አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.5K subscribers
17.4K photos
433 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ላልተወሰነ ጊዜ ተከለከለ

ከዛሬ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ጀምሮ ባለሁለት እግር ሞተር  ብስክሌት በአዲስ አበባ ማሽከርከር እንደተከለከለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ።

አንዳንድ ወንጀል ፈጻሚዎች ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም የቅሚያ እና የስርቆት ወንጀል ሲፈጽሙ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸውም ይገኛል።

ወንጀል ፈጻሚዎች ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር  እና የተሰረቁ እቃዎችን ለማጓጓዝ ሞተር ብስክሌትን በብዛት እንደሚጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል።

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንቡን እንደማያከብሩ በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ወንጀልን ለመከላከል እና በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የሚፈጸምን የደንብ ጥሰት ለመቆጣጠር ከዛሬ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌት ውጭ  በአዲስ አበባ ከተማ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች እና ባለ ንብረቶች አስፈላጊውን እንዲፈጽሙ ፖሊስ አሳስቦ ነገር ግን ይህንን ማሳሳቢያ በሚተላለፉ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍6😢1
የቴሌኮም ሰራተኞች ታስረዋል-ምንጮች‼️
በትግራይ ክልል ከትናንት መስከረም 14/2019 ዓ.ም ከምሽቱ 4:20 ጀምሮ የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን አዩዘሀበሻ መዘገቡ ይታወሳል።
የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክን ያገደው ህወሓት መሆኑ ታውቋል።
ከሰሞኑ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ኔትወርክ እንዲያቋርጡ በህወሓት የደህንነት መሪዎች ቢጠየቁም 'እኛ አናቋርጥም፣ማቋረጥ የምንችለው ከፌዴራል የፌዴራል መንግሥቱ ትዕዛዝ ከመጣ ነው' በማለታቸው የተወሰኑ ሰራተኞች ታስረዋል።
ይህን ተከትሎ ትናንት ምሽት የህወሓት የደህንነት ሰዎች የቴሌኮም ዋናውን መስመር በመቁረጥ ኔትወርክ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል። ይህን እርምጃ የወሰዱት ለደህንነት በመስጋት ነው ብለዋል።
ሳፋሪኮም ተደራሽ በሆነባቸው አካባቢዎች ይሰራል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍4😱4
ሳፋሪኮም እንዲዘጋ ትዕዛዝ ተሰጠ‼️
ሳፋሪኮም በመላው ትግራይ ሙሉ ለሙሉ እንዲዘጋ ህወሓት ለሳፋሪኮም ሰራተኞች ትዕዛዝ መስጠቱን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ አረጋግጠዋል።
ዛሬ ቀን መስከረም 15 / 2019 ዓ/ም #ረፋድ ላይ የህወሓት አመራሮች #ላጪ የሚገኘው የሳፋሪኮም ፅፈት ቤት " ኔትወርኩን በአስቸኳይ ዝጉ " የሚል ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፏል።
የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ትናንት መስከረም 14 ምሽት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ መቋረጡ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍7❤6
ህወሓት 4 አርሚዎችን አሰልፎ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ ላይ ያካሄደው ወታደራዊ እንቅስቃሴ በመክሸፉ 436 ታጣቂዎቹ መገደላቸውን መከላከያ ገለጸ‼️
የህወሓት ታጣቂ ቡድን 31ኛ፣ 26ኛ፣ 15ኛ እና 44ኛ የተባሉ አራት አርሚዎቹን ሙሉ በሙሉ በማሰለፍ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ የግዳጅ ቀጣና ላይ ያካሄደው ወታደራዊ ግስጋሴ በመክሸፉ፣ በተካሄደ የተቀናጀ የፀረ-ማጥቃት እርምጃ 436 አባላቱ ሲገደሉ 220 መቁሰላቸውን እና 44 ደግሞ መማረካቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።

የህወሓት ታጣቂዎች ከትናንት በስቲያ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ አቅጣጫ ካካሄዱት ወታደራዊ እንቅስቃሴ በኋላ፣ የተበታተኑ ኃይሎቻቸውን በማሰባሰብ ዳግም ወታደራዊ ግስጋሴ ማድረጋቸውን የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የአንድ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል አዲሱ በድሩ ገልጸዋል።

ብርጋዲየር ጀነራል አዲሱ እንደተናገሩት፤ ታጣቂ ቡድኑ በኮሩ የግዳጅ ቀጣና 31ኛ፣ 26ኛ፣ 15ኛ እና 44ኛ ብሎ የሚጠራቸውን አራት አርሚዎች ሙሉ በሙሉ አሰልፎ ተጨማሪ ማጥቃት ለመሰንዘር የሞከረ ቢሆንም፣ የኮሩ ክፍለ ጦሮች ባካሄዱት የተቀናጀ የመከላከልና የፀረ-ማጥቃት እርምጃ የቡድኑን እንቅስቃሴ ማክሸፍ ተችሏል።

በተካሄደው ወታደራዊ እርምጃ፤ 436 የታጣቂ ቡድኑ አባላት ሲገደሉ፤ 220 አባላት የቆሰሉ ሲሆን፣ 44 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ውለው ተማርከዋል ብሏል  ሠራዊቱ።

በተጨማሪም ከታጣቂ ኃይሉ ላይ በርካታ የጦር መሳሪያዎች እና የመገናኛ ሬዲዮዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል 4 ዲሽቃ፣ 18 መትረየስ፣ 6 ስናይፐር፣ 83 ክላሽንኮፍ ጠብመንጃ፣ 15 አይኮም የመገናኛ ሬዲዮ፣ 2 ዓይነት-77 ሬዲዮ እና 3 አርፒጂ ይገኙበታል ተብሏል።

እንዲሁም ከ5 ሺህ በላይ የመትረየስና 1,590 የዲሽቃ ጥይቶች፣ በርካታ ተተኳሾች እና የመሳሪያ አባሪ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዲየር ጀነራል አዲሱ በድሩ አክለው አብራርተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣16👍11❤10🥱2🕊1🙈1🤪1
ለመስቀል ደመራ በዓል ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶች

በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል፡፡

በዚህም መሰረት ከመስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ ከ5 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሐ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-

👉 22 ማዞሪያ ወደ መስቀል አደባባይ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች፣

👉 ከቦሌ ኤርፖርት ወደ መስቀል አደባባይ ደንበል ወይም ኦሎምፒያ ላይ እና ታች፣

👉 ከጎፋ ፣ በታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ፣

👉 ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለገሃር መብራት ፣

👉 ከለገሃር ቴሌ ወደ ስታዲየም ንግድ ባንክ ክቡ ህንጻ መስቀለኛ፣

👉 ከቸርቸል ጎዳና ፣ በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት፣

👉 ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መስቀለኛ፣

👉 ከካዛንቺስ መብራት ወደ መስቀለኛ መቅረዝ ሆስፒታል የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

በተጨማሪም ነገ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል፡፡

ሕብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና 990 ነፃ የስልክ መስመርን መጠቀም እንደሚችልም ተመላክቷል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤10👍6
ትናንት ጠዋት ጀምሮ በሰሜን ወሎ እና አፋር ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በ17 ግንባር ተቀስቅሶ የነበረው ውጊያ ዛሬ በአብዛኛው ግንባሮች ጋብ ያለ ሲሆን በተኩለሽ አቅጣጫ እስከዚህ ሰዓት ድረስ ውጊያ እየተደረገ ይገኛል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ለመከታተል ቻናላችንን ይቀላቀላሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤5👍4😢3
ምደባ ይፋ ሆነ።
 
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ።
 
በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ይችላሉ።
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement

ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ ተብሏል።
 
በሌላ በኩል፤ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።
 
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement  

እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሀውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍2
ሰቆጣ‼️
ዛሬ መስከረም 15/2019 ዓ.ም 11:00 ጀምሮ በዋግኽምራ ሰቆጣ ከተማ
-በመቀሌ መውጫ
-አዲስ አበባ ወይም ላሊበላ መውጫ
-እና ደሀና/አምደ ወርቅ መውጫ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ዝርዝር መረጃ እንደደረሰ ይቀርባል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤21😢11👍4🤣2
Update‼️
በትግራይ ክልል ሙሉ ለሙሉ የኔትወርክ አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ዘገባዎች ጠቁመው ነበር።

አሁን የደረሱን መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሽሬ፣አዲግራት እንዲሁም ሌሎች አካባቢዎች ላይ ከቀኑ 7:30 አካባቢ ጀምሮ መከፈቱን ነዋሪዎቹ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ሽሬ 7:00 ጀምሮ ኔትወርክ እና ዳታ ተመልሷል ብለዋል።
[አዩዘሀበሻ]

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍14❤6🤔1🙏1
ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው‼️
በሰሜን ወሎ ዋግኽምራ
ሰቆጣ ላይ መከላከያ ሰራዊትና የህወሓት ሀይሎች እጅግ ከፍተኛ የተባለ ውጊያ እያደረጉ ይገኛሉ።
በተለይ በወለህ መስመር፣ውቅር፣አማኑኤል መውጫ አካባቢው ላይ በዚህ ሰዓት (2:40) ከባድ የጨበጣ ውጊያ እያደረጉ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍18❤11🕊6👀5🤪3😢2💔2✍1😱1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው‼️ በሰሜን ወሎ ዋግኽምራ ሰቆጣ ላይ መከላከያ ሰራዊትና የህወሓት ሀይሎች እጅግ ከፍተኛ የተባለ ውጊያ እያደረጉ ይገኛሉ። በተለይ በወለህ መስመር፣ውቅር፣አማኑኤል መውጫ አካባቢው ላይ በዚህ ሰዓት (2:40) ከባድ የጨበጣ ውጊያ እያደረጉ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልፀዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Update‼️
የህወሓት አርሚ 22 ጦር ወደ ሰቆጣ ለመግባት 3 ጊዜ በመልሶ ማጥቃት ምሽቱን ሲደረግ የነበረው ከባድ የጨበጣ ውጊያ በመከላከያ ሰራዊት ብልጫ ተወስዶበታል።
አርሚ 22 ከባድ ኪሳራ ደርሶበት ወደ መሆኒ እየተመለሱ መሆኑን ምንጮቻችን ያረጋገጡ ሲሆን አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተኩሱ ቆሟል ብለዋል።
አሁን ላይ በአካባቢው የድሮን ቅኝት አለ።
Strive for peace🕊🕊🕊🕊

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍24🤪16🕊6❤5👌1
መርጌታ  ጌታቸው  የባህል መድህኒት ፈውስ  የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል

☞  ለመፍትሄ ሀብት
☞  ለህመም
☞  ለመስተፋቅር
☞  ቡዳ ለበላው
☞  ለገበያ
☞  ሚስጥር የሚነግር
☞  ለቀለም(ለትምህርት)
☞  ለመፍትሔ ስራይ
☞  ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞  ሌባ የማያስነካ
☞  ለበረከት
☞  ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞  ለግርማ ሞገስ
☞  መርበቡተ ሰለሞን
☞  ለዓይነ ጥላ
☞  ለሁሉ መስተፋቅር
☞  ጸሎተ ዕለታት
☞  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞  ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞  ለትዳር
☞  ለድምፅ
👉 0921007264 ይደውሉ መፍትሄ አለን
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🍀🌿🙏 መርጌታ  ጌታቸው  የባህል ህክምና ቀማሚ ከፈጣሪ በታች በተሰጠን ሰለሞናዊ ጥበባችን በአለም አቀፋ እዉቃና አግኝተን የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን🇪🇹።
📞09 21007264
📞09 21007264
👉 የብልት ማነስ

👉የመልፈስፈስ
👉ቶሎ የመጨረስ(የመርጨት) ችግር አለብዎት ባልሽስ አለበት

     ለበለጠ መረጃ
    👉በቴሌግራም ማውራት ለሚፈልግ ከታች ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇@Mgetachew23
በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሀለየ ይፌፅም                      
    🍀🌿 🙏በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር  ውጭም  ሆነ  ከአገር ውስጥ  መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን  
🍀🌿🙏ልብ ይበሉ  ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ

ራሳችሁን ከአጭበርባሪወች ጠብቁ!
🤪9🤣3👍2❤1😢1🥱1
ኤታማዦር ሹሙ የውጭ ኃይሎች የታጠቁ ቡድኖች ስብስብ «እየገፉ፣ እየደገፉ እና እያሰናዱ ነው» ሲሉ ከሰሱ።
 
የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የውጭ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማወክ እና ለማዳከም ሲሉ አዲስ የተመሰረተውን የታጠቁ እና የፖለቲካ ቡድኖች ስብስብ ከጀርባ ሆነው እየደገፉ ይገኛሉ ሲሉ ከሰሱ፤ ጥረቱንም ከውጭ በሚደረግ ድጋፍ ሲካሄድ የቆየ ፕሮጀክት አዲስ መልክ ይዞ መምጣት ነው ሲሉ ገልጸውታል።
 
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፣ የኢትዮጵያ ወቅታዊ የደህንነት ፈተናዎች አገሪቷን በቀጥታ ወታደራዊ ወረራ የማጥቃት አቅም የሌላቸው «ታሪካዊ» እና «ወቅታዊ» ጠላቶች የምንላቸው አካላት የሰፊው ስልታቸው አካል እንደሆነ ተናግረዋል።
 
«ሻዕቢያ እና TPLF ያለ ሱዳን፣ ያለ ግብፅ እና ከዚያም ባሻገር ያሉ ኃይሎች 'ግፋ በለው' ካላሏቸው፣ ካልደገፏቸው፣ ካልሰጧቸው፣ ብቻቸውን ተጣምረውም ቢሆን ዋጋ የላቸውም፤ ሲነጣጣሉ ደግሞ ትርጉም የላቸውም» ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣24❤19👍5🌚2🤔1👀1