አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.9K subscribers
17.5K photos
434 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ዜና፦ የተከሳሾች ጠበቃ አቶ #ዮሐንስ_ቧያለው እና ጋዜጠኞች ‘ሕገ-ወጥ’ የይቅርታ ቅድመ-ሁኔታዎችን ባለመቀበላቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ ገለጹ
 
የተከሳሾች ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ #ለአዲስ_ስታንዳርድ እንደተናገሩት፣ ተከሳሾቹ ሕገ-ወጥ በሆነ የይቅርታ ሂደት አማካይነት የቀረቡላቸውን ቅድመ-ሁኔታዎች ውድቅ ማድረጋቸውን ገልጸው፣ ባለስልጣናቱ ይቅርታን እና ክስ ማንሳትን ሕጋዊ ልዩነታቸውን በመካድ አንድ ላይ አደባልቀውታል ሲሉ ተችተዋል።
 
ከ600 በላይ ተከሳሾች በጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም “በምህረት እና በይቅርታ” ከእስር ከተፈቱት ውስጥ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክርስቲያን ታደለ፣ የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባል ካሳ ተሻገር (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ዜጎች  ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከፍተኛ አመራር ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) ይገኙበታል።
 
እንደ ጠበቃው ገለጻ፣ ሰነዱ ተከሳሾቹ በአማራ ክልል ለደረሰው ውድመት፣ ለሰዎች ሞት፣ አካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት ኃላፊነት እንዲወስዱ፣ እንዲሁም በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖችን «አክራሪ» ብለው እንዲያወግዙ የሚጠይቅ ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤11🌚3👍2😢2🤪2
የክልል መንግሥታት ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ እስከ 2% ሊቆርጡ ነው።
የክልል መንግሥታት ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ ላይ ከ0.5 እስከ 2 በመቶ የሚደርስ የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ መዋጮ የሚቆርጡበትን አሠራር መዘርጋታቸው ተሰማ። ይህ ከሠራተኞች ደመወዝ የሚቆረጥ መዋጮ በረቂቅ ደረጃ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በመጨረሻ በጸደቀው የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር አዋጅ ላይ ቀሪ መደረጉ ይታወሳል። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ክልሎች ተመሳሳይ የመዋጮ መጠን ለመሰብሰብ የወሰኑ ሲሆን፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግን ከሁሉም ከፍ ያለ ማለትም ከ1 እስከ 2 በመቶ ለመቁረጥ ወስኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢19❤13👍6
የስዌዲ ጣቢያው ጥቃት‼️
ትናንት መስከረም 9, 2019 ዓ.ም በትግራይ ሰሜን ምዕራብ ዞን በሚገኙ በርካታ ከተሞች መብራት እንዲጠፋ ተደርጎ የኤርትራ ሰራዊት በስፋት እንዲገባ ተደርጓል።
ይህንን ተከትሎ ዛሬ ረፋድ በአዲ ነብሪ ኢድ እና አዲ ዳኤሮ መካከል ባለው #ስዌዲ ጣቢያ ላይ ተከታታይ የድሮን ጥቃቶች ተካሂደዋል።
ታጣቂዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
እህል የጫነ አንዳ ተሳቢ ተመቷል፣ ህወሓት የእርዳታ እህል ነው ያለ ቢሆንም እህሉ ለታጣቂዎቹ ከኤርትራ የተላከ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች እየገለፁ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍9❤1🕊1
የወላጅነት ድካም ከመከሰቱ በፊት ራስን የማዳኛ 5 ወሳኝ መንገዶች

​ወላጅነት በደስታ እና በፍቅር የተሞላ ታላቅ ኃላፊነት ቢሆንም፣ በሒደት ግን አእምሮአዊና አካላዊ ኃይልን የሚያሰጥም ከባድ ፈተና ሊሆን ይችላል።

የኃይል ምንጫችን ቀስ በቀስ ሲደፈቅ እና ሲደርቅ ወላጆች ለአእምሮአዊና አካላዊ ድካም ይጋለጣሉ። ይህ ደግሞ በድንገት ሳይሆን በቀስ በቀስ የሚከሰት በመሆኑ፣ የመጀመሪያዎቹን ማስጠንቀቂያዎች ቀድሞ መረዳትና አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ወላጅነትን በደስታ ለመምራት ይረዳል።

​እነሆ የወላጅነት ድካምን ለመከላከልና አእምሮአዊ ብርታትን ለመመለስ የሚረዱ 5 መፍትሔዎች፦

​የብስጭትና የውጥረት ስሜትን በፍጥነት ማንሳት፦
​አጣዳፊ መፍትሔ፦ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የጡንቻ ውጥረትን ማስወገድ። ለምሳሌ፡ እጅና እግርን በኃይል ማናወጥ ወይም ስፖርታዊ ዝላይዎችን (መስራት ውጥረትን ወዲያውኑ ይቀንሳል።

​ዘላቂ መፍትሔ፦ በጭንቀት ጊዜ ነገሮችን እንደተለመደው ዝም ብሎ ከመግፋት ይልቅ፣ የሚያስጨንቁ ነገሮችን ለይቶ ማወቅና ከቤተሰብ ጋር በግልጽ መነጋገር።

​የነርቭ ሥርዓትን ማረጋጋትና የእንቅልፍ ዕረፍት ማግኘት፦
​አጣዳፊ መፍትሔ፦ የሳንባን የአተነፋፈስ ሥርዓት የሚያስተካክሉ ልምምዶችን ፣ የጡንቻ ማዝናኛዎችን ልምምዶችን ማድረግ።

​ዘላቂ መፍትሔ፦ ውጤታማነት ላይ ብቻ ሳያተኩሩ ለራስ የሚያስደስቱና ዘና የሚያስኙ እንደ የእግር ጉዞ ወይም ፈጠራ ነክ ሥራዎች ላይ መሳተፍ።

​ከራስና ከልጆች ጋር ያለውን ስሜታዊ ግንኙነት ማደስ፦
​አጣዳፊ መፍትሔ፦ የስሜት ሕዋሳትን ማነቃቃት፤ ለምሳሌ ፊትን በቅዝቃዛ ውኃ መታጠብ፣ ገላን በጣፋጭ ጠረን ባለው ክሬም ማሸት ወይም አካልን ቀስ አድርጎ በመታሸት ወደ አሁኑ ጊዜ መመለስ።

​ዘላቂ መፍትሔ፦ ከልጆች ጋር ጥራት ያለው ጊዜ ማሳለፍ፤ አብሮ ጨዋታዎችን መጫወት፣ ሽርሽር መውጣት ወይም የልጅነት ትዝታዎችን አብሮ ማሳለፍ።

​የአእምሮ ጫናን  መቀነስ፦
​አጣዳፊ መፍትሔ፦ የሚሰሩ ሥራዎችንና የሚጨነቁባቸውን ነገሮች ወዲያውኑ በወረቀት ወይም በስልክ ላይ መጻፍ አእምሮ ዕረፍት እንዲያገኝ ይረዳል።

​ዘላቂ መፍትሔ፦ በወላጆች መካከል የሥራ ክፍፍል ማድረግ፣ ግልጽ ዕቅዶችን ማውጣትና በዕቅዱ ውስጥ የግል የእረፍት ጊዜያትን ማካተት።

​የበደለኛነት ስሜትንና አላስፈላጊ ጭንቀትን ማስወገድ፦
​አጣዳፊ መፍትሔ፦ "ቅርብ ጓደኞት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ምን ይመክሩት ነበር?" ብሎ ራስን መጠየቅና ለራስ ሩህሩህ መሆን።

​ዘላቂ መፍትሔ፦ ወላጅነት ማለት ልጆችን ከማንኛውም ችግር መሸፈን ሳይሆን፣ መምራትና ማሳደግ መሆኑን ተረድቶ የኅብረተሰቡን አላስፈላጊ ግፊት አለመቀበል።

ምንጭ: ብሊክ ጋዜጣ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15👍3😢1
የአሜሪካ አስቸኳይ መግለጫ❗️

👉የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ሪያድ፣ አቡ ዳቢ፣ ዶሃ፣ እየሩሳሌም እና ሌሎችም ከትናንት ጀምሮ ያወጡት የተቀናጀ የደህንነት ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል።

በየመኑ ሁቲዎች እና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭትና የባሊስቲክ ሚሳይል ጥቃቶች ማሻቀባቸው ግጭቱ በፍጥነት ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊስፋፋ እንደሚችል ተስጋቷል።

👉 የሁቲ አማፂያን በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ የሲቪል አየር ማረፊያዎችን ጨምሮ መሠረተ ልማቶችን ኢላማ ማድረጋቸው ተጠቅሷል።

በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች በመካከለኛው ምስራቅም ሆነ ከዚያ ውጭ የሚገኙ የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ተቋማትን፣ የንግድ ድርጅቶችን እና ዜጎችን ኢላማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ኤምባሲዎቹ አሳስበዋል።

👉በአካባቢው የሚገኙ የአየር ክልሎች  በድንገት ሊዘጋጉ ስለሚችሉ፣ የበረራ ስረዛዎች እና ከፍተኛ የመንገድ መስተጓጎሎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

👉 በዱባይ፣ ዶሃ፣ አቡ ዳቢ፣ ሪያድ እና ጅዳ አየር ማረፊያዎች በኩል የሚያልፉ መንገደኞች ከቤት ከመውጣታቸው በፊት የበረራ ሁኔታቸውን ከአየር መንገዶቻቸው ጋር በቀጥታ እንዲያረጋግጡ ታዟል።

👉 በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የሌሉ የአሜሪካ ዜጎች ወደ አካባቢውም ሆነ በአካባቢው አየር ክልል አቋርጠው የሚያደርጉትን ጉዞ "በድጋሚ እንዲያጤኑት" ምክር ተሰጥቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤18👍4🤔3💯1
በኢትዮጵያ “አካታች የሽግግር መንግስት” ለመመስረት ያለመ የሰባት አማጽያን ኃይሎች እና የፖለቲካ ድርጅቶች ትብብር መመስረቱ ይፋ ተደረገ። “የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና” የሚል ስያሜ የተሰጠውን ይህን ትብብር ከመሰረቱት ውስጥ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ይህ የተገለጸው ዛሬ እሁድ መስከረም 10፤ 2019 በትግራይ ክልል በሚገኙ ዜና ማሰራጫዎች በኩል በተላለፈ መግለጫ ነው። መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው አፋብንን በሊቀመንበርነት የሚመሩት አቶ ዘመነ ካሴ ናቸው።

አቶ ዘመነ “ትብብር ለህልውና” የሚል አጭር መጠሪያ የሚጠቀመው የጋራ ትብብር ሰብሳቢ መሆናቸውም በቪዲዮ በተሰራጨው መግለጫ ላይ ተመልክቷል። የእዚሁ ትብብር ሌሎች መስራች አባላት የኦጋዴን ህዝብ ነጻነት ግንባር፣ የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር፣ የቤንሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ እና የጉሙዝ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ እንደሆኑም በመግለጫው ተጠቁሟል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤41👍13🤣5🤔2🥱2🫡2🤯1👀1🤪1
ሰባት የታጠቁ እና የፖለቲካ ኃይሎች አዲስ ጥምረት መመሥረታቸውን አስታወቁ
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰባት የታጠቁ እና የፖለቲካ ኃይሎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን አዲስ ጥምረት መሥረታቸውን የሚገልጽ መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
ቡድኖቹ አዲሱን ጥምረት «የኢትዮጵያ ሕዝቦች ትብብር ለህልውና» ወይም በአጭሩ «ትብብር ለህልውና» በሚል መጠሪያ እንደሚጠሩት ገልጸዋል።
በጥምረቱ የተካተቱት አካላት፦
በተሰራጨው መግለጫ መሠረት በጥምረቱ ውስጥ፦
• የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
• የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (OLA)
• ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)
• የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ONLF)
• የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር
• የቤንሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ
• የጉሙዝ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ
እንደተካተቱ ተጠቅሷል።
መንግሥት የታጠቁ ኃይሎችን እንቅስቃሴ የሀገርን ሰላምና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት አደጋ ላይ የሚጥል አድርጎ እንደሚመለከተው ይታወቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤56👍12🤣8😢3🕊2😡2🥰1🤔1👀1🙈1
#እንድታውቁት: የቀድሞ የይዞታ ካርታ እያለ አዲስ ሕጋዊ የካዳስተር ምዝገባ ለምን ያስፈልጋል?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የቀድሞ የይዞታ ካርታ ያላቸው ባለይዞታዎች አዲሱን ሕጋዊ የካዳስተር ምዝገባ ማካሄድ ለምን እንደሚያስፈልጋቸው በሚል በገጹ ያቀረበውን መረጃ እንናጋራችሁ።

ኤጀንሲው እንዳስታወቀው አዲሱ ምዝገባ የቀድሞውን ሰነድ ለመሻር ወይም ተመሳሳይ መብትን ለሁለተኛ ጊዜ ለመስጠት ሳይሆን፣ ያለውን የይዞታ መረጃ በዘመናዊና በተደራጀ የካዳስተር ሥርዓት ማረጋገጥን ዓላማ ያደረገ ነው።

የመብት ሰጪ እና የመዝጋቢ ተቋማት ልዩነት

ነባሩ ካርታ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመሬት ተጠቃሚነት መብት ሲፈቅድ የሚሰጠው የፈቃድ ሰነድ ሲሆን፤ በአዋጅ ቁጥር 1381/2017 መሠረት የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሚሰጠው የካዳስተር ሰርተፊኬት ደግሞ የመሬቱ ወሰን በጂፒኤስ (GPS) እና በኦርቶ ፎቶ ቴክኖሎጂ ተለክቶ የመሬቱና የንብረቱ ባለቤትነት በሕግ መረጋገጡን የሚያሳይ የዋስትና ሰነድ ነው።

አዲሱ የካዳስተር ምዝገባ የሚያካትታቸው ዝርዝሮች

አዲሱ ሥርዓት የመሬት መብት፣ ክልከላ እና ኃላፊነትን በአንድ ላይ የሚያደራጅ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል፦

⚫ የቁራሽ መሬቱ ትክክለኛ ወሰን፣ ስፋት፣ ርዝመት፣ ቅርጽና የኮኦርዲኔት መረጃ
⚫ የወሰን መገናኛ ነጥቦች፣ የአጎራባች ይዞታዎች፣ የመንገድና የአድራሻ መረጃ
⚫ የቁራሽ መሬቱ ልዩ መለያ ኮድ (Unique Identification Code)
⚫ በመሬቱ ላይ ያለው ሕንፃ ወይም ሌላ ቋሚ ንብረት መረጃ

የቀድሞ ካርታ ብቻውን የሚያስከትላቸው ችግሮች

የቀድሞ ካርታ ብቻ መጠቀም የመሬት ስፋት በተለያዩ ሰነዶች ላይ በተለያየ መጠን የመመዝገብ፣ የአጎራባች ወሰን የመደራረብ፣ ትክክለኛ ኮኦርዲኔት የመጣት እና በሽያጭ፣ ውርስ፣ ሞርጌጅ ወይም ካሳ ወቅት የሕግ ክርክር የመፈጠር ችግሮችን ያስከትላል። በተጨማሪም በወረቀት ላይ ያለ መረጃ ለዲጂታል አሰራር አይመችም።

የቀድሞ ሰነድ ህልውናና የካዳስተር ጥቅም

የቀድሞ ሰነድ በምዝገባ ሂደት ወቅት እንደ ዋና ማስረጃነት የሚያገለግል እንጂ በግድ የለሽነት የሚሰረዝ አይደለም። አዲሱ አሰራር አዲስ መሬት ለመስጠት ወይም ባለይዞታውን ለማስጨነቅ ሳይሆን፣ የይዞታ ዋስትናን በማጠናከር የመሬት መረጃን ከአንድ ልዩ መለያ ኮድ ጋር ለማስተሳሰር የተዘጋጀ ነው።

የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ነባሩ ካርታ የመሬት መጠቀሚያ ፈቃድ ሲሆን፣ በአዋጅ ቁጥር 1381/2017 መሠረት የሚሰጠው የካዳስተር ምዝገባ ሰርተፊኬት ግን የሀብትና የቤት የመጨረሻ ሕጋዊ ማረጋገጫ በመሆኑ ባለይዞታዎች ይዞታቸውን በወቅቱ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19👍6😡2
ታግደዉ የነበሩት የስፖርት ውርርድ እና ዲጂታል ሎተሪዎች በአዲስ እና ጥብቅ ማዕቀፍ ሊጀምሩ ነዉ‼️

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ጥብቅ የቁጥጥር ማዕቀፍ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የስፖርት ውርርድ እና ዲጂታል ሎተሪ አገልግሎቶችን በአዲስ መልክ ለማስጀመር አጠቃላይ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በስፖርት ውርርድ እና በዲጂታል ሎተሪ ኢንዱስትሪ ላይ ባደረገው የኦዲት ግኝት፣ ኦፕሬተሮች ለመንግሥት መክፈል የሚገባቸውን 27.5 ቢሊዮን ብር አለመክፈላቸውን ማረጋገጡን ተከትሎ፣ ዘርፉን በቴክኖሎጂ በተደገፈ የቁጥጥር ሥርዓት ውስጥ በማስገባት በድጋሚ ለማስጀመር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

የኦዲት ረቂቅ መነሻ እንደሚለው፣ ፈቃድ ያላቸው የቤቲንግ ኦፕሬተሮች ከሐምሌ 2022 እስከ ታህሳስ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ 199 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ በሲስተማቸው ያንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ ለመንግሥት መክፈል ከሚገባቸው ኮሚሽን ውስጥ እጅግ አነስተኛውን ብቻ ነው ገቢ ያደረጉት። በዚህ ጊዜ ውስጥ ሊከፈል ከሚገባው 30 ቢሊዮን ብር ገደማ ኮሚሽን ውስጥ የተከፈለው 3.6 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው። ይህም ማለት ኦፕሬተሮቹ ከሚጠበቅባቸው ክፍያ ውስጥ 12 በመቶውን ብቻ ሲከፍሉ፣ ከየአስር ብሩ ዘጠኝ ብሩን ለመንግሥት ገቢ አላደረጉም።

በምርመራው የተረጋገጠው አጠቃላይ የ27.5 ቢሊዮን ብር እዳ፣ ያልተከፈሉ ኮሚሽኖችን፣ ቅጣቶችን፣ የፈቃድ እድሳት እና የምዝገባ ክፍያዎችን ያካተተ ነው። ከዚህ እዳ ውስጥ "ዳሽ ቤቲንግ" የተባለው ድርጅት ብቻ 8.64 ቢሊዮን ብር (ከአጠቃላይ እዳው አንድ ሦስተኛውን) ያልተከፈለ ክፍያ እንዳለበት የኦዲት ውጤቱ ያሳያል። ሌሎች 10 ኩባንያዎች ደግሞ በጋራ ወደ 19 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ እዳ አለባቸው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቤዛ ግርማ ግኝቱን አረጋግጠው፣ የኦዲት ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ጋር በመተባበር ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድ ገንዘቡን ለማስመለስ እንደሚሠራ ገልጸዋል።

የስፖርት ቤቲንግ ኢንዱስትሪው ከቁጥጥር ሥርዓቱ ምን ያህል ፈጥኖ እንዳደገ የሚያሳየው፣ እ.ኤ.አ. በ2022 ዓ.ም. በዓመት ውስጥ በዘርፉ ሲንቀሳቀስ የነበረው ገንዘብ 4.7 ቢሊዮን ብር ብቻ የነበረ ሲሆን፣ በመስከረም 2025 ግን ወርሃዊ የገንዘብ ዝውውሩ ወደ 20 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱ ነው። የዲጂታል ክፍያዎች እና የሞባይል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች በአካል ወደ ቤቲንግ ቤቶች ሳይሄዱ በስልካቸው ብቻ ገንዘብ እንዲያስገቡ፣ እንዲወራረዱ እና እንዲያወጡ አስችሏቸዋል።

ይሁን እንጂ የቁጥጥር ሥርዓቱ ከዚህ የቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር እኩል ባለመጓዙ፣ በ2025 መገባደጃ ላይ መንግሥት በዘርፉ ላይ ጥብቅ እርምጃ እንዲወስድ አስገድዶታል። የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ የተደበቀ ገቢን በተመለከተ ባደረገው ምርመራ በርካታ የቤቲንግ ፈቃዶችን የሰረዘ ሲሆን፣ የሕዝብና የግል አጋርነት የዲጂታል ሎተሪ ስምምነቶችንም አቋርጧል።

ፈቃድ ያላቸው ኦፕሬተሮች ቢዘጉም፣ የቤቲንግ ፍላጎቱ ባለመቆሙ ሕገ-ወጥ የውርርድ እንቅስቃሴዎች እና የውጭ ዌብሳይቶች በስፋት መቀጠላቸው ለመንግሥት ሌላ ፈተና ፈጥሯል። ስለዚህ የአሁኑ የፖሊሲ አቅጣጫ "ቤቲንግ ሙሉ በሙሉ ይዘጋ?" የሚለው ሳይሆን፣ የመንግሥት ግብር የማይጭበረበርበት እና የደንበኞች ደህንነት የሚጠበቅበት ግልጽ ሥርዓት እንዴት ይፈጠር የሚለው ላይ ያተኮረ ነው። አቶ ቤዛ እንዳረጋገጡት፣ አገልግሎቱን "በአዲስ መልክ" ዳግም ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት አሁን ላይ ኦፕሬተሮችን ለመቆጣጠር የሚያስችል የተማከለ ዲጂታል ሲስተም እያለማ ነው። ይህ ሲስተም ኦፕሬተሮች የሚያደርጉትን እውነተኛ የገንዘብ ዝውውር ከመንግሥት ኮሚሽን እና ክፍያዎች ጋር በቀጥታ በማስተያየት ቴክኖሎጂ-መር ቁጥጥርን ዕውን ያደርጋል። በቀጣይ ወደ ገበያው መመለስ ለሚፈልጉ ኩባንያዎች ይህ አዲስ ሥርዓት ጠንካራ የክትትል መስፈርት ይዞ የሚመጣ ሲሆን፣ ባንኮች እና የዲጂታል ክፍያ አቅራቢዎችም ሕጋዊ እና ሕገ-ወጥ ኦፕሬተሮችን ለይተው ግብይቶችን እንዲያስተናግዱ ጥብቅ ኃላፊነት ይጣልባቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍4🤔4💔3👀2
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
" የጦርነቱን ሸክም እንዲሸከሙ ኤርትራ አሰልፋቸዋለች  ! " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፣  የኤርትራ መንግሥት ከግብፅ ጋር በመሆን የምስራቅ አፍሪካን ሰላም ለማናጋት እና ቀጣናውን ለማተራመስ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህን ያሉት ከ " Pulse of Africa " ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

በኤርትራ ያለው ከባድ የኑሮ ውድነት እና መጥፎ የፖለቲካ ሁኔታ በርካታ ወጣቶች ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ማድረጉን ያነሱት አቶ ጌታቸው " የሀገሪቱ ሠራዊትም ሀገር ለመጠበቅ ሳይሆን ፕሬዚዳንቱን ለመጠበቅ ብቻ የቆመ ነው " ብለዋል።

በዚህም ምክንያት ኤርትራ ራሷ በቀጥታ በጦርነት ውስጥ ከመግባት ይልቅ፣ ሌሎች ታጣቂዎችን እንደ መሣሪያ በመጠቀም ግጭቶችን ከድንበሯ ራቅ ባሉ ቦታዎች ለማቀጣጠል እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው እንዳሉት፤ እንደ ፋኖ፣  ኦነግ ሸኔ እና አሁን ደግሞ ሕወሓት ያሉ አካላት የኤርትራን ዓላማ ለማሳካት እና የጦርነቱን ሸክም እንዲሸከሙ ተሰልፈዋል።

በተለይም ሕወሓት እና የኤርትራ መንግሥት አብረው መሠለፋቸው እጅግ አደገኛና የትግራይንና የአማራን ሕዝብ ለከፋ ሁኔታ የሚዳርግ መሆኑን አስረድተዋል።

" የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እስካሁን ለሚደርሱበት የተለያዩ ትነኮሶዎች ከፍተኛ ትዕግስት እያሳየ ይገኛል " ያሉት አቶ ጌታቸው  ሆኖም ሕወሓት በኤርትራ ወጥመድ ወድቆ በፌዴራል ኃይሎች ላይ ጥቃት ከሰነዘረ፣ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሰፊ ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አጽንኦት ሰጥተው አስጠንቅቀዋል።

ቀጣናውን ከሌላ አስከፊ ጦርነት ለመታደግ እና የሰላም አፍራሾችን እንቅስቃሴ ለመግታት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኤርትራ መንግሥት እና ተባባሪዎቹ ላይ አፋጣኝ እና ጠንካራ ጫና መፍጠር እንዳለበት አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19🤣7🌚5👍2🕊2🥰1🤪1
47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የዳግም ምዝገባ መስፈርት አላሟሉም ተባለ

ራስ ገዝ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ዕድሳት አሰጣጥ መመሪያ የተቀመጠውን ዝቅተኛ የዳግም ምዝገባ መስፈርት አለማሟላታቸውን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ገለጸ።

የባለሥልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ ሥራ አስፈጻሚ ጀንበሩ ዓለማየሁ፣ ተቋማቱ በሰነድ ያቀረቡትን መረጃ መሠረት በማድረግ በሰኔ 2018 ዓ.ም. ግምገማ መደረጉንና ሁሉም ዝቅተኛውን መስፈርት አለማሟላታቸው መረጋገጡን ተናግረዋል።

ተቋማቱ ተጨማሪ 40 ቀናት እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ሰነዶቻቸውን እንዲያስገቡ ጊዜ መሰጠቱም ተገልጿል።

በዳግም ምዝገባው ሂደት ልዩ አደረጃጀት የተሰጠው ፕብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ብቻ መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13👍7
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አብዛኛዎቹ አካባቢዎች በቀጣዩቹ ቀናት እንደሚጨምር በሚጠበቀው የዝናብ ሁኔታ ሳቢያ የኮሌራ ወረርሽኝ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግ የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

በክልሉ “ሁሉም አካባቢዎች” ይህንኑ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ “የመከላከል እና የዝግጁነት ስራ” እንዲጠናከርም ኢንስቲትዩቱ መልዕክት አስተላልፏል።ተቋሙ የኮሌራ ወረረሽኝ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልዕክቱን ያስተላለፈው፤ በክልሉ ስር ለሚገኙ 12 ዞኖች ጤና መምሪያዎች እንዲሁም ለሶዶ፣ ዲላ እና አርባ ምንጭ ከተሞች በጻፈው ደብዳቤ ነው።

ባለፈው አርብ መስከረም 8፤ 2019 የተጻፈው ይህ ደብዳቤ፤ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከዓመታት በፊት የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ፤ “ቀላል የማይባል” ህመም እና ሞት ማስከተሉን አስታውሷል።በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሁኑ ወቅት የኮሌራ ወረረሽኝ “በየትኛውም አካባቢ” ያልተከሰተ መሆኑንም የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በደብዳቤው ጠቅሷል።

ሆኖም ለበሽታው መከሰት “ምቹ ሁኔታዎች ሲፈጠር”፤ ወረረሽኙ “ዳግም ሊከሰት የሚችልበት” አጋጣሚዎች እንዳሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል።ተቋሙ ለዚህ በማስረጃነት ያቀረበው፤ በኢል-ኒኖ የአየር ንብረት ክስተት ምክንያት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የዝናብ ሁኔታ እንደሚጨምር የሚቴዎሮሎጂ የትንበያ መረጃዎች ማመልከታቸውን ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤7👍3🕊1
ትግራይ ቴሌቪዥን ታገደ‼️
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን 
የትግራይ ቴሌቪዥን  መታገዱን  አስታወቀ


በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል በፕሬቶሪያ የተፈፀመውን የሰላም ስምምነት ተከተሎ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ባደረገው ውይይትና በተደረሰበት ስምምነት መሠረት፣ ቀደም ሲል በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነስቶ ወደ ሥራ መመለሱ ይታወቃል።

ከዚህም በተጨማሪ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ለትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች የሰላም ግንባታና የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ሚዲያው ወደ ሕገ-መንግሥታዊና ሙያዊ መስመር እንዲመለስ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ቴሌቪዥን በተሰጠው ዕድል ተጠቅሞ እና የሙያ ሥነ-ምግባር አክብሮ አገልግሎት መስጠት ሲገባው፤ የሀገርንና የህዝብን ደህንነት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉ እና ፅንፈኝነት የሚያበረታቱ መልእክቶች በተከታታይ እየተላለፉበት እንደሚገኝ የሚዲያ ይዘት ክትትል ግምገማችን ውጤት ያረጋግጣል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በህግ የተጣለበትን ኃላፊነት መሠረት በማድረግ፣ ከዛሬ ጀምሮ በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ላልተወሰነ ጊዜ እገዳ መጣሉን ይገልጻል።

ማንኛውም ዲጂታል፣ የብሮድካስትም ሆነ የሕትመት ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም የቴሌቪዥን ጣቢያው በህገወጥ መንገድ የሚያሰራጫቸውን  ይዘቶች አሰራጭቶ ወይም አስተጋብቶ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ይህንን መመሪያ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም ሚዲያ ላይ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ህጋዊ እና አስተዳደራዊና እርምጃዎች የሚወስድ መሆኑን አጥብቆ አሳስቧል።

@Addis_Reporter
🤪31❤27👍9🤔2🤣2🎉1🥱1💔1
ሚድሮክ ዝቅተኛውን የሰራተኞች ደመወዝ ወደ 10,000 ብር አሳደገ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2019 በጀት ዓመት አነስተኛ የወርሃዊ ደመወዝ ወለልን ከ6,000 ወደ 10,000 ብር ማሳደጉን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ጀማል አህመድ አስታወቁ።

ኩባንያው ለደመወዝ ጭማሪ ተጨማሪ 3.24 ቢሊዮን ብር የመደበ ሲሆን፣ ይህም ጠቅላላ ዓመታዊ የደመወዝ በጀቱን ወደ 13 ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል።

በተጨማሪም ባለፈው የበጀት ዓመት 1.2 ቢሊዮን ብር የቦነስ ክፍያ የተፈጸመ ሲሆን፣ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ 700 ሰራተኞች ከ100,000 እስከ 500,000 ብር የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።

ሚድሮክ ከትርፉ 10 በመቶ ለማህበራዊ ድጋፍ የዋለ ሲሆን፣ በዓመቱ 390 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱንም ገልጿል።

ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት በአጠቃላይ 80,000 ሰራተኞች አሉት።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍28❤13🤪3👌1
ወደ አማራ ክልል የተንቀሳቀሱት የህወሓት ታጣቂዎች‼️
ዛሬ ቀን ( መስከረም 11/2019 ዓ/ም ) 5፡20 ላይ የህወሓት ሰራዊቶች አርሚ 22 ኮር 3 #ጥራሪ ወንዝን ተሻግረው➡በሪዋርያ➡️በወልማርያም➡️በደረንዝባ አድርገው ወደ አማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን #ሀሙሲት እየሄዱ በነበርበት ወቅት መከላከያ ሰራዊት ከባድ_መሳሪያ ሲተኩስ አርፍዷል።
በከባድ መሳሪያ ተኩሱ ምክንያት ተበታትነው የነበሩት የህወሓት ታጣቂዎች #እንደ_አዲስ ተሰበስበው 8፡40 ላይ በራያ ዛታ ወረዳ  #ጓል_መርቆርዎስ ጣቢያ #ጥራሪ_ወንዝ ወረድ ብሎ አሁንም  #ሀሙሲት ለመግባት ተዘጋጅተው እያለ  ድንገተኛ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።

Via: አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍23🤪7❤5😢5🕊2👀1🙈1
የቻይና ሳይንቲስቶች ሰዎችን እስከ 150 ዓመት
ሊያስቆይ የሚችል እንክብል አዘጋጅተናል አሉ

አንድ የቻይና የባዮቴክኖሎጂ ኩባንያ ሰዎች እስከ 150 ዓመት እንዲኖሩ የሚያስችል «ፒሲሲ1» (PCC1) የተባለ ውህድ የያዘ እንክብል  አዘጋጅቻለሁ ብሏል። ከወይን ፍሬ ዘር የሚገኘው ይህ ንጥረ ነገር እድሜ እየገፋ ሲሄድ በሰውነት ውስጥ ተከማችተው በሽታዎችን የሚያስከትሉ ያረጁ ሴሎችን እንደሚያጠፋ ይነገራል።

ይህ ውህድ በአይጦች ላይ በተደረገ ሙከራ ዕድሜን በትንሹ እንደሚያራዝም ተስፋ ሰጪ ውጤት አሳይቷል። ሆኖም ጥናቱ እስካሁን የተደረገው በእንስሳት ላይ ብቻ በመሆኑ፣ በሰዎች ላይም ተመሳሳይ ውጤት እንደሚያመጣ የተረጋገጠ ነገር የለም። የሰዎች አኗኗር እና የእርጅና ሂደት ከእንስሳት በጣም የተወሳሰበ በመሆኑ ውህዱ በሰው ላይ ይሰራል ማለት አያስችልም።

ኩባንያው ሰዎችን ለረጅም ጊዜ ማኖር ብቻ ሳይሆን ከእድሜ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን በሽታዎች ማዘግየት ዋናው አላማው መሆኑን ይገልጻል። ነገር ግን  እንክብሉ ሰዎችን እስከ 150 ዓመት ማቆየቱ አሁን ላይ ከእውነት ይልቅ ግምት ብቻ ነው። ይህንን ለማረጋገጥ በሰዎች ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት የሕክምና ሙከራዎችን ማካሄድ የግድ ይላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19🤣17👍3
የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) “የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሃይሎች ትብብር ለሕልውና” ከተባለውና ከቀድሞው ሕወሃት (TPLF) ጋር ግንኙነት ካለው የታጠቀ ቡድን ጋር ተቀላቅሏል ተብሎ የተሰራጨውን መረጃ በፅኑ አስተባበለ።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፣ የቀድሞው ሊቀመንበር አብዱልረህማን ሼክ ማህዲ በህገ-ወጥ መንገድ የኦብነግን ስም በመጠቀም የሚሰጡት መግለጫ የግንባሩን ይፋዊ አቋም እንደማይወክል ገልጿል።

እ.አ.አ. በ2018 ከፌደራል መንግሥት ጋር የተደረገው የሰላም ስምምነት የጸና መሆኑን ያረጋገጠው ኦብነግ፣ በሶማሌ ክልል ያለውን ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስ ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ጋር ምንም ዓይነት ጥምረት የመፍጠር ፍላጎት እንደሌለው አስታውቋል።

በመጨረሻም፣ ህዝቡና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የሀሰት መረጃዎችን ሳይከተሉ፣ ከድርጅቱ ሕጋዊና ይፋዊ አመራሮች ጋር ብቻ ግንኙነት እንዲያደርጉ የኦብነግ ሊቀመንበር አብዲከሪም ሼክ ሙሴ ጥሪ አቅርበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍16❤10😡5🤡1🌚1