አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.9K subscribers
17.5K photos
434 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
" የጦርነቱን ሸክም እንዲሸከሙ ኤርትራ አሰልፋቸዋለች  ! " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፣  የኤርትራ መንግሥት ከግብፅ ጋር በመሆን የምስራቅ አፍሪካን ሰላም ለማናጋት እና ቀጣናውን ለማተራመስ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህን ያሉት ከ " Pulse of Africa " ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

በኤርትራ ያለው ከባድ የኑሮ ውድነት እና መጥፎ የፖለቲካ ሁኔታ በርካታ ወጣቶች ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ማድረጉን ያነሱት አቶ ጌታቸው " የሀገሪቱ ሠራዊትም ሀገር ለመጠበቅ ሳይሆን ፕሬዚዳንቱን ለመጠበቅ ብቻ የቆመ ነው " ብለዋል።

በዚህም ምክንያት ኤርትራ ራሷ በቀጥታ በጦርነት ውስጥ ከመግባት ይልቅ፣ ሌሎች ታጣቂዎችን እንደ መሣሪያ በመጠቀም ግጭቶችን ከድንበሯ ራቅ ባሉ ቦታዎች ለማቀጣጠል እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው እንዳሉት፤ እንደ ፋኖ፣  ኦነግ ሸኔ እና አሁን ደግሞ ሕወሓት ያሉ አካላት የኤርትራን ዓላማ ለማሳካት እና የጦርነቱን ሸክም እንዲሸከሙ ተሰልፈዋል።

በተለይም ሕወሓት እና የኤርትራ መንግሥት አብረው መሠለፋቸው እጅግ አደገኛና የትግራይንና የአማራን ሕዝብ ለከፋ ሁኔታ የሚዳርግ መሆኑን አስረድተዋል።

" የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እስካሁን ለሚደርሱበት የተለያዩ ትነኮሶዎች ከፍተኛ ትዕግስት እያሳየ ይገኛል " ያሉት አቶ ጌታቸው  ሆኖም ሕወሓት በኤርትራ ወጥመድ ወድቆ በፌዴራል ኃይሎች ላይ ጥቃት ከሰነዘረ፣ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሰፊ ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አጽንኦት ሰጥተው አስጠንቅቀዋል።

ቀጣናውን ከሌላ አስከፊ ጦርነት ለመታደግ እና የሰላም አፍራሾችን እንቅስቃሴ ለመግታት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኤርትራ መንግሥት እና ተባባሪዎቹ ላይ አፋጣኝ እና ጠንካራ ጫና መፍጠር እንዳለበት አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19🤣7🌚5👍2🕊2🥰1🤪1
47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የዳግም ምዝገባ መስፈርት አላሟሉም ተባለ

ራስ ገዝ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ዕድሳት አሰጣጥ መመሪያ የተቀመጠውን ዝቅተኛ የዳግም ምዝገባ መስፈርት አለማሟላታቸውን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ገለጸ።

የባለሥልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ ሥራ አስፈጻሚ ጀንበሩ ዓለማየሁ፣ ተቋማቱ በሰነድ ያቀረቡትን መረጃ መሠረት በማድረግ በሰኔ 2018 ዓ.ም. ግምገማ መደረጉንና ሁሉም ዝቅተኛውን መስፈርት አለማሟላታቸው መረጋገጡን ተናግረዋል።

ተቋማቱ ተጨማሪ 40 ቀናት እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ሰነዶቻቸውን እንዲያስገቡ ጊዜ መሰጠቱም ተገልጿል።

በዳግም ምዝገባው ሂደት ልዩ አደረጃጀት የተሰጠው ፕብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ብቻ መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13👍7
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አብዛኛዎቹ አካባቢዎች በቀጣዩቹ ቀናት እንደሚጨምር በሚጠበቀው የዝናብ ሁኔታ ሳቢያ የኮሌራ ወረርሽኝ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግ የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

በክልሉ “ሁሉም አካባቢዎች” ይህንኑ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ “የመከላከል እና የዝግጁነት ስራ” እንዲጠናከርም ኢንስቲትዩቱ መልዕክት አስተላልፏል።ተቋሙ የኮሌራ ወረረሽኝ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልዕክቱን ያስተላለፈው፤ በክልሉ ስር ለሚገኙ 12 ዞኖች ጤና መምሪያዎች እንዲሁም ለሶዶ፣ ዲላ እና አርባ ምንጭ ከተሞች በጻፈው ደብዳቤ ነው።

ባለፈው አርብ መስከረም 8፤ 2019 የተጻፈው ይህ ደብዳቤ፤ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከዓመታት በፊት የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ፤ “ቀላል የማይባል” ህመም እና ሞት ማስከተሉን አስታውሷል።በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሁኑ ወቅት የኮሌራ ወረረሽኝ “በየትኛውም አካባቢ” ያልተከሰተ መሆኑንም የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በደብዳቤው ጠቅሷል።

ሆኖም ለበሽታው መከሰት “ምቹ ሁኔታዎች ሲፈጠር”፤ ወረረሽኙ “ዳግም ሊከሰት የሚችልበት” አጋጣሚዎች እንዳሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል።ተቋሙ ለዚህ በማስረጃነት ያቀረበው፤ በኢል-ኒኖ የአየር ንብረት ክስተት ምክንያት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የዝናብ ሁኔታ እንደሚጨምር የሚቴዎሮሎጂ የትንበያ መረጃዎች ማመልከታቸውን ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤7👍3🕊1
ትግራይ ቴሌቪዥን ታገደ‼️
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን 
የትግራይ ቴሌቪዥን  መታገዱን  አስታወቀ


በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል በፕሬቶሪያ የተፈፀመውን የሰላም ስምምነት ተከተሎ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ባደረገው ውይይትና በተደረሰበት ስምምነት መሠረት፣ ቀደም ሲል በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነስቶ ወደ ሥራ መመለሱ ይታወቃል።

ከዚህም በተጨማሪ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ለትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች የሰላም ግንባታና የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ሚዲያው ወደ ሕገ-መንግሥታዊና ሙያዊ መስመር እንዲመለስ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ቴሌቪዥን በተሰጠው ዕድል ተጠቅሞ እና የሙያ ሥነ-ምግባር አክብሮ አገልግሎት መስጠት ሲገባው፤ የሀገርንና የህዝብን ደህንነት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉ እና ፅንፈኝነት የሚያበረታቱ መልእክቶች በተከታታይ እየተላለፉበት እንደሚገኝ የሚዲያ ይዘት ክትትል ግምገማችን ውጤት ያረጋግጣል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በህግ የተጣለበትን ኃላፊነት መሠረት በማድረግ፣ ከዛሬ ጀምሮ በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ላልተወሰነ ጊዜ እገዳ መጣሉን ይገልጻል።

ማንኛውም ዲጂታል፣ የብሮድካስትም ሆነ የሕትመት ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም የቴሌቪዥን ጣቢያው በህገወጥ መንገድ የሚያሰራጫቸውን  ይዘቶች አሰራጭቶ ወይም አስተጋብቶ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ይህንን መመሪያ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም ሚዲያ ላይ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ህጋዊ እና አስተዳደራዊና እርምጃዎች የሚወስድ መሆኑን አጥብቆ አሳስቧል።

@Addis_Reporter
🤪31❤27👍9🤔2🤣2🎉1🥱1💔1
ሚድሮክ ዝቅተኛውን የሰራተኞች ደመወዝ ወደ 10,000 ብር አሳደገ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2019 በጀት ዓመት አነስተኛ የወርሃዊ ደመወዝ ወለልን ከ6,000 ወደ 10,000 ብር ማሳደጉን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ጀማል አህመድ አስታወቁ።

ኩባንያው ለደመወዝ ጭማሪ ተጨማሪ 3.24 ቢሊዮን ብር የመደበ ሲሆን፣ ይህም ጠቅላላ ዓመታዊ የደመወዝ በጀቱን ወደ 13 ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል።

በተጨማሪም ባለፈው የበጀት ዓመት 1.2 ቢሊዮን ብር የቦነስ ክፍያ የተፈጸመ ሲሆን፣ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ 700 ሰራተኞች ከ100,000 እስከ 500,000 ብር የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።

ሚድሮክ ከትርፉ 10 በመቶ ለማህበራዊ ድጋፍ የዋለ ሲሆን፣ በዓመቱ 390 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱንም ገልጿል።

ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት በአጠቃላይ 80,000 ሰራተኞች አሉት።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍28❤13🤪3👌1
ወደ አማራ ክልል የተንቀሳቀሱት የህወሓት ታጣቂዎች‼️
ዛሬ ቀን ( መስከረም 11/2019 ዓ/ም ) 5፡20 ላይ የህወሓት ሰራዊቶች አርሚ 22 ኮር 3 #ጥራሪ ወንዝን ተሻግረው➡በሪዋርያ➡️በወልማርያም➡️በደረንዝባ አድርገው ወደ አማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን #ሀሙሲት እየሄዱ በነበርበት ወቅት መከላከያ ሰራዊት ከባድ_መሳሪያ ሲተኩስ አርፍዷል።
በከባድ መሳሪያ ተኩሱ ምክንያት ተበታትነው የነበሩት የህወሓት ታጣቂዎች #እንደ_አዲስ ተሰበስበው 8፡40 ላይ በራያ ዛታ ወረዳ  #ጓል_መርቆርዎስ ጣቢያ #ጥራሪ_ወንዝ ወረድ ብሎ አሁንም  #ሀሙሲት ለመግባት ተዘጋጅተው እያለ  ድንገተኛ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።

Via: አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍23🤪7❤5😢5🕊2👀1🙈1
የቻይና ሳይንቲስቶች ሰዎችን እስከ 150 ዓመት
ሊያስቆይ የሚችል እንክብል አዘጋጅተናል አሉ

አንድ የቻይና የባዮቴክኖሎጂ ኩባንያ ሰዎች እስከ 150 ዓመት እንዲኖሩ የሚያስችል «ፒሲሲ1» (PCC1) የተባለ ውህድ የያዘ እንክብል  አዘጋጅቻለሁ ብሏል። ከወይን ፍሬ ዘር የሚገኘው ይህ ንጥረ ነገር እድሜ እየገፋ ሲሄድ በሰውነት ውስጥ ተከማችተው በሽታዎችን የሚያስከትሉ ያረጁ ሴሎችን እንደሚያጠፋ ይነገራል።

ይህ ውህድ በአይጦች ላይ በተደረገ ሙከራ ዕድሜን በትንሹ እንደሚያራዝም ተስፋ ሰጪ ውጤት አሳይቷል። ሆኖም ጥናቱ እስካሁን የተደረገው በእንስሳት ላይ ብቻ በመሆኑ፣ በሰዎች ላይም ተመሳሳይ ውጤት እንደሚያመጣ የተረጋገጠ ነገር የለም። የሰዎች አኗኗር እና የእርጅና ሂደት ከእንስሳት በጣም የተወሳሰበ በመሆኑ ውህዱ በሰው ላይ ይሰራል ማለት አያስችልም።

ኩባንያው ሰዎችን ለረጅም ጊዜ ማኖር ብቻ ሳይሆን ከእድሜ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን በሽታዎች ማዘግየት ዋናው አላማው መሆኑን ይገልጻል። ነገር ግን  እንክብሉ ሰዎችን እስከ 150 ዓመት ማቆየቱ አሁን ላይ ከእውነት ይልቅ ግምት ብቻ ነው። ይህንን ለማረጋገጥ በሰዎች ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት የሕክምና ሙከራዎችን ማካሄድ የግድ ይላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19🤣17👍3
የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) “የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሃይሎች ትብብር ለሕልውና” ከተባለውና ከቀድሞው ሕወሃት (TPLF) ጋር ግንኙነት ካለው የታጠቀ ቡድን ጋር ተቀላቅሏል ተብሎ የተሰራጨውን መረጃ በፅኑ አስተባበለ።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፣ የቀድሞው ሊቀመንበር አብዱልረህማን ሼክ ማህዲ በህገ-ወጥ መንገድ የኦብነግን ስም በመጠቀም የሚሰጡት መግለጫ የግንባሩን ይፋዊ አቋም እንደማይወክል ገልጿል።

እ.አ.አ. በ2018 ከፌደራል መንግሥት ጋር የተደረገው የሰላም ስምምነት የጸና መሆኑን ያረጋገጠው ኦብነግ፣ በሶማሌ ክልል ያለውን ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስ ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ጋር ምንም ዓይነት ጥምረት የመፍጠር ፍላጎት እንደሌለው አስታውቋል።

በመጨረሻም፣ ህዝቡና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የሀሰት መረጃዎችን ሳይከተሉ፣ ከድርጅቱ ሕጋዊና ይፋዊ አመራሮች ጋር ብቻ ግንኙነት እንዲያደርጉ የኦብነግ ሊቀመንበር አብዲከሪም ሼክ ሙሴ ጥሪ አቅርበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍16❤10😡5🤡1🌚1
በአዲስ ምዕራብ ማከፋፈያ ጣቢያ ባጋጠመ ብልሽት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋረጠ

በአዲስ ምዕራብ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ የትራንስፎርመር ብልሽት ምክንያት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

በዚሁ ብልሽት ሳቢያ

• በእህል በረንዳ፣ አውቶብስ ተራ፣ አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት፣ ገነሜ ትምህርት ቤት፣ አማኑኤል ቤተክርስትያን ፊትለፊት፣ አዲሱ ሚካኤል እና አካባቢው

• በመሳለሚያ፣ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ ኳስ ሜዳ፣ ግሩም ሆስፒታል፣ ታይዋን ገበያ ማዕከል እና አካባቢው

• አማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ ድሬ ሕንጻ ፊት ለፊት፣ ኮልፌ 18 ጤና ጣቢያ እና አካባቢው

• ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምፕሬሄንሲቭ ትምህርት ቤት፣ ኮልፌ 18 ማዞሪያ፣ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል እና አካባቢው

• ኮልፌ መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ (በከፊል)፣ ሎሚ ሜዳ፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን እና አካባቢው

• ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ፣ መስጅድ፣ ቤተል ፓስታ ቤት እና አካባቢው

• ሆላንድ ኤምባሲ፣ የሺ ደበሌ፣ ጦር ኃይሎች ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን፣ ቻይና ኤምባሲ፣ አውጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን፣ አባ ጅፋር መስጅድ እና አካባቢው

• ወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ የቀድሞው ራሺያ ካምፕ፣ ተዘንአ ሆስፒታል፣ አውጉስታ፣ ወይብላ ማርያም፣ ጦር ኃይሎች ጎልፍ ክለብ እና አካባቢው  የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል።

የጥገና ባለሙያዎች ብልሽቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ አስተካክለው አገልግሎቱን ለመመለስ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13👍4
ጫት፣ አስካሪ አልኮል መጠጦች እና ጎጂ ልማዳዊ ጭፈራዎችን የሚያግድ አዋጅ ጸደቀ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን ብሔረሰብ ምክር ቤት ጫት እና አስካሪ አልኮል መጠጦች በማህበረሰቡ ላይ የሚያስከትሉትን ከፍተኛ ጉዳት በማስመልከት ያወጣውን አዋጅ መነሻ በማድረግ፣ የባምባሲ ወረዳ ምክር ቤት መመሪያው በሚፈቅደው መልኩ አዋጁን አጽድቆ ስራ ላይ እንዲውል ማድረጉ ተገለጸ።

​የባምባሲ ወረዳ ምክር ቤት በ2019 ዓ.ም 1ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ባጸደቀው በዚህ አዋጅ መሰረት፤ ከጫት እና ከአስካሪ አልኮል መጠጦች በተጨማሪ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት የሚያስከትሉ ጭፈራዎች እንዳይደረጉ በህግ ክልከላ ተደርጎባቸዋል።

​የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ይህንን የወጣውን ክልከላ መተላለፍ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ተገንዝቦ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍30❤14
❤6😢3🤔1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
" ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር " - ሮዛ

ባሳለፍነው ሳምንት፣ ከዓርብ መስከረም 8/2019 ዓ.ም ጀምሮ አንድ የሃይማኖት አባት የሚታዩበት ፀያፍ ነውረኛ ቪድዮ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተለቆ ብዙዎችን አስደንግጧል ፤ ጉድ አሰኝቷል።

ቪዲዮው እውነተኛ ነው ? እውነተኛ አይደለም፣ በአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ (AI) የተቀናበረ ሐሰት ነው ? የሚሉ ክርክሮችም ተነስተዋል።

በኋላ ላይ ግን " እኔ ተበዳይ ነኝ " ያለች ግለሰብ ወደ ሚዲያ ወጥታ ቪዲዮው እውነተኛ መሆኑን አፍረጥርጣ መስክራለች።

" ተበዳይ ነኝ " ያለችው ስሟ ሮዛ እንደሚባል፣ የአክሱም ነዋሪ እንደሆነችና በከተማው በሚገኝ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል በአስተናጋጅነት እንደምታገለግል ተናግራለች።

ሮዛ " ሱርያል " ለተባለ የዩቲዩብ ሚዲያ እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በድምፅ በሰጠችው ማብራሪያ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የ " ትግራይ መንበረ ሰላም ጳጳስና ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቡነ አረጋዊ " በሥራ ቦታዋ መጥተው ባገኙት የመስተንግዶ እርካታ መነሻ እንደተዋወቋት ገልጻለች።

ከዚያም የሮዛና የጳጳሱ መቀራረብ ተጠናክሮ በመቀጠሉ፣ በኋላ ላይ ራሷን እስከ መጥላት ወደ አደረሰ ጾታዊ ግንኙነት ማደጉን ተበዳይ ነኝ ባይዋ በጸጸት ተናግራለች።

ሮዛ እንደምትለው፣ ጳጳሱ በተደጋጋሚ ጊዜ " ጾታዊ ጥቃት እንዳደረሱባት " ይህንን መግቻ እንዲሆን ለጳጳሳት መኖሪያ ወደ ተፈቀደ ቤታቸው በመሄድ ጾታዊ ግንኙነት እየፈጸሙ ቪዲዮ በድብቅ መቅረጿን ተናግራለች።

የቀረጸችውን የቪዲዮ ማስረጃ ወደ ጳጳሱ ልካ ግንኙነታቸው እንዲቆም ብትማጸንም እንዳልተሳካ ተናገራለች።

በድብቅ የቀረጸችውን ቪዲዮ እንድታጠፋ ከጳጳሱ እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ እንደቀረበላትም ገልጻለች።

ሆኖም ብር ከመቀበል በላይ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህ መሰል ጸያፍ ተግባር ከሚፈጽሙ የሃይማኖት አባቶች እንድትላቀቅ ባሳየችው አቋም፣ እስከ የመግደል ሙከራ ዛቻ እንደተደረሰባት አብራርታለች።

በዚህ ሁኔታ የቀረጸችው ቪዲዮ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ በማህበራዊ ሚዲያ ሊለቀቅ ችሏል። ይግም ፍርሃትና ስጋት እንደፈጠረባትም አልደበቀችም።

ሮዛ፣ “ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ መጽሐፍ ሕግ በጽኑ በሚገዙ የሃይማኖት አባቶች መመራት አለባት” ስትል በአጽንኦት አሳስባለች።

በተጨማሪም በአክሱምና ከአክሱም ውጪ እሷን ጨምሮ የጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው 4 ሴቶችን እንደምታውቅና እንደምታጋልጥ አረጋግጣለች።

ከዚህ ቀደም ጳጳሱ ለጵጵስና በታጩበት ጊዜ " ወልደዋል " ተብሎ በቪዲዮ የተደገፈ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተሰራጭቶባቸው የነበረ ሲሆን የሰጡት መልስ አልነበረም።

በአሁኑ የቪድዮ ጉዳይም ፣ እንዲሁም ሮዛ ላወረበችው የጾታዊ ጥቃት ክስ እስካሁን በይፋ የሰጡት መልስ የለም።

" በደል ደርሶብኛል " ባይዋ ሮዛ በአሁኑ ሰዓት በቂ የሕግ አገልግሎት እየተሰጣት በአክሱም ከተማ እንደምትገኝ ገልጻለች።

መቀመጫቸው አክሱም የሆኑት አቡነ አረጋዊ በአሁኑ ጊዜ የት እንዳሉ አይታወቅም።
Tikvah

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤29🤣14😱5👍4😢2🤔1🕊1😈1
ሰበር❗ከባድ የድሮን ጥቃት ተፈፀመ‼️
ዛሬ መስከረም 12/2019 ዓ.ም በራያ አላማጣ ከተማ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተደጋጋሚ ከባድ የድሮን ጥቃት ተፈፀመ።
ጥቃቱ የጀመረው 4:10 አካባቢ ሲሆን በአላማጣ ከተማ ዋጃ መውጫ ሓውጃኖ ትምህርት ቤት ላይ፣#ፋጫ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ንጉስ_ቸኮለ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና አላማጣ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ላይ ሲሆን በሓውጃኖ ትምህርት ቤት ብቻ 17 የህወሓት ታጣቂዎች መሞታቸውን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ አረጋግጠዋል።
የቆሰሉ ታጣቂዎች በአምቡላንስ ወደ መሆኒ እየተወሰዱ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20😢11🤝6🥱4👍2🕊2
የጨጓራ ህመምን የሚያባብሱ
6 ዘመን አመጣሽ  ምግቦች!

ዛሬ በዘመናዊ አኗኗራችን ምክንያት በስፋት የምንመገባቸውና የጨጓራ ህመም እና አሲድ መዛባትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያባብሱ 6 ዋና ዋና ምግቦችና መጠጦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

የታሸጉ እና የተቀናበሩ ምግቦች (ቺፕስ እና ብስኩቶች): በውስጣቸው ከፍተኛ የኬሚካል መከላከያ እና ስብ ስላላቸው የጨጓራን ሽፋን በማስቆጣት የምግብ መፈጨት ሂደትን ያዘገያሉ።

የታሸጉ ለስላሳ እና የኃይል ሰጪ መጠጦች: በውስጣቸው ያለው ጋዝ እና አሲድ የጨጓራን በር እንዲላላ በማድረግ አሲድ ወደ ላይ እንዲመለስ (Acid Reflux) ያደርጋሉ።

የተጠበሱ ፈጣን ምግቦች (በርገር እና ፍሬንች ፍራይስ): ስብ የበዛባቸው በመሆኑ በጨጓራ ውስጥ ለመፈጨት ረጅም ጊዜ ስለሚወስዱ ጨጓራ ከመጠን በላይ አሲድ እንዲያመነጭ ያደርጋሉ።

ቅመም የበዛባቸው ዘመናዊ ምግቦች (እንደ ኮሪያ ኑድልስ): በቃሪያ ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር የጨጓራን የውስጥ ሽፋን በቀጥታ በመኮርኮር የማቃጠል ስሜት እና ህመም ያስከትላል።

 ሰው ሰራሽ ጣፋጮች እና ኬኮች: በጨጓራ ውስጥ ያሉ ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን በማዛባት ለጋዝ፣ ለሆድ መንፋት እና ለጨጓራ መቆጣት ይዳርጋሉ።

 በባዶ ሆድ የሚወሰዱ የካፌን መጠጦች (ቡና): የጨጓራ አሲድ ምርትን በከፍተኛ ደረጃ ስለሚጨምሩ የጨጓራ ማቃጠል እና ቁስለት የመከሰት እድልን ያፋጥናሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20👍7😢1
መረጃ‼️
"የብርሃኑ ጁላን የጀግንነት ጉዞ የሚተርክ 'ድል ቁርሱ' የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ"

መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን የሕይወት፣ የአመራር እና የጀግንነት ጉዞ የሚተርከው “ድል ቁርሱ” የተሰኘ መጽሐፍ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተመርቋል።

መጽሐፉ ከገጠር ተነስቶ እስከ ጦር ሜዳ ውጣ ውረድ የደረሰን ግለሰባዊ ታሪክ ብቻ ሳይሆን፣ ሀገር በፈተና ውስጥ በነበረችበት ወቅት የነበረውን የፅናት መንፈስ የሚያሳይ ተደርጎ ተስሏል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣138❤21🙉5🤔2🙈2👍1😢1🍾1🤪1
በሕይወት እያለ የራሱን የሐዘን ባነር ያዘጋጀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ‼

​በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ኦካ ቀበሌ በሕይወት እያለ የራሱን ፎቶ በመጠቀም "ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል" የሚል የሐሰት የሐዘን መግለጫ ባነር ያዘጋጀ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

​የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ዘለቀ ኮሽካ እንደገለጹት፡ድርጊቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥንና አለመረጋጋትን የፈጠረ አሳዛኝ የስነ-ምግባር ግድፈት ነው። ህብረተሰቡ የሐሰት ወሬዎችን ሳያጣራ እንዳያምንና በጥንቃቄ እንዲመለከት አሳስበዋል።

በማህበረሰቡ ሰላምና ደህንነት ላይ በሚቀልዱ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይቀጥላል።
​በግለሰቡ ላይ የሚደረገው የፖሊስ ምርመራ ተጠናቆ ህጋዊ እርምጃ እስኪወሰድ ድረስ ክትትሉ እንደሚቀጥል ጠቅሶ መረጃውን የሰሜን ቤንች ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን አጋርቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣59❤13🤯4👍2👀2🙊2🤔1
ከመኖሪያ ቤቷ ጀርባ ወስደው የ15 ዓመት ታዳጊን የደፈሩ ሁለት ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ ከመኖሪያ ቤቷ ጀርባ ወስደው የ15 ዓመት ታዳጊ ላይ የአስገድዶ መድር ወንጀል የፈፀመሙ  ሁለት ተከሳሾች  በእስራት መቀጣታቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
 
ተከሳሾቹ ማረከኝ ድንበሩ እና አማኑኤል መኩሪያ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ታዳጊዋን ከምትኖርበት ቤት ከምሽቱ 2 ሰዓት ገደማ ይዘዋት በመሄድ አንደኛ ተከሳሽ ማረከኝ ድንበሩ ታዳጊዋን ከመኖሪያ ቤቱ ጀርባ  እንሰት ስር በማስገባት ኃይል በመጠቀም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈጸሙን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
 
2ኛ ተከሳሽ አማኑኤል መኩሪያ ደግሞ የወንጀሉ ተባባሪ በመሆን ወንጀሉ እንዲፈጸም ማመቻቸቱ በአቃቤ ሕግ ማስረጃ ተረጋግጧል ተከሳሾቹ ጥፋተኛ የተባሉት በኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 620(2)(ሀ እና መ) እንዲሁም አንቀጽ 37(1 እና 4) ሥር በተደነገገው ድንጋጌ መሠረት መሆኑንም ችሎቱ አስታውቋል።

በዚህም የወረዳው ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ ማረከኝ ድንበሩን በ13 ዓመት ጽኑ እስራት 2ኛ ተከሳሽ አማኑኤል መኩሪያን ደግሞ በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤10😡9👍3😱1😢1