🥱1
ኤታማዦር ሹሙ የውጭ ኃይሎች የታጠቁ ቡድኖች ስብስብ «እየገፉ፣ እየደገፉ እና እያሰናዱ ነው» ሲሉ ከሰሱ።
 
የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የውጭ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማወክ እና ለማዳከም ሲሉ አዲስ የተመሰረተውን የታጠቁ እና የፖለቲካ ቡድኖች ስብስብ ከጀርባ ሆነው እየደገፉ ይገኛሉ ሲሉ ከሰሱ፤ ጥረቱንም ከውጭ በሚደረግ ድጋፍ ሲካሄድ የቆየ ፕሮጀክት አዲስ መልክ ይዞ መምጣት ነው ሲሉ ገልጸውታል።
 
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፣ የኢትዮጵያ ወቅታዊ የደህንነት ፈተናዎች አገሪቷን በቀጥታ ወታደራዊ ወረራ የማጥቃት አቅም የሌላቸው «ታሪካዊ» እና «ወቅታዊ» ጠላቶች የምንላቸው አካላት የሰፊው ስልታቸው አካል እንደሆነ ተናግረዋል።
 
«ሻዕቢያ እና TPLF ያለ ሱዳን፣ ያለ ግብፅ እና ከዚያም ባሻገር ያሉ ኃይሎች 'ግፋ በለው' ካላሏቸው፣ ካልደገፏቸው፣ ካልሰጧቸው፣ ብቻቸውን ተጣምረውም ቢሆን ዋጋ የላቸውም፤ ሲነጣጣሉ ደግሞ ትርጉም የላቸውም» ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣23❤18👍5🌚2🤔1👀1
የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳት ኢብራሂም ትራውሬ ለሀገራቸውን ተዋግተው ለተሰው ወይም ለተጎዱ ወታደር ቤተሰቦች የነፃ ማህበራዊ አገልግሎት ማለትም የጤና፣የትምህርት እና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በነፃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚፈቅድ ህግ አጸደቁ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤81👍26👌2
አላማጣና ሰቆጣ‼️
📌በራያ አላማጣ በሰሌን ውሀ አቅጣጫ ዛሬ መስከረም 16/2019 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ወደ ቆቦ መስመር በደና ለኮ፣በጎቱ፣በገደራ አካባቢ የጨበጣ ውጊያ እየተደረገ ይገኛል።
📌በሰቆጣ ዙሪያ ትናንት ከሰዓት ጀምሮ አስከ ለሊት 8:00 ድረስ የነበረው ከባድ የጨበጣ ውጊያ የቆመ ሲሆን አሁን ላይ ተኩስ የሚሰማው ከሰቆጣ ዙሪያ ርቆ በውቅር መስቀለ ክርስቶስ አቅጣጫ ፅቫያ ወደ ሚባለው ጻግብጂ ወረዳ መስመር ሲሆን ተኩሱ የድሽቃና የቡድን መሳሪያ ድምፆች ናቸው የሚሰሙት ሲሉ ምንጮቻችን ገልፀዋል።
8 ጊዜ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍15❤12😢2
መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፤ የአሜሪካ ዜጎች “በማንኛውም ምክንያት” ወደ አማራ፣ ትግራይ እና አፋር ክልሎች እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

በኢትዮጵያ ወደሚገኙ አምስት ክልሎች ከሚደረጉ ማንኛውም ጉዞዎች እንዲርቁ ከዚህ ቀደም ለዜጎቿ ማስጠንቀቂያ ሰጥታ የነበረችው ካናዳ፤ በዝርዝሩ ውስጥ የአፋር ክልል እንዲካተት አድርጋለች።

ካናዳ የአፋር ክልል የተካተተበትን አዲስ የጉዞ ማስጠንቀቂያ የሰጠችው በትላንትናው ነው። ጎረቤቷ አሜሪካ ዛሬ አርብ መስከረም 15፤ 2019 በኤምባሲዋ በኩል ባሰራጨችው የደህንነት ማንቂያ መልክት፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ ክልሎች ስላሉ የጸጥታ ሁኔታዎች ለዜጎቿ አጭር ማብራሪያ ሰጥታለች።

ኤምባሲው በዚሁ መልዕክቱ፤ በአማራ ክልል በላሊበላ ከተማ አቅራቢያ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የሚያመለክት መረጃ እንደደረሰው ገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትላንት ሐሙስ መስከረም 14 ጀምሮ ወደ ላሊበላ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን በመልዕክቱ የጠቀሰው ኤምባሲው፤ ወደ ከተማይቱ የሚደረጉ በረራዎች ዳግም መቼ እንደሚጀመሩ መረጃ እንደሌለው አመልክቷል።

የአሜሪካ ዜጎች ላሊበላን ጨምሮ ወደ አማራ ክልል ሌሎች አካባቢዎች ለማንኛውም ምክንያት እንዳይጓዙም ኤምባሲው መክሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13👍4🕊1
በኢትዮጵያ 58% ሴቶች ተገርዘዋል - ጥናት

በኢትዮጵያ ከ15 እስከ 49 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ካሉ ሴቶች መካከል 58 በመቶ የሚሆኑት የተገረዙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ያወጣውን ጥናት ዋቢ በማድረግ ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። የግርዛት መጠኑ በሶማሌ ክልል 94 በመቶ በመድረስ ከፍተኛው ሲሆን፣ በጋምቤላ ክልል ደግሞ 17 በመቶ በመሆን ዝቅተኛው ነው። አብዛኞቹ ሴቶች ከ5 ዓመት በታች ባለው ለጋ እድሜያቸው እንደሚገረዙና 5 በመቶ ያህሉ ደግሞ በሕክምና ባለሙያዎች እንደሚፈጸም ተጠቅሷል።

በሌላ በኩል በህብረተሰቡ አመለካከት ላይ ጥሩ ለውጦች እየታዩ ነው፤ ወደ 80 በመቶ የሚሆኑ ሴቶችና ወንዶች ድርጊቱ ማቆም አለበት የሚል እምነት አላቸው። በተጨማሪም የሴቶች ማህበራት ቅንጅት ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በኦሮሚያ፣ አማራና ሶማሌ ክልሎች የሴቶች ግርዛትና ያለ እድሜ ጋብቻን ለማስቀረት ሲሰራ የቆየው ፕሮጀክት መጠናቀቁን የቅንጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሳባ ገብረመድህን ለሸገር ሬዲዮ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በሕጉ ላይ የተቀመጠው የ3 ወር እስራትና የ500 ብር መቀጮ አነስተኛ በመሆኑ፣ በጥፋተኞች ላይ የሚጣለው ቅጣት እንዲበዛ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ለፍትሕ ሚኒስቴር መላኩን የሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በ1992 ዓ.ም ከነበረበት 80 በመቶ የግርዛት መጠን አሁን ወደ 58 በመቶ መቀነስ ብትችልም፣ ድርጊቱን ጨርሶ ለማስቀረት አሁንም ሰፊ ሥራ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣22❤9👍2😢2🤔1👀1🙈1
የአየር ጥቃት‼️
በራያ አላማጣ ወረዳ ፋጫ ቀበሌ የኢትዮጵያ አየር ሃይል በሚግ ጀት 5:35 አከባቢ ጥቃት መፈፀሙ ታወቀ።
ከዚህ በተጨማሪ በዋግኽምራ ዞን ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ 07 ድብርሳኤ፣ 02 ቲያ በተባለ ቦታ የአየር ጥቃት ተፈፅሟል።
ጥቃቱ ህወሃት የሚጠቀምባቸውን ከባድ መሳሪያዎች ያነጣጠረ መሆኑ ተሰምቷል።
ከአላማጣ ወደ ቆቦ መስመር ያለው ውጊያ የቀጠለ ሲሆን መከላከያ ከአላማጣ ከተማ ቅርብ እርቀት ላይ የምትገኘውን ዋጃ ከተማን መያዙን የአካባቢው ምንጮች ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍14❤12🤪7🕊4🤡2✍1👌1
የክፍያ ጭማሪ ተደረገ‼️
750 ብር የነበረው ብሔራዊ የድህረ ምረቃ ትም/ት መግቢያ ፈተና (NGAT) ክፍያ 3500 ብር ሆነ።
👉 500 ብር የነበረው የEXIT Exam ክፍያ 2000 ብር

👉 ለሙያ ብቃት ምዘና 3500 ብር የሚከፈል መሆኑን እንድታውቁት። ሌሎች ተጨማሪ የክፍያ ዝርዝሮች በደንብ ቁጥር 593/2018 ተዘርዝረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢45🤔8❤5👍4
ትናንት ጀምሮ በዋግኽምራ ሰቆጣ ከተማ ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ከባድ ውጊያ ሙሉ ለሙሉ ቆሟል።
በዚህ ውጊያ ከባድ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሷል። ሰቆጣ ከተማ መብራት መቋረጡን ነዋሪዎቹ ገልፀውልናል።
የህወሓት ተዋጊዎች ከሰቆጣ ከተማ ዙሪያ ወደ ሸንጎነ ሸሽተዋል ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍10
ሂውማን ራይትስ ዎች፣ ነሐሴ 14 አጋማሽ ላይ በመቀሌ በመኖሪያ ግቢ ላይ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት እንደ "የጦር ወንጀል" ተቆጥሮ ሊመረመር ይገባል አለ።

ድርጅቱ፣ በጥቃቱ ሰባት ሕጻናትን ጨምሮ 13 ሰላማዊ ሰዎች ጉዳት እንደደረሠባቸው የጠቀሠው ድርጅቱ፣ በወቅቱ ምንም ዓይነት ወታደራዊ ዒላማ እንዳልነበርና ጥቃቱ "ሕገወጥ" እና "ማንንም ያልለየ" እንደነበር ገልጧል። ባለሥልጣናት ጥቃቱን ገለልተኛና ግልጽ በኾነ መንገድ እንዲመረምሩ፣ በድርጊቱ የተሳተፉት አካላትን ለሕግ እእንዲያቀርቡና ለተጎጂዎች በቂ ካሳ እንዲከፍሉ ድርጅቱ ጠይቋል።

ከመንግስት ወገን እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤24👍9🤩4😢3